ማዲባ የድቡብ አፍሪቃውያን አባት DW Amharic December 6, 2013 Tagged with Amharic, amharic news, Ethiopia, ethiopian news in amharic, Ethiopians, News in Amharic እንደ ወጣት በእልሕ፥ እንደ ወታደር በነፍጥ፥ እንደ ሕግ አዋቂ በፍርድ ቤት ታገሉ።እንደ ወንጀለኛ ታሠሩ።እንደ ዲፕሎማት ተደራደሩ፥ እንደ ፖለቲከኛ የሕዝብ እኩልንነትን አስርፀዉ ሐገር መሩ።እና እንደ ሰዉ የምድር ሩጫቸዉን ትናንት ጨረሹ።ዘጠና አምስት አመታቸዉ ነበር።