á¨á ááľááľ á°ááá˝ á á°á´á á ááá°á á°áŤááą – ááá 15, 2013
UDJ Demonstrations in Dessie and Gondar
UDJ Demonstrations in Dessie and Gondar
የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅን መዝጋት ታሪክን ማጥፋት/ማበላሸት ነው! የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ችግራችንን ይመልከት! ልጆቹን የማይጠይቅ አባት አለን? ሙስናንና ኑፋቄን የሚያደቅ ክንድ አለን! የምንማረው በምእመናን ብር ነው፡፡ ሌቦች ሆይ፣ እጃችኹ ይሰብሰብ! ጢሞቴዎስ ሆይ፣ አደራህን ጠብቅ፡፡ (፩ኛጢሞ. ፬÷፳) ችግራችንን የሚሰማንና መፍትሔ የሚሰጠን አባት ዐጣን! የቅ/ሲኖዶሱ አባላት ትኩረት ይስጡን! ሙስናን በቃል ሳይኾን በተግባር እንዋጋ! ተማሪዎች ሙስናን በመዋጋታቸው […]![]()
News, Radio Magazine or Mestawot
ሐምሌ 7 ቀን 2005 ዓ.ም የአንድነትን የምስጋና መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ !
ሐምሌ 7 ቀን 2005 ዓ.ም የጎንደር ከተማ የገዢዉ ፓርቲ ካድሬዎችን ታላቅ አሳፋሪ አፈና ጥሶ በመሄድ ድምጹ በታላቅ ጀግንነት አሳምቷል። የአንድነት ድህረ ገጽ ላይ የወጣ በኦዶዮ የታጀበ ዝርዝር ሸገባ እንደ እንደሚከተለዉ አቅርበናል። እዚህ ይጫኑ !
አንድ ቢሊዮን ገደማ ህዝብ ባለው ክፍለ ዓለም 54 አባል ሃገራትን ያቀፈውና ዘንድሮ 50 ኛ ዓመቱን በማክበር ላይ የሚገኘው የአፍሪቃ ኅብረት በየጊዜው በሚከሠቱ የአህጉሩ ችግሮች መፈተኑ አልቀረም ። የኅብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ወይዘሮ እንኮሳዛና ድላማኒ
ክልሉ የፍትሕና ጸጥታ ዘርፍ እንዲሁም የፖሊስ ሓላፊዎች ለሁከት ፈጣሪዎቹ ወግነዋል![]()
ደቀ መዛሙርቱ ለሦስተኛ ተከታታይ ቀን የኮሌጁን የምግብ ቤት አገልግሎት ተከልክለዋል የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ደቀ መዛሙርቱ ወደ ክረምት ዕረፍት ከመሄዳቸው በፊት የማጠቃለያ ፈተና እንዲወስዱና ተመራቂዎቹ እንዲሸኙ ጥረት እያደረገ ነው፤ በፓትርያሪኩ የመወሰን አቅም ላይ ጥርጣሬ የገባቸው የሚኒስቴሩ ሓላፊዎች ልዩ ጽ/ቤቱ ደቀ መዛሙርቱን በኀይል ከኮሌጁ ለማስወጣት ያቀረበውን የድጋፍ ጥያቄ ውድቅ ባደረጉበት አቋማቸው ጸንተዋል ፓትርያሪኩ በሚይዟቸው አቋሞች ረዳት ሊቀ ጳጳሱ …![]()
የነገው አበባ ለምን ለፌደራል ፖሊስ ይሰጣል? ዳዊት ሰለሞን (ፍኖት ዘጋቢ) ሐምሌ 6 ቀን 2005 ዓ.ም አበባ የሰው ልጆች በአንድ ድምጽ «ፍቅራችንን ወክልልን» በማለት የመረጡት ይመስል የፍቅርን አደራ ተሸክሟል፡፡ከሶስተኛው አለም እስከ አንደኛው የሚገኙ የአዳም ልጆች «አበባን» የፍቅር ስጦታ በማድረግ ለሚወዱት ይቸሩታል፡፡የሚወዱት ሲሞትባቸውም ፍቅራቸውን ለሟቹ ለመግለጽ አስከሬኑ ላይ አበባ ያኖሩለታል፡፡ ወደ ደሴና ጎንደር እንምጣ፣ ነገ ከሌላው ጊዜ […]
ሐምሌ 6 ቀን 2005 ዓ.ም “ህገ መንግስት ተጥሷል !” ካልክ ድምጽህን በሰላማዊ ተቃውሞ አሰማ ! ይድረስ ትናንተም ሆነ ዛሬ ግፍ በነገሰባት ምድር፣ ኑሮን በመከራ ለምትገፋው ወገኔ ! ይድረስ መልካም አስተዳደር ጠፍቶ በደል ለተጫነብህ ፣ ፍትህ ርትዕ ተዛብቶ የአስተዳደር ሚዛኑ ኑሮህን ላጨለመው ወገኔ ! ይድረስ ከዲስኩር ባላለፈ “የእድገት ስላጣኔ መንገድ እየተጓዝክ ነው ” ለሚሉህ ፣ ይድረስ […]
ሐምሌ 6 ቀን 2005 ዓ.ም በደሴ አካባቢ ከሚገኙ ከተሞች(ከወረባቡና ሐይቅ)፣ በነገው የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ለመገኘት ወደ ከተማይቱ ለመምጣት ትራንስፖርት ያስፈልጋቸው የነበሩ ዜጎች፣ በከተማው አስተዳደር ስውር ትዕዛዝ መሰረት፣ ከዛሬ ምሽት ጀምሮ የትራንስፖርት መኪኖቹ ከአገልግሎት ውጪ እንዲሆኑ መታዘዛቸውን የየአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ለሰልፉ አዘጋጆች በመደወል እየገለጹ ነው፡፡ ሁኔታው ያሳዘናቸው ሰዎች በቻሉት መንገድ ሁሉ ወደ ሰልፉ […]
News, Call-in show or special interviews and Ye Musica Qana
ሐምሌ 6 ቀን 2005 ዓ.ም “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” የሚል መሪ ቃል በማንገብ ዕሁድ በሚካሄደዉ ህዝባዊ የተቃዉሞ ሰልፍ ላይ ሁሉም ተሳታፊ የሚከተሉትን ተግባራት ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ 1. ሰልፉን ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ማካሄድ፡፡ የተለያዩ ትንኮሳዎች ቢፈታተኑንም እንኳን ሰልፉ ስነ-ስርዓቱን በጠበቀ እና ጨዋነት በተሞላበት መልኩ ማካሄድ ይገባል፡፡ አንድ ጠጠር እንኳን ፍፁም መወርወር የለበትም፡፡ 2. የተመረጡ መፈክሮችን ብቻ […]
ሐምሌ 6 ቀን 2005 ዓ.ም የአገዛዙ ካድሬዎች ላለፉት በርካታ ሳምንታት የአንድነት ፓርቲ እያደረገ ያለዉን ሰላማዊና ሕዝባዊ ቅስቃሳ ከግቡ እንዳይደርስ ለማድረግ፣ በአለቆቻቸው ታዘው የተለያዩ የአፈና እንቅስቃሴዎችን ሲያደርጉ እንደነበረ በሰፊት ተዘግቧል። በርካታ ታሰረዋል፤ ወከባና እንግልትም ደርሶባቸዋል። ነገር ግን የአንድነት አባላትን ደጋፊዎች እንደዉም ሕዝቡ እግዚአብሄር የሰጣቸውን የዜግነት መብት ለማረጋገጥ ቀርተዉ የተነሱ ይመስላል። አፈናዉ የበለጠ እየጨመረ በመጣ ቁጥር የሕዝቡን […]
ሐምሌ 7 በጎንደርና በደሴ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተሳተፉ!! ድምፃችሁንም በአደባባይ አሰሙ!! ————————————————————– ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ ————————————————————– ፓርቲያችን አንድነት ህጋዊና ሰላማዊ መንገድ የሚታገል ፓርቲ በመሆኑ የሚያደርጋቸውን ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ኃላፊነት በተሞላበት ህጋዊ አግባብ ሲተገብር ቆይቷል፡፡ ፓርቲያችን “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት/Millions of voices for freedom” በሚል መሪ ቃል የጀመረውም ህዝባዊ ንቅናቄ የህዝባችንን መሰረታዊ ጥያቄዎችን ያነገበ […]
ሐምሌ 6 ቀን 2005 ዓ.ም ነገ እሁድ ጠዋት ሐምሌ 7 ቀን 2005 ዓ.ም. በጎንደር እና ደሴ ከተሞች ለሚደረገው ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ተፈቅዶ ከፖስተር መለጠፍ፣ በራሪ ወረቀት ከመበተን በተጨማሪ በድምፅ ማጉያ ሰልፉን ያዘጋጀው አንድነት ፓርቲ ቅስቀሳውን እያደረገ ይገኛል፡፡ ይንንም ተከትሎ በተመሳሳይ ጊዜ በደሴ ከተማ አራዳ ገበያ ህንፃ አንድነት ፓርቲ ተከራይቶ ያለውን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አከራዩ እንዲያስለቅቁ […]
በማዕከላይ አፍሪቃዊቱ ሬፓብሊክ ያማፅያን ቡድኖች የተሰባሰቡበት የየሰሌካ ህብረት የቀድሞውን ፕሬዚደንት ፍራንስዋ ቦዚዜን በመፈንቅለ መንግሥት አስወግዶ ሥልጣን ከያዘ ወዲህ ሀገሪቱ አሳሳቢ ሰብዓዊ ቀውስ ገጥሞዋታል።
በአምባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት የሐሰት ዉንጀላ ለእስር የተዳረገዉ ታዋቂዉና ተወዳጁ ጋዜጠኛና የፖለቲካ ተንታኝ እስክንድር ነጋ ዲያስፖራዉ በሀገር ዉስጥ እየተካሄደ ባለዉ ሠላማዊ ትግል ላይ በአካል ተገኝቶ እንዲሳተፍ መልዕክት አስተላለፈ፡፡ የፖለቲካና የህሊና እስረኞችን በአካል ለመጠየቅ ቃሊቲ ለተገኙ ጋዜጠኞች እና የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሕዝባዊ ንቅናቄ የግብር ሃይል አባላት አደራ ሲል ባስተላለፈዉ መልዕክቱ ከአገር ዉጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ቀጣይ በሚካሄዱ […]
Heathrow, Dreamliner, Ethiopian
ጎንደሮች በሰልፉ ለመገኘት የትኛውንም ዋጋ እንከፍላለን እያሉ ነው! ሐምሌ 5 ቀን 2005 ዓ.ም በጎንደር የአንድነት አመራሮች ፖሊስ ካሜራ እየነጠቀ ነዉ ! ‹‹እኛ ሰላማዊ ታጋዮች ነን። የያዝነው ጥያቄ እንጂ መሳሪያ አይደለም» አቶ ዘካሪያስ የማነአብ ፣ የአንድነት ብሄራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ ———————————————————– በ30/10/2005 በጎንደር ሰላማዊ ሰልፍ ለማከናወን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ያቀረበውን ጥያቄ የከተማው አስተዳደር ባቀረቡት ጥያቄ […]
ክንፉ አሰፋ
ስለ ኢትዮጵያውያን ብዙ የሚያውቁ ፈረንጆች ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ጠንቀቆ ማወቅ በጣም አስቸጋሪ እና ከባድ እንደሆነ ይናገራሉ። “ስለ ሕዝቡ ለመጻፍ የሚፈልግ አንድ ሰው ኢትዮጵያ በገባ ማዕግስት አንድ መጽሃፍ ሊጽፍ ይችላል፤ ይህ ሰው ሳምንት ሲቆይ አንድ መጣጥፍ ይጽፋል፣ ወር ሲቆይ ግን የሚጽፈው ይጠፋበታል።” ይላሉ። ይህ አባባል በከፊል ትክክል ይመስለኛል።
News, Community Heroes or Call-in, Crossfire and African Topics
በሶማሊያ የግል መገናኛ ብዙኀኗ ቁጥርከቀድሞው እየጨመረ በመሄድ ላይ ነው ። የጋዜጠኞች ቁጥርም አድጓል ። በተለይ የመዲናይቱ የመቅዲሾ ነዋሪዎች የሚያዳምጡ የሚያዩዋቸው የቴሌቪዥንና የራድዮ ጣቢያዎች የሚያነቧቸው ጋዜጦችም በዝተዋል ። የሶማሊያ መገናኛ ብዙኀን ስርጭቶች አሁን ውጭ ላሉ ሶማሊያውያንም እየደረሱ ነው ።
በአዲስ አበባ አነዋር መስጊድ ለተወሰኑ ጊዜያት ጋብ ብሎ የነበረው የሙስሊሞች ተቃውሞ ዛሬ ቀጥሏል ። በወልድያም ተመሳሳይ ሠላማዊ ተቃውሞ ተካሂዷል ።
ሐምሌ 5 ቀን 2005 ዓ.ም በሰሜን ጎንደር ዞን ዋና ከተማ፣ ጎንደር፣ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት) ሐምሌ 7 ቀን 2005 ዓ.ም ለጠራው ህዝባዊ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ፣ ህዝቡ እንዳይገኝ ለማድረግ የከተማውና የዞኑ አስተዳዳሪዎች ከፍተኛ ውጥረትና ጭንቅ ላይ ናቸው፡፡ ይህንንም ተከትሎ ከፍተኛ አመራሮቹ የብአዴን/ኢህአዴግ አባላትንና የዞኑ የየወረዳው አመራሮችን በከተማው መምህራን ማኀበር አዳራሽ ትናንት ሐምሌ 4 ቀን 2005 […]
ትናንት በታሰበው የኢትዮጵያ የችግኝ ተከላ ቀን ሱናርማ የተባለው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ያስተባበረው የዛፍ ተከላ ከደብረብርሃን ወጣ ብሎ በሚገኝ ቦታ ላይ ተካሂዷል ።
የአፍሪቃን የተፈጥሮና የሰዉ ሐይል ሐብትን ለማልማት ደግሞ የአፍሪቃ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳት እንደሚያምኑት አፍሪቃ እራሷን ከርዳታ ተቀባይነት ወደ ንግድ ተሻራኪነት፥ ወደ ወረት መስሕብነት ቀስ በቀስ እየቀየረች ነዉ። በተለይ በወረት ፍሰት እና ወጣቶችን በማሰልጠኑ መስክ ጀርመን እንድትሳተፍ ዙማ ጋብዘዋል።
ባለፈው የሳምንት መጨረሻ በዚሁ በቦን አቅራቢያ በምትገኘው የኮሎኝ ከተማ ሰመርጃም የተሰኘዉ የሬጌ የሙዚቃ ድግስ ተካሂዷል። በዚሁ ድግስ በሺዎች የሚቆጠሩ ከተለያየ ሀገር የመጡ ታዳሚዎችና የሙዚቃ ባንዶች ተገኝተዋል።
ሐምሌ 5 ቀን 2005 ዓ.ም – የደሴ ከንቲባ «ሰልፉ ይተላለፍ አሉ»። በጽሁፍ እስካልቀረበ ድረስ አንድነት ጥያቄዉን ዉድቅ አደረገው! – በጎንደርና በደሴ ለፌደራልና ለክልል ፖሊሶች አበባ ይበረከታል! የደሴ ከንቲባ ሰልፉ ለሳምንት እንዲራዘም ጠየቁ። ነገር ግን የአንድነት አመራር አባላት ሕጉ እንደሚፈቅደው በጽሁፍ እስካልቀረበላቸው ድረስ ከንቲባዉ በቃል የጠየቁትን እንደማይቀበሉ አረጋግጠዉላቸዋል። በጎንደር የከተማዋ አስተዳዳሪዎች «ሕዝቡ እናንተን አይሰማም። አምሳ ሰው […]
ሐምሌ ፭( አምት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ በአንዋር መስጊድ ከፍተኛ ህዝብ በተገኘበት ተቃውሞ ተካሂዷል። መንግስት የለም ወይ፣ የሼክ ኑር ኢማም ግድያ ድራማ ነው፣ ድራማው ይብቃ፣ መሪዎቻችን ይፈቱ፣ መሀይም አይመራንም፣ በፍትህ እጦት ድፍን አንድ አመት መንግስት ራሱ ገዳይ ራሱ ከሳሽ፣ ። አሸባሪው መንግስት ነው፣ ፍትሕ ማዳን። ፍትህ እያሉ ቃሊቲ ገቡ …
ሐምሌ ፭( አምት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በሁለቱ ከተሞች በተካሄዱት ስብሰባዎች ህዝቡ በመልካም አስተዳደር ችግሮች እየተሰቃየ እንደሚገኝ በድፍረት ለመንግስት ተወካዮች ሲገልጽ ተሰምቷል። በእንጅባራ አንድ ነጋዴ ሲናገሩ የመንግስት ባለስልጣናት የሚያቀረቡዋቸው ሪፖርቶች ለራሳቸው የሚጠቅሙ እንጅ ህዝቡ የሚያያቸው አይደሉም በማለት በማስረጃ አስደግፈው አቅርበዋል። ነጋዴው እንዳሉት እቃዎች ሳይገዙ እንደተገዙ ተደርጎ ይወራረዳሉ፣ ጥራት ያላቸው እቃዎች አይገዙም፣ የመንግስት መጋዘኖችም …
ሐምሌ ፭( አምት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ በሀላፊነት ላይ የሚገኙ የድርጅቱ ሠራተኛ እንደተናገሩት በምክትል ጠ/ሚኒስትር ማዕረግ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ሙክታር ከድር በቦርድ ሰብሳቢነት ወደመድን ድርጅት ከመጡ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ ዘረኝነትና ግልጽ የሆነ ዘረፋ በድርጅቱ ውስጥ በመንሰራፋቱ በርካታ ባለሙያዎች ድርጅቱን ለመልቀቅ እየተገደዱ ነው። ችግሩን ቦርዱ ተመልክቶ ሠራተኛውን እንዲያወያይ በተደጋጋሚ …
ሐምሌ ፭( አምት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሻለቃ ኃይሌ ፕሬዚዳንት የመሆን ፍላጎት እንዳለው ለዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን መግለጹን ተከትሎ ኢህአዴግ መራሹ ራዲዮ ፋና ባልተለመደ መልክ ዜናውን ደጋግሞ እንዳራገበው አንድ የፖለቲካ ተንታኝ ጠቅሰው ፣ ሀይሌ የሰጠውም መግለጫ ሆነ የሬዲዮ ፋና ዘገባ በድንገት የሆነ ሳይሆን ታቅዶበት የተደረገእንደሚሆን ግምታቸውን አስቀምጠል፡፡ በአሁኑ ወቅት በስልጣን ላይ የሚገኙት መቶ አለቃ …
ኮሌጁ እንዲዘጋ የውሳኔ መነሻ የሰጠው ከአቡነ ጢሞቴዎስ ተጽዕኖ ያልወጣው የኮሌጁ ቦርድ ነው አቤቱታቸውን ለመንግሥት አካላት ያሰሙት ደቀ መዛሙርቱ ‹‹ቅ/ሲኖዶስ እና ምእመናን የከፈቱት ኮሌጁ የሚዘጋው በመቃብራችን ላይ ነው!›› በሚለው አቋማቸው ጸንተዋል፤ በአስተዳደር ሕንጻው ዙሪያ የሚያደርጉትን ቁጥጥር አጠናክረዋል![]()
ሐምሌ 4 ቀን 2005 ዓ.ም ደሴ በፖለቲካ ቅስቀሳ ተናውጣላች። በአንድ በኩል፣ አንድነት ሕዝቡ ሕገ መንግስታዊ መብቱን የመጠቀም ፣ ሃሳቡን በነጻነት የመግልጽ፣ መሪዎቹን በፈለገ ጊዜ የመሾምና የመሻር መብት እንዳለው እያስተማረ፣ በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለዉን የግፍ ቀንበር በመቃወም፣ እግዚአብሄር የሰጠዉን፣ የአለም አቀፍ ሕግ ሆነ የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት የፈቀደለትን መብት በመጠቀም ደሴዎች ድምጻቸውን እንዲያሰሙ በላወድ ስፒከር እየቀሰቀሰ ነዉ። […]
ሐምሌ 4 ቀን 2005 ዓ.ም አንድነት ፓርቲ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ የከተማው መስተዳደሮችና የፀጥታ ኃይሎች ፓርቲው ህጋዊ የማሳወቅ ስራውን መስራቱን ገልፀው ሰልፉን መከልከል እንደማይችሉ ካረጋገጡ በኋላ፣ በከተማው ያሉ የቀበሌ ሰራተኞች መደበኛ ስራቸውን ጥለው በሰላማዊ ሰልፉ ዙሪያ በየቤቱ እየዞሩ ማስፈራራትና ሰላማዊ ሰልፉ ላይ ማንም እንዳይገኝ፣ ሰልፉ ህገወጥ ነው በሚል ቅስቀሳ እየሰሩ መሆናቸውን ከስፍራዉ የደረሱ ዜገባዎች ይጠቁማሉ።፡ «ነዋሪው […]
News, Cultural Mosaic, Kebele Lives and Environment or Tech
«ማንኛዉም ፖለቲካዊ ለዉጥ ቢደረግ ተጠያቂ እንሆናለን ብለዉ ያስባሉ።ለዚሕም ነዉ የሕዝብ ጥያቄን የሚያነሳ፥ የሕዝብን ጉዳይ የሚናገርን የሚያፍኑት።እኛ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲመሠረት ጥሪ እያቀረብን ነዉ።አሁን የምናየዉ ግን የዲሞክራሲ ምሕዳሩ በጣም እየጠበበ ነዉ።»
በአገራችን የኪነ-ጥበብ መድረክ ለረጅም ዓመታት ያገለገሉ እና በአሁኑ ወቅት በበሽታ በእድሜ አቅም አንስዋቸዉ ተረስተዉ የሚገኙ ታዋቂ ሰዎችን ለመርዳት በጀርመን አገር የተቋቋመዉ ማዕከል የዛሬ 10 ቀን ግድም ከኢትዮጵያ 6 ታዋቂ የመድረክ ሰዎችን ጋብዞ በተለያዩ የአዉሮጳ አገራት የመጡ ከያንያን በተገኙበት ባህላዊ የመድረክ ዝግጅትን አካሂድዋል።
ቢንላደን እንዳይያዙ በመጠበቅ ከለላ አድርገዋል ሲል በስም የጠቀሰው ባለሥልጣን ባይኖርም ከአሁኑም ሆነ ከቀድሞ ባለሥልጣናት ድጋፍ ያደረገላቸው እንደማይጠፋ ጠቅሷል ። ምዕራባውያን ተንታኞች ግን የፓኪስታን የደህንነት ባለስልጣናት ቢንላደን የኖሩበት የነበረውን ቤት ለይተው ማወቅ ያለመቻላቸው ምክንያት ቸልተኝነት ነው የሚለውን አይቀበሉም ።
የብሪታንያ ፓርላማ በኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ ሲወያይ አመሸ። ሃዉስ ኦፍ ኮመን በመባል የሚታወቀዉ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ትናንት ማምሻዉን የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታና ያለፉት 22ዓመት እንዲሁም ወደፊት እያንዣበበ የመጣ ያለዉን ችግር የዳሰሰ ጉባኤ ተካሂዷል።
ሐምሌ ፬( አራት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሀምሌ 7፣ 2005 ዓ/ም በደሴና ጎንደር ከተሞች አንድነት ፓርቲ የጠራቸው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎች በታቀደላቸው ጊዜ እንደሚካሄዱ ከመንግስት እውቅና የተሰጣቸው ቢሆንም፣ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎችና ባለስልጣናት የቅስቀሳ ወረቀቶችን የሚበትኑትን ሰዎች ከማሰር እና ከማስፈራራት አልፈው ፣ ከአዲስ አበባ የሄዱ የፓርቲው አመራሮች አልጋ እንዳያገኙ የሆቴል ባለንብረቶችን እስከ ማስፈራራት መድረሳቸውን የፓርቲው አመራሮች …
ሐምሌ ፬( አራት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መስተዳድሩ-ለፓርቲው በጻፈው ደብዳቤ- መድረክ ለእሁድ ሐምሌ 7 ቀን 2005 ዓመተ ምህረት ከጧቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6 ፡00 ሰዓት የሚቆይና ከስድስት ኪሎ ተነስቶ በአራት ኪሎ፣ በፒያሳና በቸርችል ጎዳና በማድረግ መዳረሻው ድላችን ሐውልት የሚያደርግ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ያቀረበውን ጥያቄ እንደተመለከተው በመጥቀስ፤ሰላማዊ ሰልፉ የሚደረግበት የጉዞ መስመር በአሁኑ ጊዜ እየተዘረጋ ባለው …
ሐምሌ ፬( አራት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ የወጣቶች ሊግ ሊቀመንበር ጁሊየስ ማሌማ ኢኮኖሚክ ፍሪደም ፋይተር የተሰኘ ፓርቲ መስርቷል። ወጣቱ ፖለቲከኛ በነጮች የተያዙት የአገሪቱ መሬት ለህዝቡ እንዲከፋፈል እና ዋና ዋና የማእድን ፋብሪካዎች በመንግስት ቁጥጥር ስር እንዲውሉ እንደሚታገል አስታውቋል። ማሌማ ፓርቲው ጸረ ካፒታሊዝም መሆኑም ገልጿል። “እኛ ጥቁሮች በዚህ አገር ስንኖር የምናሳያው …
ከአዲስ አበባ 401 ኪሎ ሜትር በስተሰሜን በምትገኘው ታሪካዊቷ የወሎ ክፍለ ሀገር(የአሁኑ ደቡብ ወሎ ዞን)ከተማ ደሴ ልክ እንደ አዲስ አበባ የክረምቱ ዝናብና ብርድ ቢያስቸግርም የነዋሪዎቿ እና የንግድ እንቅስቃሴዎቿ የምን አዲስ አበባ ያሰኛል፡፡ ይበልጥ ደግሞ ሲዘፈንላት የኖረው የነዋሪዎቿ ውበት፣ ተግባቢነትና በሙስልም ክርስቲያኑ በፍቅር ተግባቦት የሚያስቀና ኑሮ እንጉርጎሯዊ አድናቆት ይሰማል፡፡ ይህ ደግሞ በተግባርም እውነት መሆኑንን ስመለከት አቦ ደሴዎች […]