ኢትዮጵያዊው ስደተኛ ከሐገሩ እንደወጣ ምድር ወገብ ላይ ቀረ።
ኢትዮጵያዊው ስደተኛ ሣሙዔል መኮንን <አቡሽ> ዛሬ በዘጠኝ ሠዓት በካንፓላ መካነ ሠላም መድሐንያለም ቤተክክርስትያን በድንግል መሬት ተቀበረ።ወጣት ሣሙዔል መኮንን <አቡሽ>ከሐገሩ ተሠዶ ከወጣ አምስት ዓመታት የተቆጠረ ሲሆን ወደሌላ ሐገር ለመሻገር ሣይችል የምድር ጉዞውን በምድር ወገቧ ዩጋንዳ ጨርሷል።ከሃምሣ ያላነሡ ሥደተኞች በቀብሩ ላይ መገኘታቸውን የፔን ዘ ኢትዮጵያ ዘጋቢ የታዘበ ሲሆን ወጣቱ በጉበት ህመም ባለፈው ማክሠኞ ጧት በተኛበት ሞቶ መገኘቱን ሀኪሞች ጠቁመዎል።