የአንድነት ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ የተወሰደውን የሀይል እርምጃ እንደሚያወግዙ ገለፁ!! ምርጫ 2007 የኢህአዴግ መጨረሻ ወይስ የመጨረሻው መጀ መሪያ››በሚል ርዕስ የክርክር መድረክ ተካሔደ!!

በአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት እየተካሔደ በሚገኘው የክርክር መድረክ ላይ ተሳታፊ የሆኑ የአንድነት ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በትላንትናው እለት የ9ኙ ፓርቲዎች ህብረት የጠራውን የ24 ሰዓት ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ የመንግስት ሀይሎች የወሰዱትን ኢ-ህገመንግስታዊ እርምጃ አጥብቀው እንደሚያወግዙ ገልፀዋል፡፡

በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የወጣቶች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ‹‹ምርጫ 2007 የኢህአዴግ መጨረሻ ወይስ የመጨረሻው መጀሪያ››በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ክርክር በትዝጋጅው ፕሮግራም መሰረት ተካሂዱዋል፡፡ በክርክሩ ወጣት ጋዜጠኛ ስለሺ ሀጎስ ‹‹ምርጫ 2007 የኢህአዴግ መጨረሻ ››መሆን አለበት በሚል መከራከሪያ ሀሳቡን ያቀረበ ሲሆን የአንድነት ፓርቲ የወጣቶች ጉዳይ ሀላፊ ወጣት እንግዳ ወ/ጻዲቅ በበኩሉ ‹‹2007 ለኢህአዴግ የመጨረሻው መጀመሪያ ››መሆን አለበት በሚል ሀሳቡን አቅርቧል ፡፡ሁለቱም ተከራካሪዎች የክርክር ሀሳባቸውን ካቀረቡ በኋላ ከተሳታፊዎች የቀረቡላቸውን ጥያቄዎች አብራርተዋል፡፡ስለ ክርክሩ ዓላማና አስፈላጊነት የአንድነት ፓርቲን የህዝብ ግንኙነት ተጠባባቂ ሀላፊን ጠይቀን በሰጡን ምላሽ መሰረት፤ በፓርቲውና በህዝቡ መካከል የበለጠ መቀራረብ ለመፍጠርና በ2007 ግንቦት ለሚካሄደው ምርጫ ለምዳርገው ዘመቻ ህዝቡ በባለቤትነት የበኩሉን እንዲወጣ ለማድረግ እንደ ድልድይነት እንደሚጠቅምና በቀጣይ በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ ታላቅ ከተሞች በሀገሪቱ የሚገኙ ምሁራንን ያሳተፈና ህዝብ የሚሳተፍባቸው የክርክር መድረኮች እንደሚደረጉና ምርጫውን ህዝቡ በባለቤትነት እንዲቆጣጠረው ለማድረግ እንሰራለን››ብለዋል ፡፡

የክርክር ፕሮግራሙ በካናዳና በሰሜን አሜሪካ ለሚገኙ ፓልቶኮች በቀጥታ ስርጭት እንደተላለፈ እና በቀጣይ የሚደረጉ ክርክሮች በሀገር ውስጥ የሚገኙ ዜጎች የሚከታተሉበትን ሁኔታ ለመፍጠር እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡10426788_385236038307420_3109276557410593195_n

10670283_385236261640731_4430313618067441244_n

10848026_385236068307417_6174878508600898469_n

10848056_385236334974057_5907258866147503741_n