35 ሺ ኢትዮዽያውያን እስረኞች በኢርትራ ሳህል በረሃ ዘመኑ ያለፈው የባርያ አገዛዝ እየተፈፀመባቸው ይገኛሉ::

አስደንጋጭ መረጃከአስገደ ገ/ስላሴ
35 ሺ ኢትዮዽያውያን እስረኞች በኢርትራ ሳህል በረሃ ዘመኑ ያለፈው የባርያ አገዛዝ እየተፈፀመባቸው ይገኛሉ::
የሻዕብያ የሽፍታ መንግስት በ1983 ዓ/ም ከደርግ ጋር በነበረ ጦርነት የተማረኩ ወጣት ወታደሮች ስቪል የመንግስት ሰራኞች በዛን ጊዜ ኢርትራ ላይ ይኖሩ የነበሩ ወጣት ዜጎች በሙያ የተካኑና ለስራው ያስፈልጉኛል ብሎ በመለየት ከ 36 ሺ በላይ በሳህል በረሃዎች በዓፍዓበት በናቅፋ በሰሜን መሰራቅ ሳህል ወስዶ በሃይልና ከባድ ስራ ያሰራቸው ነበር::
በኢትዮ ኢርትትራ ጦርነት ዋዜማ በሁሉም የኢርትራ ከተሞች የነበሩ ስቪል ሕብረተሰብና በሙያቸው ጦርነቱ ከተጀመረ እስከ ሻዕብያ የተሸነፈበት የማረካቸው ወታደሮችና ምልሻዎች ከኢርትራ ዘልቆ ወደ ትግራይ እየገባ ከ1990 እስከ 2007 ዓ/ም ለ17 ዓመት ያህል በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የትግራይ የጎንደር ወጣቶች አፍሶ የወሰዳቸው::
በስራ አጥነት በድህነት በመልካም አስተዳደርና ነፃነት እጦት ወደ ሱዳን ስራ ፍለጋ ብሎም ወደ ሌላ ሃገር ለመሸጋገር የኦሮሞ የአማራ የትግራይ የጋንቤላ ወዘተ ሱዳን የገቡ የሻዕብያ ልዩ ሰላዮች ወደ ሱዳን ሰርገው በመግባት ከሚሰሩበት በረሃና ከተሞች በመጥለፍና በማፈን ወደ ወገኖቻቸው ሳህል አገቡዋቸው:: እነዚህ ግፍ ይፈፀምባቸው ያሉ ዜጎች ከ1983 ዓም እስከ ዛሬ በእሱር መልክ ተይዘው በሁሉም የሻዕቢያ አካባቢዎች በከባድ ስራ ተሰማርው ይሰሩ የነበሩ እስከ 60ሺ ይገመቱ እንደነበሩ የመረጃው ምንጮች ይናገራሉ:: አሁን ግን በሳሀል በረሃዎች በተጨባጭ የሚኖሩ 36ሺ ናቸው ይባላል ከዛም ሊበልጡ ይችላሉ የቀሩ ተገድለዋል፡፡
እነዚህ ዜጎች የሚሰሩትን ስራ በሳዋ በባርካ በሰሜን ምስራቅ ሳህል በዓፍዓበት በማይሕመት በአልጌን በናቅፋ በግዝግዝያ በከረን አካባቢና በሰሜን ባህር በፍልፍል ዓራቶ የሚባሉ ቦታዎችና በሌሎች ቦታዎች በተለያዩ ከባድ ስራዎች ያሰሩዋቸው ነበሩ በሚሰሩበት ጊዜ በከባድ ጥበቃ ነው:: ለሚደርሰው ግፍ የመቃወም ምልከት ያሳዩ ወገኖች በእሰረኞች ፊት ይረሸናሉ::
ሌላ አስገራሚ ነገር ደግሞ በኢትዮዽያ ሰላማዊ ትግል አይቻልም ኢህአደግ እሱ በመጣበት መንገድ በነፍጥ ነው የሚወገድ ብለው ከሻዕብያ ጋር ተጠግተው ከህወሓት ለሻዕብያ ከሞት ለማዳን ያደረገው ሎሌነት እነዚም ከህወሓት በባሰ መንገድ ሎሌ ሆኖው የኢሳያስ ቤተ መንገሰት የሚጠብቁ ኢሳያስ ተኩሱ ሲላቸው የሚተኩሱ ደፈጣ ተዋጊዎች በመቃወም ኢትዮዽያዊ ጥያቄ ያነሱ ሻዕብያ የሚጠረጥራቸው ኢርተራውያን ወደ ሱዳን በስደት የገቡ የቻድ የናይጀርያ ዜጎች ሳይቀሩ ከ35ሺ እሰረኞች ቀላቅለው የባርያ አገዛዝ ተቋዳሽ ናቸው:: የዚህ ሁሉ ሚስጢር ያወጡ ያሉ ከእሰረኞቹ አምለጠው ወደ ዓረብ ሃገር የገቡ ሰዎች ናቸው:: እስረኞቹ ከ 10 ዓመት በፊት መላው የኢርተራ የሻዕብያ ተቋማት የእረሻና የግድበ ስራዎች እሰከ ምሸግ መስራት የሚሰሩ ነበሩ:: ማምለጥ በመጀመራቸው ግን ወደ ሳህል አካባቢ እንዲሰበሰቡ ተደረጉ::
የሚሰሩት ስራ ሻዕብያ 30 ዓመት የተቀመጠበት የቀበሮ ጉድጓድ 180 ኪሎሚትር ርዘመት ያለው ምሸግ ማደስ ለቱሪዝም ተብሎ በአፍዓበት በናቅፋ ቤቶች መስራትና ማደስ በሰሜን ምሰራቅ ሳህል የሚገኙ ትላልቅና አነስተኛ ተፋሰሶች መገደብ የእረሻ ስራ መስራት በሳህል የሚገኘው የነ ኢሳያስ የመሬት ውሰጥ ቤተመንገስተ ማደስ:: ሻዕብያ ይጠቀምባቸው የነበረ መንገዶች ማደስ ስራ ይሰማራሉ::
በዜጎቻችን የሚፈፀም ግፍ ቀን ተሊት በጥበቃ ስር ናቸው:: በቂ መገብ ህከመና የላቸውም የማምለጥ አዝማሚያ ያሳዩ ዜጎች በሆነ መንገድ ይረሸናሉ:: ሆን ተብሎ የተመሳሳይ ፆታ ወሲብ እርሰ በራሳቸው እንዲፈፅሙ ይደረጋል:: በቂ ልበስ የላቸውም በከባድ ስራ በህመም በርሃብ ተመጣጣኝ ምገብ ባለማግኘታቸው የወደቁ እንደልገመኞች ተቆጥረው ይረሸናሉ::
በአጠቃላይ በጨለማ የሚኖሩ ተስፋ የቆረጡ መሆናቸው ይገለጣል:: ታድያ የኢህአደግ መንገሰተና የሱ መዋቅሮች የሃገር መከላከያ ሚኒስቴር የደህንነት ጀነራሎች የደህንነት ባለስልጣናትና ሰላየቹ ምን እያደጉ ናቸው:: ከ35ሺ በላይ ዜጎቹ በበረሃ በአንድ ሽፈታ ስርዓት ሲሰቃዩ 23 ዓመት ሙሉ ምን እያደረጉ ናቸው:: እንደእሰራኤል ያሉ መንገሰታት እኮ ዜጎቿ በሓማስ ታጋዮች ሲጠለፉ ከባድ ጦርነት ተካሄደ ነገር ግን ኢስራኤል ወታደር ጂልዓድ ሸሊም ነፃ ለማውጣት ኋላ ግን በኢስራኤልና ከሓማስ በተደረው ስምምነት ኢስራኤል 3ሺ የፈለስጢም እስረኞች እንድትፈታና በጂልዓድ ሸሊም በዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል አማካይነት የእሰረኞች ልውውጥ ተደርጎ ነው ነገሩ የተፈታው::
የኢህአደግ መሪዎች ግን በአስር ሺ የሚቆጠሩ ዜጎቹ የባርያ አገዛዝ እየተፈፀመባቸው ደሮ የታፈነችባቸው አይመስሉም:: በቀላሉ እንኳ በምሽግ ያለው የሻዕብያ ሰራዊት በመተራመስ በ10ሺ የሚቆጠር ወታደር ማርኮ ተደራድሮ ማስወገድ ነበረበት:: በዚሁ የሻዕብያ ሽፍታ መንግስት ግፍ የኢርትራ ህዝብም ደስተኛ አይደለም::
ሌላ ይህ የሻዕብያ የሽፍታ መንግስት የሚፈፅመው ያለ ግፍ በዓለም መንግስታት በሰብአዊ መብት ተሟጓቾች ኢህአደግ ተፅኖ ለማድረግ ይችል ነበር:: ነገር ግን ምኑም አይደለም የትግራይ ክልል መሪዎች በወልቃይት ወርቅ ሲለቅሙ ከ280 በላይ ወጣቶች ታፍሰው ሳህል ሲገቡ እያወቀ ስለእነሱ ሲጠየቅ ውሸት ነው ተቃዋሚ ፓርቲዎች ያስፋፉት ወሬ ነው አሉ::
ሌላ በሃገር ውስጥና በውጭ ያሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ስለእነዚህ ዜጎች እንደአጀንዳ ይዘው አያነሱትም:: በመጨረሻ መላው የሃገራችን ህዝብ ሙሁራኖች ተማሪዎች በውጭ የምትገኙ ዜጎች ይህ በሻዕብያ የዜጎቻችን ይፈፅመው ያለው ግፍና የህወሓትት ኢህአደግ መሪዎች ለዜጎቻቸው አለመቆርቆር ተቃውሞ በማስነሳት ተፅእኖ ሊታደርጉ ዘንድ ጥሪ አቀርባለሁ:: በተጨማሪም ለተባበሩ መንግስታት ለሰብአዊ መብት ተሟጓቾች በዲፕሎማሲ ፅኖ በማድረግ ስለዜጎች እንስራ ሚስጢሩም መላው ዓለም ይወቀው::