የጂማ አይሮፕላን ጣቢያ ተከፈተ – ግንቦት 20, 2015
Jimma airport inaugurated – 05-18-15
ኢትዮጵያዊያኑ ከየመን እየተመለሱ ነው – ግንቦት 19, 2015
ethiopian-returnees-from-yemen-05-19-15
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ግንቦት 19, 2015
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና
መጭውን ምርጫ ተከትሎ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ከፍተኛ ውጥረት እየታየ ነው
ሚያዝያ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለኢሳት የሚደርሱት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከመጪው ምርጫ ጋር በተያያዘ በተለይ በሰሜን የአገሪቱ ክፍል አብዛኛው ህዝብ ረብሻ ይነሳል ብሎ ያምናል። በዚህም የተነሳ ቀድም ብለው ገንዘባቸውን ባንክ ያስቀመጡ ሰዎች ገንዘባቸውን እያወጡ ለምግብ የሚውሉ የእህል ዘሮችን፣ ጨውና ሌሎችንም እቃዎች እየገዙ ነው። ወፍጮ ቤቶች ሰሞኑን ተጨናንቀው ታይተዋል። አቅም ያለው ቤተሰብ ለሶስት …
የብአዴን አመራሮች ድርጅታቸው የገጠመውን ፈተና ተናገሩ
ሚያዝያ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በባህርዳር ከተማ በተካሄደው የብአዴን ማእከላዊ የዞን ጽህፈት ቤት ሃላፊዎች ውይይት በቀጣይ ምን ማድረግ አለብን የሚለውን መመሪያ ለአባላቱ ባስተላለፈው የግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክት፣ ድርጅቱ በርካታ ችግሮች እንዳሉበት የድርጅቱ ልዩ ልዩ አመራሮች ተናግረዋል፡፡ የብአዴን ማእከላዊ ዞን ጽህፈት ቤቱ ሃላፊ ሲናገሩ የብአዴን አመራሮች በ1990 ዓ.ም ከታየው የጥገኝነት ዝቅጠት አንስቶ …
በእስራኤል የሚገኙ የኢትዮጵያ ቤተእስራኤላውያን የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
ሚያዝያ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ቤተእስራኤላውያን ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ በአገሪቱ ማህበራዊ ፍትህ እንዲሰፍንና ዘረና የሆነው ፖሊስ እንዲያዝ ጠይቀዋል። ከሳምንታት በፊት የተካሄደው ተመሳሳይ የተቃውሞ ሰልፍ ደም አፋሳሽ ሆኖ ቢጠናቀቅም ፣ የአሁኑ ሰልፍ በሰላም ተጠናቋል። ከ185 ሺ በላይ ቤተእስራኤላውያን በእስራኤል ምድር የሚኖሩ ሲሆን ከዘረኝነት ጋር በተያያዘ የተለያዩ አድሎዎች ይፈጸሙባቸዋል። ከዚህ …
በ97 ምርጫ የካርተር ማእከል የምርጫ ታዛቢ ዋና አማካሪ የኢትዮጵአን ምርጫ ሂደት አጣጣሉት
ሚያዝያ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ቴሬንሴ ሊዮንስ በዋሽንግተን ፖስት ላይ “ነጻና ፍትሀዊ ምርጫን ከኢትዮጵያ ጋር ምን አገናኘው?”በሚል ርዕስ ባሰፈሩት ጽሁፍ በመጪው ግንቦት 16 በ ኢትዮጵያ የሚካሄደው ምርጫ የመርሀግብር ማሟያ እንጂ ትርጉም ያለው እንዳልኾነ ገልጸዋል። ሂደቱ ከቅድመ-ምርጫ ጀምሮ ፍትሀዊና ዲሞክራሲያዊ እንዳልነበር በስፋት ያብራሩት ጸሃፊው ”ዜጎች አዲስ መንግስት የማይመርጡበት ትርጉም የለሽ ምርጫ”ሲል …
ምርጫው ቀዝቃዛ አይደለም – ገብሩ አሥራት (አረና) – ግንቦት 19, 2015
Gebru Asrat of Arena/Medrek about elections2015-ethiopia, full interview with Girmay Gebru of VOA 05-18-15
ኢትዮጵያና አሜሪካ ከፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ግንቦት 200
ዱሮ ዱሮ ምዕራባውያን የሶቭየት ኅብረትን ኮሚዩኒዝም መስፋፋት ለመቋቋም ከእሥራኤል ሌላ አጋር ሊሆኑ የሚችሉ አገሮችን ሲያስሱ፣ ኢትዮጵያ፣ ቱርክና ፋርስ እየታጩ ነበር፤ አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር የተወዳጀበትና በአስመራ ቃኘው ጣቢያን የተከለበት አንዱ ምክንያት ይኸው ነው፤ የፋርስ ጉዳይ ከንጉሠ ነገሥቱ መፈንቅለ መንግሥትና ሞት ጋር አበቃ፤ ቱርክ እያንገራገረም ቢሆን የሰሜን አትላንቲክ አገሮች ማኅበር ውስጥ አለበት፤ እሥራኤል በአረቦች አካል ላይ እሾህ […]![]()
የህወሓት አየር ኃይል ለሰላም ማስከበር ተልዕኮ ወደ ደቡብ ሱዳን የሚያደርገው ጉዞ መሰረዙ ተሰማ፡፡
በበረራ፣ ጥገና፣ ድጋፍ ሰጪ፣ ዘመቻና አስተዳደር ከ200 በላይ አባላቱን በከፍተኛ ወጪ ለ6 ወራት ሲያሰለጥን የባጀው አየር ኃይል የሰላም ማስከበሩ ተልዕኮ ወደሚከናወንበት ደቡብ ሱዳን ሊጓዙ የተመረጡት መንገደኞች ከየአየር ምድቦቻቸው ተነስተው ደብረ ዘይት ከከተቱ በኋላ ጉዞው ድንገት ተዘርዟል፡፡ ጉዞው የተሰረዘባቸው ምክንያቶች በአባላትና አባላት፣ በአባላትና አመራሮች እንዲሁመም በአመራሮችና አመራሮች መካከል አለመተማመን በመስፈኑ፤ ያለመጠን ስር ሰዶ የተንሰራፋው ጎሰኝነት ተባብሶ […]![]()
“ለውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ” ከአንዳርጋቸው ጽጌ እህት (ወ/ሮ ብዙአየሁ ፅጌ)
የግንቦት 7 ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ የሆኑት የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እህት ወ/ሮ ብዙአየሁ ፅጌ ለኢትዮጵያ ህዝብ መልዕክት አስተላለፉ! እነሆ መልዕክቱን ያንብቡ፤ ሼር በማድረግም ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ይደርስ ዘንድ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ታደርጉ ዘንድ በአክብሮት ተጠይቃችኋል! “ለውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ” ከአንዳርጋቸው ጽጌ እህት (ወ/ሮ ብዙአየሁ ፅጌ) ይድረስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጭ እንዳሸዋ ተበትናችሁ የምትገኙ ወገኖቼ እኔ የተጎዳሁትን […]![]()
የመቀሌ ሕዝብ ችግር ከሌላው የተለየ አይደለም – አዲስዓለም ባሌማ (ሕወሓት) – ግንቦት 19, 2015
Addisalem Balema of TPLF about the 2015 Elections of Ethiopia – 05-18-15
ምርጫው ቀዝቃዛ አይደለም – አቶ ገብሩ አሥራት – ግንቦት 19, 2015
Gebru Asrat of Arena about the 2015 elections of Ethiopia – 05-18-15
ወጣቶች የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሲደግፉ ምክንያታቸው ምንድነው? – ግንቦት 19, 2015
why the youth support political parties? 05-18-15
ኢሕአዴግ የምርጫ ሂደቱ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ ነው ይላል – ግንቦት 19, 2015
EPRDF says the election process is fair, democratic and peaceful 05-18-15
ኢሕአዴጎች በጣም የሚያሣፍሩና የተንኮል ቡድን ነው – በየነ ጴጥሮስ (መድረክ)
Beyene Petros about the upcoming elections – 05-18-15
በትጥቅ ትግል ለዉጥ ለማምጣት የሚታገሉ ድርጅቶች የጥምረት ስምምነት ተፈራረሙ
በገዢው የኢህአዴግ መንግስት ላይ የትጥቅ ትግልን እያካሄዱ የሚገኙ የተቃዋሚ ድርጅቶች ወደ ጥምረት እና ውህደት የሚወስዳቸውን ውይይት መጀመራቸውን ባለፈዉ አርብ ይፋ አደረጉ ። የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፥ የጋምቤላ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፥ የቤኒሻንጉል ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ፥ የአማራ ዴሞክራሲ ሀይል ነቅናቄ፥ እና የአርበኞች ግንቦት ፯ ለአንድነት እና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ የጥምረት ብሎም የውህደት ዉይይቶችን መጀመራቸውን አስታወቁ ። “ሀገርን እና ህዝብን …
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ግንቦት 18, 2015
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና
አንድ በ20ዎቹ የእድሜ ክልል የሚገኝ ወጣት አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ በዝዋይ እስር ቤት ውስጥ ተገደለ
ሚያዝያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ 22 እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚኖረው የ25 ዓመቱ ሲሳይ ተሾመ በቅጽል ስሙ ገብሬ ያለፉትን 8 ዓመታት በቃሊቲና በዝዋይ እስር ቤቶች እየተመላለሰ አሳልፏል። በተለይ ወደ ዝዋይ እስር ቤት ከተላለፈ በሁዋላ ፣ ሃጎስ የተባለው የእስር ቤቱ ሃላፊ ” አንተ የነፍጠኛ ልጅ እንበቀለሃለን፣ በእኔ እጅ ነው የምትሞተው” እያሉ …
የኢሳት የአሞስ ስርጭት እንደገና ታፈነ
ሚያዝያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢሳት በናይል ሳት ሲያስተላልፈው የነበረው ስርጭቱ በ2 ሳምንታት ውስጥ የኢህአዴግ አገዛዝ ባሳደረው የዲፕሎማሲ ጫና ከአየር ላይ እንዲወርድ ከተደረገ በሁዋላ፣ በአሞስ ስርጭቱን ቢጀምርም፣ ከአገሪቱ በሚለቀቀው ሞገድ እንደገና በመታፈኑ ከአየር ላይ እንዲወርድ ተደርጓል። ኢሳት ባለፉት 5 አማታት 8 የሳተላይት ጣቢያዎችን እየቀያየረ ስርጭቱን ሲያቀርብ ቆይቷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢሳትን …
በሶማሊ ክልል በደረሰው ድርቅ ከ2 ሺ በላይ የቤት እንስሳት አለቁ
ሚያዝያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተለያዩ አለማቀፍ ድርጅቶች የመስክ ጉብኝት በማድረግ ባወጡት ሪፖርት በሲቲ ዞን ባለፈው ወር ብቻ በተከሰተው ድርቅ ከ2 ሺ በላይ በጎችና ፍየሎች ሲያልቁ ነዋሪዎችም እየተሰደዱ ነው። በረሃቡ ምክንያት በሃዲጋላ ወረዳ ጉርጉር ቀበሌ በጎች የሌሎችን በጎች ቆዳ ሲበሉ መታየታቸውን በስእል የተደገፈው ሪፖርት ያሳያል። አይሺያ፣ ሃድሃጋላ፣ ከፊል ሽንሌ፣ ከፊል ደምበል፣ …
የስኳር ፕሮጀክቶች በፋይናንስ ችግር ምክንያት ሳይሳኩ ቀሩ
ሚያዝያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህወሃት/ኢህአዴግ መራሹ መንግስት የአምስት ዓመት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅዶች መካከል የስኳር ፕሮጀክቶች በዋነኛነት በፋይናንስ እጥረት ምክንያት እንዳልተሳኩ ከስኳር ኮርፖሬሽን የተገኘ መረጃ ጠቆመ፡፡ በሰኔ ወር 2007 መጨረሻ የሚጠናቀቀው የአምስት ዓመት መርሃግብሩ ከተያዙት ፕሮጀክቶች አንዱ የስኳር ፕሮጀክቶች ሲሆኑ ለፕሮጀክቶቹ ተስፋ ተጥሎባቸው የነበሩት አበዳሪ ተቋማት ገንዘብ ሊሰጡ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ምክንያት …
ወጣት እስማኤል ዳውድን ጨምሮ 18 ተከሳሾች ላይ ክስ ተመሰረተ
ሚያዝያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት አይኤስን ለማውገዝ ሚያዚያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም በጠራው ሰልፍ ላይ ሁከትና ብጥብጥ አስነስተዋል የተባሉትና በወረዳ 9 ፖሊስ ጣቢያ የሚገኙት ተከሳሾች ላይ መደበኛ ክስ ተከፈተ። በዚህም መሰረት የሚሊዮኖች ድምፅ ጋዜጣ አምደኛና የአንድነት አባል የነበረው ወጣት እስማኤል ዳውድን ጨምሮ በሌሎች 18 ተከሳሾች ላይ የፌደራል ዐቃቤ ህግ ክስ …
የምርጫ ገጠመኝ
ሚያዝያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከመጪው ምርጫ ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት እየተዋከቡ፣ እየታሰሩና ደብደባም እየተፈጸመባቸው መሆኑን በየጊዜው የሚደርሱን መረጃዎች ያሳያሉ። የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች አንድ ጊዜ የቡና ሌላ ጊዜ የእድር እያሉ በተለይም እናቶችን እየሰበሰቡ ኢህአዴግን እንዲመርጡ፣ ልጆቻቸውንም አመጽ እንዳያስነሱ እንዲመክሩ ለማግባባት ይጥራሉ። መራጮች በኢህአዴግ ካድሬዎች የቅስቀሳ መንገድ …
የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች ድብደባ እየተፈፀመባቸው እንደሆነ ተገለፀ
በምስራቅ ጎጃም ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች በሚሊሻዎች ድብደባ እየተፈፀመባቸው እንደሆነ የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ በቃሉ አዳነ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ታዛቢዎቹ ‹‹ከአሸባሪ ፓርቲ ጋር አብራችሁ እየሰራችሁ ነው›› እየተባሉ ድብደባ እየተፈፀመባቸው እንደሆነ የገለጹት አቶ በቃሉ ቀሪዎቹን ‹‹ከአሸባሪ ፓርቲ ጋር ሲሰሩ አገኘናቸው ብለን እንከሳችኋለን›› እያሉ እያስፈራሯቸው ነው ብለዋል፡፡ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር የምትገናኙበት ነው በሚልም ስልካቸውን […]![]()
ህገወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች የ አይ ኤስ ታጣቂዎችን ወደ አውሮፓ እንዲገቡ እያደረጉ ነው
ቢቢሲ ባወጣው መረጃ መሰረት አንድ የሊቢያ ባለስልጣን ለቢቢሲ እንደገለፁት በሜዲትራኒያን ባህር በህገወጥ መንገድ ሰዎችን ወደ አውሮፓ አዘዋዋሪዎች ከስደተኞች ጋር ታጣቂዎቹን በመቀላቀል ወደ አውሮፓ እንዲገቡ እያደረጉ ነው ታጣቂ ቡድኑ በሰሜን አፍሪካ ጀልባ ባለቤቶች ስራውን እንዲሰሩ በመፍቀድ ከገቢያቸው ደግሞ 50 በመቶ ያህሉን ይቀበላሉ እንደ ቢቢሲ ዘገባ የአይ ኤስ ታጣቂዎች በባህር በሚደረገው ጉዞ ከሌሎቹ ስደተኞች በምን […]![]()
ካድሬዎች የምርጫ ካርድ ላይ ንብን እየለጠፉ ለመራጩ እያደሉ ነው
በጋሞጎፋ ዞን ቁጫና ቦርዳ ወረዳዎች የደኢህዴን/ኢህአዴግ ካድሬዎች የህዝቡን ካርድ እየተቀበሉ የምርጫ ካርዱ ላይ የንብን ምልክት በስቴፕለር በማያያዝ ኢህአዴግን እንዲመርጡ እያስገደዱ እንደሚገኙ በጋጎፋ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪ አቶ ወንድሙ መኩሪያ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ካድሬዎቹ ህዝቡን 1ለ5 በማደራጀት የንብ ምልክት የተለጠፈበት ካርድ በማደል ‹‹የምትመርጡት ኢህአዴግን ነው›› እያሉ እያስገደዱ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ የዞኑ፣ የወረዳውና የየ ምርጫ ክልሉ ምርጫ አስፈጻሚዎች […]![]()
ሰማያዊ ፓርቲ በ አማራ ክልል እንዳይንቀሳቀስ እየተደረገ ነው
በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች መጪውን ምርጫ ተከትሎ በርካታ ዜጎች እየታሰሩ መሆናቸውን ከተለያዩ አካባቢዎች የደረሰን መረጃ አመለከተ፣ በክልሉ ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች መጪውን ምርጫ ተከትሎ በርካታ ዜጎች እየታሰሩ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል የሚንቀሳቀሰው የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሆኑ ንፁሃን ዜጎችን በትጥቅ ትግል ከሚንቀሳቀሰው ግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ሰንካላ ምክንያት የስርዓቱ ካድሬዎች ባሰማሯቸው በሆዳቸው […]![]()
ህወሃት ስለሃለማርያም የቤት ስራውን ጨርሷል ተባለ
ሃይለማርያም ከስልጣን ሲባረር እ አ አቆጣጠር በ2009 ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ጥቅምና ምቾት ለመወሰን የወጣው አዋጅ ለሃይማርያም የማያገለግልና ሃይለማርያም የዚህ ተጠቃሚ እንደማይሆን ታውቋል።
ሃይለማርያም ከስልጣን ሲባረር እ አ አቆጣጠር በ2009 ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ጥቅምና ምቾት ለመወሰን የወጣው አዋጅ ለሃይማርያም የማያገለግልና ሃይለማርያም የዚህ ተጠቃሚ እንደማይሆን ታውቋል።
ቀደም ብሎ ህወሃት ሃይለማርያምን ለማስወገድና የህወሃቱን ቴድሮስ አድሃኖም ጠ/ሚንስቴር አድርጎ ለመሾም መስማማቱን ዘግበን ነበር።
አሁን ደግሞ የደረሱን መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ሃይለማርያም ስልጣኑን ሲለቅ ከስልጣን ለተገለሉ ለከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የሚደረገው ጥቅምና እንክብካቤ ሊደረግለት እንደማይገባ ህወሃቶች ተስማምተውበታል፡
ለዚህም ያዘጋጁት ምክንያንያት
1ኛ. በProclamation No. 653/2009 አንቀጽ 12. Pension Rights ንኡስ ቁጥር
“1/ Notwithstanding any provision to the contrary under the relevant pension law, if a Senior Government Official who has served for at least one election term:”
አንድ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ቢያንስ የአንድ የምርጫ ዘመን ማገልገል አለበት የሚለውን እንደሚጠቅሱበትና እሱ ደግሞ ይህን ስለማያሟላ ጥቅማ ጥቅሙ አይገባውም። ዳግመኛም እንደማይመረጥ ተወስኗል፤ እንዳውም በምርጫ ጣቢያው በሌላ ተወዳዳሪ እንሚሸነፍ ይጠበቃል፡
2ኛ. ጥቅሙ የሚገባው በረሃ ለታገሉ እንጂ እዚህ ከተማ ተቀምጠው ከድል በሗላ ብቅ ለሚሉ መሆን የለበትም የሚሉ አክራሪ የህወሃት አባላት ለመቶ አለቃ ግርማ የሚደረገው እንክብካቤም ስህተት መሆኑንና እንደሚያንገበግባቸው ተገልጿል፡
ባለራዕዩ መሪ መለስ ዜናዊ በህይወት ኖሮ ያላገኘውን እንክብካቤና ክብር ሃይለማርያም ሊያገኝ አይገባም የሚሉም አሉ፡ ሃይለማርያም ስልጣን ከለቀቀ በሗላ የመለስን ስም የሚያገዝፍ የሃይለማርያምን ደግሞ የሚያቀጭጭ ዶክመንታሪ እንደሚሰራ፡ ዶክመንታሪውም የሃይለማርያም ንግግሮች እየተቀነጨቡ ምን ያህል ብቃት የለለው እንደነበርና እሱን መጀመሪያውኑ ስልጣን ላይ ማስቀመጥ ስህተት እንደነበር የሚዘረዝርና ባንጻሩ መለስ ዜናዊ ካደረጋቸው ንግግሮች ተመርጠው እንደሚካተቱና ምን ያህል ብልህና ባለራዕይ መሪ እንደነበር በንጽጽር እንደሚቀርብ ይጠበቃል።
ሰሞኑን ሃይለማርያም ላይ የተደረገው 15 ሰዓት የፈጀና ከላይ እስከታች እንዲተቹት የተደረገው በህወሃት አቀናባሪነት የዚህ እቅድ አካል እንደሆነ የውስጥ አዋቂ ምንጮት ይገልጻሉ፡ ከግምገማው በሗላ አሁንም ስህተቱን ለመቀበልና ለመማር ዝግጁ አደለም የሚሉት ትችቶች ሳጥኑ ላይ የመጨረሻው ምስማር መሆኑን ያመለክታል።
ዌንዲ ሸርማን እየገመዱት ያለ ድር፣
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ የዩኤስ አሜሪካ ከፍተኛ የዉጭህ ፖሊሲ አስተዳዳሪ የሆኑት ማዳም ዌንዲ ሸርማን እ.ኤ.አ ግንቦት 1/2015 ለዋሽንግተን ፖስት በላኩት ደብዳቤ “ባደረግሁት ንግግር ላይ ስም የማጥፋት ድርጊት ፈጽሟል” በማለት በአርታኢ/ኢዲቶሪያል ቦርዱ ላይ ዘለፋ አካሂደዋል፡፡ የጉዳዩ መነሻ የሆነው ዌንዲ ሸርማን እ.ኤ.አ ሚያዚያ …
የጀግና ልጅ አባት፣ እርሳቸውም የፍትህ አርበኛ የሆኑ ተወዳዳሪ – ግርማ ካሳ
የሚቀጥለው ሳምንት ምርጫ ነው። ከምርጫው የሚጠበቅ ለዉጥ ባይኖርም መድረክ እና ሰማያዊ( የአንድነት ሰዎች በብዛት በምርጫው እንቅስቃሴ ለማድረግ ስለገቡ) በጠበበው የፖለቲካ ምህዳር ዉስጥም ሆነ ሕዝቡን ለማንቀሳቀስ ጥረት እያደረጉ ነው። በተለይም መድረክ በኦሮሚያና በትግራይ ብዙ ድጋፍ እያገኘ እንደሆነ የሚያሳዩ ምልክቶች አሉ።
መድረክን እና ሰማያዊ ወክለው ለፓርላማ ከሚወዳደሩ በርካታ ኢትዮጵያዊያን መካከል እኝህ አባት ይገኙበታል። በሞያቸው ጠበቃ ናቸው። የመልካም ሴት ባላቤትና የተባረኩ ልጆች አባት ናቸው። ከእኝህ አባት ሴት ልጆች መካከል አንዷ አስተማሪ ሆና ነበር። ከደሞዟ ብዙ ችግር ያለባቸውን ተማሪዎች ትረዳና ትደግፍ ነበር። እንደ ዜጋ ሕግ መንግስት በሚፈቅደው መሰረት ጻፈች፣ አስተያየቷን ሰጠች።
እነርሱ መስማትና ማንበብ ከሚፈለጉት ዉጭ እንዲጻፍና እንዲነገር የማይፈልጉት ገዢዎች፣ የአስተሳሰብ ድሆች በመሆናቸው፣ ብእሯን መመከት አልቻሉም። ወደ ጡንቻ ሄዱ። አሰሯት። በዉሸት ክስ ሽብርተኛ ናት ብለው ከሰሷት። ጠበቃ አባቷ ተከራከሩ። ሆኖም ፍርድ ቤቶች የፍትህ አካላት ሳይሆን የሕወሃት ፖሊት ቢሮ ጉዳይ አስፈጻሚዎች በመሆናቸው፣ ፍትህ ሊገኝ አልቻለም። ይች ወጣት ለአመታት በቃሊቲ ትሰቃያለች። ይች ወጣት ርዮት አለሙ ትባላለች። በዘመናችን ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ብርቅዬና ጀግና ኢትዮጵያውያን መካከል አንዷ !!!!
ጠበቃ አባቷ፣ ምን ያህል የሕግ ስርዓት እንደሌለ በመረዳታቸው፣ ፍትህ ከፍርድ ቤት እንደማይገኝ በማወቃቸው ለዚህ ደግሞ በዋናነት ምክንያቱ የተበላሻዉና የበሰበሰው የፖለትካ ስርዓቱ በመሆኑ፣ ይሄንን ስርዓት ለመለወጥ በቀድሞ ወረዳ አራት የመድረክ ተወዳዳሪ ሆነው ቀርበዋል።እኝህ አባት ጠበቃ አለሙ ጎቤቦ ይባላሉ።
ትግል የሁሉንም ተሳትፎ ይጠይቃል። ጠበቃ አለሙ በጥብቅና ሞያቸው ቀጥለው፣ ፍትህ ቢጓደልም “ ምን አገባኝ” ብለው መቀመጥ ይችሉ ነበር። ሆኖም ከራስ አልፎ ለሌላ መቆም ትልቅነት ስለሆነ፣ እኝህን አባትም ትልቅ አባት ስለሆኑ፣ ዝምታን አልመረጡም። ፖለቲካዉን ተቀላቅለው አምባገነንነትን ለመታገል ተነሱ።
የርዮት አለሙን አባት፣ የኛም የነጻነት ናፋቂዎች ሁሉ አባት የሆኑትን፣ አቶ አለሙን እንምረጥ !!!!! አገዛዙ ከአምስት አመታት በፊት እንዳደረጉት ድምጽ እንዳይሰርቁም፣ ድምጹ እስኪቆጠር ድረስ፣ ሕዝቡ በየምርጫ ጣቢያ ቁጭ ብሎ በመጠበቅ ራሱ ማስቆጠር አለበት። 3፣ 4 አጋዚ፣ ፌዴራልና ካድሬ ፣ ሺሆችን አስፈራርተው የሕዝብ ድምጽ እንዲሰርቁ ሊፈቅድላቸው አይገባም።
የመድረኩና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ መሪ የምርጫ ቅስቀሳ
የመድረኩና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ መሪ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና በአምቦ ያካሄዱት የምርጫ ቅስቀሳ
” ኢህአዴግ ጠመንጃና ምርጫ ቦርድን እንደ ምርኩዝ ይዞ ነው የሚንቀሳቀሰው፡፡ ” ዶ/ር መረራ ጉዲና
Minilik Salsawi – በየቦታው ትንንሽ ጦርነት የሚመስሉ ነገሮች ነበሩ፡፡ የኛ ቅስቀሳ በተሳካ ቁጥር የእነሱ ብስጭት ይግል ነበር፡፡ ካድሬው ለሆዱ፣ መንግስት ለስልጣኑ በሚገባ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ይሄ አመላካች ነው፡፡ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ግን ካድሬው ሽጉጥ ታጥቆ፣ ጠመንጃ ይዞ እገባለሁ አትገባም የሚል ግብግብ እስከመፈጠር ደርሷል፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ መኪናዎቻችን እንዳይንቀሳቀሱ ተደርገው ተወዳዳሪ እጩዎቻችን ሳይቀሩ ተደብድበዋል፡፡ በአባላቶቻችን ላይ እስር፣ ድብደባና ወከባ ተጠናክሮ ቀጥሏል:: በዘንድሮ ምርጫም ኦሮምያ ላይ እናሸንፋለን ብለዋል – ዶ/ር መረራ፡፡
በኦሮሚያ ብዙ አካባቢዎች ሰፋፊ ህዝባዊ ስብሰባዎችን አካሂደናል፡፡ ባኮ፣ አምቦ፣ ጀልዱ፣ ጊንጪ የመሳሰሉት አካባቢዎች እኔ የተገኘሁባቸው ህዝባዊ ስብሰባዎች ተደርገዋል፡፡ በየስብሰባው ከ60ሺህ በላይ የሚገመት ህዝብ ነው ድጋፉን ሲገልፅልን የነበረው፡፡ በተለይ የወጣቱ ድጋፍ ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ ነው፡፡ “ከዚህ በኋላ የፀረ-ዲሞክራሲ አገዛዝ ይብቃን” የሚሉ ህብረ ዝማሬዎችን እያሰማ ነው ህዝቡ በየስብሰባው ላይ ሲታደም የነበረው፡፡ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ሲታዩ ቅስቀሳው ስኬታማ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ክልሉን እያስተዳደረ ያለው ኦህዴድ፣ በዚህ መልኩ ወጣቱ ለኛ ድጋፍ ይሰጣል ብሎ የገመተ አይመስለንም። አሁን ታዲያ የድንጋጤ እርምጃዎችን እየወሰደ ነው፡፡ በአርሲ፣ በባሌ፣ በሃረርጌ፣ በባሌ እና በሸዋ አካባቢዎች አባሎቻችንን ማሰር፣ መደብደብና ማዋከብ አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ የቅስቀሳ መኪናዎቻችንን መስተዋቶች በድንጋይ የመስበር፣ መኪኖችን በቡና ቤቶች አካባቢ ማሳደር እንዳንችል የማድረግ ሁኔታዎች በስፋት ተስተውለዋል፡፡ ብለዋል – ዶ/ር መረራ፡፡
በሁሉም የኦሮሚያ ዞኖችና አካባቢዎች ተመሳሳይ የሆነ አቀባበል ከህዝቡ አግኝተናል፡፡ በአጠቃላይ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በትግራይ እና በአዲስ አበባ በምርጫው እንወዳደራለን፡፡ በሁሉም ላይ ቦታ ሰፊ አቀባበል ያገኘን ቢሆንም በተለይ ኦሮሚያ ላይ ኢህአዴግ ምርጫውን ካላጭበረበረ በቀር የሚያሸንፍበት መንገድ የለውም፡፡ እኛ ሁለት ነገር ነው የምንጠብቀው፡፡ አንደኛ ኢህአዴግ ካላጭበረበረ በቀር ኦሮሚያ ላይ አያሸንፈንም፣ ሁለተኛ ደግሞ ፖለቲካውን በሚገባ እንዳሸነፍን አሳይተናል፡፡ ሰፊ ድጋፍ እንዳለን አስመስክረናል፡፡ በየትኛውም ሚዛን ከኦህዴድ እንደምንሻል አሳይተናል፡፡ በዚህ ተደናግጠው እኔ በምወዳደርበት አካባቢ ኦህዴዶች ህዝቡን በሬ አርደው ማብላት ሁሉ ጀምረዋል፡፡ የክልሉ ካድሬዎች አሁን አምቦ ከትመዋል፡፡ ሥራ ላይ ናቸው ማለት ነው፡፡ ኦህዴድና ህዝቡ ከተለያየ ቆይቷል፡፡ ያው በኢህአዴግ ጃንጥላና ጠመንጃ ስር ነው የሚንቀሳቀሰው፡፡ እነሱም እንደማያሸንፉ ያውቃሉ። እኛ በ97 እኮ አሳይተናቸዋል፡፡ በወቅቱ እነ አባዱላን ያሸነፉት እኮ የ6ኛ እና 7ኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው፡፡ ኦህዴድ በኦሮሚያ ሊሸነፍ እንደሚችል በ97 ምርጫ ነው ያረጋገጥነው፡፡ ብለዋል – ዶ/ር መረራ፡፡
“መድረክ” አብላጫ ድምፅ ካገኘ ጥምር መንግስት ይመሰርታል:: እኛ በፕሮግራማችን ላይ በግልፅ አስቀምጠናል። በሽግግሩ ጊዜ ጥምር መንግስት ያስፈልጋል ብለናል። ብሄራዊ መግባባት ለመፍጠር፣ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ ለማካሄድና ለመሳሰሉት ዲሞክራሲያዊ ሂደቶች መልክ ማስያዣ ይሆን ዘንድ የብሄራዊ አንድነት መንግስት ያስፈልጋል፡፡ ከማን ጋር ይመስረት የሚለው በድርድር የሚከናወን ይሆናል፤ ነገር ግን አግላይ ፖለቲካ ውስጥ አንገባም፡፡አንድ ፓርቲ ሌላውን አግልሎ ኢትዮጵያን መንግስተ ሰማያት ያደርሳል የሚሉ ካሉ ወይ የፖለቲካ ሳይንስ ያልገባቸው ወይም እስከቻልን ድረስ በፈላጭ ቆራጭነት ረግጠን እንግዛ የሚሉ ናቸው፡፡ በተረፈ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲ ለማምጣት መታለፍ ያለበት አንዱ ሂደት የብሄራዊ አንድነት መንግስት ማቋቋም ነው። ብለዋል – ዶ/ር መረራ፡፡
በአጭሩ የኢትዮጵያ መንግስት ደጋግሞ እንዲያስብበት የምመክረው ምርጫውን እንዳያጭበረብር ነው፤ ውጤቱ የፈለገ ይሁን፡፡ ምርጫን አጭበርብሮ አሸንፌያለሁ የማለት ጊዜ ማብቃቱን ማወቅ አለበት። ያንን ካላደረገ ሃገሪቷንና ህዝቦቿን ለበለጠ ተስፋ መቁረጥ ነው የሚዳርገው፤ ይሄ በተግባር እየታየ ነው። ወጣቱ ከቀይ ባህር እስከ ሜዲትራኒያን ድረስ የባህር ሲሳይ የሚሆነውና በረሃ ውስጥ እንደዚያ የሚታረደው፣ ደቡብ አፍሪካ እንደዚያ የሚቃጠለው በሃገሩ ተስፋ ስላጣ ነው፡፡ ኢህአዴግ በጠራው ሰልፍ ላይ እንኳ “የስደት ዘመን ይብቃ” ብሎ ከፖሊስ ጋር እንዴት እንደተጋጨ ተመልክተናል፡፡ አጥፍቶ የመጥፋት ፖለቲካ ይብቃ! የኢህአዴግ ባለስልጣናት ደጋግመው ያስቡበት። ህዝቡንም ወጣቱንም ተስፋ ማስቆረጥ ለማንም አይጠቅምም፡፡ በተለይ ወጣቱ በሃገሬ የተሻለ ሥራ አገኛለሁ የሚል ተስፋ ሊያድርበት ይገባል፡፡ ይሄንን ወጣት ተስፋ ማስቆረጥ ለሁላችንም አይበጅም፡፡ ብለዋል – ዶ/ር መረራ፡፡ – addisadmassnews.com

እስከዛሬ ታይቶ የማያውቅ “አስካሪ” በመባል ይታወቁ ስለነበሩ ባንዳዎች የሚያሳይ ቪዲዮ
በ1888 ዓም በተደረገው የአድዋ ጦርነትና ከ40 ዓመት በኋላ በተደረገው የማይጨው ጦርነት ጊዜና ከዛም በኋላ በነበሩት አምስት የጠላት ዓመታት ወቅት በባንዳነትና በፍጹም ታማኝነት ለጣሊያን አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ ከኤርትራ የመጡ ሰዎች “አስካሪ” ይባላሉ። አስካሪዎች በጭካኔያቸውና በክፋታቸው ተወዳዳሪ የማይገኝላቸው ሲሆን ባህር ተሻግረው፣ ድንበር …
እስከዛሬ ታይቶ የማያውቅ “አስካሪ” በመባል ይታወቁ ስለነበሩ ባንዳዎች የሚያሳይ ቪዲዮ Read more »
“ጸርሁ በዓቢይ ቃል” የታረዱት ነፍሳት ጩኸት
ዋሺንግተን ዲሲ በተደረገው ትዕይንት ላይ ሊቀርብ የተዘጋጀ በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ጽሁፉን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። የታረዱት ነፍሳት ጩኽት
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ግንቦት 17, 2015
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡
የመሪዎች እንባ
ወለላዬ

ከስም ልጀምር፣ የዛሬ ወጣቶች በተለይ ዘፋኞች ስማቸው በመጠኑ ተቆርጦ ወይም አንሶ ሲጠሩ እየሰማን ነው፤ ቴዎድሮስ – ቴዲ ብዙ ባያስከፋም ተያይዘው የቀጠሉት ዘፋኞች ግን እስከ አባታቸው ስለሚያሳንሱት ኢትጵያዊ ስም መሆኑ ራሱ አጠራጣሪ የሆነብኝ ጊዜ አለ። እስቲ አሁን ጃህ ሉድ አጥሮ ነው ወይስ ተቆርጦ ቻቺ፣ ጃኪ፣ ጂጂ፣ አቢ፣ ኢሚ፣ ዮሲ፣ ጃኪ-ጎሲ፣ ሚሊ፣ ሚኪ፣ ዮኒ፣ … ልተዋቸው።
የተቃዋሚ ፓርቲዎች አቋምና አማራጭ መርሆዎች
ኢትዮጵያ ለአምስተኛዉ ብሔራዊ ምርጫ መሰናዶዋን እያገባደደች ነዉ።በየማሕበረ-መገናኛዉ ዜዴዎች የምናነባቸዉ አንዳድ ፁሁፎች «ዉጤቱ አስቀድሞ የታወቀ» እያሉ ቢተቹትም ገዢዉ ፓርቲም፤ ተቃዋሚዎቹም፤ አስመራጭ መራጮችም ለምርጫዉ መዘጋጀት፤መከራከር፤መነጋገራቸዉ እንደቀጠለ ነዉ።
ከየመን የተመለሱ ስደተኛ ኢትዮጲያውያን ከቦሌ አየር ማረፊያ ተይዘው በመአከላዊ እስር ቤት ታስረዋል
ከየመን የተመለሱ ስደተኛ ኢትዮጲያውያን ከቦሌ አየር ማረፊያ ተይዘው በመአከላዊ እስር ቤት ታስረዋል በየመን በቀተስተው ግጭት የተነሳ ከየመን ወደ ስአውዲ ሊሻገሩ ሲሞክሩ በስአውዲ ፖሊስ ለቀናት ከታስሩ በህዋላ አምስት የሚሆኑ ኢትዮጲያውያን ከ4 ቀናት በፊት ወደ አዲስ አበባ ቢመለሱም በቦሌ አየረ ማረፊያ በፖሊሶች ተይዘው ወደ መአከላዊ ውስር ቤት መወስዳችውን የBBN ምንጮች አረጋግጠዋል ። እስረኞቹን ቤተስቦች እስረኞቹን ለማግኘት ያደረጉት […]![]()
ድምፅ አሰጣጣችን በምን ሰሌት ቢሆን ያዋጣል?። ዳዊት ዳባ
“የተራቡትን መርጠን ከምንቸገር ያው የጠገበው ይሻለናል” የሚል መልክት ያላት ማዘናጊያ ሀሳብ በየፌስ ቡክ ላይ ተበትናለች። ሲጀመር በልቶ ጠገብኩ የሚሉ መቼ ነገሱብንና። በዛ ላይ ያለአባከና በሰፊው የለመደ ሆድ ለሌላ አምስት አመት ከበሉን ለመረጃ እንኳ አጥንታችንም አይጋኝም አትቀልዱ። የሚኖር አይመስለኝም እንጂ በዚህና “ድምጽ መሰረቁ ላይቀር” አይነት አንድምታ ባላቸው ምክንያቶች ተንተርሶ ለወያኔ ድምፁን የሚሰጥ ካለ በቁሙ የሞተ ነው። […]
የትግል ጥሪ ለነጻነትና ለፍትህ :- የሚሊዮኖች ድምጽ ለፍትህና ለነጻነት !
ገዢው ፓርቲ በሰላማዊ ፓርቲዎች የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ላይ ከፍተኛ ጫና እያደረገ ነው። የፖለቲካ መሪዎችና ጋዜጠኞች ታስረዋል። የአንድነት ፓርቲን አግዶ እንደ ሰማያዊ ያሉትን እያዋከበ ነው። ነጻ ጋዜጦች ተዘግትዋል። ትግሉ የሕዝብ ጉዳይ እንጂ የድርጅት ጉዳይ ባለመሆኑ፣ የድርጅት መሪዎችን በማሰር፣ ድርጅቶችንም በማገድ፣ የህዝብንም ሆነ የታጋዮችን የነፃነት ፍላጎት መግታት አይቻልም። የአገዝዙን አፍናና በትር ለመቋቋም፣ ህዝቡን ወደአንድ አደረጃጀት ለማምጣትና በተናጥል […]
የእውነተኛው አንድነት አመራሮች በትናንትናው ዕለት ግንቦት 7/2007 ዓ.ም. በደህንነት ኃይሎች እስር እና ከፍተኛ ወከባ ተፈፅመባቸው
የማህበራዊ ጉዳይ ሀላፊ የነበረው አቶ አለነ ማህፀንቱ በትናንትና ዕለት ያለፍርድ ቤት ማዘዣ በደህንነት ኃይሎች ታፍኖ የተወሰደ ሲሆን፤ በኃይልና በድብደባ የኢሜል አድራሻውንና ፓስዎርድን ከወሰዱ በኋላ ጉለሌ ፖሊስ ጣቢያ አምጥተው እንዲታሰር አድርጓል። ከዚህም በተጨማሪ የአንድነት ሊቀመንበር የነበሩት አቶ በላይ ፍቃዱ እና ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ተክሌ በቀለ በተመሳሳይ ዕለት በደህንነት ኃይሎች ሲዋከቡ የዋሉ ሲሆን ማስፈራሪያና ማስጠንቀቂያ […]![]()