የተጠለፈው ሔሊኮፕተር ፖለቲካዊ እንድምታ ምን ሊሆን ይችላል?

(ቢልልኝ ሀብታሙ አባቡ) አንድ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የሆነ ሔሊኮፕተር ተጠልፎ በኤርትራ ምድር ማረፉ በዚህ ሳምንት ተሰምቷል፡፡ የጠለፋውን አጠቃላይ አገራዊና አለም አቀፋዊ እንድምታ ለማየት ድርጊቱ ከግለሰቡ ስሜት የሚመነጭ ተራ የዜጋ ክህደት ነው ወይስ በአገራቱ መካከል በተፈጠረ መሻከር የተነሳ የፖለቲካ ትግላቸው አንድ አካል የሚለውን ለይቶ ማስቀመጥ ያስፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት በቅድሚያ የድርጊቱ ምንጭ ምን ሊሆን ይችላል የሚለውን ጥያቄ መመለሱ ጠቃሚ ነው፡፡ የድርጊቱን መነሻ ለማወቅ ፓይለቱ ለድርጊቱ ያነሳሳው የራሱ የግለሰቡ ተራ የሆነ የግለሰብ ስሜት ነው ወይስ ከጀርባው የተለየ ተልዕኮ አለ የሚሉትን ሁለት መነሻዎች ለይቶ ማጥናት ያስፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት ከሁለቱ አንዱን መምረጥ የሚያስችሉ የአሳብ መነሻዎችን ማየት ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡ ለዚህ ዋናው መነሻ ግለሰቡ ከሌሎች አገሮች ኤርትራን ለመድረሻ የመረጠበት ምክንያት እና ግለሰቡ የኤርትራን ድንበር አቋርጦ ሲሄድ በሰላም መስተናገዱ ምንአልባት ግለሰቡ በጉዳዩ ዙሪያ ከኤርትራ መንግስት ጋር ረዘም ላለ ጊዜ በድብቅ ሲሰራ እንደቆየ ሊያመላክት ይችላል፡፡ የኤርትራ መንግስት እንደጠላት ከሚያያት አገር የጦር ሄሊኮፍተር ድንበሩን አቋርጦ ሲገባ የአፀፋ ምላሽ አለመስጠቱ አስመራው አስተዳደር ድርጊቱ እንደሚፈጸም ቀደም ብሎ ያውቅ እንደነበረ ሊያመላክት ይችላል፡፡ እነደዚህ ከሆነ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስት ጠላት ያለው በራሱ ጉያ እንጂ በሚሊየን ኪሎሜትር ርቀት ላይ እንዳልሆነ ያመላክታል፡፡ የተጠናከረውን የኢትዮጵያ መንግስት ደህንነት አልፎ ተልዕኮውን ማሳካቱ የኤርትራ መንግስት በጉዳዩ ላይ ለረጅም ጊዜ ሲሰራበት የቆየ ተልዕኮ እንዳልቀረ ያመላክታል፡፡ የኢትጵያ መንግስት ምላሽ ምን ሊሆን ይችላል? በዋናነት ውድ ዋጋ ያለው ሀብት በመወሰዱ ሳይሆን በሁለቱ አገራት […]