የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽ በኢትዮጵያ የመጀመርያውን የብረት ማዕድን ማውጫና ማቅለጫ ፋብሪካ ሊገነባ ነው፡፡ ፋብሪካው የሚገነባው በምሥራቅ ወለጋ ዞን ነቀምት ከተማ ሲሆን፣ የብረት ክምችቱም በምዕራብ ወለጋ ዞን ቢቅላል አካባቢ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

ለዚህ ግዙፍና ለአገሪቱ የመጀመርያ ለሆነው ፋብሪካና የብረት ማዕድን ማውጪያ ከሦስት ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚደረግ፣ ግንቦት 6 ቀን 2007 ዓ.ም. የፋብሪካው የመሠረት ድንጋይ በነቀምት ከተማ በተቀመጠበት ወቅት ተገልጿል፡፡

የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብርጋዴር ጄኔራል ጠና ቁሩንዴ እንደተናገሩት፣ የሚገነባው የብረታ ብረት ፋብሪካ በዓመት ከሦስት መቶ ሺሕ ሜትሪክ ቶን በላይ የተለያዩ ብረቶችን ማምረት ያስችላል፡፡

በቀድሞው ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ባለቤትነት በኢትዮጵያ መሠረታዊ ለውጥ ማምጣት ያስችላሉ የተባሉትን የድንጋይ ከሰልና የብረት ማዕድን መገኛ ለማወቅ ጥናት ተካሂዶ ነበር፡፡ በሚኒስቴሩ በተቋቋመው ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤትና የቻይና ኩባንያዎች በተሳተፉበት ጥናት፣ በምዕራብ ኢትዮጵያ ኢሉአባቦራ ዞን ያዩ አካባቢ ከፍተኛ የድንጋይ ከሰል መኖሩን፣ በዚሁ ቀጣና ውስጥ ምዕራብ ወለጋ ቢቅላል አካባቢ ደግሞ የብረት ማዕድን ክምችት (አይረን ኦር) ከሌሎች ማዕድናት ጋር መኖሩን አመልክቷል፡፡

በወቅቱ እነዚህን ማዕድናት ማውጣትና ማምረት የሚያስችል ፋብሪካ ለማቋቋም የሚፈለገው ካፒታል ከፍተኛ በመሆኑ ሳይሞከር እንደቀረ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ነገር ግን ከመከላከያ ተገንጥሎ በኢትዮጵያ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ለውጥ እንዲያመጣ የተቋቋመው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን፣ በሒደት በሁለቱም ዘርፎች በጥልቀት መግባት ችሏል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በአሁኑ ወቅት ያዩ አካባቢ የሚገኘውን የድንጋይ ከሰል በማውጣት ማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ከጀመረ ዓመት አስቆጥሯል፡፡ ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ደግሞ የብረት ማዕድን አውጥቶ የሚያቀልጥበት ፋብሪካ ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ አስቀምጧል፡፡

በብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ዘርፍ ግዙፍ ኩባንያ የሆነው ስቲሊ አርኤምአይ  የኦፕሬሽንና የፖሊሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ለማ የፋብሪካውን መገንባት አስመልክተው ለሪፖርተር በሰጡት አስተያየት፣ ከውጭ ይገባ የነበረው ቢሌት (ጥቅል ፌሮ ብረት) አገር ውስጥ ማምረት መቻል ትልቅ ትርጉም አለው፡፡

አቶ ተፈራ ጨምረው እንደገለጹት፣ አገር ውስጥ ሲመረት የቆየው ብረት ከወዳደቁ ብረታ ብረት (ስክራፕ) እና ከውጭ በሚገባ ቢሌት ነው፡፡ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ወደዚህ ዘርፍ ከገባ ዩክሬን፣ ቻይናና አውስትራሊያ የሚታወቁበት የብረት ምርት በኢትዮጵያ እንዲመረት ያስችላል፡፡

‹‹ይህ ለአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ወሳኝ ነው፤›› በማለት አቶ ተፈራ የፕሮጀክቱን ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ አብራርተዋል፡፡

የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ይኼን አዲስ ፕሮጀክት በሁለተኛው የአምስት ዓመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ ያካተተ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል፡፡

የፕሮጀክቱ ዕውን መሆን ለምዕራብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ኢኮኖሚያዊ መነቃቃት ከመፍጠሩም ባሻገር፣ በሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች የሥራ ዕድል ይፈጥራልም ተብሏል፡፡ 

 

አስተዳደሩ የኮንዶሚኒየም ቤቶችን ዋጋ የሚያጠና ልዩ ኮሚቴ ማቋቋሙ ተሰማ

ጭማሪው በካሬ ሜትር ከ27 እስከ 45 በመቶ መሆኑ ተጠቁሟል

‹‹አስተዳደሩ ያደረገው ጭማሪ 15 በመቶ ብቻ ነው›› የቤቶች ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መጋቢት 13 ቀን 2007 ዓ.ም. ለአሥረኛ ጊዜ ዕጣ ያወጣባቸው 41 ሺሕ የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ሰባት ሺሕ ለልማት ተነሽዎች ናቸው)፣ በዋጋቸው ላይ ከፍተኛ ጭማሪ መደረጉን ካቢኔው ሊቀበለው ባለመቻሉ፣ ልዩ ኮሚቴ ተቋቁሞ የዋጋ ጥናት እየተደረገ መሆኑ ተሰማ፡፡

 

የተወሰኑ የካቢኔ አባላት ሚያዝያ 26 ቀን 2007 ዓ.ም. በከንቲባው ጽሕፈት ቤት ስብሰባ አድርገው በኮንዶሚኒየሙ ወጪ ላይ መግባባት ባለመደረሱ፣ ልዩ ኮሚቴ ተቋቁሞ የዋጋ ጥናት እንዲደረግ ስምምነት ላይ መደረሱን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ቀደም ብሎ ተቋቁሞ የነበረው ኮሚቴ ስለ ኮንዶሚኒየም ቤቶች ያጠናው ጥናት ከመጠን በላይ የተጋነነ በመሆኑ፣ ከሁሉም ዘርፍ የተወጣጣ ልዩ ኮሚቴ ተቋቁሞ ዋጋው እንደገና መጠናት እንዳለበት ውሳኔ ላይ መደረሱን ምንጮች አስረድተዋል፡፡  አዲስ የተቋቋመው ኮሚቴ የመጀመርያ ስብሰባውን ግንቦት 3 ቀን 2007 ዓ.ም. ማድረጉንም አክለዋል፡፡

የከተማ አስተዳሩ ለቤቶች ልማት ፕሮግራም ከስድስት ቢሊዮን ብር በላይ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መበደሩን የሚያስታውሱት ምንጮቹ፣ ለቤቶች ግንባታ የወጣው ወጪና በባንክ ያለው ገንዘብ ሊጣጣም ባለመቻሉ ሁለቱን አጣጥሞ ለመቀጠል በቤቶቹ ላይ ዋጋ መጨመር እንዳለበት የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ እምነት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተለይ የቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት የተወሰኑ ሠራተኞች የአሥረኛው ዙር ዕድል ተጋሪ በመሆናቸው፣ ጽሕፈት ቤቱ ሥራውን እንዴት እየሠራና ምን ዓይነት ወጪ ለምንና እንዴት እየወጣ እንደሚገኝ በቅርበት ስለሚያውቁ፣ ጠንከር ያሉ ጥያቄዎችን  ያቀረቡ መሆኑንም ምንጮች ገልጸዋል፡፡ 

በቤቶቹ ላይ መደመር የሌለባቸው የተለያዩ ወጪዎች በብክነት ወይም በሌላ ወጪ መመዝገብ ሲገባቸው በቤቶቹ ላይ በመደመራቸው፣ ለግንባታና ለዲዛይን ወጪ ተገምቶ ሥራውን ለምርምር ብድር የተወሰደ ቢሆንም፣ ከባንክ ጋር የተገባውን ብድር ማፋለሱን ገልጸዋል፡፡ ካቢኔውም በተሠራው የግንባታና የዲዛይን ዋጋ መሠረት ጽሕፈት ቤቱ መሥራት ሲገባው፣ የተጋነነ ዋጋ መቅረቡ ትክክል አለመሆኑን መግለጹን  ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡ የጽፈሕት ቤቱም ሠራተኞች ወጪው ለብቻ መያዝ እንዳለበት በመግለጽ የካቢኔውን አቋም እየደገፉ መሆኑም  ተጠቁሟል፡፡ 

የካይዘን ኢንስቲትዩት ባደረገው ጥናት መሠረት በቤቶች ግንባታ ላይ 33 በመቶ ብክነት መኖሩን ለካቢኔው ማሳወቁን የገለጹት ምንጮች፣ ብክነቱን በተለያዩ ነገሮች ማወራረድ ሲቻል በቤቶቹ ዋጋ ላይ መደመር አግባብ አለመሆኑን ካቢኔውም ሆነ የዕጣው ዕድለኞች የሚስማሙበት ሐሳብ መሆኑንም ምንጮች አስረድተዋል፡፡

የቤቶች ልማት ፕሮጀክት ማንኛውም ዓይነት ክትትልና ጥንቃቄ ቢደረግበት እንኳ እጅግ በጣም አስቸጋሪና ለምዝበራ የተጋለጠ መሆኑን፣ የቤቶች ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ኃይሌ በቅርቡ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የከተማ ልማትን በተመለከተ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ባደረጉት ክርክር ላይ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ቢሮ ኃላፊ በሚያዝያ ወር የመጀመርያ ሳምንት አካባቢ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በአሥረኛው ዙር ዕጣ በወጣባቸው ቤቶች ላይ የተደረገው ጭማሪ እንደሚባለው የተጋነነ ሳይሆን፣ 15 በመቶ ብቻ እንደሆነ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡ ነገር ግን አስተዳደሩ የነባር 20/80 ባለ አንድ፣ ሁለትና ሦስት መኝታ ቤቶችና እንዲሁም የስቱዲዮ ቤቶችን ለመሸጥ ካስቀመጠው ዋጋ ላይ ከ27 እስከ 45 በመቶ ጭማሪ ማድረጉን የዋጋውን ልዩነት ያሰሉ ነዋሪዎች እየገለጹ ነው፡፡

የ10/90 ተመዝጋቢዎች ዝቅተኛ ክፍያ በካሬ ሜትር 1,310 ብር የሚከፍሉ መሆኑን በምዝገባ ወቅት የተነገረ ቢሆንም፣ በአሥረኛው ዙር ግን በካሬ ሜትር 1,910 ብር እንዲከፍሉ ተደርጓል፡፡ ልዩነቱ 600 ብር ወይም 45 በመቶ መሆኑን ነዋሪዎቹ ይናገራሉ፡፡ ዝቅተኛው የስቱዲዮ ስፋት 29 ካሬ ሜትር ነበር፡፡ 

በተመሳሳይ ሁኔታ ነባር የ20/80 ባለሁለት መኝታ ቤት ተመዝጋቢ በካሬ ሜትር የሚከፍለው 3,452 ብር የነበረ ቢሆንም፣ በአሥረኛው ዙር ዕድለኛ የሆነ ግን በካሬ ሜትር 4,394 ብር ይከፍላል፡፡ ሲመዘገብ ከሚያውቀው ዋጋ ጋር ያለው ልዩነት 942 ብር ወይም 27 በመቶ መሆኑን ነዋሪዎቹ አሥልተዋል፡፡ ዝቅተኛው ባለሁለት መኝታ ቤት ስፋቱ 65 ካሬ ሜትር ነው፡፡ 

በመሆኑም የዕጣው ባለቤቶች መንግሥት መሬት በነፃ፣ ሁሉንም የግንባታ ግብዓቶች ከአገር ውስጥ ባደረገበት ጊዜ ዋጋው ይኼንን ያህል ሊጋነን እንደማይገባ እየገለጹ ባሉበት ወቅት፣ አስተዳደሩ ዋጋው በልዩ ኮሚቴ እንዲጠና ማድረጉ ተገቢና ዕድለኞቹንም ያሰበ ሊሆን ይችላል በሚል ተስፋ ላይ መሆናቸውን ምንጮች አስረድተዋል፡፡ ነዋሪዎች የሠሩት ሥሌት ትክክል መሆን አለመሆኑንና አዲስ ስለተቋቋመው ኮሚቴም ማብራሪያ እንዲሰጡ የአስተዳደሩት ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎችንና የከንቲባ ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎችን ለማግኘት የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡

 

የግድብና የመስኖ ፕሮጀክቶች አፈጻጸማቸው ዝቅተኛ ነው ተባለ

የኢትዮጵያ የውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ከውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር ውል ፈጽሞ እያከናወናቸው ያሉ ፕሮጀክቶች አፈጻጸማቸው ዝቅተኛ ነው ተባለ፡፡

የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሚኒስትሩ አቶ ዓለማየሁ ተገኑ ለሚመራው የድርጅቱ ሥራ አመራር ቦርድ አስቸኳይ ማስተካከያ እንዲያደርግ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ተጻፈለት፡፡ 

ለሥራ አመራር ቦርዱ የማሳሰቢያው ደብዳቤ የተጻፈው የርብ የመገጭና  የጊዳቦ ግድቦች፣ የከሰም መስኖ መሠረተ ልማት ግንባታና የተንዳሆ የኅብረተሰብና የስኳር ልማትና መጠጥ ውኃ ግንባታን ለማከናወን ውል የገባው የውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት፣ ፕሮጀክቶቹን በማጓተቱና አፈጻጸሙ ዝቅተኛ በመሆኑ ምክንያት ነው ለቦርድ ማስጠንቀቂያ የተጻፈው፡፡

በውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ወንድሙ ተክሌ ሚያዝያ 21 ቀን 2007 ዓ.ም. የተጻፈው ደብዳቤ ውኃ ሥራዎች ድርጅት ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጋር በገባው ውል መሠረት በአማራ ክልል የሚገኙትን የርብና የመገጭ ግድቦች ግንባታን፣ በኦሮሚያ ክልል የጊደቦ ግድብ ግንባታን፣ በአፋር ብሔራዊ ክልል የከሰም መስኖ መሠረተ ልማት ግንባታና የተንዳሆ የኅብረተሰብና የስኳር ልማትና የመጠጥ ውኃ ግንባታ ለማካሄድ ኮንትራት የወሰደ ቢሆንም፣ ፕሮጀክቶቹ በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ሊጠናቅቁ አለመቻላቸው ደብዳቤው ያስረዳል፡፡ ሚኒስቴሩ በተደጋጋሚ የቀረቡለትን የማራዘሚያ ጥያቄዎችም በመቀበል የውል ጊዜን ያራዘመ ቢሆንም፣ አንዳንዶቹ ፕሮጀክቶች ወደ ኪሳራ ሊገቡ መገደዳቸውንም ያክላል፡፡

የርብ ግድብ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 2 ቀን 2007 ተጀምሮ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 30 ቀን 2011 የሚጠናቀቅ ቢሆንም፣ በተያዘው ዓመት እ.ኤ.አ. 2015 አፈጻጸሙ 76.5 በመቶ ነው ተብሏል፡፡ ነገር ግን እ.ኤ.አ. ከግንቦት 2011 እስከ ሰኔ 2014 ድረስ እንዲራዘም መደረጉን ለውኃ ሥራዎች ድርጅት ሥራ አመራር ቦርድ የተላከው የማሳሰቢያ ደብዳቤ ይገልጻል፡፡ የመገጭ ግድብ ግንባታም እ.ኤ.አ. መጋቢት 22 ቀን 2012 ዓ.ም. የተጀመረ ሲሆን፣ መጠናቀቅ ያለበት እ.ኤ.አ. ነሐሴ 30 ቀን 2016 ነው፡፡ በዚህ ዓመት ያለው የአፈጻጸም መጠን ግን 26.05 በመቶ ብቻ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የጊዳቦ ግንባታ ግንባታ የተጀመረው ጥር 3 ቀን 2002 ዓ.ም. ሲሆን፣ ይጠናቀቃል የተባለው ጥር 3 ቀን 2004 ዓ.ም. መሆኑ ተገልጿል፡፡ ነገር ግን አራት ጊዜ ውሉ እንዲሻሻል ተደርጎ አሁን ያለበት አፈጻጸም 63.86 ብቻ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡ በሌሎቹም ፕሮጀክቶች የሚታየው አፈጻጸም ተመሳሳይ መሆኑን የሚያብራራው የሚኒስቴሩ ደብዳቤ፣ ባለድርሻ አካላቱ ማለትም ሚኒስቴሩ የውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅትና አማካሪው የውኃ ሥራዎች ዲዛይንና ቁጥጥር ድርጅት ተመካክረው ቦርዱ እንዲያውቀው ያደረጉ ቢሆንም ሊሻሻል አለመቻሉን ያብራራል፡፡

ሦስቱ ባለድርሻ አካላት ባደረጉት ምክክር ድርጅቱ አጠቃላይ ያለበትን ሁኔታ ቦርዱ እንዲያውቀው ተደርጎ ለማበረታታት መሞከሩን፣ ድርጅቱ ያጋጠመውን የፋይናንስ ችግር በመረዳት ከክፍያ ተመላሽ የሚደረግ 250 ሚሊዮን ብር በብድር መልክ እንዲሰጠው መደረጉን ደብዳቤው ያስረዳል፡፡

ከመንግሥት ጋርም በመነጋገር ለርብና ለመገጭ ግድቦች ግንባታ ከሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን አዲስ የዋጋ ማሻሻያ መደረጉን፣ እንዲሁም መንግሥት የድርጅቱ ካፒታል እንዲያድግ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በኩል የተወሰነ ክፍያ መፈጸሙንም ደብዳቤው ያብራራል፡፡ ነገር ግን ከላይ የተገለጹት ድጋፎች የተደረጉለት ቢሆንም የፕሮጀክቶቹ አፈጻጸም ሊሻሻል አለመቻሉንም ጠቁሟል፡፡ ፕሮጀክቶቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል ከማሳየት ይልቅ ዝቅተኛ አፈጻጸም ላይ መሆናቸውን ገልጾ፣ የውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ሥራ አመራር ቦርድ ልዩ ትኩረት በመስጠትና ችግሮቹን በመፈተሽ በቀሪው ጊዜ አፈጻጸሙ የሚሻሻልበትን  የበኩሉን ሚና እንዲጫወት የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር በደብዳቤው አሳስቧል፡፡

የሥራ አመራር ቦርዱ ከሚኒስቴሩ በደረሰው ማሳሰቢያ መሠረት ምን እያደረገ እንደሚገኝ ማብራሪያ ለማግኘት የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡

 

 

ሚስቱ በይሆት ተያዘች ሚስቲቱ ሰውን በማዘዋወርና በመሽጥ አደኛ ስትሆን አቡ ስይፍ ደግሞ ሰውን ከመደል ውጭ ሌላ ሰራው ነዳጅን በመሽጥና ገንዘብ በማጠራቀም የታወቀ መሪ ነበር የአሜሪካ ኮማንዶ ሶሪያ ውስጥ ሰርጎ በመግባት አቡ ሰይፍን ሲገል ሚስቲቱን በይሆት ይዘዋታል (CNN) U.S. Special Operations forces killed a senior ISIS commander during a daring raid intended to capture him in […]

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

በቤኒሻንጉል  ከ50 በላይ ነዋሪዎች በአካባቢዉ የወያኔ ታጣቂዎች መገደላቸውን ተነገረ ፡፡ የህወሓት አገዛዝ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀመ ነው ተባለ:: አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ከውህደቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ታጋዮችን  አስመረቀ፡፡ በዚህ ሳምንት”አቦይ ስብሐት እንደአሞራ አስሬ ይዞረኛል”ሲሉ  አቶ ኃይለ ማርያም መናገራቸው ተሰምታል የመላው ኢትዮጲያ አድንድነት ድርጅት (መኢአድ) አንዱ ክንፍ ምርጫዉን ጥሎ ኤርትራ መግባቱ ተነገረ […]

በተለያዩ የሐይማኖት ተቋማትና የሲቪክ ድርጅቶች ተሳታፊነት በዛሬው ዕለት ዋሽንትግተን ዲሲ ከተማ ውስጥ በርካታ ቁጥር ያለቸው ኢትዮጵያዊያን ዘር፣ሐይማኖት፣ጾታና ዕድሜ ሳይለዩ በነቂስ በመገኘት ታላቅና ደማቅ በዓይነቱ ልዩ የሆነ ዝግጅት አድርገዋል። የዝግጅቱ ዋና ትኩረት በሊቢያ በሰማዕትነት ያለፉትን ኢትዮጵያውያን ለመዘከርና እንዱሁም በተለያዩ አገሮች ውስጥ …

በዋሽንግተን ዲሲ የቤተክርስቲያን የአንድነት ጥሪ በተሳካና በደመቀ ሁኔታ መካሄዱን የሚያሳይ በፎቶ የተደገፈ ዘገባ (ተጨማሪ መረጃ ተካቷል) Read more »

በጋምቤላ ክልል ጎደሬ ወረዳ ሜጢ ከተማ አካባቢ ሰሞኑን በተቀሰቀሰ ግጭት አምስት ሰዎች መሞታቸውን የአይን እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል ። በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ የሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ማጣታቸውን የሚናገሩት የወረዳው ነዋሪዎች የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ጥያቄዎችን ባነሱ ነዋሪዎች ላይ የሚወስዱት እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉን አስረድተዋል ። በተለይ ከሁለት ሳምንት በኋላ ከሚካሄድውን ምርጫ ጋር በተያያዘ ውጥረቱ ተባብሶ መቀጠሉን የገለጹት እማኞች፥ ከተገደሉት …

በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ ከተማ እና አካባቢዋ ያሉ አብያተ ክርስቲያንናት እንዲሁም የተለያዩ የሲቪል ድርጅቶች በቅርቡ በየመን፥ በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ኢትዮጵያዊያንን ለመዘከር እሁድ እለት በዚህ በዋሺንግተን ዲሲ ከተማ የመታሰቢያ ዝግጅቶችን አካሄዱ። ነዋሪነታቸው በዋሺንግተን ዲሲ እና በአካባቢዋ በርካታ ኢትዮጵያዊን በታደሙበት በዚህ ዝግጅት፥ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ሟች ኢትዮጵያዊያንን አስመልክቶ ያስተላለፉት የሀዘን መልክት ተነቧል። ልዪ የጸሎትና …

ሚያዝያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተጠናክሮ በደረሰው ሪፖረት ህዝቡ “እኛ ኢቲቪን (ኢቢሲን) አይተን አናውቅም ፤ ለውሸት ጣቢያ ፈፅሞ ክፍያ አንፈፅምም ፤ በአይናችን ያየነውን ለሚክድ ሚዲያ እኛ ምንም ድጋፍ አናደርግም፡፡ እንደዚህ የሚባል ጣቢያ አለ እንዴ ፤ ኢቲቪ የሚባል ጣቢያ መኖሩን አናውቅም ነበር ” የሚሉ አስተያየቶች ሲሰጡ፣ አንዳንዶች ደግሞ “እኛ ከኢሳት …

ሚያዝያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በስልጣን ላይ ያለውን አገዛዝ በማንኛውም አማራጭ ለማስወገድ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ የተቃዋሚ ሃይሎች በጋራ ለመታገል የሚያስችላቸውን ውይይት መጀመራቸውን ለኢሳት በላኩት መግለጫ አስታውቀዋል። ውይይቱን የጀመሩት የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ( ትህዴን)፣ የጋምቤላ ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ፣ የቤንሻንጉል ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ፣ የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄና አርበኞች ግንቦት7 ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ …

ሚያዝያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዘጋቢያችን በላከችው ሪፖርት የገዢው መንግስት ካድሬዎች በየመንደሩ በመዞር የሚደርጉት የምርጫ እንቅስቃሴ የነዋሪዎችን ነጻነት ከማሳጣቱ በተጨማሪ፣ ኢህአዴግ በሚጠራው የመንደር ስብሰባዎች የሚቀር ሰው የተቃዋሚ ድርጅት ደጋፊ ተብሎ ይመዘገባል። የገዢው ፓርቲ አባላትና የቀበሌ አመራሮች በየሰፈሩ በሚያደርጉት ስብሰባ በአካባቢው የሚኖሩ ባለሃብቶችን ያለ ፈቃዳቸው ለዕለቱ የሚስፈልገውን ለቡና፤ዳቦ እና ቆሎ ዝግጅት የሚውል …

ሚያዝያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው መንግስት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም የአይ ኤስ አይ ኤስን ድርጊት ለማውገዝ በጠራው ሰልፍ ላይ በተነሳበት ተቃውሞ ሰበብ ግንቦት 4/2007 ዓ.ም ተይዛ የታሰረችው የሰማያዊ ፓርቲ አባል ሜሮን አለማየሁ እንዲሁም በሰልፉ ወቅት ከተያዘ በኋላ በ25 ሺህ ብር ዋስ ወጥቶ እንደገና የታሰረው የቀድሞው አንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

ዛሬ ግንቦት 7 ቀን 2007 ዓ.ም ነው። ከዛሬ 10 ዓመታት በፊት ግንቦት 7 ቀን 1997 ዓ.ም. ነበር። አይገርምም? “የ1953ቱ የመግሥቱ ንዋይ መፈቅለ መግሥት ሙከራ ለ1966 ቱ ሕዝባዊ አብዮት ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል” ሲሉ ሩቅ .. ሩቅ የነበረ እውነት አድርጌ ስቀበለው ኖረዓለሁ። በ53 እና በ66 መካከል ያሉት 13 ዓመታት ጥቂት መሆናቸውን የገባኝ ዛሬ ነው። ይኸው እኔም ትናንትን […]

All roads lead to the the Etsako West Local Government Council Marriage Registry, Auchi on Friday as Governor of Edo state, Adams Oshiomhole, takes a new wife. Oshiomhole is remarrying four years after the death of his first wife, Clara. The bride is Ethiopian-born Miss Lara Fortes, a model and former air hostess. Already, wedding […]

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

በጋምቤላና ደቡብ ክልል ድንበር አካባቢ የሪ በምትባል ቀበሌ 7 ሰዎች በተገደሉ ማግስት ሌሎች 5 ሰዎች ደግሞ በቴፒ ከተማ እንድሪስ ቀበሌ ውስጥ ከሌሊቱ 8 ሰአት ላይ በጥይት ተደብድበው መሞታቸውን የአካባቢው ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። የአካባቢው ሰዎች እንደሚሉት ከሟቾቹ መካከል አባትና ልጅ ይገኙበታል። ዘግይቶ በደረሰን ዜና ደግሞ ገዳዮቹ ፖሊሶች ናቸው። ነዋሪዎች እንደሚሉት ሰዎቹ ይተገደሉት በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ አማጽያንን ያስጠጋሉ፣ …

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲዊ አንድነት መድረክ ቅዳሜ ግንቦት 8 ቀን 2007 ዓ.ም በጃንሜዳ የተጠራውን ህዝባዊ ስብሰባ አስመልክቶ ከኢሳት ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ በህዝቡ በኩል በተለይ ወጣቱ መንቀሳቀሱን ይሁን እንጅ ብዙ ቦታዎች ላይ የምርጫ ሜዳው መዘጋቱን ገልጸዋል። ህዝቡ በስሜት ስብሰባዎችን መሳተፉን የገለጹት ዶ/ር መረራ ፣ በምርጫው መቀመጫ ባይገኝ የህዝቡን ትግል ወደ አንድ እርምጃ ለመውሰድ በሚደረገው ሙከራ በብዙ ቦታዎች …

ፕሬዚዳንት ኑኩሩንዚዛ ለሶስተኛ ጊዜ ለመመረጥ መወሰናቸውን ተከትሎ የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ወደ መፈንቅለመንግስት ከተቀየረ በሁዋላ፣ አገሪቱ በምን ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ በትክክል ለማወቅ አልተቻለም። የፕሬዚዳንቱ ደጋፊዎች ዋና ዋና የሚባሉትን ተቋማት በተለይም የሬዲዮ ጣቢያ፣ አየር መንገዱንና ቤተመንግስቱን በመቆጣጠር መፈንቅለ መንግስቱ እንደከሸፈ ቢያስታውቁም፣ መፈንቅለመንግስቱን የሚደግፉ ሃኢሎች በበኩላቸው፣ ተቋማቱ በእነርሱ ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ እየገለጹ ናቸው። መፈንቅለመንግስቱ ያልተሳካ መሆኑን የሚያመላክቱ ፍንጮች …

ጁባ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ባወጣው መግለጫ፣ በዩኒቲ ግዛት የመንግስት ወታደሮች በወሰዱት ጥቃት በሲቪሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል። ተቃዋሚዎች አጽፋዊ እርምጃ በመውሰድ ጦርነቱን ከማባባስ እንዲቆጠቡ መግለጫው ጠይቋል። የደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር እስካሁን ውጤት ሊያመጣ ባለመቻሉ የሚፈናቀሉ ደቡብ ሱዳናውያን ቁጥር ጨምሯል። እስካሁን ባለው መረጃ ከ300 ሺ ያላነሱ የደቡብ ሱዳን ዜጎች ተፈናቅለዋል።

Wisdom Ethiopia ዛሬ በዓለማችን ላይ ትልቁን ስፍራ ይዘው የሚንቀሳቀሱት አንቀሳቃሽ ሞተሮች ገንዘብና ስልጣን ናቸው፡፡ገንዘብ ለሰው ልጆች በምድር ላይ ሲኖሩ የሚያስፈልጋቸውን ነገር ለማሟላትና ለመግዛት አስፈላጊው ነገር ነው፡፡ሀገር በአግባቡ እንድትመራና በሰው ልጆች መካከል መከባበርና ሰላም እንዲኖር ስልጣን ያለው አካል መኖር እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ነገር ግን ገንዘብም ሆነ ስልጣንም በአግባቡ ካልተጠቀምንባቸው ከጠቃሚነታቸው ይልቅ ጉዳታቸው ሊያመዝን ይችላል፡፡ማለትም ሰዎች ገንዘብን […]

ምርጫ የሚደረገው የፖለቲካ ስልጣን ለመያዝ መሆኑ ግልፅ ነው። በዚህ ወቅት ሁሉም ፓርቲዎች ወንበሩን ለመያዝ ይፎካከራሉ ማለት ነው። ህዝብም ሁሉም ፖለቲካ ፓርቲ የሚያቀርቧቸው አማራጭ ፖሊሲዎች በክርክርና በቅስቀሳ ወቅት በመገምገም ይበጀኛል የሚለውን ይመርጣል ማለት ነው። ወያኔም ዲሞክራሲያዊ መንግስት ነኝ ብሎ የሚያምን መንግስት እንደመሆኑ መጠን ይህን የመከተል ግዴታ አለበት። ሬድዋን ሁሴን ለሚዲያዎች በሰጡት ቃለ መጠይቅ ሰማያዊ ፓርቲ ለገዢው […]

* .ክርስቲያን መምህራን እና የመንግሥት ሠራተኞችተመርረው እና ተሠቃይተው ወረዳውን እንዲለቁከሥራ ማባረርን ጨምሮ እስራት፣ያለበቂ ምክንያት የደመወዝ ቅጣት፣ ያልተገባ የሥራ ምደባ እና ዝውውር እንዲኹም ‹‹እናርዳችኋለን›› በሚል የግድያ ዛቻይደረግባቸዋል፤ *.የሚያስቀድሱበት እና የሚቀበሩበት ቤተ ክርስቲያን መሥሪያ ቦታ ያገኙት በብዙ ውጣ ውረድ ነው፤የቂልጦ ጎሞሮ ቅድስት ማርያም ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንንለመሥራት በኮሚቴ የተሰባሰቡ ምእመናን በአንድነት ባሉበት ቤትበምሽት ቤንዚን በማርከፍከፍ እሳት ተለቆባቸዋል፤ የወረዳው […]

የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ እና አዲስ አበባ ውስጥ የወረዳ 17 ዕጩ ተወዳዳሪ የሆነው አቶ ዮናታን ተስፋዬ የታዛቢዎቹን ፎቶ ግራፍና አድራሻ ለምርጫ ጣቢያው እንዲያሳውቅ ተጠየቀ፡፡ እስካሁን ከታዛቢ ሙሉ ስም ውጭ ፎቶግራፍና አድራሻ የሚጠየቅበት አሰራር እንደሌለ የተገለጸ ሲሆን ምርጫ ቦርድም ለፓርቲው በላከው ደብዳቤ የታዛቢዎችን ስም ዝርዝር እንዲልኩ ማስታወቁ ተመልክቷል፡፡ ይሁንና የወረዳ 17 ምርጫ ጣቢያ ኃላፊ የሆኑት […]

ባለቤቴ የሲጃራ ሱስ አለባት፡፡ ብመክራት ባስመክራትም ማጨሷን ልትተው አልቻለችም፡፡ በተለይ ቤተሰቦቼ ጋር ይዣት ስሄድ ይሄ ልምዷ አንገቴን እያስደፋኝ ነው፤ ባለቤቴ ከዚህ ሱስ እንድትወጣ ምን ላድርግ?
ለማ (ከአዲስ አበባ)
ውድ ለማ በመጀመሪያ ደረጃ ይህን ጥያቄ በማቅረብህ ለባለቤትህ ያለህን ፍቅርና ክብር አመላካች በመሆኑ በጣም ጥሩ…

የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር መስራችና በተለያዮ አጋጣሚዎች የወያኔን ስርዓትና ብልሹ አሰራር በመተቸት በሀገራችን መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን ሲታገል የነበረው ወጣት አለማየሁ አበበ በትላንትናው እለት በታጠቁ ወታደሮች ተይዞ መታሰሩ ታውቋል። ወያኔ መጪውን ምርጫ ተከትሎ ያሰጉኛል የሚላቸውን ግለሰቦች እያደነ በማሰር ላይ መሆኑ ይታወቃል። አይዞህ ወንድማችን አሰግድ ታመነ Filed under: NEWS Tagged: Addis Ababa, Eskinder Nega, human-rights, Politics of Ethiopia

ሚያዝያ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በሰብሳቢነት የሚመሩት  ኢህአዴግ፣  ከፍተኛ የግንባሩንና የመንግስት አመራሮችን በመገምገም ለሚቀጥሉት አምስት አመታት የመንግስት ስልጣን የሚይዙትንና ድርጅቱን የሚመሩትን ሲመርጥ ከርሟል። ሁሉም የኢህአዴግ ከፍተኛ ሹሞች የተገመገሙ ሲሆን፣ የመንግስት ስልጣን ያልያዙ ነገር ግን በግንባሩ ውስጥ ያገለገሉ ነባር ታጋዮችም በግምገማው ተሳትፈዋል። አቶ ሃይለማርያም ግምገማውን በሰብሳቢነት ሲመሩ ቆይተው፣ የመጨረሻው …

ሚያዝያ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ አገዛዙን ይቃወሙ ይሆናል ተብለው የሚጠረጠሩ ሰዎች በገፍ እየተያዙ በመታሰር ላይ ሲሆኑ፣ በርካታ ወጣቶችም ከእስር ለማምለጥ መሸሸጋቸውን ለኢሳት እየገለጹ ነው። በተለያዩ ክልሎች የገዢው ፓርቲ አባል ለመሆን ፈቃደኛ ያልሆኑ ወጣቶች የሚታሰሩት ከምርጫው ጋር በተያያዘ ህዝቡን ለአመጽ ያነሳሳሉ በሚል ነው። የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መሪ …

በምዕራብ አርሲ ኮፈሌ ከተማ የዛሬ ሁለት ዓመት እስከ 25 የሚደርሱ ሰዎች ተገድለውበታል ተብሎ የሚታመነው ሰላማዊ ሰልፍ በወጡ ሙስሊሞችና የኢትዮጵያ ፌደራል ፓሊስ ግጭት የነበረውን ሁኔታ ፓሊስ እራሱ የቀረጸው ቪድዮ ይህን ይመስላል posted by Aseged TameneFiled under: NEWS

አብርሃም ዘታዬ
ፌዴራል ፖሊስ በሊቢያ የተገደሉትን ኢትዮጵያውያኖች አስመልክቶ ለኀዘን የወጡትን ሲደበድብ

በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ ከደረሰብን ኀዘን ሳናገግም በሜዲትራንያን ባህር የሰጠሙ ወገኖቻችንን መርዶ ተረዳን። በአገር ቤት ከድሮም ጀምሮ በተናጥልም በጅምላም መጨፍጨፋችን አላቆመም። ባለቅኔው “ሞትና የላሊበላ ህንጻ ሁልጊዜ አዲስ ነው” ብሎ እንደተቀኘው ስለአዲሱ አሟሟታችን እንጉርጉሮ እናውጣለት ከተባለ በሰፈር ተደራጅተን እየሞትን ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ክንፉ አሰፋ
ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ከሊብያ የተመለሱትን ኢትዮጵያውያኖች ሲቀበሉ

የፌስቡክ አርበኛው ቴድሮስ አድሃኖም ቦሌ ሄደው ከሊቢያ ነጻ የወጡ ዜጎችን ሲቀበሉ አየን። እፊታቸው ላይ የማፈር ሳይሆን የጀግንነት ስሜት ይነበባል። አቀባበላቸውም 90 ደቂቃ በኢንቴቤ የሚለውን ታሪክ ይመስላል። ኡጋንዳ ላይ የታገቱ ዜጎችዋን ለማስለቀቅ እስራኤል ያደረገችው ገድል። ቴድሮስ አድሃኖምም በኩራት እና በድል አድራጊነት ስሜት ነው ስደተኞቹን የተቀበሉት።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ኢህአዴግ በደቡብ ክልል እየተከሰቱ በሚገኙ የ‹‹ብሄር›› ግጭቶች በስተጀርባ ሰማያዊ ፓርቲ አለበት እያለ እየቀሰቀሰ እንደሚገኝና በዚህ ሰበብ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትንም እያሰረ እንደሚገኝ የሰገን አካባቢ ህዝቦች ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ዳትኮ ታዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ በአካባቢው በተለይም በደራሼ ወረዳ የእርስ በእርስ ግጭት እንደነበር የገለጹት አስተባባሪው ከምርጫው ጋር ተያይዞ ግጭቱ ሆን ተብሎ እንዲባባስ […]

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

‪#‎Ethiopia‬ #FreeZone9Bloggers 
ለተሻለች ኢትዮጵያ የተሰባሰቡ ያገባናል ያሉ ወጣቶች ከተሰባሰብን ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ጦማራችንን በይፋ ካወጅን ዛሬ ድፍን ሶስተኛ አመታችን ሆነ፡፡
እንደ ዜጋም፣ እንደ አገርም ያለመታደል ሆኖ ብዙ ብለን ተባብለን፣ የምንማማርበት ጊዜ እንዲኖረን አምባገነኖች አልፈቀዱምና ፣ የጠበበው ነጻነት ተዳፍኖብን ሥራችንን ሳይሆን እስራችንን መቁጠር ከጀመርን ደሞ አንድ ዓመት ሞላን፡፡ ራሳችንን እና የተቋቋምንበትን ስራችንን ረስተን እስራችንን ብቻ በምናስብበት ሰዓት ጎግል ልደታችንን ስላስታወሰን እናመሰግናለን፡፡
ይህ ሶስተኛ አመት በእስርና በስደት ያለን ዞን9ኛውያን ሳንነጋገር የምናስታውሰውና ወደኋላ ተመልሰን ሃሳባችንን የምናንጸባርቅበት አንደሆነ እናምናለን፡፡
ሶስቱን አመታት በሙከራችን በጥረታችን እንዲሁም በክፉ ጊዜያት አብራችን ስለቆያችሁ እናመሰግናለን፡፡
አጋርነታችሁ አይለየን ፣ ስለሚያገባን እንጦምራለን፡፡

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም     ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ  የኢትዮጵያውያን/ት ህይወት ያሳስበናል!  እ.ኤ.አ በ2005 ልክ የዛሬ 10 ዓመት በያዝነው ወር ገደማ አሁን በህይወት የሌለው እና እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ የሚጠራው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አድራጊ ፈጣሪ አምባገነን መሪ የነበረው መለስ …

ኢትዮጵያ፡ የምንወድሽ ሀገራችን ደግመሽ አልቅሽ! Read more »