Jemal, Muslim Ethiopian who was killed by ISIS is a fake story. The man on the picture is Ephrem who is Eritrean christian.

<ጀማል› የተባለ ሙስሊም ወንድማችን በሊቢያ ከተሠዉ ክርስቲያኖች ጋር አብሮ ተሠዉቷል እየተባለ ሲነገር ቆይቷል፡፡ በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞችና ሌሎችም የቅርብ ምንጮች ታሪኩ የተሳሳተ መሆኑን ቢናገሩም ሰሚ ለማግኘት ግን አልተቻለም፡፡ አንዳንዶቹም ታሪኩን የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች ፍቅር ማሳያ አድርገው ተሟግተዋል፡፡ እንደ እኔ ግን ይህንን ታላቅ ፍቅር ለማሳየት ‹ጀማል› የተባለ መሥዋዕት መፍጠር አያስፈልገንም፡፡ ፍቅሩ ነበረ፤ አለ፡፡ ተጨማሪ ፈጠራው አያስፈልገውም ነበር፡፡
‹ጀማል› ነው ተብሎ ሲነገርለት የነበረው ወንድማችን ግን ኤፍሬም የተባለ ኤርትራዊ፣ ቃኘው ሠፈር ይኖር የነበረ ክርስቲያን ነው፡፡ ቤተሰቦቹ ሁለት መርዶ እንደመጣባቸው እየገለጡ ነው፡፡ በአንድ በኩል በአሰቃቂ ሁኔታ በአይሲስ መሠዋቱ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ‹ሙስሊም› ነው መባሉ ነው፡፡ ኖርዌይ የነበሩ ኤርትራውያን ክርስቲያኖች ወዲያው ነበር ነገሩን የተቃወሙት፡፡ ነገር ግን አሥመራ ያሉት ቤተሰቦቹ እስኪረዱ ድረስ ትክክለኛ ስሙን ለመግለጥ አልተፈለገም፡፡ በዚህ መዘግየት የተነሣም ብዙ የፈጠራ ታሪኮች ተፈጠሩ፡፡ አንዳንድ የማኅበራዊ ሚዲያ አቀንቃኞች በላኩልኝ የውስጥ መልእክት የጀማልን ሙስሊምነት መካድ ሙስሊሞች ለክርስቲያኖች ያላቸውን ድጋፍና ፍቅር መካድ ነው ሲሉ ገልጠዋል፡፡ ለእኔ ግን ከተፈጠረው ‹ጀማል› ይልቅ እዚሁ አዲስ አበባ ያለው መሐመድ ካሣ ይህንን ልዩ ፍቅር ከንጋት ኮከብ በላይ አጉልቶ አሳይቶኛል፡፡ ልቡ እስኪደክም ኀዘንተኞቹን ለማጽናናትና ለመርዳት የሚደክመው፤ ለምን ጉባኤ አይደረግም፣ መዘምራን ለምን አይመጡም፣ መምህራን ለምን አያስተምሩም እያለ ልቅሶ ቤቶቹን ከክርስቲያኖቹ በላይ ሲያገለግል የነበረው፤ ተዝካራቸው መውጣት አለበት ብሎ ከካህናቱ ጋር የሚሟገተው፣ ድንበር ተሻጋሪውና ድልድይ ገንቢው መሐመድ ካሣ ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች ፍቅር ከበቂ በላይ ማሳያዬ ነው፡፡ ያየሁት፣ የነካሁት፣ የበለጠኝ ማስረጃዬ፡፡ ፈጠራ አያስፈልገኝም፡፡
ኤፍሬም ሆይ በረከትህ ይደርብን፡፡
Subscribe to Sodere YouTube channel. የዩቲዩብ ቻናልችን ደንበኛ ለመሆን ይመዝገቡ።
See below for some videos from Sodere YouTube channel
Ethiopian Movie Mena
Ethiopian comedy movie Che Belew 2
Ethiopian Movie Terafiqua Full ትራፊኳ ሙሉ ፊልም
Ethiopian Movie Ye Addis Abeba Habtam Full የአዲስ አበባ ሃብታም ሙሉ ፊልም
Ethiopian Movie Kemaebelu Wedeh Full ከማዕበሉ ወዲህ ሙሉ ፊልም
Ethiopia Yemaleda Kokoboch Final Program
Ethiopia Comedian MESKEREM Bekele Full Comedy Video
Ethiopia – Live poultry market in Abeba for Easter
Ethiopian Movie GEDAMAWITUA Full
Ethiopian Movie Ke Tsion Bestejerba Full ከፅዮን በስተጀርባ ሙሉ ፊልም
Receive Ethiopian News, Movies and Videos by email. Sign up for Email alerts
ትኩስ እና ሰበር ዜና፣ በብዛት የታዩ ቪድዮዎችን፣ ድራማዎችን፣ሙዚቃዎችን፣ ጠቃሚ ምክሮችን እና አስገራሚ ታሪኮችን በኢሜል አድራሻዎ እንልካለን። ኢሜሎን ያስመዘ