ኀዳር ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከዚህ ቀደም ሶማሊያ ውስጥ ዘምተው የነበሩና መከላከያን የአገልግሎት ዘመናቸውን በመጨረስ ወይም በጉዳት የለቀቁ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ መከላከያ ተመልሰው እንዲዘምቱ በደብዳቤ ጥሪ ቀርቦላቸዋል። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ጥሪው የደረሳቸው ወታደሮች ጥሪውን ለመቀበል ፈቃደኞች አልሆኑም። ጥሪ የተደረገላቸው የሰራዊት አባላት “የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለሰላም አስከባሪ ሃይል በሚል ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ …

Image
አምባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት ሰላማዊ ታጋዮችና በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ማሳደዱን አሁንም ቀጥሎበታል። የዘጠኙ ፓርቲዎች ትብብር ለህዳር 27 ጠርተውት በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በመንግስት ኃይሎች የተወሰደውን እጅግ አረመኔያዊ የሆነ ህገ ወጥ እርምጃ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ (አንድነት) ፓርቲ በጥብቅ ያወግዛል።

እነዚህ ፓርቲዎች የሀገሪቱ ህገ መንግስት፣ የስብሰባና ሰልፍ አዋጁ በሚፈቅደውመሰረት ለአዲስ አበባ መስተዳድር ሰልፍ እንደሚያደርጉ ቀኑንና ቦታውን ጠቅሰውአሳውቀዋል፤ በአዋጁ መሰረት ደግሞ ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ እንጂ ፍቃድ መጠየቅ ግድ የሚል አይደለም። ነገር ግን ህገ ወጥ በሆነ ሁኔታ ህጉ በሚፈቅደው መሰረት ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ከሰማያዊ ፓርቲ ፅህፈት ቤት እየወጡ የነበሩትን ሰልፈኞች በመንግስት ኃይሎች ከፍተኛ የሆነ ድብደባ
እንዲፈፀምባቸው ተደርጓል።

ከዚህም ባሻገር የትብብሩ ፓርቲዎች አመራሮችና አባላት አፍሶ በመውሰድ በጨለማ ክፍል ውስጥ አስሯቸው ይገኛል። ወዳጅና ዘመድ እንዳይጠይቃቸው መደረጉም የአንድነት ከፍተኛ አመራሮች ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በትናንትናው ዕለት በአካል ተገኝተው አረጋግጠዋል።
የአዲስ አበባ አስተዳደር ይሄ ጉዳይ በአግባቡና ህጉ በሚፈቅደው መንገድ መፍታት ሲችል፤
በሚዲያ እርምጃ እወስዳለሁ ብሎ ማወጁና በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ግፍ
እዲፈፀም በማድረጉ ሀላፊነቱን መውሰድ አለበት። በተለይ ኢህአዴግ የ2007
ምርጫ እየቀረበ ባለበት ሁኔታ እንዲህ ዓይነቱ አፈናና ህገወጥ እርምጃ መውሰዱ
ምርጫውን ችግር ውስጥ የሚከት ጉዳይ መሆኑ ሊገነዘብ ይገባል። አንድነት
ፓርቲ ይሄ ጉዳይ በዝምታ የሚያየው ነገር አይሆንም፤ በቅርቡም አስፈላጊውን
መረጃዎች ሁሉ አሰባስቦ ጋዜጣዊ ይሰጥበታል።
የዘጠኙ ፓርቲዎች አመራሮችና አባላት በህገ መንግስቱ ላይ የተቀመጠውን
ሰላማዊ ሰልፍ የማድርግ መብት ከመጠቀም ውጪ ያጠፉት ምንም ዓይነት ነገር
ስለሌለ በአስቸኳይ ሊፈቱ ይገባል። ገዥው መንግስት ከህግና ከስርዓት ውጪ
በሰላማዊያን ዜጎች፣ በፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ላይ እየወሰደ ያለውን
አፈና፣ ድብደባና እስር እንዲያቆም፤ የህግ የበላይነትን፣ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ
መብቶችን እንዲያከብር አለም አቀፉ ማህበረሰብ ተገቢውን ጫና እንዲያሳድሩ
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ (አንድነት) ፓርቲ ጥሪውን ያቀርባል። በተለይ
ደግሞ የጉዳዩ ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ይህ ህገወጥና አረመኔያዊ
ድርጊት በዝምታ ሊያልፈው አይገባም፤ ኢህአዴግ በቃህ ሊለው ይግባል።
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ (አንድነት) ፓርቲ
ህዳር 29 /03 /2007
አዲስ አበባ

የፕሮግራም መግለጫ

ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡

የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡

ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡

የዘጠና አመቱ የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ የዛኑ ፒ.ኤፍ. መሪ ሆነው በድጋሚ ተመርጠዋል። የፕሬዝዳንቱ ባለቤት ግሬስ ሙጋቤም በፓርቲው የሴቶች ክንፍ መሪ በመሆን ወደ ፖለቲካው መቀላቀላቸው ይፋ ሆኗል።

አሳካሪ-እና ግልፅ ያልሆነ ፖለቲካ።ለአዲስ አበባ በርግጥ እንግዳ አይደለም።ጥንት እንደ ቅዳሜዉ ነበረች።የዛሬ አርባ አመት የጥንት ሥርዓቷ መለወጡ በታወጀ፤ ያለምንም ደም የኢትዮጵያ እንከን እንዲወድም በተዘመረባት ማግስትም በደም ኩሬ ተነከረች።በ1983 ያቺ ጉደኛ ከተማ የሠላም፤ ዲሞክራሲን ጉዞ መጀመሯ ተነግሮባት ሳያበቃ በሌላ ደም ጨቀየች።

በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ቸልሲ ቅዳሜ ዕለት የመጀመሪያውን ሽንፈት ቀምሷል። በጆሴ ሞሪንሆ የሚመራው ቸልሲን ጉድ ያደረገው በ7ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ኒውካስል ዩናይትድ ነው። በጀርመን ቡንደስ ሊጋ ባየር ሙይንሽን እየመራ ነው፤ ዶርትሙንድ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ተደጋጋሚ ሽንፈት ለምን?

የዩኤስ አሜሪካ ፖሊስ ያልታጠቀ ጥቁሮች ላይ ያደረሰዉን ግድያ ተከትሎ በዩኤስ አሜሪካ የተለያዩ ከተሞች የጀመረዉ ተቃዉሞ በሳምንቱ መጨረሻ በበርካታ ከተሞች እጅግ ጎልቶ መታየቱ ተነግሮአል።



ፀሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
——
  ይህ ዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይ ነው፡፡ ኢህአፓዎች ከማንም በላይ የሚያከብሩትና የሚያደንቁት አርበኛና የለውጥ ብስራት ነጋሪ ፋኖ! የጽናትና የቆራጥነት ተምሳሌት ሆኖ በየዓመቱ የሚዘከር የዚያ ትውልድ ታላቅ ሰው!

       በእርግጥም ተስፋዬ ደበሳይ ቆራጥ ነበር፡፡ ላመነበት ዓላማ ሺዎችን አንቀሳቅሷል፡፡ ለጠላቶቹ ሳይንበረከክ ህይወቱን ሰውቷል፡፡ በርሱ ሞት ያዘኑት ኢህአፓዎች “ተስፋዬን ከምናጣ ሌሎች የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላቶቻችን በሙሉ ቢጠፉ ይሻለን ነበር” በማለት መሪር ሐዘናቸውን አሰምተዋል፡፡ የደርግ መንግሥት እርሱ በሞተበት ዕለት ባወጣው መግለጫ አንድ ክፍለ ጦር ሰራዊት የተደመሰሰ ያህል ነበር የፎከረው፡፡
    ተስፋዬ ደበሳይ ማን ነው? በኢህአፓ ውስጥ የነበረው ሚና ምን ይመስል ነበር?… ህይወቱ የተፈጸመው እንዴት ነው? እስቲ በጥቂቱ እንየው፡፡
                                                                          *****
    ኢሮብ በትግራይ ክፍለ ሀገር፣ አጋሜ አውራጃ ውስጥ የምትገኝ ወረዳ ናት (በአሁኑ የአስተዳደር አወቃቀር በትግራይ ክልል፣ ምስራቃዊ ዞን ውስጥ ነው የምትገኘው)፡፡ በዚህች ወረዳ ከትግርኛ ተናጋሪው ብሄረ-ትግራይ በተጨማሪ ኢሮብ የሚባለው አነስተኛ ብሄረሰብ ይኖራል፡፡ ይህ ህዝብ በውስጡ ሶስት ዐይነት ማህበረሰቦች አሉት፡፡ አንደኛው ደመክኒቶ ይባላል፡፡ የዚህ ማህበረሰብ አባላት የካቶሊክ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ ሁለተኛው ማህበረሰብ “ሀሳበላ” የሚባል ሲሆን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ይበዙበታል፡፡ ሶስተኛው ማህበረሰብ “ዳልገዳ” ይባላል፡፡ እነዚህኛዎቹ ደግሞ ሙስሊሞች ናቸው፡፡ እነዚህ ማህበረሰቦች የሚናገሩት ቋንቋ በኤርትራ ምድር ከሚነገረው የሳሆ ቋንቋ ጋር ተመሳሳይነት አለው፡፡ ሆኖም ኢሮብ እና ሳሆ በኢኮኖሚ ስምሪታቸው ይለያያሉ፡፡ የሳሆ ህዝብ ሙሉ በሙሉ አርብቶ አደር ነው፡፡ ኢሮቦች ግን በእርሻ ስራና በአነስተኛ ዕደ-ጥበባት ነው የሚተዳደሩት፡፡ የኢሮብ ወረዳ ተራራና ሸንተረር ይበዛዋል፡፡ በአካባቢው ካሉት ተራሮች መካከል “አሲምባ” እና “አይጋ” ትልልቆቹ ናቸው፡፡ 
    
   በዚህች የኢሮብ ወረዳ ውስጥ አሊቴና የምትባል አነስተኛ መንደር አለች፡፡ ይህች መንደር የአጋሜ አውራጃ ርዕሰ ከተማ ከሆነችው አዲግራት 35 ኪሎ ሜትር ያህል ትርቃለች፡፡ የመንደሪቷ ነዋሪዎች በአብዛኛው ካቶሊክ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ ተሰፋዬ ደበሳይ በዚያች አነስተኛ መንደር ውስጥ ነው በ1933 የተወለደው፡፡ ወላጅ አባቱ አቶ ደበሳይ ካህሳይ ይባላሉ፡፡ እናቱ ደግሞ ወ/ሮ ምህረታ ዓዶ-ዑማር ነበሩ፡፡ ተስፋዬ የቤተሰቡ የበኩር እና ብቸኛ ወንድ ልጅ ነው፡፡ ከርሱ በኋላ የተወለዱት ስድስት ልጆች በሙሉ ሴቶች ናቸው (ለዚህ ጽሑፍ የመረጃ ምንጭ ከሆነው የመጋቢት ወር/2005 የኢህአፓ ዘገባ ለመረዳት እንደተቻለው ከስድስት እህቶቹ መካከል አምስቱ በህይወት ይገኛሉ፤ ወላጅ አባቱም በህይወት አሉ)፡፡
  
     አሊቴና በዚያ ዘመን ትምህርት ቤት አልነበራትም፡፡ ስለዚህ ህጻኑ ተስፋዬ የትምህርት ጉጉት ቢኖረውም እድሜው አስር ዓመት እስኪሆነው ድረስ ትምህርት ቤት ለመግባት አልታደለም፡፡ በ1943 ግን አዲግራት ከሚኖሩት አክስቱ ዘንድ ሄደና ትምህርት ቤት እንዲያስገቡት ለመናቸው፡፡ አክስቱም በከተማዋ ከሚገኝ ታዋቂ የካቶሊክ ሚሽን ትምህርት ቤት አስገቡት፡፡ ተስፋዬም እስከ ስምንተኛ ክፍል በዚሁ ት/ቤት ከተማረ በኋላ ዘጠኛ ክፍልን መቀሌ በሚገኘው አጼ ዮሐንስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አጠናቀቀ፡፡ ይሁንና በወቅቱ የትምህርት ወጪውን በራሱ ሸፍኖ መማር እንደማይችል በመረዳቱ ፊት ወደ ነበረበት የካቶሊክ ት/ቤት ተመለሰ፡፡ እዚያም እስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል ከተማረ በኋላ ለከፍተኛ ትምህርት ወደ ጣሊያን ሀገር ተላከ፡፡ በሀገረ ኢጣሊያ ሮም ከተማ ካለው Urbaniana University በፍልስፍና ትምህርት የዶክትሬት ዲግሪውን ተቀበለ፡፡
    ተስፋዬ በስራው ዓለም ሲሰማራ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰራበት መስሪያ ቤት የማስታወቂያና መርሐ ብሄር ሚኒስቴር ነበር፡፡ በዚህ መስሪያ ቤት የምርምር ክፍል ሃላፊ ሆኖ እየሰራ በማታው ክፍል የአባዲና ፖሊስ ኮሌጅ አስተማሪ ለመሆን በቅቷል፡፡ በ1964 ለተጨማሪ ስልጠና ወደ አውሮጳ (ስዊዘርላንድ) ተልኳል፡፡ በዚያ እያለም በመቀጣጠል ላይ የነበረው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ልቡን ስለወሰደው ትምህርቱን ትቶ ሙሉ በሙሉ ወደዚያው ገብቷል፡፡
   
     ታዲያ እርሱ ወደ ስዊዘርላንድ በሄደበት ወቅት በአውሮጳው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማህበር እና በአሜሪካው የተማሪዎች ማህበር መካከል ከፍተኛ ውዝግብ ይካሄድ ነበር፡፡ ሁለቱ ማህበሮች የተወዛገቡት የድርጅት ምስረታና አደረጃጀት፣ የኤርትራ ጥያቄ፣ የብሄረሰቦች መብት፣ የትጥቅ ትግል አስፈላጊነት በመሳሰሉ አርዕስተ ነገሮች ዙሪያ ነበር፡፡ በጊዜው የድርጅት አስኳል ለመመስረት ጥረት ያደርግ የነበረው የአልጄሪያው የስደተኛ ተማሪዎች ቡድን ከአሜሪካው ማህበር ጋር ተቀራራቢ አቋም አሳየ፡፡ የአውሮጳው ማህበር መሪዎች በሀገር ቤት ከነበሩ ጥቂት ተማሪዎች ጋር አንድ ዓይነት አቋም ላይ ደረሱ፡፡ ተስፋዬ ደበሳይ ግን የአውሮጳው ማህበር መሪዎችን ውሳኔ በመቃወም ከአልጄሪያው ቡድን ጋር ወገነ፡፡ በዚህም መሰረት የአልጄሪያው ቡድን፣ የአሜሪካው ቡድንና አውሮጳ የነበሩት ጥቂት ተማሪዎች በድርጅት ምስረታ ሂደት ላይ መነጋገር ጀመሩ፡፡ ውይይቱ ለወራት ሲብላላ ከቆየ በኋላ በዓለም ዙሪያ ተበታትነው የነበሩ ሌሎች ኢትዮጵያዊ ተማሪዎችንም ማካለል ጀመረ፡፡ በስተመጨረሻም በሚያዚያ ወር 1964 “የኢትዮጵያ ህዝቦች አርነት ድርጅት” (ኢህአድ) ተወለደ፡፡ ተስፋዬ ደበሳይም ለድርጅቱ አመራር ከተመረጡ ሰባት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት አንዱ ሆነ፡፡
                                                                          *****
       ኢህአድ የተወለደው በውጪ ሀገር ነው፡፡ ከ1964-1966 በነበሩት ዓመታት ዋነኛ ስራው ድርጅቱን ማስተዋወቅና አባላትን ማሰባሰብ ነበር፡፡ ከፍልስጥኤም ነጻ አውጪ ድርጅትና ከኤርትራ ግንባሮች የተሰጠውን ድጋፍ በመጠቀም የትጥቅ ትግል የመጀመር እንቅስቃሴ ሲያደርግም ቆይቷል፡፡ የድርጅቱ ቀዳሚ ዓላማ ከገጠር በሚጀመር የትጥቅ ትግል በረጅም ጊዜ የስርዓት ለውጥ ማምጣት ነበር፡፡ የኢህአድ መሪዎችም ድርጅቱ ቀዳሚ ሰራዊቱን ሊያሰማራበት ወዳሰበው የአሲምባ ተራራ በመሄድ ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራር እንዲሰጡ ለማድረግ ታስቧል፡፡ ይሁንና በ1966 የፈነዳው የኢትዮጵያ አብዮት የትግሉን አቅጣጫ ሙሉ በሙሉ ቀየረው፡፡ የአሮጌው ስርዓት መውደቅ አይቀሬ እንደሆነ ሁሉም በየፊናው አወቀ፡፡ “በርሱ ቦታ ተተክቶ ሀገሪቱን የሚመራው ማን ነው?” የሚለው ጥያቄ ግን አነጋጋሪ ሆነ፡፡ በዚህም በተራማጅ አብዮተኞች መካከል ከፍተኛ ውይይት ተቀሰቀሰ፡፡ በመደምደሚያውም የፓርቲ ቅርጽ የነበራቸው ቡድኖች በከተሞች አካባቢ የፖለቲካ ትግል ቢያደርጉ ጠቀሜታው ከፍ ያለ እንደሚሆን ከስምምነት ላይ ተደረሰ፡፡ በመሆኑም በውጪ ሀገር የነበረው የኢህአድ አመራር ወደ ሀገሪቷ ለመግባት ወሰነ፡፡
   
     ከኢህአድ ከፍተኛ መሪዎች መካከል በቅድሚያ ወደ አዲስ አበባ የገባው ዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይ ነው፡፡ ጊዜውም ሰኔ 1966 ነበር፡፡ በወቅቱ የወታደሮች ቡድን የሆነው ደርግ ተመስርቶ የአጼውን መንግሥት ለመጣል እያኮበኮበ ነበር፡፡ በሀምሌ ወር አጋማሽ ላይ ደርግ የልጅ እንዳልካቸውን ካቢኔ በመሻር ልጅ ሚካኤል እምሩ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ መረጣቸው፡፡ ልጅ ሚካኤልም ካቢኔአቸውን ሲያቋቁሙ በስዊዘርላንድ የሚያውቁትን ዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይን የመሬት ይዞታ ሚኒስትር እንዲሆን ጠየቁት፡፡ እርሱ ግን ከውጪ የመጣው ለዚያ አልነበረምና አንዳች ምክንያት ፈጥሮ አሉታዊ መልስ ሰጣቸው፡፡ በምትኩ በመስሪያ ቤቱ በኤክስፐርትነት ቢቀጠር ለመስራት ፈቃደኛ እንደሆነ ገለጸላቸው፡፡ በዚህም መሰረት ከነሐሴ 1966 ጀምሮ የመስሪያ ቤቱ ሰራተኛ ሆነ፡፡
 
   ተስፋዬ ወደ ሀገር ቤት ከተመለሰ በኋላ ድርጅቱን በማስፋፋትና አባላትን በማደራጀት ስራ ላይ ነበር የተጠመደው፡፡ የድርጅቱ ልሳን የሆነችውን “ዲሞክራሲያ” ጋዜጣን ከሚያወጡ አርታኢያን መካከልም አንዱ ነበር፡፡ በድርጅቱ የመጀመሪያ ጉባኤ ዋና ጸሐፊ ሆኖ የተመረጠው ብርሃነ መስቀል ረዳ ከሰራዊቱ ጋር ስለነበር በርሱ ቦታ በጊዜያዊነት አመራር የሚሰጠውም ተስፋዬ ደበሳይ ነበር፡፡  በወቅቱ በድርጅቱ አመራር ላይ ከነበሩትም መካከል በዕድሜም ሆነ በትምህርት ደረጃ የሚበልጠው እርሱ ነበር፡፡
   
   ተስፋዬ እስከ ታህሳስ 1967 በአዲስ አበባ ከተማ ከቆየ በኋላ ከመሬት ይዞታ ጋር ለተያያዘ የመስክ ስራ ወደ ትግራይ ተጓዘ፡፡ እግረ መንገዱንም አሲምባ የሚገኘውን የድርጅቱን ጀማሪ ሰራዊት ለመጎብኘት ወደዚያው ጎራ አለ፡፡ በጊዜው የነበረውን የሀገሪቱን የፖለቲካ ሁኔታ ለሰራዊቱ ካብራራ በኋላ ግን ያልተጠበቀ ችግር ተከሰተ፡፡ ስምንት ያህል የሰራዊቱ አባላት ከጀማሪ ሰራዊቱ በመነጠል ለደርግ እጃቸውን ሰጡ (እጃቸውን የሰጡት ሰዎች ተስፋዬ መኮንን፣ ኃይለ እየሱስ ወልደ ሰንበት፣ አበበ በየነ፣ ዘከሪያ መሐመድ፣ አያሌው ከበደ፣ ጋሻው መንግሥቱ፣ ሀይሌ ወልደ ጊዮርጊስና ዳዊት አሰፋ ነበሩ፤ እነዚህ ሰዎች በ1968 መጀመሪያ ላይ “ማሌሪድ”፣ ማለትም “የማርክሲስት ሌኒኒስት ሪቮሉሽናሪ ድርጅት”ን መስርተዋል)፡፡ ታዲያ የነዚህ ሰዎች ከኢህአፓ አፈንግጦ መውጣት የዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይን ማንነት አጋለጠው፡፡ በመሆኑም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ህቡዕ ለመግባት ተገደደ፡፡
                                                                          *****
   ዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይ ህቡዕ ከገባ በኋላ የሙሉ ጊዜ አብዮታዊ ሆኗል፡፡ ኢህአድን በሙሉ አቅሙ አገልግሏል፡፡ በነሃሴ ወር 1967 ድርጅቱ ስሙን ቀይሮ “ኢህአፓ” (የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ) የተሰኘውን ዝነኛ መጠሪያውን የያዘበትን ጉባኤ በዋናነት ያዘጋጀውም እርሱ ነው፡፡ የድርጅቱ የፍልስፍና ሊቅ (ideologue) ሆኖ የሚያገለግለውም እርሱ ነበር፡፡ በኢህአፓ መስራች ጉባኤ “ዋና ጸሐፊ” የሚባል የስልጣን ተዋረድ ሲሻር በቀዳሚነት የማዕከላዊ ኮሚቴ ጸሐፊ ሆኖ ማገልገል የጀመረው እርሱ ነበር (ይህ የጸሐፊነት ቦታ በየጊዜው ይለዋወጥ ነበር፤ ጸሐፊው የሚመረጠውም በፓርቲው ጉባኤ ሳይሆን በፖሊት ቢሮው ነው)፡፡
   እስከ 1968 አጋማሽ ድረስ በነበረው ጊዜ የኢህአፓ አመራሮች ማንነት በግልጽ አይታወቅም፡፡ በዚያን ጊዜ ህቡዕ ለመግባት የተገደዱት ብርሃነ መስቀል ረዳ እና ተስፋዬ ደበሳይ ብቻ ናቸው፡፡ በመሆኑም አብዛኛው የፓርቲው ስራ የሚከወነው በተስፋዬ ነበር (ብርሃነ መስቀል ለፖሊት ቢሮው ስላልተመረጠ ከፍተኛ ሃላፊነት አልተሰጠውም፤ በተጨማሪም ከሌሎች መሪዎች ጋር መነታረክ ጀምሮ ነበር) ፡፡
   
    የህዝብ ድርጅት ጉዳይ ጊዜያዊ ጽ/ቤት ከተመሰረተ በኋላ ግን አመራሩን ለአደጋ የሚያጋልጥ ሁኔታ ተከሰተ፡፡ በጽ/ቤቱ የተመረጡት ከፍተኛ ካድሬዎች የኢህአፓ መሪዎችን ስለሚያውቋቸው ለደርግ አሳልፈው ይሰጡአቸዋል የሚል ስጋት ሰፈነ፡፡ በመሆኑም በ1968 መጨረሻ ገደማ ሁሉም መሪዎች ህቡዕ ለመግባት ተገደዱ፡፡ ታዲያ የኢህአፓ የትግል ስትራቴጂም መለወጥ የጀመረው ከዚህ ወቅት ጀምሮ ነው፡፡ ከ1968 ክረምት ወራት በፊት በከተሞች አካባቢ የፖለቲካ ትግል ብቻ ያደርግ የነበረው ኢህአፓ የደርግ ፋሺስትነትን ለመከላከል በሚል የከተማ ትጥቅ ትግል የጀመረው ያኔ ነው፡፡
      አንዳንድ ወገኖች የትጥቅ ትግሉ በዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይ ግፊት የመጣ ነው ይላሉ፡፡ ከሊቀመንበር መንግሥቱ ኃይለማሪያም ጀምሮ መገደል ያለባቸውን ከፍተኛ የደርግና የመኢሶን ባለስልጣናት ዝርዝር እያዘጋጀ የሞት ፍርድ ያስወስን የነበረው ተስፋዬ ደበሳይ ነው በማለት ይሞግታሉ፡፡ ከዚህ እልፍ ሲል ደግሞ የተስፋዬን ትግሬነት በመጥቀስ ብቻ ሻዕቢያ በአዲስ አበባ ከተማ ሽብር ለመቀስቀስ የመደበው የጥፋት ወኪል ነው የሚል መረጃ የሚያስነብቡ ጽሁፎችን ማየት የተለመደ ሆኗል (ለነገሩ ተስፋዬ የኢሮብ ተወላጅ ነው እንጂ ትግሬ አልነበረም)፡፡ ይሁንና እንዲህ ዓይነቱን የተናጥል ክስ በተስፋዬ ላይ የሚያጠናክር ማስረጃ የለም፡፡ ኢህአፓ የከተማ ትጥቅ ትግል እንዲጀምር የወሰኑት ብዙሃኑ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ናቸው እንጂ ተስፋዬ ደበሳይ ብቻ አልነበረም፤ ውሳኔውን የተቃወሙት ጌታቸው ማሩ እና ብርሃነ መስቀል ረዳ ብቻ ነበሩ (በጊዜው የኢህአፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የነበሩት ዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይ፣ ዮሐንስ ብርሃኔ፣ ዮሴፍ አዳነ፣ ክፍሉ ታደሰ፣ ክፍሉ ተፈራ፣ ዘርዑ ክህሸን፣ ኢያሱ አለማየሁ፣ ሳሙኤል አለማየሁ፣ አበራ ዋቅጅራ፣ ፍቅሬ ዘርጋው፣ ጸጋዬ ገብረመድህን፣ ብርሃነ መስቀል ረዳ፣ ጌታቸው ማሩ እና ጸሎተ ህዝቅያስ ነበሩ)፡፡
                                                                          *****
  መስከረም 13 ቀን 1969፡፡ በዚህች ዕለት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማሪያምን ለመግደል ያልተሳካ ሙከራ ተደረገ፡፡ በዚህም የተነሳ ኮሎኔሉ ኢህአፓን ለማጥፋት ቆርጠው ተነሱ፡፡ በስውር የሚያካሄዱትን ርሸና ይፋ ማውጣት ጀመሩ፡፡ በታህሳስ ወር የኮሎኔሉን እርምጃ የሚቃወሙ መኮንኖች በደርግ ውስጥ መዋቅራዊ ለውጥ አካሄዱ፡፡ ይሁን እንጂ ከአንድ ወር በኋላ (ጥር 25/1969) ኮሎኔል መንግስቱ ማንም ባላሰበው መንገድ ጠላቶቻቸውን በማጥፋት “ለምሳሌ ያሰቡንን ቁርስ አደረግናቸው” በማለት አወጁ፡፡ “አብዮቱ ከተከላካይነት ወደ አጥቂነት ተሸጋግሯል” ተባለ፡፡ “ቀይ ሽብር” በይፋ ታወጀ፡፡ “ነጻ እርምጃ” ተፈቀደ፡፡
   
    በወቅቱ የኢህአፓው ዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይ አዲስ አበባ ውስጥ እንደነበረ ደርጎች ያውቁ ነበር፡፡ ነገር ግን አድራሻውን በትክክል ማወቅ አልቻሉም፡፡ ኢህአፓም ከጥር ወር መጨረሻ ጀምሮ እየተባባሰ በመሄድ ላይ የነበረውን የደርግ እርምጃ ለመቀልበስ እንደማይችል አውቆታል፡፡ ይሁንና የከተማውን የትጥቅ አመጽ አላቋረጠም፡፡ ደግሞም ዋና መሪውን ከደርግ አፍንጫ ስር አውጥቶ ከደህና ቦታ ለማድረስ አልሞከረም፡፡
  
   ታዲያ ኢህአፓዎች መሪአቸው ከከተማው ወጥቶ ለደህንነቱ አስተማማኝ በሆነ ቦታ ቢደበቅ ይፈልጉ ነበር፡፡ በተለይ በመጋቢት ወር አጋማሽ (1969) ከሚካሄደው የቤት ለቤት አሰሳ ነፍሱን እንዲታደግ ይመኙ ነበር፡፡ ይሁንና መሪው ከከተማው ለመውጣት ምንም ዓይነት ፍላጎት አልነበረውም፡፡ “በዚህ ክፉ ቀን ተከታዮቼን ጥዬ ከከተማ አልሰደድም” በማለት ቆርጧል፡፡ አሰሳ&#4813

በሰላማዊ ሰልፉ ታፍሰው አዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ (ሶስተኛ) ታስረው የሚገኙት የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር አመራሮች፣ አባላትና የሰልፉ ተሳታፊዎች ‹‹ህገ መንግስቱን በኃይል በመናድ›› ወንጀል ተከሰው 14 ቀን ተቀጠረባቸው፡፡ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት፣ አቶ አርጫፎ ኤርዳሎ፣ አለሳ መንገሻና ሌሎቹም የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር አመራሮች፣ አባላትና በሰልፉ ላይ የታፈሱ ዜጎች አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው ለታህሳስ 13/2007 ዓ.ም ተቀጥሮባቸዋል፡፡ ችሎቱ በዝግ የታየ […]

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር አመራሮች ‹‹ህገ መንግስቱን በኃይል በመናድ›› ወንጀል ተከሰሱ
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎AddisAbebaprotest‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎Blueparty‬ ‪#‎Miniliksalsawi‬
– ‹‹ህገ መንግስቱን ማየት አለብኝ›› ዳኛው
– በርካታ ህዝብ ተገኝቶ የነበር ቢሆንም እንዳይገባ ተከልክሎ ችሎቱ በዝግ ታይቷል፡፡
– የአብዛኛዎቹን ታሳሪዎች ቤት ሊፈትሽ እንደሚችልም ከፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
Minilik Salsawi
በሰላማዊ ሰልፉ ታፍሰው አዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ (ሶስተኛ) ታስረው የሚገኙት የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር አመራሮች፣ አባላትና የሰልፉ ተሳታፊዎች ‹‹ህገ መንግስቱን በኃይል በመናድ›› ወንጀል ተከሰው 14 ቀን ተቀጠረባቸው፡፡ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት፣ አቶ አርጫፎ ኤርዳሎ፣ አለሳ መንገሻና ሌሎቹም የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር አመራሮች፣ አባላትና በሰልፉ ላይ የታፈሱ ዜጎች አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው ለታህሳስ 13/2007 ዓ.ም ተቀጥሮባቸዋል፡፡

ችሎቱ በዝግ የታየ ቢሆንም ሶስተኛ ከሚገኙት ሴት ታሳሪዎች ጠይቀን ማረጋገጥ እንደቻልነው ‹‹ሁከት በመፍጠር ህገ መንግስቱንና ህጋዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ እና መንግስት ያልፈቀደው ሰልፍ በመውጣት›› የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡ ታሳሪዎቹ በበኩላቸው ‹‹እኛ ህጋዊና ሰላማዊ ታጋዮች ነን፡፡ በህጉ መሰረት ሰልፉን እንደምናደርግ አሳውቀናል፡፡ በመሆኑም የዋስ መብታችን ተከብሮ ልንለቀቅ ይገባል›› ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ አቃቤ ህግ ‹‹ምርመራዬን አልጨረስኩም፡፡ የምሰበስበው ተጨማሪ መረጃ አለ፡፡ መረጃዎችን ይደብቁብኛል፡፡ ሌሎች ተባባሪዎችም አሉ፡፡›› ሲል የጊዜ ቀጠሮ እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡ በሌላ በኩል ዳኛው ‹‹ህገ መንግስቱና ሌሎቹም ህጎች ለሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቅ እንጅ ማስፈቀድ አይጠበቅም የሚሉ ከሆነ ህገ መንግስቱንና ሌሎቹንም ህጎች ማየት አለብኝ፡፡›› ብለው 14 ቀጥረውባቸዋል፡፡ አቃቤ ህግ ‹‹የምሰበስበው ተጨማሪ መረጃ አለ፡፡›› ባለው መሰረት የአብዛኛዎቹን ታሳሪዎች ቤት ሊፈትሽ እንደሚችልም ከፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከታሳሪዎቹ መካከል 9ኝ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ ለየብቻቸው ቅዝቃዜ የበዛበትና ጨለማ ቤት ውስጥ እንደታሰሩ የታወቀ ሲሆን በምርመራ ወቅት ከፍተኛ ድብደባ እየተፈጸመባቸው እንደሆነም አቤቱታ አቅርበዋል፡፡ ሆኖም ዳኛው የቀረበውን አቤቱታ ትኩረት ሳይሰጡ እንዳለፉት ታሳሪዎቹ ገልጸውልናል፡፡ ታሳሪዎቹ አራዳ ምድብ ችሎት በቀረቡበት ወቅት ችሎቱ በበርካታ የፌደራል ፖሊስ ታጥሮ ታይቷል፡፡ የፍርድ ሂደቱን ለመከታተል በርካታ ህዝብ ተገኝቶ የነበር ቢሆንም እንዳይገባ ተከልክሎ ችሎቱ በዝግ ታይቷል፡፡

ኢህአዴግ የታገለለት የቡድን መብት በተግባር የታለ!?
ያቀረብነው ‹‹የሃይማኖት ነጻነት ይከበርልን›› ጥያቄ የዜግነትም የቡድንም መብት ቢሆንም ይኸው ሶስት ዓመት ሙሉ ምላሽ ተነፍጎታል!
ሰኞ ህዳር 29/2007

ሃገራችን ኢትዮጵያ ብዙ ብሄር ብሄረሰቦች በጋራ የሚኖሩባት እንደመሆኗ መጠን ህብር የተላበሰ ማህበረሰብን አቅፋለች። በተመሳሳይም ብዝሃ ሃይማኖትን መርህ አርርጋ ሃይማቶችን ከጥንስሱ ጀምሮ ተቀብላ ያስተናገደችም ሃገር ነች። ይሁን እንጂ ብሄር ብሄረሰቦችም ይሁኑ ሃይማኖቶች በሃገሪቱ አስተዳዳሪዎች በእኩል የታዩበት እና እንደዜጋ በተመሳሳይ መልኩ የተዳደሩበት የታሪክ አጋጣሚ አናሳ ነው። ያም ሆኖ ማህበረሰባችን እንደ ህዝብ የሚደርሱበትን የበላይ ተጽዕኖዎች ተቋቁሞ ለዘመናት አብሮ ኖሯል።

የታሪካችን ዳራ የሚያሳየው አብይ መገለጫ ይህን ቢመስልም ቅሉ የነበሩትን የበደል እና ኢ-ፍትሃዊነት ፈተናዎች መቋቋም ሲሳናቸው ለአማራጭ መፍትሄ የተነሱበት አጋጣሚ በርካታ ነው። በሃገራችን በከፍተኛ ህዝብ ቁጥር የሚወከሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ከማህበረ-ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ህይወት በስልት እና በግዳጅ ሲገለሉ ማስተዋል የተለመደ የታሪካችን ገጽታ ነው። ስለዚህም ነው መንግስት ለብሄር ጥያቄም ይሁን የሃይማኖት ነጻነትን ለሚሹ የህብረተሰባችን ክፍሎች ተገቢ ምላሽ መስጠት የሚያሻው። ይህ ባልሆነበት ግን ሁለቱም ቢሆን መብታቸውን ለማስከበር መነሳታቸው አይቀሬ ነው። ይህም በሃገራችን የቅርብ ጊዜ ታሪክ የተስተዋለ እውነታ ነው። ከእነኚህ ተገፊ የህዝብ አካላት መካከል የተወሰኑ ብሄር ብሄረሰቦች እና ሃይማኖታዊ ቡድኖች ቀዳሚዎቹ ሲሆኑ በስርዓተ ጾታ ተጽዕኖ ስር የወደቁ የሃገራችን ሴቶችም ተመሳሳይ መድሎ እና መገለልን አስተናግደዋል።

ይህ ሲባል አንድ የሃገራችን ሴት በሴትነቷ ከሚደርስባት ጫና ባሻገር በምታምንበት ሃይማኖት፣ ብሎም በወከለችው ብሄረሰብ መገለል ምክንያት ድርብርብ ግፍን ልታስተናግድ የምትችልበት እድል ሰፊ ነው። በእርግጥም ከተለመደው የስርዓተ ጾታ ጫና ባለፈ መንግስት በወሰደው የሃይል እርምጃ እና የሒጃብ ማገድ ጸረ-ሴኩላሪዝም ዘመቻ ብዙ ሙስሊም ሴቶች ሰለባ መሆናቸው ቀጥሏል። በአንጻሩም የአንድ እምነት ተከታይ በሃይማኖቱ ሰበብ ከሚደርስበት መገፋት ባለፈ በብሄሩ ምክንያትም ለመገለል የሚዳረግበት አሰራር ለዘመናት ተስተውሏል። በመሆኑም ከብሄራቸው እና ቋንቋቸው ጋር የተዛመደ መድልዎን ሲቃወሙ ከብሄር ጉዳይ ጎን ለጎን የሃይማኖት ነጻነት ጥያቄን አብረው ያነገቡ ቡድኖችን ማግኘት የተለመደ ይሆናል። በብዙዎቹ የሃገራችን ክፍሎች እንደሚስተዋለው የአንድ ብሄር ተወላጆች በአንድም ይሁን በሌላ የታሪክ አጋጣሚ ሙሉ በሙሉ፣ አልያም በአብዛኛው የአንድ ሃይማኖት ተከታይ ሊሆኑ ይችላሉና። የሃገራችን ነባራዊ ገጽታ እንደሚያስረዳው ተገፊ የሆኑ የሃይማኖት እና የብሄር መገለጫዎች በአንድ የህብረተሰብ ክፍል ውስጥ ተነባብረው የመገኘት እድላቸው ሰፊ ነው። ስለሆነም መንግስት የብሄር መብትን ማስከበር የሚችልበት ሁኔታ ሊፈጠር ቢችል እንኳን የሃይማኖት እኩልነትን እስካላረጋገጠ ድረስ እነኚህ የሃገራችን ህዝቦች በበደል አዙሪት ውስጥ ይኖራሉ ማለት ነው። ከዚህ መሰል የበደል ድግግሞሽ ለመላቀቅ ሁለቱንም የቡድን መብቶች ያለምንም መሸራረፍ በህገ-መንግስቱ መርሆች መሰረት ማረጋገጥ ብቸኛ አማራጭ ሆኖ ይታያል።

ይሁን እንጂ የኢህአዴግ መንግስት ‹‹ሴኪውላር (ዓለማዊ) መንግስት በመመስረት አስከብሬዋለሁ›› የሚለውን የሃይማኖት እኩልነት አጀንዳ መልሶ በቀን ብርሃን ሲንደው ተስተውሏል። ‹‹መንግስታዊ ሃላፊነትን ከሃይማኖታዊ ሚና ነጥያለሁ›› ያለው መንግስት በሃይማኖታችን አዛዥ ናዛዥ ከነበሩት ቀደምት ሃይማኖታዊ መንግስታት መሪዎች በምንስ ተለየ? ሌሎች አካላትን ‹‹የአጼውን ስርዓት ናፋቂ›› ሲል የሚያወግዝበትስ አቅም ይኖረዋልን? ለቡድን መብት መከበር የታገለ እና በተግባርም እውን መሆኑን የሚሻ ቢሆን ኖሮ ሙስሊሙን ከሃገራችን ሁለገብ የህይወት ዘርፍ ማግለልን እና ሃይማኖታዊ የቡድን መብቱን በጠራራ ጸሃይ መግፈፍን ጀብዱ አድርጎ ሊቆጥር ባልቻለ ነበር። መንግስት ለቡድን መብት ዘብ በቆመ ኖሮ ባለፉት ሶስት የትግል ዓመታት ላነሳናቸው ህገ መንግስታዊ የእምነት ነጻነት ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ በህጋዊ መንገድ ሊሰጥ በቻለ ነበር። ቀደም ካሉት ዓመታት ጀምሮ የእምነት ተቋሞቻችንን በመቆጣጠር በሃይማኖታችን ላይ የተፈጸመው ደረቅ ጣልቃ ገብነት ከጅምሩ የሃይማኖት እኩልነት ጥያቄን ‹‹ጥያቄ ምልክት ውስጥ›› ባላስገባም ነበር።

ሙስሊሙን የማጥቃቱ ዘመቻ ሙስሊም ሴቶችን እና ወጣት ተማሪዎችን በስመ ሴኩላሪዝም ከትምህርት በማፈናቀል እየተተገበረ ይገኛል። በመሆኑም የኢህአዴግ መንግስት ረጅም ዘመን ትግል ለሃይማኖትም ሆነ ለጾታ እኩልነት ከወሬ ያለፈ ቁርጠኝነት እና ለመርህ ተገዥነት እንዳላሳየ ሙስሊሙ ላነሳቸው የመብት ጥያቄዎች ጆሮ ከመንፈጉ እና ከዚህ ሙስሊም ሴቶችን አነጣጥሮ ከሚያጠቃው መንግስታዊ መድሎ የበለጠ ሁነኛ ማሳያ የለም። በተለይ ደግሞ መንግስት በደነገገው መመሪያ ምክንያት በርካታ እህቶቻችን ጦሳቸውን እያዩበት ያለው ሒጃብ ኢህአዴግ ‹‹እኩልነትን አጎናጸፍኳቸው›› በሚላቸው ብሄሮችም ዘንድ እንደ ባህል መዘውተሩ አንድ እውነታ ነው። እነኚህ ብሄሮች ባህላቸው እና ቋንቋቸው እውቅና ከተቸረው አለባበሳቸውንም በነጻነት ሊተገብሩ የሚችሉበት አጋጣሚ በአመት አንዴ በጭፈራ በሚከበረው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ብቻ ሊሆን አይገባም። የቡድን መብት የሆነው የብሄር እኩልነት እና የሃይማኖት ነጻነት ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ ከሚውልበት ከዚህች የአንድ ቀን የሚዲያ ሽፋን ሊያልፍ ይገባል። በዓመት አንዴ የሚደረግ ጭፈራ የእኩልነት ማሳያ እና መለኪያ ፈጽሞ ሊሆን አለመቻሉን መንግስት ራሱ የሚገነዘበው እውነታ ነው። በብሄር ብሄረሰቦች በዓል ላይ ሂጃብ መልበስ መብት እና ባህል ተደርጎ በትምህርት ተቋማት ግን መታገዱ ማን የት ላይ እንዲኖር እንደተሳበ የሚያረጋግጥ ነው፡፡

በዚህ ረገድ መንግስት በ‹‹ልዩ ድጋፍ›› ወደዩኒቨርስቲ አመጣሁ የሚላቸውን የ‹‹ታዳጊ›› ክልል ተወላጅ ሴቶች በአለባበሳቸው ምክንያት ብቻ መልሶ ከዩኒቨርስቲው በሃይል እያባረረ ነው። እውን ታዲያ የታዳጊ ክልሎችን እና በውስጣቸው የሚኖሩ ብሄሮችን የወደፊት እጣ ፈንታ ሊቀይሩ የሚችሉ የተማሩ የሰው ሃይሎችን እያፈናቀሉ ‹‹በልዩ ድጋፍ የክልሎችን ዓቅም ገነባን፣ ሴቶችን አበቃን›› ለማለት ያስደፍራልን? ይህ የመንግስት መድሏዊ አሰራር የሴቶችን፣ ሙስሊሞችን፣ ብሄር ብሄረሰቦችን (ባህሎችን) እና የታዳጊ ክልሎችን ተዋጽዖ የሚፈታተን ከመሆኑም በላይ በየትኛውም መልኩ የቡድን መብት ለብሄሮችም ይሁን ለጾታዎች፣ እንዲሁም ለሃይማኖቶች እንዳልተረጋገጠ የሚያመላክት አብይ ተጨባጭ ነው። በተለይ ይህ እውነታ በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ ጎልቶ የሚታይ መሆኑ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ‹‹የመንግስት የቡድን መብት ማስከበር ሂደት ሆን ተብሎም ይሁን በቸልታ ለምን እኛን አይመለከትም? ለምንስ መድልዎ ይፈጸምብናል?›› የሚል ጥያቄ እንዲያነሱ ይገፋል።

አዎን! የቡድን መብት አስከብራለሁ የሚለው መንግስት ከቃላት ጨዋታ ባለፈ በተግባር የታገዘ መሬት ላይ የሚወርድ መፍትሄ መሻት ግድ ይለዋል። በመርህም ይሁን በአፈጻጸም ረገድ የብሄር እና የእምነት ነጻነትን እና እኩልነትን ማረጋገጥ ያልቻለ መንግስት ህዝብን የማስተዳደር የሞራል ብቃት ሊኖረው አይችልም። በተለይም ለዘመናት ታገልኩለት ለሚለው እና ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ለሚደሰኩርለት የቡድን መብት ጥያቄ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ መፍትሄ ሰጥቶ ለጉዳዩ መቋጫ ያላደረገ መንግስት እንደምንስ ‹‹ለቡድን መብት ታጋይ እና ጠበቃ ነኝ›› ሊል ይቻለዋል!? ለሃገራችን ግማሽ ህዝብ መሰረታዊ የህልውና ጉዳይ የሆነውን የእምነት መብት ገርስሶ ‹‹ለሃይማኖት እኩልነት ሰራሁ›› ቢል ማንስ ይሰማዋል!? ‹‹ንግግርህን እንዳልሰማ ተግባርህ ይጮህብኛል›› እንዲል ብሂሉ ከንግግር በላይ ጮሆ የሚናገረው እና ሰሚ ጆሮ የሚያገኘው ተግባሩ አይደለምን!!? የቡድንም ይሁን የተናጠል መብቶች በቃላት ሽንገላ፣ በአሰልቺ ፕሮፖጋንዳ እና በሚዲያ ልፈፋ ሊመሰረቱ አይችሉም። ይህ ሁሉ መሬት ላይ ጠብ የሚያደርገው ምንም ፋይዳ የለውምና!! ህዝብ በዕለት ተዕለት ህይወቱ ሊያስተውል የሚችለውን እውነተኛ እኩልነት እና የመብት ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ይሻል። ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ግን መብትን ከመጠየቅ ይልቅ ከጠባቂነት ተላቆ ወደማስከበር ምዕራፍ ይሸጋገራል። ባለፉት ሶስት ዓመታት የተስተዋለው ህዝባዊ የመብት ማስከበር እንቅስቃሴ የሚያመላክተውም ይህንኑ ነው።

ዛሬ መንግስት ህዝብን ጆሮ ሰጥቶ ሊያደምጥ ግድ የሚልበት ጊዜ ላይ ተደርሷል። ህዝብ በተራ ሽንገላ የሚታለልበት ዘመንም አልፏል። ከሌላው የዓለማችን ክፍሎች በተለየ የሰለጠነ አካሄድ ‹‹መብቴን አላስነጥቅም›› ማለትን መርሁ አድርጓል። ይህ ህዝብ ‹‹መሪዎቹ›› ለዘመናት ታገልንለት ቢሉም በተግባር ግን እውን ላላደረጉለት የቡድን መብትም ይሁን ግለሰባዊ ነጻነቶች መከበር በሰላማዊ መንገድ መትጋቱን ይቀጥላል። ከገባበት ‹‹የመብቴ ይከበር›› ትግልም ምንም አይመልሰውም – የመብቱ በእውን መረጋገጥ ሲቀር!!

ህዝብ መርህን ባማከለ መልኩ እንደሚፈልገው መኖርን እንጂ እንዲኖር በተደረገው መልኩ ማሰብን አይሻም። ላለፉት ሁለት ዓስርት ዓመታት የተሰበከውን ሁሉ ጠንቅቆ ተረድቶ አፍረጥርጦ መጠየቅን እና ‹‹ለምን?›› ማለትን ተለምዶው አድርጎታል። ይህ የህዝብን የብስለት ደረጃ አመላካች ነው። መብት እና ግዴታውን ለይቶ የተረዳ ህዝብን ፈጽሞ እያታለሉ መኖር የማይቻል ሆኗል። አልገዛም ባይነት እና ለጭቆና እምቢተኝነትን በስብዕናው የተላበሰ ዜጋ በግዳጅ አምባገነንነትን ሊጭኑበት አይፈቅድም። ያለው የህግ መርር እንዲተገበር በህጋዊ መንገድ መጠየቁም አይቀሬ ነው፤ ማስተካከል የማይችል የስልጣን ጥመኛ ሲገጥመው ግን መብት እና ፍላጎቱን የሚያሟላበትን እና የሚያሟላለትን አማራጭ ለመፈለግ ይገደዳልና።

በእውን የቡድን መብት መከበሩን ማረጋገጥ ካስፈለገ በማህበረ-ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ፣ እንዲሁም ሌሎች ተቋማዊ አሰራሮች የሁሉንም አቻ ተሳታፊነት በተግባር ማሳየት የግድ ነው። በማህበራዊ ግልጋሎት ተደራሽ ያልሆነን፣ በልማት ፖሊሲ ያልታቀፈን፣ በአግላይ ፖሊሲ የተገፋን፣ በህግ ስርዓቱ ተበዳይ የተደረገን አንኳር የህዝብ ክፍል ይዞ ‹‹የብሄሮችን እኩልነት አረጋገጥኩ›› ብሎ በየዓመቱ መዘመር የብሄሮች እና የሃይማኖቶች እኩልነትን ከወረቀት ባለፈ ሊያረጋግጥልን አይችልም። በማደግ ላይ ባለች ሃገር ውስጥ ‹‹ታዳጊ›› የሚባሉ በርካታ ክልሎች እና ብሄረሰቦች ባሉበት ሁነት የብሄሮች እኩልነትን መረጋገጥ የሚያሳይ ተጨባጭ አስረጂም አይገኝም። በተለይ ደግሞ እነኚህ ክልሎች እና ብሄሮች በብዛት የአንድ ሃይማኖት ተከታዮች መሆናቸው ግምት ውስጥ ሲገባ እና በሌሎች ክልሎች እንደሚገኙት የእምነት ወንድሞቻቸው ሁሉ እነሱም በእምነታቸው ምክንያት በደል እና የሃይማኖት መብት ጥሰት ማስተናገዳቸው የሃይማኖት እኩልነትም እንዳልተረጋገጠ በቂ ማሳያ ነው።በመሆኑም እውነተኛ ፍትህ እና እኩልነት የሰፈነበት ሁለንተናዊ ህይወት በሃገራችን ላሉት ሁሉም ብሄሮች እና ብሄረሰቦች፣ እንዲሁም እምነቶች (ሃይማኖቶች) እንዲረጋገጥ ማድረግ ለነገ የማይባል አጣዳፊ የመንግስት ግዴታ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።

መንግስት ወደራሱ ዞር ብሎ የሚናገረውን እና የሚፈጽመውን ተዛምዷዊነት ፈትሾ በግልጽ ተግባሩን እንደ ቃሉ ማድረግ መጀመር ይጠበቅበታል፡፡ ይህን ካልፈቀደ ደግሞ ህዝብን ተግባር አልባ በሆነ ጮሌ ምላስ ለመሸንገል መታገሉን ትቶ በአዋጅ የመንግስት ፖለቲካዊ ማዕዘናትና እኩልነት ጽንሰ ሐሳቦች መፍረሳቸውን ሊያውጅ ይገባል!! ያኔ ህዝብም የ‹‹ህግ ይከበርልን›› ጥያቄውን ፍትህ እስኪሰፍን እና መብቱ እስኪከበርለት በቁርጠኝነት ይገፋበታል፤ አልያም ‹‹ፈጽሞውኑ ህግ የለም!›› ሲል ስለ ህጋዊነት ይሰብካል!!

ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምፃችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

Image

በበርካታ አጫጭር እና ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎች ላይ በትወና ተሳትፏል። በተለይ በቅርቡ በቴሌቪዥን በተላለፈው የ«ሰው ለሰው» ተከታታይ ድራማ እና አሁን በመታየት ባለው «ሞጋቾቹ» ድራማ ይታወቃል። መንፈሣዊ ዜማዎቹም በኢንተርኔት እና በሲዲ ተሰራጭተዋል።

የአንድ ‹‹ህዝብ›› የእምነት፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ… መብቱ በግለሰብ ደረጃ ካልተጠበቀለት በስተቀር የ‹‹ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ…›› መብት ሊጠበቅ አይችልም፡፡ ችግሩ የ‹‹ብሄርና›› ሌሎች ማንነቶችን የሚጠቀሙ የፖለቲካ ቡድኖች ከግለሰብ ማንነት ይልቅ ጥቅል ማንነትን የሚያስቀድሙት ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ መሆኑ ነው፡፡ ከፊሉን በእምነቱ፣ ከፊሉን በኢኮኖሚው፣ ከፊሉን እናከብርልሃለን በሚሉት ቋንቋው፣ ከፊሉን በነጻነቱ…. እያሉ ግን ሁሉንም ይጨቁኑታል፡፡ ሁሉንም ይጎዱታል፡፡ መስፈርቱ በብሄር ሳይሆን በግለሰብ ቢሆን […]

ምንም ያህል ልዩነት ቢኖረው የአንድን አገር ህዝብ የማይለወጠው የጋራ ማንነቱ ዜግነቱ ነው፡፡
Minilik Salsawi
የአንድ ‹‹ህዝብ›› የእምነት፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ…መብቱ በግለሰብ ደረጃ ካልተጠበቀለት በስተቀር የ‹‹ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ…›› መብት ሊጠበቅ አይችልም፡፡ ችግሩ የ‹‹ብሄርና›› ሌሎች ማንነቶችን የሚጠቀሙ የፖለቲካ ቡድኖች ከግለሰብ ማንነት ይልቅ ጥቅል ማንነትን የሚያስቀድሙት ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ መሆኑ ነው፡፡ ከፊሉን በእምነቱ፣ ከፊሉን በኢኮኖሚው፣ ከፊሉን እናከብርልሃለን በሚሉት ቋንቋው፣ ከፊሉን በነጻነቱ…. እያሉ ግን ሁሉንም ይጨቁኑታል፡፡ ሁሉንም ይጎዱታል፡፡ መስፈርቱ በብሄር ሳይሆን በግለሰብ ቢሆን ግን የሚድበሰበስ ነገር አይኖርም፡፡….. የአንድን አገር ህዝብ የማይለወጠው የጋራ ማንነቱ ዜግነቱ ነው፡፡ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የግለሰቦች ጥርቅም እስከሆኑ ድረስ ኦነግ፣ ኦብነግ፣ ግንቦት ሰባት፣ ጽንፈኛ፣ አሸባሪ፣ ኪራይ ሰብሳቢ፣ ተላላኪ፣ ኒዮ ሌንራል፣…….የሚባሉት መለጠፊያዎች እየተሰጧቸው አሳራቸውን የሚበሉት ‹‹ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች›› ናቸው፡፡

ምንም ያህል ልዩነት ቢኖረው የአንድን አገር ህዝብ የማይለወጠው የጋራ ማንነቱ ዜግነቱ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ከሌሎች ህዝቦች ይልቅ የሚያመሳስሉን፣ የምንጋራቸው በርካታ እሴቶች አሉን፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ ኢትዮጵያውይነታችን (ዜግነታች) የጋራችን ነው፡፡ ብሄር፣ ብሄረሰብ፣ ህዝብ ተብሎ በጅምላ ዜግነት ሊሰጠው አይችልም፡፡ አንድ ሰው ኢትዮጵያዊ ለመሆን መደራጀት አይጠበቅበትም፡፡

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ግለሰብ ኦሮምኛ ተናጋሪዎችን ‹‹ኦሮሞ››፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩትን ግለሰብ አማርኛ ተናጋሪዎች ‹‹አማራ››፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ግለሰብ ሶማልኛ ተናጋሪዎን ‹‹ሶማሊ››…….እያሉ ነው ኢትዮጵያውያንን ‹‹ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች›› በሚል አዲስ ማምነት የሚደረድሩን፡፡ ብሄር፣ ብሄረሰብ፣ ህዝብ የሚባለው ከግለሰቦች እንጅ ከምንም የመጣ አይደለም፡፡ የብሄር ብሄረሰቦች መብት መከበር ካለበት መጀመሪያ መቅደም የሚገባው የስሪታቸው የግለሰቡ መብት ነው፡፡

ኦሮሞ፣ አማራ፣ትግሬ….› እየተባሉ የተቦደኑት ህዝቦች አንድ አይነት አይደሉም፡፡ እንዲያውም ኦሮምኛ ተናጋሪው ‹‹ኦሮሞ›› ከሚባለው ውጭ ከአማርኛ ተናጋሪው ጋር የሚጋራው በርካታ ማንነቶች ይኖሩታል፡፡ አማርኛ ተናጋሪው ‹‹አማራ›› ከተባለው ይልቅ ከኦሮምኛ ተናጋሪው ጋር የሚያመሳስሉት በርካታ ማንነቶች ይኖሩታል፡፡ ለአብነት ያህል ትግርኛ፣ አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ሶማሊኛ፣ ….ተናጋሪው ህዝብ ከቋንቋውም በላይ አንዱ የሌላውን ድንበር ተሸግሮ ከሌላኛው ቋንቋ ተናጋሪ ጋር በእምነት፣ በፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ሌሎች ገመዶች ይገናኛል፡፡ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የአንድ ብሄር ሰዎች አይደሉም፡፡ የሙስሊሙ እንቅስቃሴ እንዲህ እስካሁን በጥንካሬ የዘለቀው በድንበር ተሸጋሪው ማንነቱ እንጅ በጠባብ ‹‹የብሄር›› ማንነት ታጥሮ አይደለም፡፡ ኦርቶዶክሶቹ፣ ፕሮቴስታንቶቹ፣ ካቶሊኮቹ በ‹‹ብሄር›› የታጠሩ አይደሉም፡፡

የአንድ ‹‹ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ…›› የእምነት፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ…መብቱ በግለሰብ ደረጃ ካልተጠበቀለት በስተቀር የ‹‹ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ…›› መብት ሊጠበቅ አይችልም፡፡ ችግሩ የ‹‹ብሄርና›› ሌሎች ማንነቶችን የሚጠቀሙ የፖለቲካ ቡድኖች ከግለሰብ ማንነት ይልቅ ጥቅል ማንነትን የሚያስቀድሙት ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ መሆኑ ነው፡፡ በ‹‹ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ፣ሶማሊ…….›› ስም በጅምላ ከመነገድ ያለፈ ስለ እያንዳንዱ ህዝብ አያስጨንቀቃቸውም፡፡ 30 ወይንም 40 ሚሊዮን የአንድ ‹‹ብሄር›› ህዝብ በአንድ ጉዳይ ሊከፋ አይችልም፡፡ ቢያንስ ከገዥዎች ጋር ሆኖ የሚጠቀም አይጠፋም፡፡

ከፊሉን በእምነቱ፣ ከፊሉን በኢኮኖሚው፣ ከፊሉን እናከብርልሃለን በሚሉት ቋንቋው፣ ከፊሉን በነጻነቱ…. እያሉ ግን ሁሉንም ይጨቁኑታል፡፡ ሁሉንም ይጎዱታል፡፡ መስፈርቱ በብሄር ሳይሆን በግለሰብ ቢሆን ግን የሚድበሰበስ ነገር አይኖርም፡፡ ሁሉም የግለሰብ መብቶች እስከተከበሩ ድረስ የአገሪቱ ህዝብ መብት ይከበራል፡፡ የግለሰብ መብት ካልተከበረ ግን የማንም መብት ሊከበር አይችልም፡፡ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የግለሰቦች ጥርቅም እስከሆኑ ድረስ ኦነግ፣ ኦብነግ፣ ግንቦት ሰባት፣ ጽንፈኛ፣ አሸባሪ፣ ኪራይ ሰብሳቢ፣ ተላላኪ፣ ኒዮ ሌንራል፣…….የሚባሉት መለጠፊያዎች እየተሰጧቸው አሳራቸውን የሚበሉት ‹‹ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች›› ናቸው፡

በዘመነ መሳፍንት ወቅት፤ ለስሙ በዙፋኑ ላይ የዘር ግንድ ያለውን ሰው አስቀምጠው፤ ራሳቸውን እንደራሴ በመሾም፤ ጉልበተኞች ያደረጉት ሁሉ ግልጽ ነው። የውጭ ሀገር መንግሥታት ደግሞ በወኪሎቻቸው አማካኝነት ፀረ-ኢትዮጵያ ሚና ተጫወቱ። በደንብ በዝርዝር የሚያስረዳ መዝገብ ግን አላገኘሁም። ከዚህም ከዚያም ለቃቅሜ የተገነዘብኩትን ይዣለሁ። የእስክንድርያውን የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን በመጠቀም፤ ግብፅና ቱርክ በአንድ በኩል፣ በፖርቹጋሎች የተጀመረውን ግንኙነት በመጠቀም፤ የካቶሊክ ቤተክርስትያን በሌላ በኩል፣ […]

በአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት እየተካሔደ በሚገኘው የክርክር መድረክ ላይ ተሳታፊ የሆኑ የአንድነት ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በትላንትናው እለት የ9ኙ ፓርቲዎች ህብረት የጠራውን የ24 ሰዓት ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ የመንግስት ሀይሎች የወሰዱትን ኢ-ህገመንግስታዊ እርምጃ አጥብቀው እንደሚያወግዙ ገልፀዋል፡፡ በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የወጣቶች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ‹‹ምርጫ 2007 የኢህአዴግ መጨረሻ ወይስ የመጨረሻው መጀሪያ››በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ክርክር በትዝጋጅው ፕሮግራም መሰረት ተካሂዱዋል፡፡ […]

የፕሮግራም መግለጫ

ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡

የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡

ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡


ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
—-
    በዩኒቨርሲቲ ቆይታዬ (ከ1989-እስከ 1992 በነበረው ጊዜ) “ሐቄ” የምትባል ልጅ አውቃለሁ፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት የሴቶች ጉዳይ ሃላፊ የነበረችው (በኋላ በኮትዲቯር የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆነችው) ወ/ሮ ታደለች ሀይለሚካኤል የዚያች ልጅ እናት እንደነበረች ይወሳ ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ የባለስልጣን ልጅ መሆኗን በመፍራት ብቻ ብዙዎች አይጠጓትም ነበር፡፡ ከልጅቷ ጋር የሚቀራረበው ተወልደ መዝገቡ የሚባል የአዲግራት ልጅ ብቻ እንደነበረ አስታውሳለሁ፡፡
    
     የዩኒቨርሲቲው ትምህርት ከተጠናቀቀ ከጥቂት ወራት በኋላ መጽሔቶችን ሳገላብጥ ያቺ ልጅ ለምልክት ከሞት የተረፈች የፈጣሪ ተአምር እንደሆነች ተረዳሁ፡፡ አባቷ ነፍሲያውን ሊጠነቅ በተቃረበበት ወቅት ታሪኩን ትመሰክር ዘንድ የዘራት ብቸኛ ፍሬው ነበረች፡፡ ብዙዎች በእናቷ ሆድ የነበረችበትን ጊዜ በብዕራቸው ነካክተውታል፡፡ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማሪያም በበኩላቸው ያቺ ነፍስ በእናቷ ሆድ ውስጥ በመገኘቷ እናቷን ከሞት ያተረፈች መሆኗን መስክረውላታል፡፡ ለዚህም ይመስላል እናቷ “ሐቄ” የሚለውን ስም የሰጠቻት፡፡
ህይወት ተፈራ Tower in the sky የተባለውን መጽሐፍ ስትጽፍ ለዚያች ልጅ መጠነኛ ሽፋን ሰጥታለች፡፡ ከእናቷ ጋር የተነሳችውንም ፎቶግራፍ በመጽሐፉ ውስጥ አካተዋለች፡፡
                                                                          *****
   በፎቶግራፉ ላይ የምትመለከቱት የዚያች ልጅ አባት የነበረውን ሰው ነው፡፡ ይህ ሰው ከታሪካዊው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ መሪዎች መካከል አንዱ የነበረውና የመጀመሪያው የኢህአፓ ዋና ጸሓፊ ሆኖ የተመረጠው ብርሀነ መስቀል ረዳ ነው፡፡ ለብዙሃን ህይወት መለወጥ በብርቱ የታገለ፣ ሁለቱን ጠንካራ ስርዓቶች ፊት ለፊት የተጋፈጠ፣ ላመነበት ዓላማ ትምህርቱን ሰውቶ መታገልን የመረጠ፣ ከሀገር ወጥቶ በሰው ሀገርና በበረሃ የተንከራተተ፣ በመጨረሻ ላይ ግን ከገዛ ጓዶቹ ጋር ተጣልቶ የራሱን መንገድ የመረጠ፣ በዚህም ከፍተኛ የውዝግብ ርዕስ ለመሆን የበቃ የዚያ ዘመን ፋኖ!…
 
  ብርሀነ መስቀል ማን ነው?… በኢትዮጵያ ህዝቦች የፖለቲካ ትግል ውስጥ ምን ሚና ነበረው?… የርሱ ህይወትና የትግል መንገድ እንዴት ይገመገማል?… እነኝህ በኔ አቅም የሚመለሱ ጥያቄዎች አይደሉም፡፡ ታሪኩ እስከ አሁን ድረስ እያወዛገበ ስለሆነ ሐቁን ከግርድፉ ማጣራቱ ከባድ ጥረት ይጠይቃል፡፡ ብርሀነ መስቀል በወዳጆቹም ሆነ በጠላቶቹ የሚከበርና የሚፈራ መሆኑን ግን ማንም አያስተባብልም፡፡ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማሪያም በእስር ቤት አናዝዘውት ከገደሉት በኋላ “የመርሐቤቴ ገበሬዎች ገደሉት” እያሉ ለመዋሸት ቢሞክሩም በኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ውስጥ የነበረውን ሚና በአዎንታዊ መልኩ ነው የገለጹት፡፡ በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው የቅርብ ጓደኛው የነበሩት አንጋፋው ገጣሚና ባለቅኔ ኃይሉ ገብረ-ዮሐንስ (ገሞራው) “ችኩል እና ቁጡ ከመሆኑ በስተቀር ለሀገር መሪነት የሚበቃ ስብዕና ነበረው” በማለት መስክረውለታል፡፡
      ከሁሉም በላይ የብርሀነ መስቀልን ቆራጥነትና ልዩ ተሰጥኦ ሰፋ ባለ ሁኔታ የገለጹት የኢህአፓው ክፍሉ ታደሰ ነበሩ፡፡ አቶ ክፍሉ “ያ ትውልድ” በተሰኘውና በከፍተኛ ደረጃ ተነባቢ ለመሆን በበቃው መጽሐፋቸው “ብርሀነ መስቀል በኢህአፓ ውስጥ የራሱን አንጃ ፈጥሯል” የሚል ክስ እያቀረቡበት እንኳ ለትግሉ ያበረከተውን አስተዋጽኦ በተዋቡ ቃላት ገልጸዋል፡፡  ለምሳሌ ያህል የሚከተለውን መጥቀስ ይቻላል፡፡
    “በተማሪው እንቅስቃሴ ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከተውና አንደበተ ርቱእ የሆነው ብርሃነ መስቀል፣ በእንቅስቃሴው ውስጥ ሲታሰርና ሲፈታ የኖረ ነው” (ክፍሉ ታደሰ፣ ያ ትውልድ፣ ገጽ- 144)
                                                                          *****
    ብርሀነ መስቀል ለደርግ መርማሪዎች የሰጠው ቃል ሰሞኑን በኢንተርኔት ተበትኖ የብዙዎች መነጋገሪያ ሆኗል፡፡ እኔም ይህ 98 ገጾች ያሉት የምርመራ ቃል ከአንድ የፌስቡክ ጓደኛዬ ደርሶኝ እያነበብኩት ነው (ሙሉውን ዶክመንት www.debteraw.comከተሰኘ ዌብሳይት ማግኘት ትችላላችሁ)፡፡ እስከ አሁን ድረስ 1/3ኛ ያህሉን አገባድጄዋለሁ፡፡ ይሁንና ፊት ከማውቀው የብርሀነ መስቀል ታሪክ የተለየ ነገር አላገኘሁበትም፡፡ በሚቀጥሉት ቀናት አትኩሮት የሚስቡ መረጃዎችን ካገኘሁበት ልመለስ እችላለሁ፡፡ እስከዚያው ግን ስለብርሀነ መስቀል በትንሹ ላውጋችሁ፡፡
   ብርሃነ መስቀል ረዳ ወልደ-ሩፋኤል በ1930ዎቹ አጋማሽ በትግራይ ገጠር ነው የተወለደው፡፡ ያደገው ግን በደሴ ከተማ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ በነበሩት አጎቱ ቤት ነው፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደሴ በሚገኘው የወይዘሮ ስሒን ት/ቤት ካጠናቀቀ በኋላ በ1955 ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ገብቷል፡፡ በዩኒቨርሲቲ ቆይታው ትምህርቱን ከመከታተል ይልቅ ተማሪዎችን ለተቃውሞ በማንቀሳቀሱ ላይ ነበር ያተኮረው፡፡ በዚህም መሰረት ወደ ዩኒቨርሲቲው እንደገባ ከርሱ ቀደም ብለው “አዞዎቹ” በሚል ቡድን ዙሪያ የተሰባሰቡትን የስር-ነቀል ለውጥ ደጋፊ ተማሪዎችን ለመቀላቀል በቅቷል፡፡ ከዓመት በኋላ በ1956 በዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ተማሪዎች ህብረት ውስጥ የመረጃ ኦፊሰር ሆኖ ተመርጧል፡፡ በአመቱ ደግሞ የብሔራዊ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት ዋና ጸሓፊ ሆኖ ነበር፡፡
Berhane Mesqel Redda
    
ብርሃነ መስቀል በ1957 የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች “መሬት ላራሹ” የሚል መፈክር አንግበው ድምጻቸውን ለፓርላማ ያሰሙበትን ታሪካዊ ሰልፍ ካደራጁት መካከልም ነበር፡፡ በዚያ ሰልፍ ሳቢያ ከትምህርታቸው ከተባረሩት ዘጠኝ ተማሪዎች መካከልም አንዱ ነው (በወቅቱ ከርሱ ጋር የተባረሩት ገብሩ ገብረወልድ፣ ሀይሉ ገብረዮሐንስ፣ ዮሐንስ ስብሐቱ፣ ታዬ ጉርሙ፣ ዘርዑ ክህሸን፣ ስዩም ወልደ ዮሐንስ፣ ሀብቴ ወልደ ጊዮርጊስና ሚካኤል አበበ ናቸው)፡፡ እነዚያ ተማሪዎች ከአንድ ዓመት በኋላ ወደ ዩኒቨርሲቲው ቢመለሱም በተረጋጋ ሁኔታ ትምህርታቸውን መከታተል አልቻሉም፡፡ በየጊዜው በሚካሄዱት ሰልፎችና የተቃውሞ ስብሰባዎች ግንባር ቀደም ተጠያቂ እየሆኑ ይታሰሩ ነበር፡፡ በስተመጨረሻ ግን የ“አዞዎቹ” ቡድን አባላት ከነአካቴው ከዩኒቨርሲቲው ተባረሩ፡፡ በመሆኑም በተደራጀ ሁኔታ ለመታገል ወሰኑ፡፡
   
   በዚህም መሰረት ብርሃነ መስቀልና አምስት ጓደኞቹ ከባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ የሚበር አንድ አውሮፕላን በመጥለፍ ወደ ካርቱም ኮበለሉ፡፡ ከጥቂት ወራት በኋላም ወደ አልጄሪያ ተሻገሩ፡፡ በአልጀርስ ቆይታቸው እጅግ ቀስቃሸ የሆኑ ጽሑፎችን እያዘጋጁ ወደ ሀገር ቤት ይልኩ ጀመር (በዚያ ዘመን “ጥላሁን ታከለ” በሚል የብዕር ስም በመጠቀም አስደናቂ ጽሑፎችን ይጽፍ የነበረው ብርሃነ መስቀል ረዳ እንደሆነ ነው የሚታመነው)፡፡ በአልጄሪያ የነበሩት ስደተኛ አብዮተኞች በውጪው ዓለም ትምህርታቸውን ከሚከታተሉ ኢትዮጵያዊያን ጋር በሚያደርጓቸው ግንኙነቶች በተደራጀ መንገድ የሚታገሉበትን መንገድ ቀየሱ፡፡ እነዚያ ውይይቶች እያደጉ ሄደው በ1964 ኢህአድ (የኢትዮጵያ ህዝብ አርነት ድርጅት) የተሰኘ ህቡዕ ፓርቲ ተወለደ፡፡ ብርሀነ መስቀል ረዳም የድርጅቱ ዋና ጸሐፊ ሆኖ ተመረጠ (የድርጅቱ ስም በ1967 “የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ” በሚል ተለውጧል፤ ይህም በአህጽሮት “ኢህአፓ” የሚባለው ነው)፡፡
     ብርሀነ መስቀል የኢህአድ ዋና ጸሓፊ በነበረበት የመጀመሪያ ዓመት በአብዛኛው ፓርቲውን የማስተዋወቅና ድጋፍ የመፈለግ ስራዎችን ነበር የሰራው፡፡ በዚህም ከአውሮፓ እስከ መካከለኛው ምስራቅ ድረስ ተጉዟል፡፡ ከባለቤቱ ታደለች ሀይለሚካኤል ጋር የተዋወቀው በዚያን ጊዜ ነው፡፡ በ1966 ብርሃነ መስቀልና ጥቂት ሰዎች የድርጅቱን የትጥቅ ትግል እንዲጀምሩ ወደ ኤርትራ ተላኩ፡፡ ወታደራዊ ስልጠና ለመውሰድ ለአንድ ዓመት በኤርትራ ከቆዩ በኋላ በ1967 መጀመሪያ ላይ ትግራይ ውስጥ ወደሚገኘው አሲምባ ተራራ ተሻገሩ፡፡ ሆኖም የትጥቅ ትግሉን ሳይጀምሩ በአሲምባ ቤዛቸው ለስድስት ወራት ቆዩ፡፡ በዚህ መሀል ስምንት ያህል የቡድኑ አባላት ከብርሀነ መስቀል ጋር የነበራቸውን ቀየሜታ በማሳበብ ድርጅቱን ጥለው ለደርግ መንግሥት እጃቸውን ሰጡ፡፡ ብርሀነ መስቀል በፋኖዎቹ አድራጎት በመቆጣቱ በሌሉበት የሞት ፍርድ ፈረደባቸው፡፡ ሆኖም ይህ ውሳኔው ከሌሎች የኢህአፓ አባላት ተቃውሞ ገጠመው፡፡ የኢህአፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጉዳዩን ካጣራ በኋላ በሰዎቹ ላይ የተላለፈው የሞት ፍርድ እንዲነሳ ወሰነ፡፡ ብርሀነ መስቀልም ከሰራዊቱ ተነጥሎ ወደ አዲስ አበባ እንዲሄድ ተወሰነ፡፡ ይህም በብርሀነ መስቀልና በሌሎቹ የኢህአፓ መሪዎች መካከል ንትርክ ፈጠረ፡፡
     ይህ በእንዲህ እንዳለ በነሐሴ ወር 1967 አህአፓ ራሱን በአዲስ መልክና በአዲስ ስም ሲያደራጅ “ዋና ጸሐፊ” የሚባል የስልጣን እርከን ተሰረዘ፡፡ ድርጅቱ ሊቀመንበርም ሆነ ዋና ጸሐፊ የለውም ተብሎ ታወጀ፡፡ ብርሀነ መስቀል ይህንን እርምጃ እርሱን ከቦታው ለማንሳት የተሸረበ ሴራ አድርጎ ስለወሰደው ከፍተኛ ቅሬታ አደረበት፡፡ ከማዕከላዊ ኮሚቴው ጋር የሚያደርገውንም ግንኙነት ማቀዝቀዝ ጀመረ፡፡ የደርግ መንግሥት በሚያዚያ ወር 1968 በህቡዕ ለተደራጁ ድርጅቶች ሁሉ የግንባር ጥሪ ሲያደርግ ብዙሃኑ የኢህአፓ አመራር ጥሪውን በመሰረቱ እንደሚቀበል ከገለጸ በኋላ መሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች አስቀመጠ፡፡  እነዚያ ሁኔታዎች ካልተሟሉ በስተቀር ከደርግ መንግሥት ጋር እንደማይሰራ ገለጸ፡፡ ብርሀነ መስቀል ግን “ቅድመ- ሁኔታ ማስቀመጡ ልክ አይደለም” በማለት ተከራከረ፡፡ በነሐሴ ወር 1968 የኢህአፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ “ራሳችንን ለመከላከል የከተማ ትጥቅ ትግል ማድረግ አለብን” በማለት ሲወስን ብርሀነ መስቀል “ውሳኔው አደገኛ ነው፤ ኢህአፓን ያስመታል፤ ደግሞም ደርግ ማርክሳዊ ነኝ ብሎ ያወጀ መንግሥት ስለሆነ ማርክሳዊ መንግሥትን በትጥቅ አመጽ መቃወም የአብዮታዊያን ጸባይ አይደለም” በማለት በብርቱ ተቃወመው፡፡ ይህም ታቃውሞ ከኢህአፓ አመራር ጋር እስከ ወዲያኛው አቆራረጠው፡፡
 
   የኢህአፓ አመራር ብርሀነ መስቀል ያሳያቸውን የአቋም ልዩነቶች ከገመገመ በኋላ ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነቱ ሰረዘው፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላም “ብርሀነ መስቀል በፓርቲው ውስጥ የራሱን አንጃ ለመመስረት ጥረት እያደረገ ነው” የሚል ክስ አቀረበበት፡፡ በድርጅቱ ጋዜጦች ላይ ግለ-ሂስ እንዲያደርግም አዘዘው፡፡ ብርሀነ መስቀልም ሂሱን ካወረደ በኋላ በድርጅቱ ታጣቂዎች እንዲጠበቅ ተደረገ፡፡ በሚያዚያ 1969 ግን ለማንም ግልጽ ባልሆነ መንገድ ከአዲስ አበባ ከተማ ተሰውሮ ወደ መርሐቤቴ አውራጃ ገባ፡፡ እዚያም ከተወሰኑ ሰዎች ጋር የትጥቅ ትግል ለማድረግ ሞከረ፡፡ ይሁን እንጂ በእርምጃው ከጥቂት ወራት በላይ አልዘለቀም፡፡ የደርግ አዳኝ ሀይሎች በ1970 መጀመሪያ ላይ ይዘውት ወደ አዲስ አበባ አመጡት፡፡ ለአንድ ዓመት ከሰድስት ወራት ያህል በታላቁ ቤተ መንግሥት ከታሰረ በኋላ በሚስጢር ተገደለ፡፡
                                                                          *****
      የብርሀነ መስቀል አንጃ የመፍጠር ሙከራ በራሱም አንደበት የተረጋገጠ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ብርሀነ መስቀል “እኔ ያካሄድኩት የእርማት ንቅናቄ እንጂ ፓርቲውን ለማጥፋት ያለመ አንጃ አልፈጠርኩም” ባይ ነው፡፡ በተጨማሪም ባለቤቱ ወይዘሮ ታደለች ሀይለ ሚካኤል በአንድ ወቅት በሰጡት ቃለ ምልልስ ብርሀነ መስቀል የእርማት ንቅናቄ ለማካሄድ መሞከሩን ተናግረዋል፡፡ በዚያ ዘመን በርሱ ስም የተሰራጩትን ልዩ ልዩ ዶክመንቶች በሙሉ የርሱ ናቸው ለማለት ይከብዳል፡፡ አንደኛው ጽሑፍ ግን በርሱ እጅ ጽሑፍ የተጻፈ መሆኑ ስለሚታወቅ የርሱን እምነት ይገልጻል ተብሎ ይታመናል፡፡ ብርሀነ መስቀል በዚያ ጽሑፉ የኢህፓን አመራር ቢኮንንም ደርግንም በሚገባ ይቃወማል፡፡ እንዲሁም በርሱ ስም ድርጅቱን የበጠበጡ በርካታ ቅጥረኞች እንደነበሩም ያወሳል፡፡ ሆኖም የኢህአፓ አመራር እርሱ ያለውን አምኖ የተቀበለው አይመስልም፡፡ ኢህአፓዎች “ለድርጅቱ ብተና ፈር የቀደደ ከሀዲ ነው” ነው የሚሉት፡፡
   ማንም የማይክደው አንድ ሐቅ ግን አለ፡፡ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ሲነሳ ብርሀነ መስቀልን መርሳት በጭራሽ አይሞከርም፡፡ በርካታ የለውጥ ፈላጊው ትውልድ አባላት የርሱን አርአያ በመከተል ወደ ትግሉ ጎራ መቀላቀላቸውንም ማስተባበል አይቻልም፡፡ ስለዚህ ምሁራን በቅጡ ያልተመረመውን የዚህን ፋኖ ታሪክ ጎልጎለው በትግሉ ውስጥ የነበረውን አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ሚና ሳይሸፋፍኑ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
                                                                          *****
አፈንዲ ሙተቂ
ህዳር 28/2006

የፕሬዚዳንት ሙጋቤ ባለቤት የዚምባቡዌ ቀጣይ የሀገር አስተዳዳሪ ለመሆን ራሳቸውን እጩ እስከመሆን አበቁ። ቀዳማዊት እመቤት ግሬስ ሙጋቤን የገዢው ዛኑ ፒ ኤፍ ፓርቲ ሀራሬ ውስጥ ባካሄደው ስብሰባ የ49 ዓመቷን ወ/ሮ ከሴቶች ክፍል ተጠሪ አድርጎ ሰይሟል። ወይዘሮ ግሬስ አንዱን ቀን የሀገሪቷ ፕሬዚዳንት መሆን እንደሚሹም አመላክተዋል።

የፕሬዚዳንት ሙጋቤ ባለቤት የዚምባቡዌ ቀጣይ የሀገር አስተዳዳሪ ለመሆን ራሳቸውን እጩ እስከመሆን አበቁ። ቀዳማዊት እመቤት ግሬስ ሙጋቤን የገዢው ዛኑ ፒ ኤፍ ፓርቲ ሀራሬ ውስጥ ባካሄደው ስብሰባ የ49 ዓመቷን ወ/ሮ ከሴቶች ክፍል ተጠሪ አድርጎ ሰይሟል። ወይዘሮ ግሬስ አንዱን ቀን የሀገሪቷ ፕሬዚዳንት መሆን እንደሚሹም አመላክተዋል።

Image

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ባለፈው አንድ ወር ‹‹ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ›› በሚል መርሃ ግብር ቀርጸን ስንቀሳቀስ ዋናው አላማችን የስርዓቱን አረመኔያዊነት ለህዝብ በማጋለጥ የኢትዮጵያ ህዝብ በትግሉ እንዲሳተፍ ማድረግ ነው፡፡ እንደጠበቅነው ገና ከጅምሩ የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ ትግላችንን በጭካኔ ለማስቆም ጥሯል፡፡ ህዳር 7/2007 ዓ.ም የመጀመሪውን የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ በጠራንበት ወቅት ስብሰባውን በኃይል በትኗል፡፡

ትብብራችን ከመቸውም ጊዜ በላይ ያሰጋው ህወሓት/ኢህአዴግ በተለይ የህዳር 27/28 2007 ዓ.ም የአደባባይ አዳር ሰልፍን እንዳይካሄድ የትብብሩን አመራሮችና አባላቶቻችን በማዋከብ፣ በመደብደብና በማሰር ተጠምዶ ሰንብቷል፡፡ በተለይ በትናንትናው ዕለት ሰልፍ በወጣንበት ወቅት ስርዓቱ አመራሮችንን፣ አባላቶቻችንን፣ ተሳታፊዎችንን እንዲሁም አልፎ ተርፎ መንገደኛውን ህዝብ በጭካኔ ደብድቧል፡፡ አፍሶ አስሯል፡፡ ሙስሊም እህትና ወንድሞቻችን በየጎዳናው ታፍሰው የአገዛዙ አረመኔያዊ እርምጃ ሰለባዎች ሆነዋል፡፡ በርካቶችም በእ
በየ እስር ቤቶቹ ታጉረዋል፡፡ እስካሁን ባለን መረጃ ከ300 በላይ የትብብሩ አመራሮችና አባላት የታሰሩ ሲሆን የትብብሩና የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበርን ጨምሮ በርካታ አመራሮች ከፍተኛ የአካል ጉዳት ድርሶባቸዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ አባል የሆነው አቤል ኤፍሬም ራሱን እስኪስት ተደብድቧል፡፡ በሰላማዊ ሰልፉ የተገኙ ሴት አመራርና አባላት አንድ አገርን እየመራሁ ነው ከሚል አካል በማይጠበቅ መንገድ በጭካኔ ተደብድዋል፡፡ እነዚህ በጭካኔ የተደበደቡ አመራሮች፣ አባላትና የሰልፉ ተሳታፊዎች ህክምና እንዳያገኙ ተከልክለዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በጥበቃ ሰራተኝነት የሚሰሩ የ72 አመቱ አቶ ቀኖ አባጆቢር ከስራ ሲወጡ በደህንነት ኃይሎች ታፍነው የተወሰዱና እስካሁን የት እንደደረሱ ያልታወቀ ሲሆን ይህም አገዛዙ የመጨረሻው የአረመኔነት ደረጃ ላይ እንደደረሰና ይህን የስርዓቱ ውንብድና ለማስቆም ጊዜ የማይሰጠው ተግባር መሆኑን በግልጽ የተገነዘብንበት ነው፡፡

አገዛዙ በትናንትናው ዕለት በፍጹም ሰላማዊ ሰዎች ላይ የወሰደው የውንብድና እና አረመኔያዊ እርምጃ በትግሉ ውስጥ የምንጠብቀውና ስርዓቱ ለኢትዮጵያ የማይበጅ መሆኑን ዳግመኛ ያያ

ረጋገጠበት ነው፡፡ የትናንትናው ትላችን አገዛዙ ለይስሙላ እከተለዋለሁ ከሚለው ‹‹ህጋዊ ሰርዓት›› ይልቅ ስልጣኑን በኃይል ለማስጠበቅ ቆርጦ መነሳቱን እና በህገ መንግስት ስም ህዝብን የሚበድልበትን የአረመኔያዊነት ጭንብል ገልጠን ለዓለም ያሳየንበት የትግላችን ውጤት ነው፡፡

አገዛዙ ላላፉት 24 አመታት ስልጣኑን በኃይል ለማስጠበቅ ሲጥር ቆይቷል፡፡ በትናንትናው ዕለት የፈጸመው ፍጹም አረመኔያዊ እርምጃም እንደተለመደው ሰላማዊ ታጋዮችን ያሸማቅቃል ብሎ አስቦ እንደሆነ እሙን ነው፡፡ ነገር ግን ይህ የአገዛዙ አረመኔያዊነት ከሰላማዊነታችን ፍጹም ወደኋላ ሊያንሸራትተን አይችልም፡፡ ወደ ትግል ስንገባ የስርዓቱን ጭካኔና ለኢትዮጵያ የ

ማይመጥን መሆኑን አውቀንና የሚያስከፍለውን መስዋዕትነት ለመክፈል ተዘጋጅተንም ነው፡፡ አሁንም አገዛዙ የህዝብን ድምጽ በማፈን ስልጣኑን ለማስጠበቅ ተመሳሳይ እርምጃ እንደሚወስድ እንጠብቃለን፡፡ ነገር ግን መጀመሪያውንም ትግሉን ስንቀላቀል አስበን የገባነው እየቆሰልን፣ እየታሰርንም፣ እየሞትንም ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ ለመሆን ነውና ከትግላችን ቅንጣት ሊያደናቅፈን አይችልም፡፡ ስለሆነም ወደፊትም ይህን የአገዛዙን አረመኔያዊነት በማጋለጥና ህዝቡን በትግሉ በማሳተፍ ለኢትዮጵያ የሚገባት ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ለመመስረት በቀጣይነትም ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን፡፡

በዚህ አጋጣሚ ሰላማዊ ሰልፉን ለማሳካት እንዲሁም የህወሓት/ኢህአዴግ ቡድን የፈጸመውን ጭካኔ በማውገዝ ከጎናችን ለቆማችሁ ሁሉ ምስጋናችን የላቀ ነው፡፡ ከህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ ጋር የሚደረገው ትግል እልህ አስጨራሽ፣ ከፍተኛ መስዋዕትነት የሚያስከፍልና የእያንንዳንዳችን ትብብር የሚጠይቅ መሆኑን ተገንዝበን ሁላችንም በጋራ እንድንቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን

ያለ መስዋዕትነት ድል የለም፡፡


ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
—–
  ተነገወዲያ ህዳር ህዳር 29/2007 ዘጠነኛው የብሄርና ብሄረሰቦች ቀን ሊከበር ነው፡፡ ይህ ቀን ለበዓሉ አከባበር የተመረጠው የኢፌዴሪ ህገ-መንግሥት የጸደቀበት ስለሆነ ነው ተብሏል፡፡ ታዲያ በዚሁ ቀን አንድ ታላቅ አብዮታዊ ተገድሎ ነበር፡፡ የሚገርመው ደግሞ በዚያች ቀን የሞተው ሰውዬ በኢትዮጵያ ውስጥ የብሄርና ብሄረሰቦች መብት መከበር አለበት በማለት ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ የጻፈ ሰው መሆኑ ነው፡፡
                                                                          *****
      ህዳር 29/1964፡፡ ረፋዱ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ቦይንግ 708 ጄት አውሮፕላን ከአዲስ አበባ በአስመራ በኩል ወደ አቴንስ ሊበር ነው፡፡ በአውሮፕላኑ የሚጓዙ መንገደኞች ቦታ ቦታቸውን ይዘዋል፡፡ ሰባት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም ከአውሮፕላኑ ውስጥ ተሳፍረዋል፡፡ የበረራው ሰዓት ሲደርስ አውሮፕላኑ ከመሬት ተነሳ፡፡ ከሰማዩ ገብቶ መብረር ሲጀምር ግን ያልታሰበ ሁኔታ ተከሰተ፡፡ እነዚያ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አውሮፕላኑን በቁጥጥራቸው ስር ማዋላቸውን አስታወቁ፡፡  እነርሱ ወደሚፈልጉት ሀገር እንዲበሩም አብራሪዎቹን አዘዟቸው፡፡ ተማሪዎቹ የጠለፋ እወጃውን ካሰሙ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ደግሞ ሌላ ያልታሰበ ነገር ተከሰተ፡፡ አውሮፕላኑን ከጠለፋ እንዲታደጉ የታዘዙ ኮማንዶዎች በቀጥታ በጠላፊዎቹ ላይ በማነጣጠር ተኮሱባቸው፡፡ ስድስት ጠላፊዎች ተገደሉ፡፡ አንዲት ጓደኛቸው ደግሞ በከባድ ሁኔታ ቆሰለች፡፡ የአውሮፕላኑ ወለል በሙታኑ ደም ታጠበ፡፡
Walelign Mekoneen
                                                                          *****
    በዚያች ዕለት የሞተው ታዋቂው የተማሪዎች ንቅናቄ መሪ ዋለልኝ መኮንን ነበር፡፡ ከርሱ ጋር የተገደሉትም ማርታ መብራህቱ፣ ጌታቸው ሀብቴ፣ ተስፋዬ ቢረጋ፣ ዮሐንስ በፈቃዱ እና አማኑኤል ዮሐንስ ናቸው፡፡ እነዚያ ወጣቶች አውሮፕላኑን ለመጥለፍ የሞከሩት የስርዓቱ ክትትል መፈናፈኛ ስላሳጣቸው ነው፡፡ ዓላማቸው ወደ ውጪ ከኮበለሉት ጓደኞቻቸው ጋር በመቀላቀል ለስር-ነቀል ለውጥ የሚታገል ድርጅት መመስረት ነበር፡፡ ከድርጅቱ ምስረታ በኋላም ወደ ሀገር ቤት ተመልሰው ትግሉን በየአቅጣጫው ለማፋፋም አስበዋል፡፡ ሆኖም እንደተመኙት አልሆነላቸውም፡፡ አውሮፕላን ለመጥለፍ ማቀዳቸው ቀደም ብሎ ተጠቁሞ ስለነበር የጸጥታው ክፍል በአየር ላይ አፍኖ አስቀራቸው፡፡
                                                                          *****
     ከላይ በተገለጸው አሳዛኝ ገቢር (ትራጄዲ) ህይወቱ የተቋጨው ዋለልኝ መኮንን በወሎ ክፍለ ሀገር የሳይንት (ቦረና) አውራጃ ተወላጅ ነው፡፡ የአንደኛና ደረጃ ትምህርቱን በደሴው ንጉሥ ሚካኤል ትምህርት ቤት አጠናቀቀ፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱንም እስከ አስረኛ ክፍል ድረስ ደሴ ከተማ በሚገኘው ታሪካዊው ወይዘሮ ስሒን ት/ቤት ተከታለለ፡፡ አስራ አንደኛና አስራ ሁለተኛ ክፍልን ደግሞ የዘመኑ ምርጥ ተማሪዎች መማሪያ በነበረው በአዲስ አበባው በዕደማሪያም ትምህርት ቤት አገባደደ፡፡ በ1958 ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከገባ በኋላም እጅግ የተለየ አብዮታዊ ሆነ፡፡
ዋለልኝ በ1959 በዩኒቨርሲቲው በተደረገው የግጥም ውድድር “ሙት ወቃሽህ መጣው” በሚለው ግጥም አንደኛ ወጥቷል፡፡  በዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ህብረት ይዘጋጅ በነበረው የታገል መጽሔት ከማንም በላይ የነቃ ተሳትፎ ያደርግ ነበር፡፡ በህቡዕ የሚዘጋጁ ጽሑፎችንም እያዘጋጀ ያሰራጭም ነበር፡፡ በተለይ “አዞዎቹ” የሚባለው የስር-ነቀል ለውጥ ደጋፊ የተማሪዎች ስብስብ በአቋም ደረጃ የተስማማባቸውን ሀሳቦች በጽሑፍ እያቀናበረ የሚያዘጋጀው እርሱ እንደነበር በያኔው እንቅስቃሴ የተሳተፉትም ሆነ የዘመኑን ታሪክ ያጠኑ ምሁራን ይመሰክራሉ፡፡
 
   ከዋለልኝ ጽሑፎች መካከል  ዝነኛ የሆኑት ሁለት ናቸው፡፡ አንደኛው ከላይ የጠቀስኩትና ህዳር 10/1961 በታተመው “ታገል መጽሔት” ላይ የወጣው “የብሄረሰቦች ጥያቄ በኢትዮጵያ” የሚል ርዕስ ያለው ጽሑፍ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ በ1962 የተማሪዎች ህብረት ፕሬዚዳንት የነበረው ጥላሁን ግዛው ሲገደል የአጼው ስርዓት በተማሪዎቹ ላይ ያደረገውን ዛቻ በመቃወም “ለአዋጁ አዋጅ” በሚል ርዕስ በህቡዕ ጽፎ የበተነው ጽሑፍ ነው፡፡ ዋለልኝ በጽሑፎቹ ሳቢያ በተደጋጋሚ ጊዜያት ታስሯል፡፡ በተለይ “ለአዋጁ አዋጅ”ን የጻፈው እርሱ መሆኑ ሲታወቅ በችሎት ፊት ቀርቦ አምስት ዓመት እስራት ተፈርዶበታል (ሆኖም ተማሪዎች ባደረጉት ከፍተኛ የተቃውሞ ጫና ከዓመት በኋላ ተፈትቷል)፡፡
     ከ1962 በኋላ ሁለት ክስተቶች የተማሪውን ንቅናቄ አቅጣጫ ቀይረውታል፡፡ እነዚህም በስርዓቱ የሚደረገው አፈና መጠናከር እና የድርጅት ምስረታ ጥያቄ መቀስቀስ ናቸው፡፡ በዚህም መሰረት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንደ ቀድሞው ጊዜ የተቃውሞ ሰልፍ ከማድረግ ይልቅ የጥናት ክበቦችን እየመሰረቱ መወያየቱን መረጡ (የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በተቃውሞ ቀጠሉ)፡፡ ዋለልኝም በውይይት ክበቡ በሚያደርገው ጥናት ላይ አተኮረ፡፡ ከሀገር ተሰደው በአልጄሪያ ከሚገኙት እነ ብርሀነ መስቀል ረዳ ጋር በሚያደርገው የደብዳቤ ልውውጥ አማካኝነትም ሰፊ መሰረት ያለው ድርጅት ለመመስረት በሚደረገው ውይይትም ውስጥ ይሳተፍ ነበር፡፡ ህዳር 29/1964 በውጪ ካሉት ጓደኞቹ ጋር ለመቀላቀል ሲል አውሮፕላን ጠለፈ፡፡ ሆኖም ካሰበው ስፍራ ሳይደርስ በአውሮፕላኑ ውስጥ ተገደለ፡፡
                                                                          *****
     ከያኔው የተማሪዎች ንቅናቄ መሪዎች መካከል ዋለልኝ መኮንን ልዩ የሚያደርገው አንድ ነገር አለ፡፡ ይኸውም የተለያየ አመለካከት ባላቸው የፖለቲካ ድርጅቶች እንደ ታላቅ ሰማዕት የሚታይ መሆኑ ነው፡፡ ደርግ፣ ኢህአፓ፣ ህወሐት፣ ኦነግ፣ ሻዕቢያ፣ መኢሶን፣ ወዘተ… ሁሉም ለርሱ በጎ አመለካከት ነው ያላቸው፡፡ ታዲያ በዋለልኝ ታሪክ ላይ የሚደረገው ሽሚያም በጣም የጠነከረ ነው፡፡ አንዳንዶቹ ታሪኩን ከራሳቸው ድርጅት ጋር ለማቆራኘት ይሞክራሉ፡፡ በወቅቱ የነበረው የርሱና የጓደኞቹ አሰላለፍ ሲገመገም ግን ዋለልኝ ኢህአፓን ከመሰረቱ ወጣቶች ጋር ተመሳሳይ የፖለቲካ መስመር የነበረው ሆኖ ነው የሚታየው፡፡ ኢህአፓን የመሰረቱትም የርሱ የቅርብ ጓደኞች ናቸው፡፡ በመሆኑም ዋለልኝ በህይወት ቢሰነብት ኖሮ የዚሁ ድርጅት አባል ይሆን ነበር ተብሎ ነው የሚገመተው፡፡
                                                                          *****
ዋለልኝ መኮንን ከብዙ በጥቂቱ ይህ ነበር፡፡ ወደፊት ሰፋ ባለ ሁኔታ ስለርሱ እጽፋለሁ ብዬ አስባለሁ፡፡ እናንተም በበኩላችሁ የምታውቁትን እንድታጋሩን በአክብሮት እንጠይቃችኋለን፡፡
——                                                        
ሰላም
አፈንዲ ሙተቂ
ህዳር 29/2006

አዲስ አበባ፣ ህዳር 26፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በውጪ ሃገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በማህበር ተደራጅተው ቤት ለመስራት በተቀረፀው ፕሮግራም መሰረት ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በያሉበት ሃገር ምዝገባ እንደሚጀምር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ከክልሎች ከከተማ መስተዳደሮች ጋር በተደረገው ቅድመ ዝግጅት ላይ የተወያየ ሲሆን፥ የመመሪያ ማውጣት ስራዎችና…

9ኙ ፓርቲዎች በጠሩት ሰላማዊ ሰልፍ በፓርቲ አመራሮች እና የሰልፉ ተሳታፊዎች በፌዴራል ፖሊስ ከፍተኛ ድብደባ የደረሰባቸው ሲሆን በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የታፈሱትና ጨርቆስ ፖፖላሬ እስር ቤት ታስረው የነበሩት የፓርቲ አመራሮች፣ አባላትና የሰላማዊ ሰልፍ ተሳታፊዎች ማዕካለዊ ጥግ ወደሚገኘውና በተለምዶ ሶስተኛ ተብሎ ወደሚጠራው እስር ቤት መዛወራቸው ታወቀ፡፡ ታሳሪዎቹ ከጨርቆስ ፖሊስ ጣቢያ ወደ ሶስተኛ የተዛወሩት ከምሽቱ አንድ ሰዓት በኋላ ሲሆን […]

የፕሮግራም መግለጫ

ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡

የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡

ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡

በይፋ ለሦስት ጊዜያት እንደተገረሰሰ ቢነገርም፥ ዛሬም ቢሆን በሞሪታንያ የባርነት ስርዓት ጭቆና አልተወገደም። የዕድሜያቸውን እኩሌታ በባርነት ቀንበር ሲማቅቁ የነበሩ አንድ ሞሪታኒያዊ ትውስታቸውን ያካፍላሉ። በመካከለኛው አፍሪቃ ሪፐብሊክ የሰፈረው የፈረንሣይ ጦር ሠላም ማስፈን ተስኖታል እየተባለ ነው።

(በአማን ነጸረ) ባለፈው ጽሑፍ እንዳመለከትኩት፡- ሁለት ጽንፍ የያዙ ኃይላት ያገሪቱን የፖለቲካ መድረክ ተቆጣጠረዋል–ያንድነት ኃይላት ነን ባዮችና ብሔረሰባውያን፡፡ የየራሳቸው በጎ ጎን እና መነሻ እንዳላቸው የምረዳ ቢሆንም በጎ በጎውን ላቆየውና የሚያሥከፋኝን ልናገር፡፡ (ባለፈው ጽሑፍ ስለአማራ ልሂቃንና አስተሳሰባቸው ያወሳሁ ሲሆን አሁን ደግሞ የኦሮሞ ልሂቃንን እቃኛለሁ፡፡ 1– ያለፈው ሥርዓት የሕዝብ ለሕዝብ ማኅበራዊ ገጽታ የሌለው ይመስል ስለጭቆና ዘላለም እያወሩ ፖለቲካውን ብቻ ማጮኽ ርካሽነት ነው!!በፖለቲካውም ቢሆን የኃይለሥላሴን ከፊል-ፊውዳል ሥርዓት በመታገል ረገድ እንደ ልሂቅም፤እንደ ማኅበረሰብም በግልና በነጠላ የሰሜኑ ክፍል ያደረገው ጥረት ከኦሮሚያው ያነሰ አይመስለኝም፡፡ትረካው ቢስተካከል!! 2— “ለእኛ እስከተመቸን ድረስ ሌላው ስለ እኛ ፖሊሲ አያገባውም” የሚል አስበርጋጊና በተለይ ሀቀኛ የኦሮሞ ትግልን ሳይቀር ሌላው ማኅበረሰብ በጥርጣሬ እንዲመለከት ማድረግ ለሌላው ስሜት አለመጨነቅ ነው–ራስ ወዳድነት!!ቢቻል ትግላችን ጭቆናውን ለሚያለባብሰው ልሂቅ የሚተርፍ እንዲሆን መስራት፣ካልሆነም መብታችን ላይ የቆመውን ልሂቅ ነጥሎ ብቻውን ማስቀረት ሲቻል በልሂቁ ሰበብ ሕዝብ ማስቀየም ማንንም አይጠቅምም!!መጀመል ይቅር!! 3– ምኒልክ በሰላም እጅ ያልሰጠውን የኦሮሞ ክፍል በኃይል ማስገበሩ ባይካድም በሂደቱ በተፈጠው አብሮነት አድዋ ላይ የውጭ ወራን በጋራ መመከታችንና በዚህም ዛሬ ማንኛውም የኦሮሞ ተወላጅ የትም አገር ቀና ብሎ እየሄደ፣በግንኙነቱ እንደ ነጭና ጥቁር የልዩነት አጥር ሰርተን ሳይሆን በማ/ሰብ ደረጃ እንደ ማንኛውም ኢ/ዊ ርስ በርስ ከመሳፍንቱ ሳይቀር ተጋብተን ተዋደን መኖራችን እየታወቀ፣“የኢ/ያ ታሪክ የ100 አመት ነው” የሚለውን ትረካ በበኩሌ በፍጹም ባልቀበለውም እሱም ቢሆን የጋራ ማንነት ለመገንባት ከበቂ በላይ መሆኑን ባለማስተዋል፣ምኒልክ ሲዘምቱ በአከባቢያዊ ገዥዎች ቅርምት የተያዘች እንጅ አንድ […]

(በፍቃዱ ወ/ገብርኤል) የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ቀን ሲከበር ዘጠነኛ አመቱን የያዘ ሲሆን በአገረ አሜሪካም ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሎምበስ ኦሃዮ ይከበራል። የብሄር ብሄረሰቦች ቀን የሚከበርበት ዋና ዓላማ ለዘመናት ተጨቁነውና ተመዝብረው፤ ተንቀውና ተገልለው በሁለተኛና ሶስተኛ የዜግነት ደረጃ ይታዩ የነበሩትን ብሄር ብሄረሰቦች መብትና ነጻነት ያረጋገጠውን የፌደራል ስርአት ለመዘከርና አጽናኦት ለመስጠት ሲሆን በዚህም በአል ብሄር ብሄረሰቦች በተወካዮቻቸው አማካይነት ራሳቸውን የሚያስተዋውቁበትና ከሌሎች የሚተዋወቁበት፤ ልምዳቸውንና አገራዊ ጉዳዮችን የሚወያዩበት፤ የጋራ እምነታቸውንና ተስፋቸውን የሚጋሩበት የአንድነታቸው የደስታ መግለጫ መድረክ ነው። የኢትዮጵያ ፌደራል ስርአት የህዝቦችን እኩልነት ያረጋገጠና ላለፉት ሁለት አስርተ አመታት ለአገሪቱ አንድነት ሰላም መረጋጋትና እድገት መሰረት የጣለ አዲስ ግኝት ነው። ይህ ህያውና አዳጊ ተመንዳጊ የሆነ የአንድነት መሰረት ዛሬ ኢትዮጵያ በጽናት እንድትቆም ያስቻላት ብቻ ሳይሆን በምታደርገው ፈጣንና ሁለገብ የዕድገት ጎዳና ጉዞ ከምትራመድበት ሁለት እግሮችዋ መካከል የመጀመሪያው ነው። እንደሚታወቀው ሁለተኛው ደግሞ የምትመራበት የልማታዊ መንግስት መርሃ ግብር ነው። የብሄር ብሄረሰብች ቀን ሲታሰብና ሲዘከር የዛሬዋ ኢትዮጵያ የመንፈስና የነፍስ አባት (Founding Father) ከሆነው ከታጋዩ ከመለስ ዜናዊ ጋር ስሙ ሳይጠቅስ የማይታለፈው ዋልልኝ መኮንን ነው። የብሄር ብሄረሰቦች የመብትና የእኩልነትን ጥያቄ በአደባባይ በማስተጋባት የአደባባይ ምስጢርንቱ ተገፎ በኢትዮጵያ የፖሊቲካ መድረክ የመሃል መስመር ስፍራ (main stream politics) እንድሆን ካበቁት ስመ-ጥር የመላው ኢትዮጵያ ህዝቦች ልጆች መሃል ዋለልኝ መኮንን አንዱ ነው። ዋለልኝ መኮንንን የተለየ ቦታ እንዲሰጠው የሚያደረገው የንጉሱን ስርአት ጸረ-ህዝብነትና በህዝቦች ላይ የተጫነውን ‘fake’ የ”ኢትዮጵያዊንትን” ጭንብል በዛ በጭለማ ዘመን በሰላ ብዕሩ በአደባባይ ማራቆቱ […]

ወደ አውሮፓ የሚያስገባውን ቪዛ እና ትኬት ይዞ ከወዳጆቹ ጋር ጉዞውን ለመጀመር ወደ ቦሌ አለም-ዓቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ አቀና። እዚያው እንደደረሰ የተለመደው የፓስፖርትና ትኬት ቁጥጥር ተደረገ። ሁሉም የተሟላ ነበር። ቴዲ ሸኚዎቹን ተሰናብቶ ወደ ውስጥ ጋባ። እለተ ሐሙስ፣ ህዳር 28 ቀን 2007 ዓ.ም.። የአውሮፓው ኮንሰርት በፊንላንድ፣ ሄልሲንኪ ቅዳሜ፤ ህዳር 28 ቀን ይጀምራል። ፊንላንድና አካባቢው ያሉ የቴዲ አድናቂዎች ትኬት […]

የደህንነትና ፖሊሶቹን በመጣስ ህዝቡ ወደ ሰማያዊ ጽ/ቤት እያቀና ነው፡፡

የሰልፉ ተሳታፊዎች ከሚያዋክቡትና በርካቶችን በማሳሰል ከሚታወቁት መካከል አንዱ ደህንነት ፊት ለፊት የሚያየው ነው፡፡ ከእሱ አጠገብ አራቱም ፊታቸውን አዙረው የሚሄዱት ደህንነቶች ናቸው፡፡ሰላማዊ ሰልፉ ሊጀምር ደቂቃዎች ቀርተውታል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት የሚገኘው ህዝብ ከሌሎች ቦታዎች የሚነሱት በመጠባበቅ ላይ ናቸው
Image
ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተላለፈ መልዕክት and update (Read more)

መነሻውን ሰማያዊ ጽ/ቤት የሚያደርገው እንደተጠቀ ሆነ ባለው አፈና እና ወከባ ምክንያት ሰላማዊ ሰልፉን የተለያዩ ቦታዎች ላይ መነሻውን እንዲያደርግ ወስነናል፡፡ እነዚህን የሰልፍ መነሻዎች የምንገልጽ በመሆኑ ህዝቡ በንቃት እንዲከታተል እንገልጻለን! ያለ መስዋዕትነት ድል የለም!
update
ሰላማዊ ሰልፉ በሚነሳበት የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በኩል ወደ መገናኛ እና 22 የሚያሳልፈው መንገድ ተዘግቷል፡፡ ከመስቀል አበባይ፣ ፒያሳ፣ አራት ኪሎ በካሳንቺስ አድርጎ የሰማያዊ ፓርቲ የሚገኝበት እንደራሴ በኩል ወደ 22 እና መገናኛ የሚያስኬደው መንገድ ተዘግቷል፡፡
update
በየ ክፍለ ሀገሩ የሚገኙ የ9ኙ ፓርቲዎች አመራሮችና አባላት አዲስ አበባ የሚገኘውን ዝግጅት እየተቀላቀሉ ነው፡፡
ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተላለፈ መልዕክት!

ከሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት የሚነሳው ሰላማዊ ሰልፍ እንደተጠበቀ ሆኖ ለመስቀል አደባባይ ቅርብ የሆኑ10 ቦታዎች ላይ ሰልፉን ለማድረግ ዝግጁቱ ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን ከደቂቃዎች በኋላ እንደሚጀምር በየቦታው ካሉ አስተባባሪዎች መረጃ ደርሶናል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ ሰላማዊ ሰልፍ ይደረግባቸዋል በተባሉ መሰመሮች የሚሰሩ ታክሲዎች በግዳጅ በሌሎች ቦታዎች እንዲሰማሩ እየተደረገ እንደሆነ ታውቋል፡፡

ኀዳር ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤትን ከበው ካደሩ በሁዋላ የተወሰኑ ወጣቶችን እየለቀሙ በማሰር የተቃውሞ ሰልፉን ለማደናቀፍ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ነው። የነገረ ኢትዮጵያ ምክትል ዋና አዘጋጅ በላይ ማናየ፣ የሰማያዊ ፓርቲ የወጣቶች ጉዳይ ምክትል ሃላፊ እና የብሄራዊ ምክር ቤት ጸሃፊ ወጣት ሳሙኤል አበበ፣ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ አባል …

ኀዳር ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ያቀረቡ የከንባታ ጠንባሮ ነዋሪዎች ህዳር 26/2007 ዓም በዱራሜ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። የከምባታ ህዝብ ኮንግረንስ ሊቀመንበር አቶ ኤርጨፎ ኤርዴሎ እንደተናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች ለኮሌጅ መስሪያ ተብሎ የተፈቀደውን ቦታ የመንግስት ሹማማምንት  ለዘመዶቻቸው አከፋፍለው በመገኘታቸው እንዲሁም ከሾኔ እስከ ዳውሮ ያለውን አስፋልት ለማድረግ ታቅዶ በለመሳካቱ ህዝቡ ተቃውሞውን …

ኀዳር ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለስልጣኑ አሳታሚዎች ዓመታዊ የንግድ ፈቃዳቸውን ለማሳደስ ወደንግድ ሚኒስቴር ሲሄዱ በየዓመቱ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ እንዲያቀርቡ የሚገደዱ ሲሆን የሙያ ብቃቱን ለማግኘት ባለፉት ወራት ወደብሮድካስት ባለሰልጣን የሄዱ አሳታሚዎች ያልጠበቁትን ግዴታ እነዲገቡ የሚቃወሙ ከሆነ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሠርተፊኬት እንደማይሰጣቸው በተነገራቸው መሠረት አብዛኛዎቹ ተገደው ፈርመዋል፡፡ በንግድ ምዝገባ ፈቃድ መስጫ መደብ ቁጥር 89 …

የፕሮግራም መግለጫ

ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡

የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡

ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡



(አፈንዲ ሙተቂ)
——
  በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ላይ ነው፡፡ በታላቋ ብሪታኒያ ዋና ከተማ፡፡ በጊዜው አንድን አስገራሚ ገጸ-ባህሪ ያማከለ ተከታታይ የምርመራ ልብ ወለድ የሚጽፍ ወጣት ደራሲ ነበር፡፡፡ ታዲያ ይህ ደራሲ በዚያ ገጸ-ባህሪው ላይ ለአስር ዓመታት ከጻፈ በኋላ “ኤጭ! ይሄ ሰውዬ አሁንስ እጅ እጅ አለኝ፡፡ ስራ አስፈታኝ እኮ አቦ!… ከዚህ በኋላ ገድዬው ልረፍና ሌላ ድርሰት ልጻፍ” በማለት እራሱ የፈጠረውን ገጸ ባህሪ ይገድለዋል፡፡
 
     ይሁንና ገጸ-ባህሪውን የገደለው ደራሲ እንደተመኘው ሌሎች ድርሰቶችን በሰላም ሊጽፍ አልቻለም፡፡ ሺህ ምንተሺህ ደብዳቤዎች ከየአቅጣጨው ጎረፉለት፡፡ “አንተ ቀፋፊ፣ የማትረባ ወስላታ፣ አረመኔ ነህ” እየተባለ ተወቀሰ፤ ተወገዘ፡፡  “እኛ የምንወደውን ሰውዬ ገድለህ በሰላም መኖር አትችልም! አንተም ዋጋህን ታገኛታለህ” የሚሉ ማስፈራሪያዎችም እየተከታተሉ ደረሱት፡፡ በማስከተልም በሺህ የሚቆጠሩ አንባቢያን በለንደን ጎዳናዎች ላይ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ደራሲው የገደለውን ገጸ-ባህሪ ከሞት እንዲያስነሳው ጠየቁት፡፡
  ደራሲው በዚህ ጉዳይ ተጨነቀ፡፡ ተጠበበ፡፡ የህዝቡን ፍላጎት ካላሟላ አደጋ ሊከተለው እንደሚችል ገመተ፡፡ ስለዚህ ሳይፈልግ በግዴታ በራሱ ብዕር የገደለውን ገጸ-ባህሪ ነፍስ ዘርቶበት እንደገና ወደ ስነ-ጽሑፍ ዓለም መለሰው፡፡ ህዝቡም የተመኘውን በማግኘቱ “እፎይ!” አለ፡፡
                                                     *****
  ያ ሰላማዊ ሰልፍ የተወጣለት ገጸ-ባህሪ “ሼርሎክ ሆምዝ” (Sherlock Holmes) ይባላል፡፡ በስነ-ጽሑፍ ዓለም ምንጊዜም ከማይረሱ ልዩ ገጸ-ባህሪያት አንዱ ነው፡፡ ሼርሎክ ሆምዝ የግል ወንጀል መርማሪ ነው፡፡ የመንግሥት ባለስልጣናትም ሆኑ ግለሰቦች አዕምሮአቸውን ያስጨነቀ ወንጀል-ነክ ጉዳይ ሲያጋጥማቸው ወደ ቢሮው እየሄዱ ጉዳያቸውን ያዋዩታል፡፡ እርሱም ልዩ ልዩ ፍንጮችን እየተከተለ ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ ውጤቱን ለባለጉዳዮቹ ያሳውቃል፡፡ በዚህም መሰረት ወንጀሉ ተፈጽሞ ከሆነ ወንጀለኛው ርቆ ሳይሄድ በቁጥጥር ስር እንዲውል ይደረጋል፡፡ ወንጀሉ ወደፊት ሊፈጸም የታቀደ ከሆነ ደግሞ ሼርሎክ ሆምዝ ወንጀሉ ከመፈጸሙ በፊት ወንጀለኛውን በቁጥጥር ስር ያውለውና ከነማስረጃው ለፖሊስ ያስረክባል፡፡
  ታዲያ ሸርሎክ ሆምዝ የሚፈጽማቸውን ጀብዱዎች የምንሰማው ከርሱ አንደበት አይደለም፡፡ የዕለት ተዕለት ውሎውን እየተከታተለ ለኛ የሚዘግብልን ዶ/ር ጆን ኤች ዋትሰን የሚባል ጓደኛው ነው፡፡ ዶ/ር ዋትሰን የሼርሎክ ሆምዝ የልብ ጓደኛ እና ሚስጢረኛው ነው፡፡ ሁለቱ ሰዎች ለብዙ ጊዜ አይለያዩም፡፡ አንድ ልዩ ኦፕሬሽን የሚካሄድ ከሆነ ሼርሎክ ሆምዝ ጓደኛው ዶ/ር ዋትሰን እንዲሳተፍበት ያደርጋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ዋትሰን ከሎንዶን ወደ አውሮጳ እየተላከ ሼርሎክ ሆምዝ የሚፈልጋቸውን መረጃዎች እንዲያሰባስብ ይደረጋል፡፡
 
    በዶ/ር ዋትሰን ገለጻ መሰረት ሼርሎክ ሆምዝ ቀጠን ዘለግ ያለ እንግሊዛዊ ነው፡፡ ቢሮው በደቡብ ለንደን በሚገኘው የቤከር ጎዳና ነው፡፡ አንዲት የነተበች ባርኔጣ ይለብሳል፡፡ አጭር ከዘራም ከእጁ አያጣም፡፡ ሼርሎክ ሆምዝ በጣም አጫሽ ነው፡፡ ፒፓውን ከአፉ የማይነጥል የትምባሆ ሱሰኛ! ደግሞ ግማሽ ጭልፋ የምታክል ሌንስ (አጉሊ መነጽር) ከኪሱ አትጠፋም፡፡ በርሷ ብዙ ነገሮችን ይመረምራል፡፡ በተለይም የሰው ዱካ የሚመረምረው በዚህች ሌንስ ነው፡፡ 
 
    የሼርሎክ ሆምዝ ወንጀል መርማሪነት እንዲህ ቀለል ያለ አይደለም፡፡ ኬሚካሎችንና ቅመማ ቅመሞችን በደንብ ለይቶ ያውቃል፡፡ የሲጋራዎችን አመድ በማየት ብቻ አንድ ሰው ምን ዓይነት ሲጋራ እንደሚያጨስ ለይቶ ያውቃል፡፡ ደግሞም ሼርሎክ ሆምዝ የጁዶ ጥበበኛ ነው፡፡ ወንጀለኞች ሊያጠቁት ከመጡ በጁዶ ይዘርራቸዋል፡፡ በመላው ለንደን በርካታ ሰላዮች አሉት፡፡ ሊስትሮዎች፣ ለማኞች፣ ጎዳና ተዳዳሪዎች፣ ሴተኛ አዳሪዎች፣ የባንክ ሰራተኞች ወዘተ… ልዩ ልዩ መረጃዎች እንዲያመጡለት ይቀጥራቸዋል፡፡ ከነዚህ ምንጮች በሚያገኛቸው መረጃዎች ላይ የራሱን የምርመራ ጥበብ እያከለ አስደናቂ ውጤቶችን ያገኛል፡፡
                                                     *****
    ሼርሎክ ሆምዝን የፈጠረው ደራሲ ሰር አርተር ኮናን ዶይል ይባላል፡፡ በዓለም የስነ-ጽሑፍ ታሪክ ዘወትር ከሚታወሱ ድንቅ ደራሲዎች አንዱ ነው፡፡ ኮናን ዶይል የስኮትላንድ ተወላጅ ነው፡፡ በጉርምስናው ዕድሜ ላይ ህክምናን ሊያጠና ኤዲንበርግ ዩኒቨርሲቲ ይገባል፡፡ ታዲያ እዚያ እያለ ፕሮፌሰር ጆሴፍ ቤል ከሚባሉት አስተማሪው ላይ ባየው ነገር በጣም ይመሰጣል፡፡ እኝህ ፕሮፌሰር ሀኪም ጭምር ናቸው፡፡ የህመምተኞችን በሽታ በትክክል ለማወቅ የሚጠቀሙበት የተጠየቅ (logic) አካሄድና ጥቃቅን የሆነችውን ነገር ሁሉ ለማወቅ የሚያደርጉት ጥረት በወጣቱ ተማሪ አርተር ኮናን ዶይል ላይ የማይረሳ ትውስታ ጥሎ ያልፋል፡፡
   
  ኮናን ዶይል ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ የራሱን ክሊኒክ ከፍቶ መስራት ይጀምራል፡፡ ነገር ግን ጀማሪ በመሆኑ የሚመጣለት በሽተኛ በጣም ትንሽ ነበር፡፡ ታዲያ ኮናን ዶይል አልሰነፈም፡፡ የመጡለትን በሽተኞች ካከመ በኋላ በሚኖረው ትርፍ ጊዜ ቁም-ነገር ለመስራት ወሰነ፡፡  በመሆኑም የዩኒቨርሲቲ አስተማሪውን ሁኔታ እያሰበ የሚመጣለትን ሃሳብ በወረቅ ጫር ጫር ማድረግ ጀመረ፡፡ የጻፈውንም The Study in the Scarlet የሚል ርዕስ ሰጠውና Beeton’s Christmas Annual  በተሰኘ መጽሔት ላይ አሳተመው፡፡
     ጽሑፉ “ሼርሎክ ሆምዝ” የተባለ ወንጀል መርማሪ በአስገራሚ የተጠየቅ ዘዴ ወንጀሎችን እንዴት እንደሚመረምር የሚተርክ አጭር ልብ ወለድ ነው፡፡ አንባቢያን ጽሑፉን ስለወደዱት The Strand የሚባል መጽሔት በቋሚነት የሼርሎክ ሆምዝን ታሪክ እንዲጽፍለት ቀጠረው፡፡ ደራሲው ኮናን ዶይልም ለአምስት ዓመታት ያለመሰልቸት የሼርሎክ ሆምዝን ታሪክ ጻፈ፡፡ በአምስተኛው ዓመት በታተመው አንድ ጽሑፍ ላይ ግን “ሼርሎክ ሆምዝ ሌሎች የልብ ወለድ ስራዎችን እንዳልጽፍ እያደረገኝ ነው” በማለት ገድሎት ሊገላገለው ወሰነ፡፡ The Final Problem የሚል ርዕስ የተሰጠው አጭር ልብ ወለድ ጻፈና ሼርሎክ ሆምዝን  በብዕሩ ገደለው፡፡ ደራሲው እንዲህ ሲያደርግ “ሼርሎክ ሆምዝ ሞቷል፤ ከእንግዲህ ታሪኩን አትጠብቁ” ማለቱ ነው፡፡
    ይሁንና ከላይ እንደገለጽኩት ህዝቡ በጄ አላለውም፡፡ “ሼርሎክ ሆምዝን ገድለህ አንተም በሰላም አትኖራትም!” በማለት ማስጠንቀቂያና ዛቻ ላከለት፡፡ ከዚህ ሌላም  ሃያ ሺህ የስትራንድ መጽሄት ቋሚ ደንበኞች (Subscribers) ደንበኝነታቸውን አቋረጡ፡፡ የእንግሊዝ ንጉሣዊያን ቤተሰብ ንዴቱንና ብስጭቱን ለደራሲው ገለጸለት፡፡ የስትራንድ መጽሔት አዘጋጅ ኮናን ዶይልን ክሊኒኩ ድረስ ሄዶ ለመነው፡፡ “መጽሔታችን በኪሳራ ሊዘጋ ነው፤ ያ እንዳይሆን እባክህ ሼርሎክ ሆምዝን ከሞት ቀስቅሰውና ታሪኩን ጻፍልን” አለው፡፡
   ኮናን ዶይል የመጽሔቱ አዘጋጅ ቢሮው ድረስ ሲመጣበት ይሉኝታ ያዘውና “እምቢ!” ማለት አቃተው፡፡ ስለዚህ በዘዴ ላባርረው በማለት “በወር ሃያ አምስት ፓውንድ የምትከፍሉኝ ከሆነ እጽፋለሁ” በማለት በዘመኑ ተሰምቶ የማይታወቅ ከፍተኛ ክፍያ ጠየቀ፡፡ የስትራንድ መጽሔት አዘጋጅ “አሳምሬ እከፍላለሁ! አንተ ብቻ ጻፍልኝ እንጂ” አለው፡፡ ኮናን ዶይል ከዚያ በፊትም ከህዝቡ የመጣበትን ዛቻ ፈርቶ ሼርሎክ ሆምዝን ሊቀሰቅሰው ወስኖ ስለነበረ የስትራንድ መጽሔት አዘጋጅ ክፍያውን ሲጨምርበት አዲስ ጉልበት አገኘ፡፡ በመሆኑም ሼርሎክ ሆምዝን ከሞት ሊያስነሳው ወሰነ፡፡ እናም “The Adventure of the Empty House” የሚል ርዕስ የሰጠውን ልብ ወለድ ጻፈና ዝነኛውን ገጸ-ባህሪ እንደገና ከሞት ቀሰቀሰው፡፡ አንባቢዎቹም ሼርሎክ ሆምዝ አለመሞቱን ሲረዱ በደስታ ፈነደቁ፡፡
      ታዲያ ኮናን ዶይል ሼርሎክ ሆምዝን የቀሰቀሰው እንዴት መሰላችሁ?….. ጓደኛው ዶ/ር ዋትሰን ቢሮው ውስጥ ሆኖ ሲተክዝ ቆፍጣናው ሼርሎክ ሆምዝ በድንገት ወደ ቢሮው ይገባል፡፡ ዋትሰን ዐይኑን ማመን አቃተው፡፡ ካለበት በደስታ ተነስቶ አቀፈው፡፡ ከናፍቆት ሰላምታ በኋላ ዋትሰን “ሞተሃል ተብሎ አልነበረም እንዴ?…” ይለዋል፡፡ ሼርሎክ ሆምዝም “ሆን ብዬ ያስወራሁት ወሬ ነው፡፡ በጋዜጣም ማስታወቂያ እንዲነገር ያደረግኩት እኔ ነኝ፡፡ አየህ! አንድ የምከታተለው አደገኛ ወንጀለኛ አለ፡፡ ያ ወንጀለኛ አልያዝ ብሎ አስቸግሮኛል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዱካው ጠፍቶብኝ ነበር፡፡ ስለዚህ መሞቴን በጋዜጣ አሳወቅኩ፡፡ እንደዚያ ያደረግኩት ወንጀለኛው መሞቴን ሲረዳ ከተደበቀበት እንደሚወጣ ስለማውቅ ነው” በማለት ትረካውን ይጀምርለታል፡፡ ከዚያም ዝርዝሩን አንድ በአንድ ለዶክተር ዋትሰን ያጫውተዋል፡፡ ከዚያች አጭር ልብ ወለድ በኋላም ሼርሎክ ሆምዝ እንደ አዲስ መነበብ ይጀምራል፡፡
                                                      *****
    አርተር ኮናን ዶይል የሼርሎክ ሆምዝን ድንቅ ምርመራዎች የሚተርኩ 56 አጫጭር ታሪኮችንና አራት ሙሉ ልብ ወለዶችን ጽፏል፡፡ እርሱ ከሞተ በኋላ ደግሞ ሼርሎክ ሆምዝ በሺህ በሚቆጠሩ ፊልሞች፣ ቲያትሮችና ልዩ ልዩ የጽሑፍ ውጤቶች ውስጥ ለጥበብ ታዳሚዎች ቀርቧል፡፡ በዓለም ዙሪያ በርካታ የሼርሎክ ሆምዝ ቡድኖች አሉ፡፡ በለንደን ከተማ በየዓመቱ ሁለት ጊዜ የሼርሎክ ሆምዝ ፌስቲቫል ይካሄዳል፡፡ ከዚህም በላይ ደግሞ በሺህ የሚቆጠሩ ቱሪስቶች ሼርሎክ ሆምዝ ይኖርበታል ተብሎ የተጠቀሰውንና በቤከር ጎዳና የሚገኘውን የቤት ቁጥሩ 212B የሆነውን ህንጻ በየዓመቱ ይጎበኙታል፡፡ በህንጻው ውስጥ በሼርሎክ ሆምዝ አምሳል የተሰራ አዳፋ ኮፍያ የያዘ፣ ከዘራ ያነገተና ፒፓውን በአፉ የጎረሰ አርቲፊሻል ሰው ቆሞበታል፡፡
 
  ይህ ሁሉ ክብርና ፍቅር የሚሰጠው በምናብ ለተፈጠረ ገጸ-ባህሪ ነው፡፡ ክላሲክ የሚባሉት ጸሐፍት እንደ ሼርሎክ ሆምዝ ያሉትን ከሰው ልብ የማይጠፉ ልዩ ገጸ-ባህሪያትን የመፍጠር ብቃት ነበራቸው፡፡ ዣንቫልዣ፣ ዶን ኪኾቴ፣ አንክል ቶም፣ ራስኩልኒኮቭ፣ ሐምሌት፣ ኦቴሎ፣ ወዘተ የመሳሰሉ ገጸ-ባህሪያትን የሚያውቁ የስነ-ጽሑፍ አፍቃሪዎች ሼርሎክ ሆምዝንም ዘወትር ያስታውሱታል፡፡ እኛም ዘወትር እናስታውሰለዋን፡፡
ሰላም!
  —-
መጋቢት 26/2006
አፈንዲ ሙተቂ

በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ «አዲስ ሾፒንግ ፌስቲቫል» የተባለ ፌስቲቫል አዲስ አበባ ውስጥ በማካሄድ ላይ ይገኛል። ስለ ፌስቲቫሉ ምንነት እና ይዘት በዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት እንቃኛለን።

የደቡብ አፍሪቃዉ የነፃነት ታጋይና የሰላም ኖቤል ተሸላሚ ኔልሰን ማንዴላ ልክ በዛሬዋ ቀን የዛሬ ዓመት ነበር ላይመለሱ ይህችን ዓለም የተሰናበቷት። በአንደኛ የሙት ዓመታቸዉ ዛሪ ታድያ የሀገሪቱ ነዋሪ ከዳር እስከ ዳር በቩቩዜላ ጡሩምባ፤ የፖሊስ እና የቀይ መስቀል ጡሩምባን በማስጮኽ ለስድስት ደቂቃ አስተጋብቶላቸዋል፤ አስቦአቸዋልም።

10ኛው ዓለም አቀፍ የአፍሪቃ መገናኛ ብዙኀን ጉባዔ፣ ትናንት ጧት አዲስ አበባ ውስጥ ተጀምሮ ማምሻውን ተደምድሟል ።ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ የአፍሪቃ አገሮች የተውጣጡ ጋዜጠኞች በተሳተፉበት ጉባዔ የመነጋገሪያ አጀንዳው ኢቦላነበረ። አፍሪቃውያን ጋዜጠኞች