My wife cigarette addiction is embarrassing me ባለቤቴ በሱስ መጠመዷ አንገቴን እያስደፋኝ ነው

ባለቤቴ የሲጃራ ሱስ አለባት፡፡ ብመክራት ባስመክራትም ማጨሷን ልትተው አልቻለችም፡፡ በተለይ ቤተሰቦቼ ጋር ይዣት ስሄድ ይሄ ልምዷ አንገቴን እያስደፋኝ ነው፤ ባለቤቴ ከዚህ ሱስ እንድትወጣ ምን ላድርግ?
ለማ (ከአዲስ አበባ)
ውድ ለማ በመጀመሪያ ደረጃ ይህን ጥያቄ በማቅረብህ ለባለቤትህ ያለህን ፍቅርና ክብር አመላካች በመሆኑ በጣም ጥሩ ነው፡፡ የተጠቀሰውን ችግር ለመፍታት የሁለታችሁም የጋራ ጥረት ያስፈልጋል፡፡ በዋናነት ባለቤትህ ከፍተኛ ሚና ይጠበቅባታል፡፡
የሲጋራ ሱስን ለመቀነስ ተመራጭ የሆኑ መንገዶች አሉ፡፡ ከእነዚህ መካከል በምታጨስበት ወቅት የሚሰማትን ጥሩና መጥፎ ስሜት መፃፍ ነው፡፡ ወረቀት ላይ ጥሩና መጥፎ ስሜቷን የምትፅፍበትን በሁለት ቦታ ትከፍላለች፡፡ ከጥሩና ከመጥፎ ስሜቷ ባሰፈረች ቁጥር አዎንታዊ ጎኑ ካመዘነ ሲጋራ ለማጨስ ዝግጁ ትሆናለች፡፡
ሌላው ሲጋራ በማጨስ ምትክ የተለያዩ ሊያዝናኗት የሚችሉ ነገሮችን ለመተካት መሞከር ነው፡፡ ለምሳሌ የተለያዩ ፍራፍሬዎችን መመገብ፣ መዝናናት፣ የእግር ጉዞ ማድረግ ናቸው፡፡ እንዲሁም ባለፈ ህይወቷ የሰራቻቸውን ተግባራትን ማስታወስና ከሱስ በፊት የነበራትን ጠንካራ ጎንና ተግባሮች ከአሁን ጋር ማነፃፀር፤ ይህ ሲሆን የራስ መተማመን ብቃቷን ያጎለብታል፡፡
ገንዘብ እንድታጠራቅም ማድረግ ሌላው አማራጭ መንገድ ነው፡፡ ለሲጃራ ታወጣ የነበረውን የገንዘብ መጠን ማስቀመጥ፡፡ በዚህም ምን ያህል ገንዘብ እንዳባከነች ትረዳለች፡፡ በከፍተኛ ደረጃ ከፍላ ማግኘት የምትፈልጋቸውን ነገሮች ማግኘት እንደምትችል ታረጋግጣለች፡፡
ከሲጋራ ጭስ የፀዳ አካባቢ መፍጠርም ይቻላል፡፡ ቤት፣ መኪና፣ ካፌ፣ . . ወዘተ እሷ በምትገኝበት ቦታ ሲጋራ እንዳይጨስ ማድረግ፡፡ ጥናቶች እንደሚያረጋግጡት በጭንቀትና በቁዘማ ወቅት ሲጋራ ለማቆም የሚደረግ ሙከራ አዋጭ አይደለም፡፡ ከዚህ ይልቅ በተስተካከለና በጥሩ ሁኔታ ውስጥ /ሙድ/ ስትሆን ሙከራ አድርግ፡፡
ከዚህ ችግር ባለቤትህን ለማውጣት ከላይ የተጠቀሱትን መንገዶች ሂድባቸው መልካም እድል እንዲገጥምህ እመኛለሁ፡፡

Subscribe to Sodere YouTube channel. የዩቲዩብ ቻናልችን ደንበኛ ለመሆን ይመዝገቡ።

See below for some videos from Sodere YouTube channel
Ethiopian Movie Sidet (Exodus) Full

Ethiopian Movie AYREFDEM Full

Ethiopian Movie Kanchi Befit Full

Ethiopian Movie MEZEZ Full

Ethiopian Movie Yefeker Ken full

Ethiopian Movie Yalteneka Full

Ethiopian Movie Kistet Full

Ethiopian Movie Saken Meleskut Full

Ethiopian Movie Bethelehem Full

Ethiopian Movie Setota Full

Ethiopian Movie Mena

Ethiopian comedy movie Che Belew 2

ትኩስ እና ሰበር ዜና፣ በብዛት የታዩ ቪድዮዎች፣ ፊልሞች፣ ድራማዎች፣ ሙዚቃዎች፣ ጠቃሚ ምክሮችን እና አስገራሚ ታሪኮችን በቀን አንዴ በኢሜል አድራሻችሁ እንልካለን። ይህንን ሊንክ በመጠቀም ኢሜላችሁን አስመዝግቡ። Receive Ethiopian News, Movies and Videos by email. Sign up for Email alerts