(ቢልልኝ ሀብታሙ አባቡ) አንድ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የሆነ ሔሊኮፕተር ተጠልፎ በኤርትራ ምድር ማረፉ በዚህ ሳምንት ተሰምቷል፡፡ የጠለፋውን አጠቃላይ አገራዊና አለም አቀፋዊ እንድምታ ለማየት ድርጊቱ ከግለሰቡ ስሜት የሚመነጭ ተራ የዜጋ ክህደት ነው ወይስ በአገራቱ መካከል በተፈጠረ መሻከር የተነሳ የፖለቲካ ትግላቸው አንድ አካል የሚለውን ለይቶ ማስቀመጥ ያስፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት በቅድሚያ የድርጊቱ ምንጭ ምን ሊሆን ይችላል የሚለውን ጥያቄ መመለሱ ጠቃሚ ነው፡፡ የድርጊቱን መነሻ ለማወቅ ፓይለቱ ለድርጊቱ ያነሳሳው የራሱ የግለሰቡ ተራ የሆነ የግለሰብ ስሜት ነው ወይስ ከጀርባው የተለየ ተልዕኮ አለ የሚሉትን ሁለት መነሻዎች ለይቶ ማጥናት ያስፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት ከሁለቱ አንዱን መምረጥ የሚያስችሉ የአሳብ መነሻዎችን ማየት ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡ ለዚህ ዋናው መነሻ ግለሰቡ ከሌሎች አገሮች ኤርትራን ለመድረሻ የመረጠበት ምክንያት እና ግለሰቡ የኤርትራን ድንበር አቋርጦ ሲሄድ በሰላም መስተናገዱ ምንአልባት ግለሰቡ በጉዳዩ ዙሪያ ከኤርትራ መንግስት ጋር ረዘም ላለ ጊዜ በድብቅ ሲሰራ እንደቆየ ሊያመላክት ይችላል፡፡ የኤርትራ መንግስት እንደጠላት ከሚያያት አገር የጦር ሄሊኮፍተር ድንበሩን አቋርጦ ሲገባ የአፀፋ ምላሽ አለመስጠቱ አስመራው አስተዳደር ድርጊቱ እንደሚፈጸም ቀደም ብሎ ያውቅ እንደነበረ ሊያመላክት ይችላል፡፡ እነደዚህ ከሆነ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስት ጠላት ያለው በራሱ ጉያ እንጂ በሚሊየን ኪሎሜትር ርቀት ላይ እንዳልሆነ ያመላክታል፡፡ የተጠናከረውን የኢትዮጵያ መንግስት ደህንነት አልፎ ተልዕኮውን ማሳካቱ የኤርትራ መንግስት በጉዳዩ ላይ ለረጅም ጊዜ ሲሰራበት የቆየ ተልዕኮ እንዳልቀረ ያመላክታል፡፡ የኢትጵያ መንግስት ምላሽ ምን ሊሆን ይችላል? በዋናነት ውድ ዋጋ ያለው ሀብት በመወሰዱ ሳይሆን በሁለቱ አገራት […]

የሶማሊያ አክራሪ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን አሸባብ ትናንት መዲና ሞቃዲሾ የሚገኘዉ የአፍሪቃ ሕብረት ጦር ላይ ጥቃት መሰንዘሩ ተረጋግጧል። በዚሁ ጥቃት ከአፍሪቃ ሕብረት ወታደሮች ጋር በተከፈተ የተኩስ ልውውጥ ሶስት ወታደሮችን ጨምሮ ቢያንስ 9 ሰዎች መገደላቸው ተሰምቷል።

ሊቀመንበሩ እንደሚሉት የግንባሩ አባላት በቅርቡ ባደረጉት ጉባኤ የፓርቲያቸዉ ሕልዉና እንዲከስም ወስነዋል።የአፋር ነፃ አዉጪ ግንባር (ALF) አመራር አባላት ነን የሚሉ የአፋር ፖለቲከኞች ግን ዉሕደቱን እንደማይቀበሉት አስታዉቀዋል።

በኢንዶኔዥያ የዛሬ አስር ዓመት የደረሰዉን ከፍተኛ ማዕበል የደረሰዉን ጥፋት በማሰብ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በህንድ ዉቅያኖስ ዳርቻ በመገኘት በከፍተኛ የፀሎት ሥነ-ስርዓት አስቡ።

የአንድነት ፓርቲ የሰሜን ቀጠና አደራጅ አቶ አዕምሮ አወቀ በመንግስት የደህንነት ሀይሎች ታፍነው ዝርፊያና ድብደባ እንደተፈፀመባቸው የፓርቲው ድርጅት ጉዳይ ለፍኖተ ነፃነት አስታወቀ፡፡ አቶ አዕምሮ ዝርፊያና ድብደባው የተፈፀመባቸው በትላንትናው ዕለት በግምት ከምሽቱ 12 ሰዓት ተኩል የፓርቲያቸውን ሰነድ እንደያዙ ከአንድ ኢንተርኔት ካፌ ሲወጡ አምስት የመንግስት የደህንነት አባላት ታርጋ በሌለው ሚኒባስ ውስጥ አስገድደው በማስጋት ከባህርዳር ከተማ በግምት የ35 ደቂቃ […]

ልማታዊው ቀልድ
————————
–ኢትዮጵያ ውስጥ አንዲት ሴት … አንዱን
ወንድ “3500 ብር
ሰረቀኝ ” ብላ ትከሰዋልች :: ተከሳሹም
ፍርድ ቤት ቀርቦ የተባለውን ገንዘብ መስረቁን
ያምናል ::
የሰረቀበትን ምክንያትም ሲያስረዳ ደግሞ
“3500ቱ ብር ላይ ከራሴ 1500 ብር
ጨምሬበት … የአባይ
ግድብ ቦንድ ገዛሁበት ” ብሎ ያስረዳል ::
የህንን የሰሙት ‘”ልማታዊ ” ዳኛ …አንተ
“ልማታዊ ሌባ “
ስለሆንክ … በነጻ ተለቀሀል … ከሳሽህ
ደግሞ “የልማት አደናቃፊ ” ስለሆነች
እንድትታሰር ወስነናል ‘
ብለው “ልማታዊ ” ውሳኔአቸውን አሰሙ::

አስደንጋጭ መረጃከአስገደ ገ/ስላሴ
35 ሺ ኢትዮዽያውያን እስረኞች በኢርትራ ሳህል በረሃ ዘመኑ ያለፈው የባርያ አገዛዝ እየተፈፀመባቸው ይገኛሉ::
የሻዕብያ የሽፍታ መንግስት በ1983 ዓ/ም ከደርግ ጋር በነበረ ጦርነት የተማረኩ ወጣት ወታደሮች ስቪል የመንግስት ሰራኞች በዛን ጊዜ ኢርትራ ላይ ይኖሩ የነበሩ ወጣት ዜጎች በሙያ የተካኑና ለስራው ያስፈልጉኛል ብሎ በመለየት ከ 36 ሺ በላይ በሳህል በረሃዎች በዓፍዓበት በናቅፋ በሰሜን መሰራቅ ሳህል ወስዶ በሃይልና ከባድ ስራ ያሰራቸው ነበር::
በኢትዮ ኢርትትራ ጦርነት ዋዜማ በሁሉም የኢርትራ ከተሞች የነበሩ ስቪል ሕብረተሰብና በሙያቸው ጦርነቱ ከተጀመረ እስከ ሻዕብያ የተሸነፈበት የማረካቸው ወታደሮችና ምልሻዎች ከኢርትራ ዘልቆ ወደ ትግራይ እየገባ ከ1990 እስከ 2007 ዓ/ም ለ17 ዓመት ያህል በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የትግራይ የጎንደር ወጣቶች አፍሶ የወሰዳቸው::
በስራ አጥነት በድህነት በመልካም አስተዳደርና ነፃነት እጦት ወደ ሱዳን ስራ ፍለጋ ብሎም ወደ ሌላ ሃገር ለመሸጋገር የኦሮሞ የአማራ የትግራይ የጋንቤላ ወዘተ ሱዳን የገቡ የሻዕብያ ልዩ ሰላዮች ወደ ሱዳን ሰርገው በመግባት ከሚሰሩበት በረሃና ከተሞች በመጥለፍና በማፈን ወደ ወገኖቻቸው ሳህል አገቡዋቸው:: እነዚህ ግፍ ይፈፀምባቸው ያሉ ዜጎች ከ1983 ዓም እስከ ዛሬ በእሱር መልክ ተይዘው በሁሉም የሻዕቢያ አካባቢዎች በከባድ ስራ ተሰማርው ይሰሩ የነበሩ እስከ 60ሺ ይገመቱ እንደነበሩ የመረጃው ምንጮች ይናገራሉ:: አሁን ግን በሳሀል በረሃዎች በተጨባጭ የሚኖሩ 36ሺ ናቸው ይባላል ከዛም ሊበልጡ ይችላሉ የቀሩ ተገድለዋል፡፡
እነዚህ ዜጎች የሚሰሩትን ስራ በሳዋ በባርካ በሰሜን ምስራቅ ሳህል በዓፍዓበት በማይሕመት በአልጌን በናቅፋ በግዝግዝያ በከረን አካባቢና በሰሜን ባህር በፍልፍል ዓራቶ የሚባሉ ቦታዎችና በሌሎች ቦታዎች በተለያዩ ከባድ ስራዎች ያሰሩዋቸው ነበሩ በሚሰሩበት ጊዜ በከባድ ጥበቃ ነው:: ለሚደርሰው ግፍ የመቃወም ምልከት ያሳዩ ወገኖች በእሰረኞች ፊት ይረሸናሉ::
ሌላ አስገራሚ ነገር ደግሞ በኢትዮዽያ ሰላማዊ ትግል አይቻልም ኢህአደግ እሱ በመጣበት መንገድ በነፍጥ ነው የሚወገድ ብለው ከሻዕብያ ጋር ተጠግተው ከህወሓት ለሻዕብያ ከሞት ለማዳን ያደረገው ሎሌነት እነዚም ከህወሓት በባሰ መንገድ ሎሌ ሆኖው የኢሳያስ ቤተ መንገሰት የሚጠብቁ ኢሳያስ ተኩሱ ሲላቸው የሚተኩሱ ደፈጣ ተዋጊዎች በመቃወም ኢትዮዽያዊ ጥያቄ ያነሱ ሻዕብያ የሚጠረጥራቸው ኢርተራውያን ወደ ሱዳን በስደት የገቡ የቻድ የናይጀርያ ዜጎች ሳይቀሩ ከ35ሺ እሰረኞች ቀላቅለው የባርያ አገዛዝ ተቋዳሽ ናቸው:: የዚህ ሁሉ ሚስጢር ያወጡ ያሉ ከእሰረኞቹ አምለጠው ወደ ዓረብ ሃገር የገቡ ሰዎች ናቸው:: እስረኞቹ ከ 10 ዓመት በፊት መላው የኢርተራ የሻዕብያ ተቋማት የእረሻና የግድበ ስራዎች እሰከ ምሸግ መስራት የሚሰሩ ነበሩ:: ማምለጥ በመጀመራቸው ግን ወደ ሳህል አካባቢ እንዲሰበሰቡ ተደረጉ::
የሚሰሩት ስራ ሻዕብያ 30 ዓመት የተቀመጠበት የቀበሮ ጉድጓድ 180 ኪሎሚትር ርዘመት ያለው ምሸግ ማደስ ለቱሪዝም ተብሎ በአፍዓበት በናቅፋ ቤቶች መስራትና ማደስ በሰሜን ምሰራቅ ሳህል የሚገኙ ትላልቅና አነስተኛ ተፋሰሶች መገደብ የእረሻ ስራ መስራት በሳህል የሚገኘው የነ ኢሳያስ የመሬት ውሰጥ ቤተመንገስተ ማደስ:: ሻዕብያ ይጠቀምባቸው የነበረ መንገዶች ማደስ ስራ ይሰማራሉ::
በዜጎቻችን የሚፈፀም ግፍ ቀን ተሊት በጥበቃ ስር ናቸው:: በቂ መገብ ህከመና የላቸውም የማምለጥ አዝማሚያ ያሳዩ ዜጎች በሆነ መንገድ ይረሸናሉ:: ሆን ተብሎ የተመሳሳይ ፆታ ወሲብ እርሰ በራሳቸው እንዲፈፅሙ ይደረጋል:: በቂ ልበስ የላቸውም በከባድ ስራ በህመም በርሃብ ተመጣጣኝ ምገብ ባለማግኘታቸው የወደቁ እንደልገመኞች ተቆጥረው ይረሸናሉ::
በአጠቃላይ በጨለማ የሚኖሩ ተስፋ የቆረጡ መሆናቸው ይገለጣል:: ታድያ የኢህአደግ መንገሰተና የሱ መዋቅሮች የሃገር መከላከያ ሚኒስቴር የደህንነት ጀነራሎች የደህንነት ባለስልጣናትና ሰላየቹ ምን እያደጉ ናቸው:: ከ35ሺ በላይ ዜጎቹ በበረሃ በአንድ ሽፈታ ስርዓት ሲሰቃዩ 23 ዓመት ሙሉ ምን እያደረጉ ናቸው:: እንደእሰራኤል ያሉ መንገሰታት እኮ ዜጎቿ በሓማስ ታጋዮች ሲጠለፉ ከባድ ጦርነት ተካሄደ ነገር ግን ኢስራኤል ወታደር ጂልዓድ ሸሊም ነፃ ለማውጣት ኋላ ግን በኢስራኤልና ከሓማስ በተደረው ስምምነት ኢስራኤል 3ሺ የፈለስጢም እስረኞች እንድትፈታና በጂልዓድ ሸሊም በዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል አማካይነት የእሰረኞች ልውውጥ ተደርጎ ነው ነገሩ የተፈታው::
የኢህአደግ መሪዎች ግን በአስር ሺ የሚቆጠሩ ዜጎቹ የባርያ አገዛዝ እየተፈፀመባቸው ደሮ የታፈነችባቸው አይመስሉም:: በቀላሉ እንኳ በምሽግ ያለው የሻዕብያ ሰራዊት በመተራመስ በ10ሺ የሚቆጠር ወታደር ማርኮ ተደራድሮ ማስወገድ ነበረበት:: በዚሁ የሻዕብያ ሽፍታ መንግስት ግፍ የኢርትራ ህዝብም ደስተኛ አይደለም::
ሌላ ይህ የሻዕብያ የሽፍታ መንግስት የሚፈፅመው ያለ ግፍ በዓለም መንግስታት በሰብአዊ መብት ተሟጓቾች ኢህአደግ ተፅኖ ለማድረግ ይችል ነበር:: ነገር ግን ምኑም አይደለም የትግራይ ክልል መሪዎች በወልቃይት ወርቅ ሲለቅሙ ከ280 በላይ ወጣቶች ታፍሰው ሳህል ሲገቡ እያወቀ ስለእነሱ ሲጠየቅ ውሸት ነው ተቃዋሚ ፓርቲዎች ያስፋፉት ወሬ ነው አሉ::
ሌላ በሃገር ውስጥና በውጭ ያሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ስለእነዚህ ዜጎች እንደአጀንዳ ይዘው አያነሱትም:: በመጨረሻ መላው የሃገራችን ህዝብ ሙሁራኖች ተማሪዎች በውጭ የምትገኙ ዜጎች ይህ በሻዕብያ የዜጎቻችን ይፈፅመው ያለው ግፍና የህወሓትት ኢህአደግ መሪዎች ለዜጎቻቸው አለመቆርቆር ተቃውሞ በማስነሳት ተፅእኖ ሊታደርጉ ዘንድ ጥሪ አቀርባለሁ:: በተጨማሪም ለተባበሩ መንግስታት ለሰብአዊ መብት ተሟጓቾች በዲፕሎማሲ ፅኖ በማድረግ ስለዜጎች እንስራ ሚስጢሩም መላው ዓለም ይወቀው::

የባህር ዳሩ ገዳይ ካለምንም ጥያቄ በቀጥታ ለፖሊስ እጁን ሰቷል:: ባሳለፍነው ሳምንት በአዲስ አበባ ካሳንቺስ ከቀድሞ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ጀርባ ከሚገኘው ድብቅ የደህንነት እስር ቤት ውስጥ በመገኘት በከፍተኛ የሴኩሪቲ ጥበቃ የነጻነት ታጋይ የሆነውን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር Greg Dorey እንዳነጋገሩ ሲታወቅ ከአንዳርጋቸው ጋር ያደረጉትን ቆይታ በተመለከተ ዝርዝር ማብራሪያ ባይገኝም በደህና ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ሲገልጹ […]

በአሸናፊ ደምሴ
በአገራችን ከ25 እስከ 40 በመቶ የሚሆኑ እናቶች ከደም መፍሰስ ጋር በተያያዘ በየዓመቱ ህይወታቸው እንደሚያልፍና ለዚህም ችግር መፍትሄ ይሆን ዘንድ የብሔራዊ ደም ባንክ አገልግሎት ከደም ለጋሾች ጋር በመተባበር እየሠራ መሆኑ ተገለፀ። ይህ የተገለፀው የብሔራዊ ደም ባንክ አገልግሎት “የሚዲያ ተቋማት አስተዋፅኦ በበጐ ፈቃድ የደም ልገሳ መበራከት ዙሪያ” በሚል ለመገናኛ…

መንገድ አቋርጣለሁ፡፡ በእግሬ፡፡ ሁለት ጎልማሶች በመንገዱ ማቋረጫ ላይ ተገናኙ፡፡ ከሁለት አንዳቸው ቀድመው ወይም ተከትለው ማለፍ አለባቸው፡፡ ሁለቱም ቆሙ፡፡ ከዚያም አንዱ ሌላኛው ቀድሞ ያልፍ ዘንድ ጋበዘ፤ የተጋበዘውም ጋባዡ  እንዲያልፍ ለመነ፡፡ ግብዣው ጥቂት ደቂቃዎች ፈጀ፡፡ እኛም ከኋላ ያለነው ትኅትናቸውን አድንቀን በትዕግሥት ቆምን፡፡ በመጨረሻ አንደኛው እያመሰገነ አለፈ፡፡ ሌላኛውም ‹ምን አይደል›› እያለ አሳልፎ አለፈ፡፡ 
ደግሞ ሄድኩኝ፤ እነሆም በአንድ መስቀለኛ የአስፋልት መንገድ ላይ ደረስኩ፡፡ መኪኖቹ ከአራቱም አቅጣጫ ይመጣሉ፡፡ ሁሉም ወደ መስቀለኛው መጋጠሚያ ይገባሉ፡፡ አራቱም በአንድ ጊዜ ለማለፍ ይሞክራሉ፡፡ ነገር ግን አይችሉምና የመኪኖቹ አፍንጫዎቻቸው ተፋጥጠው ይቆማሉ፡፡ ለማለፍ እንጂ ለማሳለፍ የሚጥር አላይም፡፡ አራቱም በመስኮት ብቅ ብለው ‹ወደ ኋላ በልልኝ ልለፍ› ይላሉ፡፡ እነርሱ ሲከራከሩ ሌሎች ባለመኪኖችም ይመጣሉ፡፡ እንደ ዘንዶ ተጣጥፈው በአራቱ መኪኖች መካከል ለማለፍ ይሞክራሉ፡፡ እነዚያ ቀድመው የመጡትም ይናደዱና ወደ ፊት ገፍተው መንገዱን ያጠባሉ፡፡ በዚህ የተነሣም እነዚያም ከኋላ የመጡት በተራቸው ይቆማሉ፡፡ ሁሉም ቀድሞ ለማለፍ በሚያደርገው ፍትጊያ ሁሉም ይቆማሉ፡፡ እለፍ፣ እለፍ ተባብሎ መገባበዝ የለም፡፡ 
እየገረመኝ አልፋለሁ፡፡
አልፌም አንድ ያረጀ የዕድር ድንኳን የተጣለበት ጋ እደርሳለሁ፡፡ ድንኳኑ ለሁሉም አይበቃምና ከድንኳኑ ውጭ አግዳሚ ወንበር ላይ ሰዎች ተቀምጠዋል፡፡ ሌሎች ልቅሶ ደራሾ ሲመጡ ቀድመው ተቀምጠው የነበሩት ግር ብለው ይነሡና ወንበር ይለቃሉ፡፡ ‹ይቀመጡ አልቀመጥም› የግብዣ ግብግብ ይፈጠራል፡፡ በመካከል ገላጋይ ገብቶ እንግዳ ይቀመጣል፡፡ ‹ኖር› መባባል መልቶ ሰፍቶ ይከናወናል፡፡ ሰውን በአግዳሚዎቹ መካከል ለማሳለፍ ሁሉም እግሩን ያነሣል፣ ወይ ራሱ ይነሣል፡፡
እያደነቅኩ አለፍኩ፡፡
የማልፍበት መንገድ በግራ በቀኝ ቤት ሠሪዎች አሸዋና ጠጠር፣ ድንጋይና ብረት አውርደውበታል፡፡ እዚህም እዚያም ተጀምረው ያላለቁ፣ አልቀው ደግሞ ሰው የገባባቸው ቤቶች አሉ፡፡ አሸዋውና ድንጋዩ፣ ጠጠሩና ብረቱ መሐል መንገድ ላይ ይቆለላል፡፡ ሰው በምን ይተላለፋል? መኪና በምን ያልፋል? ብሎ ነገር የለም፡፡ ሁሉም በቤቱ ፊት ለፊት ይደፋል፡፡ ሲብሰው ደግሞ መሐል መንገድ ላይ ሲሚንቶ ያቦካል፣ ድንጋይ ይፈልጣል፡፡ እዚያ ድንኳን ውስጥ የነበረው ‹ኖር› መባባል፣ በአግዳሚዎች መካከል ሰው ለማሳለፍ መከራ መቀበል፣ እንግዳ ሲመጣ ከመቀመጫ ተነሥቶ ክብር መስጠት በቤት ሠሪዎቹ ዘንድ የለም፡፡
ይህንንም አለፍኩት፡፡
እነሆም በኑሮ ደከም ያሉ ሰዎች ወደሚኖሩበት መንደር ደረስኩ፤ የቆርቆሮ ጣራና የቆርቆሮ ግድግዳ ወደሚበዛባቸው፡፡ አቡኪዎቻቸው በእድሜ ገፍተው በሞቱ የጭቃ ግድግዳዎች ወደተሠሩ፤ ተቃቅፈው እንደሚሄዱ የሦስተኛ ክፍል ተማሪዎች ትከሻ ለትከሻ የተደጋገፉ ግድግዳዎች ወዳሏቸው ቤቶች መንደር፡፡ በዚያም ሳቋርጥ ‹‹ወ/ሮ እንትና ደኅና አደሩ፤ ምነው ሰሞኑን አላየሁዎትም› የሚል የጎረቤት ድምጽ ሰማሁ፡፡ ወ/ሮ እንትናም አብራሩ፡፡ እልፍ ስል ደግሞ ‹‹እ-ን-ት-ና፣ ቡ-ና-ው ፈ-ል-ቷ-ል› የሚል ዘለግ ያለ የግብዣ ጥሪ አዳመጥኩ፡፡ ደግሞ ልጆቹም ሰብሰብ ብለው በመንደሩ መካከል ከምትገኘው የእጣቢ መድፊያ መስክ ላይ አፈር ልሰው አፈር መስለው ይጫወታሉ፡፡ ውሾም ከልጆቹ ጋ ይዘላሉ፡፡
እነሆ ያንንም መንደር አለፍኩትና ከመንገዱ ማዶ ተሻገርኩ፡፡
ይኼ ደግሞ የባዕለ ጸጎች ሠፈር ነው፡፡ እያንዳንዱ ግን በአጥር ተከልሏል፡፡ ወደዚያ መንደር ለማለፍም እንደ መንግሥት መሥሪያ ቤት መታወቂያ ይጠየቃል፤ ወደ ውስጥ ስትዘልቁ እንደ ሙታን መንደር ጭር ያለ ነው፡፡ መስክ ላይ ተሰባስበው የሚጫወቱ ልጆች አታዩም፤ ሁሉም ወይ ጌም ላይ ናቸው ወይም ቲቪ እያዩ ነው፡፡ አለያም ግቢያቸው ውስጥ ናቸው፡፡ ወላጆቻቸውም ግቢ ግቢያቸውን ዘግተው አይጠያየቁም፡፡ እንዲያውም ጎረቤታቸው ማን እንደሆነ የማያውቁም አሉ፤ ከግቢያቸው ሲወጡ ‹‹ወ/ሮ እገሊት ደኅና አደሩ፤ ምነው ሰሞኑን አይታዩምሳ›› ብለው አይጠይቁም፡፡
በዚህም ተገረምኩ፤ አለፍኩም፡፡
እነሆም ሰዎች ታክሲ ለመሣፈር ወረፋ የያዙበት ቦታ ደረስኩ፡፡ ረዥም ሰልፍ፡፡ ልጆች፣ ወጣቶች፣ አረጋውያን፣ በከዘራ የሚሄዱ፣ ጎንበስ ብለው መሬት መሬት የሚያዩ፣ ጥላ የያዙ፣ በወረቀት ፀሐይን የሚከልሉ፣ ሁሉም ተሰልፈው የታክሲውን መምጣት ይጠባበቃሉ፡፡ ቆምኩና አየኋቸው፡፡ ታክሲዎቹ በመጡ ቁጥር የቻሉትን ሰው ይጭናሉ፡፡ በዚያ ፀሐይ ጨዋነታቸው ይነበባል፡፡ ራሳቸው ተራ አስከባሪዎች ከሚፈጥሩት ግርግር በቀር ግርግር ለመፍጠር የሚቻኮል ያንን ያህል ሰው የለም፡፡
ይህንንም አይቼ አለፍኩ፡፡
አለፍኩና ወደ አንድ ማደያ ዘንድ ደረስኩ፡፡ የነዳጅ ወረፋው የመንገዱን ጥግ የመኪና መሸጫ አስመስሎታል፡፡ ወደ ማደያው አካባቢ ሸውደው ለማለፍ የሚሞክሩ፤ አልፈው የሚሄዱ መስለው በሰው ሰልፍ የሚገቡ፣ ያንን ረዥም ሰልፍ እያዩ ሌላ ሰልፍ የሚፈጥሩ፣ መኪናቸውን አቁመው ጓደኛቸውን የሚያስገቡ ባለመኪኖች ይታያሉ፡፡ ከመኪኖቻቸው ውስጥ የብልግና ስድቦች ይወጣሉ፤ ይወራረፋሉ፤ ታክሲ እንደሚጠብቁት ሰዎች ፀሐይና አቧራ አያገኛቸውም፤ ከታክሲ ጠባቂዎቹ በላይ ግን ትዕግሥት የለሾች ናቸው፡፡ በመካከል ነዳጅ አልቋል ሊባል እንደሚችል ያውቃሉ፤ ነገር ግን ከኋላቸው የተሰለፉት ሰዎች ድካም ምንም ሳይመስላቸው ከነዳጅ ታንከራቸው በተጨማሪ በጀሪካቻኖቸው ይሞላሉ፡፡
እነሆ ይህንንም ታዝቤ አለፍኩ፡፡
አሁን ግን ዝም ብዬ አላለፍኩም፤ ያሳስበኝ ጀመር፡፡ እንዴው የኛ በጎ በጎ ባሕላችን በድህነት ላይ ነው እንዴ የተመሠረተው? አልኩ፡፡ በድሃው ማኅበረሰብ አካባቢ የምናያቸው የመከባበር፣ የመተባበር፣ የመጠያየቅ፣ የመረዳዳት፣ የመተሳሰብ ባሕሎች የተሻለ ገቢ ያለው ማኅበረሰባችን ላይ ሲታዩ ወይ ጠፍተዋል ወይም ቀንሰዋል፡፡ የዘመዶቻቸውን ልጆች እንደራሳቸው አድርገው የሚያሳድጉ ክቡራን ወላጆችን በብዛት የምናየው ድሃው ወገናችን ዘንድ ነው፡፡ የአንድ ሰው ጉዳይ አሳስቦት የት ነበርክ? ብሎ የሚየጠይቀው፣ ያለውን ተካፍሎ ለመብላት የሚተጋው፣ ጉርብትናው የሚያምረው፣ መከባበሩ ሞልቶ የሚፈሰው እዚህ ደሃው ወገናችን ላይ ነው፡፡
የተሻለ ኑሮና ዕውቀት ያለው ጋ ስትሄዱ ግለሰባዊነት፣ ብቸኛነትና ድንበርተኛነት ሠፍኖ ታዩታላችሁ፡፡ የማይለብሳቸው ብዙ ልብሶች አሉት፣ ግን አይሰጥም፤ የማይመገበው ትርፍ ምግብ አለው ግን፤ ግን አይመጸውተውም፡፡ ታላላቅ ግቢ አለ፤ ነገር ግን ተረት የሚያወሩ፣ ባሕል የሚያስተምሩ አክስቶች፣ አጎቶችና አያቶች አይኖሩበትም፡፡
እነዚያን የመንደር ሐኪሞች፣ እነዚያን እጆቻችንን አሽተው ያዳኑን ወጌሾች፣ እነዚያን ሐረግሬሳ በጥሰው፣ ስሚዛ ጨምቀው ያዳኑንን የመንደር እናቶችን አስቡና የአሁኑን የሕክምና ሥነ ምግባር አስቡት፡፡ ጠዋት ከዕንቅልፍ ብንቀሰቅሳቸው፣ በምሳ ሰዓት ብንሄድባቸው፣ በእኩለ ሌሊት ብንጠራቸው ለመንደሩ ሰዎች የነበራቸው ትጋት፤ ዛሬ ከዘመናዊ የሕክምና ተቋማት ለምን ተወሰደ? ይበልጥ ባወቅንና ይበልጥ ባገኘን ቁጥር ይበልጥ ጨዋነት ይጠፋብናል ማለት ነው? ከጉልት ሻጮች ይልቅ በሱፐር ማርኬቶች፣ ከመንደር ሱቆች ይልቅ በገበያ አዳራሾች ለምን ማጭበርበሩ በዛ?
ከተለያየ ጎሳና ነገድ ይበልጥ ተዋሕዶ፣ ተጋብቶና ተዛምዶ የምናገኘው የትኛውን ኅብረተሰብ ነው? ከውስኪ ቤትና ከጠጅ ቤት ኢትዮጵያን የሚያሳየን የትኛው ነው? በሀገር ቤት ከሚኖረውና በውጭ ከሚኖረው የትኛው ነው ጠባቡ? በአውቶቡስ ከሚሄድና በአውሮፕላን ከሚሄደው የትኛው ነው የሚገባበዘው? የትኛውስ ነው የሚጨዋወተው?   
ባደግንና በተለወጥን ቁጥር፣ ዕውቀትና ሀብትም ባፈራን ቁጥር፣ የኑሮ መደባችንም በተቀየረ ቁጥር እነዚያን የኛ ናቸው የምንላቸውን ወጎች፣ ልማዶች፣ ሥነ ምግባሮችና ባሕሎች እየተውናቸው እንሄዳለን ማለት ነው? ሥልጣኔና ብልጽግና የበጎ ባሕል ማጥፊያ ናቸው እንዴ? ኢትዮጵያዊ የምላቸው ባሕሎች፣ ወጎችና ልማዶች ካልተማረው ይልቅ በተማረው፣ ከሀብታሙ ይልቅ በደሃው ማኅረሰብ ዘንድ ይበልጥ የሚከበሩትና የሚጠበቁት ለምንድን ነው? ይበልጥ በበለጸግን ቁጥር፣ ይበልጥስ በተማርን ቁጥር ይበልጥ ኢትዮጵያዊነታችንን እንለቃለን ወይስ?

ሰንደቅ 10ኛ ዓመት ቁጥር 485 
በአሸናፊ ደምሴ

አስራ ሦስት ዓመት ባልሞላው ሕፃን ላይ የግብረ ሰዶም ጥቃት ፈፅሟል ሲል የፌዴራሉ ዐቃቤ ሕግ ክስ የመሠረተበት የ23 ዓመቱ ወጣት ሳሙኤል መርዕድ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ20 ዓመት እሥራት እንዲቀጣ የፌዴራሉ የመጀመሪያ…

ሰዎች ሃሳባቸውን በነጻነት የመግለጽ መብት አላቸው::የህዝቦችን ነጻነት መጋፋት ጋዜጠኛ አያሰኝም:: ጥፋተኛው የኢሳት ኢዲቶሪያል ሳይሆን የጥቂት ግለሰቦች የማናለብኝነት እና በስሜት የመነዳት ፖለቲካ ነው:: አዎን ምናልባት አንዳንዶች በልቅ የፖለቲካ ስድነት ያሸበረቁ ግለሰቦች ስማቸውን የቀያየሩ ሰውን በየድህረገጹ የሚዘልፉ የኢሳት ጋዜጠኞች ይህ ጽሁፍ ላይመቻቸው ይችላል:: ኢሳት ገና ከጅምሩ ሲመሰረት ህዝባዊ አላማ አንግቦ እና ህዝባዊ ስራዎችን ለመስራት እንደተቋቋመ የማይካድ ሃቅ […]

መታሰር ክፉ ነው፡፡ የታሰረ ሰው ተስፋው ሁሉ ውጪ በቀረው ታጋይ ላይ ነው፡፡ የሀብታሙ አያሌው እና የየሺዋስ አሰፋ ልብ የሚነካ ተማፅኖ አእምሮዬን ሁሉ ተቆጣጥሮታል፡፡ ‹‹እባካችሁ ተባበሩ›› ‹‹እስቲ ቀረብ ብላችሁ ተነጋገሩ›› በየንግግራቸው መሀል እየደጋገሙ የሚያስተላልፉት መልዕክት ነው፡፡ ‹‹እኛ እኮ ከዛሬ ነገ ለውጥ መጥቶ ኑ ውጡ እንባላለን ብለን ነው የምንጠብቀው……በተናጠል ድርጅቶች ያላቸውን አቅም የምናውቀው ነው….እባካችሁ ተባበሩ›› ሀብታሙ አያሌው፡፡ […]



(አፈንዲ ሙተቂ)
——
እነሆ ስለሒሳብና ስለ እውቁ የሒሳብ ጀግና በጥቂቱ ልናወጋችሁ ነው፡፡ ጀግናችን ፎቶግራፍ ከተፈጠረበት ዘመን አስቀድሞ የኖረ በመሆኑ ፎቶውን ልናሳያችሁ አንችልም መቼስ!…. በምስሉ ላይ የምትመለከቱት የሒሳቡ ጀግና የተወለደበት 1200ኛ ዓመት ሲከበር ታላቋ የሶቪየት ህብረት ያሳተመችውን  የመታሰቢያ ቴምበር ነው፡፡ ሰውየውን ከሶቪየቶች ጋራ ምን አገናኘው? ከወደታች እንመጣበታለን፡፡ አሁን ወጋችንን በመሰረታዊ ጉዳዮች እንጀምር፡፡
          *****
  እስቲ ከዜሮ ጀምሩና በቅደም ተከተል የሚመጡትን ቁጥሮች ጻፉ፡፡ 1፣ 2፣ 3፣ ….. አስር ስትደርሱ ሌላ ቁጥር ለማግኘት አትችሉም አይደል?… አዎን! አስር ለማለት ከፈለጋችሁ አንድና ዜሮን ጎን ለጎን በማድረግ ትጽፋላችሁ፡፡ ሌሎቹንም ቁጥሮች ለመጻፍ ከፈለጋችሁ በነዚህ ቁጥሮች ትጠቀማላችሁ፡፡
   በጥንት ዘመን ግን እንዲህ ዓይነት ነገር አልነበረም፡፡ የጥንት ግብጻዊያን ይገለገሉበት በነበረው የሄሮግሊፍ (hieroglyphic) አጻጻፍ ሁሉንም ነገር በተለየ ምስል ስለሚመስሉ የሚጠቀሙባቸው ቁጥሮች ብዛትም ማለቂያ አልነበረውም፡፡ ሮማዊያን በበኩላቸው ፊደልን እንደ ቁጥር ሲጠቀሙ ነው የኖሩት፡፡ ይህኛው የቁጥር ዘዴም ወጥ የሆነ ቀመር ስለሌለው ትልልቅ ቁጥሮችን ለመጻፍ ይቅርና በመቶና በአንድ ሺህ መካከል ያሉ ቁጥሮችን እንኳ ሳይደናግሩ ሊጽፉበት ይከብዳል፡፡ በሌሎች የዓለም ክፍሎች ያሉ የቁጥር ዘዴዎችም (numeration systems) ተመሳሳይ ጉድለቶች አሏቸው፡፡ በመሆኑም ከጭንቀት ለመገላገል የሚፈልግ ሰው በመግቢያዬ ወደጠቀስኩት የአቆጣጠር ዘዴ መመለሱ የግድ ነው፡፡
  ይህ ዘዴ “የሂንዱ-ዐረብ የቁጥር ዘዴ” (Indo-Arabic Numeration System) ይባላል:: ከስያሜው እንደምትረዱት “ህንድ”ና “ዐረቢያ” በጋራ በመሆን ለዓለም ህዝብ ያበረከቱት ታላቅ ገጸ-በረከት ነው፡፡ የቁጥሮቹ መሰረት የሆኑት ምልክቶች የተወጠኑት ከክርስቶት ልደት በፊት በሀገረ-ህንድ ነው፡፡ እነዚያ ምልክቶችም 1-እስከ 9 ያሉትን ቁጥሮች ብቻ የሚወክሉ ነበሩ፡፡ ከክርስቶስ ልደት በኋላ በመጀመሪያው ምእተ- ዓመት ምልክቶቹ ከህንድ ተሻግረው ወደ ፋርስ፣ ግብጽ፣ ሜሶጶጣሚያ፣ ሶሪያና ዐረቢያ ገቡ፡፡ በነዚህ ሀገራት የሂሳብ ሊቃውንትና በነጋዴዎች እጅ ሲሸከረከሩም ቆዩ፡፡ በ800 ዓ.ል. ገደማ ግን አንድ ሰው ከባግዳድ ተነሳና ምልክቶቹን በማሻሻል አሁን ያሉትን ቁጥሮች አስገኘ፡፡
 ታዲያ ይህ ሰው ቁጥሮችን በማስገኘቱ ብቻ አላበቃም፡፡ ከዚያ በፊት የማይታወቁ የሂሳብ ጽንሰ-ሐሳቦችንም ለዓለም አስተዋውቋል፡፡ ከነዚያ ጽንሰ-ሐሳቦች መካከል የመጀመሪያው “the concept of Zero” ይባላል፡፡ ሰውዬው ዘጠኙ ቁጥሮች በትክክል ሊሰሩ የሚችሉት ዜሮ ከታከለችባቸው ብቻ መሆኑ ገብቶታል፡፡ በዚህም መሰረት ዜሮን በራሱ በመፈልሰፍ በአስሩ ቁጥሮች ሁሉንም ዐይነት “ህልቅ” (number) ለመጻፍ እንደሚቻል አሳይቷል፡፡ በተጨማሪም በቁጥሮቹ በትክክል ለመጠቀም ከተፈለገ የሂሳቡ ዓምድ “አስር” (base ten) መሆን እንዳለበት አስገንዘቧል (ከዚያ በፊት ሂሳቡ ወጥ ዓምድ አልነበረውም፡፡ ግሪኮች አስራ ሁለትን ወይንም “ደርዘን”ን ነበር እንደ ዓምድ የሚጠቀሙት፡፡ ለባቢሎኒያ እና ለአሶሪያ ሰዎች ደግሞ የሂሳቡ ዓምድ “ስድሳ” ቁጥር ነበረ)፡፡
          *****
ለጥንት ሰዎች ሂሳብ ማለት ሁለት ነገር ነው፡፡ አንደኛው በየቀኑ ነገሮችንና የምንደምርበት፣ የምንቀንስበት፣ የምናባዛበትና የምንቀንስበት መሰረታዊው የሂሳብ ዘርፍ ነው፡፡ ይህም “አርቲሜቲክ” ይባላል፡፡ ሌላኛው ደግሞ ስፋት፣ ርዝመት፣ ወርድ፣ መጠነ ዙሪያ፣ ቁመት ወዘተ የመሳሰሉትን ለመስፈር የምንጠቀምበት “ጂኦሜትሪ” ነው፡፡
 ታዲያ ከላይ የጠቀስነው የባግዳዱ ሰውዬ ከሁለቱ የሂሳብ ዘርፎች ወጣ በማለት መመራመር ጀመረ፡፡ የምርምሩን ውጤትም “ሒሳቡል ጀብር ወል-ሙቃበላ” በሚል ርዕስ አሳተመ፡፡ መጽሐፉ በልዩ ልዩ ምሁራን እጅ ሲገባም ጥንት  ያልነበሩ አዳዲስ የሂሳብ ስልቶችን፣ ስሌቶችንና ዘዴዎችን አጭቆ የያዘ አዲስ የሂሳብ ዘርፍ እንደፈጠረ ታወቀለት፡፡ በመሆኑም አዲሱ የሂሳብ ዘርፍ በመጽሐፉ ስም “ሒሳቡል-ጀብር” በሚል ተሰየመ፡፡ መጽሐፉ ወደ ላቲን ሲተረጎም ደግሞ ስያሜው “አልጄብራ” ተብሎ ተቀየረ፡፡
          *****
ያ የሒሳብ ሊቅ “ሙሐመድ ኢብን ሙሳ” ይባላል፡፡ የተወለደውና አብዛኛውን ዘመኑን ያሳለፈው በአሁኗ የኢራቅ መዲና በባግዳድ ውስጥ ነው፡፡ ይሁንና ወላጆቹ “ኸዋሪዝም” ከምትባለው የመካከለኛው እስያ ክፍለ ሀገር (በኡዝቤኪስታን ውስጥ የምትገኝ) ወደ ባግዳድ የመጡ በመሆናቸው ራሱን ሲጠራ “አል-ኸዋሪዝሚ” በሚል ስም ይጠቀም ነበር፡፡ የዓለም ህዝብም እርሱን የሚያውቀው በዚሁ ስም ነው፡፡ የሒሳብ ሊቃውንት በበኩላቸው ስራዎቹ ዘወትር ይታወሱ ዘንድ “አልጎሪዝም” (algorithm) የተባለውን የስሌት ዘዴ በስሙ ሰይመውለታል፡፡
 አል-ኸዋሪዝሚ በመላው ዓለም የተከበረ ምሁር ነው፡፡ በዓለም ታሪክ ከፍተኛ ተጽእኖ ፈጣሪ ናቸው ከሚባሉት 100 ሳይንቲስቶች መካከልም ስሙ አለ፡፡ በዚህም የተነሳ እርሱ የተወለደባት ኢራቅ፣ ለተወሰነ ጊዜ የኖረባት ኢራን እና ወላጆቹ የተገኙባት ኡዝቤኪስታን “የኔ ነው” በሚል ይወዛገቡበታል፡፡ እንግዲህ የቀድሞዋ ሶቪየት ህብረት በምስሉ ላይ የምትመለከቱትን የመታሰቢያ ቴምብር ያሳተመችው “አል-ኸዋሪዝሚ የኔ ነው” በሚል መነሻ ነው (ኡዝቤኪስታን ከ1924 እስከ 1991 የሶቪየት ህብረት አካል እንደነበረች አስታውሱ)፡፡
  
ቢሆንም አል-ኸዋሪዝሚን የአንድ ሀገር ብሄራዊ ጀግና ብቻ አድርጎ ማየቱ ለዚህ ዘመን ሰው አይስማማም፡፡ ስራው መላውን ዓለም ያዳረሰ በመሆኑ የሁሉም ህዝቦች ብሄራዊ ሀብት ተደርጎ ቢታይ ነው የሚመረጠው፡፡
  —–
አፈንዲ ሙተቂ
ህዳር 8/2007
The writer, Afendi Muteki, is a researcher and author of the ethnography and history of the peoples of East Ethiopia.  You may like his facebook page and stay in touch with his articles and analysis: Just click the following link to go to his page.

ተጻፈ በ  

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለሥልጣን በተያዘው የበጀት ዓመት 15 አዳዲስ የቴሌቪዥን…

ኢትዮጵያውያን ዓለም በደረሰበት የሕክምና ደረጃ ተጠቃሚ እንደሆኑ የማድረግ አላማን አንግቦ የተነሳው ጌትዌል የጤና ማማከር አገልግሎት ተቋም ስራውን መጀመሩን አስታወቀ። የጌትዌል የጤና ማማከር አገልግሎቶች መስራችና ዋና ዳይሬክተር ዶክተር በጋሻው ባይለየኝ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ ተቋሙ በሀገራችን ለሚገኙ ህሙማን የተሻለ ህክምናን በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲያገኙ ለማስቻል የሚሠራ…

(ቃለየሱስ በቀለ) የኢትዮጵያ አየር ኃይል ንብረት የሆነ ተዋጊ ሔሊኮፕተር ባለፈው ዓርብ ተጠልፎ ኤርትራ ግዛት አሰብ ማረፉ ተረጋገጠ፡፡ የዘወትር የበረራ ልምምድ ላይ የነበረውን የኢትዮጵያ አየር ኃይል ሩሲያ ሠራሽ ኤምአይ 35 ተዋጊ ሔሊኮፕተር ይዞ ወደ ኤርትራ የኮበለለው ዋና አብራሪ ሻምበል ሳሙኤል ግደይ፣ ይህንን ዓይነት ተግባር ይፈጽማል ብለው እንደማያስቡ ባልደረቦቹ ገልጸዋል፡፡ ከሻምበል ሳሙኤል ጋር በኢትዮጵያ አየር ኃይል አብረው የሠለጠኑና የሠሩ የሥራ ባልደረቦቹ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ግለሰቡ መልካም ባህሪ ያለውና በፖለቲካ አቋሙ ገለልተኛ የሚባል ነው፡፡ ‹‹እጅግ በጣም ጥሩ ሰው ነው፡፡ የመንግሥት ተቃዋሚ አልነበረም፡፡ ራሱን ከፖለቲካ ጉዳዮች የሚያገል፣ ሥራውን ብቻ የሚሠራና ልጆቹን በኃላፊነት የሚያሳድግ ሰው ነበር፤›› ብለው በድርጊቱ ግራ መጋባታቸውን ገልጸዋል፡፡ አክለውም በትንሽ ነገር የሚከፋና የሚደሰት፣ በቅጽበት የሚለዋወጥ ባህሪ እንዳለው ተናግረዋል፡፡ በግል ሕይወቱም የሚበሳጭበት ጉዳይ እንደነበርና አልፎ አልፎም በዚሁ ጉዳይ ይደበት እንደነበር አልሸሸጉም፡፡ ሻምበል ሳሙኤል ለሥልጠና ወደ ኢትዮጵያ አየር ኃይል የገባው በ1994 ዓ.ም. ሲሆን፣ የቅጥር ውል የፈረመው በታህሳስ ወር 1995 ዓ.ም. ነበር፡፡ የኢትዮጵያ አየር ኃይልን ለ12 ዓመታት አገልግሏል፡፡ በ2003 ዓ.ም. የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ወደ ዳርፉር ሱዳን ያሰማራው የሰላም አስከባሪ ኃይል አባል በመሆን ለአንድ ዓመት ያህል እንዳገለገለና በዚያም ተልዕኮ ዳጐስ ያለ ዶላር ይዞ መመለሱን ባልደረቦቹ ተናግረዋል፡፡ ሻምበል ሳሙኤል ተወልዶ ያደገው በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ መሆኑን፣ ወላጆቹ የመቀሌ ነዋሪ መሆናቸውን ባለቤቱና ሁለት ልጆቹ ቢሾፍቱ እንደሚኖሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡  ባለፈው ዓርብ ማለዳ ከረዳት አብራሪው መቶ አለቃ ቢልልኝ ደሳለኝና የበረራ ቴክኒሺያን […]

የአማራ ክልል ባለስልጣናት የኮንስትራክሺንና ቤቶች ልማት ኤጀንሲ በባህርዳሩ ግዮን ሆቴል ላይ ያለውን የባለቤትነት መብት እስካሁን ማስከበር አልቻሉም፡፡

ታኀሳስ ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከፌደራል ፕራይቬታይዜሽንና የመንግስት የልማት ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ተረክቦ ቦታውን ለልማት ለማዋል ዝግጅት የጀመረው የክልሉ የኮንስትራክሺንና ቤቶች ልማት ኤጀንሲ ሆቴሉን ነጻ ለማድረግ ከህዳር 15 ቀን ጀምሮ አገልግሎቱን እንዲያቋርጥ እና በውስጡ ያሉትን የግለሰብ ንብረቶች ለማስወጣት ያደረገው እንቅስቃሴ ለአንድ ወር ያህል አለመሳካቱን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ኤጀንሲው በቁጥር ኮቤልኤ-ዋሥ/32/1108 በቀን 16/ 03/07ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ በግቢው ውስጥ የሚገኙትን የግለሰብ ንብረቶች ከ15/03/07 ዓ.ም ጀምሮ በህጋዊ መንገድ እንዲያወጡ በመጠየቅ፣ ንብረቱ ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ የማያወጡ ከሆነ በቤቱና በግቢው ውስጥ ለቆዩበት ጊዜ ሁሉ በቀን ሃያ ሽህ ብር እና ሌሎች ኪሳራዎችን የቤቱ ባለቤት የሆነው የክልሉ መንግስት ተወካይ የኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ኤጀንሲ የሚያስከፍል መሆኑን በመግለጽ ንብረቱ እንዲነሳ በመጠየቅ ሆቴሉን አሽጎ ሰራተኞችን መበተኑ ታውቋል፡፡

ለአስራ አምስት ቀናት ቢጠብቅም ምንም ውጤት ያላየው ኤጀንሲ በ01/04/07 ዓ.ም ባወጣው ድጋሚ ደብዳቤ « መንግስት በቦታው ላይ ያቀደውን የልማት ስራ እርስዎ ንብረትዎትን ባለማውጣትዎ ምክንያት ሊያቆም ስለማይገባ በግቢው ውስጥ ያለውን ንብረት ወደ አንድ ቦታ በማሰባሰብ የልማት ስራውን ለማስቀጠል ስላስፈለገ እቃው በሚሰባሰብበት ወቅት በእርስዎ በኩል በታዛቢነት የሚኖር ሰው ሰኞ ታህሳስ 8ቀን 2007 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ሆቴሉ መግቢያ በር እንዲገኝ እያሳሰብን የእርስዎ ተወካይ ወይም ታዛቢ ባይገኝ ሌሎች ታዛቢዎች በተገኙበት በግቢው ውስጥ ያለውን ዕቃ ወደ አንድ ክፍል የሚያሰባሰብ መሆኑን እየገልጽን መንግስት ይህንን እና ሌሎች ለስራው የሚያስፈልጉ ወጭዎችን ቀደም ሲል በተሰጠዎ ማስጠንቀቂያ መሰረት ከእርስዎ እንደሚጠበቅ አንዲያውቁት እናሳስባለን፡፡” ብሎአል።

በባህርዳር ከተማ ነዋሪ የሆኑት የአቶ መለስ ዜናዊ የቅርብ ዘመድ አቶ ወልዱ ወልደ አረጋይ መንግስት ማግኘት የነበረበትን ከ900 መቶ ሺህ ብር በላይ እንዳያገኝ ያደረገ ታክሰ በማጭበርበር ወንጀል ተከሰው ወልዱና ቤተሰቡ ኃላፊነት የተወሰነ የግል ማህበር በእስራትና በገንዘብ እንዲቀጣ የምዕራብ ጎጃም ዞን የባህርዳር ምድብ ችሎት ውሳኔ ማስተላለፉን የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የውሳኔ መዛግብት ዋቢ በማድረግ መዘገባችን ይታወሳል።

የምዕራብ ጎጃም ፍርድ ቤት ባህርዳር ምድብ ችሎት ወልዱና ቤተሰቡ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ አቶ ወልዱ ወልደ አረጋይ እና አቶ ብስራት ወልዱ ወልዳረጋይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰብስቦ ያለማሳወቅና ያለመክፈል እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ ባልሆነ ደረሰኝ ግብይት በማካሔድ ወንጀል በአመት ስድስት ነጥብ ሶስት ሚልዩን ብር መሰብሰባቸው መጠቀሱንና ከዚህም ለመንግስት መግባት የነበረበት ከስድስት መቶ ሺ ብር በላይ ለግል ጥቀማቸው አውለዋል በማለት ተከሳሽ ወልዱ ወልዳረጋይ በ7 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ አንደኛ ተከሳሽ ወልዱና ቤተሰቡ ሀላፊነቱ የግል ማህበርን በተመለከተ በህገ-ሰውነት የተሰጠው ድርጅት በመሆኑ በወንጀል ህግ አንቀፅ 90/3 መሰረት የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰብስቦ ያለማሳወቅ፣ ያለመክፈል ወንጀልና ግብር ለመንግስት ያለመክፈል ወንጀል ክሶች እያንዳንዳቸው የብር 10 ሽህ መነሻ ቅጣት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ባልሆነ የደረሰኝ ግብይት ማካሔድ ወንጀል ክስ ደግሞ ብር 5 ሺህ ባጠቃላይ 25 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጫ እንዲከፍሉ ውሳኔ መተላለፉን ዘግበናል፡የባህርዳር ነዋሪዎች በድርጅቱና በልጅቻው ላይ የተሰጠውን ውሳኔ ቀልድ ነው ማለታቸውም ይታወሳል ፡፡

ከ10 ቀን በፊት ከባህር ዳር ማረሚያ ቤት ከገዢው መንግስት ባለስልጣናት በተሰጠ ቀጭን ትዕዛዝ የእስር ጊዜያቸውን ሳያጠናቅቁ ሳይሆን ሳይጀምሩ የተፈቱት አቶ ወልዱ ወልደ አረጋይ ፣ ኤጀንሲው በሰጠው ማስጠንቀቂያ መሰረት ንብረታቸውን ያላነሱ ሲሆን በኤጀንሲው ውሳኔ መሰረት ንብረታቸውን ላላነሱበትና ልማቱን ላደናቀፉበት 30 ቀናት ከ600 ሽህ ብር በላይ እንደሚጠበቅባቸው ምንጮች ገልጸዋል፡፡፡የባህርዳሩ ግዮን ሆቴልን ለረዢም አመታት በአምስት ሽህ ብር የክራይ ዋጋ ሲጠቀሙበት የነበሩት አቶ ወልዱ ወልደ አረጋይ ኤጀንሲው እንዲከፍሉ የወሰነባቸውን ገንዘብ መክፈል ሳይሆን በሌሉበት እና በህግ ጥላ ስር እያሉ በማናለብኝነት ሆቴሉ በመዘጋቱና ሰራተኞችንም በመበተኑ ላደረሰባቸው ኪሳራ የክልሉን የኮንስትራክሺንና ቤቶች ልማት ኤጀንሲን በህግ ለመጠየቅ ከጠበቆቻቸው ጋር እየተመካከሩ መሆኑን እማኞች ለዘጋቢያችን ገልጸዋል፡፡

አቶ ወልዱ ግዮን ሆቴልን የሚያክል ድርጅት የአቶ መለስ ዜናዊ ዘመድ በመሆናቸውና በትጥቅ ትግሉ ወቅት መረጃ በማቀበል ላገለገሉበት እንደውለታ ተቆርጦላቸው እጅግ እርካሽ በሆነ መንገድ በሆቴሉ ከ20 አመታት በላይ ሲጠቀሙበት መቆየታቸው በክልሉ ህዝብ ከፍተኛ ቅሬታ ያስነሳ ጉዳይ ሆኖ ቆይቷል። አሁንም ባለስልጣናት ደፍረው የፍርድ ቤት ትእዛዝ ለማስፈጸም እንዳልቻሉ ታውቋል።

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ምርጫ ቦርድ ነፃና ገለልተኛ እንዳልሆነ የሚገነዘብ ቢሆንም ባለፈው ታህሳስ 12/04/2007 ዓ.ም የተካሄደው የህዝብ ታዛቢዎች ምርጫ በሀገራችን የምርጫ ቦርድ አለ ወይ?! እንዲል አድርጎታል። የታህሳሱ 12/04/2007 ዓ.ም የህዝብ ታዛቢዎች ምርጫ ነፃና ገልልተኛ አልነበረም ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የምርጫ ህጉን ተከተሎ ያልተካሄደ ሌላው ይቅርና የራሱ የምርጫ ቦርድ መመሪያን እንኳን ያልተከተለ ከመሆኑ አንፃር ተካሄዷል ብለን […]

ታኀሳስ ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ህዳር 11 ቀን 2007 ዓም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በደቡብ ሱዳን በአቤይ ግዛት ተሰማርቶ የነበረው የሰላም አስካባሪ ቡድን አዛዥ ሌ/ጄኔራል ዮሃንስ ገብረመስቀል ተስፋማርያም በእኤአ ጁን 19፣ 2014 ተልእኮዋቸውን ጨርሰው በሜ/ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ገላልቻ መተካታቸውን ቢገልጽም፣ ኢሳት በዜና እወጃው አዛዡ ጊዜያቸውን ሳይጨርሱ መሰናበታቸውን ጠቅሶ ዘግቧል። የዲፕሎማቲክ ምንጮች እንደገለጹት ሌ/ጄኔራል …

ታኀሳስ ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቦርዱ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በየምርጫ ክልሉ ጽሕፈት ቤቶች ከታህሳስ 16 እስከ ጥር 27 ቀን 2007 ዓ.ም ምዝገባ እንደሚካሄድ የሚታወቅ ቢሆንም አንድነትና መኢአድ ፓርቲዎች ከምርጫ ቦርድ ጋር ከገቡት አሰጥ አገባ ጋር ተያዞ በምርጫው የመቀጠላቸው ነገር አጠራጣሪ መሆኑ ታውቆአል፡፡ አንድነት እና መኢአድ በመጪው ምርጫ ለመወዳደር ወስነው የምርጫ ምልክት …

ታኀሳስ ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከፌደራል ፕራይቬታይዜሽንና የመንግስት የልማት ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ተረክቦ ቦታውን ለልማት ለማዋል ዝግጅት የጀመረው የክልሉ የኮንስትራክሺንና ቤቶች ልማት ኤጀንሲ ሆቴሉን ነጻ ለማድረግ ከህዳር 15 ቀን ጀምሮ አገልግሎቱን እንዲያቋርጥ እና በውስጡ ያሉትን የግለሰብ ንብረቶች  ለማስወጣት ያደረገው እንቅስቃሴ ለአንድ ወር ያህል አለመሳካቱን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ኤጀንሲው በቁጥር ኮቤልኤ-ዋሥ/32/1108 በቀን 16/ 03/07ዓ.ም በተጻፈ …

የፕሮግራም መግለጫ

ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡

የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡

ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡

የገና ወይም የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የጎሮጎሮሳዉያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተለዉ የክርስትና እምነት ተከታይ ዘንድ ዛሬ ተከብረ። በዓሉን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ሐገራት የሐይማኖት መሪዎችና ፖለቲከኞች ለየተከታዮቻቸዉ መንፈሳዊና ዓለማዊ መልዕክት አስተላልፈዋል።

መፀዉ ወይም መኽር ወር፤ ከመስከረም ሃያ ስድስት እስከ ታህሳስ ሃያ አምስት ይዘልቃል፤ ከታህሳስ ሃያ ስድስት ደግሞ በጋ ይጀምርና እስከ መጋቢት ሃያ አምስት ይዘልቃል። በዚህም ኢትዮጵያዉያን የገና በዓልን የሚያከብሩት ታህሳስ መጨረሻ በበጋ ወርራት ዉስጥ ነዉ።

የትግሬ ወያኔ ዐማራን ከመጨፍጨፍ እና ከመጥላት አልፎ ንቆታል፤  ይህ ደግሞ ነገ ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍላል! አንድ ሰው ወይም ቡድን ሌላን ሰው ወይም ቡድን በጅምላ መጥላት ከጀመረ፣ የጠላውን ሰው ወይም ቡድን በቀጥተኛ እና በተዘዋዋሪ መንገድ ለማጥፋት ይጥራል። አልፎ ተርፎ ይህ ሰው ወይም ቡድን የጠላውን ሰው ወይም ቡድን መናቅ ሲጀምር እርሱን ለማጥፋት ሰበብ አይፈልግም። ንቀት ያሳደረበትን ሰው ወይም […]

ሰዎች ሃሳባቸውን በነጻነት የመግለጽ መብት አላቸው::የህዝቦችን ነጻነት መጋፋት ጋዜጠኛ አያሰኝም::
ጥፋተኛው የኢሳት ኢዲቶሪያል ሳይሆን የጥቂት ግለሰቦች የማናለብኝነት እና በስሜት የመነዳት ፖለቲካ ነው:: አዎን ምናልባት አንዳንዶች በልቅ የፖለቲካ ስድነት ያሸበረቁ ግለሰቦች ስማቸውን የቀያየሩ ሰውን በየድህረገጹ የሚዘልፉ የኢሳት ጋዜጠኞች ይህ ጽሁፍ ላይመቻቸው ይችላል::

ኢሳት ገና ከጅምሩ ሲመሰረት ህዝባዊ አላማ አንግቦ እና ህዝባዊ ስራዎችን ለመስራት እንደተቋቋመ የማይካድ ሃቅ ነው::ኢሳት የሰራቸው በጎ ተግባራት እንደተጠበቁ ሆነው እጅግ ሊሻሻሉ እና ሊታረሙ የሚገባቸው ጥፋቶችም በገሃድ አይተናል እያየን ነው::አብዛኛው ጥፋቶች የሚከሰቱት ዲሲ ከሚገኘው እና የግንቦት ሰባት አመራሮች በስሜት ፖለቲካቸው ከሚነዱት ስቱዲዮ መሆኑን ስንመለከት ደሞ ራሳችንን እንድንጠይቅ አድርጎናል::

ለኢሳት ስኬት አስፈላጊውን አስታውጾ እና ድጋፍ እስካደረኩ ድረስ የኢሳት ጉዳይ ያገባኛል ይመለከተኛል:: አንዳንድ ኢሳት የነሱ ብቻ የሚመስላቸው አዋቃጭ ግለሰቦች በደመነብስ የሚናገሩትን አልባሌ ቦለቲካቸውን ወደ ጎን በመተው ኢሳት ሊጠናከር የሚችለው ያለበትን ሲያርም እና በውስጡ የተወሸቁ ስሜታዊ እና ልቅ ጋዜተኞችን ሃይ ማለት ሲችል ብቻ ነው::አንድ ሳው አስተያየት በሰጠ ሰአት ሁሉ እየተነሱ የኒዛለፉ እና የሚሳደቡ ባለጌ ጋዜጠኞች እና አዋቃጭ ተባባሪዎቻቸውን ሊያርማቸው ይገባል::ጥላቻን ማራመድ በቀረበት በዚህ ስልጡን ዘመን ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያውያን ላይ ጥላቻ እንዲያራምዱ የሃገር ጉዳይ ተረስቶ ግለሰቦች እንዲዘረጠጡ በተራ አሉባልታ እና የስድብ ናዳ ጊዜ እንዲጠፋ የሚያደርጉ ሰዎችን ታቅፎ መጓዝ ከተጠያቂነት አያድንም::

የኢሳት ጋዜጠኞች በሃገር ውስጥ እና በውጪ ሃገር የሚገኙ የፖለቲካ ድርጅቶችን ወደ አንድነት እና የጋራ አጀንዳ እንዲመጡ መስራት ሲገባቸው እየከፋፈሉ የህዝብ የለውጥ ጥያቄ እና የነጻነት ጥማት እንዲዘገይ አድርገዋል::በሃገር ቤት የሚገኙ ፓርቲዎችን አንዱን ከፍ አንዱን ዝቅ በማደረግ በየፕሮግራሞቻቸው እኩልነትን ባላስተናገደ መልኩ በመዝለፍ እጅግ አሳፋሪ የሆነ የጋዜጠኝነት ስራ ስውርተዋል::በስሜት የሚነዱ ጥቂቶች የህዝብ ቤት ይሆናል የተባለውን ኢሳትን የራሳቸው የስሜት ሃሳብ መጋለቢያ አድርገውታል::በውጪ ሃገር የሚገኙ የፖለቲካ ድርጅቶችን በማግለል የአንድ የፖለቲካ ድርጅት ስም ገኖ እንዲወጣ ተግተው ሲሰሩ በተግባር እያየን ነው::ስለዚህ ኢሳት የኔ ነው እስካልን ድረስ የኢሳት ጉዳይ ይመለከተናል እንዲታረምም ሂስ የመስጠት መብታችን የተጠብቀ ነው::ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ብዙ ማለት ይቻል ነበር ግን የኢሳት ቦርድ ሁኔታውን አይቶ ሊያስተካክል ይገባል::
Image

መታሰር ክፉ ነው፡፡ የታሰረ ሰው ተስፋው ሁሉ ውጪ በቀረው ታጋይ ላይ ነው፡፡ የሀብታሙ አያሌው እና የየሺዋስ አሰፋ ልብ የሚነካ ተማፅኖ አእምሮዬን ሁሉ ተቆጣጥሮታል፡፡ ‹‹እባካችሁ ተባበሩ›› ‹‹እስቲ ቀረብ ብላችሁ ተነጋገሩ›› በየንግግራቸው መሀል እየደጋገሙ የሚያስተላልፉት መልዕክት ነው፡፡ ‹‹እኛ እኮ ከዛሬ ነገ ለውጥ መጥቶ ኑ ውጡ እንባላለን ብለን ነው የምንጠብቀው……በተናጠል ድርጅቶች ያላቸውን አቅም የምናውቀው ነው….እባካችሁ ተባበሩ›› ሀብታሙ አያሌው፡፡
አንድነት እና ሰማያዊ በትብብሩ ውስጥ አብረው መስራት ለምን አይችሉም???
አብረው መስራት የማይችሉበት ምንም ምክንያት ፈልጌ ላገኝ አልቻልኩም፡፡ ከሁለቱም በኩል በቀና እና ለውጥ ፈላጊ ልቦና ተቀራርቦ መነጋገር ከተቻለ የሚያግዳቸው ምንም ነገር አይኖርም፡፡ ሀብታሙ አያሌው እና የሺዋስ አሰፋ ቂሊንጦ ሲገቡ ተግባብተዋል፡፡ እኛም ነገ ቂሊንጦ ከገባን መግባባታችን አይቀርም፡፡ ከዛም እንደ የሺዋስ እና ሀብታሙ ውጪ ያለውን ሰው ተባበሩ እያልን እንመክራለን፡፡ በተስፋ ምግብም መንፈሳችንን በሂወት ለማቆየት እንጥራለን…..ከንቱ ልፋት፡፡
ወህኒ ሳንወርድ አሁን ላይ መግባባት ስለምን ይሳነናል???
አሁን ባለው ነባራዊ እውነታ አንድነት እና ሰማያዊ በትግል ስልታቸው ላይ መጠነኛ ልዩነት ያላቸው ይመስላል፡፡ ነገር ግን እንዲህ አይነት መጠነኛ ልዩነት አይደልም በሁለት ፓርቲ መሀል ይቅርና በአንድ ፓርቲ ውስጥም ባሉ ግለሰቦች መሀል የሚከሰት ነው፡፡ አንድነት ያለምንም ቅድመ ሁናቴ ምርጫ ውስጥ እገባለሁ ብሏል፤ ሰማያዊ ደግሞ ቅድመሁናቴ አስቀጧል፡፡ ነገር ግን ከምርጫ ሂደት ውስጥ ወጥቻለሁ ያለ የለም፡፡ በመሆኑም ምርጫውን ያለቅድመ ሁናቴ የሚሳተፈውና ቅድመሁናቴ ያስቀመጠው አካል የምርጫ ምህዳሩን ለማስፋት፤ ምርጫው አልሆን ካለ ደግሞ ለህዝባዊ እምቢተኝነት ተባብረው የማይሰሩበት ምክንያት አይታየኝም፡፡
አንድነት ወደ ትብብሩ ያልመጣበት ምክንያት ከመድረክ ከወጣሁ በኋላ እንደገና ያለጥናት በፍጥነት ወደ ሌላ ትብብር ውስጥ መግባት የለብኝም የሚል ነው፡፡ ነገር ግን አንድነት ፓርቲ ውህደት ከሆነ በማንኛውም ጊዜ ዝግጁ ነኝ ይላል፡፡ ለመዋሀድ ዝግጁ የሆነ አካል ደግሞ ለመተባበር ይከብደዋል ብዬ ማሰብ ያቅተኛል፡፡ በመሆኑም ለመተባበር ዛሬ ነገ ሳይል ቢወስን ደስ ይለኛል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ትብብሩ ውስጥ ያሉት ፓርቲዎች ግማሽ መንገድ ሄደው አንድነትን መቀበል አለባቸው ብዬ አምናለሁ፡፡ አንድነት ካለው ድርጅታዊ አቅም አንፃር ታይቶ የትብብሩ ምክር ቤት አባል ብቻ ሳይሆን የትብብሩ ስራ አስፈፃሚም ውስጥ ተወካዩን እንዲያስገባ ሊፈቅዱለት ይገባል እላለሁ፡፡ ይህ ደግሞ ለአረናም ሆነ ለኦፌኮ የሚሰራ ይመስለኛል፡፡
በዚህ መልኩ ተባብረው የሚሰሩ ከሆኑ ምናልባትም አሁንም ቢሆን ጊዜው አረፈደም እና ሁሉም ፓርቲዎች በስምምነት በአንዱ ፓርቲ የምርጫ ምልክት ሊወዳደሩ ይችላሉ፡፡ ይህ እንኳን ባይሆን በእጩ አቀራረብ ላይ እየተመካከሩ ድምፅ የማይነጣጠቁበትን መንገድ መፈለግ ይችላሉ፡፡ ምርጫው ነፃ እስካልሆነ ድረስ አላስፈላጊ ነው ብለው ካሰቡም በጋራ ህዝቡን ለህዝባዊ እምቢተኝነት የሚያነቁበትን እና የሚያደራጁበትን መንገድ መፈለግ ይችላሉ፡፡
በቅርቡ አንድነት ፓርቲ በተለያዩ ክፍለሀገሮች ሰልፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡ ትብብሩም ሁለተኛ ዙር መርሀግብሩን አውጥቷል፡፡ እነዚህን ሁለት እንቅስቃሴዎች ማቀናጀት አስፈላጊ ነው፡፡ ለዚህም ከእንቅስቃሴዎቹ በፊት ፓርቲዎቹ አንዳች ስምምነት ላይ መድረስ አለባቸው፡፡
የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ እኔም ሆንኩ ሌሎች ጓዶች መታሰራችን እንደማይቀር አውቀዋለሁ፡፡ እስር ቤት ከገባሁ በኋላ ግን ውጪ ያለውን አካል እንዲተባበር መለመንን አልሻም፡፡ ‹‹ቀን ሳለ ሩጥ›› እንዲሉ ዛሬ ውጪ እያለሁ ፓርቲዎቹ እንዲተባበሩ ሙሉ ጊዜየን ሰጥቼ እሰራለሁ፡፡ ሌሎችም እንዲሰሩ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡
Image

ኢሳት የሚድያ ተቋም በበርካታ ሽህ ማይሎች ርቀት ላይ የሚገኝ ላገር ያስባል ተብሎ የተቋቋመ ድርጅት ነዉ፡፡እንደሚለዉ የኢትዮጵያዉያን አይንና ጀሮ ይሆናል ብለንም አስበን ነበር፡፡የኢድቶርያል ቦርዱን ፖሊሲ ብናዉቀዉ ደስ ባለን፡፡መስራቾች ብዙ ለፍተዉና ሩቅ አልመዉ እንዳቆሙት ይታመናል፡፡አንድነትን በፖሊሲ ደረጃ እየታገሉት ከሆነ ያሳዝናል፡፡የሁለትና ሶስት ጋዜጠኞች የግል ፍላጎትና ጨዋታ ከሆነም እናያለን፡፡
Image
እንዳለመታደል የአንድነት አባላትና ደጋፊዎች ሁሉ ባለብዙ ሚድያ፤ባለ ሙሉ ጦርና(ፌደራል ፖሊስ) ያገር ሃብት ይዞ ለሚያፍነን ፀረ ዲሞክራሲና አንደነት የሆነዉን ስረኣት እየታገልን ለዚህ ድርጊት የምንሸበር አንሆንም፡፡እነዚህ ጋዜጠኞች ግን የአንድነትን አወንታዊ የሰላማዊ ትግሉን እንቅስቃሴ፤የተመዘገበዉን ዉጤት ሳይሆን የእስርና እንግልት እንደሚያጎሉት እናዉቃለን፡፡ እኛ የጣልነዉን ወይ የወደቀብንን በማንሳት የኢቲቪን ስራ ሲደግሙብንም እንታዘባለን፡፡ይህንንም ከዚህ በፊት በሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባለቤትነት ግዜ በግብረሃይሉ ተገምግሞኣል፡፡

ብሶታችንን ብቻ ሳይሆን ያሉንን አማራጮች፤ስልተና እስትራተጂክ ግባችንን እንድናብራራ ቅርብ ያለዉ ሲዘጋብን እነሱዉ ቢከፍቱልን መላካም ነበር፡፡የሚፈልጉን ለብሶት ከሆነ ህዝቡ በቅርብ ስለሚያዉቀዉ ብዙም አያምሩንም፡፡ህዝቡ እንዲደራጅና ህገ መንግስታዊ መብቱን እንዲጠቀም ጉልበት እንዲኖረዉ ቢያስተምሩ በጎ ነበር፤እንድ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራርና የፓርላማ አባል ከሌላ ፓርቲ የፓርላማ አባልና የግዜዉ ባለስልጣን ተጨባበጠ ብሎ ክስ ግን ያስገምታል፡፡አንድነት የተከበሩ ዶ/ር ነጋሶን አምጥቶ መሪ፤እነ ሃብታሙ አያሌዉን ከፍተኛ አመራር… ያደረገበትን አገራዊ ፋይዳ የዘነጉት ይመስለኛል፡፡ዛሬም የአንድነት በር ወንጀለኛ ላልሆነ የኢህአዴግ አባልና ኢትዮጵያዊ ሁሉ በሩ ክፍት ነዉ፤ለዉይይትም ለትግልም፡፡

ሚድያ ናቸዉና ከሰራን ይዘግባሉ፡፡አንድነቶች በያለንበት ወደ ስራ!!! ሰላማዊ ለዉጥ እንዲመጣ የበኩላችሁን ገንቢ አስተዋፅኦ ለምታደርጉ የየትኛዉም ሚዲያ አይነት አካለት ግን በግሌ ክብር እሰጣለሁ፡፡ኢሳትና አንድነት ባላንጣም፤ወዳጆችም ሊሆኑ አይችሉም፡፡
ለለዉጥ እንደራጅ!!

Image

የባህር ዳሩ ገዳይ ካለምንም ጥያቄ በቀጥታ ለፖሊስ እጁን ሰቷል:: Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
ባሳለፍነው ሳምንት በአዲስ አበባ ካሳንቺስ ከቀድሞ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ጀርባ ከሚገኘው ድብቅ የደህንነት እስር ቤት ውስጥ በመገኘት በከፍተኛ የሴኩሪቲ ጥበቃ የነጻነት ታጋይ የሆነውን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር Greg Dorey እንዳነጋገሩ ሲታወቅ ከአንዳርጋቸው ጋር ያደረጉትን ቆይታ በተመለከተ ዝርዝር ማብራሪያ ባይገኝም በደህና ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ሲገልጹ የኤምባሲው ምንጮች እንዳሉት ስለ አንዳርጋቸው መረጃ ያላቸው ለስርአቱ ቅርብ የሆኑ ክፍተኛ የደህንነት አባላት እና የአንድ ብሄር ተወላጅ የሆኑ አንድ ቋንቋ ተናጋሪዎች እንደሆኑ ገልጸዋል::እንዲሁም አመነስቲ ኢንተርናሽናል አንዳርጋቸውን በተመለከተ ከታፍነ 6 ወር መሆኑን ገልጾ ሁኔታው አሳሳቢ ነው ሲል ለእንግሊዝ መንግስት አቤት ያለበተን መግለጫ ባሳለፍነው ሳምንት መግለጫ አውጥቶ ነበር::

ይህ በ እንዲህ እንዳለ በባህር ዳር ከተማ ውስጥ ድብ አንበሳ እየተባለ በሚጠራው ሆቴል አካባቢ አንድ አርሶ አድር ታጣቂ ሚሊሻ በሚመስል ጸጉረ ልውጥ ሰው የእንግሊዝ ዜግነት ያለው ቱሪስት መገደሉ ታውቋል::የአምባሰደሩ የአንዳርጋቸው ጽጌ ጉብኝት ተከትሎ የእንግሊዛዊ ቱሪስት መገደል ድንጋጤ ፈጥሯል::ገዳዩ ለግድያው እንደተዘጋጀበት በሚያስታውቅ መልኩ በአከባቢው አድብቶ ሲጠባበቅ የነበረ እና ወዲያው እንግሊዛዊውን እንደገደለው ለፖሊስ ያለምንም ጥያቄ እጁን ሰቷል::በአከባቢዉም የታተቁ ፖሊሶች የነበሩ ሲሆን ግድያው ሲፈጸም ምንም ያደረጉት መከላከል አልነበረም::ግድያው የተቀነባበረ ነው ሲል የባህር ዳር ህዝብ እየተናገረ ነው::

እኔ የዓረና-መድረክ ኣባል ከመሆኔ የተነሳ በምርጫ 2007 ዓ/ም ለፌደራል ወይም ለክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ እንደምሆን የራሴ እቅድ ይዤ ነበር፤ እናንተም በተመሳሳይ ግምት እንደምትጠብቁ እገምታለው። ኣሁን እየሆነ ያለው ግን “…ለምሳ ያሰቡን ለቁርስ ኣደረግናቸው..” ዓይነቱ የጓድ ሊቀ መንበር መንግስቱ ዓይነት ተግባር ህወሓት መራሹ የትግራይ መንግስት እጩ “ሽብርተኛ” ኣድርጎው ኣጭተውኛል። እም በኣቅሚቲ “..የኣሸባሪነት..” ካባ ለብሼ ቅሊንጦ ወይም […]

የቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንትና በኋላ የፌዴራል ደህንነት ዋና ባለስልጣን የሆኑት የሕወሐት ፖሊት ቢሮ ባል አቶ ፀጋዬ በርሄ በመቀሌ ልዩ ስሙ “አፕርታይድ መንደር” ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ያስገነቡት ባለሁለት ፎቅ ዘመናዊ ቪላ መሸጣቸውን ታማኝ ምንጮች አረጋገጠዋል። 10 ሚሊዮን ብር ገደማ እንደፈጀ የሚነገርለት የአቶ ፀጋዬ ቪላ ለአንድ ባለሃብት 25ሚሊዮን ብር እንደተሸጠ ቢነገረም በትክክል የተሸጠበትን ዋጋ ማወቅ እንዳልተቻለ ምንጮቹ […]

የፕሮግራም መግለጫ

ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡

የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡

ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡

ታኀሳስ ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የአየር ሃይል ደህንነቶች ወደ ጠፉት አብራሪዎች ቤት በድንገት በመሄድ ፍተሻዎችን ያካሄዱ ሲሆን፣ በቤቶች ውስጥ የተገኙ ሰነዶችን፣ የበረራ ማኑዋሎችን፣ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችን፣ ትጥቆችንና ሌሎችም ቁሳቁሶች ወስደዋል። ከደህንነቶች ጋር ምንም አይነት ፖሊስ ያልነበረ ሲሆን፣ ደህንነቶች ፍተሻውን ለማካሄድም የፍርድ ቤት ማዘዣ አላሳዩም። የመከላከያ ሰራዊት ባወጣው መግለጫ ሁለቱ …

ታኀሳስ ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የክልሉ ወኪላችን እንደገለጸችው ማንነቱ በውል ያልታወቀው እንግሊዛዊ ጧት ላይ ባዶ እጁን ወደ ጊዮርጊስ አካባቢ ሲንቀሳቀስ በአንድ የሚሊሺያ አባል ተገድሏል። ገዳዩ መሳሪያ በመያዝ ድብ አንበሳ እየተባለ በሚጠራው ሆቴል አካባቢ ሟቹን ሲጠባበቀው እንደነበር ዘጋቢያችን ያነጋገረቻቸው ሰዎች ገልጸዋል። በሆቴሉ አካባቢ ጫማ በመጥረግ የሚተዳደሩ ነዋሪዎች  ገዳዩ መሳሪያውን ይዞ ከእነሱ ጋር …

ታኀሳስ ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ በሽብርተኝነት ወንጀል የተከሰሱት የሰማያዊ፣ የአንድነትና አረና አመራሮች ከሌሎች 6 ተከሳሽ ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ልደታ በሚገኘው 19ኛው ወንጀል ችሎት ቀርበው በእስር ቤት ውስጥ ስለሚደርስባቸው እንግልትና የደህንነት ስጋት ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አሰምተዋል። የተከሳሾች ቤተሰቦች እስረኞችን ለመጠየቅ በሚሄዱበት ጊዜ በተለየ መዝገብ መመዝገባቸውን በመቃወም ለፍርድ ቤት ባሰሙት …

ታኀሳስ ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የደቡብ አፍሪካው መሪ ጃኮብ ዙማ ደቡብ ሱዳናዊያን ለ2 ሚሊዮን ህዝብ መፈናቀል ምክንያት የሆነውን ጦርነት በድርድር እንዲፈቱ ጠይቀዋል። በአዲስ አበባ የሚካሄደው የሰላም ድርድር ውጤት ለማምጣት በተሳነው  በዚህ ወቅት፣ ደቡብ አፍሪካ ተጨማሪ ግፊት እያደረገች ነው። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሁለቱ ተፋላሚ ሃይሎች ችግሮቻቸውን የማይፈቱ ከሆነ ማእቀብ ይጣልባቸዋል ሲሉ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።

የተለያዩ አራት ዓይነት የደንጉ ትኩሳት በሽታ አምጭ ተሐዋሲዎችን ለመከላከል የተገኘዉ መድሐኒት በሽታዉን ለማምከን አቅም እንዳለዉ ቢገለፅም፤ በክትባት መልክ ለተጠቃሚ ለማድረስ የሚደረገዉ ጥረት ግን ብዙ መሰናክል ተደቅኖበታል።

Image
በባህር ዳር ከተማ አንድ ኢንግሊዛዊ ቱሪስት ከአንድ ግለሰብ በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ አለፈ::በባህር ዳር ከተማ አንድ ኢንግሊዛዊ ቱሪስት ከአንድ ግለሰብ በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ አለፈ።ድርጊቱ የተፈፀመው ዛሬ ረፋድ 4 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ላይ ነው።በግድያው የተጠረጠረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ የወንጀል ድርጊቱ እየተጣራ ነው ። የሟቹም አስክሬን በሆስፒታል እንደሚገኝ ተመልክቷል።