የመስቀል በዓል በዓለም ቅርስነት መመዝገቡ

ባኩ-አዘርባጃን ዉስጥ በመካሄድ ላይ ባለው 8 ተኛው የዓለም ህልናዊ ባህላዊ ቅርሶች ጉባኤ ላይ የተለያዩ ሃገራት 30 ህሊናዊ ቅርሶች እንዲመዘገቡላቸው አቅርበው ነበር ። የመስቀል በዓል አከባባር በባለሞያዎች ተገምግሞ በዚህ ጉባኤ ተቀባይነት ካገኙት ህሊናዊ ቅርሶች አንዱ ነው ።