ያስጠበቡኝ ጠባብ የኦሮሞ ልሂቃንና ያስጠበበኝ አመለካከታቸው
(በአማን ነጸረ) ባለፈው ጽሑፍ እንዳመለከትኩት፡- ሁለት ጽንፍ የያዙ ኃይላት ያገሪቱን የፖለቲካ መድረክ ተቆጣጠረዋል–ያንድነት ኃይላት ነን ባዮችና ብሔረሰባውያን፡፡ የየራሳቸው በጎ ጎን እና መነሻ እንዳላቸው የምረዳ ቢሆንም በጎ በጎውን ላቆየውና የሚያሥከፋኝን ልናገር፡፡ (ባለፈው ጽሑፍ ስለአማራ ልሂቃንና አስተሳሰባቸው ያወሳሁ ሲሆን አሁን ደግሞ የኦሮሞ ልሂቃንን እቃኛለሁ፡፡ 1– ያለፈው ሥርዓት የሕዝብ ለሕዝብ ማኅበራዊ ገጽታ የሌለው ይመስል ስለጭቆና ዘላለም እያወሩ ፖለቲካውን ብቻ ማጮኽ ርካሽነት ነው!!በፖለቲካውም ቢሆን የኃይለሥላሴን ከፊል-ፊውዳል ሥርዓት በመታገል ረገድ እንደ ልሂቅም፤እንደ ማኅበረሰብም በግልና በነጠላ የሰሜኑ ክፍል ያደረገው ጥረት ከኦሮሚያው ያነሰ አይመስለኝም፡፡ትረካው ቢስተካከል!! 2— “ለእኛ እስከተመቸን ድረስ ሌላው ስለ እኛ ፖሊሲ አያገባውም” የሚል አስበርጋጊና በተለይ ሀቀኛ የኦሮሞ ትግልን ሳይቀር ሌላው ማኅበረሰብ በጥርጣሬ እንዲመለከት ማድረግ ለሌላው ስሜት አለመጨነቅ ነው–ራስ ወዳድነት!!ቢቻል ትግላችን ጭቆናውን ለሚያለባብሰው ልሂቅ የሚተርፍ እንዲሆን መስራት፣ካልሆነም መብታችን ላይ የቆመውን ልሂቅ ነጥሎ ብቻውን ማስቀረት ሲቻል በልሂቁ ሰበብ ሕዝብ ማስቀየም ማንንም አይጠቅምም!!መጀመል ይቅር!! 3– ምኒልክ በሰላም እጅ ያልሰጠውን የኦሮሞ ክፍል በኃይል ማስገበሩ ባይካድም በሂደቱ በተፈጠው አብሮነት አድዋ ላይ የውጭ ወራን በጋራ መመከታችንና በዚህም ዛሬ ማንኛውም የኦሮሞ ተወላጅ የትም አገር ቀና ብሎ እየሄደ፣በግንኙነቱ እንደ ነጭና ጥቁር የልዩነት አጥር ሰርተን ሳይሆን በማ/ሰብ ደረጃ እንደ ማንኛውም ኢ/ዊ ርስ በርስ ከመሳፍንቱ ሳይቀር ተጋብተን ተዋደን መኖራችን እየታወቀ፣“የኢ/ያ ታሪክ የ100 አመት ነው” የሚለውን ትረካ በበኩሌ በፍጹም ባልቀበለውም እሱም ቢሆን የጋራ ማንነት ለመገንባት ከበቂ በላይ መሆኑን ባለማስተዋል፣ምኒልክ ሲዘምቱ በአከባቢያዊ ገዥዎች ቅርምት የተያዘች እንጅ አንድ […]