በዋሽንግተን ዲሲ የቤተክርስቲያን የአንድነት ጥሪ በተሳካና በደመቀ ሁኔታ መካሄዱን የሚያሳይ በፎቶ የተደገፈ ዘገባ (ተጨማሪ መረጃ ተካቷል)
በተለያዩ የሐይማኖት ተቋማትና የሲቪክ ድርጅቶች ተሳታፊነት በዛሬው ዕለት ዋሽንትግተን ዲሲ ከተማ ውስጥ በርካታ ቁጥር ያለቸው ኢትዮጵያዊያን ዘር፣ሐይማኖት፣ጾታና ዕድሜ ሳይለዩ በነቂስ በመገኘት ታላቅና ደማቅ በዓይነቱ ልዩ የሆነ ዝግጅት አድርገዋል። የዝግጅቱ ዋና ትኩረት በሊቢያ በሰማዕትነት ያለፉትን ኢትዮጵያውያን ለመዘከርና እንዱሁም በተለያዩ አገሮች ውስጥ በግፍ ለተገዱትን ወገኖች ጸሎተ ፍትሃት ለማድረግ ነው። በዝግጅቱ ላይ የሕጋዊው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ቅዱስ ሲኖዶስ የእየሩሳሌምና አውስትራሊያ ሊቀጳጳስ የሆኑት አቡነ መቃሪዮስ ተገኝተው ቃል ምዕዳን ሰጥተዋል። ከዚህም በተጨማሪ የዘመናችን የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አንጋፋው ሊቅ ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ እጅግ ወቅታዊ የሆነ ቀስቃሽና አነቃቂ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ፈርስት ሂጅራ በመባል የሚታወቀው የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ማህበር ተወካይ አይሲስ የሚባለው ሽብርተኛ ድርጅት እስልምናን የማይወክልና ስራውም ከእስልምና የወጣ መሆኑንን ጠቁመው በኢትዮጵያዊያን ላይ ሊቢያ ውስጥ በደረሰው ግድያ በኢትዮጵያዊነታቸው ማዘናቸውንና መቆጨታቸውን ልብ በሚነካ ሁኔታ ገልጸዋል። አይሲስን ለመቃወም የሚያስፈልገው ሃይማኖተኝነት ሳይሆን ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው ብለዋል። ከዚህም አያይዘው የአይሲስ ስራ ከአውሬም የከፋ መሆኑ ጠቁመው ጅብ ሌላ ጅብን እንዲሁም አንበሳ ሌላ አንበሳን አይበላም አይሲስ ግን ከነዚህ አራዊት በከፋ ሁኔታ ሰውን ያርዳል ብለዋል።በመጨረሻም ኢትዮጵያዊያን በሙሉ በአንድነት መቆም እንዳለብን ማሳሰቢያ ሰጠተዋል።እንዲሁም ዝግጅቱን አስመልክተው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባም ያስተላለፉት መልዕክትም ተነቧል።
ይህ ታሪካዊ ዝግጅት ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ ሥራውን በማስተባበርና በመምራት እንዲሁም አስፈላጊውን ነገር በሙሉ በማሟላት የዋሽንግተን ዲሲ ርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ከፍተኛ አስተዋጾ አድርጋለች። በዚህም መሠረት የቤተክርስቲያኒቷ አስተዳዳሪ ሊቀ ማዕምራን ቀሲስ ዶ/ር አማረ ካሣዬ የግንባር ሥጋ በመሆን ከፍተኛ ርብርቦሽ በማድረጋቸው “ትወልደ ጻድቃን ይትባረኩ” እንደሚለው ልጆቻቸውን እግዚያብሔር ይባርክላቸው እንላለን።በዚህ ታሪካዊ ዝግጅት ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ የተደረገላቸው የዋሽንግተን ዲሲ ከተማ አካባቢ ቤተክርስቲያኖች ቁጥራቸው በርካታ ቢሆንም በስፍራው ላይ የተገኙት ግን ጥቂቶች ብቻ ናቸው። አንዳንዶቹ ላለመሳተፋቸው የሰጡት ምክንያት ጥሪ “በስማችንና በአድራሻችን” አልተላከልንም ወዘተ.. የመሳሰሉ ተልካሻና ውሃ የማቋጥሩ ሰበቦችን ቢደረድሩም፣ አብዛኛው የዝግጅቱ ተሳታፊዎች ግን እውነተኛው ምክንያታቸው አንዱ እግራቸው ቤተክርስቲያን ውስጥ ሌላው እግራቸው ደግሞ ወያኔ ውስጥ በመገኘቱ ነው የሚል አስተያየት ሰጥተዋል።
እነዚህ ባለሁለት ባሕርይ ካህናት ለማኛውም አገራዊ ጉዳይ በተለይም ወያኔን በሚነኩ ጉዳዮች ላይ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ሲጠየቁ የሚሰጡት ምክንያት ዙሪያው ጥምጥም የሆነ “ፖለቲካ ውስጥ አንገባም፣ቤተክርስቲያን እራሷን አዋርዳ ለዓለም ገዥዎች ሰልፍ አትወጣም፣ እኛ ጸሎት ብቻ ነው የምናደርገው ወዘተ..” እያሉ ምዕመናንን በማዘናጋት ከወያኔዎች ጋር በተለያየ ጥቅሞች ተቆራኝው የሕዝብን መከራ በማራዘም ላይ ይገኛሉ። ወገኖቻችን የስራና የኑሮ ሁኔታዎች ስለጨለሙባቸው ከአገራቸው በመሰደድ ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው መልካም ቀን ይመጣልን ይሆናል ብለው በማለም በበረሃ ውስጥ ለአይሲሲ አራጆች የተዳረጉት በወያኔዎች ምክንያት እንደሆነ እየተወቀ፣ እነዚሁ ሆዳም ካህናት ሁኔታዎችን አለባብሰው ለማለፍና ወያኔን ከተጠያቂነት ለማዳን የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም።
እጅግ የሚያሳዝነው ዐቢይ ጉዳይ ደግሞ እነዚህ መምህራንና ካህናት ወንጌል እንደሚያስተምረን እውነቱን እውነት፣ ሀሰቱንም ሀሰት ማለት የተሳናቸው ለሁለት ጌቶች ያደሩ አጭበርባሪዎች የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተወሕዶ ቤተክርስቲያንን ያሽመደመዱና አቅመ ቢስ ያደረጉ በመሆናቸው በነሱ ላይ የመረረ ተቃውሞ የሚያሰሙ ምዕመናን ሁልቆ መሳፍርት ናቸው። በቅርቡ በሊቢያ ውስጥ የተሰዉ ወገኖቻቸን ማተባቸውን አንበጥስም ብለው አንገታቸውን ለሰይፍና ጭንቅላታቸውን ለጥይት ሲሰጡ ያስተማሪን ታላቁ ቁም ነገር አስመስሎና ቀላምዶ ከመኖር እውነተኛውን ነገር ጨብጦ ይህንን አላፊ ጠፊ ዓለም በክብር ማለፍን ነው። ሆኖም ዛሬ በየቤተክርስቲያናቱ ውስጥ የተሰገሰጉ አንዳንድ ጥቅመኛ ካህናት ምንያህል የዘቀጡና የተዋረዱ መሆናቸውን ከሥታቸው ለመረዳት አስቸጋሪ አይሆንም። ሆኖም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በረዥም ዓመት ታሪኳ እንደአሁኑ ዓይነት የፈተና ጊዜዎችን ተቋቁማ በማለፍ ከትውልድ ወደ ትውልድ ስትሸጋገር ኖራለች። ወደፊትም ትኖራለች።እውነት ምንም ብትቀጭጭም ብትደበዝዝም ጨርሳ ስለማትጠፋ ከሕዝብ ወገን የሆኑ እውነተኛ ካህናትን እንደነ አቡነ መቃሪዮስ፣ ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ፣ ቀሲስ ዶ/ር አማረ ካሣዬ፣ መምህር ሳሙኤልና ሌሎችንም እግዚያብሔር ስለሰጠን ነገን በእምነትና በተስፋ እንድንጠብቅ አስችሎናል። የእነዚህን አባቶቻችንን ቁጥር ያብዛልን።
በዝግጅቱ ላይ የተነሱ ፍቶግራፎችን ይመልከቱ።









One-of-a-kind event I have ever attended in Washington D.C. The event was very organized, pertinent and representatives of all sectors of Ethiopia. Thank you so much all of the participants in this historic event to commemorate Ethiopians who were killed in Libya, south Africa, Yemen, Saudi Arabia and other countries.
yeethiopiya hzboch beselam befqr beortodoks haymanotachw sr honew k3000chi amet befit and honew beshewa ngusachw sr eyegeberu norewal yezih zemen etyopiyanoch lehaymanotachw machoch neberu beteley bengus dawit zemen ethiopiyanoch legbs krstiyan teketayoch bagerachew yalu muslimoch siyatekachew dersewlachwal wede ethiopiyam yegitachn mesqel endegeba baletarikoch 100% yamnalu yeetiopiya hzboch mesqeln asi mesqel eyalu yakebrut neber yh bagerachn yemesqel tarik beityopiya eslmna haymanot saygeba befit yenebere yeityopiyanoch tarik new slezih yeityopiya hzboch bhir bhireseboch beteley beortodoks haymanotachw sr honew betarikach and honew nurewal yh yemayfeta yeityopiyanoch tarik weyanina meseloch ortodoksn atften etiopiyawinetn enbetnalen blew yetenesut yeandnetachn tarik ortodoks bemehona new andnet hayl new mot lemikefaflun
በትናንትናው ዝግጅት በጣም የረካሁ ቢሆንም፤በዲሲ ከተማና አካባቢዋ ያሉ አንዳንድ ካህናት ሳይገኙ መቅረታቸው ግን በጣም አሳዝኖኛል። እነዚህ የውሸት ካህናት እዚሁ ዲሲ ተቀምጠው እውነተኞች ካህናት ከላስቬጋስ፤ ከካንሳስና ከሌሎችም ሩቅ ከተማዎች ሲመጡ የያዛቸው የፍርሃት ቆፈን አላላውስ ስላላቸው በሰበብ ባስባቡ አመካኝተው ወያኔን ላለማስቆጣት እቤታቸው ተደብቀው አሳልፈዋል። አንዱ ከነዚህ አወናባጅ ቀሳውስት/መምህራን አንዱ ከሳምንት ገደማ በፊት ዲሲ ማርያም ቤተክርስቲያን ተገኝቶ የራሱን ንግግር ካራገፈና ማስታወቂያውን ካስነገረ በኋላ የሌሎችን ሀቀኛ ካህናት በወያኔ ላይ ያነጣጠረ ንግግር ሳያዳምጥ ከቤተክርስቲያን ሾልኮ ሊወጣ ሲል፤ ጉዱ ይጋለጥ ሲለው መኪናው በሌላ መኪና ስለተዘጋበት የዘጋጅሁ ሰዎች አንሱ ተብሎ ስሙ ተጠቅሶ በማስታወቂያ ለሄድ መሆኑ ሲነገር ይህ ሰው የተዘጋጀ ስነ ስርአት ሳይጠናቀቅ ለምንድን ነው ካህን ሆኖ ረግጦ የሚሄደው ብዬ ነበር። ለካስ አጭበርብሮ ለማለፍ ታስቦ የተደረገ የመሰሪ ድርጊት ነበር። እስከመቼ ግን እነዚህን አራሙቻዎችና ጥቅመኞች ቤተክርስቲያን ተሸክማ ትኖራልች?
I wholeheartedly agree with this report. I didn’t see Memeher Tesfsye Mekoya and Memeher Dr. Zebene Lemma last Sunday. Can anyone tell me the reason for their no show? Why they missed this historic event?
Great to be an Ethiopian, the event filled my spirit more than any other time, it was uncorrupted, true and real… it influenced me to become more Ethiopian in commitment and more upfront to attain freedom. It was the voice of the voiceless; it was an encouragement for those who do understand life or death is a question of survival, and a wake-up call for those who don’t understand to differentiate that politics is not a question of the rights of human nature. Men and women are born equal and shall remain equal under the law…. This is not politics but a right by birth and indiscriminate by contract with a government of the state. Thank you the organizers!!!
ይገማል በጣምም ያሳዝናል። ለኔ በዚህ ፈታኝ ዘመን እግዚብሔር ፈቅዶልኝ ሰማዕታትን በመፅሐፍት ብቻ ሲወደሱ እሰማ የነበረውን በአይኔ በመመልከቴ የተዋህዶ እምነቴን እጅግ ከፍ አርጎታል ። ሆኖም ግን የኢትዬጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ አዳዲስ ተኩላዎች በተለይ በዋሽንግተን ዲሲ እያመሱን ይገኛሉ ። አርብ ኤዝፕሪል 24 ቅድስት ማርያም የነበረውን መርሐ ግብር ይመራ የነበረው ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ ነበር ። ልክ ፕሮግራሙ እንደተጀመረ በቤተክርስቲያናችን ደንብ መሠረት በእድሜ የበለፀጉ አባቶችን ሳያስቀድም መምህር ዘበነን በትልቅ ልመና በሚያስገርም መልኩ ” መምህር ዘበነ እበክዎ መድረኩን ይያዙ እባክዎ በቁመትም ይበልጡኛል …..” ሌላም ብዙ ብሎ ጋበዘውና መምህር ዘበነም ዘሎ ወጣና ስለ አንድነት ስለ ምን ስለምናምን ተናግሮ ሲጨርስ እነኛ የእድሜ ባለፀጎች የሚሉትን ለመስማት ሳይገደው ሾልኮ ሲሄድ በአጋሩ ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ አንደበት ተጋለጠ። ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ እንደዛ ያዙኝ ልቀቁኝ “ኢትዬጵያዊ ኢትዬጵያዊነቱን ነብር ዥንጉነቱን አይለቅም” የሚለውን ጥቅስ እየጠቀሰ በቁጭት ይናገር የነበረው ቆብ የጫነ ሰው ምን ነክቶት እንደቀረ መመርመር አለበት ። ለእግዚአብሔር ቤት ወይስ ለወያኔ ቤት ያደሩ እንበላቸው? መምሕር ዘበነ ደግሞ አይኑን በጨው ታጥቦ አንጋፋውን ቤተ ክርስቲያን የእንግሊዝኛ ቁዋንቁዋ መማሪያ መድረክ አርጎታል። በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ኢትዬጵያውያን በሚገኙበት መንተባተቡ አሳፋሪና የታሪክ ጉድፍ ነው።
I will give credit for Memehir Zebene Lemma for immediately releasing a video about the Ethiopian Martyrs in Libya. However, he failed to do things that are basic and essential afterwards. We don’t know whether he might have been criticized about the video by TPLF management. We don’t know that. But, let me say this; he did not mention the recognition of those killed in Libya as Martyrs by the Legitimate Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Synod. It’s sicking and very frustrating for our priests to play dirty politics. I know he’s a young man who is trying to impress everybody. But he has to be careful in not crossing the red line.
Assefa good point but what is the porpoise of his service? why did he get in theological teachings? The Bible tells us to tell the truth and stand for the truth. Do we see Zebene doing it? NO, NO, NO. Who are this priests? why are they here? I don’t think they belong to the same Church Abune Petros who died for Ethiopia and Ethiopians. God help us
TPLF is responsible for the division of our church, by removing the legitimate Patriarch, Abune Merkorios and installing its own cadres, Abune Paulos and Abune Mathias. In regard to Abune Mathias, memebers of Medhane Alem Church don’t forget how their church’s money was stolen by Abune Mathias. TPLF = Abune Mathias
ስለእንግሊዝኛ ቋንቋ አጠቃቀም በቤተክርስቲያን ውስጥ ለተባለው መጥፎ አይመስለኝም። መሆን ያለበት ግን አማርኛ ለማይችሉ ልጆቻችንና የኛን እምነት ለተቀበሉ የሌላ አገር ተወላጆች ብቻ ነው። ኢትዮጵያውያን ብቻ በሚገኙበት ቤተክርስቲያን ውስጥ በአንግሊዝኛ አገልግሎት ለመስጠት መሞከር ክፈረንጅ አምላኪነትና ከበታችነት ስሜት የመነጨ እንጅ ሌላ ምንም አይነት አሳማኝ ምክንያትና ጠቀሜታ የለውም። በየሳምንቱ አፀደ ቤተክርስቲያን የሚገኙ ብዙ ኢትዮጵያውያን እንግሊዝኛ የማይናገሩ እንዳሉ እየታወቀ እነሱ ባሉበት እንግሊዝኛ መጠቀም “እነሱን ውጡልን አንፈልጋችሁም” ማለት እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል። እንግሊዝኛ ለሚናገሩትም ቢሆን የዘበነ አይነት አማርኛ በጣም የተጫነው accent ስብከት ለመከታተል ይከብዳል። የእንግሊዝኛ ሰዋሰው (grammar) አጠቃቀምም እራሱን የቻለ ፈተና ነው። በንባብ መልክ ሲሰጥ ደግሞ ስብከት ሳይሆን ተራ ንግግር ሰለሚመስል ሁሉንም ነገር ያበላሸዋል። ስለሆነም የእንግሊዝኛው አገልግሎት ለእንግሊዥኛ ቋንቋ ተጠቃሚዎች ብቻ ሆኖ የአክሰንት ችግርን ለመቅረፍ sub-title በእንግሊዝኛ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ባሉ ሰሌዳዎች ላይ መጻፍ የግድ አስፈላጊ ነው። ሌላው ከዚህ ነጥብ ላይ ማንሳት የምፈልገው፤ ከኢትዮጵያ በቅርቡ እንደ መምህር ዶክተር ዘበነ ከኮሌጅ ተመርቀው የሚመጡ መምህራን የግእዝ ቋንቋ ችሎታቸው አጥጋቢ አለመሆኑን እነሱም እራሳቸው ስለማይክዱት ለማሻሻል ቢያስቡበት መልካም ነው። በተለይ የቆሎ ተማሪነት ባህልና አሰራር ከሌላቸው የአገሪቱ ክፍሎች የሚመጡት መምህራን የግእዝ ቋንቋ ችሎታቸውን ማዳበርና ማሰልቀጥ እንዳለባቸው መገንዘብ አለባቸው።
I have also noticed a lack of Geez proficiency in the new “Memeherane”. They absolutely have to do a better job mastering GEEZ!