ፍኖተ ነጻነት – የደሴ ትራንስፖርት ህዝብ እንዳያመላልስ ተደረገ
ሐምሌ 6 ቀን 2005 ዓ.ም
በደሴ አካባቢ ከሚገኙ ከተሞች(ከወረባቡና ሐይቅ)፣ በነገው የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ለመገኘት ወደ ከተማይቱ ለመምጣት ትራንስፖርት ያስፈልጋቸው የነበሩ ዜጎች፣ በከተማው አስተዳደር ስውር ትዕዛዝ መሰረት፣ ከዛሬ ምሽት ጀምሮ የትራንስፖርት መኪኖቹ ከአገልግሎት ውጪ እንዲሆኑ መታዘዛቸውን የየአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ለሰልፉ አዘጋጆች በመደወል እየገለጹ ነው፡፡
ሁኔታው ያሳዘናቸው ሰዎች በቻሉት መንገድ ሁሉ ወደ ሰልፉ በመምጣት ድምጻቸውን እንደሚያሰሙና መሰናክሉን እንደሚያልፉት አስታውቀዋል፡፡