በምስራቅ አፍሪካ የሰብአዊ መብቶች ሊግ ለኢሳት በላከው መግለጫ ፣ አምና በሚያዚያ ወር ከ79 በላይ የኦሮሞ ወጣቶች በአምቦና አካባቢዋ ከተገደሉ በሁዋላ፣ ባለፉት 10 ቀናት ደግሞ 50 የዩኒቨርስቲና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች መያዛቸውን ገልጿል፤፡ ከ20 በላይ ወጣቶች በድብደባ ጉዳት ደርሶባቸው በአምቦ አጠቃላይ ሆስፒታል በህክምና ላይ ይገኛሉ። ድርጅቱ ባሰባሰበው መረጃ በእስር ላይ የሚገኙ 20 ተማሪዎችን ስም ይፋ አድርጓል። ወጣቶቹ …

ሚያዚያ 27 ቀን 2007 ዓም ከሌሊቱ 9 ሰዓት ገደማ በጣለው ድንገተኛ ዝናብ፣ እስካሁን ባለው መረጃ 9 ሰዎች በጎርፍ ተወስደዋል። ሟቾቹ ለገሃሪ እንደገበሬ በሚባለው አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ናቸው። የ9 ሰዎች አስከሬን ተፈልጎ መገኘቱን ምንጮች ገልጸዋል። ድሬዳዋ ከዚህ ቀደም በደረሰ ጎርፍ በርካታ ነዋሪዎቿን ማጣቷ ይታወቃል።

በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ሳውድ አረቢያዊ የሆኑት ቢሊየነሩ ሼክ አላሙዲን በሸራተን አዲስ ተገኝተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ፣ በስፍራው የተገኙትን የመንግስት ጋዜጠኞችና አንዳንድ የግል ሚዲያ ሃላፊዎችን ወቅሰዋል። ሼክ አላሙዲን በአሜሪካና በአውሮፓ የደሀ መሬት እየወሰዱ ነው እያሉ ስማችንን የሚያጠፉ ስራፈት ሚዲያዎች አሉ ያሉ ሲሆን፣ እናንተም የተባለው ትክክል ነው ወይስ አይደለም ብላችሁ፣ መርምራችሁ ለህዝቡ ማቅረብ ነበረባችሁ በማለት ለዘገባ የተላኩ …

በጋምቢያ ዋና ከተማ ባንጁል በማካሄድ ላይ ባለው 56ኛው አፍሪካ የሰብአዊ መብት ኮሚሽንና ህዝቦች መብቶች መደበኛ ጉባኤ ላይ ፣ አሪድ ላንድስ ኢንስቲቲዩት የተባለው ተቋም ባቀረበው ጽሁፍ ፣ ነጻነትን በማፈን የአለም ሻምፒዮን ከሆኑ አገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዳ መሆኗን ገልጿል። በኢትዮጵያ የሚባለውና የሚደረገው የተለያየ ነው የሚለው ድርጅቱ ፣ የአገሪቱ ህዝብ አማራጭ የመገናኛ ብዙሃንን እንዳያገኝ መታፈኑን ገልጿል። በአገሪቱ አስገድዶ …

ይህ የምርጫ ማኒፌስቶም ሀገሪቱ አሁን ካለችበት የኢህአዴግ አምባገነናዊ አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በሚደረግ ሽግግር ወቅት በሀገራችን ሰማያዊ ፓርቲ በምርጫ ተወዳድሮ ማሸነፍ ቢችል የሚያከናውናቸውን ተግባራት በዝርዝር የሚተነትን ነው፡፡ ይህ የምርጫ ማኒፌስቶ በዋናነት በሦስት ምዕራፍ የተከፈለ ሲሆን የመጀመሪያው የፖለቲካ ሥርዓቱ አደረጃጀት ምን መምሰል እንዳለበት የሚገልፅ ክፍል ነው፡፡ በዚህ ምዕራፍ ሰማየዊ ፓርቲ ባለፉት 24 ዓመታት የህወሀት/ኢህአዴግ መራሹ ሥርዓት በሀገራችን ላይ የፈፀማቸውን የተሣሣቱ የፖለቲካ ሂደቶች በዝርዝር የሚያስቃኝ ሲሆን፤ በአንፃሩም ፓርቲው በሥልጣን ላይ ቢቀመጥ በዋነኛነት በቋንቋ ላይ የተመሰረተውን የፌደራል ሥርዓት በመቀየር መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥን፣ የሕዝብ አሰፋፈርንና፣ ልማትና ሌሎች ማህበራዊ ትስስሮችን መሰረት ያደረገ እንዲሆን ለማድረግ እንደሚሠራ ተገልጿል፡፡ በመንግሥት አወቃቀሩ፣ በነፃ-ፕሬስ፣ በመከላከያ ፖሊስና ደህንነቱ አወቃቀር እንዲሁም የውጭ ግንኙነት አማራጭ ፓሊሲውም በዝርዝር በማኒፌስቶው ላይ የተቀመጡ አንኳር ጉዳዮች ናቸው፡፡

በሁለተኛዉ ምዕራፍ የማህበራዊ ሥርዓቱን በተመለከተ የተዘረዘሩ ነጥቦችን የያዘ ሲሆን ህወሃት /ኢህአዴግ በሀገራችን ሕዝብ ላይ በማህበራዊ ዕድገቱ ላይ ያስከተለውን ሁለንተናዊ ቀውሰ በማስቃኘት፤ የሰማያዊ ፓርቲ መሠረታዊ የማህበራዊ ጉዳይ ፍልስፍና የሆነውን ጤነኛና በእውቀት ላይ የተመሠረተ በራሱ የሚተማመን ዜጋን ለመፍጠር ዋነኛ ምሰሶ የሆነውን ትምህርትና ጤና ላይ ያለውን ፖሊሲ በማስቃኘት ጀምሮ በማኅበረሰቡ ውስጥ በዕድሜያቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ የዕድሜ አንጋፋዎችና በተፈጥሮና በአደጋ አካላቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸውን የኅብረተሰቡ ክፍሎች የሚሰጠውን ድጋፍ ይተነትናል፡፡ በተጨማሪም ሰማያዊ ፓርቲ ሃይማኖት፣ ባህል፣ ኪነ-ጥበብ፣ ስፖርት እና መሰል ማኅበራዊ ጉዳዮች የሚመለከትባቸውን እይታዎች ያስቃኛል፡፡

በመጨረሻም በዚህ ማኒፌስቶ በጥልቀት የተገለፀው የፓርቲውን የኢኮኖሚ አማራጭ የሚያሣየው ምዕራፍ ነው፡፡ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ የህወሃት/ኢህአዴግ ሥርዓት እከተለዋለሁ የሚለውን ገጠርን ማዕከል ያደረገ ግብርና መር የኢንዱስትሪ ልማት የኢኮኖሚ ፖሊሲ ከዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ በማስቀድም ልማት የሀገሪቱ መሠረታዊ ጥያቄ ስለሆነ በሚል ለኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲ ቅንጦት እንደሆነ በመቁጠር ሁሉ ነገራችንን ለልማት በሚል ሰበብ በሀገራችን ኢኮኖሚ ለውጥና ዕድገት ላይ የፈጠረውን ደንቃራ በጥልቀት ይመረምራል፣ ትችቱንም ያቀርባል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሰማያዊ ፓርቲ በሕዝብ ተመርጦ የመንግሥትነት ሥልጣኑን ቢይዝ፤ በሀገሪቱ ውስጥ የሚያሰፍነውን የኢኮኖሚ መርህ ያሳያል፡፡ በዚህም መሠረት ሰማያዊ በሀገራችን ተግባራዊ ለማድረግ ያቀዳቸዉን የኢኮኖሚ ፖሊሲ አማራጮች በዝርዝር ያስቀመጠ ሲሆን በዋነኝነትም የግብርናውን ክፍለ ኢኮኖሚ በተመለከተ አርሶ አደሩን የመሬቱ ባለቤት የሚሆንበትን መብት ማረጋገጥ፤ እንዲሁም ሁሉም የኢኮኖሚ ዘርፎች የትኩረት አቅጣጫ ገበያ መር ሆኖ ዜጎች በፈለጉት ሙያ እና የሥራ መስክ ተሰማርተው፣ ሀብት የማፍራት፣ በሕጋዊ መንገድ የንብረት ባለቤት የሚሆኑበት በተጨማሪም በሀገሪቱ በሁሉም አቅጣጫዎች ተሰማርተው የሚሠሩበትን መብት የሚያረጋግጥ እንዲሆን የሚረዳ የፖሊሲ አማራጩን አስቀምጧል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ትናንት ሚያዝያ 29/2007 ዓ.ም ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በላከው ደብዳቤ ምርጫ ቦርድ በህግ የተሰጠውን ኃላፊነት እንዲወጣ ጠይቋል፡፡ የተሻሻለውን የምርጫ ህግ 532/1999 ዓ.ም አንቀፅ 58 ቁጥር 1 ላይ ‹‹አንድ ዕጩ ተወዳዳሪ መታወቂያ ካገኘበት ቀን አንስቶ ምርጫው ሁለት ቀን እስኪቀረው ድረስ ከአስተዳደሩ ሆነ ከማዘጋጃ ቤት ፈቃድ ሳይጠይቅ በፅሁፍ በማሳወቅ ብቻ የድጋፍ ስብሰባዎች አሊያም ሰላማዊ ሰልፎችን የመጥራት […]

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከሚያዝያ ፳፯ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. የመክፈቻ ጸሎት ሥነ ሥርዐት ጀምሮ ለአራት ቀናት ያካሔደውን የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ኹለተኛ ዓመታዊ ቀኖናዊ ጉባኤ ሲያጠናቀቅ ባወጣው ባለዐሥራ አንድ ነጥቦች መግለጫው÷ በሊቢያ ራሱን እስላማዊ መንግሥት(ዳኢሽ) እያለ የሚጠራው ዓለም አቀፍ አሸባሪ ቡድን ስለ ክርስቲያንነታቸው በግፍ እና በአሠቃቂ አኳኋን የገደላቸውን ኢትዮጵያውያን እና ግብጻውያን ኦርቶዶክሳውያን የሰማዕትነት ሥያሜ …

  ባለፈው ቅዳሜ ከወልቂጤ ከተማ ወጣ ብላ በምትገኘው አነስተኛዋ የዳርጌ ከተማ በፖሊሶች እና በአካባቢው ነዋሪዎች መካከል የተነሳው ግጭት ይህንን ዜና እስከፃፍኩበት ድረስ የቀጠለ ሲሆን በርካቶች ከተማዋን በመልቀቅ ወደወልቂጤ እና ወሊሶ ከተሞች በመሠደድ ላይ ይገኛሉ፡፡ በአካባቢው ከሚኖር ግለሠብ ለማጣራት እንደሞከርኩት ግጭቱ የተቀሰቀሰው ቅዳሜ በ24/08/2007 ዓ.ም አንድ በአካባቢው በስራ ላይ የተሠማራ ፖሊስ በግብርና የሚተዳደር ግለሠብን በአጋጣሚ በተነሳ […]

የዙሉ አክራሪዎች በኢትዮጵያዉያን እና ሌሎች የአፍሪካ ዜጎችን ላይ ኢሰብዓዊ ጥቃት በሚፈጽሙበት ጊዜ፣ እንደ ናይጄሪያ ያሉ አገሮች በዙማ መንግስት ላይ ጠንካራ አቋም ወሰዱ። ዙማ ተጽኖ ሲበረታባቸው፣ አስቸኳይ እርምጃዎች ለመዉሰድና ነገሮችን ለማረጋጋት ተገደዱ። ከነናይጄሪያ በደረሰው ግፊትና ጫና በደቡብ አፍሪካ ያለው ሁኔታ ለጊዜውም ቢሆን መረጋጋት ታየበት። በዚሁ ሁሉ ግን ሕወሃት/ኢሕአዴጎች የተከሰተዉን ቀውስ አሳንሰው በማቅረብ፣ ለኢትዮጵያዉያን ጥብቅና የቆሙ ሳይሆን፣ […]

“ይሄስ እገጭ ይላል” የኢትዮጵያዊያንና የኤርትራዊያን የጋራ የዘፈን ምሽት ደረጀ አሻግሬ ነፍሷን ይማርውና አያቴ የማይመስል ነገር ሲገጥማትና የማይሆን ወሬ ስትሰማ “ይህስ እገጭ ይላል” ትላለች። የሰማችው ነገር ፍሬ ከርስኪ ወይም እጅግ መናኛ ሆኖ ተስምቷት እያለ ያወራላት ሰው እንዴት ደፍሮ ተናገረው፣ አደባባይ አዋለው …

“ይሄስ እገጭ ይላል” የኢትዮጵያዊያንና የኤርትራዊያን የጋራ የዘፈን ምሽት Read more »

ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ገዥው ፓርቲ ምርጫውን ከአሁኑ እንደጀመረው ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች ካድሬዎች መራጮችን በጋንታ፣ በሴልና በኔትወርክ እያደራጁ ‹‹ኦህዴድ/ኢህአዴግን መርጫለሁ›› በሚል እያስፈረሙና ፎርም እያስሞሉ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በጋንታ፣ በሴልና በኔትወርክ ተደራጅተው ‹‹ኦህዴድን መርጠናል›› ብለው እንዲፈርሙ የተደረጉ ዜጎች ፎርሙን ከሞሉበት ቀን ጀምሮ የምርጫ ካርዳቸውን ለጋንታ፣ ሴልና ኔትወርክ መሪዎቻቸው እንደሚሰጡ ታውቋል፡፡ የጋንታ፣ የሴልና የኔትወርክ […]

በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን የሚገኙት የብአዴን ኢህአዴግ አመራሮች ህዝብ አይመርጠንም የሚል ስጋት ስላደረባቸው ለህብረተሰቡ የማደናገርያ ቃል እየገቡለት መሆናቸውን ተገለፀ፣የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው- የብአዴን ኢህአዴግ አመራሮች በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን የሚገኘውን ህዝብ በማዳበሪያ እዳ ተማርሮ እንደሚገኝ አስቀድመው ስለተረዱ ሱሪያችሁን በጭንቅላታችሁ አውጡ አይነት አስገዳች መመሪያ በመስጠት እያስጨነቁት እንዳልቆዩ አሁን ላይ ደርሰው ከህብረተሰቡ በርካታ ተቃውሞ ስላጋጠማቸው የወሰዳችሁትን […]

ሚያዝያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የግንቦት 7 ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በከፍተኛ ህመም በመሰቃየት ላይ ሲሆኑ እስካሁን በዶክተሮች ለመጎብኘት አልቻሉም። አያያያዛቸው የከፋ መሆኑን በማስመልከት የእንግሊዝ መንግስት አስቸኳይ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት መጻፉንም ምንጮቻችን ገልጸዋል። አቶ አንዳርጋቸው ያለፉትን ተከታታይ ወራት ጸሃይ የሚባል ነገር ሳያዩ ጨለማ ቤት …

ሚያዝያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎች ተይዘው በወረዳ 5 ቀበሌ 08/09 በሚገኝ እስር ቤት ውስጥ እንዲቆዩ የተደረጉ ወጣቶች ዛሬ ጧት ላይ በሶስት አይሲዙ መኪኖች ተጭነው ወዳልታወቀ ስፍራ መወሰዳቸውን የአይን እማኞች ተናግረዋል። ወጣቶቹ በቅርቡ በአዲስ አበባ የተደረገውን ተቃውሞ ተከትሎ ከየስፍራው የተሰባሰቡ ሲሆን፣ ከምርጫው ጋር በተያያዘ ረብሻ ሊያስነሱ ይችላሉ በሚል …

ሚያዝያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምክትል የውጭ ጉዳይ ሃላፊዋ ውንዲ ሸርማን በቅርቡ ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት በመንግስት ሚዲያ የኢትዮጵያን ዲሞክራሲና ምርጫ አድንቀው መናገራቸው ከየአቅጣጫው ተቃውሞ አስነስቶባቸዋል። ዋሽንግተን ፖስት የተባለው ታዋቂ ጋዜጣ በርእሰ አንቀጹ ወንዲ ሽርማንን የተቸ ሲሆን፣ ባለስልጣኗም ጋዜጣው በተሳሳተ መንገድ እንደተረዳቸውና ትችቱ ተገቢ አለመሆኑን በጽሁፍ መልስ ሰጥተዋል። ባለስልጣኗ ኢትዮጵያ አስቸጋሪ በሆነበት …

ሚያዝያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሬውተርስ የግብጽ መንግስታዊ  የዜና ማሰራጫን ጠቅሶ እንደዘገበው ፤ ሊቢያ ውስጥ ታግተው የነበሩና በግብጽ ጦር ጥረት ከታገቱበት የተለቀቁ 27 ኢትዮጰያውያን ዛሬ ሀሙስ ካይሮ አውሮፕላን ማረፊያ ገብተዋል። ኢትዮጰያውያኑ በግብጽ አውሮፕላን ተጉዘው ካይሮ ሲደርሱ በግብጽ ፕሬዚዳንት በአብደል ፋታህ አል-ሲሲ እና በሌሎች ከፍተኛ የግብጽ ባለስልጣናት አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን፤የአቀባበል ሥነ-ስር ዓቱ …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

የኤጲስ ቆጶሳትን ሢመት ጨምሮ በርካታ አጀንዳዎች ለጥቅምት ምልዓተ ጉባኤ ተላልፈዋል የአ/አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት አመራሮችን ለማሳሰር በአማሳኞች አጋሮች ተሞክሮ ነበር በሰንበት ት/ቤቶቹ ጥያቄ የተቆጡት ፓትርያርኩ፣ ረዳት ሊቀ ጳጳሱን በቀስቃሽነት ከሠዋል ከስድስት ያልበለጡ አጀንዳዎችን በማጽደቅ ትላንት የተጀመረው የ፳፻፯ ዓ.ም. የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ፣ ኹለተኛ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ማጠናቀቁ ተገለጸ፤ በነገው ዕለት ጠዋት መግለጫ […]

ሚያዝያ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት በቅርቡ በዩቴልሳት ስርጭቱን በአዲስ መልክ ማሰራጨት ቢጀምርም፣ ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ምክንያቱ በውል ባልተወቀ ሁኔታ ስርጭቱ ተቋርጧል። እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያን የስርጭቱ መቋረጥ ምክንያቱ እንዲገለጽላቸው  ለሚያቀርቡት ጥያቄ አስተዳደሩ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት እየሰራ መሆኑን አስታውቓል። የኮሚኒኬሽን መስሪያ ቤት የኢሳትን ስርጭት በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ተጽእኖ እየፈጠረ ነው …

ሚያዝያ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ( ኢሰመጉ) የአሁኑ ሰመጉ ሚያዚያ 26 ቀን 2007 ዓም ባወጣው መግለጫ በአዋሳና አዲስ አበባ በሚገኙ የድርጅቱ ፅህፈት ቤቶች ላይ ጉዳት እንደደረሰበት አስታውቋል። መንግስት በተለያዩ ወቅቶች ላይ በድርጅቱ ላይ አፍራሽ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን የጠቀሰው ሰመጉ፣ ሚያዚያ 24 ቀን 2004ዓም የሰመጉ የሃዋሳ ቅርንጫፍ …

ሚያዝያ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 9/2007 ዓ.ም መስቀል አደባባይ ላይ ህዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ ቢያቅድም ፣ ማካሄድ እንደማይችል ተነግሮታል። አስተዳደሩ ‹‹መስቀል አደባባይ ከፍተኛ የሆነ የትራፊክ መጨናነቅ ያለበት ከመሆኑም በላይ በርካታ የተከማዋ ነዋሪ የሚተላለፍበት እና የከተማው ነዋሪ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥር ነው” በማለት ጥያቄውን አለመቀበሉን ገልጿል። መንግስት በቅርቡ …

ሚያዝያ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው በመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ ፕሮጀክቶች ብቻ በዲዛይንና በሙስና በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ በመባከኑ፣ ግብር ከፋዩ ለአላስፈላጊ ወጪ ይዳረጋል። በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ባለቤትነት በፌደራል የውሃ ዲዛይንና ቁጥጥር ድርጅት አማካሪነት እና በፌደራል ውሃ ስራዎች ቁጥጥር ድርጅት ተቋራጭነት የግንባታ ስራው እየተካሄደው ባለው የርብ መስኖና ግድብ …

ሚያዝያ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሳሚ ሹክሪ ወደ ጁባ በማቅናት ከአገሪቱ ባለስልጣናት ጋር የሚመክሩ ሲሆን፣ ወደ ኤርትራም በማቅናት በሽበርተኝነት፣ እና በአካባቢው ባሉ የጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚመክሩ የግብጹ አል ሃራም ዘግቧል። ጉብኝቱ የደቡብ ሱዳን መንግስት ተቃዋሚዎች ከኢህአዴግ መንግስት ጋር አዲስ ግንኙነት መጀመራቸውን ባስታውቁ ማግስት እንዲሁም ሱዳን፣ ኢትዮጵያ እና ግብጽ የአባይን ግድብ በተመለከተ …

ሚያዝያ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኤደንን ለመያዝ በሃውቲ ሚሊሺያዎችና በቀድሞው ፕሬዚዳንት ሃዲ መካከል ከፍተኛ ጦርነት እየተካሄደ ሲሆን፣ 80 ሲቪሎች በጦርነቱ መሃል መገደላቸው ተዘግቧል። የሃውቲ ሚሊሺያዎች በቀድሞው ፕሬዚዳንት ታማኞችና በአረብ አገራት ጥምረት የአየር ሃይል ጥቃት የተነሳ እስካሁን የኤደንን ከተማ ለመያዝ አልቻሉም።የከተማ ነዋሪዎች በከፍተኛ የምግብና የውሃ እጥረት እየተሰቃዩ ነው።

(በዳንኤል አማረ)

የደም ማነስ ምልክቶች እንዳለብን የደም ማነስ አይነቶች ይለያያል መነሻው፣ የበሽታው ከባድነት እና ማንኛውም የጤና ችግር(ክንታሮት፣ ቁስለት፣ የወር አበባ ችግር ወይም ካንሰር የመሳሰሉት) አስተዋጽዎ ያደርጋሉ። ያለብዎት የደም ማነስ ቀለል ያለ ከሆነ ወይም…

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ዝርዝር መግለጫው በይፋ የሚወጣው በቀጣዩ የጥቅምት ምልዓተ ጉባኤ ነው በስደት ያሉ የሚመለሱበትና በኑሯቸው የሚቋቋሙበት ጠንካራ ውሳኔ ተወስኗል ከልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ጋራ የሚሠራ ኮሚቴ ይቋቋማል

 የምዕራብ ጎጃም – ፍኖተ ሰላም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ የባሕር ዳር ከተማ ሀገረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መደባቸው፡፡ ምልዓተ ጉባኤው ብፁዕነታቸውን የመደበው፣ የባሕር ዳር ከተማ የአዊ እና መተከል ዞኖች ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሚያዝያ ፱ ቀን በድንገተኛ ሕመም ማረፋቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ለብፁዕነታቸው መልካም የሥራ ዘመን …

በግፈኛው አይሲስ ከተሠዉት ወንድሞች መካከል ብርሃኑ ጌታነህ የተባለው በአዲስ አበባ አቧሬ አካባቢ ይኖር የነበረው ወንድም ይገኝበታል፡፡ ብርሃኑ ከሀገሩ የወጣው ከአራት ወራት በፊት ሲሆን ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ነበረ፡፡ ቤተሰቦቹ እንደሚናገሩት ወደ ሱዳን ሲሄድ ለባለቤቱ የ3 ወር የቤት ኪራይ ከፍሎ ነበር የሄደው፡፡ ሁለቱ ልጆቹ የስምንትና የአራት ዓመት እድሜ ያላቸው ሲሆኑ ቤተሰቡ በችግር ላይ እንደሚገኝ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተለው መሐመድ ካሣ ማክሰኞ ምሸት ወደ አሜሪካ ልበር ስል ነግሮኝ ነበር፡፡ እስካሁን መርዶ የተረዱት የሰማዕታቱ ቤተሰቦች ወላጆች፣ እኅቶች ወይም ወንድሞች ሲሆኑ ብርሃኑ ግን ባለቤቱና ገና ክፉና ደግ ያልለዩት ሁለቱ ልጆቹ ናቸው የተረዱት፡፡

ፎቶ፡- ያሬድ ሹመቴ

ከሰማዕታቱ ቤተሰቦች መካከል ይበልጥ ትኩረት የሚፈልጉት እነዚህ ምንም የማያውቁ ሕጻናትና እናታቸው ናቸው፡፡ መማር፣ ተምሮም ማደግ አለባቸው፡፡ ለዚህ ደግሞ መኖሪያ ቤትና የትምህርት ቤት ክፍያ ይፈልጋሉ፡፡ እናታቸውንም በሥራ ማሠማራት ይጠይቃል፡፡ በመሆኑም የክፉዎቹ ሥራ ውጤት እንዳይኖረው እነዚህን ሁለት ሕጻናትና እናታቸው እንርዳ፡፡ ቤታቸው አቧሬ አድዋ ድልድይ አካባቢ ነው፡፡  

ጉዳዩን በሚገባ ለመረዳትና ርዳታውን ለማስተባበር መሐመድ ካሣን ብታነጋግሩት ያግዛችኋል፡፡ ስልኩ 0911602795 ነው፡፡
ዳላስ አውሮፕላን ማረፊያ፣ ዋሽንግተን ዲሲ

በሊቀ ጳጳስ ሥር የማትመራ ቤተ ክርስቲያን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ናት ለማለት ያስቸግራል እንደቀደሙ ጠንክረን በማስተማር ወደ አንዲት ቤተ ክርስቲያን ጉያ ማሰባሰብ ይገባናል ቀኖናን በመጠበቅ ተልእኳቸውን በአንድነት እንዲያጠናክሩ ኹኔታው ሊመቻችላቸው ይገባል ይህን ጊዜያዊ ስሕተት ለማስተካከል በሚደረገው ጥረት ምእመናን ተባባሪ መኾን ይጠበቅባቸዋል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤውን፣ ዛሬ ሚያዝያ ፳፰ ቀን ፳፻፯ …

ከወደ ብሩንዲ ሕዝብ ነቅሎ ተነስቷል። በአገሪቱ ሊካሄድ ጥቂት ጊዜያት በቀሩት አገራዊ ምራጫ ላይ ለሶስተኛ ጊዜ ለመወዳደር ራሱን በእጩነት ያቀረቡት አንባገነኑ ፔሬ ኑኩሩንዚዛን ሕዝብ በቃህ በማለት ተናንቋቸዋል። ጭንቅ ውስጥ የገባው የፔሬ አገዛዝ ከሕዝባዊ ማዕበሉ ለመትረፍ እየተወራጩና አንዳንድ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ቢሆንም ሕዝቡ እርምጃዎችን ሳይገቱት ፊት ለፊት በመጋፈጥ ጉዞውን ወደ ቤተ መንግስቱ አድርጓል። ከጥቂት አመታት በፊት የሰሜን […]

የቀድሞዋ የጎንደሬዎች ከተማ ሁመራ አሁን ደግሞ የጎንደሬዎች መቀበሪያዋ የጅምላ መጨፍጨፊያዋ ሁመራ በየቀኑ የወገን የድረሱልን የሰቆቃ ድምፅ ይሰማል ሁኖም ግን ሰሚ ጀሮን አላገኘም ። ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ በሰሜን ጎንደር ምዕራባዊ ክፍል ከአማረኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያዊ የፀዳ ክልል ለመፍጠር ከ40 ዓመታት በላይ የሰራበት ቢሆን እንዳሁኑ ለይቶለት አያውቅም ቀደም ሲል በወልቃይት በጠገዴ በትግል በበረሃ እያሉ ጀምረው ነዋሪዎችን ሌሊት […]

  የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ትናንት ሚያዝያ 27/2007 ዓ.ም ከአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ኃላፊዎች ጋር መወያየታቸውን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት የዴሞክራሲ፣ ሰብአዊ መብትና ሰራተኞች ምክትል ዋና ፀኃፊ የሆኑት ሚስተር ስቲቭ ፌልድስቴይን ጨምሮ ሌሎችንም ኃላፊዎች አግኝተው ስለ ኢትዮጵያና ስለ ቀጠናው ሰፋ ያለ ውይይት […]

ሚያዝያ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዛሬ ሚያዚያ 27 ቀን 2007 ዓም የመተማ ከተማ ነዋሪዎች በህገወጥ መንገድ ተሰርተዋል የተባሉ ቤቶችን ለማፍረስ በሄዱ ቤት አፍራሾችና የወረዳው ባለስልጣናት ላይ ተቃውሞዋቸውን ለማሰማት ቢሞክሩም፣ የፌደራል ፖሊሶች በወሰዱት ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ 2 ነዋሪዎች በጥይት ተመትተው ሲገደሉ፣ 3 ደግሞ ለህይወት አስጊ በሆነ ሁኔታ ቆስለዋል። ከ50 ያላነሱ ሰዎች ደግሞ …

ሚያዝያ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሊቢያና ደቡብ አፍሪካ በግፍ የተገደሉ ኢትዮጵያውያንን ለመዘከርና ቁጣቸውን ለመግለጽ ገዢው ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ላይ የተገኙ ወጣቶች መንግስትን ሰድባችሁዋል በሚል ታፍሰው ከታሰሩ በሁዋላ፣ “ተቃውሞውን ያስነሱት በእስር ላይ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች ናቸው” ብላችሁ ካልመሰከራችሁ አትለቀቁም መባላቸውን የእስረኞች ቤተሰቦች ገልጸዋል። ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ቤተሰቦች ለኢሳት እንደተናገሩት፣ ወጣቶች ማታ …

ሚያዝያ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያን ወራሪውን የጣሊያን ጦር ድል ያደረጉበት 74 ኛ አመት በአዲስ አበባ ጀግኖች አባት አርበኞች በተገኙበት ተከብሯል። በአድዋ ጦርነት ወቅት ሽንፈትን የተከናነበው ጣሊያን፣  ከ40 አመት በሁዋላ ራሱን በዘመናዊ መሳሪያ፣ በገንዘብና በሰው ሀይል አደራጅቶ ኢትዮጵያን ቢወርም፣ አባት አርበኞች ለ5 አመታት በዱር በገደሉ ባደረጉት ተጋድሎ፣ የፋሽስት ሙሶሎኒን ጦር ድል …

ሚያዝያ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ” የኢንዱስትሪውን  ልማት በተሳለጠ መንገድ ይዘን በመጓዝ የአምስት አመቱን ዕቅድ ለማጠናቀቅ  በስኬት ጎዳና ላይ ነኝ ” በሚል  የገዢው መንግስት ቢናገርም፤ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሃብቶች በርካታ ችግር እየገጠማቸው መሆኑን ተናገሩ፡፡ ሰሞኑን በተካሄደው የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት  ከከፍተኛ ባለሃብቶች ጋር ባደረጉት የውይይት መድረክ ላይ ፣ ባለሃብቶች  እንደገለጹት …