ሐምሌ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ወሎ ዞን ከወልድያ ከተማ በ140 ኪሜ ርቅት ላይ በትምገኘዋ መቀት ወረዳ የሚገኙ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ከፍተኛ እንግልት እደረሰባቸውና አካባቢውንም ለቀው እንዲወጡ ግፊት እየተደረገባቸው መሆኑን ገልጸዋል። እስካሁን በደረሰን መረጃ 10 የሚሆኑ የሀይማኖቱ ተከታዮች አካባቢውን ለቀው የወጡ ሲሆን፣ አንድ ተመስገን የተባለ ወጣት ለተባባሪ ዘጋቢያችን እንደገለጸው አማኞቹ ድንጋይ ይወረወርባቸዋል፣ ቤታቸውም …

ሐምሌ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ ልሳን የሆነው ፋና እንደዘገበው ከ2003 ዓመተ ምህረት ጀምሮ በጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ ለተሰማሩ ማህበራት 4 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ብድር ቢሰጥም ከ1 ቢሊየን ብር በላይ የሚሆነው አልተመለሰም ። ብድርን በማስመለስ በኩል የቅንጅት እጦት ፣ አስቀድሞ የመስሪያ ቤቶችን ያለማዘጋጀትና የገበያ ትስስሮሽን በበቂ ሁኔታ አለመፍጠር መሰረታዊ ጅግሮች መሆናቸው ተጠቅሷል። ገንዘብ …

ሐምሌ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኒዮን የስዊዘርላንድ ከተማ የተካሄደው 11ኛው የአውሮፓ የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል ቅዳሜ ጁላይ 20 በደማቅ ሁኔታ ተጠናቋል። ከተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት፣ ከሰሜን አሜሪካ፣ ከኢትዮጵያ እንዲሁም ከተለያዩ አህጉራት የመጡ በርካታ ኢትዮጵያውንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ለበዓሉ ድምቀት አስተዋጽዖ አድርገዋል። ይህ በአውሮፓ የኢትዮጵያውያን ፌስቲቫል ላለፉት 11 ዓመታት በተከታታይ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን፣ በአህጉሪቱ የሚገኙና ከሌሎች …

ሒዝቡባላሕ ግን ፍረጃዉን «የአሜሪካና የፅዮናዉያን ሴራ» በማለት ሲያወግዘዉ፥ የሊባኖስ መንግሥት ደግሞ ለሊባኖስ «ተጨማሪ ችግር ፈጣሪ» በማለት ተቃዉሞታል።የፖለቲካ ተንታኞችም የአዉሮጳ ሕብረት ዉሳኔን ገቢራዊነት ይጠራጠራሉ

በፌስ ቡክ የከፈተችዉን ዘመቻ «አንድ ብርድ ልብስ ለአንድ ጎዳና አዳሪ» በሚል ሥም ሰይማዋለች።ከያዘለት ለአዲስ አበባ የጎዳ አዳሪዎች አምስት ሺሕ ብርድ ልብስ ለመሰብሰብ ነዉ ዕቅዷ

በብሪታንያ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የወጣቶቹ ልዑል ዊልያም እና የባልተቤታቸው ልዕልት ካትሪን(ኬት)ሚድልተን ወንድ ልጅ ትናንት በለንደን የሴይንት ሜሪ ሀኪም ቤት ተወልዶዋል።

በቅርቡ ለንባብ የበቃው “ድርጅታዊ ምዝበራ” የተሰኘው መጽሃፍ ደራሲ ዶክተር ኣክሎግ ቢራራ ጎንደር ተማሪ በነበሩበት ወቅት በኣንድ ነገር ተመስጠው ነበር። ይህ ምናባቸውን የገዛው ነገር በጎንደር ውስጥ እድሜው የትየለሌ የሆነ የኣንድ የዋርካ ዛፍ ተፈጥሮ ነበር። ይህን ዋርካ ባዩት ቁጥር ምናባቸው ተዛምዶን ይፈጥራል። ግዙፉ ዋርካ ዙሪያውን ያሉትን ቅርንጫፎችና ቅጠሎች ይዞ ዝንት ዓለም ይኖራል። ከምድሪቱ የሚያገኘውን ኣስፈላጊ ነገር እያመላለሰ […]

ከሐምሌ አንድ እስከ ሐምሌ ሰድስት 2013 እ ኤ አ፣ ለኢትዮጵያውያን ሰላሰኛውን ዓመት ለሚያከብረው የእግር ኳስ ውድድር በዲሲ ተገኝቼ ነበር። ይህ በዓል በኢሳት ተነግሮ ሰለነበር በዓለም ዙሪያ ከኢትዮጵያ ሣይቀር ዲሲን እንደ ቁለቤ ገብርኤል ልንሣለማት እንደ ድሬ ሼክሁሴን ሙዳ ልንላት ተገኝተናል። በአገራችን ከማንኛውም ክፍለሃገር ዛሬ ጎረቤት አገር ከተባለችው ኤርትራ ሣይቀር የሐረሩን የቁልቤ ገብርኤል የባሌውን ድሬ ሼክሁሴን እስላም […]

ከአዲስ አበባ ወደ አውስትራልያ ልጓዝ ነው፡፡
ትነሣላችሁ የተባልነው ከምሽቱ አራት ሰዓት ከ15 ነበር፡፡ ‹ነበር› ካልኩ ነገር አለ ማለት ነው፡፡ የመሳፈሪያው አዳራሽ ውስጥ ተቀምጠን ግን የመሳፈሪያው ሰዓት በረረ፡፡ ሰዓቱ እኛን ጥሎን በሌላ አውሮፕላን ይብረር፣ ወይም የመሳፈሪያውን ሰዓት ያደረገው የአየር መንገዱ ሠራተኛ ሳይመጣ ይቅር የታወቀ ነገር የለም፡፡ ደግነቱ የአየር መንገዱም ሠራተኞች የተሰጣቸው መመሪያ ‹‹የመሣፈሪያ ሰዓት ካለፈ ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ ሳታስነቁ ወዲያ ወዲህ ማለት ነው› የሚል ሳይሆን አይቀርምና አንዳቸውም ምን አልተነፈሱም፡፡
መቼም ኢትዮጵያ ውስጥ መረጃ ለማግኘት የሚታወቅ መንገድ (system) ስለሌለ የሚታወቅ ሰው መፈለግ ነው፡፡ አንዱን የማውቀውን ሰው ጠጋ ብዬ ስጠይቀው ለንደን ላይ አውሮፕላናችን መጠነኛ ችግር እንደገጠመው ሹክ አለኝ፡፡ ምናልባት በዚያ ተደናግጠው ይሆናል ብዬ ይቅር አልኳቸውና መጠበቅ ጀመርኩ፡፡ ከጥቂት ጊዜ ቆይታ በኋላም ሕዝቡን ወደ ስታዮም እንደሚገባ ተመልካች አንጋግተው ይዘውት ወረዱ፡፡ ‹‹ሕጻናት ያላችሁ፣ የቢዝነስ ክፍል አባላት፣የሼባ ማይልስ የወርቅ አባላት›› ብሎ ነገር የለም፡፡ ‹‹እየየ ሲዳላ ነው›› አሉን፡፡ የሰው ጎርፍ ወደ ታችኛው ፎቅ በደረጃው ፈሰሰ፡፡ 

በአውቶቡሱ በኩል ተሸጋግረን ወደ አውሮፕላኑ ገባን፡፡ የመቀመጫ ለውጥ እንጂ የሰዓት ለውጥ አልነበረውም፡፡ ለነገሩ ብዙ ጊዜ በሀገሪቱ የመቀመጫ ለውጥ ነው የሚመጣውና አልተገረምንም፡፡ ‹መሣፈሪያ አዳራሹ ውስጥ መቀመጥ ሰለቸን› ያልናቸው ይመስል አውሮፕላኑ ውስጥ አንድ ሰዓት አስቀመጡን፡፡ ደግነቱ አብራሪው እየደጋገመ ይቅርታ ይጠይቃል፡፡ ከተለያየ ሀገር የሚመጡ ተሸጋጋሪ መንገደኞች እየተጠበቁ መሆኑንም ይነግረናል፡፡ መቼም የመጣውን አስቀምጦ ያልመጣውን መጠበቅ የተለመደ ነውና አላዘንኩበትም፡፡ ሠርግም ላይ፣ ስብሰባም ላይ፣ ጉባኤም ላይ፣ ግብዣም ላይ በሰዓቱ አክብረው የመጡት የዘገዩት እስኪመጡ እንዲጠብቁ በሚደረግበት ባህል ውስጥ ስላለን የሚገርም አይደለም፡፡
ከመቅረት መዘግየት ይሻላል ብሎ አውሮፕላኑ ወደ ዱባይ ተነሣ፡፡ ከጎኔ አንዲት እንደኔ አፍሪካዊት የሆነች፣ እንደ እኔ ግን ኢትዮጵያዊት ያልሆነች ሴት ተቀምጣለች፡፡ እርሷ እቴ ወደ አውሮፕላኑ እየገባች ሳይሆን አይቀርም ዕንቅልፍ የጀመራት፡፡ ደግሞ ስፋቷ ለሚኒ ባስ ታክሲ የመጨረሻው ወንበር እንጂ ለአውሮፕላን ወንበር የሚሆን አይደለም፡፡ ከመደገፊያው ተርፎ እኔ ጋ እየመጣ አስቸገረኝ፡፡ ሦስት ትራስ ደራርባ፣ በዚያ ላይ ፎጣ መሳይ ነገር ለብሳ ትለጥጠዋለች፡፡
እኔን መከራ ያሳየኝ ዕንቅልፏ አይደለም፡፡ እየተረፈ የሚመጣው ሰውነቷ አልበቃ ብሎ እንደ ፔንዱለም ስትወዛወዝ ትከሻየ ላይ እየመጣች ዘፍ የምትለው ነገር ነው፡፡ ሴትዮዋ የመጣችው ‹ሶሪ› ከሌለበት ሀገር ነው መሰለኝ ትከሻዬን ገጭታው ስትመለስ ከጥቁሩ ፊቷ መካከል ብልጭ የሚል ባለ ቀይ ድድ ጥርሷን ብቻ አሳይታኝ ‹ካለፈው የቀጠለ› ብላ ወደ ዕንቅልፏ ትገባለች፡፡ ትቆይና ደግሞ ክላሲካል ትለቃለች፡፡ ‹‹ፉርርርርርር›› የሚል የኩርፊያ ክላሲካል፡፡
መቼም በዚህ ክላሲካል ታጅቦ እንኳን ዕንቅልፍ መተኛት ቅዠት መቃዠትም አይቻልምና ከያዝኳቸው መጻሕፍት አንዱን አወጣሁ፡፡ ‹‹የአሲምባ ፍቅር›› የሚል ካሕሣይ አብርሃ በተባለ የኢሕአሠ(የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ሠራዊት) ታጋይ የተጻፈ መጽሐፍ፡፡ መጽሐፉ ከሥነ ጽሑፍ አንጻር ብዙ የሚቀሩት ነገሮች ቢኖሩም የዚያን ዘመን ወጣቶች ታሪክ በማሳየት አንጻር ግን ማራኪ ነው፡፡  መቼም ሰው በአውሮፕላን ሲሄድ አውሮፕላኑ እንዳይወድቅ እንጂ ከአውሮፕላኑ ውስጥ ሰው እንዳይወድቅ የሚሰጋ አይመስለኝም፡፡ እኔ ግን አንድ ገጽም ሳላነብብ በቀኝ ትከሻዬ በኩል የሆነ ነገር ዘፍ አለብኝና ሰጋሁ፡፡ ተጠንቅቄ ዘወር ስል ሴትዮዋ ሳታስፈቅደኝ ትከሻዬን ተንተርሳዋለች፡፡ እንደምንም ታግዬ ሳስለቅቃት ነቅታ ጥርሷን ብልጭ ታደርግና ዕንቅልፏን ከተቋረጠበት ትቀጥላለች፡፡
አሁን ምን ተብሎ ይጸለያል? እኔ እስካሁን በቀኝ ትከሻ በኩል ዘፍ ለምትል ሴት መከላከያ የሚሆን ጸሎት የነገረኝ ሰው የለም፡፡ ከኔ መለስ ሳደርጋት በወዲያኛው በኩል ወደተቀመጠው ፈረንጅ ሄዳ ዘፍ አለች መሰል ‹ኦ ማይ ጎድ› ሲል ሰማሁት፡፡ ‹‹እስኪ ያንተ ጸሎት ከሠራ እኔም እጠቀምበታለሁ›› ብዬ ጠበቅኩት፡፡ ሲብስበት ጊዜ ከወንበሩ ተነሥቶ ወደ መጸዳጃ ቤት አመራ፡፡ የፈረንጅ ነገር፣ ለሁሉም ችግር ወደ መጸዳጃ ቤት ነው፡፡ ‹ከአፍርንጅ የምንለይበት›› የሚለው የ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የሀገራችን መጽሐፍ ትዝ አለኝ፡፡   
‹‹የአሲምባ ፍቅር›› የዚያ ዘመን ወጣቶች ለሀገራቸው የነበራቸውን ፍቅር፣ ለነጻነት የነበራቸውን ታጋይነት፣ ላመኑበት ነገር ይከፍሉት የነበረውን መሥዋዕትነት፣ በሌላው ዓለም ያዩትንና ያነበቡትን በሀገራቸው ለማምጣት የነበራቸው ሕልም፣ ለአብዮት የነበራቸውን ጽኑ ፍቅር ያሳያችኋል፡፡ ያንን የመሰለ ትውልድ በጦርነት፣ በእሥርና በግድያ፣ በስደትና በጉስቁልና ማጣት ሀገሪቱን ምን ያህል እንደ ጎዳት ታዩበታላችሁ፡፡ ውጊያና ትግል፣ ስብሰባና ግምገማ፣ ኮንፈረንስና የእርምት ንቅናቄ፣ ተሐድሶና የፖለቲካ ትምህርት፣ ቋንቋው የነበረ አንድ ትውልድ እንዴት እንደጠፋ ትታዘባላችሁ፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የአመራር እጦት፣ የብስለት መጥፋት፣ የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ያላስገባ የትግል ስልት፣ የግለሰብን ነጻነት ያጠፋ ቡድናዊ አምባ ገነንነት፣ ችግሮችን ሁሉ በመሣሪያ አፈሙዝ ለመፍታት የነበረው አመለካከት፣ ራስን በምሁራዊ አምባ ላይ አስቀምጦ ሌላውን የመናቅ አባዜ፣ ከተማ ላይ ተቀምጦ የገጠርን ትግል የመምራት ድንግርግር፣ በሀገሪቱ ትውልድ ላይ ያመጣውን ምስቅልቅልም ታያላችሁ፡፡
እነዚህን መሰል መጻሕፍት ሳነብ እጅግ የሚገርመኝ ነገር ያ ትውልድ ፈጽሟቸዋል ብለን የምናስባቸው ስሕተቶች ዛሬም እንደገና እየተመላለሱ መፈጸማቸው ነው፡፡ አሁንም ችግሮችን በኃይል ለመፍታት ስንሞክር፣ አሁንም ድርጅቶች፣ ማኅበራት፣ ፓርቲዎች ከግለሰብ ነጻነት በላይ ሲሆኑ፣ አሁን የፓርቲ መሪዎች ችግሮችን በመከፋፈልና በመለያየት ሲፈቱ፣ አሁንም ሕዝብና ፀረ ሕዝብ፣ አንድነትና ፀረ አንድነት፣ አብዮታዊና ሊበራል፣ ኮሙኒስትና ካፒታሊስት የመከፋፈያ መሣሪያዎቻችን ሲሆኑ፣ አሁንም በጠላት መቃብር ላይ ሕንጻ የመሥራት አባዜ አልለቀን ሲል፣ አሁንም የተቃራኒያችንን አመለካከት ለማዳመጥ ትዕግሥት ሲያንሰን፣ ምን ያህል ከዚያኛው ዘመን ስሕተት እንዳልተማርን ያሳዩናል፡፡
ተዋጊዎቹ ወጣቶች በአንዳንዶቹ ውጊያዎች አይስማሙም፣ በአንዳንዶቹ ውጊያዎች ደግሞ ከአመራሮቻቸው ተቃራኒ የሆነ መረጃ አላቸው፣ ፓርቲውና ድርጅቱ እየተሳሳተ ያዩታል፣ ስሕተቶቹ የሚያስከፍሉትን ዋጋ በርግጠኛነት እያገኙት ነው፤ ነገሮች እንደማይሁኑ ሲሆኑ እየታዘቡ ነው፤ በተሳሳተ አመራር፣ በተሳሳተ የመፍትሔ ጉዞ፣ በተሳሳተ አሠራር የተነሣ ውድ የሀገሪቱ ልጆች ሕይወታቸውን ከጎናቸው ሲሠው እያዩ ነው፡፡ ነገር ግን ድርጅት፣ ፓርቲ፣ አመራር የሚባሉት ሰዎች አይሳሳቱም፣ እነርሱ ያሉት ሁሉ ቅዱስ ነው፣ እኔ ካየሁት ያላየው አመራር ይበልጣል፤ እኔ ስሕተት መሆኑን ባውቅም ፓርቲው ትክክል ነው ካለ ትክክል ነው፤ ሁለትና ሁለት ተደምሮ አራት የሚሆነው ፓርቲው ወይም ድርጅቱ አራት ነው ካለ ብቻ ነው፡፡ ያለበለዚያ ግን ሦስትም አምስትም ሊሆን ይችላል ብሎ የማሰብ አባዜ ዋጋ ሲያስከፍል እናያለን፡፡ ዛሬም ግን ይሔው አስተሳሰብ በዚህች ሀገር ውስጥ ሥሩን ተክሎ ቅጠል አውጥቶ፣ አብቦና አፍርቶ እየታየ ነው፡፡ ካለፈው ተምሮ እርሱን ለማረም የሚተጋ አይታይም፡፡
አውሮፕላናችን ሁለት ሰዓት ያህል ዘግይቶ ዱባይ ገባ፡፡ እኔ ዱባይ የገባሁት ቀጣዩን አውሮፕላን ለመያዝ 15 ደቂቃ ብቻ ሲቀረኝ ነው፡፡ ምድር ከወረደ በኋላ የበረራ አስተናጋጆች የተወሰን ሰዎችን ስም ጠርተው ውጭ የአየር መንገዱን ሰዎች እንድናነጋግር አሳሰቡን፡፡ እሺ ብለን ስንወጣ አገኘናቸው፡፡ የሆነች ወረቀት ሰጡንና እንዲህ ያለ ቦታ ሄዳችሁ የሆነ ሰው ታገኛላችሁ ሩጡ አሉን፡፡ መቼም አበበና ማሞ፣ ምሩጽና መሐመድ ከድር፣ ኃይሌና  ቀነኒሳ ከተወለዱበት ሀገር የመጣን ነን ብለን ወደተባለው ቦታ ሮጥን፡፡ ሲዖል ይዘጋላችሁና የነገሩን ቦታ ሁሉ ዝግ ነው፡፡ አንዳች ሰው በአካባቢው የለበትም፡፡ ‹አይ አየር መንገዳችን፤ እነ ክበበው ገዳ የት ሄደው ነው እርሱ እንዲህ ያለ ቀልድ የሚቀልደው› ብዬ ተገረምኩ፡፡ ማንን እናናግር፡፡ በኋላ አንድ የአውሮፕላን ማረፊያውን ፖሊስ አገኘነውና ችግራችንን ስንነግረው በፍተሻ ማለፊያው በኩል አድርጎ ወደ ምድር ቤት ወሰደን፡፡
 ምድር ቤት ወርደን የኢትዮጵያ አየር መንገድ መስኮት ስንደርስ እነርሱ ምን አለባቸው አራት ሆነው ቁጭ ብለዋል፡፡ ‹‹ምናለ አንዳችሁ እንኳን እዚያ ተገኝታችሁ ብትረዱን›› አልኳቸው፡፡ ‹‹እገሊትኮ ነበረች›› አሉን፡፡ ትኬታችንን ተቀብለው አየት አደረጉና ‹‹አሁንማ ረፍዷል ቀጣይ አውሮፕላን ካለ እንይላችሁ›› አሉን፡፡ ለእነርሱ እየተባበሩን ነው፡፡ ስሕተቱን የፈጸሙት እነርሱ፣ የዘገዩት እነርሱ የምንቀጣው እኛ፡፡ እንዴው ግን እስከ መቼ ነው የኢትዮጵያ አየር መንገድና የደንበኞቹ ግንኙነት የባላባትና የጢሰኛ የሚሆነው? በባላባቶች ፍርድ ‹‹ምን ባላባት ቢያጠፋ ጢሰኛ ይክሳል›› ይባላል፡፡ አየር መንገዳችንም እንዲህ ሆነብንኮ፡፡ ‹‹ይቅርታ፣ እስኪ ዐረፍ በሉ፣ ችግሩን እንፈታዋለን›› ከአማርኛችን ውስጥ የሌሉ ይመስል ምነው ከአንደበታቸው አልወጣ አሉ?
‹‹እናንተ ባጠፋችሁ ቁጥር እኛ መቀጣት አለብን?›› አልኳቸው ኃላፊ የመሰሉትን ሴትዮ፡፡ምንም አልመሰላቸውም፡፡ ከሌላው አየር መንገድ ጋር በስልክ ተነጋገሩ፡፡ ደግነቱ ያኛው አውሮፕላን አርፍዷል፡፡ ‹‹ትደርሳላችሁ ሂዱ አሉን፡፡›› ሄድን፡፡ እንደተባለውም ደረስን፡፡ ዛሬ ከአየር መንገዳችን ጋር የሚወዳደሩም የሚፎካከሩም አየር መንገዶች በበዙበት ጊዜ እንዲህ በደንበኞች አገልግሎት ላይ መቀለድ ምን ሊያመጣ እንደሚችል ለአየር መንገዳችን ኃላፊዎች ደጋግሞ ማሳሰብ ይገባል፡፡ የያዛችሁት አየር መንገድ ‹የኢትዮጵያ› ነው፡፡ የእናንተ አይደለም፡፡ እናንተ በምትፈጥሩት ስሕተት ግን የምትቀጣው ኢትዮጵያ ናት፡፡ ዛሬ እነ አልጀዚራ ስለ ኢትዮጵያ የሚወራ ክፉ ነገር ፍለጋ አሰፍስፈው በሚጠብቁበት ዘመን እናንተ ተባባሪ ሆናችሁ ክፉ ዜና የምትሰጡበትን ምክንያት እንኳን እኛ እናንተም የምታውቁት አልመሰለኝም፡፡
አሁን ከዱባይ ወደ ብሩናይ ለመጓዝ በሮያል ብሩናይ አውሮፕላን የመንገደኞች ማስተናገጃ ክፍል እገኛለሁ፡፡ ‹‹ባለቤት ያቃለለውን አሞሌ ባለ ዕዳ አይቀበለውም›› ይባል ነበር፡፡ እዚህ ግን ፉርሽ ተደረገ፡፡ አየር መንገዳችን ያቃለለንን መንገደኞች የብሩናይ አየር መንገድ ሰዎች ጋብዘውና ተከባክበው ካሱን፡፡ ‹‹ብሩናይ የሚባል ስም ከዚህ ጉዞ በፊት ሰምቼ አላውቅም፡፡ በዙሪያየ የተቀመጡት እስያውያን ናቸው፡፡ ሰውነታቸው ቀጨጭ፣ ዓይናቸው ሰለምለም፣ ልብሳቸው ደመቅመቅ፣ ፀጉራቸው ወረድረድ ያሉ ሕዝቦች፡፡ በአካባቢው ያለሁት አፍሪካዊ እኔ ብቻ ነኝ፡፡ ከዐርባ ደቂቃ በኋላ እንነሣለን ተብሏል፡፡ እስኪ ቀጣዩን መንገድ ደግሞ ሰላም ያድርገው፡፡
ዱባይ አውሮፕላን ማረፊያ፣ ዐረብ ኤምሬት  

በደቡብ ወሎ ዞን በረባቡ ወረዳ በስግደት ላይ የነበሩ የአንድነት ፓርቲ አባል የሆኑት አቶ አብዱ መሐመድ እና አቶ እንድሪስ አህመድን ጨምሮ 45 ወጣቶች መታሰራቸውን ምንጮቻችን ከስፍራው በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡ ከታሰሩት መካከልም ወጣት ሱልጣን መሐመድ በከፍተኛ ህመም እየተሰቃየ እንደሚገኝና እስካሁንም የህክምና እርዳታ እንዳልተደረገለት ተጠቁሟል፡፡ መንግስት የወረዳውን ነዋሪዎች የደሴው ሼህ ኑሩ ይማምን መገደል በሰላማዊ ሰልፍ ካላወገዛችሁ የመሬት […]

ሐምሌ ፲፭(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእነ አቶ ተሻለ በካሻ መዝገብ ተከሰው ከሁለት አመታት በላይ በእስር ቤት የቆዩት እስረኞች ሰሞኑን ከፍተኛ ድብደባ ከተፈጸመባቸው በሁዋላ ለተከታታይ ቀናት ምግብ ባለመመገባቸው ህይወታቸው አደጋ ላይ መውደቁን በመግለጽ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲደርስላቸው አቤት ብለዋል። እስረኞቹ በጻፉት ደብዳቤ ላይ  ከውጭ የመጡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በፌሮ ክፉኛ እንደደበደቡዋቸውና ህክምና በማጣታቸው ከፍተኛ ስቃይ …

ሐምሌ ፲፭(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አንድነት የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት በማለት የጠራው ህዝባዊ ንቅናቄ ገዢውን ፓርቲ በማስደንገጡን አዲስ ከጀመራቸው ግምገማዎችና የህብዕ እንቅስቃሴዎች ለመረዳት ተችሎአል። በደሴ እና በጎንደር የተካሄደውን ስላማዊ ሰልፍ ተከትሎ  የፖሊስ እና የቀበሌ የፖለቲካ አመራሮች በጠንካራ ግምገማ ተይዘው መሰንበታቸውን ከኢህአዴግ ምንጮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ስማችን እና ድምጻችን አይተላለፍ ያሉት ምንጮች እንደገለጹት በ1ለ5  አደራጃጀት …

ሐምሌ ፲፭(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የግንባሩ 9ኛ ጉባዔ ሪፖርት እንደሚያሳየው በ2003 እና በ2004 ዓ.ም ግንባሩ 88 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ገቢ ያገኘ ሲሆን ቀድሞ በባንክ አካውንት ውስጥ ከነበረው ሒሳብ ጋር ሲደመር ገቢው 171 ነጥብ 2 ሚሊየን መድረሱንም ይፋ አድርጓል፡፡ 46 በመቶ የሚሆነው ገቢ የተገኘው ከ“አዲስ ራዕይ” እና “ህዳሴ” ከተሰኙ ሕትመቶች ሽያጭ ነው ፡፡ …

ሐምሌ ፲፭(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህር ዳር ከተማ በህዝበ ሙስሊሙ መካነ መቃብር አጠገብ የሚገኘውን ትንሽ ቦታ መንግስት ሞይንኮ ለተሰኘ  የመኪና ጋራጅ  ድርጅት አሳልፎ መስጠቱን ተከትሎ የአካባቢው ሙስሊም ባነሳው ተቃውሞ ምክንያት  ድርጅቱ ቦታውን እንደማይወስድ እና እንደማይረከብ አስታውቆ ነበር። ትናንት ህዝበ ሙስሊሙ ቦታውን ለማጠር እና አታክልት ለመትከል ሲሰባሰብ የፌደራል ፖሊስ በፍጥነት በመምጣት ያስቆማቸው ሲሆን እርምጃውን …

ከተመስገን ደሳለኝ

ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ

…አራት ኪሎ በሚገኝ አንድ ካፍቴሪያ ከጓደኞቼ ጋር የደራ ወግ በመያዜ፣ የእጅ ስልኬ የ‹‹መልስ ስጠኝ›› ጩኸቱን ደጋግሞ ሲያሰማ ልብ አላልኩትም፤ እናም ጮኾ ጮኾ ሲጨርስ፣ እንደገና ይምራል፡፡ ይኼኔ ጥሪውን እንዳላስተዋልኩ የተረዳው ጓደኛዬ ወደ ስልኩ ሲያመላክተኝ፣ ቁጥሩን አየሁት፤ አውቀዋለው፡፡ የእስክንድር ነጋ ባለቤት የጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል ነው፤ አነሳሁት፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

ባሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ በጆሐንስበርግ ደቡብ አፍሪቃ ፤ ወደ 500 የሚጠጉ ኢትዮጵያዉያን በአንድ ዉይይት ላይ መገኘታቸዉ ታውቋል። በዉይይት መድረኩ የተለያዩ ምሁራንና የሲቪክ ማሕበራት ተሳታፊዎች እንደነበሩ ለመገንዘብ ተችሏል።

የአፍሪቃ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ዶክተር እንኮሳዛና ድላሚኒ ዙማ፤በዛሬው ዕለት የግብዕን ጊዜያዊ መንግሥት ልዩ መልእክተኛ አምባሳደር ሞና ኦማርን አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው የኅብረቱ ዋና ጽ/ቤት ተቀብለው ማነጋገራቸው ተመለከተ።

ሥለ NSA የተለያዩ መፅሐፍት ያሳተመዉ ጋዜጠኛ ጀምስ ባምፎርድ እንደሚለዉ፥ እርስዎ ከዱባይ ወይ ከለንደን አዲስ አበባ ላለች ፍቅረኛዎ የፍቅር ኢሜል ይመይላሉ እንበል።ስኖዳን እና ብጤዎቻቸዉ ሐዋይ፥ ሜሪላንድ ወይም የፈለጉበት ቦታ ሆነዉ-ከፍቅረኛዎ እኩል ምናልባትም ቀድመዉ ኢሜልዎን ያነባሉ።ስልኩም—

መድረክ በመቀሌ የጠራው ህዝባዊ ስብሰባ በስኬት እንደተጠናቀቀ የአንድነት ፓርቲ የትግራይ ዞን ጸሀፊ ለፍኖተ ነፃነት አስታወቁ፡፡ የአንድነት ፓርቲ የትግራይ ዞን ጸሀፊ አቶ ክብሮም ብርሃነ ለፍኖተ ነፃነት እንዳስታወቁት መድረክ ዛሬ ሐምሌ 14 ቀን 2005 ዓ.ም በመቀሌ ከተማ ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ ቀኑ 7 ሰዓት ያካሄደው ህዝባዊ ስብሰባ ከአንድ ሺ በላይ ሰዎች የተገኙበት ነበር፡፡ በአብዛኛው […]

ኢትዮጵያ ዉስጥ በ1997 የተደረገዉ ምርጫ ዉጤት ደም ባፋሰሰ ግጭት ካሳረገ ወዲሕ መንግሥትን በአደባባይ ሠልፍ መቃወም ለኢትዮጵያዉያን ዝግ ሆኖ ነበር።

«ነጻነትን ማንም አይሰጥህም። እኩልነትና ፍትህንም ማንም አይሰጥምህ። ሰው ከሆንክ፣ አንተዉ እራስህ ተቀበለው» ነበር ያሉት፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ማልኮም ኤክስ። ነጻነትና ሰላም፣ ዴሞክራሲና ፍትህ፣ እኩልነትና መልካም አስተዳደር፣ ሌሎች የሚሰጡን ሳይሆን፣ ፈጣሪ በቸርነቱ የለገሰን፣ ደፍረንና ፈቅደን የምንቀበላቸው፣ የኛዉ የሆኑ በረከቶች ናቸው። ነገር ግን ለአመታት መብታችንና ነጻነታችን፣ በጥቂቶች ተገፎ፣ ሁላችንም በየጓዳችን ስንናደድ፣ ስናማርር፣ ስናዝን፣ ስንራገም፣ ልባችን ሲደማ፣ «እንደዉ […]

በቅድሚያ ርዕሰ-ጥያቄው አንፃራዊ መልስ የሚሻው በጣም አሳሳቢ እና :- የአገር ፍቅርን:-የሚገድል ዝምታ በኢትዮጵያውያን ላይ ሃያ ሁለት ዓመታት በመንገሱ ነው።ይህ አቢይ ጉዳይ እና ወሳኝ በመሆኑ ዝምታውን ለመስበር ደግሞ ወቅታዊነቱን እንረዳለን።የኢትዮጵያውያን እስልምና ዕምነት ተከታዮችን አንድነት እና ጥንካሬ በአፅንኦት ይመለከቷል:: እኛ ኢትዮጵያውያን ከሁሉም በፊት አስቀድሞ:- “እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ ነው።”{መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ-፻፲፩ ከቁጥር-፲ ፤መጽሐፈ ምሳሌ ም፩ ቁ፯ […]

በማለዳው ከእንቅልፍ ስነቃ ለዛሬው ለማለዳ ወግ ቅኝቴን ሁለት ሰሞነኛ ትኩስ ወጎች ከፊ ለፊቴ ገጭ ብለው ጠበቁኝ ! . . አንዱ ሰሞነኛ ወግ ስልጣኔ ዘመነኛ የመገናኛ ዘዴዎችን ማግኘት የታደለው የሃገሬ ሰው አይኑን አፍጦ በማህበራዊ ገጾች እና በተለያዩ የኢንተር ኔት ድህረ ገጽ ስር ባሉ የመረጃ መረቦች ሲከታትለው የሰነበተው የጁሃር መሃመድ ሃይማኖትና ዘርን ቀላቅሎ የተናገረበት አሳፋሪ፣ አሳዛኝ እና […]

መድረክ ነገ ሐምሌ 14 በመቀሌ ከተማ ለሚያደርገው ህዝባዊ ስብሰባ በመኪና ሲቀሰቅሱ የነበሩት የአረና ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ሱልጣን ህሺ እንዲሁም የአንድነት ፓርቲ የትግራይ ዞን ጸሀፊ አቶ ክብሮም ብርሀኔ ከቀኑ 9 ሰአት ላይ በህገወጥ መንገድ መታሰራቸውን የአረና ፓርቲ ለፍኖተ ነፃነት አስታውቋል፡፡ ፓርቲው ጨምሮ እንዳስታወቀው ለነገው ስብሰባ ቅስቀሳ እንዳይደረግ የክልሉ መንግስት ሀላፊዎች ክልከላ ቢያደርጉም በነገው እለት […]

ያሬድ ክንፈ ከኒዮ፣ ስዊዘርላንድ (ጥቂት ፎቶግራፎች ይዘናል)

በዓሉን ካደመቁት ሕፃናት በጥቂቱ
Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሐምሌ 13 ቀን 2005 ዓ.ም. July 20, 2013)፦ ረቡዕ ሐምሌ 10 ቀን 2005 ዓ.ም. (ጁላይ 17፣ 2013) በኒዮን የስዊዘርላንድ ከተማ የተጀመረው 11ኛው የአውሮፓ የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል ዛሬ ቅዳሜ ይጠናቀቃል። ከተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት፣ ከሰሜን አሜሪካ፣ ከኢትዮጵያ እንዲሁም ከተለያዩ አህጉራት የመጡ በርካታ ኢትዮጵያውንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ለበዓሉ ድምቀት አስተዋጽዖ አድርገዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ከመስፍንነጋሽ

ወንድሜ ጁዋር መሀመድ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በኦሮሞ ፖለቲካ እና አሁን ደግሞ ስለኦሮሞ-ኢስላም ያቀረባቸው ንግግሮች ኮርኳሪ ሆነዋል። ኮርኳሪነታቸው የሚመነጨው ግን ሐሳቦች አዲስ ስለሆኑ አይደለም፤ በአቀራረባቸውም ቢሆን ያልተለመዱ አይደሉም። “የአግራሞቱ” ወይም የንዴቱ ምንጭ ጃዋር የገነባው ወወይም እየገነባው የመሰለን የፖለቲካ ማንነትና በቅርብ ያንጸባረቃቸው አቋሞቹ እጅግ የሚቃረኑ ስለሚመስሉ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

/መሰፍን/ማርያም

የሚወለድበትን መሬት ማንም ሰው አይመርጥም፤ የዘመኑ ቅንጦት ኢትዮጵያ አርግዞ አሜሪካ መውለድ ቢሆንም፣ ልጁ ምርጫው ውስጥ የለበትም፤ አንኳን ልጁ አባትዬውም ምርጫው ውስጥ የሚገባ አይመስለኝም፤ በእንደዚህ ያለው ኢትዮጵያን አስጠልቶ ሌላእንዲሆን በተፈጠረ ቅንጦት የሚወለድ ኢትዮጵያዊ ምን እንደሚሆን መተንበይ ያዳግታል፤ ልጁ ወይም ልጅቱ በራሳቸው ዝንባሌ፣ ፍላጎትና ጥረት ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸው ግንኙነት በእልህ ከአልተለወጠ እናቶቻቸው የተለሙላቸው ማንነት ከኢትዮጵያዊነት ይገነጥላቸዋል፤ ነገር ግን የኢትዮጵያዊነት ስሜት እንዲህ በቀላሉ ተቀርፎ የሚወድቅ አይደለም፤ ሲደንቀኝ የቆየ ነገር ልናገር፤

ሙሉውን አስነብበኝ …

መ/ር ፍሥሐ ጽዮን ደመወዝ በማስተማር ሥራ ብቻ ይወሰናሉ የአቡነ ጢሞቴዎስ ቀጣይነት እየተጤነ ነው አቡነ ጢሞቴዎስን የሚተካ ዋና ዲን እስኪሾም ኮሌጁ በጊዜያዊ ሓላፊ ሊመራ ይችላል ጥቅመኛው፣ ሀኬተኛው (ክፋተኛው) እና መናፍቁ ዘላለም ረድኤት በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ከያዘው የቀን መደበኛ መርሐ ግብር አስተባባሪነት እንዲወገድ ቋሚ ሲኖዶስ ከስምምነት ላይ ደረሰ፡፡ ቋሚ ሲኖዶሱ ከዚህ ዐቢይ የስምምነት ውሳኔ ላይ የደረሰው …

ከማከብራቸው የዲሞክራሲ አክቲቪስት መካከል አንዱ የሆኑት፣ አቶ ተድላ አስፋዉ፣ አቶ ጃዋር መሃመድ ለተናገራቸው አንዳንድ አባባሎች የሰጡትን ምላሽ አነበብኩ። አቶ ጃዋር የተወለደው በአርሲና በሃረርጌ ድንበር አካባቢ ነዉ። በዚያ አካባቢ ነዉ አርባ ጉጉ (ምእራብ አርሲ) እና በደኖ (ምስራቅ ሃረርጌ) የሚገኙት። ወያኔ/ኢሕአዴግና ኦነግ ስልጣን በጨበጡ ጊዜ፣ በአርባ ጉጉና በደኖ የተፈጸሙትን ሁላችንም የምናወቀዉ ነዉ። አካባቢዉን ከክርስቲያኖችና ከ«አማራዎች» ለማጽዳት ፣ […]

ብሔርተኝነትን መግለፅ ለኤርትራዉያን ወጣቶች የሚመጣ ችግርን መከላከያ ጥሩ ሥልት ነዉ።ሌላ ቢሎ መዘዙ ሌላ ነዉ።አምስት ሚሊዮን ሕዝብ ያላት ትንሽ ሐገር እራሷን ከተቀረዉ ዓለም ዘግታለች።ከሠላሳ ዓመት ጦርነት በሕዋላ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ድጋፍ ነፃነትዋን በይፋ ያወጀችዉ በ1985 ነዉ።

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) ዕሁድ ሐምሌ 6 ቀን 2005 ዓ. ም በጎንደርና በደሴ ከተሞች የተካሄዱትን ትዕይንተ-ሕዝቦች ይደግፋል። ”የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት!” በሚል መሪ ሃሳብ ሥር በአንድነት ፓርቲ አቀነባባሪነት የተጀመረው የሕዝብ እንቅስቃሴ፤ የተጋረጠበትን እንቅፋት ሁሉ አልፎ እነሆ በደሴና በጎንደር ከተሞች በከፍተኛ የሕዝብ ተሳትፎ በሕዝባችን ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ የፍራቻ ድባብን ሰብሮ በይፋ ለመግልጥ መቻሉ ሁሉንም […]

በነገው ዕለት በመንበረ ፓትርያሪኩ በሚያካሂዱት ከፍተኛ የተቃውሞ ትዕይንት ምእመኑ ከጎናቸው እንዲሰለፍ ጥሪያቸውን አቅርበዋል አቡነ ጢሞቴዎስ ደቀ መዛሙርቱን በፖሊቲከኝነት መወንጀል ጀምረዋል የተማሪዎች መማክርት የኮሌጁን አስተዳደር በሕግ ለመጠየቅ እየተዘጋጀ ነው ምእመናን ቤተ ክርስቲያን ከመሳለምና ገንዘብ ከመስጠት/ከመመጽወት ባሻገር ስለ ቤተ ክርስቲያናቸው ጉዳይ በመጠየቅ ቀጥተኛ ተሳታፊ መኾን እንደሚገባቸው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት አሳሰቡ፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ማሳሰቢያውን ያስተላለፉት፣ …