ዕርቀ ሰላሙን በሚያወርደው የሁለቱም ወገኖች ስምምነት መሠረት ከኅዳር ወር ፳፻፫ ዓ.ም. ጀምሮ ከሐዋሳ ደብረ ምሕረት ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ተለይተው ‹‹ወንዲታ›› በተባለው የግለሰብ ስቱዲዮ ውስጥ ሲሰበሰቡ የነበሩ ምእመናን÷ በሰንበት ት/ቤት፣ በስብከተ ወንጌል እና በልማት ኮሚቴዎች ውስጥ የመሳተፍና የማገልገል መብታቸው ይጠበቅላቸዋል፡፡ በዚህም መሠረት በሰንበት ት/ቤቱ አመራርና በስብከተ ወንጌል ኮሚቴ ሁለት፣ ሁለት፤ በልማት ኮሚቴ ውስጥ ደግሞ በሰበካ ሳይወሰኑ …

ኢትዮጵያዊው ስደተኛ ሣሙዔል መኮንን <አቡሽ> ዛሬ በዘጠኝ ሠዓት በካንፓላ መካነ ሠላም መድሐንያለም ቤተክክርስትያን በድንግል መሬት ተቀበረ።ወጣት ሣሙዔል መኮንን <አቡሽ>ከሐገሩ ተሠዶ ከወጣ አምስት ዓመታት የተቆጠረ ሲሆን ወደሌላ ሐገር ለመሻገር ሣይችል የምድር ጉዞውን በምድር ወገቧ ዩጋንዳ ጨርሷል።ከሃምሣ ያላነሡ ሥደተኞች በቀብሩ ላይ መገኘታቸውን የፔን ዘ ኢትዮጵያ ዘጋቢ የታዘበ ሲሆን ወጣቱ በጉበት ህመም ባለፈው ማክሠኞ ጧት በተኛበት ሞቶ መገኘቱን ሀኪሞች ጠቁመዎል።

የታላቁን የነጻነት ታግይ መሞት ተከትሎ ከወያኔ ጎረምሶች የሚወረወሩ ቃላቶች የፖለቲካ ብስለትን ያላገናዘቡ እና የስልጣን ጥመኝነትን የሚያሳብቁ የጭፍን ድጋፍ ሩጫዎች ሲሆኑ ማንዴላን በተመለከት ከተለያዩ ኢትዮጵያውያን የሚወረወሩ የነጻነት ስሞች እና የአፓርታይድ ቃላቶች የውስጥ ህመም ሆኖባቸው ሟች አምባገነናቸውን እያነሱ መቀባጠር ጀምረዋል::

የማንዴላ ሞት አለም ያለቀሰበት የአሜሪካ ባንድራ ለ3 ቀን ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ (President Barack Obama ordered American flags to be lowered immediately to half-staff until Monday in tribute to Mandela, a rare honor for a foreign leader.)የተወሰነበት ነጭ ከጥቁር ሳይል ክብሩን የገለጸበት መሆኑን በወያኔ ጎረምሶች ለምን መካድ እንደተፈለገ አይገባኝም ? የተቃዋሚ ሃይሎች ለማንዴላ ሞት ሃዘናቸውን ስለገለጹ? አሊያስ የአለም ህዝብ አትኩሮቱ ሁሉ ወደ ደቡብ አፍሪካ ስለሆነ? ወይንሳ ለመለስ ሞት የህን ያህል …አለመደረጉ ?

ደቡብ አፍሪካ ላይ ሌጋሲ የሚባል ነገር ወላ የፖለቲካ ህዳሴ አሊያም የሚዲያ ፍጆታ ወሬ ምንምን አይሰራም:: የማንዴላ ጣኦትነት አይሰበክም :: የማንዴላ ሌጋሲ አይሰበክም :: የምንሰማው በጽናት የሃገራቸውን ነጻነት ያረጋገጥኡ በአለም አቀፍ ደረጃ የነጻነት ቀንዲል የሰላም እና የአንድነት አባት መሆናቸውን እና ፈለጋቸውን እንድንከተል እንጂ ትራንስፎርሜሽናቸውን እያጨበጨብን እንድንቀበል አይደለም::

ወያኔ የሚሰራውን ግፍና ሰቆቃ ስለሚያውቀው የነጻነት የዲሞክራሲ ጥያቄ እና የጎሳ ፌዴራሊዝም ተቃውሞ በተነሳ ቁጥር ራስ ምታት ይሆንበታል:: በአለም አቀፍ ደረጃ ለዚህ የታገሉ ሰዎች ስማቸው ሲጠራ ያመዋል:; አብሶ ተቃዋሚዎች ከተናገሩ ያቃጥለዋል:: አጸ ምንሊክ … ቀኃሥ … ማንዴላ… ምናምን እየተባላ ሲተራ ያሳክከዋል ..ያራውጠዋል:….. የአገዛዝ ስልቱ በኒዎ አፓርታይድ ላይ ስለተመሰረተ የደቡብ አፍሪካው የጸረ አፓርታይድ ትግል ሲነሳ የስልጣን ማስረዘሚያው ዘዴ የተነቃበት ስለሚመስለው ይጨፍራል ለማዘናጋት ይራወጣል:: ኢትዮጵያውያን ስለእንደዚህ አይነት ነገር መስማት የለባቸውም:: አርፈው መገዛት አለባቸው ይህ ከተነሳ ወያኔ በሽታው አብሮ ይነሳል ይፈራል:ስራውን ስለሚያውቅ::

የዛሬው የወያኔ ጎረምሶች ጭፈራ በከፊል የህን የተመረኮዘ ነው::በአለም በአፍሪካ በሃገር ቤት አንድ ነገር በመጣ ሰአት ሁሉ ወያኔ የሚለቃቸውን የፖለቲካ ፍጆታ ነጠላ ዜማዎች ለማቆም መጣር እንዳለበት ልንመክረው እንፈልጋለን::

የኢትዮጵያ አንድነትንና የመንግስት ስርዓቱን የሚመለከቱት የመለስ ሃሳቦችና ድርጊቶች ለኢትዮጵያ ህዝብ ከባድና አሳሳቢ ትርጉም አላቸው፡፡ የአንድነቱ ጥያቄ የኢትዮጵያ እንደ አገር የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ ሲሆን፣ ስርአቱ ደግሞ በኢትዮጵያ ህዝብ መብቶች ላይ ማን መወሰን እንደሚችል ያመለክታል፡፡ የአገር ህልውና እና የህዝብ መብትን ያህል ትልቅ ጉዳይ ሊኖር ስለማይችል ክብደቱና አሳሳቢነቱ አያጠያይቅም፡፡ መለስ አንድነትን በሚመለከተው ሃሳቡ ትግራይን ከመገንጠል ኣላማ ጀምሮ ሳይተገብረው […]

ህዳር ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ደቡብ አፍሪካውያን ለነፃነት አባታቸውና ለቀድሞ መሪያቸው ለኔልሰን ማንዴላ ሀዘናቸውን ለመግለጽ ወደ ጁሀንስበርግበና ሶዌቶ እየተሰበሰቡ ሲሆን፤ ታላላቅ የዓለማችን መሪዎችና ታዋቂ ሰዎችም በማንዴላ ሞት ሀዘናቸውን እየገለፁ ነው። በርካታ ደቡብ አፍሪካውያን በስዌቶ በሚገኘው በቀድሞው የኔልሰን ማንዴላ መኖሪያ ቤት በመሰባሰብ በባህላዊ ስርአታቸው መሰረት በልዩ ልዩ የብሔረሰቦች የሀዘን ጭፈራ  ለመሪያቸው ያላቸውን አክብሮች እየገለፁ …

ህዳር ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጋሞጎፋ ዞን በቁጫ ወረዳ ከማንነት ጋር በተያያዘ የተነሳው ተቃውሞ መፍቴ አጥቶ እንደቀጠለ ባለበት ወቅት በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እየታሰሩ መሆኑን የአነጋግረናቸው የአገር ሽማግሌዎች ገልጸዋል። በዛሬው እለት በርካታ የአገር ሽማግሌዎች የጸጥታ ሀይሎች እያደረሱባቸውን ያለውን ስቃይ ለማስታወቅ በጠቅላይ ሚኒሰትሩ ጽህፈት ቤትና በፌዴሬሽን ምክር ቤት ቢገኙም የሚያነጋግራቸው አጥተው ተመልሰዋል። አገር ሽማግሌዎቹ …

ህዳር ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከፋ ዞን በቦንጋ ከተማ የሚገኙ መምህራን ፣ መንግስት ለአባይ ግድብ በማለት ያለፈቃዳቸው የቆረጠባቸውን ደሞዝ በአስቸኳይ ካልመለሰ ሰኞ የስራ ማቆም አድማ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። መምህራኑ ዛሬ ወርሀዊ ደሞዛቸውን ለመቀበል ወደ ባንክ ሲሄዱ ለአባይ ግድብ በሚል ደሞዛቸው ተቆርጦ ተሰጥቷቸዋል። በሁኔታው የተበሳጩት መምህራን ወደ ትምህርት ጽህፈት ቤት ሲያመሩ መስተዳድሩ ያዘዘው በመሆኑ ምንም …

ህዳር ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅድመ መደበኛ ት/ቤት ገብተው መማር ከሚገባቸው እድሜያቸው ለትምህርት ከደረሱ ሀፃናት ውስጥ 23 በመቶዎቹ ወደ ትምህርት ቤት አለመምጣታቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው ሰነድ ያስረዳል። ከ1ኛ አስከ 4ኛ ክፍል ድረስ የትምህርት ገበታቸው ላይ የተገኙ ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ መሆኑን የሚያሳያየው ሰነዱ፣ከ5ኛ አስከ 8ኛ ክፍል ድረስ ገብተው መማር የነበረባቸው ተማሪዎች   ቁጥር አነስተኛ መሆኑንም  …

ዓለም፥ ድፍን ዓለም የሩሲያዉ ፕሬዝዳት ቭላድሚር እንዳሉት «የዘመኑን ታላቅ ፖለቲከኛ» በማጣቱ ተከዘ።አብዛኛዉ ዓለም አዘነ።ደቡብ አፍሪቃዎች ደግሞ በሐገሪቱ ፕሬዝዳት በጄኮብ ዙማ አገላለፅ «መሆን የሚፈልጉትን እንዲሆኑ ባደረጓቸዉ» ታላቅ ሰዉ ሞት አረገዱ።

እንደ ወጣት በእልሕ፥ እንደ ወታደር በነፍጥ፥ እንደ ሕግ አዋቂ በፍርድ ቤት ታገሉ።እንደ ወንጀለኛ ታሠሩ።እንደ ዲፕሎማት ተደራደሩ፥ እንደ ፖለቲከኛ የሕዝብ እኩልንነትን አስርፀዉ ሐገር መሩ።እና እንደ ሰዉ የምድር ሩጫቸዉን ትናንት ጨረሹ።ዘጠና አምስት አመታቸዉ ነበር።

የዓለም የኤድስ ቀን ባለፈው እሁድ በዓለም ዙሪያ ታስቦ ውሏል። በአጠቃላይ የHIV ቫይረስ በደማቸው የሚገኝ ሰዎች ቁጥር ቢቀንስም በወጣቶቱ ዘንድ ቁጥሩ በእጥፍ መጨመሩን ነው ሰሞኑን የወጣው የተመድ ዘገባ የሚያስረዳው። «ኤድስ እና የወጣቱ ግንዛቤ» የዛሬው የወጣቶች ዓለም ርዕስ ነው።

መቼም ሰው ሥጋ ነኝና ታከተኝ እረፍት ለጎኔ ናፈቀኝ ሩጫዬን ግን ጨርሻለሁ እምነቴንም ጠብቂያለሁ እነሆ ከፊቴ ………. ከሰማዩ ከላይ ኣባቴ የድል ኣክሊል ተዘጋጅቶልኛል የሰላም የፍትህና የ’ኩልነት ደግሞ የህግ በላይነት ዋንጫዎች ይጠብቁኛል እስትንፋሴ ሳይለይ ግን ኣንድ ነገር ልበል…….. ኣንቺ ኣፍሪካ……… እትብቴ ስወለድ የተቀበረብሽ ዘመኔን ሁሉ የሰጠሁሽ እናት ዓለም ኣዳምጪኝማ ኑዛዜ ቃሌን ጻፊልኝማ ኣዳምጪኝማ ልንገርሽ ምክር ተግሳጼን ልስጥሽ […]

የነጻነት ታጋዩ ኔልሰን ማንዴላ በ95 አመታቸው ከዚህ አለም ሲለዩ፤ የተለያዩ አገሮች እንደየራሳቸው ግንኙነት የራሳቸውን ታሪክ ሲያወሩ ነበር። የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ሃዘናቸውን ሲገልጹ ከማንዴላ ጋር የነበራቸውን ግንኙነት በመግለጽ ነበር። እኔ በምኖርበት አትላንታ ከተማ ዜናው ሲቀርብ፤ ኔልሰን ማንዴላ አትላንታ በመጡበት ወቅት፣ ከነአንድርው ያንግ ጋር ሆነው የማርቲን ሉተር ኪንግ ማዕከልን ስለመጎብኘታቸው ነበር – ዋናው ዜና። ሁሉም አገር ስለማንዴላ የየራሱ […]

የኢትዮጵያ አንድነትንና የመንግስት ስርዓቱን የሚመለከቱት የመለስ ሃሳቦችና ድርጊቶች ለኢትዮጵያ ህዝብ ከባድና አሳሳቢ ትርጉም አላቸው፡፡ የአንድነቱ ጥያቄ የኢትዮጵያ እንደ አገር የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ ሲሆን፣ ስርአቱ ደግሞ በኢትዮጵያ ህዝብ መብቶች ላይ ማን መወሰን እንደሚችል ያመለክታል፡፡ የአገር ህልውና እና የህዝብ መብትን ያህል ትልቅ ጉዳይ ሊኖር ስለማይችል ክብደቱና አሳሳቢነቱ አያጠያይቅም፡፡ መለስ አንድነትን በሚመለከተው ሃሳቡ ትግራይን ከመገንጠል ኣላማ ጀምሮ ሳይተገብረው […]

ታላቁ የነፃነት አርበኛ ኔልሰን ማንዴላ በአይቀሬው ሞት ሲረቱ ጆሀንስበርግ ብቻዋን የሀዘን ቡልኮ አላጠለቀችም።መላ ዓለም በሀዘን በረዶ ተመቷል።አፓርታይድን ወደ ከርሠ መቃብር ያወረደ ጀግና በአይቀሬው ሞት ተረታ።
እንደኔ ምኞት አፍሪቃ በየማዕዘኑ የማንዴላን አይነት መሪ ብታገኝ ምን ያህል የታደለች አህጉር በሆነች ነበር<>የተባበሩት የአፍሪቃ አንድ ገናና ስቴት በሆንን ነበረ።ነገ የሚሆነውን ለመተንበይ ነብይ መሆን ቢያስፈልግም አሁን ያለችው አፍሪቃ ከሃምሣ አራት ግዛትነት ወደ አንዲት አህጉር እንድትመጣና አንዲት ሐገር ለመሆን በየቤታችን ያለው ማነቆና የገዢ ፓርቲዎች ማቱሣላዊ ቆይታ ድቅድቅ ላይ መሆናችንን ጠቋሚ ነው።ወደ ስልሣና ሠባ ትናንሽ ሐገራት እንዳንከፋፈልም የሚያሠጉ ሁኔታዎችም መኖራቸውን መገንዘብ ይኖርብናል።
ከማንዴላ ጋር የጠበቀ ቁርኝት የነበራት የኔዋ ፀረ አፓርታይድ የነበረችው ኢትዮጵያ ጠያይም ሐገር በቀል አፓርታይዳዊ ስርዓት አራማጆች እያቆጠቆጠባት መሆኗን መደበቅ ለኔ ህሊና አይመጥንም።
የስራ ባልደረባዬ እስክንድር ነጋ በግፈኞች የተፈረደበት ጠበንጃ አንስቶ ወይም ፓርቲ መስርቶ ለስልጣን ስለታገለ እንዳልሆነ አሳሪዎቹ ጭምር የሚገነዘቡት መራራ ሐቅ ነው።
እስክንድርና ማንዴላ የነፃነት ታጋዮች ናቸው።ማንዴላ አፓርታይድን ለመዋጋት ቢያንስ ወታደራዊ ስልጠና በሐገራችን ጭምር እንደወሠዱ ከታሪክ ተገንዝበናል።እስክንድር የጦር መሣርያና የጦር ሠፈርፊትም ይሁን ወደፊት ከእስር ሲወጣ እንደማይረግጥ ስለማውቀው ላረጋግጥ እችላለሁ።የእስክንድር ኡዚ ብዕሩ ነው።ሟቹ ለገሠ ዜናዊ ጥይት በማይበሳው መኪና ታጅቦ ሲጓዝ አናቱን ብሎ ያዞረው ከእስክንድር ቀለም ተፊ ሠላማዊ ኡዚ ብዕሩ የተተኮሰ ህዝባዊ ማዕበል ቀስቃሽ ፅሁፉ ነው።ያሣሠረውም ሙያውና ሕዝባዊ አመለካከቱ ነው።
ከአሜሪካ ቅምጥል ኑሮን ንቆ የመጣው ለውጥ መጥቷል፣በሐገሬ በሙያዬ የበኩሌን ላበርክት ብሎ በመወሰኑ ነበር።ከሃያ ዓመታት በላይ ስርዓቱን በስክሪብቶ ሲፋለም የኖረው።
ማንዴላ ቢባል ኣይበዛበትም።ለሃገሩ ብሎ ያላጣው ነገር የለም።
ነገ እንደ እስክንድር ነጋ አይነት ዜጎች የሐገራችን ተስፋ ይሆናሉ።የነ ስብሐት ነጋ ስርዓት ሲመሽበትና የነብርሃኑ ነጋ ዘመን ሲመጣና እውነተኛ የሚተገበር ህገ መንግስት ሲዘርጋ ህዝቡ የመረጠው ፓርቲ ስልጣን ላይ ሲወጣ የዛሬ ስምንት ዓመት ጥያት ወደወሁባት የአፍሪቃ መዲናይቱ እትብቴ የተቀበረባት እውነተኛዎ ሪፐብሊክ ኦፍ ዴሞክራቲክ ኢትዮጵያ በወጣሁበት ሞያሌ ሳይሆን በቦሌ እገባለሁ።ዘወትር የምጠብቃት ቀን ደሞ ትመጣለች።
ማንዴላ ታሪክ ሰርቶ አልፏል።ኢትዮጵያዊያን የራሣችንን ኤኤንሲ መስርተን በማቆጥቆጥ ላይ ያለውን አፓርታይዳዊ ሥርዓት በህዝባዊ ሱናሚ ኣስወግደን እስክንድርን በፍትሐዊ ምርጫ እንደማንዴላ ለመሪነት ለማብቃትና ቃሊቲ ያሉ ጀግኖቻችንን ነፃ ለማውጣት የማንዴላን ፈልግ እንከተል የሚለው መልዕክቴ በዛሬዋ ዕለት በስደት ከምማቅቅባት ሐገር ይድረሳችሁ ።
ነፍስ ይማር ለታላቁ የአፍሪቃ ብርቅዬ ልጅ ኔልሠን ማንዴላ
ደረጀ በጋሻው
የቀድሞ የአስኳል ጋዜጣ
ዋና አዘጋጅ
ምስራቅ አፍሪቃ

 አራቱ ኃያላን መጽሐፍን በተመለከተ በኢትዮጵያ የመካከለኛው ዘመን ታሪክና በጽንዐት በሚታወቁት አባቶች ታሪክና አስተዋጽዖ ዙሪያ ጎንደር ከተማ ላይ ልዩ መርሐ ግብር ይኖረናል፡፡ በጎንደር ዙሪያ፣ በባሕርዳር፣ በደብረ ታቦርና አካባቢው ያላችሁ ሁሉ ተጋብዛችኋል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ

·   ዶክተር ውዱ ጣፈጠ

·   ዶክተር አምሳሉ ተፈራ

·   አቶ ባንተ ዓለም ታደሰ – ጥናት ያቀርባሉ

ቀን ፡- ታኅሣሥ 20 ቀን 2006 ዓም

ሰዓት ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ

ቦታ ፡- ጎንደር ታየ በላይ ሆቴል

የመግቢያውን ካርድ ለማግኘት የሚከተሉትን ስልክ ቁጥሮች ይጠቀሙ

0918190868 / 0913788769

ህዳር ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመኖሪያና የስራ ፈቃድ የላችሁም በሚል ከሳዑዲዓረቢያ ወደ አገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ሲሆን ቁጥሩ መንግስት አስቀድሞ ካሰበው እጅግ አሻቅቧል፡፡ በዚህ ም ምክንያት ተመላሾቹን ለመቀበልና ለማቋቋም  መንግስት በቂ በጀት አለመያዙ እንደ አገር አሳፋሪ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልጸዋል፡፡ መንግስት የተመላሾቹ ቁጥር 23 ሺ ገደማ መሆኑንና እነዚህም …

ህዳር ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-8ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ለማክበር በሚል የጅጅጋ ከተማ በፌደራል ፖሊስ  አባላት መወረሯን ነዋሪዎች ገልጸዋል። የፌደራል ፖሊስ አባላት ከተማውን ከተቆጣጠሩት በሁዋላ ልዩ ፖሊስ እየተባሉ የሚጠሩት ሀይሎችን ወደ ዳር የገፉዋቸው ሲሆን፣ ፖሊሶቹ በየተወሰኑ ሜትሮች ቁጥጥር እያደረጉ ነው። የጸጥታ ጥበቃው በሄሊኮፕተር ላይ በሚደረግ ቅኝት የታጀበ ሲሆን፣ በየ አቅጣጫውም በዙ 23 እና …

ህዳር ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመርካቶ በተለምዶ ጆንያ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ትላንት ከቀትር በኃላ የደረሰውን የእሳት አደጋ በወቅቱ ከመቆጣጠር ይልቅ ጉቦ ለማግኘት የእሳት አደጋ ሰራተኞች በድርድር ጊዜ በማጥፋታቸው ንብረታችንን እንድናጣ አድርጎናል ያሉ ነጋዴዎች የአዲስአበባ ከተማ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ኤጀንሲን ለመክሰስ መወሰናቸውን አስታወቁ፡፡ ከተጎጂ ነጋዴዎች መካከል አንዱ የሆኑት ለአዲስ አበባው ዘጋቢ …

ህዳር ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ አገሪቱን እንደተቆጣጠረ ተሀድሶ አልወሰዱም በሚሉና በተለያዩ ሰበቦች የጡረታ መብታቸው ላልተከበረላቸው የቀድሞ የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት አባላት፣ የጡረታ መብታቸውን ለማስከበር መንግስት ጥሪ ማቅረቡ ታውቋል። የመንግስት ሹሞች የቀድሞ ወተዳሮቹን  ፎርም እንዲሞሉ እያደረጉዋቸው መሆኑን አንዳንድ ወታደሮች ለኢሳት ገልጸዋል። መንግስት በአሁኑ ጊዜ ይህን እርምጃ ለምን ለመውሰድ እንደፈለገ አልታወቀም። ለጉዳዩ  ቅርበት ያላቸው ሰዎች …

ህዳር ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት በአደጋው 40 ሰዎች የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል። የአደጋው መንስኤም ከአቅም በላይ ጭነት መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። በጭልጋ ወረዳ ደግሞ አንድ ነዳጅ የጫነ ቦቴ መኪና ተገልብጦ ተሽከርካሪዎች ለመተላላፍ ባለማቻላቸው መቸገራቸውን ለማወቅ ተችሎአል። መኪናው ነዳጅ እንደጫነ በመገልበጡ እሳት ይፈጠራል የሚል ስጋት ማሳደሩን የአካባቢው ሰዎች ግልጸዋል።

Ethiopia Zare (ረቡዕ ሕዳር 25  ቀን 2006 ዓ.ም. Dec 5, 2013)አፓርታይድን ከምድረ ሳውስ አፍሪካ እስከመጨረሻው ለመገርሰስ በተደረገው ታላቅ ተጋድሎ በዋንኛነት ተጠቃሽ የነበሩትና የሰላም አባት በመባል አላማቀፋዊ ሽልማቶችን የተጎናጸፉት የደቡባዊት አፍሪካ የነጻነት አባት ኔልሰን ማንዴላ አረፉ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

የአዲስ አባብን ገጽታ ለመቀየር በወጣው ትልቅ የመሰረተ-ልማት ዝርጋታ ውጥኖች መሰረት ሰፊ የግንባታ ስራ እየተካሄደ ነው። አንድን የሀገር መዲናን በአጭር ጊዜ ለመቀየር የሚደረግ ጥረት አንደምታም ሊኖረው እንደሚችል ተገልጿል።

SHARE:

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ፓርቲውን በአውሮፓ እና በአሜሪካ የማስተዋወቅ ስራቸውን ቀጥለው በዛሬው እለት በስዊዘርላንድ ጀኔቫ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኢትዮጵያዊያን በሳውዲ መንግስት ላይ በሚያደርጉት ተቃውሞ ሰልፍ ላይ በመገኘት መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ ከሰልፉም መጠናቀቅ በኋላ ከአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት( IOM ) ከአለምአቀፍ የሰራተኞች ድርጅት (ILO) እና ከተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ( UN Human Rights Commission) ሀላፊዎች ጋር በሳውዲ ስለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ጉዳይላይ ሰፊ ውይይቶችን አድርገዋል፡፡ በነገው እለትም በጂኔቫ የመሸኛ የእራት ፕሮግራም የተዘጋጀላቸው ሲሆን ቅዳሜም ወደ ሆላንድ አምስተርዳም በመብረር እዛ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ ጋር ውይይት ያደርጋሉ፡፡

ላሳለፈነው ሰኞ ተቀጥሮ የነበረው በእሥር ላይ የሚገኙት የሙስሊሙ ኅብረተሰብ ጥያቄ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የእነ አቡበከር አሕመድ ጉዳይ ለፊታችን ታኅሣስ 3/2006 ዓ.ም ተቀጥሯል፡፡


ወያኔ የካደው እና ግንቦት ሰባት የተነፈሰው የእንደራደር ጥያቄ የአናጎሜዝን የአዲስ አበባ ቆይታ ተከትሎ የወጣ ጉዳይ ነው::

Image

ምንሊክ ሳልሳዊ :-ይህን ሰሞን በሃገር ውስጥ እና በውጪው ሃገር ኢትዮጵያውያን ዘንድ የመወያያ ርእስ የሆነው እና ይየወያኔ ካድሬዎችን ቀልብ የገፈፈው እና ከሰል ያለበሳቸው ወያኔ ለግንቦት ሰባት ያቀረበው የድርድር ጥያቄ ነው::በስፋት አሁንም እየተከራከሩበት ያለው ይህ ጉዳይ አገሩን በጡዘት አምሶት የሃገሪቱ የፖለቲካ ሂደት አንድ ተስፋ የሰጠ ሁኔታ እንደሚታይ እየተተነበየ ነው::

ወያኔ በእርግጥ በማይጥም የፖለቲካ እሰጥ አገባ የተጠመደ ቢሆንም የወያኔ ፕሮፓጋንዳ ለላውን ከማዘናጋት ውጪ ምንም አይነት ፋይዳ እንዳሌለው እና ራሱን እየፈተሸ እንደሆነ ያጋለጠ ጉዳይ ነው:: የድርድር ጥያቄ አላቀረብኩም ያለው ወያኔ እንደለመደው ከኦነግ ከኦብነግ ከሻእቢያ ጋርም እየተደራደረ ጥያቄውን እራሱ እያቀረበው ሲክድ የቆየ ሲሆን በቅርቡ እንኳን በኬንያ ከኦብነግ በጀርመን ከሻእቢያ ጋይ ያደረጋቸውን ድርድሮች እየታከካቸው አልፏል::

ወያኔ የካደው እና ግንቦት ሰባት የተነፈሰው የእንደራደር ጥያቄ የአናጎሜዝን የአዲስ አበባ ቆይታ ተከትሎ የወጣ ጉዳይ ነው:: በእርግጥ በተለያዩ ጊዜያት ለወያኔ እና ለግንቦት ሰባት የቅርብ ርቀት የሆኑ ሰዎች ይህንን ጉዳይ በግል አንስተውት የሆነ ቢሆንም ባይሆንም ግን የአና ጎሜዝ የአዲስ አበባ ምላስ ተከትሎ ግንቦት ሰባት ለህዝብ ይፋ ያደረገው ጉዳይ አሁንም ሚዛኑ ወደ ግንቦት ሰባት እንዲሆን አድርጎታል::

እንቅልፍ የነሳቸው የወያኔ ባለስልታናት የቀን ተቀን የስብሰባ መቀመጫቸው ግንቦት ሰባት ነው:; በወታደሩ በደህንነቱ እና በታማኝ ካድሬው ዙሪያ ውይይቱ ምስጢሩ ግንቦት ሰባት ነው:: እነዚህ የሚስጥር ተወያዮች እንደሚጠቁሙት ሲሰበሰቡ በውይይት ወቅት ግንቦት ሰባትን አሸባሪ ብለው አይጠሩትም:; አሸባሪ የሚለውን ቃል የሚጠቀሙት ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታቸው አደባባይ ላይ መሆኑን በይፋ የተረጋገጠ መረጃ ይጠቁማል::
በቅርቡ ከአባቱ ሻእቢያ ጋር ጀርመን ላይ የተወያየው ወያኔ ግንቦት ሰባት የራስ ምታት ስለሆነበት እንዲያደራድረው አሊያም እንዲገላግለው ተማጽኖ ቢሆንስ??? ወይኔ ሻእቢያ የሚፈልጋቸውን ተቃዋሚ ኤርትራውያንን እያፈነ እንደሚሰጥ የህን ሰሞን ሃተታዎች እየጠቆሙ ነው እንዲሁም በሱዳን በኩል እያሽከረከረም እንደሚያስረክብ::ነገሩ የጨነቀው እርጉዝ ያገባል አይነት ነው ….
የአቶ ታምራት ላይኔም ወደ ፖለቲካው ለመቀላቀል ማቆብቆብ እኮ የዚሁ የድርድር አንዱ አካል ነው:; ብኣዴን ታምራት ላይኔን ይፈልገዋል:: አገሬ በፈለገችኝ ሰአት ለማገልገል ተዘጋጂቻለሁ የሚለው ታምራት ጠጋ በል እየተባል መሆኑስ የወያኔ አንድ የጭንቀት ምልክት አይደል?! … ወደ ሚዲያዎች አያሰገገ መምጣቱ ሌላ ምስጢር የለውም::

አና ጎሜዝ ከአዲስ አበባው ቆይታቸው ሁለት ንግግሮችን ከአንደበታቸው ሰምተናል:: አንዱ “ከባለስልጣናት ጋር ያደረኩት ውይይት በጎ እና ገንቢ ነው መልካም ምላሽ እንዳገኙም በእርካታ ተናግረዋል:; በመተማመን ስሜት ደሞ “አዲስ ንፋስ አለ” ሲሉ ተስፋቸውን አብርተዋል:: ይህንን የፖለቲካ ስሜታቸውን ያልተረዱ የደፈናው ጋዜጠኞች የወያኔን የሞተ እስትንፋስ ሊያበረቱ ቢሞክሩም የሚሳካ ካለመሆኑም ሌላ ወያኔም …ጌታ….ተላላኪ…;;እያለ ቢዘላብድም ታምኝነት ሊያገኝ አልቻለም:: አና ጎሜዝ ይህንን ሲናገሩ ከባለስልጣናት አንደበት የሰሙት እና የተላኩት መልእክት እንዳለ ይጠቁማል:: አና ጎሜዝ ወደ ግንቦት ሰባት ብቻ ሳይሆን ለተለያዩ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን የለውጥ ጠያቂዎችም የብሄራዊ ድርድርን ጉዳይ አስረግጠው አዋይተዋል:;በእርግጥ ስለግንንቦት ሰባት ባያነሱም ይህ የእንደራደር ጥያቄ የመልስ ምቱን ወያኔ ለማወቅ ፈልጎ ያደረገው ሊሆን የሚችል የማጭበርበሪያ የፖለቲካ ስልት ቢሆንም የድርድሩ ጥያቄ ግን የአና ጎሜዝን የአዲስ አበባ ቆይታ እና የአዲስ ነፋስ ምልክታን ተከትሎ መነገሩ እውነታውን ያጎላዋል:; ይህ የሚያሳፍረው ወያኔን ቢሆንም ወያኔ ግን ምንተእፍረቱን አይኑን በጨው አጥቦ ቢክድም አሁንም ግንቦት ሰባትን እንዲያደራድሩት ከትን እንዲያደበጀርባ እየተለማመጠ እንደሚገኝ ለማስገንዘብ እወዳለሁ:: #MinilikSalsawiምንሊክሳልሳዊ

ጋዜጠኞቹ በኤርትራ ከሚደርስባቸው ጫና በመሸሽ በተሰደዱበት ኡጋንዳ በጀመሩት United Hearts በተባለ ድረ ገፃቸው ጠንካራ ዘገባዎች በማቅረባቸውና ቡና ልዩ ልዩ ሃሳቦችንም በነፃነት በማስተናገዳቸው ለሽልማት በቅተዋል ።

ወታደሮቻቸውን አፍጋኒስታን ያዘመቱት የሰሜን አትላንቲክ የጋራ መከላከያ ቃል ኪዳን ድርጅት በምህፃሩ NATO አባል ሃገራት ካርዛይ ውሉን በአስቸኳይ ካልፈረሙ ሃገሪቱ የሚሰጣት የእርዳታ ገንዘብ ይቋረጣል ሲሉ እየዛቱ ነው ። የሃገሪቱ የፀጥታ ጥበቃም አደጋ ላይ እንደሚወድቅ ማስጠንቀቃቸውን ቀጥለዋል ።

በያዝነዉ ሳምንት ህዳር 24፤ የዓለም የአካል ጉዳተኞች ቀን ለ22 ኛ ግዜ ታስቦ ዉሎአል። የተመድ ያወጣዉ ዘገባ እንደሚያመላክተዉ በዓለም ከሚኖሩ ህዝቦች መካከል 15 ከመቶዉ ቀላል እና ከባድ የአካል ጉዳተኞች ናቸዉ። በኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ላይ የሚደርስዉ ተፅኖ እና በተለያዩ ዘርፎች ያላቸዉ እንቅስቃሴ ምን ይመስላል?

ባኩ-አዘርባጃን ዉስጥ በመካሄድ ላይ ባለው 8 ተኛው የዓለም ህልናዊ ባህላዊ ቅርሶች ጉባኤ ላይ የተለያዩ ሃገራት 30 ህሊናዊ ቅርሶች እንዲመዘገቡላቸው አቅርበው ነበር ። የመስቀል በዓል አከባባር በባለሞያዎች ተገምግሞ በዚህ ጉባኤ ተቀባይነት ካገኙት ህሊናዊ ቅርሶች አንዱ ነው ።

እነ ሌኒን በሚሉት መልኩ ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› የሚባለው አገራችን ውስጥ የለም፡፡ የስታሊን ጠባብ ብሄርተኝነት፣ የምዕባራዊያኑ ‹‹ካፒታሊዝምና ዴሞክራሲ›› በስም ደረጃ፣ የአልባኒያና የቻይና አምባገነንነት፣ የሻዕቢያና አረብ አገራት ጥላቻ፣ የሞሶሎኒ ፋሽዝም……ተደባልቀው የተሰራ ውጥንቅጡ የጠፋበት ‹‹ርዕዮት ዓለም›› ነው፡፡ የአሁኑ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ከሁሉም ጎን የወሰደው መጥፎ ጎናቸውን እንጅ መልካሙን አይደለም፡፡ እነዚህ የየዘመኑን ትውልድ ያሰከሩ አስተሳሰቦችን መጠናቸውን ሳያውቅ የደባለቀው አብዮታዊ ዴሞክራሲ ከአልኮንነትም አልፎ መርዝ ወደመሆን ደርሷል፡፡ አልኮል ብቻውን ከሚወሰደው በላይ ሲደባለቅ ያሰክራል፡፡ ያሳብዳልም፡፡

ፋሽስቶች ለኢትዮጵያውያንና ለሌሎች ካልሆነ በስተቀር ለአገራቸው ህዝብ ክብር ነበራቸው፡፡ እነ ሌኒንም ቢሆን ለአገራቸው አንድነት እንጅ ተገንጣይነት አልሰሩም፡፡ አረቦቹ ለአገራቸው ጥቅም ሲሉ ነው ኢትዮጵያን ይጠሉ የነበሩት፡፡ የአስተሳሰባቸው መርዝነት ለእኛ እንጅ ለራሳቸው ህዝብ አልነበረም፡፡ ምንም ያህል ቢያብዱና ቢሰክሩ ለአገራቸው ህዝብ ክብር ነበራቸው፡፡ ለብሄራዊ ጥቅማቸው ይጨነቁ ነበር፡፡

ድብልቅልቁ የወጣው ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ግን ኢህአዴግን ጨርቁን አስጥሎታል፡፡ ለዛም ነው ይህን ያህል ያበዱት የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› የአልኮል መጠን ስንት ቢሆን ነው?›› ብየ የጠየቁት፡፡ ከወራት በፊት ለግራዚያ ሲቆም አብዮታዊ ዴሞክራሲ ምን ያህል እንደሚያሰክር፣ እንደሚያሰብድ አሰይቶናል፡፡ ይህ ከእነ ሞሶሎኒ የተወሰደው የአልኮል ክፍል መሆኑ ነው፡፡ ከሳምንታት በፊት ኢትዮጵያውያንን በአረብ ዱላ ገረፈ፡፡ ይህኛው ከአረቦቹ ጥላቻ የተዘነቀው የአብዮታዊ ዴሞክራሲ አልኮል ነው፡፡ አሁን ደግሞ የአጤ ምኒልክን ሙት አመት አታከብሩም ብሎ ከልክሏል፡፡ ይህኛው የሁሉም ውጤት ነው፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ መጨረሻ ቀላቅሎ ያለ አቅሙ አይኑን ጨፍኖ የተጎነጨው ይህኛውን አልኮል ነው፡፡ ጸረ ኢትዮጵያውይነት! የአሁኑ ጣሊያኖች የምኒልክ ታሪክ እንዳይወደስ የሚፈልጉበት ምንም አይነት ምክንያት የለም፡፡

በግራዚያኒ ላይ የጣሊያን ግራ ዘመም ፓርቲዎች በነጻነት ተቃውሞ አሰምተው በሰላም ገብተዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን ግንወገኖቻቸው በተጨፈጨፉበት ጎዳና እንደገና ተደብድበዋል፡፡ ታስረዋል፡፡ ይህ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ የተለከፈ መንግስት ከያኔው ጨፍጫፊዎችም በላይ ይሆንብኛል፡፡ ስካር ሱስ ነው፡፡ በሽታም ጭምር፡፡ እንዲህ የጠደባለቀ መርዛማ አልኮል መጎንጨትን ልማዱ ያደረገ ድሮ ሰክሮ የሚሰራውን ጉዳይ ምሎና ተዘክሮ እተዋለሁ ቢልም የሚሰራው ግን ያው የስካሩን፣ የእብደት ተግባሩን ነው፡፡ ለግራዚያኒ የቆመው ኢህአዴግ ከውስጥም ከውጭም ተቃውሞ ሲገጥመው ስህተቱ ስካሩ መሆኑን ሳይረዳው ቀርቶ አይደልም፡፡ ግን ለሳውዲዎች ቆሞ ደገመው፡፡

አሁን ደገሞ ለድሮዎቹ፣ አድዋ ላይ ለተሸነፊት ጣሊያኖች ቆሞ ከለከለ፡፡ ኢህአዴግ ከአረቦቹ፣ ከፋሽስቶቹ፣ ከእነ ስታሊን….የደባለቀውን የውስጡን ጥላቻ በአብዮታዊ ዴሞክራሲው አልኮል አወጣው፡፡ ይህን ታዲያ ከስካርና ከእብደት ውጭ ምን ይሉታል? እኔ ይህን ናላ አስቶ፣ ጨርቅ አስጥሎ በአገር ህዝብ ላይ የሚያዘምት፣ ህዝብ ላይ የሚያስጨክን፣ ብሄራዊ ጥቅምን የሚያስጠላ ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› የአልኮል መጠኑን መገመት አልቻልኩም፡፡ ከመጠን በላይ መሆኑን፣ መርዛማነቱ ማመዘኑን ከመገመት ውጭ! ግን ኢህአዴግ እስከመቼ እንዲህ ጨርቁን ጥሎ ይዘልብናል?

(ሪፖርተር፤ ኅዳር ፳፮ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.) ኄኖክ ያሬድ የኢትዮጵያው የመስቀል ክብረ በዓል በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ዩኔስኮ አስታወቀ፡፡ ዩኔስኮ የመስቀል ክብረ በዓልን (Commemoration feast of the finding of the True Holy Cross of Christ) በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ኅዳር 25 ቀን ይፋ ያደረገው፣ በኢንታንጀብል (መንፈሳዊ) ባህላዊ ቅርሶች ጥበቃና ክብካቤ ላይ የሚሠራው ኮሚቴው ስምንተኛውን ጉባኤ እያካሄደባት ካለው የአዘርባጃኗ …