ሰዎች ሃሳባቸውን በነጻነት የመግለጽ መብት አላቸው::የህዝቦችን ነጻነት መጋፋት ጋዜጠኛ አያሰኝም::
ጥፋተኛው የኢሳት ኢዲቶሪያል ሳይሆን የጥቂት ግለሰቦች የማናለብኝነት እና በስሜት የመነዳት ፖለቲካ ነው:: አዎን ምናልባት አንዳንዶች በልቅ የፖለቲካ ስድነት ያሸበረቁ ግለሰቦች ስማቸውን የቀያየሩ ሰውን በየድህረገጹ የሚዘልፉ የኢሳት ጋዜጠኞች ይህ ጽሁፍ ላይመቻቸው ይችላል::

ኢሳት ገና ከጅምሩ ሲመሰረት ህዝባዊ አላማ አንግቦ እና ህዝባዊ ስራዎችን ለመስራት እንደተቋቋመ የማይካድ ሃቅ ነው::ኢሳት የሰራቸው በጎ ተግባራት እንደተጠበቁ ሆነው እጅግ ሊሻሻሉ እና ሊታረሙ የሚገባቸው ጥፋቶችም በገሃድ አይተናል እያየን ነው::አብዛኛው ጥፋቶች የሚከሰቱት ዲሲ ከሚገኘው እና የግንቦት ሰባት አመራሮች በስሜት ፖለቲካቸው ከሚነዱት ስቱዲዮ መሆኑን ስንመለከት ደሞ ራሳችንን እንድንጠይቅ አድርጎናል::

ለኢሳት ስኬት አስፈላጊውን አስታውጾ እና ድጋፍ እስካደረኩ ድረስ የኢሳት ጉዳይ ያገባኛል ይመለከተኛል:: አንዳንድ ኢሳት የነሱ ብቻ የሚመስላቸው አዋቃጭ ግለሰቦች በደመነብስ የሚናገሩትን አልባሌ ቦለቲካቸውን ወደ ጎን በመተው ኢሳት ሊጠናከር የሚችለው ያለበትን ሲያርም እና በውስጡ የተወሸቁ ስሜታዊ እና ልቅ ጋዜተኞችን ሃይ ማለት ሲችል ብቻ ነው::አንድ ሳው አስተያየት በሰጠ ሰአት ሁሉ እየተነሱ የኒዛለፉ እና የሚሳደቡ ባለጌ ጋዜጠኞች እና አዋቃጭ ተባባሪዎቻቸውን ሊያርማቸው ይገባል::ጥላቻን ማራመድ በቀረበት በዚህ ስልጡን ዘመን ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያውያን ላይ ጥላቻ እንዲያራምዱ የሃገር ጉዳይ ተረስቶ ግለሰቦች እንዲዘረጠጡ በተራ አሉባልታ እና የስድብ ናዳ ጊዜ እንዲጠፋ የሚያደርጉ ሰዎችን ታቅፎ መጓዝ ከተጠያቂነት አያድንም::

የኢሳት ጋዜጠኞች በሃገር ውስጥ እና በውጪ ሃገር የሚገኙ የፖለቲካ ድርጅቶችን ወደ አንድነት እና የጋራ አጀንዳ እንዲመጡ መስራት ሲገባቸው እየከፋፈሉ የህዝብ የለውጥ ጥያቄ እና የነጻነት ጥማት እንዲዘገይ አድርገዋል::በሃገር ቤት የሚገኙ ፓርቲዎችን አንዱን ከፍ አንዱን ዝቅ በማደረግ በየፕሮግራሞቻቸው እኩልነትን ባላስተናገደ መልኩ በመዝለፍ እጅግ አሳፋሪ የሆነ የጋዜጠኝነት ስራ ስውርተዋል::በስሜት የሚነዱ ጥቂቶች የህዝብ ቤት ይሆናል የተባለውን ኢሳትን የራሳቸው የስሜት ሃሳብ መጋለቢያ አድርገውታል::በውጪ ሃገር የሚገኙ የፖለቲካ ድርጅቶችን በማግለል የአንድ የፖለቲካ ድርጅት ስም ገኖ እንዲወጣ ተግተው ሲሰሩ በተግባር እያየን ነው::ስለዚህ ኢሳት የኔ ነው እስካልን ድረስ የኢሳት ጉዳይ ይመለከተናል እንዲታረምም ሂስ የመስጠት መብታችን የተጠብቀ ነው::ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ብዙ ማለት ይቻል ነበር ግን የኢሳት ቦርድ ሁኔታውን አይቶ ሊያስተካክል ይገባል::
Image

መታሰር ክፉ ነው፡፡ የታሰረ ሰው ተስፋው ሁሉ ውጪ በቀረው ታጋይ ላይ ነው፡፡ የሀብታሙ አያሌው እና የየሺዋስ አሰፋ ልብ የሚነካ ተማፅኖ አእምሮዬን ሁሉ ተቆጣጥሮታል፡፡ ‹‹እባካችሁ ተባበሩ›› ‹‹እስቲ ቀረብ ብላችሁ ተነጋገሩ›› በየንግግራቸው መሀል እየደጋገሙ የሚያስተላልፉት መልዕክት ነው፡፡ ‹‹እኛ እኮ ከዛሬ ነገ ለውጥ መጥቶ ኑ ውጡ እንባላለን ብለን ነው የምንጠብቀው……በተናጠል ድርጅቶች ያላቸውን አቅም የምናውቀው ነው….እባካችሁ ተባበሩ›› ሀብታሙ አያሌው፡፡
አንድነት እና ሰማያዊ በትብብሩ ውስጥ አብረው መስራት ለምን አይችሉም???
አብረው መስራት የማይችሉበት ምንም ምክንያት ፈልጌ ላገኝ አልቻልኩም፡፡ ከሁለቱም በኩል በቀና እና ለውጥ ፈላጊ ልቦና ተቀራርቦ መነጋገር ከተቻለ የሚያግዳቸው ምንም ነገር አይኖርም፡፡ ሀብታሙ አያሌው እና የሺዋስ አሰፋ ቂሊንጦ ሲገቡ ተግባብተዋል፡፡ እኛም ነገ ቂሊንጦ ከገባን መግባባታችን አይቀርም፡፡ ከዛም እንደ የሺዋስ እና ሀብታሙ ውጪ ያለውን ሰው ተባበሩ እያልን እንመክራለን፡፡ በተስፋ ምግብም መንፈሳችንን በሂወት ለማቆየት እንጥራለን…..ከንቱ ልፋት፡፡
ወህኒ ሳንወርድ አሁን ላይ መግባባት ስለምን ይሳነናል???
አሁን ባለው ነባራዊ እውነታ አንድነት እና ሰማያዊ በትግል ስልታቸው ላይ መጠነኛ ልዩነት ያላቸው ይመስላል፡፡ ነገር ግን እንዲህ አይነት መጠነኛ ልዩነት አይደልም በሁለት ፓርቲ መሀል ይቅርና በአንድ ፓርቲ ውስጥም ባሉ ግለሰቦች መሀል የሚከሰት ነው፡፡ አንድነት ያለምንም ቅድመ ሁናቴ ምርጫ ውስጥ እገባለሁ ብሏል፤ ሰማያዊ ደግሞ ቅድመሁናቴ አስቀጧል፡፡ ነገር ግን ከምርጫ ሂደት ውስጥ ወጥቻለሁ ያለ የለም፡፡ በመሆኑም ምርጫውን ያለቅድመ ሁናቴ የሚሳተፈውና ቅድመሁናቴ ያስቀመጠው አካል የምርጫ ምህዳሩን ለማስፋት፤ ምርጫው አልሆን ካለ ደግሞ ለህዝባዊ እምቢተኝነት ተባብረው የማይሰሩበት ምክንያት አይታየኝም፡፡
አንድነት ወደ ትብብሩ ያልመጣበት ምክንያት ከመድረክ ከወጣሁ በኋላ እንደገና ያለጥናት በፍጥነት ወደ ሌላ ትብብር ውስጥ መግባት የለብኝም የሚል ነው፡፡ ነገር ግን አንድነት ፓርቲ ውህደት ከሆነ በማንኛውም ጊዜ ዝግጁ ነኝ ይላል፡፡ ለመዋሀድ ዝግጁ የሆነ አካል ደግሞ ለመተባበር ይከብደዋል ብዬ ማሰብ ያቅተኛል፡፡ በመሆኑም ለመተባበር ዛሬ ነገ ሳይል ቢወስን ደስ ይለኛል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ትብብሩ ውስጥ ያሉት ፓርቲዎች ግማሽ መንገድ ሄደው አንድነትን መቀበል አለባቸው ብዬ አምናለሁ፡፡ አንድነት ካለው ድርጅታዊ አቅም አንፃር ታይቶ የትብብሩ ምክር ቤት አባል ብቻ ሳይሆን የትብብሩ ስራ አስፈፃሚም ውስጥ ተወካዩን እንዲያስገባ ሊፈቅዱለት ይገባል እላለሁ፡፡ ይህ ደግሞ ለአረናም ሆነ ለኦፌኮ የሚሰራ ይመስለኛል፡፡
በዚህ መልኩ ተባብረው የሚሰሩ ከሆኑ ምናልባትም አሁንም ቢሆን ጊዜው አረፈደም እና ሁሉም ፓርቲዎች በስምምነት በአንዱ ፓርቲ የምርጫ ምልክት ሊወዳደሩ ይችላሉ፡፡ ይህ እንኳን ባይሆን በእጩ አቀራረብ ላይ እየተመካከሩ ድምፅ የማይነጣጠቁበትን መንገድ መፈለግ ይችላሉ፡፡ ምርጫው ነፃ እስካልሆነ ድረስ አላስፈላጊ ነው ብለው ካሰቡም በጋራ ህዝቡን ለህዝባዊ እምቢተኝነት የሚያነቁበትን እና የሚያደራጁበትን መንገድ መፈለግ ይችላሉ፡፡
በቅርቡ አንድነት ፓርቲ በተለያዩ ክፍለሀገሮች ሰልፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡ ትብብሩም ሁለተኛ ዙር መርሀግብሩን አውጥቷል፡፡ እነዚህን ሁለት እንቅስቃሴዎች ማቀናጀት አስፈላጊ ነው፡፡ ለዚህም ከእንቅስቃሴዎቹ በፊት ፓርቲዎቹ አንዳች ስምምነት ላይ መድረስ አለባቸው፡፡
የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ እኔም ሆንኩ ሌሎች ጓዶች መታሰራችን እንደማይቀር አውቀዋለሁ፡፡ እስር ቤት ከገባሁ በኋላ ግን ውጪ ያለውን አካል እንዲተባበር መለመንን አልሻም፡፡ ‹‹ቀን ሳለ ሩጥ›› እንዲሉ ዛሬ ውጪ እያለሁ ፓርቲዎቹ እንዲተባበሩ ሙሉ ጊዜየን ሰጥቼ እሰራለሁ፡፡ ሌሎችም እንዲሰሩ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡
Image

Image

የባህር ዳሩ ገዳይ ካለምንም ጥያቄ በቀጥታ ለፖሊስ እጁን ሰቷል:: Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
ባሳለፍነው ሳምንት በአዲስ አበባ ካሳንቺስ ከቀድሞ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ጀርባ ከሚገኘው ድብቅ የደህንነት እስር ቤት ውስጥ በመገኘት በከፍተኛ የሴኩሪቲ ጥበቃ የነጻነት ታጋይ የሆነውን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር Greg Dorey እንዳነጋገሩ ሲታወቅ ከአንዳርጋቸው ጋር ያደረጉትን ቆይታ በተመለከተ ዝርዝር ማብራሪያ ባይገኝም በደህና ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ሲገልጹ የኤምባሲው ምንጮች እንዳሉት ስለ አንዳርጋቸው መረጃ ያላቸው ለስርአቱ ቅርብ የሆኑ ክፍተኛ የደህንነት አባላት እና የአንድ ብሄር ተወላጅ የሆኑ አንድ ቋንቋ ተናጋሪዎች እንደሆኑ ገልጸዋል::እንዲሁም አመነስቲ ኢንተርናሽናል አንዳርጋቸውን በተመለከተ ከታፍነ 6 ወር መሆኑን ገልጾ ሁኔታው አሳሳቢ ነው ሲል ለእንግሊዝ መንግስት አቤት ያለበተን መግለጫ ባሳለፍነው ሳምንት መግለጫ አውጥቶ ነበር::

ይህ በ እንዲህ እንዳለ በባህር ዳር ከተማ ውስጥ ድብ አንበሳ እየተባለ በሚጠራው ሆቴል አካባቢ አንድ አርሶ አድር ታጣቂ ሚሊሻ በሚመስል ጸጉረ ልውጥ ሰው የእንግሊዝ ዜግነት ያለው ቱሪስት መገደሉ ታውቋል::የአምባሰደሩ የአንዳርጋቸው ጽጌ ጉብኝት ተከትሎ የእንግሊዛዊ ቱሪስት መገደል ድንጋጤ ፈጥሯል::ገዳዩ ለግድያው እንደተዘጋጀበት በሚያስታውቅ መልኩ በአከባቢው አድብቶ ሲጠባበቅ የነበረ እና ወዲያው እንግሊዛዊውን እንደገደለው ለፖሊስ ያለምንም ጥያቄ እጁን ሰቷል::በአከባቢዉም የታተቁ ፖሊሶች የነበሩ ሲሆን ግድያው ሲፈጸም ምንም ያደረጉት መከላከል አልነበረም::ግድያው የተቀነባበረ ነው ሲል የባህር ዳር ህዝብ እየተናገረ ነው::

Image
በባህር ዳር ከተማ አንድ ኢንግሊዛዊ ቱሪስት ከአንድ ግለሰብ በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ አለፈ::በባህር ዳር ከተማ አንድ ኢንግሊዛዊ ቱሪስት ከአንድ ግለሰብ በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ አለፈ።ድርጊቱ የተፈፀመው ዛሬ ረፋድ 4 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ላይ ነው።በግድያው የተጠረጠረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ የወንጀል ድርጊቱ እየተጣራ ነው ። የሟቹም አስክሬን በሆስፒታል እንደሚገኝ ተመልክቷል።

ሻምበል ሳሙኤል መልካም ባህሪ ያለውና በፖለቲካ አቋሙ ገለልተኛ የሚባል ነው፡፡ ሪፖርተር :?:

” አብራሪዎቹ ከፖለቲካ ራሳቸውን ገለልተኛ ያደረጉት ባለው መንግስት ላይ ያላቸውን ጥላቻ እና ቂም ያመለክታል::በአንድ ሃገር የደህንነት ህዝባዊ ጥበቃ ስራ ላይ የተሰማራ ወታደር ከአምባገነኖች ፖለቲካ ራሱን ማግለሉ ህዝባዊ ተቆርቋሪነቱን ያሳያል:: ” Minilik Salsawi

ባለፈው ወር የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከፍተኛ አመራሮች ጠንከር ባለ ግምገማ ተወጥረው ነበረ::
የተጠለፈው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ሔሊኮፕተር አሰብ ማረፉ ተረጋገጠ ::
ሪፖርተር :- የኢትዮጵያ አየር ኃይል ንብረት የሆነ ተዋጊ ሔሊኮፕተር ባለፈው ዓርብ ተጠልፎ ኤርትራ ግዛት አሰብ ማረፉ ተረጋገጠ፡፡ የዘወትር የበረራ ልምምድ ላይ የነበረውን የኢትዮጵያ አየር ኃይል ሩሲያ ሠራሽ ኤምአይ 35 ተዋጊ ሔሊኮፕተር ይዞ ወደ ኤርትራ የኮበለለው ዋና አብራሪ ሻምበል ሳሙኤል ግደይ፣ ይህንን ዓይነት ተግባር ይፈጽማል ብለው እንደማያስቡ ባልደረቦቹ ገልጸዋል፡፡

ከሻምበል ሳሙኤል ጋር በኢትዮጵያ አየር ኃይል አብረው የሠለጠኑና የሠሩ የሥራ ባልደረቦቹ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ግለሰቡ መልካም ባህሪ ያለውና በፖለቲካ አቋሙ ገለልተኛ የሚባል ነው፡፡ ‹‹እጅግ በጣም ጥሩ ሰው ነው፡፡ የመንግሥት ተቃዋሚ አልነበረም፡፡ ራሱን ከፖለቲካ ጉዳዮች የሚያገል፣ ሥራውን ብቻ የሚሠራና ልጆቹን በኃላፊነት የሚያሳድግ ሰው ነበር፤›› ብለው በድርጊቱ ግራ መጋባታቸውን ገልጸዋል፡፡

አክለውም በትንሽ ነገር የሚከፋና የሚደሰት፣ በቅጽበት የሚለዋወጥ ባህሪ እንዳለው ተናግረዋል፡፡ በግል ሕይወቱም የሚበሳጭበት ጉዳይ እንደነበርና አልፎ አልፎም በዚሁ ጉዳይ ይደበት እንደነበር አልሸሸጉም፡፡ ሻምበል ሳሙኤል ለሥልጠና ወደ ኢትዮጵያ አየር ኃይል የገባው በ1994 ዓ.ም. ሲሆን፣ የቅጥር ውል የፈረመው በታህሳስ ወር 1995 ዓ.ም. ነበር፡፡ የኢትዮጵያ አየር ኃይልን ለ12 ዓመታት አገልግሏል፡፡ በ2003 ዓ.ም. የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ወደ ዳርፉር ሱዳን ያሰማራው የሰላም አስከባሪ ኃይል አባል በመሆን ለአንድ ዓመት ያህል እንዳገለገለና በዚያም ተልዕኮ ዳጐስ ያለ ዶላር ይዞ መመለሱን ባልደረቦቹ ተናግረዋል፡፡

ሻምበል ሳሙኤል ተወልዶ ያደገው በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ መሆኑን፣ ወላጆቹ የመቀሌ ነዋሪ መሆናቸውን ባለቤቱና ሁለት ልጆቹ ቢሾፍቱ እንደሚኖሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ባለፈው ዓርብ ማለዳ ከረዳት አብራሪው መቶ አለቃ ቢልልኝ ደሳለኝና የበረራ ቴክኒሺያን ፀጋ ብርሃን ግደይ ጋር በኤምአይ 35 ተዋጊ ሔሊኮፕተር የዘወትር የልምምድ በረራ ለማድረግ ከጠዋቱ 2፡35 ሰዓት ድሬዳዋ ከሚገኘው የአየር ኃይል ቤዝ እንደተነሱ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ዋና አብራሪው ከአጭር ጊዜ በረራ በኋላ የበረራ ከፍታውን በመቀነስ ወደ ኤርትራ በማቅናት ሔሊኮፕተሩን አሰብ ማሳረፉን ምንጮች ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

መከላከያ ሚኒስቴር ባለፈው ሰኞ ባወጣው መግለጫ ተዋጊ ሔሊኮፕተሩን ዋና አብራሪው ይዞ ወደ ኤርትራ መኮብለሉን አምኗል፡፡ ሚኒስቴሩ በመግለጫው ዋና አብራሪው ቴክኒሺያኑንና ረዳት አብራሪውን በማስገደድ ኤርትራ ማረፉን አስታውቋል፡፡

ሔሊኮፕተሩ ባለፈው ዓርብ ከጠዋቱ 2፡35 ሰዓት ጀምሮ በመደበኛ የሥልጠና ልምምድ ላይ እንደነበር ጠቅሶ፣ ሔሊኮፕተሩ ከግንኙነት ውጪ በመሆኑ ሠራዊቱ በአካባቢው ማኅበረሰብና አጋሮች ለተከታታይ ቀናት ፍለጋ ሲደረግለት መቆየቱን አትቷል፡፡ ‹‹ሆኖም ሔሊኮፕተሩ በከሀዲው ዋና አብራሪ አማካይነት ቴክኒሻንና ረዳት አብራሪውን በማስገደድ ኤርትራ ማረፉን መረጃዎች ይጠቁማሉ፤›› ብሏል፡፡ ያነጋገርናቸው የኢትዮጵያ አየር ኃይል አብራሪዎች ዋና አብራሪው የሔሊኮፕተሩ አዛዥ በመሆኑ የትም ወስዶ ሊያሳርፈው እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

‹‹ረዳት አብራሪው ጀማሪ ነው፡፡ የበረራ ቴክኒሺያኑ ቴክኒካዊ ጉዳዮችን መከታተል ነው፡፡ ዋና አብራሪው ረዳት አብራሪውና ቴክኒሺያኑ እያወቁም ወይም ያለነሱ ዕውቅና የፈለገበት ወስዶ ሊያሳርፍ ይችላል፤›› ብለዋል፡፡ ባለፈው ወር የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከፍተኛ አመራሮች ጠንከር ባለ ግምገማ ተወጥረው መክረማቸውን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ኤምአይ 35 ሔሊኮፕተር መትረየስና ተወንጫፊ ሮኬቶች የተገጠሙለት ዘመናዊ ተዋጊ ሔሊኮፕተር ነው፡፡ ከኋላው ስምንት ወታደሮችን ወይም ሁለት የቁስለኛ አልጋዎችን መያዝ ይችላል፡፡ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ኤምአይ 17 እና ኤምአይ 8 የትራንስፖርት ሔሊኮፕተሮች ሲኖሩት፣ ለውጊያ የሚጠቀምባቸው በደርግ ጊዜ የተገዙ ኤምአይ 24 ሔሊኮፕተሮችን ነበር፡፡ በግንቦት 1990 ዓ.ም. የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ሲጀመር አሥር ኤምአይ 35 ሔሊኮፕተሮች የተገዙ ሲሆን፣ በጦርነቱ ወቅት ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡

የ1997 ዓ.ም. ሦስተኛ ብሔራዊ ምርጫ ተከትሎ የተነሳውን ግርግር ተከትሎ ሁለት የኢትዮጵያ አየር ኃይል አብራሪዎች (ሻምበል አብዮት እና ሻምበል በኃይሉ) አንድ ኤምአይ 35 ሔሊኮፕተር ይዘው ወደ ጐረቤት አገር ጂቡቲ መኮብለላቸው ይታወሳል፡፡ ብዙም ሳይቆይ የጂቡቲ መንግሥት አብራሪዎቹን አሳልፎ ለኢትዮጵያ መንግሥት የሰጠ ሲሆን ሔሊኮፕተሩንም መልሷል፡፡ አብራሪዎቹ የጦር ፍርድ ቤት ቀርበው በአሁኑ ወቅት በእስር እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በተመሳሳይ ወቅት በቤላሩስ በሥልጠና ላይ የነበሩ ሰባት የኢትዮጵያ አየር ኃይል የኤስዩ 27 ተዋጊ ጀት አብራሪዎች ከድተው ጥገኝነት መጠየቃቸው ይታወሳል፡፡ አብራሪዎቹ በተለያዩ የምዕራብ አገሮች ጥገኝነት ማግኘታቸው ይነገራል፡፡

ቀደም ሲል ሻምበል ተሾመ ተንኮሉ የተባለ የአየር ኃይል ባልደረባ በ1995 ዓ.ም. ኤል 39 የተሰኘ የመለማመጃና ቀላል የውጊያ አውሮፕላን ለልምምድ በረራ ከመቀሌ ቤዝ ይዞ እንደተነሳ ወደ ኤርትራ ኮብልሎ ነበር፡፡

እስከ ማክሰኞ ታኅሳስ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ምሽት ድረስ የኤርትራ መንግሥት ስለተጠለፈው ኤምአይ 35 ሔሊኮፕተር ምንም ዓይነት መግለጫ አልሰጠም፡፡
source Reporter ሪፖርተር
Image

በነ ሀብታሙ አያሌው የክስ ጉዳይ የተሰየመው ችሎት ‹አስገራሚ› ውሎ

∙ተከሳሾቹ ‹‹ዘረፋ›› ተፈጽሞብናል ብለዋል ∙‹‹ለማን አቤት ይባላል?›› ሀብታሙ አያሌው

በላይ ማናዬ : ዛሬ ታህሳስ 15 ቀን 2007 ዓ.ም በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮችን ጨምሮ 10ሩም ተከሳሾች በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ 19ኛው ወንጀል ምድብ ችሎት ቀርበው ነበር፡፡ የሰማያዊ፣ የአንድነትና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች የሆኑት አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና አቶ አብርሃ ደስታ እንዲሁም አንደኛ ተከሳሽን ጨምሮ ስድስት ተከሳሾች ተሟልተው ፍርድ ቤት ተገኝተዋል፡፡

ችሎቱ የተሰየመው ታህሳስ 9 ቀን 2007 ዓ.ም በነበረው የፍርድ ቤት ውሎ ወቅት ተከሳሾች በቀረበባቸው የሽብር ክስ ላይ የሰጡትን መልስ በተመለከተ 7ኛ ተከሳሽ መልስ በዕለቱ ባለማቅረባቸው አሟልተው እንዲቀርቡ ነበር፡፡ በተጨማሪም ተከሳሾች በእስር ላይ ባሉበት ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሊጎበኟቸው የሚሄዱ ቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው ወደ እስር ቤቱ ሲገቡ በተለየ መዝገብ እንዲመዘገቡ እየተደረጉ መሆናቸውን ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅርበው ስለነበር ይህን በተመለከተ ማረሚያ ቤቱ ማብራሪያ እንዲሰጥ በታዘዘው መሰረት ማብራሪያውን ለመስማት ነበር፡፡
Image
የተከሳሾች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች በጥየቃ ወቅት በተለየ መዝገብ ይመዘገባሉ የተባለውን አቤቱታ በተመለከተ፣ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በደብዳቤ መልስ መስጠቱ የተገለጸ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ‹‹ማረሚያ ቤቱ በሰጠው መልስ እስረኞች ከሌሎች በተለየ የደረሰባቸው ችግር የለም›› ማለቱን ገልጾ ይህንኑ መልስ ሙሉ ለሙሉ መቀበሉን አስታውቋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን በዛሬው የችሎቱ ውሎ ላይ ተከሳሾች ለየት ያለ አቤቱታ በጠበቆቻቸው በኩል አቅርበዋል፡፡ ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ለችሎቱ እንዳስረዱት ደንበኞቻቸው ከሌሎች በተለየ መልኩ ከፍተኛ በደል እየተፈጸመባቸው ነው፡፡ አቶ ተማም አባቡልጉ በታህሳስ 12 ለ13 ቀን 2007 ዓ.ም አጥቢያ ሌሊት ስምንት ሰዓት ጀምሮ ደንበኞቻቸው ላይ ድንገተኛ ፍተሻ ተደርጎ የግል ማስታወሻዎቻቸው፣ ገንዘብ እና በተከሰሱበት ጉዳይ ላይ እያዘጋጁት የነበረው መቃወሚያና መከራከሪያ ተወስዶባቸዋል ብለዋል፡፡

‹‹ደንበኞቼ ላይ እየተደረገ ያለው ጉዳይ ለህይወታቸውም የሚያሰጋቸው ነው፡፡ በማረሚያ ቤቱ በሌሊት ፍተሻ ያደረጉባቸው ሰዎች ቀደም ሲል በምርመራ ወቅት ‹ህገ-ወጥ› ተግባራት ሲፈጽሙባቸው የነበሩ የፌደራል ፖሊስና የደህንነት አባላት ሰዎች ናቸው፡፡ እነዚህን ሰዎች ደንበኞቼ ያውቋቸዋል፡፡ ስለሆነም ፍተሻው የተከናወነው በማረሚያ ቤቱ ፖሊሶች አልነበረም ማለት ነው፡፡ ድርጊቱ የተፈጸመው የተለየ የስም ዝርዝር ተይዞ ከሌሎች በተለየ መልኩ ነው፡፡ ለአብነት ደንበኞቼ አቶ አብርሃ ደስታና በሌላ የክስ መዝገብ የተከሰሰው አብዱራዛቅ አክመድ ላይ የሆነው ከሌሎቹ በተለየ መልኩ ነው፡፡ ፍተሻው ስለት ነገር አልያም ሌላ ህገ-ወጥ ቁሳቁስ ለመያዝ የተደረገ አለመሆኑን ከተወሰዱት ንብረቶች ማየት ይቻላል›› ሲሉ አቶ ተማም ለፍርድ ቤቱ በደንበኞቻቸው ላይ የተፈጸመውን ድርጊት አስረድተዋል፡፡

ይህን በተመለከተ አስተያየት የሰጡት የፌደራል አቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ በበኩላቸው፣ ‹‹ማረሚያ ቤቱ መንግስት ዜጎች ታንጸው እንዲወጡ ያሰራው ነው፡፡ ይህን አሰራር ለመጠበቅም የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር የተለያዩ ስራዎችን ሊሰራ ይችላል፡፡ እየቀረበ ያለው አቤቱታም ከዚህ አኳያ መታየት ያለበት ነው›› ብለዋል፡፡

ጠበቃ ተማም የደንበኞቻቸውን አቤቱታ ከህግ አንጻር ያስረዱ ሲሆን፣ ‹‹በመሰረቱ ፍተሻ ሊካሄድ መቻሉ ላይ አይደለም አቤቱታው፡፡ የተካሄደው ፍተሻ ግን ህገ-ወጥ ነው፤ ምክንያቱም ፍተሻው የተከናወነበት ሰዓት ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ባለው ጊዜ ሳይሆን ሌሊት 8 ሰዓት ጀምሮ ነው፡፡ ይህ ህገ-ወጥ ነው፡፡ በሌላ በኩልም ፍተሻው በማረሚያ ቤቱ ፖሊሶች አይደለም የተከናወነው፡፡ በደህንነቶችና የፌደራል ፖሊሶች ነው ፍተሻው የተደረገው፡፡ ይህም ማረሚያ ቤቱ ደንበኞቼን ለመጠበቅ ፍላጎቱም ሆነ ብቃቱ እንደሌለው ያሳያል፡፡ ስለሆነም ፍርድ ቤቱ ይህን መሰል ድርጊት የፈጸሙት አካላትና በማን ትዕዛዝ እንደተፈጸመ ምርመራ እንዲካሄድ ትዕዛዝ እንዲሰጥልን እንጠይቃለን›› ብለዋል፡፡

ጠበቃ ተማም በተጨማሪ ከደንበኞቻቸው ላይ በፍተሻው ወቅት የተወሰዱባቸው ንብረቶችና ማስታወሻዎች እንዲመለሱላቸው ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው አመልክተዋል፡፡ ይህንኑ ጉዳይ በተመለከተ ‹‹የተለየ ከፍተኛ በደል ደርሶብኛል›› በሚል ለፍርድ ቤቱ እንዲያስረዱ ዕድል እንዲሰጣቸው ጠይቀው የነበሩት 3ኛ ተከሳሽ አቶ ዳንኤል ሺበሺ የጠየቁት የመናገር እድል ሳይፈቀድላቸው ቀርቷል፡፡

በጠበቆቹ አማካኝነት የቀረበው አቤቱታን በተመለከተ ችሎቱ አስተያየት የሰጠ ሲሆን በተለይ ጠበቃ ተማም አቤቱታውን ባቀረቡበት ወቅት ‹‹ማረሚያ ቤቱ ደንበኞቼን ለመጠበቅ ፍላጎትም ብቃትም የለውም›› ያሉት አገላለጽ ተገቢ ስላልሆነ እንዲታረሙ ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡ ይህንኑ ጉዳይ በቃል የገለጹት የመሐል ዳኛው፣ ‹‹እንዲህ አይነት አገላለጽ ማረሚያ ቤቱ የበቀል እርምጃ እንዲወስድ የሚገፋፋ እንዳይሆን…›› በማለት ሌላ አስገራሚ መነጋገሪያ ከፍተዋል፡፡

ይህን የዳኛውን ንግግር ተከትሎ 2ኛ ተከሳሽ አቶ ሀብታሙ አያሌው የመናገር እድል ከተደጋጋሚ ጥያቄ በኋላ ለአጭር ጊዜ ተፈቅዶለታል፡፡ እናም፣ ‹‹እርስዎ እያሉት ያለው ነገር ተገቢ አይደለም፡፡ በህይወቴ ላይ የደህንነት ስጋት አለብኝ ነው እያልኩ ያለሁት፡፡ ይህንን ስጋቴን ለችሎት እያስረዳሁ ነው፡፡ ግን እርስዎ ‹የበቀል እርምጃ› እንዲወሰድብን ማሳሰቢያ እየሰጡ ነው፡፡ ይህ ተገቢ አይደለም፡፡ በእርግጥ አሁንም የበቀል እርምጃ እንደማይወሰድብን ማረጋገጫ የለንም፡፡ እሺ ለማን አቤት ይባላል? የደረሰብንን በደል ለፍርድ ቤት ከማስረዳት ውጭ ለማን አቤት እንላለን….አሁን እኮ ፍርድ ቤቱ ከማረሚያ ቤቱ ጋር መወገኑን ነው እያየን ያለነው፡፡ ፍርድ ቤቱ የእኛን አቤቱታ እየሰማ አይደለም፡፡ ከፍርድ ቤት ውጭ ለማን አቤት እንበል?›› ሲል አቤቱታውን በስሜት ውስጥ ሆኖ አስረድቷል፡፡

የሀብታሙን ንግግር አዳምጠው አንደኛ ዳኛ ‹‹እኛ ሳንሆን ህጉ ነው ይህን እንድንል የሚያደርገን›› በማለት አጭር መልስ ሰጥተዋል፡፡

በዚህ መልኩ ቀጥሎ የዋለው ችሎት በተከሳሾች በኩል የቀረበውን አቤቱታ መርምሮ ፍርድ ቤቱ ይህን ጉዳይ የማየት ስልጣን አለው ወይስ የለውም በሚለው ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት፣ እና መደበኛ ክሱን ለማየት ለታህሳስ 24 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተጥቷል፡፡
‪#‎NegereEthiopia‬

Image
– የድሬደዋ አየር ሃይል መምሪያ በግምገማ ታመሰ::
– መጭውን ውህደት የሚያሳፈጽሙ የአርበኞች ግንባር አባላት ከአውሮፓ እና አውስትራሊያ ተወከሉ::
http://ireport.cnn.com/docs/DOC-1200173
አርብ እለት ከድሬዳዋ ተነስተው በደቡባዊ ኤርትራ አሰብ ዘልቀው የገቡት የወያኔው አየር ሃይል አብራሪዎች እና ቴክኒሺያኖች በደህና ሁኔታ ውስጥ ሲገኙ በኤርትራ የአየር ክልል የተቀበላቸው እና በ1987 አመተምህረት በወያኔ እና የደርግ መኮንኖች የሰለጠነው የሻእቢያ ኮማንዶ ጦር አጅቧቸው ወደ አስመራ ቤተመንግስት ከገቡ በኋላ በቤተ መንግስቱ ውስጥ ለሁለት ቀን በእንግዳ ማረፊያ ክፍል ውስጥ ቆይተው ወደ ሆቴል መዘዋወራቸውን ከአስመራ የተገኙ ምንጮች ጠቁመዋል::

በቤተ መንግስት ቆይታቸው አስፈላጊ ጥያቄዎች እና ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን ከደምህት ጦር ጋር በመቀላቀል እየተገነባ ባለው ዘመናዊ አየር ሃይል ውስጥ አገልግሎት እንዲሰጡ የተጠየቁ መሆኑን ምንጮቹ ሲናገሩ አብራሪዎቹ ግን ወደ አውሮፓ ለመጓዝ ፍላጎቱ እንዳላቸው እና አውሮፓ ሆነው ትግሉን መርዳት እንደሚችሉ ሲናገሩ ተደምጠዋል::አብራሪዎቹ እጃቸውን የሰጡትም ሆነ የተቀላቀሉት ከኤርትራ መንግስት ጋር እንጂ ከሌላ አካል ጋር እንዳልሆነ ምንጮቹ አረጋግጠዋል::

ከደብረዘይት አየር ሃይል አከባቢ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በድሬዳዋ ያለው የአየር ሃይል ካምፕ ሃላፊዎች ላይ ከፍተኛ ግምገማ ተደርጓል::በዚህም መሰረት የሃገሪት የአየር ክልል ሳይቀር ከራዳር ውጪ ነው የሚል ጉዳይ ተነስቶ መነጋገሪያ እና መገማገሚያ ሆንዋል::እርስ በርስ መወነጃጀል እንኳን ባልተደፈረበት ግምገማ ላይ እያንዳንዱ መኮንን ሃላፊነቱን ወስዶ ዋጋ ሊከፊል ዪገባዋል ሲሉ ከፍተኛ አዛዦች በቁጣ ተናግረዋል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ በመጪዎቹ ሳምንት በሚካሄደው የግንቦት ሰባት እና የአርበኞች ግንባር ውህደት ላይ እስካሁን ወኪል ያላከው የአርበኞች ግንባር አንድ ሰው ከአውሮፓ አንድ ሰው ከአውስትራሊያ በመምረጥ ለእህደት ስብሰባው ማስትላለፉን ምንጮቹ ተናግረዋል::የተመረጡት አስመራ እንደደረሱ በውህደቱ ዙሪያ ንግግር እንደሚጀመር እና የፊርማው ውህደት እንደሚጸድቅ ኮሎኔል ፍጹምን ዋቢ ያደረጉ ምንጮች ጠቁመዋል::

Image

“ካልመለሱልኝ በውጊያ አስመልሰዋለሁ::” የደነገጠው ወያኔ
(ምንሊክ ሳልሳዊ)
ስርአቱን ከዱ የተባሉት አብራሪዎች ከድሬዳዋ ተነስተው በጅቡቲ ድንበር አስታከው በአሰብ ዘልቀው ኤርትራ ያሳረፉት ሄሊኮፕተር በሱዳን በኩል እንዲመለስለት ሻእቢያን መጠየቁን የሱዳን ዲፕሎማቶች ጠቆሙ::

ወያኔ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚያደርገውን ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እና በአየር ሃይሉ ውስጥ የሚፈጸመውን ደባ በመቃወም ከድተዋል የተባሉት 2 ፓይለቶች(ካፒቴን ሳሙኤል እና ቢሊሊኝ )እና አንድ ቴክኒሽያን(ጸጋ ብርሃን)ለኤርትራ መንግስት እጃቸውን የሰጡ ሲሆን ይህንንም የወያኔው ቴሌቭዥን ጣቢያ እማኝነቱን ሰቷል:: http://andargachewtsige.com/?p=383 ) አብራሪዎቹ ይዘውት የሄዱትን ሄሊኮፕተር እንዲመለስለት ወያኔ የሱዳን ዲፕሎማቶችን የላከ ሲሆን ሻእቢያ የማይመልስ ከሆነ የወያኔ መከላከያ ሰራዊት ከባድ አጸፋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አንድ ለስርአቱ ቅርብ የሆነ ድህረገጽ ጽፏል::

በሃገር ውስጥ እና በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንደ ፖለቲካ ድል ሲቆጥሩት አንዳንዶቹ ወያኔ የሻእቢያን አየር ሃይል በሰው ሃይል እየገነባ ሊሆን ይችላል ከጀርባ ሌላ ደባዎች በወያኔ እና ሻእቢያ ሊሰራ ይችላል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አልጠፉም::የወያኔ መክላከያ ሰራዊት አጸፋዊ እርምጃ ይወስዳል የሚል ስጋት ቢያይልም;ሃገር ወዳዶች ግን ምንም እርምጃ አይወስድም የፍርሃት ዛቻ ነው ሲሉ ተደምጠዋል::

ከመከላከያ ሰራዊት እንዲባረሩ የታሰቡ ከፍተኛ ባለማእረግ መኮንኖች ለስርአቱ ደህንነት ሲባል በቦታቸው እንዲቆዩ መደረጉ ታወቀ::

ክምርጫ መረጋጋት በኋላ በርካታ መኮንኖች ሊባረሩ ይችላሉ::
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

በከፍተኛ የመከላከያ ሰራዊት አመራር ውስጥ በከፍተኛ ሃላፊነት ሲሰራ የነበረው ሌተናል ጄነራል አበባው ታደሰ ባለፈው አመት ከቦታው መባረሩ ተከትሎ መባረር አለባቸው ተብለው ውስጥ ለውስጥ የተጨረሰላቸው በርካታ ከፍተኛ ባለማእረግ መኮንኖች ቢኖሩም፤ ከኋላ ሊነሳ የሚችለውን ችግር ግምት ውስጥ በማስገባት በተደረገው ግምገማ ላይ በማስጠንቀቅያ ብቻ እንዲታለፉ መደረጉን ታውቋል::

መባረር አለባቸው ተብለው ከተቀመጡት ከፍተኛ መኮነኖች አብዛኛዎቹ የሌተናል ኮረኔል ማእረግ ያላቸው እንደሆኑ የገለፀው መረጃው የጄኔራል አበባው ተከታዮች ስለሆኑና እንቅፋት ስለሚፈጥሩብን ተብለው እንዲባረሩ የተወሰነባቸው ቢሆንም፤ በመጪው ምርጫ ታሳቢ በማድረግ በህዝቡ መሃል ገብተው ኢህአዴግን ለመጣል ሊያነሳሱ ስለሚችሉ ግምገማ በማድረግ በማሰጠንቀቂያ እንዲታለፉ መደረጋቸውን መረጃዎች አምልክተዋል::መረጃዉም አያይዞ እንደጠቀሰው ክምርጫ መረጋጋት በኋላ በርካታ መኮንኖች ሊባረሩ ይችላሉ::

Image

በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ የሚደርሰዉን በድልና ጭቆናን በመቃወምና የኢትዮጵያን ወቅታዊ ጉዳዮችአስመልክቶ በዋሽግተን ዲሲ የሚገኘዉ ፈርስት ሒጅራህ ፋዉዴሽን የ አቋም መግለጫ አወጣ
ባለስድስት ነጥብ የሆነዉ የ አቋም መግለጫ የ ኢትዮጵያን ወቅታዊ ጉዳዮች ያጠቃለለ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ መንግስት በዜጎቹ ላይ የሚያደርሰዉን በደልና ጭቆና ለመታደግ ፈርስት ሒጅራህ ፋዉዴሽን አገራዊ ሐላፊነቱን ለመወጣት የሚጠበቅበትን ሁሉ እደሚያደርግ የ አመራር አካላቱ ለ ቢቢኤን ገልጸዋል። የአቋም መግለጫዉም እንደሚከተለዉ ይነበባል፦

• ሆን ተብሎ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ መንግስት ሲፈፅም የቆየዉን ኢሰብአዊ ድርጊት ባዲስና በከፋ መልኩ የጀመረዉን እርምጃ አጥብቀን እናወግዛለን

• ሙስሊም እህቶቻችንን የእምነት ነፃነት በመንፈግ ባአዲስ አበባ ዩኒፈርሲቲና በሌሎች የትምህርት እንዲሁም በመንግስት መስሪያ ቤቶች ሂጃባቸዉን እንዲያወልቁ የማስገደዱ ጉዳይ ሙስሊም ሴቶችን ከእምነታቸዉና ከትምህር እንዲሁም ከእምነታቸዉና ሰርተዉ ከመኖር ምረጡ እየተባሉ የሚደረግባቸዉን ተፅእኖን አጥብቀን እናወግዛለን

• በግፍ ታስረዉ ባሉት የሙስሊም መሪዎች ቤተሰቦች ሂጃባችሁን ካላወለቃችሁ ገብታችሁ ወዳጆቻችሁንን መጠየቅም ሆነ ምግብ ማቅረብ አትችሉም ተብለዉ የሚደርስባቸዉን መጉላላት በጥብቅ የምናወግዝ መሆናችንንም እንገልፃለን

• እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስቴር ሃይለማርያም ደሳለኝ ካንድ ጠቅላይ ሚንስቴር በማይጠበቅ አፀያፊ አነጋገር ጨዋዉንና ታታሪ ሰራተኛዉን የስልጤን ብሄረ ሰብ መዝለፋቸዉን አጥብቀን እንቃወማለን

• በቪዎች የሚቆጠሩትን ካገርና ከወገን ተለይተዉ ቤተሰቦቻቸዉንና ዘመዶቻቸዉን ለመርዳት የሚደርስባቸዉን ያካልና የመንፈስ ተፅእኖን በመቇቇም ለሚያደርጉት መስዋእትነት መመስገንናና መደነቅ ሲገባቸዉ ጠቅላይ ሚኒስተር ሃይለማርያም ባልተገራ አንደበታቸዉ እህቶቻችንን ገረዶች ብለዉ አንቇሸዉ መጥራታቸዉ እጅጉን አስከፍቶናል። የኢትዯዽያ ህዝብንም ይቅርታ ይጠይቁ ዘንድ እናሳስባለን።

• በተጨማሪም በቅርቡ ሰማያዊ ፓርቲ በጠራዉ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ሰልፈኞች ላይና እንዲሁም ባህር ዳር ላይ ሰላማዊ ሰልፍ የወጣዉ ክርስቲያን ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመዉን ኢሰብአዊ መንግስታዊ እርምጃ አጥብቀን እናወግዛለን

“ፈርስት ሂጅራ ፋዉንዴሽን የኢትዯዽያ መንግስት ከቀን ወደቀን የህዝቡን ሰብአዊ መብት እየጨፈለቀ መቀጠሉን አጥብቀን እንደሚያወግዝና ሌላዉም የሰዉ መብት ያገባኛል የሚል ስብእና ያለዉ ሰዉ ያወግዝ ዘንድ ጥሪዉን ያቀርባል” በሚል የጥሪ መልክት የ አቋም መግለጫዉ ተቋጭቷል። የፈርስት ሒጅራህ የአመራር አካላት መጠነ ሰፊ የሆነዉን ጭቆናና በደል ለመታደግ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ እንደሚሰሩ በመግለጽ በቀጣይነትም የሚያከናዉኗቸዉ የተቃዉሞ መርሃ ግብሮች እንደሚኖሩ ለቢቢኤን ገልጸዋል።

ካድሬዎቹ በባህር ዳር የተደረገውን ግድያ በንጹሃን ዜጎች ላይ የተፈጸመ ነው ሲሉ ተናግረዋል::
Minilik Salsawi – ባለፈው አርብ በባህር ዳር ሰላማዊ የሆነ ጥያቄ ይዘው አደባባይ በወጡት ንጹሃን ዜጎች ዙሪያ እና በመጭው ምርጫ ዙሪያ በአዲስ አበባ ብአዴን ካድሬዎቹን በመሰብሰብ ያደረገው ውይይት ክለመስማማት መበተኑን ለምንሊክ ሳልሳዊ የውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል::

እንደ ምንጮቹ ዘገባ ከሆነ ካድሬዎቹ ሕዝብን ማሳመን የማንችልበት ደረጃ ላይ ደርሰናል::ንጹሃን በአደባባይ መግደል የፖለቲካ ትርፉ ምንድነው የሚሉ እና በባህር ዳር የተደረገው ድርጊት በመጭው ምርጫ ላይ ከባድ ተጽእኖ ያጠላበታል ሲሉ አስተያየታቸን እና ጥያቄዎቻቸውን ሰንዝረዋል::ይህንን ድርጊት ፖሊሶቹ እንዲፈጽሙ ለምን ከፌዴራሉ ትእዛዝ መቀበል አስፈለገ? የክልሉ መንግስት የተደረገውን ሰልፍ በሰላም ለመበተን ያደረገው ጥረት ምንድነው ማብራሪያ እንፈልጋለን ሲሉ ካድሬዎቹ ያነሱትን ጥያቄ ተከትሎ ለውይይት የተጠራው ስብሰባ ወደ ጫጫታ ተለውጧል::

ካድሬዎቹ እንደሚሉት ማንኛውንም ጥያቄ በሃይል እየደፈጠጥን በምርጫው ወቅት ስንሸነፍ ሽንፈታችንን ተከትሎ በህዝብ ላይ ላለመተኮሳችን ማረጋገጫው ምንድነው ይህ ከባድ አደጋ ስለሆነ ባህር ዳር ላይ ለተፈጸመው ግድያ እና ድብደባ የክልሉ መንግስት እና መሪ ድርጅቱ ኢሕአዴግ ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው::ሌሎች አስፈላጊውን ሮሮ ሳያሰሙ ለጉዳተኞች ካሳ ሊከፈል ይገባል በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል::
የካድሬዎቹ ውይይት ከመጭው ምርጫ ላይ ያላቸውን ስጋት እና በህዝብ ላይ ይደርሳል ያሉትን ጥፋት በመናገር ያላቸውን ስጋት የገለጹ ሲሆን እንደ አባልነታቸው ደህንነታቸው ላይ ያለውን ጉዳይ በተመለከተም ጥያቄ አንስተዋል:: ለ 6 ሰአታት ያህል የዘለቀው ስብሰባ በስተመጨረሻ በምክክር ተጨማሪ ስብሰባዎች ይኖሩናል በሚል ካለመስማማት በጫጫታ መበተኑን ምንጮቹ ለምንሊክሳልሳዊ ገልጸዋል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

“ ቅ/ ሲኖዶሱ በአድባራት ሓላፊዎች ላይ ያሳለፈው ሕገመንግሥቱን የሚፃረር ነው ” /ፓትርያርኩ/
Image

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ ‹‹የቤተ ክርስቲያን አባቶችና ቤተ ክርስቲያን ዕውቅና በሰጠችው ማኅበር ላይ ተገቢ ያልኾነ ቃል ተናግረዋል›› ባላቸው አንዳንድ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አድባራት አስተዳዳሪዎች ላይ ያሳለፈው ውሳኔ አፈጻጸም ‹‹ሕገ መንግሥቱንና ሰብአዊ መብትን የሚፃረር ነው›› በሚል ፓትርያርኩ ማገዳቸው ተገለጸ፡፡
ፓትርያርኩ ባለፈው ኅዳር 30 ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በጻፉት ደብዳቤ ‹‹አፈጻጸሙ እንዲቆይ›› በማለት ያገዱት የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ፣ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና በጠቅላይ ቤተ ክህነት በተካሔዱ ጉባኤዎች÷ ‹‹ተገቢ ያልኾነ ቃል ተናግረዋል፤ ይህም አነጋገር ጉባኤውን ቅር አሰኝቷል፤›› ያላቸው የአድባራት አስተዳዳሪዎች፤ቀኖናዊ ምክርና ተግሣጽ እንዲሰጣቸው በአንድ ድምፅ ተስማምቶ ያሳለፈው እንደነበር ተጠቅሷል፡፡
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፣ በመንበረ ፓትርያርክና በጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌል አዳራሾች በተካሔዱት ስብሰባዎች የቤተ ክርስቲያኒቱን መልካም አስተዳደርና ወቅታዊ ችግሮች የተመለከቱ የጉባኤተኞች አስተያየቶችና ሐሳቦች መቅረባቸውን በደብዳቤያቸው ያስታወሱት ፓትርያርኩ፤ ተሰብሳቢዎቹ ሐሳባቸውንና አስተያየታቸውን በግልጽ መናገራቸውና አሉ የተባሉ ችግሮች መፍትሔ እንዲያገኙ መጠየቃቸው ‹‹በዓለም አቀፍ ደረጃም ኾነ በሀገራችን ለሕዝብ የተፈቀደ ዴሞክራሲያዊ መብት መኾኑ አያጠያይቅም›› ብለዋል፡፡ ሐሳባቸውንና አስተያየታቸውን በግልጽ ያቀረቡ ሰዎችን መገሠጽና መውቀስም ሕገ መንግሥቱን እንደሚፃረር ጠቁመዋል፡፡
ጉባኤዎቹ በቤተ ክርስቲያን ጠሪነት የተካሔዱ እንደነበሩና ተሰብሳቢዎቹም የቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት፣ አገልጋዮችና ሠራተኞች መኾናቸውን ፓትርያርኩ ጠቅሰው÷ የጎደለው እንዲሟላ የጠመመው እንዲቃና ያላቸውን አስተያየት በማቅረባቸው ተግሣጽና ማስጠንቀቂያ እንዲሰጣቸው ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳለፈው ውሳኔ ‹‹የስብሰባ ነፃነትንና መብትን ነፍጎ ሐቁ እንዳይነገር›› የሚከለክልና ውጤቱም ‹‹ጊዜ ያለፈበትን አፈና በማንገሥ ችግሮች ተባብሰው እንዲቀጥሉ የሚያደርግ ነው›› ብለዋል፡፡ “በውይይቱ ወቅት ‹‹የዳኅፀ ልሳን ወለምታ›› አጋጥሞም ከኾነ በወቅቱ ማብራሪያና ማስተካከያ ይሰጥበታል እንጂ እንደ ከባድ ጥፋት ተቆጥሮ ሰዎች ሊገሠጹበትና ሊወቀሱበት አይገባም፤ ሕግም አይፈቅድም፡፡” ሲሉ ገልጸዋል – በደብዳቤያቸው፡፡
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ‹‹ተገቢ ያልኾነ ቃል ተናግረዋል›› ያላቸው አንዳንድ የአድባራት አስተዳዳሪዎች በጠቅላይ ቤተ ክህነት በኩል ቀርበው ቀኖናዊ ምክርና ተግሣጽ እንዲሰጣቸው ያሳለፈው ውሳኔ ‹‹ሕግንና ሰብአዊ መብትን የሚፃረር›› ብቻ ሳይኾን ‹‹ትልቁን ጉባኤ በታሪክና በሕግ ዐዋቂዎች ዘንድ ግምት ውስጥ የሚጥለው እንዳይኾን አቡነ ማትያስ አስጠንቅቀው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶሱ ጉዳዩን እንደገና በጥልቀትና ከሕግ አንጻር ፈትሾ እንዲያጤነው በማለት አፈጻጸሙ እንዲቆይ አስታውቀዋል፡፡
በሕገ ቤተክርስትያን ት/ሲኖዶሱ በሙሉ ድምፅ ተስማምቶ ያሳለፈውን ውሳኔ ፓትርያርኩ የማገድ ሥልጣን እንደሌላቸው ያመለክታል፡፡ ሕገ መንግሥቱ ከተጠቀሰበት አግባብ አኳያም፣ “ቤተ ክርስቲያናችን በቂ ሕግጋት አሏት፤ እነዚህ ሕግጋት ማዕከሉ ተጠብቆ ሊሠራባቸው ይገባል፤” ሲልም ቅ/ሲኖዶሱ አሳስቧል፡፡
ባለፈው መስከረም መጨረሻ “የቤተ ክርስቲንን አስተዳደራዊ አስተሳሰብ ማበልጸግ” በሚል መርሕ በተካሔደው ስብሰባ አንዳንድ የአድባራት አስተዳዳሪዎች፤ ‹‹ፈጣሪ የለም ይላል፤ አሸባሪና አክራሪ ነው፤›› በማለት ቤተ ክርስቲያኗ ዕውቅና የሰጠችውን ማኅበረ ቅዱሳንን ከዓለም አቀፍ ጽንፈኞች ጋራ እያመሳሰሉ መወንጀላቸው ተገቢ እንዳልኾነና የማኅበሩ አገልግሎት ለቤተ ክርስቲያን አስፈላጊ እንደኾነ ቅዱስ ሲኖዶሱ አረጋግጧል፡፡
‹‹ቆራጣ ደብዳቤ ይበቃዋል፤ ከመንግሥት ጋራ በመተባበር እስከ ጫፍ አድርሱልን፤ በቶሎ ቁረጡት›› እያሉ መጠየቅ፤ ሊቃነ ጳጳሳቱንም “ከፈለጉ ቆባቸውን አስቀምጠው ወደዚያው ይግቡ” እያሉ መዝለፋቸውስ በምን መመዘኛ ነው ዴሞክራሲያዊና ሕገ መንግሥታዊ የሚኾነው በማለት የሚገልጹ የስብሰባው ተሳታፊዎች በበኩላቸው፤ ፓትርያርኩ የውሳኔውን አፈጻጸም ማገዳቸው፣ አድሏዊ እንደሚያደርጋቸውና በካህናቱና በምእመናኑ ዘንድ መንፈሳዊ አባትነታቸውንና ታማኝነታቸውን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባው እንደሚኾን ጠቁመዋል፡፡

ቃሊቲ እስር ቤት የሚገኙ እስረኞች ባልታወቀ ምክንያት ‹‹ከማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ታዘን ነው›› በሚሉ የፌደራል ፖሊሶች እቃቸው በድንገት እንደተበረበረና እንደተወሰደ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡

ዛሬ እሁድ ታህሳስ 12/2007 ዓ.ም ጠዋት ጀምሮ ቃሊቲ እስር ቤትና አካባቢው በበርካታ የፌደራል ፖሊሶች ተከቦ እንደነበር የገለጹት ምንጮቹ ባልታወቀ ምክንያት የሁሉም እስረኞች እቃ በድንገት የተበረበረ ሲሆን በተለይም ፖለቲካ ነክ ጽሁፎች የሰፈሩባቸው ማስታወሻዎችና ሰነዶች መወሰዳቸውን ከእስረኞቹን ጠይቀው እንደተረዱ ምንጮች ገልጸውልናል፡፡

ፖሊስ ባደረገው ብርበራም የታዋቂው ጋዜጠኛ እና የፖለቲካ ተንታኝ እስክንድር ነጋ ከ30 በላይ ገጽ የፖለቲካ ትንታኔ ጽሁፎች፣ እንዲሁም የአንዱ ዓለም አራጌ ማስታወሻዎች መወሰዳቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ፖሊስ ማስታወሻዎችንና ሌሎቹንም የእስረኞቹን ንብረቶች እያስፈረመ የወሰደ ሲሆን እስከ ቀኑ ስድስት ሰዓት ድረስ እስር ቤቱ አካባቢ በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት እንደነበሩ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች አክለው ገልጸዋል፡፡
Image

“የታዛቢዎችን ምርጫ ለማወክ ተንቀሳቅሳችኋል::” – ፖሊስ ===== Minilik Salsawi
ዛሬ በየቀበሌው የሚካሄደውን የታዛቢዎች ምርጫ ተከትሎ ወደ ሚኖሩበት ጉለሌ ክፍለከተማ ወረዳ 3 ያመሩት የሰማያዊ አባላቶቹ ኢየሩሳሌም ተስፋው እና እመቤት ግርማ የታዛቢዎችን ምርጫ ለማወክ ተንቀሳቅሳችኋል በሚል በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የምርጫ ታዛቢ መሆን የሚችሉት ገለልተኛየሆኑ እንጂ የኢህአዴግ አባላት የሆኑ አይደሉም በሚል ባነሱት ክርክር ምክንያት ለማወክ እየሞከራችሁ ነው በሚል ፖሊስ ሊይዛቸው ችሏል፡፡

Image

ሞክረው ( ሄኖክ የሺጥላ )

ትናንት ባህርዳር ላይ አማሮች ተገደሉ ፣ ከትናንት በስትያ አምቦ ላይ ኦሮሞዎች ፣ ከዛ በፊት ጋምቤላ ላይ ፣ ከዛ በፊት አርባ ጉጉ ላይ ፣ ከዛ በፊት በደኖ ላይ ፣ እያለ እያለ ይቀጥላል ። በዘር የከፋፈልነው ሬሳ ኢትዮጵያዊ መሆን ያቃተው ለምን እንደሆነ ባላውቅም አንተ አዛኝ ቅቤ አንጉዋች ግን ምን ታመጣለህ ። ግፋ ቢል ሁለት ገጽ የ ፒዲ -ኤፍ ( PDF ) መግለጫ ታወጣለህ ፣ ትንሽ ትዝታለህ ፣ ትንሽ ትሳደባለህ ፣ አይቀርም በቅርብ ምናምን ብለህ ተስፋ ትሰጣለህ ፣ ግድያው ይቀጥላል ።

ውስጥ ውስጡን የሸዋ አማራ ለኢትዮጵያ ጂው ነው ፣ ወይጦው ጅን ነው ፣ ጎጃሜው አድር ባይ ነው ፣ ጎንደሬው ሲፋቅ ትግሬ ነው ፣ መንዜው በጥርሱ እየሳቀ ገዳይ ነው ፣ ወዘተ ወዘተ ትላለህ ። ውጭ ውጩን የአማራ ታጋይ!!!
ኦሮሞውም ጋ እንዲህ ነው ፣ ወለጋ ኮለል ያለ የጠራ ኦሮሞነት መስፈሪያ ነው ፣ የሰላሌ ኦሮሞ አማራነት ያለቀቀው ኦሮሞ ነው ፣ የሸዋ ኦሮሞ ኦሮሞ አይደለም ፣ የባሌ ኦሮሞ ለ አረብነት ይቀርባል እና ወዘተ፣ ውስጥ ውስጡን ልብህን ያደነደነው ነገር ነው ። ዝለዚህ ከዚህ በሽታህ እስካልዳንክ ድረስ ግድያው ይቀጥላል ፣ አንተም መግለጫ እየሰጡ መኖሩን ትቀጥላለህ ።

ስልጤውም ጋ ፣ ሶዶ ጎርደናውም ጋ ፣ ሰባት ቤቱም ጋ ፣ ቅማንቱም ጋ ( ቅማንት የሚባል ነገር ካለ ) ፣ ይሄ በሽታ አለ ። ይሄን በሽታህን ፣ ይሄን የመከፋፈል ነቀርሳህን ሳትድን ፣ ከቁጭት ውጭ ምንም አታመጣም ። አንዳች ለውጥ በሀገርህ ምድር አይፈነጥቅም ።

እስኪ አምላክ ያሳይህ ትናንት በ ሰሜን ጎንደር ቅማንት እራሱዋን በራሱዋ ታስተዳድር ዘንድ አንዳንድ ሽር ጉዶች እየተደረጉ እንደሆነ ሰማን ፣ መቼም መስማት እምቢ አይባልም ፣ ከመሃል ጎንደር እስከ መተማ ጎንደር ልጆቿን ልትበላ ይኸው ሌላ ውርጅብኝ ሊወርድባት ነው ። አንተ ግን ይሄን ሁሉ የሚያረገው ከትግሬ ክፍለ ሀገር የመጣ ከይሲ ስርዓት ነው ማለት ልብህ ይፈራል ።ጠላቶችህን በስማቸው ለመጥራት ልብህ ይራራል ።

ሌላም ታሪክ ልንገርህ
ጅማ ላይ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሲያስቀድሱ የተገደሉትን ሰዎች አይተካል ፣ ታዲያ ማን ይመስልሃል ገዳዩ ? ኦሮሞዎች ? አይደለም ! አየህ ያንተ ችግር ይሄ ነው ወያኔ እንድታስብ የሚፈልገውን ነው የምታስበው ፣ ግድያውን የፈጸሙት ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ሊሆኑ ይችላሉ ፣ ድርጊቱን ያሴረው ግን አሁንም የትግሬ ወያኔ ነው ፣ ወንድም በወንድሙ ላይ እንዲነሳ ያደረገው ። ጅማማ እኮ ጂማ! የሰቃ ጨቆርሳ ሀገር! የጌራ ሀገር! የጉማ ሀገር! የጎማ ሀገር! የሊሙ ሂናሪያ ሀገር! አምስቱ የጊቤ መንግሥታት የለመለሙባት ምድር!!
ጅማ! የአባ ሚዛን ሀገር! የአባ ቆሮ ሀገር! የአባ ገንዳ ሀገር! የአባ ዱላ ሀገር! በኦሮሞ ምድር የዘመናዊ ቢሮክራሲ ጥንስስ የተጀመረባት ሰፈር!
ጅማ! የአቦል ሀገር! የበረካ ሀገር! የቃህዋ ጀባ ሀገር! ለስምንት መቶ ዓመታት ተወዳጅነቱ ሳይቀንስ የዘለቀውን “ቡና”ን ለዓለም ያበረከተች የሙሐባ መንበር!! ጅማ! የተሚማ ሀገር! የገሜቲ ሀገር! የአያንቱ ሀገር! የአስሊያ ሀገር! የበድሪያ ሀገር! የፈይሩዝ ሀገር! ውብ ልዕልታትና ወይዛዝርት የወጡባት ምድር!! ነች ይላታል ጸሐፊው ፣ ጅማ ይህንን አታደርግም ፣ ጅማ ላይ አታቂም ፣ አይንህን ወደ ሰሜን ፣ ልብህን ወደ ትግሬ ወያኔ አዙር !

ይገሉሃል አንተ ግን ባጉል ፍቅር ታጥረሃል ፣ ያጠፉሃል አንተ ግን የትግሬ ወያኔ አጥፊህ መሆኑን መናገር ትፈራለህ ፣ መነኩሴ በጥይት ሲመቱ አንተ ዘረኛ እንዳትባል ትፈራላህ ፣ ሀጻናት ሲገሉ አሁንም በስማቸው ለመጥራት ትፈራለህ ፣ ማን እንደሆኑ እያወቅህ ” እነ አከሌ ” ለማለት በጣም ትፈራለህ ፣ በልብህ ትታበያለህ ፣ በአንደበትህ ትስታለህ ፣ በልቦናህ ግን ከራስህ ጋ ትነጋገራለህ ። ጠላትህን በስሙ እስካልጠራኸው ድረስ አታሸንፍም ፣ ጠላትህን እስካላስገለልከው ድረስ በፍጹም ነጻ አትሆንም ። ገዳዮችህ ሩቅ አይደሉም፣ ብዙዎቹ ያንተ ጎረቤቶች ናቸው ፣ ካንተ ጋ እየበሉ ፣ ካንተው ጋ እየጠጡ የሚውሉት የትግሬ ወያኔዎች ናቸው ይሄን ሁሉ በደል እያደረሱ ያሉት ፣ ይሄንን አንተ አታውቅም ብዬ አላስብም ፣ እርግጥ በደንብ ታውቃለህ ግን እውቀትህ ከውስጥ የማይወጣ የጋን መብራት አይነት ሆነብኝ ፣ ጠላትህ ለመለየት አተኩረህ እየው ( ግንባሩን እየው አላልኩም ) ግንባሩ ፍንጭ ከሰጠህ ማየት መብትህ ነው ፣ ግን አተኩረህ ካየኸው ታውቀዋለህ ። እሱ አንተን ለማጥፋት አንዳች ይሉኝታ የለውም ታዲያ ያንተ የሉኝታ ከወዴት የመጣ ይሆን ። ነገርኩህ እኮ እነሱ ( የትግሬ ወያኔዎች ) ሊገሉህ ኢያሰቡም እንኩዋ ይወልዱልሃል ። ግማሹ ጦርነት ጠላትን ማወቅ ነው ይላሉ አንዳንድ አዋቂዎች ፣ ይህ ትልቅ እውነት ነው ፣ የተቀረው ግማሹ ደሞ ጦርነት መግጠም እንዳይመስልህ ፣ የተቀረው ራስን ማወቅ ነው !

ጠላትህን እስካለየህ ድረስ ጠላትህን አታሸንፈውም ! ይሄ የ ስደት ፖለቲካውን እርሳው ፣ ለአፈ ግም አፍንጫ ድፍን ያዝለታል ነው ፣ አንተ ግን ጠላትህን በስሙ ጥራው ። የትግሬ ወያኔ ጠላቴ ነው በል ፣ እሱን ማለት ስትጀምር ማሸነፍ ትጀምራለህ ። ሞክረው! ሞክረው ! ሞክረው !

በመግለጫ ነገር መወራወር የጀመሩት የተቃዋሚ ፓርቲእ አንድነት እና የወያኔው ምርጫ ቦርድ መላተም መጀመራቸውን ከዙሪያቸው የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ በዚህም መሰረት የኢሕአዴግ ተቋም የሆነው የምርጫ ቦርድ አንድነት እና መኢአድን ከ2007 ምርጫ ውጪ ለማድረግ ዳር ዳር እያል ነው ሲሉ አንድ የአንድነት ከፍተኛ አመራር ጽፈዋል:: ከፍተኛ አመራሩ በጽሁፋቸው እንዳሉት የኢህአዴግ ጎፈሬ ከማበጠር ውጪ ምንም ፋይዳ የሌለው “የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ” አንድነትንና በመኢአድን በምርጫው እንዳይወዳደሩ ለማድረግ ላይና ታች እያለ ይገኛል ያሉት አመራሩ እነዚህ ፓርቲዎች ባለፈው ነሐሴ ወር 2006 ዓ.ም. ውህደት ለመፈፀም ተስማመተው የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሰው የነበረ ቢሆንም፤ ውህደቱን የከለከለውና እንዲሰናከል ያደረገው ይሄው ምርጫ ቦርድ ተብዬው የመሸጦ ተቋም ነበር። በማለት በጽሁፋቸው አስፍረዋል::

አሁን ከየትኛውም ጊዜ በላይ ግልፅ እየሆነ ያለው ነገር የዚህ ምርጫ ቦርድ ዋና ዓላማ ፓርቲዎች ተጠናክረው እንዳይወጡ መከላከልና የኢህአዴግ ወንበር መጠበቅ እንደሆነ ከዚህ በላይ ማረጋገጫ የለም።ያሉት አመራሩ አያይዘውም ከእንግዲህ ይለይልናል ሲሉ አስጠንቅቀዋል::

ህዝባዊ እምቢተኝነቱ ከአሁኑ እንዲጀምር እድል ተፈጥሯል ማለት ነው። አሁን ነው ወገብን ጠበቅ አድርጎ አመራር ለመስጠትና ለመታሰር ዝግጁ መሆን የሚያስፈልገው። እኛ የምንችለው ሁሉ አድርገናል ከዚህ በኋላ የፈለገው ቢሆን የሚፀፅተን ነገር አይኖርም።ሲሉ ህዝቡ ለህዝባዊ እምቢተኝነት እንዲዘጋጅ እድሉን እንዲጠቀምበት መሪ በመሆን የሚፈለግባቸውን ድርሻ ለመወጣት ፓርቲያቸው መዘጋጀቱን አሳውቀዋል::

የአንድነት አመራሩ እንዳሉት ፓርቲዎቹ በምርጫው እንሳተፋለን ሲሉ፤ ምን አስበው ነው ተብሎ የለም አትሳተፉም የሚባል ከሆነ ይህን መብታቸውን ለማስጠበቅ ተባብረው ህዝባዊ እምቢተኝነቱን ማካሄድ ግድ ይላቸዋል ማለት ነው። መቼም ዘንድሮ በኢህአዴግ ቤት ማሰቢያው ጨርሶ እንደጠፋ ከዚህ በላይ ማረጋገጫ የለም፤ እዚያ ቤት ግን የተፈጠረው ነገር ምን ይሆን? ሲሉ ጽሁፋቸውን ድል የህዝብ መሆኑን በመግለጽ አጠቃለዋል::
Image

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የ2ዐዐ7 ዓ.ም አገራዊ ምርጫ እንደሚሳተፍና ለዚህም መተማመኛው ሕዝቡ መሆኑን ገልፀ ‹‹ተደራጅ 2007 ለለውጥ›› በሚል መፈክር አንግቦ አገራዊና ሕዝባዊ ኃላፊነቱን ለመወጣትና ኢህአዴግን በቃህ ለማለት ሌት፣ ከቀን በንቃትና በትጋት እየሠራ ይገኛል፡፡

በአሁኑ ወቅት ነፃ ሚዲያ በታፈነበትና በተዘጋበት አንድነት የራሱን የማተሚያ ማሽን ገዝቶ በየጊዜው ሆን ተብሎ በሚመስል መልኩ በሚጠፋው የኤሌክትሪክ ችግርን ለማሸነፍ የራሱን ከፍተኛ ኃይል ያለው ጀነሬተር በመግዛት በሣምንት የራሱን ጋዜጦችን እያተመ እያንዲያሰራጭ ተገዷል፡፡ ምሁራን፣ ወጣቶች፣ ጋዜጠኞችና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለወሳኑ የ2ዐዐ7 ምርጫ ትግል እየተቀላቀሉት ይገኛሉ። አንድነት በአሁኑ ሰዓት ከመቼውም ጊዜ በላይ ትግሉን በአግባቡ ለመምራትና ለውጥ ለማምጣት በተሻለ ቆመና ላይ ነው ያለው።

በምርጫ ቦርድ በአንድት ፓርቲ መተዳደሪያ ደንብ ሆነ በገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ መተዳደሪያ ደንብ ውስጥ የሌለውን የጠቅላላ ጉባኤ አባላትና የምላተ-ጉባኤ ቁጥር በተሻሻለው ደንባችን ውስጥ እንድናካትት የተወሰነብንን ፈርድ ገምድል ድርጊት ሕገ-ወጥ መሆኑን ብናውቀውም ጠቅላላ ጉባኤ መጠራትን እንደ ጉዳት ሳይሆን አንደ ልዩ እድል በመቁጠር፣ 32ዐ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት በመጥራት የምርጫ ቦርድ ተወካይ በተገኘበት የተሳካና አንፀባራቂ ጠቅላላ ጉባኤ አካሄደናል፡፡ የጠቅላላ ጉባኤውንም ሰነድ ታህሣሥ 1ዐ ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም ለምርጫ ቦርድ ገቢ ተደርጓል፡፡

ሁሉ እንደሚገነዘበው በአሁኑ ሰዓት ሕዝቡ በኑሮ ውድነትና በሥራ እጦት ከመሰቃየቱም በላይ ሙስና ሰፍኗል፤ መልካም አስተዳደር የሕግ የበላይነት ከቶውንም ጠፍቷል፡፡ የሕዝብ የነፃነትና የዴሞክራሲ ጥያቄ ገዝፎና አፍጥጦ እየመጣ ነው፡፡ በመሆኑም ኢህአዴግ በፍርሃትና በጭንቀት እየራደ ነው፡፡ ምረጡኝ ብሎ ሕዝብ ፊት ለመቅረብ የሚያስችለው የፖለቲካና የሞራል ኃይል ስለሌለው ውሸት፣ ማስፈራራት ማሰር መግደል ማሸነፊያ መሣሪያዎች እንዳልሆኑትም በግልጽና በትክክል ተደራጅቷል፡፡ አሁን የቀረው ማሸነፊያው መንገድ አንድነት ፓርቲን በመዝጋት ነው የሚል ድምዳሜ ላይ በመድረሱ ጥንቱንም የአንድ ሣንቲም ሁለት ገጽታዎች የሆነውን ወኪሉን በመጠቀም በአንድነት ላይ ዘመቻ ከፍቷል፡፡

ታህሣሥ 1ዐ ቀን 2ዐዐ7 ዓም በምርጫ ቦርድ ከፍተኛ አመራር የተሰጠው በቅጥፈትና በውሸት የተሞላው መግለጫም የሚያሳየውና የሚመሰክረው ይህንኑ ነው፡፡ ነገር ግን እውነቱን በአጭሩ እንደሚከተለው እናስቀምጣለን፡፡

አንድነት ፓርቲ ታህሣሥ 19 እና 2ዐ ቀን 2ዐዐ6 ዓም ያካሄደውን የጠቅላላ ጉባኤ ሰነድ ለምርጫ ቦርድ ካስገባ በኋላ ምርጫ ቦርድ ሐምሌ 2ዐ ቀን 2ዐዐ6 ዓም በተፃፈ ደብዳቤ በዘጠኝ ነጥቦች ላይ ማብራሪያ እንድንሰጥ ጠይቄን መልስ ሰጠን፤ በመቀጠልም ጥቅምት 2ዐ ቀን 2ዐዐ7 ዓም በተፃፈ ደብዳቤ ጥያቄ ከዘጠኝ ወደ ሦስት አውርዶ ላከልን ለዚህም አንድነት መልስ ሰጠ፡፡ ቀጥሎም ቦርዱ ህዳር 1ዐ ቀን 2ዐዐ7 በተፃፈ ደብዳቤ ጥያቄውን ወደ አንድ አወረደው እንዲያውም በመጨረሻ ህዳር 19 ቀን 2ዐዐ7 ዓም በተፃፈ ደብዳቤ፡፡ ‹‹ፓርቲው በሰጠው ምላሽ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ብዛት 32ዐ እንደሆነ አሳውቋል፡፡ ይሁን እንዷ በተሻሻለው መተዳደሪያ ደንብ ውስጥ አካቶ ያላቀረበ በመሆኑ ይህንኑ አሟልታችሁ እንድታቀርቡ በአክብሮት እናሳውቃለን›› የሚል ነው፡፡ እኛም ጠቅላላ ጉባኤ ጠርተን ይህንኑ ጥያቄ እንዲሟላ ከማድረጋችንም ባሻገር በሕገ-ደንባችን መሠረት በብሔራዊ ም/ቤት ተመርጠው የነበሩት የፓርቲውን ፕሬዚደንት ሹመት በጠቅላላው ጉባኤ አፀድቀናል፡፡ እንጂ አይነቱን በሕገ-ደንቡና በሥነ-ሥርዓት ለተከናወኑ ጉዳዮች ያልተገባና የተሳሳተ መግለጫ መስጠት በጣም አሳኝ ነው፡፡ በተለይም የሕዝብ ታዛቢዎች ታህሣሥ 12 ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም እንደሚመረጡ እየታወቀ ይህን ዓይነት መግለጫ መስጠት ሕዝቡ በጥንቃቄና በተደራጀ ምልኩ ትክክለኛነትና ሀቀኞች የሆኑ ታዛቢዎችን እንዳይመርጥ ለማሰናከል የታቀደ ይመስላል፡፡ በመሆኑም ዛሬም ሆነ ነገ አንድነት ፓርቲ ከሕዝብ ጋር ሆኖ ትግሉን አጠንክሮ ይቀጥላል አባላትም ሆነ ሕዝቡ ከፓርቲያችን ጎን ተሰልፎ ትግሉን እንዲያጧጡፈው ከአክብሮት ጋር እንጠይቃለን፡፡
ድል የህዝብ ነው!

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
ታህሣሥ 11 ቀን 2ዐዐ7 ዓም
አዲስ አበባ

Image

ህ.ወ.ሐ.ት 40ኛ ዓመት በዓሉ ለማክበር እያደርገው ያለው አከባበር ከመግለጼ በፊት የህ.ወ.ሐ.ት መሪዎች ለምን የትጥቅ ትግል መረጡ የሚለውን ትንሽ ለአንባብያን መረጃ ሰጥቼ ልለፍ፡፡ ህ.ወ.ሐ.ት የመሰረቱ ሰዎችና የትግራይ ወጣቶች ነፍጥ አንስተው ደርግን በጦርነት አስወግደው የደርግን ስርዓት ለመለወጥ የተነሱበት ዋናው ምክንያት ደርግ ዘውዳዊውን ስርዓት አሰወግዶ በትረ-ሥልጣኑ የጨበጠው ራሱ ታግሎ ያመጣው ለውጥ ሳይሆን የኢትዮጵያ ሙሁራኖች፣ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች፣ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ አረሶ አደሮች፣ ወዝ አደሮች፣ የመንግስት ሰራተኞች ወ.ዘ.ተ በተደራጀና ባልተደራጀ መንገድ ያነሱት ዲሞክራሲያዊ ጥያቄ ዘወዳዊው ስርዓት ሊመልሰው ሰላልቻለ የበሰበሰው መዋቀሩ በመፍረክረኩ ደርግን ያን አጋጣሚ ተጠቅሞ ስልጣኑን ሊጨብጥ አስቻለዉ፡፡

እነዛ ዲሞክራሲያዊ ጥያቄ አንስተው ፤ዘውዳዊው ስርዓት ያፍረከረኩ ወገኖች ደርግ በግብታውነት በትረ ስልጣኑን በመያዙና እነዚ የህዝቦች ዲሞክራሳያዊ ጥያቄዎች ደርግ በሚድያና በዲኘሎማሲ በመደናገር የህዝባችን ጥያቄ በመቀልበስ ፀረ-ዲሞክራሲያዊ የሆኑ አምባገነን አዋጆች በማወጅ ህዝባዊ ማዕበሉን በማፈን ሁሉም ዓይነት ጥያቄዎች ገና በጥዋቱ ማፈን ጀመረ፡፡

ደርግ የአምባገነንነቱና ፋሽስታውነቱም መግለጫ የዘውዳዊው ስርዓት ከ60 በላይ ሚንስትሮች ፡ ጀኔራሎች በመሰበሰብ በጥይት ደብድቦ ገደላቸው ፤ የህዝቦች ሰለማዊ ትግል ደርግ በዜጎች ደም ታጥቦ ትግሉን አኮላሸው፡፡ በዚህም ምክንያት በኢትዮጵያ ህዝባዊ መንግሥት ሊመሰረት አልተቻለም፡፡ መድበለ-ፓርቲ ፡ ዩንር፣ሁሉም ዓይነት ዲሞክራሲያዊ መብቶች፣ የሃይማኖት ነፃነት፣ ፍትህና የህግ የበላይነት ይከበር፡ የሚሉ ጥያቄዎች መልሳቸው ልክ አሁን የህ.ወ.ሐ.ት/ኢህአዴግ መንግሥት እያደርገው ያለው ዓይነት እምቢ ላለሰው፤ እሰረው ፡ ግረፈው፡ ግደለው፡ እንደሚለው ያለው ደርግም እምቢ ላለሰው ጥይት አጉርሰው ብሎ አወጀ የህዝቦች ጥያቄዎች አፈናቸው ፡፡
በዛን ግዜ የኢ/ያ ህዝቦች በተለይ በንቃተ ህሊና ትንሽ መጥቀው የነበሩ ሙሁራንና ሰራተኛች በደርግ ስርዓት ሰለማዊ ትግል ለማድረግ አይቻልም በማለት በረሃ ወጥተው የትጥቅ ትግል ለማከላሄድ ወሰኑ፡፡ አንዳ አንዶቹም ደርግ በትጥቅ ትግል ሳይሆን በከተማ ነውጥ ነው ማስወገድ የሚቻለው በማለት የነውጥ ስትራቴጂ መርጠው መንቀሳቀስ ጀምረው ነበር፡፡ በሌላ በኩል ከደርጎን በመሆን በጎ በጎውን መንገድ እንዲከተል መንገድ በማሳየት ዲሞክራሲያዊ መንግሥት ማድረግ ይቻላል አሉ፡፡ ይህ የዘመኑ ሙሁር የየራሱ የተለያየ ፍልስፍና በመያዝ በየፊናው በመዝመት በአንድነት ታግሎ ዲሞክራሲያዊና ህዝባዊ መንግሥት የመመስረት የህዝቡን ተስፋ አጨለመበት፡፡ በአንፃሩ የዚያን ጊዜ ሙሁራን በየፊናቸው ተደራጅተው በሃገራዊና ብሄራዊ ጥያቄ ሥር ብዙ ፀረ-ደርግ የፖለቲካ ኃይሎች ተመሰረቱ፡፡
ከነዚህ ውስጥ የትጥቅ ትግል ስትራቴጂ ከመረጡት ውስጥ አንዱ ህ.ወ.ሐ.ት ነበር፡፡ በህቡዕና በግልፅ ተደራጅቶ በየካቲት 11/06/1967ዓ.ም በ11 ሰዎች በረሃ ደደቢት ወጥቶ የጥቅ ትግል ጀመረ ፡፡ እኖሆ ህወሐት ዘንድሮ 40ኛ ዓመት የልደት በዓሉ ለማክበር ሸርጉድ እያለ ይገኛል፡፡
ህ.ወ.ሐ.ት ዩዞዋቸው የተነሳ ዓላማዎች፡-
አባገነኑን ፋሽስታዊ ደርግን በማስወገድ ህዝባዊ መንግሥት መመስረት፡
የመድብለ-ፓርቲ ስርዓት እንዲኖርና በነፃ የመደራጀት፣ ነፃ የምርጫ ውድድር መኖር እንዳለበት፡፡
የብሄራዊ መብት የራስን ዕድል በራስ መወሰን ዕድል እንዲይኖር ፡፡ የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ መሆኑ፡፡
ብሄራዊ ትግል እንደ የሰልት ትግል ተጠቅሞ መደባዊ ትግሉን እዳር በማድረስ ለኢትዮጵያ አንድነትና እኩልነት መታገል ፡፡
የገጠርና የከተማ መሬት የህዝብ መሆን እንዳለበት፡፡
በፖለቲካም ማርክሰሌኒናዊና ማአዘዲንጋዊ ስነ ሃሰሳብ መመሪያው እንደሆነ፡፡
የአብዮቱ ጠላተች፤ ፉሽስታዊ ደርግ፣ መስፍናዊ ስርዓት፣ ሃብታም ገበሬ ፡ ሃገራዊ ባለ ሃብት፣ ከፍተኛ ሙሁርና ኢንፔርያሊዝም እንደሆኑ ፡፡

ከላይ የተጠቀሰው የኃይል አሰላለፍ በፅሁፍ ተሰንዶ በማኒፈስቶ ደረጃ የተቀመጠ አልነበረም፡፡ እንዲሁ በሰመበለው ነበር የሚነገረው ፡፡ እላይ የተዘርዘረው አÌም የህ.ወ.ሐ.ት አÌም ሆኖ አልቀጠለም ፡፡

በ1968 ዓ.ም አጋማሽ አከባቢ ግን አንድ አስደንጋጭ አÌም ተያዘ፡ ይህ አÌም ታጋዮች ተዋይተውበት ወይም በድርጅቱ በጉባኤ ቀርቦ የፀደቀ አልነበረም፡፡አማራሩ አስቦበት አትለው በግብታውነት አትለው የመጣ አቋም ነበር፡፡ ለታጋዩ፣ ለኢ/ያ ህዝብና ለሌሎች ፖለቲካዊ ድርጅቶች ግን ድንገት ነበር፡፡

ትግላችን ከአማራ ቀኝ ገዥዎች ነፃ ለመውጣት (ነፃ ሪፓብሊክ ትግራይ ለመመስረት) ነው ብለው በትግርኛ፡ በአማርኛ፡ በእንግሊዘኛ የተፃፈ፡ በነ አቶ ስዩም መስፍን ፡መለስ ዜናዊ ፡ ስብሃት ነጋ፡፡ በሙሉጌታ ሓጎስና በሌሎችም የተጻፈ ሥዩም መስፍን ሱዳን ሄደ በመጽሐፍ መልክ አሳትሞ ወደ አገር ገብቶ ለተጋዮችና ለከተማ ደጋፊዎች ለውጭ አገርም እንዲሰራጭ ተደረገ በቃ የህ.ወ.ሐ.ት መሪዎች ጠባብነት ፀሐይ ላይ ወጣ ፡፡
የዚሁ ማኒፌስቶ በቅድምያ የተቃወመ ኢ.ህ.ኣ.ፖ ነበር፡ ቀጥሎ ትንሽ ቀለም በቆጠሩ ታጋዮችና በከተማ ደጋፊዎች ትልቅ ተቃውሞ አገጠመው ፡፡ ጥያቄ ላነሱ ታጋዮች በተለይ ከ1969 ዓ.ም እስከ 1970 ዓ.ም እርምጃ ተወሰደባቸው፡፡ ብዙ ታጋዮች እየሸሹ ከተማ ገቡ፡፡ ዕድል ያገጠማቸውም ወደ ሱዳን ሸሹ፡፡ትላትና በኢ/ያ የመደብለ-ፓርቲ መኖር አለበት የሚል አÌም የነበራቸው የህ.ወ.ሐ.ት መሪዎች በሰሜን ኢ/ያ ለነበሩ ፀረ-ደርግ ኃይሎች መጀመርያ ግንባር ገድሊ ሓርነት ትግራይን (ግ.ገ.ሓ.ት)መቱ፡፡ ቀጥለው ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ ጣራናፊት ኮሚቴ አጠፉ፡፡በመቀጠልም የኢ/ያ ዲሞክራሲያዊ ህብረት(ኢ.ዲ.ህ እና ኢ.ህ.ኣ.ፖ) ግዝፎች ኃይሎች ተዋጡ፡ በድርጅቱ ውስጥም ጦርነቱንና ጠባብነቱንና የተቃወሙ፣የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ አይደለም ብለዉ የተማጎቱ ጅግኖቹም እንደዚህ ተዋጡ፡፡ በቃ የህ.ወ.ሐ.ት መሪዎች ፀረ-መደብለ-ፓርቲና ፀረ-ዲሞክራሲ መሆናቸው ተጋለጠ፡፡ ግን ደግም ፋሽስታዊ ደርግ በትግራይ ህዝብ ጠላትና ወዳጅ ሳይለይ በማከናይዘድ፣ በእግረኛ ወታደር፣ በአየር በጋዝና በናፖልም መርዝ በመጠፍጨፉ ህዝቡ የሩቅ ጀብ ከሚበላኝ የራሴን ጅብ ይብላይኝ በሚል ህዝቡ ዕድሜ ፡ፆታና ሃይማኖት በማይለይ ከህ.ወ.ሐ.ት ጎን ቆሞ ልጆቹ ወደ ትጥቅ ትግሉ እንዲዘመቱ፣ ገንዘቡና በሁሉም ዓይነት ሀብቱ ህ.ወ.ሐ.ትን ለመደገፍ ተነሳ ፡፡
የትግራይ ህዝብ ግን ምንም እንኳን ከደርግ ህ.ወ.ሐ.ት ቢወድም ፡ ህ.ወ.ሐ.ት በጣባብነት አÌሙ የኤርትራን የቅኝ ግዛት ጥያቄ መደገፉ የሻአብያ ካድሬ ሆኖ መንቀሳቀሱ፣ይባስ ብሎ ሻአብያን ከደርግና ከጀብሃ ለመከላከል በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ወጣት ታጋዮች ወደ ሳህል በረሃ በማዝመቱ አምርሮ ይተጋለውና ይቃወመው ነበር፡፡ በዚሁ ተቃውሞ ምክንያት አድመኞች ተብለው እርምጃ የተወሰደባቸው እጅግ ብዙ ፡ አርሶአደሮችና የከተማ ነዋሪዎች ነበሩ፡፡
የትግራይ ህዝብና የህ.ወ.ሐ.ት የልደት በዓል የካተቲት 11፡-
ከላይ እንደዘረዘርኩት ደርግ ጠላትና ወዳጁ ሳይለይ ይጨፈጭፈው ነበር፡፡ የህ.ወ.ሐ.ት መሪዎችም ያ ጠባብነትና ፀረ-ዲሞክራሲ ባህሪያቸው የህዝብና የተጋዮች ፊት ያሰጋቸው ስለነበር ስግተው ጠባያቸው በመቀየር ብዙ ስለት ይገቡለት ነበር ፡፡ የካቲት 11 የትግል ቀን በመሆኑና ብዙ መስዋእት ስለከፈለበት በዓሉ ሲከበር ከሚወደው አምላክ በማይተናነስ ሁኔታ የየአመቱን በዓል በበለጠ አምልኮት (እምነት) በማሳደር ቤቱ ያፈራውን ሁሉ አይነት የሚበላ የሚጠጣ በመዘጋጀት በሰለማዊ ሰልፍ ልጆቹ በመመልመል ልብስና ቀለብ በመስጠት ወደ ወታሃደራዊ መሰልጠኛ (02) የሚሸኝበት ግዜ ነበር ፡፡

ይህ የሆነበት ምክንያትም የህ.ወ.ሐ.ት መሪዎች በዛን ግዜ ቃል የገቡለት ሰለት ከድተው ራሳቸው፣ ልጆቻቸውና ዘር-መንዘራቸው ሃብት መካበት፣ምርጥ ቪላዎችና ሰማይ ጠቀስ ፎቆች ባገር ውስጥና በውጭ ሰርተው የሃገራችን ዶላር እየዛቁ በውጭ ባንኮች አስቀምጠው ለክፉ ቀን እየተጠባበቁ ይገኛሉ፡፡ ያን ግዜ በታጋይነት ጊዜ፣የመሴ ደቀመዝሙር በነበሩበት ጊዜ፤መድረክ ወጥተው በካድሬዎቻቸውና ራሳቸው ሲናገሩ ህ.ወ.ሐ.ት ደርግ አስወግዶ ባጭር ግዜ የህቡን ችግር ይፈታል የሚል እምነት የሚያሳድር ነበር፡፡ ነገር ግን ህወሐት ቃሉና ተግባሩና ለየብቻ ሆኖ ቀረ፡፡ ህዝቡ ልጆቹን መርቆ ለመስዋእትነት ሲልክ የስደት ፡የድህነት፡ የስራ አጥነት ችግሮች መፍትሄ አግኝበታሎህ ብሎ ተስፋ በመጣል ነበር፡፡ ነገር ግን ህዝቡና ታጋዩ አንድ ያልተገነዘበው ነገር ነበር፡፡እነዚህ የህወሐት ቁንጮ አመራሮች ማንነት በምንመረምርበት ጊዜ ለህዝብ ጥቅም ለመቆም ምንም ምክንያት(background)የላቸውም፡፡ የነሱ ወደ ትጥቅ ትግል መግባት የአባቶቻቸው ስልጣን አሻሽለው ራሳቸውን ገዥዎች ለመሆን አስበው የተነሱ “ታጋዮች” ናቸው፡፡ ስለሆነም ነው አሁን በመቶ ሺ የወጣቱ መስዋእትነት ስልጣን ላይ ወጥተው የአገር ለአላውነት መደፈር፡ የሰብኣዊ መብት ረገጣ ፡ የህግ በላይነት አለመኖር፣ ባጠቃላይ በአገሪቱ በመድብለ-ፓርቲ ስርዓት፣ የዲሞክራሲያዊ መንግሥት መመስረት የቃል መፈክር ሆኖ እንዲቀር ያደረጉት፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች በነፃ ውድድር ህዝቡ በነፃ የመሰለውን የፖለቲካ ፓርቲ መርጦ መንግሥት እንዳይመሰርት የከለከሉት የአባቶቻቸውና የአያቶቻቸው ስልጣን አሳልፈው ላለመስጠት ነው፡፡ የካቲት 11/1967 ዓ.ም በረሀ ሲገቡ ይህንን ድብቅ ዓላማ ከ4 የአንጎላቸው ክፍል በአንዱ ሥር አስቀምጠው ነበር ሲንቀሳቀሱ የነበሩት፡፡ በትጥቅ ትግሉ ለህዝብ የቆሙ፣ብቃት የነበራቸው ታጋዮች የአሁኖቹ አመራሮች የአባቶቻቸው የስልጣን ኮርቻ ላይ እንዳይወጡ ስጋት ሁነው ስለተገኙ በትጥቅ ትግሉ እንዲቀጥሉ አልተፈለገምና እንዲወገዱ ተደረገ፡፡ ህዝቡ የካቲት 11 የሁሉም ነገር መፍትሔ ናት ብሎ ያምን ነበር፡፡ነገር ግን የካቲት 11 ደርግ ደምስሳ ሰላም፣ ፍቅር፣ የኢ/ያ አንድነት ማረጋገጥ አልቻለችም፡፡ የ17 ዓመት ሙሉ የትጥቅ ትግል፣የመቶ ሺዎች ወጣቶች መስዋእነት ለፊውዳል ልጆች የአባቶቻቸውና የአቶቻቸው ስልጣን እንዲረከቡ አስቻላቸው፡፡ ህዝቡ የካቲት 11 ሲያ ከብር ቀደም ብሎ ከልቡ በመነጨ ፍቅር ነበር የሚያከብራት፡፡ ሁኔታው ቀስ በቀስ እየተረዳው ሲመጣ ግን ዕለቱን ለማክበር ድርጅቱ ህዝቡን በማስገደድ እንዲያከብር ያደርገው ጀመር፡፡ህወሐት/ኢህአዴግ ስልጣን ላይ የወጣው በኃይል በማሸነፍ እንጂ በሐሳብ በማሸነፍ( defeat not win) ስላይደለ የህዝብ መብቶች ማስከበር አይችልም፡፡

የህ.ወ.ሐ.ት 40ኛ የልደት በዓልና የትግራይ ህዝብ፡-
የህ.ወ.ሐ.ት መሪዎች በአፈቀላጤዎቻቸው አማካኝነት ባለፉት 24 ዓመታት የስልጣን ዘመናቸው በኢ/ያ ፍትህ፣ የህግ የበላይነት፣ የዜጎች ሰብኣዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ተከብረዋል፣ የብሄር ብሄረሰብ መብት የራስን እድል በራስ የመውሰን መብት ተከብረዋል፡፡ የታገልንበት መደብለ-ፓርቲ ህልውና በኢ/ያ ተረጋግጣል ፡፡ ነፃ የምርጫ ኮሚሽን፣ የሰብኣዊ መብት ኮሚሽን፣ የእንባ ጠባቂ ኮሚሽን ተÌቁማል፡፡ የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ተÌቁማል ፡፡ የነፃ የፍትህ አካላት ተመስርተዋል ይሉናል፡፡
በኢኮኖሚም በአለም ደረጃ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገሮች ተርታ ለመድረስ ተቃርበናል ፡፡ በመሰረተ ልማት፤ በመንገድ፣ በሃድሮ -ኤሌክትሪክ አድገናል ፣ የማይደፈር አባይን ደፍረናል፡፡ የባቡር ሃዲድ እየሰራን ነው፡፡ በቲክኖሎጂ አድገናል፡፡ በእርሻ አድገናል፡፡ የእርሻ ኢንቨስትመት ተስፍፍቷል፡ የመስኖ ስራ ተሰፋፍቷል ፡ ህዝባችን በቀን ሦወስት ግዜ በልቶ እንዲኖር አድርገናል ፡፡ በኢንዳስትሪ ከበለፀጉ አገሮች ተወዳዳሪ ወደ መሆን ደርሰናል፡፡በማህበራዊ አገልግሎት በትምህርት፣ በሕክምና፣ በውሃ ሽፋን በኤሌክትሪክ አገልግሎት ፡ ከነበሩት መንግሥታት በአጭር ዓመታት ውስጥ በበለጠ መሰረታዊ ዕድገት አስመዝግበናል ይሉናል፡፡
በፀጥታና በፍትህ ህዝባችን የተሻለ አገልግሎት አግኝቷል፡፡ የህግ የበላይነት ተረጋግጧል ፡፡ በሃገራችን የተረጋጋና ሰለማዊ ሁኔታ ተረጋግጧል ይላሉ፡፡
የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎችና አጃቢዎቻቸው በ40ኛ የልደት በዓላቸው ይህንን ለመሸፋፈን እያደረጉት ያለ ዝግጅት፡-
ህ.ወ.ሃት በአሁኑ ግዜ 40ኛ የልደት በአሉ ሲያከብር ካለፉት 39 አመታት የበለጠ አከባበር ለማክበር እየተዘጋጀ ነው፡፡ለዚሁም ከውጭ አገር (ከዲያስፖራው) ማህበረሰብ ከ100.000 በላይ እንግዶች እንደሚመጡ ከወዲሁ አውጃዋል፡፡ ካገር ውስጥም ከክልል መሰተዳደሮች ተወካዮች ሰቢክ ማህበራት እነዚህም በመቶሺ የሚቆጠሩ እንግዶች ይመጣሉ፡፡ በሁሉም ክልሎች የሚገኙ የትግራይ ተወላጅችም ከእንግዶች ውስጥ እንደሆኑ ተነግረዋል፡ የሃገራችን የኪነት ባለሙያዎች ፀሐፊዎች ከወዲሁ እየተነገራቸው ነው፡፡ በትግራይ ክልልም ከሁሉም ዘኖች፣ ወረዳዎችና ቀበሌዎች የተወከሉ እድምተኖች በመቶሺዎች ይጠራሉ፡፡ የመቀሌ ህዝብ ከ300,000 በላይ ተጨምሮበት መቀሌ እጅግ ብዙ ሰው ታሰተናግዳለች፡፡ በተጨማሪ በዞን፣ በወረዳና በቀበሌ እስከ ቤተሰብ ቤት ቁጥር በግድ ያከብራል ሃብትም ይባክናል፡፡

በትራንስፖርት መስከም በሃገራችን ያሉ ምርጥ ኤም.ቢ.ኤም ኮብራዎች አውቶቡሶች ይዘጋጃሉ፡፡ በገንዘብ ሲተመን ለነዳጅ ለታዳሚዎች ውሎ አበል የሚወጣ እጅግ ብዙ ሚልዮን ብር ነው፡፡ በዚሁ በመቀሌ ለእድምተኛች የሚወጣ ገንዘብ በመቶ ሚልዮን የሚገመት ነው፡፡ የአየር መንገድና የመከላከያ ሚንስቴር አውሮፕላኖችም ለዚሁ በዓል ማክበር የፀጥታ ኃይሎች የሃገር መከላከያ ፡ ፌደራል ፖሊስ፡ ድህንነትም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሊመጡ ናቸው ፡፡ ለዚሁ በዓል ዝግጅትና ምግብ ለመÙÙዝ ከሚያጠፉት የመንግሥት የስራ ግዜ ሳይቆጠር የሚባክነው ገንዘብ በብዙ መቶ ሚልዮን የሚገመት ይሆናል፡፡

ህ.ወ.ሃ.ት የ40ኛ የልደቱ አመት ለማክበር ይህ ሁሉ ወጪ ሲያወጣ ዛሬ ብቻ አይደለም፡፡ ስልጣን ከያዘ ቀን ጀምሮ እስከዛሬ በቢልዮን የሚገመት ሃብት አባክነዋል፡፡ ይህ የማባከን ጉዳይ ግን በህ.ወ.ሃ.ት ውስጥ ታጥሮ የቀረ አልነበረም፡፡ ሌሎች አጃቢ የፖለቲካ ድርጅቶችም የህ.ወ.ሃ.ት ሞዴልነት በመከተል፡ የብአዴን፣ የአሆዲድ፣የዲህዳን ፡ የጋንቤላ፡ የዓፋር ፡ የቤንሻንጉል፡ የሶማል ፡ የሃደሬ፡ በዓላትም እጅጉን አባካኝ ፍፃሜዎች ታይተዋል ፡፡ በተጨማሪ ለግንቦት 20 ብዙ ባክነዋል አሁንም 20ኛ ዓመት ሊከበር ነው፡፡ ይህ ሁሉ በልማት ስራ ቢውል ኖሮ ስንት ድህነት በቀረፈ ስንት ህዝብ ከስደት በዳነ ነበር፡፡ ህ.ወ.ሃ.ት ግን ራሱን ለማዝናናት ይወዳል፡፡ አለማውም ይኸው ነው፡፡በአሁኑ ግዜ በትግራይ ዲግርና ዲፕሎማ የተመረቀ በመቀሌ ብቻ ከ30,000 በላይ ስራጥ ወጣት አለ፡፡ 10ኛ፣12ና 8ኛ ክፍል የወደቁ ተማሪዎች አይቆጠሩም፡፡ ህወሐት ይህ ሁሉ ቢልዮን ብር ለክርስትናው ከሚያጠፋ እነዚህ በትምህርት ጥራት ዕጦት ምክንያት የወደቁ ተማሪዎች ማስተማርና ማብቃት መምረጥ ነበረበት፡፡ነገር ግን የካቲት 11 የህወሐት አመራር ከድሮውም የአባቶቻቸውና የአያቶቻቸው ስልጣን ለማስረከብ ቀይሰው የተጓዙበት ዕለት በመሆኑ በብልዮን መሆኑ ቀርቶ ዓቅም የላቸውም እንጂ በትሪልዮን ብር በዓሉ ቢከበርላቸው ደስታው አይችሉትም፡፡

የጥፋት ዝግጅቱና ዓለማው ፡-
40ኛ የህወሐት የልደት በዓል ዋናው ዓላማው የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች በአሁኑ ግዜ በትግራይ ህዝብ ዘንድ የነበራቸው አመኔታ ጭራሹን ተማጥጦና ተጠልተው እንደምራቅ የተተፉበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡በመሆኑም በዚሁ በዓል ብዙ የውሸት ይዕድገት ድርሳናት ተደርሰው በፎቶግራፍ፣ በፊልም፣ በሙዚቃ፣ በሬድዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በግብዣና በዲስኩር በማደንዘዝ የህዝብን አቅጣጫ በመቀየርና በማላሳለስ የስልጣን እድሚያቸው ለማራዘም እንደልማዳቸው የትግራይን ህዝብ እንደመጠቀምያ ለማድረግ ነው፡፡ ሌላው ዓላማ በ2007 ዓ.ም የፓርላማ ምርጫ ዘመን እጅጉን ስለሰጉ በዚህ በዓል አመካኝተው የምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግና የህዝቡ አስተሳሰብ መቀየር፣ የህዝቡን ብሶት ለማብረድ፤ወጣትን የውሸት ታሪክ በመደርደርና በመፈረክ በኘሮፖጋንዳ ለማዳንዘዝና በአጉል የተስፋ መንገድ እንዲቆም ለማደረግ ነው፡፡
የህ.ወ.ሃ.ት 40ኛው የልደት በዓልና ፋይዳው፡-
ህወሐት የተነሳለት ብሄራዊና መደባዊ ጭቆና በመጣል በህዝብ የተመረጠ ህዝባዊ መንግሥት መመሰረት የሚል ዓላማ ለማሳካት አልቻለም፡፡ ይባስ ብሎም ከዘውዳዊው ስርዓትና ከፋሽስታዊ ደርግ ስርዓት በባሰ መንገድ ህዝቡን እየጨቆነና እየበዛበዘው ይገኛል፡፡ህዝቡ የድሮ የበሰበሱ በዝበዥ ስርዓቶች አስወግዶ፡ 17 ዓመታት ሙሉ ታግሎ የአባቶቻቸውና የአያቶቻቸው አሮጌውን ስርዓት አሳድሰው ህዝቡን በዘመናዊ መንገድ የሚጨቁኑ ገዥዎች አፍርተዋል፡፡

ሰብአዊና ዲሞክራሳዊ መብቶቹ አልተከበሩለትም፡፡ የየካቲት 11 ውጤት ይህ መሆን ነበረበት፡፡ ህዝቡ ደርግን ማስወገድ ብቸኛው መፍትሔ ይመስለው ነበር፡፡የካቲት 11 ገዥዎች ነቅላ ሌሎች ገዥዎች ታመጣለች ብሎ ህዝቡ አስቦ አያቅም ነበር፡፡ ሀቁ ግን ይህ ሆኖ ቀረ፡፡ የካቲት 11 አደራ በልተሻል ብለው ለተቃወሙ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ታስራለች፣አገር ለቀው እንዲሄዱ እያደረገች ነው፡፡ የካቲት 11 ያ ሁሉ ወጣት በጉያሽ አቅፈሽ፣ለክብርሽ መስዋእት ሆኖ ለአዲስ ገዥዎች አሳልፋ መስጠቷ በየካቲት 11 ያገኘነው ነገር ካለ ልጆቻችን መስዋእት መሆናቸው እንጂ የፈየደችን ነገር የለም እያሉ ናቸው፡፡ የካቲት 11 ይህ ሁሉ ወጣት በልተሽ ለጥቂት የገዥ መደብ ልጆች ጥቅም መቆምሽ ከበደል በደል ነው፡፡

የካቲት 11 40ኛ ዓመትሽ ሲከበር እኛ ህዝቦች ከደርግ መንግሥት የዜሮ ዲሞክራሲ ወጥተን በራሳችን ፍቃድ የኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላውነት ተከብሮ እርስ በራሳችን ተፋቅረን እንኖራለን ብለን ነበር፡፡ በ40ኛ ዓመትሽ በህወሐት/ኢአዴግ መንግሥት እርስ በራሳችን ብጥርጣሬ ዓይን እንድንተያይ፣አንዱ በሌላው ክልል ሄዶ ሰርቶ የመኖር ዕድል ዘግቶ ይገኛል፡፡ እርስ በራሱ እንደጠላት እንዲተያይ እየተደረገ ነው፡፡ ደርግ ሃይማኖት ለማጥፋት ሲጥር ህወሐት/ኢህአዴግ ደግሞ በሃይሞት ነፃነት ጣልቃ በመግባት እርስ በራሳችን የነበረንን የመከባበር እሴት በማደፍረስ አንድነታችንን እንዲላላ በማድረግ ለፖለቲካ ፍጆታው እያዋለው ይገኛል፡፡
ደርግ ዜጎች የመደራጀት፣የመናገር፣የመጻፍ መብት የከለከለ መንግሥት ስለነበር እኛ የጊዜው ወጣቶች ታጥቀን ደርግን እንድናስወግደው ያንችን ጥሪ ሰምተን ታግለናል፡፡ ውጤቱ ለዚህ ብለን አልነበረም፡፡ የፊውዳል ልጆች የአባቶቻቸውና የአያቶቻቸው ሥልጣን ለማስረከብ ብለን አይደለም ደደቢት የወጣነው፡፡

የካቲት 11 አሁን 40ኛ ዓመትሽ እየተከበረ ነው፡፡ እርግጥ ነው ጤና እንዳላገኘሽና በአከባብያችን እንደሌለሽ ይገባናል፡፡ ከአጠገባችን ብትኖሪ ኖሮ ይህ ሁሉ ግፍ ብህዝቡ እየወረደ ዝም ብለሽ ማየት እንደማትችይ ይገባናል፡፡
የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች መሬት ላራሹ፣ የከተማ መሬት በነፃ ለህዝብ በእኩልነት ይታደል ብለው የታገሉና ለህዝብ አነስስተው ደርግን ለመጣል ያስቻላቸው የመሬት ጥያቄ በመክዳት፣ መሬት የመንግስት ናት በማለት የከተማና በከተማ አካባቢ የሚገኙ የህዝብ መሬት በመቀማት በመሸጥ ለራሳቸውና ለዘር መንዝራቸው የሃብት ምንጭ አድርገውታል ፡፡ የገጠር መሬት የህዝቡን ባለቤትነት በመንጠቅ በአርሶአደሩ የማልማት ዓቅም ለሌላቸው ግለሰዎች በመሰጠቱ ወጣት አርሶ አደር የወጣት ጥንቻው ሊያሳርፍበት የሚችል መሬት ባለማግኜቱ ጉሳሳ ጎጆ ሰርቶ የሚተኝበት መሬት ተከልክሎ በረሃና ባህር ተሸግሮ ወደ ስደት ፈልሰዋል ፡፡ በአንፃሩ የህ.ወሃ.ት መሪዎችና ልጆቻች ባገር ውስጥና በውጭ ሰማይጠንቀስ ህንፃዎች ሰርተው የሚኖርበት ሁኔታ ተፈጥረዋል፡፡
የካቲት 11 40ኛ ዓመት የልደት በዓልሽ ስናከብር ይህንን ጉድ ተሸክመን ነው፡፡ግን የካቲት 11 ልጠይቅሽ እነዚህ ቱጃሮች ለመፍጠር ነበር የትግሉ ዓላማ?

አይደለም ፍፁም አይደለም ፡፡ በኛ በኩል አስበነውም አናቅም፡፡እነሱ ግን ይህንን ዓልመው ይጓዙ ስለነበር ያሰቡትን አሳክተዋል፡፡ የካቲት 11 40ኛ ዓመትሽ ስናከብር በሃዘን መሆኑ ማወቅ አለብሽ፡፡ ምኞታችን የነበረው በ40ኛው የልደት በዓልሽ ገጠሪቷ ትግራይ ከ13 ዓመት ዕድሜ በላይ ወጣት የማይኖርበት፣ በገጠር ህፃን፣ ሽማግሌ ከሞተ ሬሳ ተሸክሞ ወደ መቃብር የሚወስድ ወጣት ይጠፋል ብለን ኣናስብ ነበር ግን ሆነ ፡፡ የገጠር ወጣቱ አብዛኛው ወደ ጎረቤት አገሮች ሲሰደድ የቀረው ወጣት ወደ ክልል ከተሞችና አዲስአበባ ፈልሰው ከተሞችን አጣብበዋል ፡፡ ሴት እህቶቻችን ባገር ውስጥም በውጭም ካለፉት ስርአቶች በባሰ ለዝሙት ስራ ተጋልጠው እየተዋረዱ ይገኛሉ ፡፡ ለመጥፎ በሽታ ተጋልጠዋል፡፡ የገጠር ሴቶች ባሎቻቸው ወደ ስደት በመፍላሳቸው ህፃናት ይዘው በሃገር ቤት በረሃብ በበሽታ ይሳቃያሉ፡፡ የካቲት 11 40ኛ ዓመትሽ ስናከብር ይህንን ስቃይ እያየን ነው፡፡

በከተማ ያለው የተማረና ያልተማረ ወጣትም በስራ አጥነት ምክንያት ለፀጥታና ለሰላም ጠንቅ ሆኖ ይገኛል፡፡ በተለይ በዮኒቨርሲቲዎች የተመረቁ ወጣቶችም በመጥፎ ሁኔታ ይገኛሉ፡፡ ያቺ እንደ እሳት አደጋ ማጥፈያ የሚጠቀሙላት ከቡልስ

Image
የተለያዩ መፈክሮችን የያዙ ፊኛዎች ወደ ተውለብለበዋል :: ፊኛዎቹ የተለያዩ መፈክሮች የተጻፈባቸው ሲሆን ከነዚህም መካከል : – ትግሉ ይቀጥላል ፍትህ ነጥፏል ፤ሂጃብ መለያችን፤ኒቃብ ውበታችን ፤ትግላችን ቀጥሏል
ፍትህን ማዘግየት ፍትህን መንፈግ ነው ፤ትግላችን እንደቀጠለ ነው ::

ፍትህ ፍትህ ፍትህ ;We Need Justice ፤Hijab Is Beauty ፤ justice Is Denied የሚሉት መፈክሮች ይገኙበታል፡፡ በርካታ ፊኛዎች የተውለበለቡና ወደ ሰማይ የተለቀቁ ሲሆን ተቃውሞው በከፍተኛ ድምቀት ተከናውኗል፡፡ መንግስት በሴኩላሪዝም ሽፋን እየፈጸመ ያለውን የሂጃብ ገፈፋ የሚያወግዝ ሲሆን በተጨማሪም በህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ላይ እጸፈጸመ ያለውን የፍትህ መዛባት ፤ በማረሚያ ቤቱ የሚፈጸሙ ግፎችን ለማውገዝ ነው፡፡ መንግስት ሙሉ በሙሉ ተቋሞውን በሃይል አስቁሚያለሁ ሲል የነበረ ሲሆን ህዝበ ሙስሊሙ ግን ድንገተኛ ተቃውሞ በማድረግ አስገራሚ ተቃውሞውን ገልጽዋል፡፡

Please wait, video is loading…

Minilik Salsawi – ባሳለፍነው የትግል አመታት ውስጥ የተቃዋሚዎች እርስ በ እርስ መፈራረጅ መወነጃጀል መናናቅ ለስልጣን ጥመኝነት መሮጥ እንዲሁም ለስም እና ለዝና መትጋት ያለመደማመጥ እና ያለመከባበር ፖለቲካ ተቀራርቦ ያለመነጋገር እና ያለመመካከር ፖለቲካ ሃገራኢ ሆደሰፊነት እና መቻቻልን ያላዘለ ፖለቲካ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተረፈው ነገር ቢኖር ከጭቆን ወደ ጭቆና ማቅ ውስጥ ከመዘፈቅ ውጪ ምንም የናፈቀውን የነጻነት አየር እንዲተነፍስ አላደረግነውም። የተቃዋሚ ሃይሎች ጥንካሬ እንዲጎለብት በየድርጅቱ ውስጥ ያሉትን እንከኖች በማጥራት በጋራ እና በተመቻቸ የሃሳብ መግባባት ተቻችሉ እና ተግባብቶ የትግል ስትራቴጂን ግብ ለማድረስ ለአንድ ወጥ ህዝባዊ እና ሃገራዊ አጀንዳ ተግቶ መስራት ይጠበቅብናል።

ወያኔ የተቃዋሚዎችን እና የለውጥ ሃይሎችን እርስ በእርስ መፈነካከት በማየት አርጩሜውን ተስፋ በሚጣልባቸው ግለሰቦች እና ፓርቲዎች ላይ እያወናጨፈ ባለበት እንዲሁም የውስጥ አሰራራቸውን በመሰለል በትግሉ ውስጥ ያላቸውን ሚና እንዲኮላሽ በመስራት የውስጥ ድክመቶቻቸውን በመጠቀም እርስ በርስ እንዲፋጁ እና ተቃዋሚዎች እንዲከስሙ ጥንካሪያቸውን እንዳያገኙ ሲሰራ ይህንን እንዴት አድርገን በማሻሻል የወያኔን ሴራ ማክሸፍ አለብን የሚል አመኔታ የሚያስገኝ ሕዝባዊ ስራዎችን በመስራት ጥንካሬን ማግነት እንዲሁም ሕዝባዊ ድጋፎችን ማግኘት ግድ የሚልበት ጊዜ ላይ መሆናቸውን ተቃዋሚዎች ሊያውቁት ይገባል::ተቃዋሚዎች ካለፈው ድክመቶቻችን ተምረን ከዘለፋ እና ከስድብ እንዲሁም ከመፈራረጅ የሴራ ፖለቲካ በመውጣት ጥንካሬዎቻችንን የምናሳይበት ለውጥ የምናመጣበት አመት እንዲሆን በጋራ ጠንክረን መስራት አለብን።አንድነት ሃይል ነው የሚለው ብሂል ለሃገራዊ አጀንዳ መተግበር ትልቅ አስታውጾ አለው::ከኛ በላይ ላሳር ከኛ በላይ አዋቂ የለም የሚል አመለካከት ይዞ ከመክነፍ የህዝብን ጥያቄ መሰረት አድርጎ ተቀራርቦ በመነጋገር እና በመወያየት ሃገራጂ ማኒፌስቶ በማምጣት የጋራ ሃገራዊ አጀንዳ በመቅረጽ ለለውጥ መትጋት ግዴታ ነው::

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል። ይህ ሳይታለም የተፈታ እና የሁሉም የነጻነት ፈላጊ ሃይሎች ጥያቄ ነው። በሃገር ውስጥ ያሉትን ፓርቲዎች መዋቅሮቻቸውን በማጠናከር የውስጥ ድክመቶቻቸውን በመቅረፍ እንዲጠነክሩ የማድረግ ግዴታ ከለውጥ ፈላጊ ሃይሎች ይጠበቃል። መመካከር መተራረም ግድ ይላል። በውጪው አለም የሚገኙ የነጻነት እና የለውጥ ሃይሎች እንዲጠናከሩ እና ከጥልፍልፎሽ ፖለቲካ ወተው ጠንካራ ሃይል እንዲሆኑ የዲያስፖራው ሃይል ከበፊቱ በበለጠ መልኩ ሊሰራ ግድ ይለዋል። የወያኔ የጎን ውጋት እና የራስ ምታት የሆነው ዲያስፖራው የጀመረውን የትግል ስልት እና ትጋት በማስፋት ሚዲያዎችን በማጠናከር እና የነጻ አውጪ ፓርቲዎችን በመርዳት በማግባባት ጠንካራ ሰንሰለት ከሃገር ቤት ጋር በመፍጠር ሕዝብን ከጨቋኞች ነጻ ማውጣት አለበት።ዲያስፖራው በየቀኑ ወያኔ የሚፈጥረውን ተራ የቤት ስራ እና የማደናገሪያ ማዘናጊያ አሉባልታ ፊት ሳይሰጠው በለውጡ ጉዳይ ላይ በማተኮር በሃገር ቤት ያለው ሃይል እንዲስማማ የፖለቲካ ጡዘቶች ክፍተት እንዳይኖር ተቀራርቦ እንዲሰራ ትልቁን ሚና መጫወት አለበት::

የሚዲያ ተቋማት እና የድህረገጽ ውጤቶች ሕዝብን በማስተማር ሕዝብን መብቱን እና ነጻነቱን አውቆ ለሌላው እንዲያስተምር በማድረግ ረገድ አስፈላጊውን ወቅታዊ መረጃ እና መነሳሳትን በማስረጽ ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል። ያለፉ እና የከሰሙ ወሬዎችን እና አሉባልታዎችን ከመርጨት የወያኔ የፈጠራ አደናባሪ እና አዘናጊ አጀንዳዎችን እኝኝ በማለት ከማውራት ብሄር ተኮር ክፋፋይ ሃሳቦችን ከማርከፍከፍ አዛኝ መሳይ መርዝ ሃሳቦችን ከመናገር ተቆጥበን ሕዝቡን ስለመብቱ እና ነጻነቱን በማስተማር ረገድ መትጋት ከተያዘ ለውጥ የማይመጣበት ምንም ምክንያት የለም። ትችትን እና ሂስን ላለመዋጥ እውነትን ላለመቀበል የሚደረጉ ሩጫዎች ታጥቦ ጭቃ እንጂ የትም እንደማያደርሱ እንዲሁም ፓርቲዎችን እና ሰዎችን መፈረጅ እና መወንጀል ሃሳቦችን ማጣጣል ምንም ለውጥ እንደማያመጣ ካለፈው ተምረናል ። ያሳልፍነው የትግል ሂደት ከጭብጨባ እና ስብሰባ ያለፈ ፋይዳ እንዳሌለው ተገንዝበን የወሬ እና ሆይሆይ ትግል ስለማያዋጣ ጥንካሬን እና ለውጥን የምናመጣበትን የትግል ስልት በመመካከር እና በመወያየት ሃሳብን በማቻቻል መረጃ በመለዋወጥ ሃገራዊ የጋራ አጀንዳ ሊኖረን ይገባል እላለሁ።

Image

በአዳር ሰልፍ ወቅት ተይዘው ከፍተኛ ድብደባ የደረሰባቸው የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት (መአሕድ) ምክትል ፀኃፊ መቶ አለቃ ተሰማ ወንድሙ ራሳቸውን ስተው ሆስፒታል እንደገቡና ሕይወታቸው አደጋ ውስጥ እንደሆነ የፓርቲው ፕሬዝደንት አቶ ሽዋንግዛው ገ/ስላሴ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

መቶ አለቃ ተሰማ ወንድሙ በአዳሩ ሰላማዊ ሰልፍ ወቅት ተይዘው ከፍተኛ ድብደባ የደረሰባቸው ሲሆን ለአምስት ቀናት ቀዝቃዛና ጨለማ ቤት ውስጥ ታስረው ቆይተዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ከታሰሩበት ጊዜ ጀምሮ የስኳር በሽታ መድሃኒታቸውን በመቀማታቸውና ህክምናም ባለማግኘታቸው ታመው እንደነበር ለማወቅ መገለጹ ይታወሳል፡፡

መቶ አለቃ ተሰማ ወንድሙ በድብደባውና በስኳር በሽታ ምክንያት በአሁኑ ወቅት ዘውዲቱ ሆስፒታል የሚገኙ ሲሆን ሆስፒታል ከገቡበት ቅዳሜ ታህሳስ 4/2007 ዓ.ም ጀምሮ ሰው ማናገር አለመቻላቸውን የፓርቲው ፕሬዝዳንት አክለው ገልጸዋል፡፡

Image
የሰማያዊ ፓርቲ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ አቶ እያስፔድ ተስፋዬ ከሚሰራበት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአዳር ሰላማዊ ሰልፉን ተከትሎ በደረሰበት እስር ምክንያት ከስራው ታገደ፡፡ እያስፔድ ተስፋዬ በሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ጨለማና ቀዝቃዛ ክፍል ታስረው ከነበሩት አመራሮች መካከል አንዱ ሲሆን ከእስር ከተፈታ በኋላ ታስሮ ስለመቆየቱ ማስረጃ ቢወስድም ለ15 ቀን ከስራ ታግዶ እንዲቆይ ተደርጓል፡፡

‹‹ታስሬ መቆየቴን የሚያሳይ ማስረጃ ወደምሰራበት ቅርንጫፍ ስወስድ ከእኛ አቅም በላይ ስለሆነ ወደ ዲስትሪክት ውሰድ ተባልኩ፡፡ ዲስትሪክት ስወስድ የንግድ ባንክ ዳይሬክተር የሰው ኃይል አስተዳደር ማመልከቻና ታስረህ የቆየህበትን ማስረጃ አስገባና እነሱ ወደ ስራ ገበታህ ተመለስ ካሉህ ነው የምትመለስ፤ እነሱ ተመለስ እስኪሉህ ድረስ ግን ወደ ስራ ገበታ መመለስ አትችልም አሉኝ፡፡ ባሉኝ መሰረትም ለሰው ኃይል አስተዳደር ደብዳቤና ከፖሊስ ጣቢያ የተሰጠህን ማስረጃ ወሰድኩ፡፡ እሱ እስኪያየው ድረስ ተብሎ አንድ ቀን ቀጠሮ ተሰጠኝ›› የሚለው እያስፔድ በቀጠሮው መሰረት ሲሄድ ጉዳዩ ለቅሬታ ሰሚ ኮሜቴ እንደተላከ፣ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አባሎች ስልጣና ላይ በመሆናቸው ለ15 ቀን ስራ መግባት እንደማይችልና ለታገደበት ቀናትም ደመወዝም እንደማይከፈል እንደተገለጸለት ለነገረ ኢትዮጵያ አስረድቷል፡፡

ቀደም ሲል የሰላማዊ ሰልፉን ተከትሎ አቶ ወሮታው ዋሴ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተባረሩ መሆናቸው ይታወሳል፡፡

Image

በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮችን ጨምሮ 10ሩም ተከሳሾች ለታህሳስ 15 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ተከሳሾቹ የክስ መቃወሚያ አቅርበዋል

ዛሬ ታህሳስ 9 ቀን 2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ 19ኛው ወንጀል ምድብ ችሎት የቀረቡት የሰማያዊ፣ የአንድነትና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች የሆኑት አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና አቶ አብርሃ ደስታ እንዲሁም አንደኛ ተከሳሽን ጨምሮ ስድስት ተከሳሾች በጠበቆቻቸው አማካኝነት የክስ መቃወሚያቸውን ይዘው ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡

ሆኖም ግን 7ተኛ ተከሳሽ አቶ አብርሃም ሰለሞን የሰጠው የተከሳሽነት ቃል ከክሱ ጋር ተያይዞ ለጠበቃው አለመቅረቡን ተከትሎ ጠበቃው የክስ መቃወሚያ ለማዘጋጀት ባለመቻላቸው የተከሳሽ ቃልን የያዘውን ዶክሜንት ከጽ/ቤት ወስደው መቃወሚያቸውን እንዲያስገቡ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ የተከሳሾችን የክስ መቃወሚያ መርምሮ ብይን ለመስጠት ለታህሳስ 15 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
በሌላ በኩል ተከሳሾች በእስር ላይ ባሉበት ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሊጎበኟቸው የሚሄዱ ቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው ወደ እስር ቤቱ ሲገቡ በተለየ መዝገብ እንዲመዘገቡ እየተደረጉ መሆናቸውን ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል፡፡ ተከሳሾች ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዱት ቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው በተለየ መዝገብ በመመዝገባቸው ከሌላው በተለየ ማሸማቀቅ እየተፈጸመባቸው ነው፡፡

ይህን በተመለከተ ለማረሚያ ቤቱ አቤት ቢሉም ሊሻሻል አለመቻሉን ተከሳሾቹ ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ፍርድ ቤቱ ለማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ጠይቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም አቤቱታቸውን ተቀብሎ በቀጣይ ቀጠሮ የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ስለጉዳዩ ቀርቦ እንዲያስረዳ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

ሃገሪቱን የሚያሰጋት የሃይማኖት አክራሪነት/አሸባሪነት ሳይሆን የፖለቲካ የበላይነት የፈጠረው አሸባሪነት ጽንፈኝነት እና አክራሪነት ነው:: ጥላችሁን እንዳታምኑ እየተባለ ሃይማኖት መንግሥታዊ ቅርጽ ይዞ እንዲወጣ ለማድረግ መሞከር አክራሪነት ነው፡፡

«መጾም፣ መጸለይ፣ ሥርዓተ-አምልኮን መፈጸም ሃይማኖታዊ አልባሳትን መልበስ ለሃይማኖቱ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እንጂ አክራሪነት ሊባል አይችልም፤»…የአክራሪ ክርስትና ወይንም እስልምና ቡድን መኖር የክርስትና እና እስልምና ተከታዮችን በሙሉ «አክራሪ» አስብሎ ሊያስፈርጃቸው አይችልም::አክራሪ ተብሎ የሚፈረጀው የሚራመዱ የፖለቲካ ጡዘቶች በሰዎች ላይ ሌላ እምነትን በመጫን በግዳጅ እና በሃይል ሊያስገድዱ ሲሞክሩ ይህ ማለት አህበሽን እና ተሃድሶን በጥንታውያኑ እስልምና እና ተዋህዶ ላይ በኢትዮጵያ እንደተሞከረው ማለት ነው::

አክራሪነት አሉታዊ ትርጉም ሲኖረው የራስን እምነትና አመለካከት በሌሎች ላይለመጫን መሞከር ነው፡፡ ሃይማኖት መንግሥታዊ ቅርጽ ይዞ እንዲወጣ ለማድረግ መሞከር ራሱ አክራሪነት ነው፡፡ አክራሪነት የፖሊቲካ ገጽታ ያለው ነው፡፡ ኾኖም ግን ሃይማኖትን ማጥበቅ አክራሪነት አይደለም፡፡ሃይማኖት ፍጹም እውነታን በፍጹም እምነት ስለሚቀበል ከሌሎች ግላዊ አስተሳሰቦች የተለየ ነው፡፡ የሃይማኖት መገለጫዎችን መጠቀም የዚያን ሃይማኖት ጥልቀት የሚያሳይ እንጂ እንደ ችግርም የሚወሰድ ወይም አክራሪነት ሊኾን አይችልም፡፡ «መጾም፣ መጸለይ፣ ሥርዓተአምልኮን መፈጸም ሃይማኖታዊ አልባሳትን መልበስ ለሃይማኖቱ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እንጂ አክራሪነት ሊባልአይችልም፤» ይላሉ የዘርፉ ምሁራን፡፡

የአክራሪነትና የአጥባቂነት ፅንሰ ሐሶቦች በጥሩ ኹኔታ ተለይተው ተገልጸዋል፡፡ አንዳንድ ሰነዶች ወያኔም ለይስሙላ የገለበጣቸው ሰነዶቹ አክራሪነትንና አጥባቂነትን በአግባቡ ለይተውና ተንትነው ያስቀምጣሉ፡፡ በዚሁ መሠረት አጥባቂነትን፣ ‹‹የግል ሃይማኖትን ሃይማኖቱ በሚያዘው መሠረት ሳይንጠባጠብ ሁሉንም ትእዛዛት መፈጸም ነው፤» በማለት ሲፈታው አክራሪነትን ደግሞ፣ «ከራስ እምነት ወጥቶ ሌላውን መተንኮስና የሌሎችን ሃይማኖት መኖር አለማመንና አለመፍቀድወይም ሌሎቹን አስገድዶ የራስ እምነት ተከታዮች ለማድረግ መጣር ነው፤» ይላል፡፡ በተግባር ላይ አለመዋሉ እና በጣልቃ ገብነት መተርጎሙ ጉዳት አመጣ እንጂ::

ከዚህ ብያኔ ስንነሣ ክርስቲያንም ሆነ ሙስሊም ከርሱ ውጭ የኾኑትን የሌሎቹን መኖር የማይቀበልና ከግለሰቦቹ ፈቃድ ውጭ አስገዳጅ እስከኾነ ድረስ እርሱን አክራሪ ማለት ይቻላል፡፡መብትን መጠየቅ ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት መሸሽ አክራሪነት አይደለም:: በዚህ መልኩ አክራሪው ይህንኑ ድርጊት ሊፈጽም የተነሣውን ቡድን ብቻ እንጂ «አክራሪው ቡድን» የወጣበትን/የተገኘበትን ቤተ እምነት ሊወክል አይችልም፡፡ ስለዚህ በአለማቀፍ ደረጃ የአክራሪ ክርስትና እና እስልምና ቡድን መኖር የክርስትና እና እስልምና ተከታዮችን በሙሉ «አክራሪ» አስብሎ ሊያስፈርጃቸው አይችልም፤ ለሌላው ቤተ እምነትም እንዲሁ፡፡ ሃገሪቱን የሚያሰጋት የሃይማኖት አክራሪነት ሳይሆን የፖለቲካ የበላይነት የፈጠረው አሸባሪነት ጽንፈኝነት እና አክራሪነት ነው:: #ምንሊክሳልሳዊ

(ይህ የግሌ አስተያየት ነው!)

ምርጫ ካልተገባ ሌላኛው አማራጭ ትጥቅ ትግል ብቻ ነው ያለው ማነው? ሲጀመርስ ምርጫ የዲሞክራሲ መገለጫ ነው እንጂ ከመቼ ወዲህ ነው የሰላማዊ ትግል አካል ሊሆን የሚችለው፡፡ ሰላማዊ ትግል ዲሞክራሲ በሌለበት የሚደረግ ትግል ከሆነ ዘንዳ የዴሞክራሲ መገለጫ የሆነው ምርጫ ሰላማዊ ትግል ነው ማለትስ ምን ማለት ነው?

ሰላማዊ ትግል እኮ ሰላማዊ ትግል ያስባለው መሳሪያ የሚያስነሳ ጭቆና መኖሩ ነው፡፡
ግልፅ በሆነ መንገድ ለማስቀመጥ
በምርጫ የሚደረግ ትግል ህዝቡ የስልጣኑ ባለቤት በሆነበት ሀገር እንጂ ሁሉም ነገር በአገዛዙ መዳፍ ስር በሆነበት ሁናቴ አይደለም፡፡

ሰላማዊ ትግል ዲሞክራሲ ጨርሶውኑ በሌለበትና እየሞቱ ማሸነፍ ግድ የሆነበት የትግል አካሄድ ነው፡፡
የትጥቅ ትግልም ዲሞክራሲ ፈፅሞ በሌለበት ሀገር ውስጥ እየገደሉም እየሞቱም ለማሸነፍ የሚደረግ ትግል ነው፡፡

ከዚህ በመነሳት
1- አሁን ባለንበት ሁናቴ ምርጫ ማካሄድ የዴሞክራሲ ሂደት ኢትዮጵያ ውስጥ አለ ማለት ሲሆን
2- ኢህአዲግን በፈቃዳችን እንደ መንግሰት እውቅና መስጠት ነው

ስለዚህ፡- ትግሉ ሰለማዊ ትግል ነው የምንለው ምርጫ ማድረግ የሚቻልበትን ምህዳር መፍጠር፤ ህዝቡን የስልጣኑ ባለቤት ማድረግ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ በመሁኑ ነው፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን ማቸውንም የፖለቲካ ስራ በነፃነት መስራት በማይቻልበት ሁናቴ ነፃነት እንዲኖር መታገል ከሁሉ በፊት መሆን ያለበት ትግል ነው፡፡ ይህ ትግል በባህሪይው እልህ አስጨራሽ፣ ተስፋ አስቆራጭ፣ ብዙ ዋጋ የሚያስከፍል … ፍሬው ግን ዘላቂና እጅግ አስደሳች ነው፡፡ ለዛ ነው ደጋግመን ህይወታችንንም ቢሆን እስከመስጠት ድረስ ፍፁም ሰላማዊ ሆነን እንታገላለን የምንለው፡፡

ሰለማዊ ትግል ከነፍጥ ትግል የሚለየውም በዚሁ ባህሪይው ነው፡፡ በመውደቅ በመነሳት ውስጥ ማሸነፍ፤ ሳይገድሉ በመሞት ማሸነፍ፡፡ ይህ መንገድ በምርጫ ከሚደረግ የስልጣን ትግልም ሆነ መሳሪያ አንስተው በሀይል ስልጣን ለመያዝ ከሚደረግ ትግል ፍፁም የተለየ ነው፡፡ ነፃነት ትግል ይፈልጋል፡፡ ፍፁም ሰላማዊ ሆነን እናሸንፋለን!
Image

Image

ተስፋዬ ገ/ኣብ በየሄደበት ሁሉ መርዝ መርጨቱን ኣያቆምም፡፡ በቅርቡ የኦሮሞ ልጅነትን (ፎርጅድ) አግኝቻለሁ በማለት ተናግሮ ሳይጨርስ ነጻ ሆኖ ይንቀሳቀስ የነበረዉን የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ (OMN) አደጋ ውስጥ ጨምሮታል፡፡ OMN ከተመሰረተ እንኳ አንድ አመት ሳይደፍን ይኸዉ ከሁለት መከፈሉን የተለያዩ ሚዲያዎች እየነገሩን ነዉ፡፡
ይህ የሚዲያ ተቋም የሰዉ ሀይል ችግር ኖሮበት አይመስለኝም፡፡ እነ በፈቃዱ ሞረዳ ከዚህም በላይ መስራት የሚችሉ ሰዎች ናቸዉ፡፡ በፈቃዱ በተደጋጋሚ ባደረጋቸዉ ቃለ መጠይቆች ወገንተኝነትን የማይፈልግ ፍጹም የጋዜጠኛነት ሙያ የሰረጸዉ ሰዉ መሆኑን አስመስክሯል፡፡
በእኔ እምነት ችግሩ ተስፋዬን ወደ ህብረታቸዉ ማስጠጋታቸዉ ነዉ፡፡ ተስፋዬ ገብረ አብ በማንኛዉም መንገድ ለኦሮሞም ሆነ ለሌላዉ ኢትዮጵያዊ ህብት እንደማይፈልግ እነ በፈቃዱና ሌሎችም የተረዱት አልመሰለኝም፡፡ እናም ይኸዉ አንድ አመት ሳይደፍን ከጆሀር መሀመድ ጽንፈኝነት ጋር ተጨማምሮ ሚዲያዉን ህልዉና ተፈታተነዉ፡፡
viewtopic.php?f=2&t=90612

Image

‹‹በሰላማዊ ሰልፈኛ ላይ ዱላ መሰንዘር ሽንፈት ነው›› እስክንድር ነጋ

ሰማያዊ ፓርቲ እና ሌሎች በትብብሩ ውስጥ የታቀፉ ፓርቲዎች በጠሩት የአዳር ሰልፍ ላይ የወጡ ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የተወሰደውን አሳፋሪ እርምጃ ሰምቻለሁ፡፡ እርምጃው ሁለት ነገሮችን በጉልህ ያሳዬ ነበር፡፡ አንደኛ የኢህአዴግ መራሹ መንግስት ሽንፍትን ያሳየ ነው፤ ሁለተኛው ደግሞ ሰላማዊ ትግሉ እየተጠናከረ መምጣቱን ያመላከተ ነው፡፡

አንተ ባዶ እጅህን መብትህን ለመጠየቅ ስትንቀሳቀስ፣ መሳሪያ ወደታጠቀ አካል በሰላም ስትገሰግስ ባለመሳሪያው ዱላውን ከሰነዘረብህ አሸናፊው አንተ ሰላማዊው ታጋይ ነህ፡፡ በትብብሩ ሰልፍ ላይ የሆነው ይኸው ነው፡፡ አሁን ሰላማዊ ትግሉ ፍጹም ሰላማዊነቱን እንደጠበቀ መጠናከር ነው ያለበት፡፡ ሰላማዊ ትግል ላይ ልብ ማለት ያለብን ነገር አለ፤ እሱም ሰላማዊ ሆኖ መዝለቅ የሚለው ጉዳይ ነው፡፡

ሰላማዊ ታጋይ ይሰደባል፣ ይደበደባል፣ ይሞታልም፡፡ ግን ደግሞ ሰላማዊ ታጋይ አይሳደብም፣ አይደባደብም፣ አይገድልም፡፡ ይህ ከሆነ ሰላማዊ ትግል ያሸንፋል፡፡ አምባገነኖች ሰላማዊ ታጋዮችን በተለያየ መንገድ ከሰላማዊነታቸው እንዲወጡ ሊገፋፏቸው ይሞክራሉ፤ ስሜት ውስጥ በመክተትም የኃይል በትራቸውን ለማሳረፍ ይቋምጣሉ፡፡ ይህ ሴራ ሰላማዊ ታጋዮችን ሊያዘናጋቸው አይገባም፡፡

በቀደም በተደረገው ሰልፍ ላይ ድብደባው በሰላማዊ ሰዎች ላይ መፈጸሙ ለተደብዳቢዎቹ ሳይሆን ሽንፈቱ ለደብዳቢዎቹ ነው፡፡ በደረሰው ድብደባ ባፍርም፣ ባዝንም በውጤቱ ግን ደስተኛ ነኝ፤ ምክንያቱም ሰላማዊ ሰልፈኞች ሰላማዊነታቸውን አሳይተዋልና! በሰልፉ ወቅት ድብዳባ እና እስር የደረሰባቸውን የመብት ጠያቂዎች ሁሉ በርቱ ልላቸው እፈልጋለሁ፡፡ ባደረጉት ሰላማዊ እንቅስቃሴ በጣም ኮርቻለሁ፡፡ ሰላማዊና ህጋዊ ትግላችሁን ቀጥሉ ማለትም እፈልጋለሁ!

‹‹አሸናፊው ህዝብ ነው›› አንዱዓለም አራጌ

ግለሰቦች የለውጥ ሐዋርያ ሊሆኑ ይችላሉ፤ በዚያው ልክ የሚሳሳቱትም ግለሰቦች ናቸው፡፡ የግለሰቦች አስተሳሰብ ህዝባዊ ከሆነ ግን በአሸናፊው ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ይኖራቸዋል፡፡ ምክንያቱም አሸናፊው ህዝብ ነው፤ አሸናፊው ሀገር ነው፡፡ የሁላችንም አሸናፊነት የሚገለጸው ሀገር ከፍ ከፍ ስትል ነው፡፡ ስለዚህ ስራችን ሁሉ ሀገርን ከፍ ለማድረግ መሆን አለበት፡፡

በትብብሩ ፓርቲዎች በተጠራው ሰልፍ ላይ የሆነውን ሰምቻለሁ፡፡ በሆነው ነገር አዝኛለሁም፤ ኮርቻለሁም፡፡ ያዘንኩት በደረሰው ድብደባ እና እስር ነው፡፡ የኮራሁት ደግሞ መብታቸውን በሰላማዊ መንገድ ሊጠይቁ በድፍረት አደባባይ በወጡት ታጋዮች ነው፡፡ በእነዚህ ታጋዮች የእውነት ኮርቻለሁ፡፡

በቀጣይ ፓርቲዎች በአጋርነት መስራት አለባቸው ብዬ አምናለሁ፡፡ በተለይ በቀጣዩ ምርጫ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ፓርቲዎች ከእጩ አቀራረብ ጀምሮ ተቀራርበው መስራት ይኖርባቸዋል፡፡ በተለይ ሰማያዊ እና አንድነት ተቀራርበው ቢሰሩ የበለጠ ውጤታማ የሚሆኑ ይመስለኛል፡፡ በተረፈ ግን በትብብሩ ሰልፍ ወቅት ጉዳት ለደረሰባቸው ሁሉ ጥንካሬን እንዲሰጣቸው እመኛለሁ፡፡ ትግላቸውንም አጠናክረው እንዲቀጥሉ አደራ እላለሁ፡፡

‹‹ቃላችሁን ጠብቃችኋልና ክብር ይገባችኋል፣ ኮርቸባችኋለሁም!›› የሺዋስ አሰፋ

ሰማያዊ ፓርቲ መርህ አለው፡፡ ያመነበትን ነገር ህጋዊና ሰላማዊነቱን ጠብቆ እንደሚፈጽም አውቃለሁ፡፡ ትብብሩ በጠራው ሰልፍ ላይም የሰማያዊ ወጣቶችና ሌሎችም ቃላቸውን ጠብቀው ሰልፍ ወጥተዋል፡፡ በእውነት በጣም ኮርቸባቸዋለሁ፡፡ እንደሁሌውም ቃላቸውን ጠብቀው ለህዝቡ መብት መቆማቸውን አይቼ ደስ ብሎኛል፡፡ እኔ በእስር ላይ ብሆንም ሌሎች የትግል ጓዶቼ ባደረጉት ነገር በጣም ነው ደስ የተሰኘሁት፡፡

ድብደባውና እስሩ የፈሪ ዱላ ነው፡፡ ኢህአዴግ በህዝብ ፊት ኪሳራን ነው ያተረፈው፡፡ ሰላምን እና ህግን ማስጠበቅ የሚቻለው በልምምጥ ሳይሆን ትክክለኛ መስመርን በመከተል ነው፡፡ በዚህ መሰረት የትግል ጓዶቼ ትክክለኛ መስመር ላይ እንደሆኑ ይገባኛል፡፡ በርቱልኝ ማለት እፈልጋለሁ፡፡ በዚህ መሰል ሰላማዊነት ነው አምባገነኖችን ማሸነፍ የሚቻለው፡፡ በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

Image
የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይሎች (Amara Force) እኛ በውህደቱ የለንበትም ብሏል::
Minilik Salsawi ምንሊክ ሳልሳዊ – ከአስመራ ከተማ የሚገኙ ምንጮቼ በስልክ እንዳስታወኩኝ ካለፈው ሃሙስ ጀምሮ የግንቦት ሰባት አመራር አባላት የሆኑት አቶ ነእመን ዘለቀ:የአቶ አንዳርጋቸው ወንድም አቶ ብዙአየሁ ጽጌ አቶ አበበ ቦጋለ እና ሌሎች የኢሳት ሪፖርተሮችን አስከትለው አስመራ የገቡ ሲሆን የአርበኞች ግንባር አመራሮች ወደ አስመራ የሚልኩትን ሰው መርጠው ባለመጨረሳቸው እንደዘገዩ ሲጠቆም እስከ እሁድ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል::ዶክተር ብርሃኑ ነጋ መግባታቸውን ለማረጋገጥ ቢሞከርም ሆተሎች ጥብቅ የጸጥታ ክትትል ስለሚደረግባቸው መረጃዎች ለጊዜው እንዲዘገዩ ተደርጓል::

በአስመራ የተለያየ ሆተል ማረፊያ የተዘጋጀላቸው የግንቦት ሰባት አመራሮች የአርበኞች ግንባር አመራሮች እንደገቡ በመጭው አዲስ አመር ጥር መጀመሪያ የውህደት መስራች ጉባያቸውን በማድረግ የአርበኞችና ግንቦት ሰባት ዲሞክራሲያዊ ግንባር ይመሰርታሉ ተብሎ ሲጠበቅ ውህደቱን የአርበኞች ግንቦት ሰባት ደምህት እና ሻእቢያ ሰራዊቶች ሊያጅቡት ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል ሲሉ ምንጮቹ ከአስመራ ገልጸዋል::

እንደ ደምሕት እና ኦነግ እንዲሁም የጋምቤላ ቤንሻንጉል እና አፋር ነጻ አውጪዎች በውህደቱ እንዳይሳተፉ ተደርጓል ያሉት የአስመራ ምንጮች ሻእቢያ የጎሳ ድርጅቶችን ለአላማው ስለሚተቀምባቸው ከአንድነት ሃይሎች ጋር እንዲዋሃዱ አይፈሊግም ሲሉ ተናግረዋል::(በዚህ ጉዳይ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ምንጮቹ አሁን እንዳይጻፍ ጠይቀዋል::)

የአይሮፕላን ወጪያቸውን ሸፍነው አስነራ የደረሱት ነጻ አውጪዎች በሻእቢያ አስመራ ከተማ ውስጥ ሙሉ ወጪያቸው ሲሸፈን የመብራት አገልግሎት እንዳይቋረጥባቸው ጄኔራተር በመትከል እና እንዲሁም የደህንነት እና የጸጥታ ጥበቃ በማድረግ ላይ እንደሆነ ምንጮቹ ሲናገሩ በግንባር ያገኟቸው የግንቦት ሰባት ሰዎች ለጊዜው ዝርዝር ምረጃ ሊሰጡ ፈቃደኞች እንዳልሆኑ ገልጸዋል::

በውህደቱ ዙሪያ በአርማጮ በረሃ ያሉትን የአማራ ፎርስ ሰራዊት አመራሮችን አነጋግሬቸው እንደመለሱልኝ ከሆነ ክታሰሩ አባሎቶቻችን ውጪ በአስመራ ያለንን ሃይል ያስወጣን እና ከሻእቢያ ጋር ያለውን ግንኙነት ዘግተናል ሲሉ የገለጹ ሲሆን ካሁን በፊት ባወጡት መግለጫ ከአስመራ መንግስት ጋር ሆኖ ዪትዮጵያን ህዝብ ነጻነት ማሰብ ስህተት መፍጠር ነው ሲሉ ገልጸው ነበር::በአስመራ በኩል የተዘጋጁትን ነጻ አውጪዎች የተሳካ ቀሪ ዘመን እየተመኘው ቀሪ ዝርዝር ዘገባ ይዤ ለመመለስ ቃል እገባለሁ:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Image
Eyasped Tesfaye
ይህን ሁለት ቀን በማህበራዊ ድህረ-ገፆች ላይ በትብብሩ እና በፓርቲዬ ላይ እየተናፈሰ ያለውን አቧራ ማጥራት ግዴታ ስለሆነብኝ የሚከተለውን ፅፊያለሁ፡፡ ልቦና ያለው ልብ ይበል፡፡
ሰማያዊ እና ትብብሩ የምርጫ ምልክት ወስደዋል እንዲሁም ደግሞ የትብብሩ ዋና ፀሀፊ ያለምንም ቅድመ ሁናቴ በምርጫው እንደሚሳተፉ በፌስቡክ ገፃቸው መግለጫ ሰጥተዋል በሚል ከተለያዩ አቅጣጫዋች የተለያዩ ድንጋዮች እየተወረወሩ ነው፡፡ የዚህ ነገር መነሾ ለእኔ ሁለት ምክንያት ያለው ይመስለኛል፡፡
1ኛ፡- ከጥቂት ሳምንታት በፊት አንድነት ፓርቲ ያለምንም ቅድመ ሁናቴ በምርጫው እሳተፋለሁ ማለቱን ተንተርሶ በሶሻል ሚዲያው ላይ አንድነት ፓርቲን የሚያጥላሉ ፅሁፎች በርክተው ነበር፡፡ አሁን እንደገባኝ ከሆነ ወንድሜ አስራት አብርሀምን ጨምሮ የተወሰኑ ሰዎች አንድነት ላይ ዘመቻውን የከፈቱት ሰማያዊዎች ናቸው የሚል ግንዛቤ ወስደው የነበረ ሲሆን የአሁኑ ፅሁፋቸው የመልስ ምት እንደሚሉት አይነት መሆኑ ነው፡፡ በወቅቱ ግን ወዳጄ ዮናታን ተስፋዬ(የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ) በፌስቡክ ገፁ ላይ ከዚህ በታች በፎቶ ያያዝኩትን ፅሁፍ ፅፎ ነበር፡፡ ሰሚ አላገኘም እንጂ፡፡
2ኛ፡- የሰሞኑን አቧራ ያስነሱት ሰዎች ምርጫውን ያለምንም ቅድመሁናቴ እንሳተፋለን ብሎ መግለጫ በመስጠት እና ‹ነፃነት ለፍትሀዊ ምርጫ› ብሎ ምርጫው ፍትሀዊ እንዲሆን በመታገል መካከል ያለውን ልዩነት በቅጡ ያልተገነዘቡ ናቸው፡፡
ማብራሪያ፡-
ሰማያዊ ፓርቲና ሌሎች ስምንት ፓርቲዎች በጋራ በመሆን ነፃነት ለፍትሀዊ ምርጫ የሚል እንቅስቃሴ እያደረጉ እናዳለ ሁሉም የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡ የዚህን እንቅስቃሴ ስያሜ እንኳን በቅጡ ብናየው ሁለት ነገሮችን እንገነዘባለን፡፡ የመጀመሪያው ነገር ነፃነት ሳይኖር ምርጫ ሊኖር አይችልም ስለዚህም ነፃነት የምርጫ ቅድመሁናቴ ነው የሚል ሀሳብ የያዘ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በነፃነት የሚደረግ ምርጫ እንዲኖር ትግል እንደሚደረግ አመላካች ነው፡፡
ከፊታችን የሚደረገው የ2007ቱ ምርጫ ነፃና ፍትሀዊ እንዲሆን ታግዬ ነፃ ሲሆን እሳተፋለሁ ማለት እና ያለምንም ቅድመ ሁናቴ በምርጫ እሳተፋለሁ ብሎ መግለጫ መስጠት ልዩነቱ እዚህ ላይ ነው፡፡ ለነገሩ የዛሬው ጫጫታ ከጀርባው ሌላ ተንኮል እንዳለው አንዱ ማሳያ የትብብሩ ፀሀፊ የሆኑት አቶ ግርማ ከዛሬ 10 ቀን በፊት ከግርማ ካሳ ጋር በኮመንት ሲከራከሩ ኮመንት ያደረጉትን ነገር አዲስ መግለጫ እንደሰጡ በማስመሰል ‹‹ሰማያዊ ያለምንም ቅድመ ሁናቴ በምርጫው እንደሚሳተፍ ገለፀ›› ብሎ ዜና መስራቱ በራሱ የጤነኝነት አይመስልም፡፡ ምናልባትም ሰማያዊም ሆነ ትብብሩ ነፃነት ከሌለ ምርጫ የለም በሚል በያዙት ጠንኳራ አቋም ምክንያት ያገኙትን ሰፊ የህዝብ ድጋፍ ለማሳጣት የታለመም ይመስላል፡፡
ሰማያዊ የምርጫ ምልክት ወሰደ ማለትስ በምርጫው ውስጥ ያለምንም ቅድመሁናቴ በምርጫው እሳተፋለሁ ብሎ መግለጫ ሰጠ ወይም ወሰነ ማለት የሚሆነው እንዴት ነው??? ሰማያዊ ፓርቲ ምርጫ 2007ትን ከወዲሁ ቦይኮት ማድረጉን ቢገልፅ እና ከሂደቱም ራሱን ቢያገል፤ በአንፃሩም ሰማያዊ እና ትብብሩ ነፃነት ለፍትሀዊ ምርጫ በሚል እያደረጉ ያሉት እንቅስቃሴ ውጤት ቢያመጣና ምርጫው ነፃ ቢሆን ማን በጠረገው መንገድ ማን ሊሄድ ነው??? ይህ የነፃነት ለፍትሀዊ ምርጫ የሚለው ትግል እኮ ቢያፈራ ፍሬውን ለመሰብሰብ በሂደቱ ውስጥ መቆየት ግድ ነው፡፡
አንድነት ያለምንም ቅድመሁናቴ በምርጫው እሳተፋለሁ ብሎ መግለጫ መስጠቱን አልቃወምም፡፡ አባላቶቼን ከወዲሁ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ይረዳኛል ብሎ ይሆናልና፡፡ ልክ እንደዚሁም ሁሉ ሌላውም የእኛን አቋም እንዲያከብርልን እሻለሁ፡፡ ሰማያዊ እና ትብብሩ ምርጫ የሚኖረው ነፃነት ሲኖር ነውና ነፃነት ለፍትሀዊ ምርጫ ብለው እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ አዲስ ነገር የለም! አይኖርምም!!!

Image

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ፀኃፊ አቶ ግርማ በቀለ በማህበራዊ ድረ ገጽ በሰጡት አስተያየት ትብብሩ ያለ ቅድመ ሁኔታ ወደ ምርጫ እንደሚገባ በማህበራዊና በሌሎች ሚዲያዎች ተላልፏል፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶ ጥያቄ ያቀረብንላቸው አቶ ግርማ እንደሚከተለው መልስ ሰጥተውበታል፡፡

አንድ የሌላ ፓርቲ ደጋፊ ማህበራዊ ድረ ገጽ ላይ ምርጫው ውስጥ ስለመግባትና አለመግባት ላይ ባነሳው ክርክር የግል አስተያየቴን ሰጥቼ ነበር፡፡ ይህ የግል አስተያየትም ትብብሩም ሆነ አባል ፓርቲዎች በምርጫው ሂደት ላይ ምንም አይነት ጥያቄ ሳያነሱ ወደ ምርጫው እንደሚገቡ ተደርጎ በማህበራዊ ሚዲያዎች ተሰራጭቷል፡፡

አንድ ፓርቲ በምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ በሰላማዊ መንገድ እንቀሳቀሳለሁ ሲል የምርጫ ፓርቲ ነው ማለት ነው፡፡ በመሆኑም የምርጫ ፓርቲ ሆኖ እንደ ስልት በምርጫ ላይ ቅድመ ሁኔታ ሊያቀርብ አይችልም፡፡ ቅድመ ሁኔታ ሊያቀርብ የሚችለው በምርጫው ሂደት ላይ ነው፡፡ በሌላ በኩል አንድ በሰላማዊ መንገድ እንቀሳቀሳለሁ የሚል ፓርቲ ስልጣን ሊይዝ የሚችለው በምርጫ ነውና ምርጫ እገባለሁ ብሎ ሊያውጅ አይችልም፡፡ የምርጫው ሂደት ላይ ጥያቄ ሲያነሳ ደግሞ ከምርጫው ራሱን አገለለ ማለት አይደለም፡፡ እኛ በምርጫው ሂደት ላይ ጥያቄ በማንሳታችን ከአሁኑ ራሳችን ከምርጫ ያገለልን የሚመስላቸው አካላት አሉ፡፡ ግን እኛ ራሳችን አላገለልንም፡፡ ከአሁኑ ምርጫ እንሳተፋለን ብሎ ማወጅም አላስፈለገንም፡፡ ከዚህ ይልቅ ‹‹ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ›› በሚል ምርጫው ፍትሓዊ እንዲሆን እየታገልን ነው፡፡

ስለሆነም ምርጫው ሂደት ላይ ጥያቄዎችን አንስተን ምርጫው ፍትሓዊ እንዲሆን እየታገልን ነው፡፡ ስለሆነም በምርጫው ሂደት ላይ አለን ማለት ነው፡፡ ነገር ግን በሂደቱ ላይ አለን ማለት ጥያቄዎቹ ሳይመለሱ ምርጫውን እንሳተፋለን ማለት አይደለም፡፡ በምርጫው ሂደት ሲሳተፍ ቆይቶ ሂደቶቹ ፍትሓዊ ባለመሆናቸው፣ የተነሱት ጥያቄዎች ባለመመለሳቸውና በሂደቱ ላይ የተቀመጡት ቅድመ ሁኔታዎች ባለመሟላታቸው ምርጫው አንድ ቀን ሲቀረው ራሱን ከምርጫው ያገለለ ፓርቲ አውቃለሁ፡፡

ከአሁኑ ምርጫው ላይ ጥያቄ በማንሳታችን ከምርጫው ራሳችን አግልለናል ማለት አይደለም፡፡ እኛም ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጥነው ምርጫ ላይ ሳይሆን የምርጫ ሂደቱ ላይ ነው፡፡ ሂደቱ ፍትሓዊ ካልሆነ አጃቢ መሆን አንፈልግም፡፡ ለዛም ነው ሂደቱን ለማስተካከል ‹‹ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ›› በሚል እየታገልን ያለነው፡፡ በትግላችን መሰረት ሂደቱን እናስተካክለዋለን ብለን እናስባለን፡፡

ፓርቲያችን አንድነት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ሠላማዊ የሥልጣን ሽግግር እንዲኖር ለማድረግ በሠላማዊ ትግል ትንቅንቅ ውስጥ ካሉ ፓርቲዎች ግንባር ቀደሙ ነው!

በትግሉ ውስጥ ከፍተኛ ዋጋ በመክፈል ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ልዕልና እየተጋ ያለው ፓርቲያችን በየጊዜው በሚገጥሙት መሠናክሎች ከመዳከም ይልቅ እየጠነከረ፤ ውስጣዊ ዴሞክራሲው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያጎለበተ የመጣ እንዲሁም የኢትዮጵያን ሕዝብ ጥያቄ በአስተማማኝ መንገድ ለመመለስ በሀገር አቀፍ ደረጃ ቁርጠኛ አባላትን ያፈራ በመሆኑ ኩራታችን ከፍ ያለ ነው፡፡

አንድነት በ2ዐዐ7 ዓ.ም. በሚካሄደው ምርጫ አሸናፊ ኃይል ሆኖ ለመውጣት መሠረተ ሠፊ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ይገኛል፡፡ በዚህ ሠፊ እንቅስቃሴያችን ምክንያትም ገዢው ፓርቲ በአባላትና አመራሮቻችን ላይ ከፍተኛ የሆነ የእስር፣ የማሳደድና የማጥፋት ሥራ እየሰራ ቢሆንም ፓርቲያችን ይህንን ሁሉ ጫና በመቋቋም አሁንም በሠላማዊ ትግል የኢትዮጵያን ሕዝብ የሥልጣን ባለቤት ለማድረግ በቁርጠኝነት ቆሟል፡፡

ለዚህ ቁርጠኝነታችንና ፓርቲያችን ስላለው መሠረተ ሠፊ አደረጃጀት ከዚህ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ በላይ ምስክር የለም፡፡ በአንድ ሳምንት ውስጥ ደረጃውን የጠበቀ ጉባኤ ለማድረግ ችለናል፡፡ ይሄ ፓርቲያችን የደረሰበትን እድገት የሚጠቁም ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ፓርቲዎችም አርአያ ለመሆን የሚበቃ ነው፡፡

እኛ የእዚህ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አባላትም በዛሬው እለት ባደረግነው አስቸኳይ ስብሰባም የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፈናል፡፡

1. የፓርቲው ብ/ም/ቤት የቀድሞው የፓርቲው ፕሬዚደንት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ተከትሎ ብ/ም/ቤቱ ባለው የጠቅላላ ጉባኤ ውክልና መሠረት ያካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ተገቢና ሕገ-ደንባዊ መሆኑን አረጋግጦ አቶ በላይ ፍቃዱን እስከሚቀጥለው የፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ የፓርቲው ፕሬዚደንት እንዲሆኑ በከፍተኛ ድምጽ ወስነናል፡፡

2. በመተዳደሪያ ደንቡ ውስጥ ከብ/ም/ቦርድ የሚፈለጉ ማብራሪያዎችን እና ሃሳቦች ተከትሎ ጠቅላላ ጉባኤው የተወሰኑ ማሻሽያዎች አድርጓል፡፡

3. መድረክን በተመለተ በፓርቲያችን ላይ የጣለውን ሁለተኛ እገዳ ተከትሎ የፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ በወሰነው መሠረት ብ/ም/ቤቱ ከመድረክ እንዲወጣ የወሰነውን ውሳኔ ተገቢ ሆኖ ስላገኘው በከፍተኛ ድጋፍ አፀድቋል፡፡

4. ገዢው ፓርቲ ህገ መንግሥቱን በመጣስ በእየእስር ቤቱ ያጎራቸውን የዴሞክራሲ አርበኞች በአስቸኳይ እንዲፈታ ጉባኤው አጥብቆ ይጠይቃል፡፡

5. የዜጎችን በነፃ የመደራጀት ነፃ አመለካከታቸውን በአምባገነንነት በማፈን ያሰራቸውን የነፃነት አርበኞች ፖለቲከኞች ፣ ጋዜጠኞች፣ ብሎገሮች፣ የቤተ እምነት መሪዎች በአስቸኳይ እንዲፈቱ እየጠየቅን መንግሥት በሩን ለብሔራዊ ውይይት ክፍት እንዲያደርግ ጉባኤው ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

6. የተቀማነውን ነፃነታችንን በድምፃችን ለማስከበር ‹2ዐዐ7 ለለውጥ› የሚል የህዝባዊ ንቅናቄ ዘመቻ አንድነት በዛሬው እለት ጠቅላላ ጉባኤው አውጇል፡፡ ስለዚህ መላ የኢትዮጵያ ሕዝብ በምርጫው በንቃት በመሳተፍ በምርጫ ካርዱ ነፃነቱን እንዲያስከብር አንድነት ፓርቲ ጥሪውን ለመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ በአክብሮት ያስተላልፋል፡፡

በምርጫው በንቃት በመሳተፍ ነፃነታችንን እናስከብር!

የአንድነት አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ታህሣሥ 3/2ዐዐ7 ዓ.ም
አዲስ አበባ

* ምርጫው ላይ ለመሳተፍ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጠናል
* በምርጫው ልንሳተፍም ሆነ ላንሳተፍ ውሳኔ የምናሳልፈው እኛ ሳንሆን ሂደቱ ነው
ትንሽ ስለ አንዳንድ ጉዳዮች ማብራሪያ አቀርባለሁ ዮናታን ተስፋዬ ረጋሣ

ኢትዮጵያ ውስጥ በህጋዊ መንገድ ተመዝግቦ የሚንቀሳቀስ ፓርቲ ምርጫ ስላለመግባቱ እንጂ ምርጫ ስለመግባቱ ዜና ሲሆን በጣም ግራ ያጋባል፡፡ ምርጫን መሳተፍ አንዱ የትግል አካል የሆነውን ያህል አለመሳተፍ የራሱ የሆነ ፋይዳ አለው፡፡ ያን የሚወስነው ግን ሂደቱ እንጂ ፓርቲዎቹም ይሁኑ ምርጫ ቦርዱ አይደለም፡፡ ከዚህ አንፃር በሂደቱ ውስጥ አንድ ፓርቲ ወይም ፓርቲዎች አንሳተፍም ሊሉ ይችላሉ (ህጋዊነትም አለው)፡፡ ምክንያታቸውንም በዝርዝር አስቀምጠው መግለጫም ይሁን ሌላ ሌላ ነገር ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ያም ዜና ከመሆን ባለፈ ባጠቃላይ የህዝቡንም የዓለም አቀፍ ማሕበረሰቡንም ትኩረት ያገኛል፡፡
ከዚህ ውጪ ግን አንዱ ያለ ቅድመ ሁኔታ ምርጫ እሳተፋለሁ ስላለ እና ሌላው ደግሞ ሂደቱ እንዲወስን እድል ስለሰጠ ምርጫ ተሳታፊና ምርጫውን የማይሳተፍ ብሎ ማቅረቡ በራሱ አንድም ስህተት ነው ሲልም ከንቱ ራስ ማዋደጃ ፕሮፖጋንዳ ነው፡፡ ይህ ግልፅ ነገር እንዲገባው ያልፈለገ እና ህመም የሆነበት ማስታገሻ ወስዶ ቢያርፍ መልካም ነው፡፡
ጓደኞቼም ሆነ እኔ ኢሳትና ቪኦኤን ጨምሮ በብዙ መገናኛ ብዙኃን እና በዲፕሎማቶች በኩል በተደጋጋሚ በምርጫው ጉዳይ ላይ ሰማያዊ ፓርቲ የያዘውን አቋም በተጠየቅንበት ወቅት የሰጠነው የማያሻማ መልስ ከላይ ያሰፈርኩትን ነው (ሚዲያዎቹ ላይ ፈልጎ መስማት ይቻላል)፡፡ ‹‹ምርጫ ለመሳተፍም ሆነ ላለመሳተፍ አሁን የመወሰኛ ጊዜ አይደለም፤ ሂደቱ እንጂ እኛ(ተቃዋሚም ይሁን ኢህአዴግ) አሁን ልንወስነው የሚገባ ጉዳይ አይደለም፡፡›› ይህ በግልፅ የሚያሳየው ነገር ሂደቱ ውስጥ ተሳታፊ እንደምንሆን ሲሆን ለመጨረሻው ውሳኔ ግን በወቅቱ የሚፈጠረው ሁናቴ እንደሚወስን ነው!
እንደ አንድ ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ የምርጫ ጉዳይ ኮሚቴና ጊዜውን መሰረት ባደረገ 70 ሰው ያቀፈ የምርጫ ግብረሃይል አቋቁመን፣ የዓመቱ እቅዳችንም በምርጫ ላይ ሆኖና በትብብሩም የጀመርነው ዘመቻ ‹‹ነፃነት ለፍትሓዊ ምርጫ›› እያለ ለምርጫ የማንዘጋጅ አስመስሎ ማቅረቡ ምንአልባት ከተሳሳተ ግንዛቤ አልያም ከተንኮል ያለፈ ሊሆን እንደማይችል ግልፅ ነው፡፡ የምርጫ ምልክትን መውሰድም የሂደቱ አካል እንጂ የመጨረሻው ውሳኔ አይደለም፡፡ ከዚህ ተነስቶም በእርግጠኛነት ምርጫ ይሳተፋሉ ብሎ መደምደም ተገቢ ነው ብዬ አላምንም! ባጠቃላይ ግን ለምርጫው ያስቀመጥናቸውን ቅድመ ሁኔዎች በሂደቱ የማይመለሱ ከሆነ ያኔ ውሳኔው ከነምክንያቱ ይፋ ይሆናል ማለት ነው፡፡
በግልፅ ቋንቋ ምርጫውን ለመሳተፋችንም ሆነ ላለመሳተፋችን አጠቃላይ ሂደቱ፣ በሂደቱ ውስጥም ያነሳናቸው ጥያቄዎችና ያስቀመጥናቸው ቅድመ ሁኔታዎች እንጂ ማናችንም ወሳኝ ልንሆን አንችልም! የምርጫ ምልክትም ስንወስድ መነሻችን ይኸው እውነታ እና ነባራዊ ሁኔታ ብቻ ነው! ይህ የኛ መንገድ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ያለ ቅድመ ሁኔታ ባለው የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ ምርጫ እሳተፋለሁ ብለው ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ምንም ይሁን ምንም፣ ሂደቱ ይመርም አይመርም ምርጫውን ለመሳተፍ ወስነው ወደ ስራ የገቡትን ውሳኔያቸውን አከብራለሁ፡፡
የመረጥነውን መንገድ መደገፍም መንቀፍም ያባት ነው፤ እየጠመዘዙ ሌላ መልክ እንዲይዝ ማድረግ ግን ራስን ከማስገመት ያለፈ ጥቅም ያለው መስሎ አይሰማኝም፡፡
(ይህ ርዕስ ከዚህ በላይ መወያያ ባይሆን ምኞቴ ነው!)
ሊንኩን በመጫን ለምርጫ ቦርድ የስገባውን ደብዳቤ እና ያስቀመጥናቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ይመልከቱ፡-
https://www.facebook.com/semayawiethio/ … =3&theater

Image
በቅርቡ የአንድ ወር መርሃ ግብር አዉጥቶ ሲንቀሳቀስ የነበረው የሰማያዊ ፓርቲና የዘጠኝ ድርጅቶች ስብስብ፣ ፓርቲዎች ትብብር፣ ያለ ቅድሜ ሁኔታ በመጪው የ2007 ምርጫ እንደሚሳተፍ አሳወቀ። ትብብሩ ለምርጫ ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጡን የምገልጹ አንዳንድ ዘገባዎች በተለይም በዳያስፖራ አካባቢ የሚሰሙ እንደሆነ ቢታወቅም፣ የትብብሩ ዋና ጸሃፊ አቶ ግርማ በቀለ በፌስ ቡክ በግልጽ በሰጡት አስተያየት፣ ትብብሩ ለምርጫ ቅድመ ሁኔታ አለማስቀመጡን ገልጸዋል።

“NO Precondition is set by members of Tibibir. We decided to be part of the election and advised all members to take their election Sign. Believe me, it is all the decision of Tibibir that is under action by its members and Blue is not an exception to present and decisions are being made in participatory process.” ሲሉ የትብብሩ አባል ድርጅቶች ለምርጫ የሚያስፈልገውን የምርጫ ምልክት በአስቸኳይ ለመዉሰድ መስማማታቸውንም አቶ ግርማ በቀለ ገልጸዋል።

በዚሁም መሰረት፣ የሰማያዊ ፓርቲንም ጨምሮ ሌሎች የትብብሩ አባል ድርጅቶች የምርጫ ምልክት ከሌሎች ድርጅቶች ቀድመው እንደወሰዱም የሚገልጹ መረጃዎች እየደረሱን ነው። ምርጫ ቦርድ ከአንድ ሳምንት በኋላ የድርጅቶቹን ምልክት ይፋ የሚያደርግ ሲሆን፣ የሰማያዊን ጨመሮ የሌሎች ድርጅቶች የምርጫ ምልክትም ምን እንደሆነ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
በዚህ ጉዳይ ላይ ያነጋገርናቸው የፖለቲካ ተንታኝ የትብብሩን ዉሳኔ አስፈላጊና ጠቃሚ ዉሳኔ ሲሉት፣ ሰማያዊ/ትብብሩ ወደ ምርጫ ያለ አንዳች ቅድሜ ሁኔታ ለመሳተፍ በመወሰኑም፣ በምርጫው ረገድ ከአንድነት ፓርቲ ተመሳሳይ አቋም እንደያዘ በግልጽ ያመላከት እንደሆነም አስረድተዋል።

“ያለ ቅድመ ሁኔታ ወደ ምርጫ ለመግባት ሰማያዊ/ትብብር ከወሰኑ፣ ለምርጫው መዘጋጀት አለባቸው። ድርጅታዊ ሥራ ላይ ማተኮሩ የድግ ነው። ተመሳሳይ ፕሮግራም ካላቸው ከነ አንድነት ጋር በምርጫው ረገድ መተባበር ያስፈልጋቸዋል” ሲሉ እኙ ተንታኝ ትብብሩ ወደ ምርጫ ከገባ ዘንዳ የምርጫ ዘመቻውን አብሮ ከሌሎች ጋር ለማቀናጀት እንዲዘጋጅም ጠይቀዋል።

በተያይዘ ዜና የአንድነት ፓርቲ የምርጫ ታዛቢዎች በማስመረጥ ዙሪያ በተቻለ መጠን ገለልተኛ የሆኑ የሕዝብ ታዛቢዎች እንዲመረጡ ለማድረግ በየዞኖቹና በየወረዳዎች ስምሪት እንደጀመረም ለማወቅ ችለናል።

አቡጊዳ

አቶ ሽመልስ ከማል ከአቶ ሬድዋን ሁሴን ጋር በመጋጨታቸው አኩርፈው ቤት መቀመጣቸው ተሰማ

የመንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት አቶ ሽመልስ ከማል ከ ሚኒስትሩ ሬድዋን ሁሴን ጋር መግባባት ባለመቻላቸው አኩርፈው ቤት በመቀመጥ መደበኛ ሥራቸውን እያከናወኑ አለመሆኑን ምንጮች ገልጸዋል።

አቶ ሽመልስ ከደባል ሱስ ጋር በተያያዘ በመደበኛ የስራ ሰዓታቸው ሊገኙ ባለመቻላቸው ሚኒስትሩ ይህን ባህሪያቸውን እንዲያስተካክሉ ቢነግሩዋቸውም ሊያስተካክሉ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የተፈጠረ መሆኑን ምንጮች ይገልጻሉ።የአቶ ሽመልስን ሃላፊነት ደርበው እየሰሩ ያሉት በቅርቡ ከዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዳይሬክተርነት ተነስተው የመንግስት ኮምኒኬሽን ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን የተሾሙት አቶ እውነቱ ብላታ ናቸው።

አቶ ሽመልስ በቅርቡ የታዩት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ ሊቀመንበር በመሆናቸው በድርጅቱ ስብሰባ ላይ ብቻ ነው፡፡ የፕሬስ ድርጅት ስራ አስኪያጅ አቶ ሰብስቤ ከበደ ከአቅም ማነስና የመልካም አስተዳደር ችግር ጋር ተያይዞ በድርጅቱ ጋዜጠኞች እየቀረበባቸው ያለውን ግልጽ ትችትና ቅሬታ በተደጋጋሚ ስብሰባዎች ላይ በመገኘት ከማስተባበላቸውም በተጨማሪ ጥያቄውን የሚያነሱ ጋዜጠኞችን እስከማስፈራራት የደረሰ ንግግር ሲያደርጉ የተሰሙት አቶ ሽመልስ፣ መደበኛ ስራቸውን መተዋቸው በኮምኒኬሽን መ/ቤቱ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖአል፡፡

አቶ ሽመልስ ከማል በአቶ በረከት ስምኦን ደጋፊነት የብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ስራአኪያጅ የነበሩ ሲሆን፣ የ97 ምርጫን ተከትሎ የቅንጅት አመራሮችና ጋዜጠኞች በተከሰሱ ወቅት አቃቤ ሕግን ወክለው ሐሰተኛ መረጃዎች እንዲቀርቡና ሐሰተኛ ምስክሮችን በገንዘብ በመግዛትና በመደለል ለኢህአዴግ ውለታ ለመስራት የጣሩ ሰው መሆናቸው ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጅ አቶ በረከት ከጤና ጋር በተያያዘ ስራቸውን እየተዉ በመምጣታቸው አቶ ሽመልስ ብቸኛው ደጋፊያቸውን አጥተዋል። አቶ ሽመልስ አቶ በረከትን የመተካት ህልም ቢኖራቸውም ሳይሳካላቸው አቶ ሬድዋን ቦታውን እንዲወስዱ ተደርጓል። በሁለቱ ባለስልጣኖች መካከል ባለው ልዩነት የተነሳ፣ አቶ ሽመልስ ከስራቸው የሚባረሩበት ቀን እሩቅ ላይሆን እንደሚችል ወይም በገዛ ፈቃዳቸው ስራቸውን በመልቀቅ ከአገር ለመውጣት ሙከራ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ታዛቢዎች ይገልጻሉ። የአቶ ሽመልስ የስልጣን ቆይታ በከፍተኛ ህመም ከሚሰቃዩት ከአቶ በረከት ስምኦን ህልውና ጋር የተያያዘ መሆኑን ታዛቢዎች ይናገራሉ።

ታኀሳስ ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና

Image

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰማያዊ ፓርቲ የፋይናንስ ጉዳይ ኃላፊ የሆኑትን አቶ ወሮታው ዋሴን ከስራ አባረረ፡፡ ‪
ከሁለት አመት በፊት በኢሜል ለህዳሴው ግድብ ገንዘብ እንዲያዋጡ በተጠየቁበት ወቅት ለተላከው የኢሜል መልዕክት አልከፍልም ብለው በመመለሳቸው ‹‹ሰራተኛ በማሳመጽ፣ የኢንዱስትሪ ሰላም በማናጋት›› በሚል ተከሰው ተባርረው በፍርድ ቤት ወደ ስራ መመለሳቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡አቶ ወሮታው ከስራ የተባረሩት ጥፋት ያጠፋን ሰራተኛ አልቀጣህም በሚል ሲሆን በእሳቸው ስር የነበረውና አጠፋ የተባለው ሰራተኛ ጉዳይ ተመርምሮ ወደ ስራ መመለሱ ታውቋል፡፡
Image

አቶ ወሮታው ከእሳቸውም በላይ ጉዳዩ የሚያገባው የማኔጅመንት አባል በተመሳሳይ ጉዳይ የአምስት ቀን ደመወዝ ብቻ ሲቀጣ እሳቸው ከስራ መባረራቸው በፖለቲካ አመለካከታቸው ላይ የተመሰረተና ፖለቲካዊ ውሳኔ እንደሆነ ያሳያል ብለዋል፡፡ ከስራቸው ይሰራ የነበረው ሰራተኛ ጥፋተኛ አለመሆኑን የገለጹት አቶ ወሮታው ‹‹በፖለቲካ አመለካከቴ ምክንያት ሁልጊዜም እኔን ማባረር ይፈልጋሉ›› ሲሉ የተባረሩት በፖለቲካ አመለካከታቸው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

አቶ ወሮታው ዋሴ ከሁለት አመት በፊት በኢሜል ለህዳሴው ግድብ ገንዘብ እንዲያዋጡ በተጠየቁበት ወቅት ለተላከው የኢሜል መልዕክት አልከፍልም ብለው በመመለሳቸው ‹‹ሰራተኛ በማሳመጽ፣ የኢንዱስትሪ ሰላም በማናጋት›› በሚል ተከሰው ተባርረው ከሁለት አመት በኋላ በፍርድ ቤት ወደ ስራ መመለሳቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በወቅቱ አየር መንገድ አቶ ወሮታው ዋሴ ካሳ ተከፍሏቸው እንዲለቁ ይግባኝ ጠይቆ የነበር ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለሁለት አመት ካራዘመ በኋላ ወደ ስራ እንዲመለሱ አዝዞ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ ጥፋተኛ ነው ብሎ ያባረራቸው አየር መንገድ ወደ ስራ በተመለሱ በ15 ቀናት ውስጥ ሰርተውበት ወደማያውቁት ክፍል በማዘዋወር እድገት አግኝተው የማኔጅመንት አባል እንደሆኑ እንደገለጸላቸው የሚናገሩት አቶ ወሮታው እድገቱ ሰራተኛ ሲባረር የመክሰስ መብት ስላለው፣ በተቃራኒው ግን ሳይፈልጉት በእድገት የማኔጅመንት አባል እንዲሆኑ የተደረገው የማኔጅመንት አባል የሆነ ግለሰብ ቢባረርም የመክሰስ መብት የሌለው በመሆኑ ሆን ተብሎ ለማባረር የተደረገ ስልት ነው ብለዋል፡፡ አቶ ወሮታው በወቅቱ ይህን እድገት አልቀበልም ብለው እንደነበርም ገልጸውልናል፡፡

አቶ ወሮታው ዋሴ አሁን ከስራ ባባረራቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ለ14 ዓመታት ያህል ማገልገላቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

Image

በአፈና፣ በኃይል እርምጃና በውንብድና መብታችንን ለድርድር አናቀርብም!
ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሰጠ መግለጫ ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎NegereEthiopia‬ ‪#‎Miniliksalsawi‬

• ትግሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
እኛ 9 ፓርቲዎች በትብብር ለመሥራት በፈጸምነው ስምምነት ያወጣነውን የጋራ ዕቅድ ለማስፈጸም ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ስንገባ ህገ መንግስቱ፣ የምርጫና የሰላማዊ ሠልፍና ህዝባዊ ስብሰባ አዋጆች በሚፈቅዱት መሰረት ያቀረብናቸውን ጥያቄዎች በቢሮክራሲያዊ ሴራና ማስፈራራት ለማፈን የአዲስ አበባ መስተዳድር የተከተለውን ህገወጥ አካሄድና ይህንኑ ተከትሎ የተወሰዱትን የኃይል እርምጃዎች በሚመለከት ፡-

1ኛ/ ‹‹በቢሮክራሲያዊ ሴራ የዜጎችን ህገመንግሥታዊ መብት ማፈን ሠላማዊ ትግሉን አያቆመውም !!››በሚል ርዕስ ሕዳር 08 ቀን 2007 ዓ.ም.
2ኛ/ ‹‹ማስፈራራትና አፈና የዲሞክራሲ ጥያቄዎችንና ሠላማዊ ሕዝባዊ የለውጥ ንቅናቄዎችን አይቀለብስም!!›› በሚል ርዕስ ሕዳር 17 ቀን 2007 ዓ.ም. መግለጫዎች ማውጣታችን፣ እንዲሁም በአባል ፓርቲዎቻችንን አማካኝነት –
1. ‹‹ የህገ መንግሥቱ የበላይነትና የዜጎች ህገ መንግሥታዊ መብት እንዲረጋገጥ ›› ለተከበሩ የተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ፣
2. ‹‹በአገሪቱ ህገመንግሥትና ህጎች የተረጋገጡ የዜጎች መብቶች እንዲተገበሩ ›› ለተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ህዳር 24/2007 ዓ.ም ጥያቄ ማቅረባችንና በግልባጭ ለ- ኢትዮጵያ ሰብዐዊ መብት ኮሚሽን፣- የህዝብ እንባ ጠባቂና -ሰብዐዊ መብት ጉባኤ ማሰማታችን ይታወሳል፡፡
የእነዚህ መግለጫዎችም ሆነ ደብዳቤዎች ይዘት ሲጠቃለል ‹‹የአገሪቱ ህገመንግሥት ይከበር ›› የሚል ጥያቄና መስተዳደሩ በሚወስዳቸው ህገወጥ እርምጃዎች ከያዝነው ህጋዊና ሠላማዊ ትግል የማናፈገፍግና የትኛውንም መስዋዕትነት በመክፈል ለህገመንግሥታዊ መብታችን መከበር የጀመርነውን የጋራ ትግል እንደምንገፋበት፣ የአዲስ አበባ መስተዳድር ከህገ ወጥ ድርጊቱ እንዲታረም፣ ጥሪ ማቅረብና ግልጽ አቋማችንን ማሳየት ነበር፡፡ በዚሁ ሂደት ያጋጠሙንን ህገወጥ ድርጊቶች በሙሉ በዝርዝር ለህዝባችንና ለባለድርሻ አካላት በሙሉ በፕሬስ ሬሊዞችና ዕለታዊ የውሎ ዘገባና ዜናዎች አድርሰናል፡፡ ግን ሰሚ ጆሮ ሊናገኝ አልቻልንም፡፡ የአዲስ አበባ መስተዳድር የመረጠው መንገድ ለጥያቄዎቻችንና ጥሪዎቻችን ተገቢውን ህጋዊ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ በህገ ወጥ ድርጊቱ መግፋትና ጥያቄዎቹን በኃይል እርምጃ ማፈን ነው፡፡ አፈ ጉባኤውም ሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምንም ባለማለታቸው መስተዳድሩ ‹‹በያዝከው ግፋበት ፈቃድ›› በማግኘቱ ለበለጠ ህገወጥነትና የኃይል እርምጃ በመበረታታት ለህዳር 27 እና 28 ቀን 2007 በጠራነው ህጋዊ ሠላማዊ ሠልፍ ሂደት ላይ በሰጠው ከመንግሥት የማይጠበቅ የቅጥፈት መግለጫ ፣ በዕለቱ በሠላማዊ ዜጎች ላይ በተወሰደው አረመኔኣዊ እርምጃና ጥይት እራሱ ገሎ እራሱ ይጮኃል እንዲሉ በንጹኃን የመብት ጠያቂ ዜጎች ላይ የተለመደውን የፈጠራ ክስ ለመፈብረክ በተጠቀመው ነጭ ውሸት አረጋግጧል ፡፡ የአብነት ማሳያዎችም–
1. ኢቲቪ/ኢብኮ/ ሰሚ ባላገኘው የ‹‹ማስፈራሪያ›› ማስጠንቀቂያው ‹‹በሌላ ቦታ እንዲያደርጉ›› የቀረበላቸውን አማራጭ ባለመቀበልና እዚያው ካልሆነ ሞተን እንገኛለን በማለት ‹‹አሉ›› ያለው እኛ ዓርብ(26/03/07) ከሰዓት በኋላ እስከ ቀኑ 10፡30 ድረስ ውሳኔ ከማይሰጡ (ሥልጣኑ ከሌላቸው) የመስተዳድሩ ሹማምነት ጋር ቆይተን ‹‹የማሪያም በር›› ልንሰጣቸው ከሞከርነው ጋር የማይጣጣምና መግለጫው ‹‹ ባይበላስ ቢቀር›› የሚያስብል መሆኑ፤
2. ከ80 በላይ ንጹኃን የመብት ጤቂ ዜጎች ላይ የተፈፀመው እስራትና ከ50 በላይ በሆኑት ላይ የ ለማመንና መቀበል የሚያስቸግርና (በተለይ በሴት እህቶቻችን ላይ)አረመኔያዊ ድብደባ (ፖሊስ ጣቢያ ግቢ ውስጥ ጭምር) በተፈጸመበት የተሞከረው ‹‹ ከባድ የኮንስትራክሽን መሣሪያ በኪሳቸው ደብቀው›› ልማቱን አደናቀፉ ዓይነት የፈጠራ ውንጀላና ክስ ማቅረባቸውን፤ መጥቀስ ብቻ ይበቃል፡፡
በመሆኑም መስተዳድሩ ከሠልፉ ዕለት በፊትና እስከዛሬ እነዚህን ዓይን ያወጡ ህገመንግሥቱን የደፈጠጡ የአደባባይ እውነታዎች ለመሸፈን በፓርቲዎች ላይ በተለመደው መንገድ በህዝብ ሃብት የሚተዳደሩትን የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን በተለይም ኢቲቪ/ኢብኮ/ በመጠቀም በሰራው የበሬ ወለደ ፕሮፖጋንዳ ማንነቱን ፍንትው አድርጎ ለህዝብ አሳይቷል፣ ራቁቱን አስቀርቶታል፣ተጋልጦበታል፡፡
በእኛ በኩል ከሂደቱም ሆነ ከተወሰደው እርምጃና ከተሞከረው ርካሽ ፕሮፖጋንዳ ለቀጣዩ የጋራ ትግላችን ብዙ ተምረንበታል፤ አስተምረናል፣አትርፈንበታል እንጂ ከዓላማችን አልተገታንም፣ ቃላችንን አላጠፍንም፡፡በመሆኑም
1. ከዚህ በኋላ ለሰልፍም ሆነ ስብሰባ ገዢው ፓርቲ በዘመናት በማለማመድ ፈቃጅ ሆኖ ለመታየት ያደረገውን ጥረት ሰብረን ዕውቅና ከመስጠት ያለፈ ህጋዊ ሥልጣን የሌለው መሆኑን እንዲያውቅ/እንዲማር አድርገናል፤
2. በማስፈራራት ትግሉን መግታት እንደማይቻልና ለዚህም ለነጻነታቸውና ክብራቸው የቱንም መስዋዕትነት ለመክፈል የተዘጋጁ ታጋዮች በተለይም ወጣቶች መኖራቸውን አሳይተናል፤
3. የህዝቡ የለውጥ ፍላጎት የደረሰበትን ደረጃና የንቃተ ኅሊና መዳበር ከክልል ጭምር በመምጣት በጋራ ትግሉ በመሳተፍና የትግል አጋርነታቸውን በመግለጽ ባደረጉት አስተዋጽኦና በመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ፕሮፖጋንዳ ያለው እምነት መሟጠጡን ፣እንዲሁም የገዢው ፓርቲ በሠላማዊ ትግል ያደረበትን የፍርኃትና ሥጋት ደረጃ ለክተንበታል፤
4. ህዝቡ ለፈጠራ ወንጀሎች እንዳይፈራና ይልቁንም በመንግሥት አሠራርና አመራር ላይ ያለው እምነት ከጥያቄ እንዲወድቅ፤ፖሊስንና ፍርድ ቤቶችን ጨምሮ አስፈጻሚ አካላት ያለባቸውን ተጠያቂነት እንዲረዱና ራሳቸውን እንዲጠይቁ የሚያስችል ስሜት ፈጥረናል፤
በአጠቃላይ የገዢውን ፓርቲ እየባሰ የመጣውን አምባገነናዊ ባህሪይ አጋልጠን ፣ኢትዮጵያዊያን ለተባበረ የጋራ ትግል ያላቸውን ድጋፍ በተግባር ተመልክተን፣ የጀመርነው የ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› ፕሮግራማችንን ትክክለኛለትና ተቀባይነት ለክተን ትግሉ ወደማይቀለበስበት የላቀ ደረጃ መሸጋገሩን አረጋግጠናል፡፡ስለሆነም የጋራ ትግላችንን አጠናክረን በበለጠ ጽናትና የኃላፊነት መንፈስ በጥበብ በመምራት እንደምንቀጥል እያረጋገጥን የሁለተኛውን ዙር ፕሮግራም ዕቅድ በቅርብ ጊዜ እንደምናሳውቅ እየገለጽን –
1ኛ/ በአገር ቤትና በውጪ የምትገኙ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ከጎናችን በመቆም ላደረጋችሁት ሁለንተናዊ ድጋፍ፣ በአምባገነኑ ሥርኣት የተወሰደብንን አረመኔያዊ እርምጃ በመቃወም በሰልፍ፣ በመግለጫ፣በታሰርንበት አስፈላጊውን በማቅረብና ተመላልሳችሁ በመጠየቅ … የትግሉ ባለቤትነታችሁን ላረጋገጣችሁና አጋርነታችሁን ለገለጻችሁና ላኮራችሁን ክፍ ያለ ምስጋናችን እያቀረብን፣በዚህ ረገድ ድምጻችንን ከህዝባችንና ከዓለም ህዝብ ዘንድ በማድረስ ፣ከወገኖቻችን ጋር በማወያየት ከፍተኛውን ሚና ለተጫወታችሁ በአገር ቤትና በውጪ ለምትገኙ መገናኛ ብዙኃን አድናቆታችንን እየገለጽን በቀጣዩ ፕሮግራማችንም ከጎናችን እንድትቆሙ ፣
2ኛ/ገዢው ፓርቲ/መንግሥት የወሰደውን ኢህገመንግሥታዊና ህገወጥ እርምጃና አሰራር አጥብቀን እየተቃወምን፣ይህ ዓይነቱን ለማንም የማይበጅ አካሄድ መርምሮና የህዝቡን የለውጥ ፍላጎት ተረድቶ ቆም ብሎ ራሱን እንዲፈትሽ፣ከገባበት ፍርኃትና ሥጋት ተላቆ ለህዝብ ጥያቄዎች ተገቢውን ወቅታዊ ምላሽ በመስጠት ህገመንግሥቱን አክብሮ እንዲያስከብር፤
3ኛ/ የዓለም አቀፉ ማኅበረ ሰብ አባላትም ተገቢውን አዎንታዊ ተጽዕኖ በገዢው ፓርቲ/መንግሥት ላይ በማሳረፍ ለሰብዐዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መከበርና ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድታበረክቱ፤ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ያለመስዋዕትነት ድል የለምና ትግሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

Image

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ሁለተኛ ዙር መርሓ ግብሩን በቅርቡ እንደሚጀመር አስታወቀ
‹‹ገዥው ፓርቲ ከፍርኃት ተላቆ ለህዝብ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት አለበት!››

ከህዳር ወር 2007 ዓ.ም ጀምሮ የአንድ ወር መርሓ ግብር ነድፎ ሲንቀሳቀስ የቆየው የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር በዛሬው ዕለት ታህሳስ 5/2007 ዓ.ም ‹‹በአፈና፣ በኃይል እርምጃና በውንብድና መብታችንን ለድርድር አናቀርብም!›› በሚል ባወጣው መግለጫ ሁለተኛ መርሓ ግብሩን በቅርብ ቀን ይፋ እንደሚያደርግ ገልጾአል፡፡

መግለጫው ለህዳር 7/2007 ዓ.ም ታቅዶ የነበረው ህዝባዊ አደባባይ ስብሰባ፣ እንዲሁም ለህዳር 27/28 2007 ዓ.ም ታቅዶ የነበረው የአዳር ሰልፍ በገዥው ፓርቲ የፖሊስና የደህንነት ኃይሎች እንደተበተነ የሚታወቅ ሲሆን ትብብሩ መርሓ ግብሮቹን ለማስፈጸም ህጋዊ መንገድ ቢከተልም በወቅቱ ስርዓቱ የወሰደውን ህገ ወጥ እርምጃ በዝርዝር አስቀምጧል፡፡

ትብብሩ በመግለጫው በአንዱ ወር መርሓ ግብር ወቅት ስርዓቱ አፋኝ እርምጃዎችን ቢወስድም ገዢው ፓርቲ በዘመናት በማለማመድ ፈቃጅ ሆኖ ለመታየት ያደረገውን ጥረት ሰብሮ ዕውቅና ከመስጠት ያለፈ ህጋዊ ሥልጣን የሌለው መሆኑን እንዲያውቅ ማድረጉን፣ በማስፈራራት ትግሉን መግታት እንደማይቻልና ለዚህም ለነጻነታቸውና ክብራቸው የቱንም መስዋዕትነት ለመክፈል የተዘጋጁ ታጋዮች በተለይም ወጣቶች መኖራቸውን እንዳሳየበት ገልጾአል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የህዝቡ የለውጥ ፍላጎት የደረሰበትን ደረጃና የንቃተ ኅሊና መዳበር፣ ህዝቡ ለፈጠራ ወንጀሎች እንዳይፈራና ይልቁንም በመንግሥት አሠራርና አመራር ላይ ያለው እምነት ከጥያቄ እንዲወድቅ፣ ፖሊስንና ፍርድ ቤቶችን ጨምሮ አስፈጻሚ አካላት ያለባቸውን ተጠያቂነት እንዲረዱና ራሳቸውን እንዲጠይቁ የሚያስችል ስሜት ፈጥሬበታለሁ ብሏል፡፡

‹‹የገዢውን ፓርቲ እየባሰ የመጣውን አምባገነናዊ ባህሪይ አጋልጠን፣ ኢትዮጵያዊያን ለተባበረ የጋራ ትግል ያላቸውን ድጋፍ በተግባር ተመልክተን፣ የጀመርነው የ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› ፕሮግራማችንን ትክክለኛለትና ተቀባይነት ለክተን ትግሉ ወደማይቀለበስበት የላቀ ደረጃ መሸጋገሩን አረጋግጠናል፡፡›› ያለው ትብብሩ የጋራ ትግሉን በበለጠ ጽናትና የኃላፊነት መንፈስ በመምራት የሁለተኛ ዙር እቅዱን በቅርብ ቀን ይፋ እንደሚያደርግ ገልጾአል፡፡

ትብብሩ በአንድ ወሩ መርሓ ግብር ወቅት በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላደረጉለት ሁለንተናዊ ድጋድ፣ በስርዓቱ እርምጃ በመቃወም በሰልፍ፣ በመግለጫ፣ በታሰርንበት አስፈላጊውን በማቅረብና በመጠየቅ ላደረጉት ትብብር ምስጋናውን አቅርቧል፡፡ በተመሳሳይ የወሩ መርሓ ግብር ከተጀመረ አንስቶ ጉዳዩን ለህዝብ ለማሳወቅ የጣሩትን በአገር ቤትና በውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን፤ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ በማመስገን በቀጣዩ ፕሮግራም ከጎኑ እንዲቆሙ ጥሪ አስተላልፏል፡፡

በሌላ በኩል ገዥው ፓርቲ ‹‹ለማንም የማይበጅ አካሄድ መርምሮና የህዝቡን የለውጥ ፍላጎት ተረድቶ ቆም ብሎ ራሱን እንዲፈትሽ፣ ከገባበት ፍርኃትና ሥጋት ተላቆ ለህዝብ ጥያቄዎች ተገቢውን ወቅታዊ ምላሽ በመስጠት ህገ መንግሥቱን አክብሮ እንዲያስከብር›› ሲል ጥሪ አቅርቧል፡፡

Image

የመድረክ የወጣቶች ክንፍ ከፖሊስ እና ከፀጥታ አካላት እጅና ጓዋንት ሆኖ የክትትል፤ የኢንተለጀንስ እና የቁጥጥር ስራውን በአግባቡ እንዲሚወጣ ለመግለፅ እንፈልጋልን፡፡ የሚል የህዝብ ግንኙነት ስራ ትዝብት ውስጥ የጣለው የመድረክ ፓርቲ ከገንፍሌ ተነስቶ፣ በኣዋሬ ኣልፎ በየካ ክፍለ ከተማ የሚገኝ ኳስ ሜዳ መጨረሻው ያደረገው ሰለማዊ ሰልፍ ተጠናቀቀ።
Image

በዘጠኙ ፓርቲ ላይ የደረሰውን እስር ድብደባ እና እንግልት እንዳላወገዘ የሚነገርለት መድረክ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ሁለት ሺህ የሚጠጋ የኣዲስ ኣበባ ኑዋሪ የተሳተፈበት ሰልፍ በወጣቶች የመድረክ ኣመራር፣ የሴቶች ተወካይ፣ ኣቶ ቡልቻ ሚደቅሳና የወቅቱ የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ዼጥሮስ ባሰሙት ንግግሮች ተጠቃሏል።
ሰለማዊ ሰልፉ የኢህኣዴግ መንግስት ሊያርማቸው የሚገቡ፣ መመቻቸት ያሉባቸው ፖለቲካዊ ምህዳር፣ መወገድ ያለበት የፀረ ሽብር ህግ ፣ ምርጫው ፍትሃዊ እንዲሆን ሊያደረጉ የሚገቡ ስራዎች እንዲሰሩ፣ በየቦታው እያጋጠመ ያለው ዓፈና፣ እስርና እንዲሁም ግድያዎች እንዲቆሙ ጥሪ ቀርበዋል።
Image
የመድረክ ኣመራሮችና ወጣቶች እየመሩት የተካሄደው የሰለማዊ ሰልፉ ዓላማዎች የምያንፀባርቁ መፈክሮች በወጣቶች ኣባላት ተነበዋል። ከመፈክሮቹ

1- ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በነፃና ፍትሐዊ ምርጫ እንጂ በአስመሳይ ፕሮፓጋንዳ፣ በኃይልና በተጽኖ አይገነባም!!

2- የሀገራችን ችግሮች በነፃና ፍትሐዊ ምርጫ በሚገለጽ የሕዝብ ውሳኔ እንጂ በኃይል እርምጃ አይፈቱም!!

3- ከምርጫ በፊት የምርጫ ውድድር ሜዳው የሚስተካከልበት ውይይትና ድርድር እንዲካሄድ አጥብቀን እንጠይቃለን!!

4- በማስመሰያ ምርጫ በየአምስት አመቱ ሕዝብን ማታለልና ሀብቱን ማባከን ይቁም!!

5- የማስመሰያ ምርጫ ለማካሄድ ለሚባክነው የሀገርና የሕዝብ ሀብት ኢህአዴግ ተጠያቂ ነው!!

6- ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ በሌለበት ሁኔታ የሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት እውን ሊሆን አይችልም!!

7- ሕዝባችን በ1ለ5 መረብ አፈናና ቁጥጥር ከሚካሄድ የምርጫ ድምጽ አሰጣጥ ነፃ እንዲሆን እንጠይቃለን!!

8- ያለገለልተኛ የምርጫ አስተዳደርና ያለገለልተኛ የምርጫ ታዛቢ ታአማንነት ያለው ምርጫ ሊኖር አይችልም!!

9- ገለልተኛ የምርጫ ቦርድ በፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎ ይቋቋም!!

10- በካድሬዎች የሚከናወን የምርጫ አስፈጻሚነትና ታዛቢነትን አንቀበልም፣ እናወግዛለን!!

11- ነፃ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ታዛቢዎች ምርጫውን በነፃነት የሚከታተሉበትና የሚታዘቡበት ሁኔታ
እንዲመቻች እንጠይቃለን!!

12- በምርጫ ወቅት በታጠቀ ኃይል በሕዝባችን ላይ የሚፈጸም ማስፈራሪያና ወከባን እናወግዛለን!!

13- በሰላማዊ ተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ላይ የሚካሄድ እስራትና ወከባ በአስቸኳይ ይቁም!!

14- ኢህአዴግ በመንግሥት ሀብትና ንብረት የሚያከሄደውን ሕገወጥ የምርጫ ዘመቻ እናወግዛለን!!

15- የጸጥታ ኃይሎች የሕዝብ አገልጋዮች እንጂ ሕዝብን ማስፈራሪያና ማሸማቀቂያ መሆን የለባቸውም!!

16- ያልተሟላ የምርጫ ሥነምግባር ኮድ ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ ለማካሄድ አያስችልም!!

17- ከድምጽ መስጫ ጣቢያዎች የተቃዋሚ ፓርቲ ታዛቢዎችን ማባረር የሕዝብን ድምጽ ለመስረቅ ስለሆነ በአስቸኳይ
እንዲቆም እንጠይቃለን!!

18- የሕዝብን ድምጽ መዝረፍ ዴሞክራሲን መገንባት ሳይሆን መቅበር ነው!!

19- የምርጫ ጣቢያዎች ከአስተዳደር አካላትና ከታጣቂ ሠራዊት ተጽኖና አፈና ነፃ ይሁኑ!!

20- በምርጫ ወቅት በምርጫ ጉዳዮች ፈጣን ውሳኔ የሚሰጡ ነፃና ገለልተኛ ዳኞች በየደረጃው እንዲኖሩ እንጠይቃለን!!

21- ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን ማሰር፣ ማሰቃየትና መግደል ሕዝባችን በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የሥልጣን ባለቤት ለመሆን
የሚያካሄደውን ትግል አይገታም!!

22- ሀሳብን የመግለጽ ሕገመንግስታዊ መብታቸውን በመጠቀማቸው የታሰሩ የሕልና እስረኞች በሙሉ በአስቸኳይ ይፈቱ!!

23- በግፍ የታሰሩ ሰላማዊ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት፣ ጋዜጠኞችና የሙስሊሙ ማሕበረሰብ መፍትሔ አፈላላጊዎች በአስቸኳይ ይፈቱ!!

24- የፀረ-ሽብር ሕጉን ለፖለቲካ ዓላማ መጠቀሚያ ማድረግን እናወግዛልን!! ሕገ-መንግሥታዊ መብትን በማይጥስ
ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲሻሻልም እንጠይቃለን!!

25- የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ለገዥው ፓርቲ የሚያሳዩትን ወገንተኝነት በአስቸኳይ ያቁሙ!!

26- ሁሉም ፓርቲዎች በሕጋዊና ፍትሐዊ አግባብ ከመንግሥት በጀት ድጋፍ የሚያገኙበት ሥርዓት እንዲኖር አጥብቀን እንጠይቃለን!

27- በነፃነት የመሰብሰብና የመደራጀት መብታችን ይከበር!!

28- የአንድ አምባገነን ፓርቲ ሳይሆን ትክክለኛ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት እንሻለን!!

29- ኢህአዴግ ለሕገመንግሥትና ለሕግ ተገዥ በመሆን ለነፃ ምርጫ እራሱን እንዲያዘጋጅ እንጠይቃለን!!

30- የሕግ የበላይነት ባልተከበረበት ሁኔታ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት አይቻልም!!

31- የኑሮ ውድነቱና የተጎሳቆለው የሕዝባችን ሕይወት የኢህአዴግ የኢኮኖሚና ማሕበራዊ ፖሊሲ ውጤቶች ናቸው!!

32- በወገንተኝነትና በአድልኦ በሕዝባችን ላይ የሚጫን ግብር በአስቸኳይ ይስተካከል!!

33- በልማት ስም በሕገወጥና ግብታዊ በሆነ መንገድ ሕዝብን ማፈናቀልና ለችግር ማጋለጥ እንቃወማለን!!

34- የመሬት ወረራ ይቁም!!

35- በሙስና የተዘረፈው የሕዝብ ሀብት ለሕዝቡ ይመለስ!! ሙሰኞችም ለፍርድ ይቅረቡ!!

36- የውኃ፣ የማብራት፣ የትራንስፖርትና የስልክ አገልግሎቶች ችግሮቻችን በአስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጣቸው እንጠይቃለን!!

37- የአህአዴግ አገዛዝ በሐይማኖቶች የውስጥ ጉዳዮች የሚፈጽማቸውን ጣልቃ ገብነቶች እናወግዛለን!!
እነዚህ መፈክሮች ለመላ ዓለም ይሰራጫሉ ተብለው ይጠበቃል።

ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማያም ደሳለኝና ዉሸታቸዉ

ጠቅላይ ሚኒስቴሩ የሚናገሯቸዉ ንግ ግሮች በጣም አሳፍሪ ናቸዉ። አቶ ሐይለማሪያም ሰብእናቸዉ የተዛባ ነዉ፣እፍረት ከሚባል የህሊና ሚዛን አፈንግጠዋል፣ አገራችንና ህዝባችንን ወክለዉ በአለም መድረክ ላይ መንቀሳቀሳቸዉ ብሔራዊ ዉርደት ነዉ የሚሉ ብዙ ናቸዉ።
ከታች ያለዉን ሊንክ በመጫን የተዘጋጀዉን ልዩ ፕሮግራም ያዳምጡ።

http://goo.gl/sIujv2
http://goo.gl/sIujv2
ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማያም ደሳለኝና ዉሸታቸዉ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ የሚናገሯቸዉ ንግ ግሮች በጣም አሳፍሪ ናቸዉ። አቶ ሐይለማሪያም ሰብእናቸዉ የተዛባ ነዉ፣እፍረት ከሚባል የህሊና ሚዛን አፈንግጠዋል፣ አገራችንና ህዝባችንን ወክለዉ በአለም መድረክ ላይ መንቀሳቀሳቸዉ ብሔራዊ ዉርደት ነዉ የሚሉ ብዙ ናቸዉ። ከታች ያለዉን ሊንክ በመጫን የተዘጋጀዉን ልዩ ፕሮግራም ያዳምጡ። http://goo.gl/sIujv2 http://goo.gl/sIujv2

Image

‪#‎stopbanningofhijab‬

መንግስት በሰኪዩላሪዝም ሽፋን ህዝብን ሀይማኖት አልባ ለማደረግ የጀመረውን እንቅስቃሴ በአስቸኳይ ያቁም!

የኢፌድሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 90(2) የሚደነገገው ትምህርት በማናቸውም ረገድ ከሃይማኖት፣ ከፖለቲካ አመለካከቶች እና ከባህላዊ ተጽእኖዎች ነጻ በሆነ መንገድ መካሄድ እንዳለበት ያስቀምጣል። የዚህን አንቀጽ ቀጥተኛ ትርጓሜ ስንመለከት በትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚሰጥ ትምህርት አንድን ሃይማኖት፣ የፖለቲካ ፓርቲ አቋም ወይም የተወሰነ ማህበረሠብን ባህልና እሴት ማንጸባረቅ አይኖርበትም። በተጨማሪም የአንቀጹን ትርጓሜ በምንመለከትበት ወቅት አንቀጹ ”ትምህርት” እንጂ የትምህርት ተቋማት እንደማይል እንገነዘባለን::

ይህም የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና ሀገራችን የብዙ ብሄር ብሄረሰቦችና የተለያዩ ሀይማኖት ተከታዮች በእኩልነት ተቻችለውና ተከባብረው የሚኖሩባት ስለሆነች ሁሉም የሃገሪቷ ዜጎች ትምህርት ላይ እኩል ተጠቃሚ እንደሆኑም ጭምር የሚያረጋግጥልን አንቀጽ ነው::

በአሁን ሰዓት የመንግስት አካላት ይህን አንቀጽ በመጥቀስ ተማሪዎች በትምህርት ተቋማት ውስጥ ሃይማኖታዊ ቀኖናዎችንና ማንነታቸውን እንዳተገብሩ እየከለከሉ ይገኛሉ፡፡ ይህን የህገ መንግስቱን አንቀጽ በሚቃረን ሁኔታ የትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መመሪያ ላይ የራሱን ስልጣን በመጠቀም ትምህርት የሚለውን የትምህርት ተቋም የሚል ትርጓሜ ሰጥቶት የግልም ሆነ የጋራ(ስብስብ) ሀይማኖታዊ ቱፊቶችን(አለባበስ፣ አመጋገብ እና ፀሎት) እንዲከለከል አድርጓል::

የአንቀጹን ትክክለኛ ትርጓሜ ስንወስድ ግን በቡድን የሚደረጉ ሃይማኖታዊ ስርዓቶችንም ይሁን በግል እሚፈጸሙትን በምንም አይነት መልኩ ትምህርት ላይ ተጽዕኖ አያሳድር:: ከላይ የተጠቀሱት አንቀጾች ግን በቡድንም ይሁን በግል እሚፈጸሙትን ሃይማኖታዊ ስርዓቶችንም ከዚሁ የህገ መንግስቱ አንቀጽ አያይዘው ትክክለኛ ያልሆነ ትርጓሜ በመስጠት በርካቶችን ከትምህርት ገበታ እያባረሩ ፣ በርካቶችንም እያሰሩ ይገኛሉ፡፡

የሀገራችን Secularism ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ሁለት አበይት ነጥቦች ማካተት ይኖርበታል፡-

1/ Secularism ከአሁን በፊት በኢትዮጵያ ለረዥም ጊዜ በሰፊው የተስተዋለውን ያልተገባ የሃይማኖቶች ግንኙነት በማረም የአንድን ሃይማኖት የተናጥልና ኢ-ፍትሃዊ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጫና በማስወገድ የሃይማኖቶችን እከኩልነት ማረጋገጥ፣

2/ የSecularism አንፃራዊ ባህርይ በመገንዘብ የመንግስትና የሃይማኖት መነጣጠል የኢትዮጵያን ሃይማኖቶች ባሕርይ ከግምት ውስጥ ያስገባ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ምክንያቱም Secularismን ከምዕራቡ Judeo- Christian ባህል አኳያ ብቻ ማየቱ በኢትዮጵያ ዉስጥ ለሚገኙ ሁሉም ሃይማኖቶች አግባብነት ላይኖረው ስለሚችል ነው፡፡

የኢትዮጳያ መንግሰት Secular መሆኑን ለማረጋገጥ የወጡ የህገ-መንግስት ድንጋጌዎችም ከአጠቃላይ የ Secularism ዕይታ፣ ከሕገ-መንግስቱ አጠቃላለይ መንፈስና ዓላማ አንፃር እንዲሁም የሀገራችንን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ሊተረጎሙ ይገባቸዋል፡፡ በጥቅሉ Secularism ማለት ሀይማት አልባ መንግስት መመስረት እንጂ ሀይማኖት አልባ ህዝብ መፍጠር አይደለም፡፡ ስለዚህ መንግስት ሀይማኖት አልባ ህዝብ ለመፍጠር እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ በአስቸኳይ ይቁም!

በተማሪዎች( በተለይ ሙስሊም ተማሪዎች ላይ ) ላይ የተከፈተው ዘመቻ በአስቸኳይ እንዲቆምልን እንጠይቃለን፡፡ ተማሪዎች የተነፈጉትን መብት እስኪመለስላቸው ድረስ እኛም ፀንተን እንታገላለን!

የህገ-መንግስቱ አንቀጽ 90 ይከበር!

በሰኪዩላሪዝም ሽፋን የሚፈፀመው የሂጃብ ገፈፋ በአስቸኳይ ይቁም!!!

አላሁ አክበር!!!

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የጠራው ጠቅላላ ጉባኤ የተጀመረ ሲሆን ተሳታፊዎች የብሔራዊ ምክር ቤት አባላት አረንጓዴ ፤የአዲስ አበባ ምክር ቤት ቢጫ፤ የክልል ዞን ተወካዮች ቀይ ቲሸርቶችን በመልበስ ለጉባኤው ድምቀት ሰጥተውታል፡፡
Image

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አርብ (03/04/07) ጠቅላላ ጉባኤውን ያደርጋል፡፡ ፓርቲው ከዚህ ቀደም በታህሳስ 19/20/2007 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን አመት ሳይሞላ ሌላ ጠቅላላ ጉባኤ ለማድረግ ለምን እንዳስፈለገ የጉባኤ ጠሪ ኮሚቴ የሆኑትን አቶ አስራት ጣሴን አነጋግረን ነበር፡፡ አቶ አስራት እንዳብራሩት በታህሳስ 2006 ዓ.ም ተካሂዶ በነበረው ጠቅላላ ጉባኤ ምርጫ ቦርድ ማብራሪያ ጠይቆ ነበር፡፡ አቶ አስራት በተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ማቋቋሚያ አዋጅ 573/2000 መሰረት ምርጫ ቦርድ የጠቅላላ ጉባኤ ሪፖርት ማብራሪያ መጠየቅ እንደሚችል ገልፀው በሀምሌ 25 ቀን 2006 ዓ.ም በፃፈው ባለ ሶስት ገፅ ደብዳቤ ዘጠኝ ማብራሪያ የሚፈልጉ ጥያቄዎችን አቅርቦ ነበር፡፡
Image
አንድነት ፓርቲ በበኩሉ ሀምሌ 30 ቀን 2006 ዓ.ም ለተጠየቁት ጥያቄዎች ማብራሪያ ላከ፡፡ ከተላከው ማብራሪያ በመነሳት ምርጫ ቦርድ ጥቅምት 19 ቀን 2007 ዓ.ም ጥያቄዎቹን ወደ 6 ዝቅ አደረገ፡፡ ፓርቲው በበኩሉ ጥቅምት 21 ቀን 2007 ዓ.ም ለተጠየቁት ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጠ፡፡ ከዚያ በመቀጠል ምርጫ ቦርድ ህዳር 10 ቀን 2007 ዓ.ም ሶስት ማብራሪያ ያስፈልጋቸዋል ያላቸውን ጥያቄዎች ያቀረበ ሲሆን ፓርቲውም ህዳር 11 ቀን 2007 ዓ.ም ማብራሪያ ሰጥቶባቸዋል፡፡
Image
ለአሁኑ ጠቅላላ ጉባኤ መጠራት ምክንያት የሆነው ህዳር 19 ቀን 2007 ዓ.ም ወደ አንድ ወርዶ በምርጫ ቦርድ የቀረበው ጥያቄ ነው፤ ፓርቲው የጠቅላላ ጉባኤ ተሳታፊ ቁጥሩን እንዲገልፅ የተጠየቀበት፤ ፓርቲው የጠቅላላ ጉባኤ ቁጥሩ 320 መሆኑን ገለፀለት፡፡ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ ይህ ቁጥር ታህሳስ 19 እና 20 ቀን 2006 ዓ.ም በተደረገው ጉባኤ በተሻሻለው በደንብ ባለመካተቱ ተካቶ ይቅረብልኝ ሲል ጠየቀ፡፡ በዚህ ሁኔታ በፓርቲው ደንብ መሰረት የጠቅላላ ጉባኤ ቁጥር መወሰን የሚችለው ራሱ ጉባኤው በመሆኑ ጠቅላላ ጉባኤ መጥራት እንዳስፈለገ አቶ አስራት ጣሴ ገልፀውልናል፡፡
አቶ አስራት በመጨረሻ ባስቀመጡት ሀሳብ ምርጫ ቦርድ ምርጫ ሲደርስ እንዲህ ዓይነት ጥያቄ መጠየቁ እኛን አጣብቂኝ ውስጥ ለመክተት ቢሆንም ህጋዊ መሰረት ግን አልነበረውም ብሏል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ በደንቡ ላይ የጠቅላላ ጉባኤውን ተሳታፊ ቁጥር የወሰነው ብቸኛው ፓርቲ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ብቻ እንደሆነ ታውቋል፡፡
Image
Image

Image
– የተቃዋሚዎች እንቅስቃሴ በዚህ ከቀጠለ ወያኔ እድሜ አይኖረውም::
– የያዝነው መስመር አያዋጣም:እስከመቼስ እንዲህ ይቀጥላል?” የሚሉ አመራሮች ተነስተዋል::
– ካድሬዎች ሕዝቡን እየዞሩ በመቀስቀስ ዳግም እንዲያደራጁ እየተደረገ ነው::

Minilik Salsawi

ከምርጫው መምጣት ጋር በተያያዘ የወያኔው ጁንታ በህዝብ እና በተቃዋሚ ሃይሎች ላይ እየወሰደ የሚገኘውን እርምጃ ተከትሎ በወያኔ/ኢሕአዴግ ፓርቲ ውስጥ በአመራሮች ደረጃ የውስጥ መተራመሱ መቀጠሉ ታውቋል::ሕዝቡን ማዋከብ እና ተቃዋሚውን ማሰር እንዲሁም በየጊዜው የሚከሰተው የውጪ ሃይሎች ጫና አደጋ ውስጥ ይከተናል ልንጠነቀቅ ይገባል የያዝነው መስመር አያዋጣም በሚሉ እና በሕወሓት አመራሮች መካከል ከፍተኛ የሆነ ውዝግብ መከሰቱን ለፓርቲው ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገልጸዋል::

የተወሰነን ከመተግበርና ከማስፈጸም ውጪ ምንም አስተያየት መስጠት አትችሉም የሚል የቁጣ ቃላቶች ከአቶ ደብረጽዮን የሚወርድባቸው የአቶ ሃይለማርያም የደቡብ ኢትዮጵያ ፓርቲ አመራሮች በማንኛውም የፓርቲ ስብሰባ ላይ የተባለውን ከመደገፍ ውጪ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ ታዘዋል::በኢሕአዲግ ውስጥ እየተከሰተ ያለው የአካሄድ ልዩነት አመራሮቹን ከማተራመሱም በላይ በአሁን ወቅት እየተወሰዱ ያሉት እርምጃዎች ከምርጫ በኋላ ቢሆኑ ይሻላል የሚሉ አስተያየቶችና የምንከተለው መስመር አዋጪነቱ ምን ያህል ነው የሚሉ ጥያቄዎች በከፍተኛ አመራሩ መካከል ልዩነት መፍጠሩ ታውቋል::የተቃዋሚዎችን እንቅስቃሴ መስመሩን ለማሳት አዳዲስ የተሳሳቱ መረጃዎች እና የቤት ስራዎች (በተለይ ለዲያስፖራው) እየተዘጋጁ መሆኑን የውስጥ ምንጮቹ ገልጸዋል::

ከአዲስ አበባ የሚደርሱ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ከተማዋ በውጥረት ውስጥ መሆኗ በገሃድ እየታይ ነው የሃገሪቱ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሕዝቡን ካለማስደሰቱም ውጪ ክፍተኛ የሆኑ የቢዝነስ ስራዎች ከቀድሞው በባሰ መልኩ ቀዝቅዘዋል::የገዢው ፓርቲ ተላላኪዎች በተለያዩ ቦታዎች በመዘዋወር ስለላ እያካሄዱ ሲሆን ሕዝቡም ያለውን ሁኔታ በንቃት እየተከታተለ መሆኑ ታውቋል:: የተቃዋሚዎች እንቅስቃሴ እንደጅምሩ ከቀጠለ ለውጥ እንደሚመጣ እና ወያኗም እድሜ እንደማይኖረው በሚነገርበት በአሁን ሰአት የወያኗ ጁንታ በምርጫው ለሚሳተፉ ተቃዋሚዎች ከፓርላማ 15% ወንበር እንዲመቻችላቸው ከምርጫ ቦርድ ጋር እየሰራ ሲሆን ፓርላማ መግባት ያለባቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦችን በመለየት እና በማዘጋጀት ላይ መሆኑ ታውቋል::

በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች የተከሰተውን ውጥረት ተከትሎ ካድሬ የመንግስት ሰራተኞች ውጡና ቀስቅሱ አደራጁ በማለት ፓርቲያቸው መከራ አብዝቶብናል ሲሉ ማማረራቸው ተሰምቷል::ዳግም በየመንደሩ እየዞሩ በማደራጀት እና በመቀስቀስ ላይ የተሰማሩት ካድሬዎች ወጣቶችን በመቀስቀስ በማደራጅት በመመልመል ዙሪያ አዳዲስ ውይይቶች በኢሕአዴግ አመራሮች ትእዛዝ እየተሰጠ መሆኑ ታውቋል::በዚህም መሰረት አዲስ አበባ ውስጥ በየቀጠናው ካድሬዎቹ የመንግስት ሰራተኞች ስራቸውን እየተዉ ቢሯቸውን ዘግተው ለዚሁ የአደረጃጀት የምልመላ እና ቅስቀሳ ጉዳይ መሰማራታቸው ሲታወቅ መረጃውን ያደረሱኝ ተቃዋሚዎች ወያኔ ያደራጀውን ሃይል
ተጠቅመው የጀመሩትን የለውጥ ትግል ገፍተው መቀጠል አለባቸው ሲሉ አስገንዝበዋል::

Image

መሐሙድ የሱፍ የተወለደው በ1980ዓ.ም ከሶማሌ ክልል ርእሰ-መዲና ጅጅጋ 500 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘውዶሀን ከተማ ነው፡፡ ለቤተሰቡ ሰባተኛ ልጅ ሲሆን፤ አምስት እህቶችእና ሦስት ወንድሞች አሉት፡፡ በጅጅጋ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እስከ አስረኛ ክፍል ድረስ መዝለቁቢሳካለትም፤ ከዚህ በላይ ግን ሊቀጥል አልተቻለውም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የኢትዮጵያመንግስት የደህንነት ሠራተኞች የ1999ዓ.ም የግንቦት ሃያ በዓል በጅጅጋ ከተማ ስታዲዬም በተከበረበት ዕለት፣ የኦጋዴን ነፃአውጪ ግንባር (ኦብነግ) በሰነዘረው የቦንብ ጥቃት ተሳትፈሃል በሚል ለእስር በመዳረጉነው፡፡ ይህንን ተከትሎምከምድራችን አስከፊ ማሰቃያዎች መካከል ግንባር ቀደም በሆነውና የክልሉ

ነዋሪ “ጄል-አዳብ” (የገሃነም እስር ቤት) እያለ በሚጠራው ማጎሪያ ውስጥ እጅግ በጣም የከፋ ምድራዊ መከራ እንደተቀበለሀዘን በተጫነው ድምፅ ይናገራል፡፡ በሠውነቱ የተለያዩ ክፍሎች ላይ እንደ ፍም ቀልተው የሚታዩት ጠባሳዎቹም ያሳለፈውንሥቃይ አፍ አውጥተው ይመሰክራሉ፡፡ ለአራት ወራት ያህል አንድ ክፍል ውስጥ ለብቻው ተቆልፎበት፤ ሃያ አራት ሠዓታትሙሉ እጆቹ በካቴና ተቀፍድደው፣በቀን ከአምስት ጊዜ በላይ ለምርመራ እየተጠራ ያለዕረፍት ከባድ ስቅየት (ቶርቸር)ሲፈፀምበት ቆይቷል:፡ በመጨረሻም ለአንዲትም ቀን የፍርድ ቤት ደጅ ሳይረግጥ፣ ለኦብነግ አባላት አንድ ፓኬት ሲጋራሲያቀብል እጀ-ከፈንጅ ተይዟል በሚል ክስ የጅጅጋ ዞን ፍርድ ቤት በሞት እንዲቀጣ መወሰኑን እዛው እስር ቤት ሆኖከኢትዮጵያ ሬዲዮ የዜና እወጃ እና ከቪኦኤ ሶማሊኛ ፕሮግራም ሠምቷል፡፡

ከፍርዱ በኋላም በተመሳሳይ ወንጀል ከተከሰሰ አንድ እስረኛ ጋር በካቴና ተጠፍሮ በቀን አንድ እንጀራ ለሁለት ተካፍሎእንዲበላ እንደ ውሻ እየተወረወረለት 60 ቀናትን አሳልፏል፡፡ መሐሙድ በተለይም በእንቅልፍ ወቅት እርሱ ወይምየሰንሰለት ደባሉ የተገላበጠ እንደሆነ ካቴናው የሚያደርስበትን የመለብለብ ቃጠሎ ሲያስታውስ ዓይኖቹ በእንባ ይሞላሉ፡፡በአሁኑ ወቅት በዝዋይ ማጎሪያ ከባድ ጥበቃ ለሚደረግባቸው ብቻ በተመደበ ‹‹ዘጠነኛ ቤት›› ውስጥ አስራ አንድ ሶማሊኛተናጋሪዎችን ጨምሮ በድምሩ ሰላሳ አራት ሰዎች ጋር ከዛሬ ነገ የግፍ ፍርዱ ተፈጻሚ ሊሆንብኝ ይችላል በሚል ሰቀቀንእየባነነ በስጋት ተጠፍንጎ መኖር ከጀመረ እነሆ ሰባት ዓመት ሊደፍን ሦስት ወራት ብቻ ቀርተውታል፡፡

የተዋረደው የፍትሕ ሥርዓት!. . .

ርግጥ ነው ይህ በጨረፍታ ያቀረብኩት አሳዛኝ ታሪክ የመሐሙድ የሱፍ ብቻ አይደለም፡፡ ሌሎች ሰባት ‹‹አባሪዎቹ››ስቃዩንም ሆነ የሞት ፍርዱን ይጋሩታል (በነገራችን ላይ በአንድ መዝገብ የተወነጀሉት እነዚህ ስምንት የሞት ፍርደኞች፡-መሐድ ኢብራሂም፣ አረብ ሰዋኔ ዱልባንቲ፣ ሐሰን መሐመድ ዑስማን፣ ሐሰን መሐመድ ዓሊ፣ ሙክታር መሐመድ ዓብዱላሂ፣ከድር ሽኩር ሙሳ እና ካሚል ዓብዱልናስር እንኳን በጋራ መንግሥት ላይ ሊያሴሩ ቀርቶ እርስ በርስም የተዋወቁት እስር ቤትውስጥ ነው፡፡ ከጅጅጋ ወደ ዝዋይ ‹‹ዘጠነኛ ቤት›› ተዘዋውረው በርካታ ዓመታትን ያሳለፉትም በጭካኔው ወደርእንደማይገኝለት የሚነገረው የክልሉ ፕሬዚዳንት አብዲ

በአደራ እንዲቀመጡ በመተላለፋቸው መሆኑን ነግረውኛል፡፡) እንደ መሐሙድ ሁሉ እነርሱም ፍርድ ቤት ቀርበውአያውቁም፤ ምንም ዓይነት የሰውም ሆነ የሰነድ ማስረጃ አልተቆጠረባቸውም፡፡ እዚህ ጋ የማነሳው አሳዛኝ ገጠመኝከመካከላቸው አንዳቸውም ራዲዮ ስላልነበራቸው የተጣለባቸውን የሞት ፍርድ ውሳኔ የሠሙት፣ ዜናው ከተላለፈ ከበርካታቀናት በኋላ ሬዲዮ ካላቸው እስረኞች መሆኑ

ነው፡፡ ይህ እጅግ አሳፋሪና አስደንጋጭ መንግሥታዊ ውንብድና በደንብ ይብራራ ዘንድ ለተከሳሶቹ ከተሰጣቸው ባለ አንድገፅ የክስ ቻርጅ የሁለቱን ብቻ በአዲስ መስመር እጠቅሳለሁ፡-‹‹በሶማሌ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ አቃቤ ሕግና ፍትሕቢሮ በሶማሌ ክልላዊ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት

ጅጅጋ

የዐ/ሕግ/መ/ቁ 90/2000

ዝዋይ እስር ቤት ያለው

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከሳሽ፡- ዐ/ሕግ

ተከሳሽ፡- ሐሰን መሐመድ ዑስማን (ሐንን መድቤ)

ዕድሜ፡- 21

ሥራ፡- ተማሪ

አድራሻ፡- ጅጅጋ ከተማ፡- 06 ቀበሌ

ወንጀል

በ1996ዓ/ም የወጣውን የኤ.ፌ.ዴ.ሪ የመ.መ.ሥ.ሥ.ህ.ቁ. 240(3) እና 251(መ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ፣

የወንጀል ዝርዝር

ተከሳሽ ከመስከረም 1999 ዓ.ም. ጀምሮ እራሱን ኦ.ብ.ነ.ግ. እያለ ከሚጠራው ተቃዋሚና አሸባሪ ድርጅት ጋር በራሱፈቃድ

በዚሁ በጅጅጋ ከተማ ከላይ በተጠቀሰው ዓመተ-ምህረት አባል በመሆን በጫካ በዚሁ አካባቢ ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ጋርበከተማም

ሆነ በጫካ በመገናኘት በኢኮኖሚ ረገድ የሚያስፈልጋቸውን፡- ጫማ፣ ልብስ የመሳሰለውን እዚያው ድረስ ሄዶ በማቀበልአብሮ

ሲንቀሳቀስ በመቆየቱ ተከሶ ቀርቧል፡፡››

ሁለተኛው የክስ ቻርጅ ደግሞ እንዲህ ይነበባል፡-

‹‹በሶማሌ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ አቃቤ ሕግና ፍትሕ ቢሮ

በሶ/ክ/መ/ ጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት

ጅጅጋ

የዐ/ሕ/መ/ቁ 90/2000

ከሳሽ፡- ዐ/ሕግ

ተከሳሽ፡- መሐድ ሼክ ኢብራሂም

ዕድሜ፡- 28

ሥራ፡- የለውም

አድራሻ፡- ጅጅጋ ከተማ፡- ቀበሌ 05

1ኛ ክስ

ወንጀሉ

በ1996 ዓ/ም የወጣውን የኤ.ፌ.ዴ.ሪ የመ/መ/ህ/ ቁ. 241 እና 251(መ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ፣

የወንጀሉ ዝርዝር

ተከሳሹ በ1998 ዓ.ም. ወራትና ቀኑ በውል ካልታወቀ ጊዜ ጀምሮ እራሱን ኦ.ብ.ነ.ግ. እያለ ከሚጠራው ተቃዋሚ የፖለቲካ

ድርጅትና አሸባሪ ጋር በራሱ ፈቃድ አባል በመሆን ከዚህ ሕገ-መንግሥቱን ከሚፃረር ድርጅት በቀጥታ ፌዴሬሽኑእንዲከፋፈል፣ ክልሉን

የመገንጠል ዓላማ ለማሳካት ይህንኑ ድርጅት ከዚሁ በጅጅጋ ከተማ ለጊዜው ካልተያዘ ግብረ-አበሩ ጋር በመሆን ይህንኑአሸባሪ ድርጅት

በሚያስፈልገው ማቴሪያል ሁሉ፡- ጫማ፣ የፖሊስ የደንብ ልብስ፣ መድሃኒት. . . የመሳሰለውን በማቀበሉ፡፡

2ኛ ክስ

ወንጀሉ

በ1996ዓ/ም የወጣውን የኤ.ፌ.ዴ.ሪ የመ/መ/ህ/ ቁ. 36 (ለ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ፣

የወንጀሉ ዝርዝር

ተከሳሹ ከ1996 ዓ.ም. ጀምሮ የተለያዩ መ/ቤቶች ማለትም፡- የክልሉ ት/ቢሮን፣ የቀብሪ-ደሐር ት/ቢሮን፣ እንዲሁም የMSF

እና የተለያዩ መሥሪያ ቤቶችን እና የትምህርት ተቋማትን ማህተም በማስመሰል አትሞ እና የኃላፊዎችን ፊርማ ዓይነትአስመስሎ

በማስፈር ሐሰተኛ ሰነድ አዘጋጅቶ በመገኘቱ ተከሶ ቀርቧል፡፡››

(ሁሉም የክስ ቻርጆች ማኅተም እና አንጋው አፈወርቅ ምንተስኖት የተባለ የክልሉ ዐቃቤ ሕግ ፊርማ አላቸው)

እነሆም ያለአንድ ምስክር፣ ያለምንም የሰነድ ማሰረጃ፣ አንድም ቀን ችሎት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃል ሳይጠየቁ እና

ሳይከራከሩ (ያውም የዞን ፍርድ ቤት) በነዚህ በስም በጠቀስኳቸው በስምንቱ ኢትዮጵያውን ላይ የሞት ቅጣትን የመሰለየመጨረሻ

ውሳኔ እንደቀልድ አስተላልፎባቸዋል፡፡ (በነገራችን ላይ ሌሎች 13 የኢትዮጵያ-ሶማሌ ተወላጆችም በተመሳሳይ የሐሰትውንጀላ የዕድሜ

ልክ እስር ተፈርዶባቸው ዝዋይ ይገኛሉ፡፡ የሚገርመው ጉዳይ ደግሞ ም ቢሆኑ መጀመሪያ ተጠርጥረው በተያዙበት ወንጀልአይደለምየተጠየቁት፡፡ ጉዳዩ ጭራሽኑ በምርመራም ወቅት አልተነሳም) መቼም በዚህ መልኩ በተቀናበረ የውሸት ክስ ከ20-27 ዓመት የሚገኙ

ወጣቶችን በሲኦላዊ እሳተ-ነበልባል ስቅየት ውስጥ እንዲያልፉ ከማድረግም በዘለለ፣ ብሩህ ቀናቸውን አጨልሞ ላይመለሱወደመቃብር

የሚሸኝ ቅጣት ሲጣል ከመመልከት የበለጠ የትኛውንም ዜጋ የሕሊና ስቃይ ውስጥ ከትቶ፣ አንገት አስደፍቶ፣ በቁጣ ቀስቅሶ

ወደአደባባይ የሚያወጣ ገፊ-ምክንያት አለ ብዬ አላምንም፡፡

ማነው ተጠያቂው?

በእነዚህ ንፁሃን ኢትዮጵያውያን ላይ ‹በጄል-አደብ› የደረሰባቸው በነውረኝነት የታጀለ ኢ-ፍትሐዊ ፍርድ እና ስቅየት፣

የሥርዓቱን እውነተኛ ማንነት ገሃድ የሚያወጣ ተጨባጭ ተግባር መሆኑ ባይካድም፡ ይህንን አረሜናዊ ድርጊት በፊት-አውራሪነት

የመሩት፡- ኮሎኔል ሞኒ መንገሻ በጊዜው የክልሉ የፀረ-ሽብር ግብረ-ኃይል ዋና ኃላፊ የነበረ አሁን ወደአዲስ አበባ ተቀይሮ‹ሕገ-ወጥ

የሠው ዝውውር ወንጀል መከላከል› ኃላፊ፣ ቢኒያም የተባለ የክልሉ የደህንነት ኃላፊ፣ ሻለቃ ዘገየ በክልሉ የፌዴራል ፖሊስኃላፊ፣

ወልደአራዌ የክልሉ ፖሊስ ም/ኮሚሽነር፤ እንዲሁም ሻለቃ ወንድሜ፣ ሻለቃ በለጠ እና ታሰረ የተባሉ ኃላፊነታቸውንለይተው

የማያስታውሷቸው ግለሰቦች መሆናቸውን ግፉአኖቹ በተሰበረ ልብ፣ ምሬት በሞላው ድምፅ፣ ተስፋ በቆረጠ ስሜትሲተርኩልኝ ዓይኖቼ

ላይ የተቋጠረው የእንባ ከረጢት ገንፍሎ እንዳይፈስ ብርቱ ትግል ማድረጌን አልሸሽግም፡፡

የሆነው ሆኖ እነዚህ የሥርዓቱ ሹማምንት የፍርድ ቤት ደጅ ሳይረግጡ፣ የሞት ቅጣት እንዲተላለፍባቸው ባደረጓቸው

ምስኪኖች ላይ የማሰቃያ ጥበቦቻቸውን በሙሉ ከሞከሩባቸው በኋላ፡- ‹‹ሞት እንፈርድባችኋለን!!›› እያሉ ያስፈራሯቸውናይዝቱባቸው

ነበር፤ እነርሱም፡- ‹‹እናንተ ፍርድ ቤት ናችሁ እንዴ?›› ብለው በግርምትና ባለማመን ሲጠይቋቸው፣ ማናአህሎኝነትያሳበጣቸው የፀጥታ

ኃላፊዎች እንዲህ በማለት አስረግጠው መልስ መስጠታቸውን ሰምቻለሁ፡-

‹‹አዎን! ፍርድ ቤት ማለት እኛ ነን!!››

በርግጥ ከዚህ ሁሉ መከራ በኋላ የተላለፈባቸው ውሳኔ፣ ያውም በሞት እንዲቀጡ የሚል መሆኑን ስናስተውል የዛቻውን

መነሾ መረዳቱ አዳጋች አይሆንብንም፡፡ በአናቱም በምርመራ ወቅት ዕድል ፊቷን ያዞረችበትን ተጠርጣሪ እዛው እስረኛ ፊትበሽጉጥ

ግንባሩን በርቅሰው እንደ መናኛ ነገር ሜዳ ላይ ይዘረጉት እንደነበረ የዓይን እማኞች ይመሰክራሉ፡፡

በጥቅሉ ይህ ሁነት በሀገሪቱ አለቅጥ የተንሰራፋውን የፍትሕ እጦት፣ የሠብአዊ መብት ጥሰት፣ ዳኞች ከሕግ ይልቅ ከቤተ-

መንግሥት በሚላክላቸው የፍርድ ውሳኔ ንፁሃኑን ለምድራዊ ስቃይ ከመዳረግም አልፈው ተርፈው በጭካኔሕይወታቸውንም

እንደሚነጠቁ በቂ ማስረጃ ይመስለኛል፡፡

‹‹ጄል-አዳብ››

የክልሉ ኗሪዎች ‹‹ጄል-አዳብ›› (የገሃነም እስር ቤት) እያሉ የሚጠሩት የጅጅጋው ማሰቃያ ቤት ክፍሎች የተሠሩት አራትመቶ

ታሳሪዎችን እንዲይዙ ታስቦ ቢሆንም፣ አብዛኛውን ጊዜ ከአራት ሺህ በላይ ታሳሪዎች እንደሚታጎሩበት አረጋግጫለሁ፡፡ይህም አንድ

ሰው ከአንድ ሰዓት በላይ በእንቅልፍ ማሳለፍ እንዳይችል አድርጎታል፡፡ ምክንያቱም ቦታውን ለተረኛው የመልቀቅ ግዴታአለበትና፡፡

ምናልባት እንቅልፍ ቢጥለው እንኳ ተረኞቹ ቀስቅሰው (ጎትተው) ያስነሱታል፡፡

ከ‹‹ጄል-አዳብ›› በሕይወት ተርፎ የሚወጣ ሰው ዕድለኛ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ በዚህ ቦታ ከቤተሰብ ጋር መገናኘት ጭራሽ

አይሞከርም፡፡ ማሰቡ እንኳ እንደ ቅንጦት ነው የሚታየው፡፡ በእስር ቤቱ አጥር ሦስት መቶ ሜትር ክልል ርቀት ዙርያ ውስጥመገኘትም

ለከባድ ስቃይ (አንዳንዴም ለሞት ቅጣት) ይዳርጋል፡፡ በሃያ አራት ሰዓት አንዴ፣ አንድ እንጀራ ለሦስት እየተቃመሱለአምስት ዓመት

በዛ እስር ቤት ያሳለፈ ምስኪን አጋጥሞኛል፡፡ ይህ ወጣት በ2004ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ ሦስት ዓይነት ተላላፊ በሽታ(ተቅማጥ፣

ሰውነትን የሚያሳክክና ጉሮሮን አሳብጦ ለአዕምሮ መቃወስ የሚዳርግ) ተከስቶ በቀን እስከ አስራ አራት ሰው ድረስ ይሞትእንደነበር

ያስታውሳል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ሕክምና ብሎ ነገር አልነበረም፡፡ እንዲያውም በግልባጩ የክልሉ አስተዳዳሪዎችጭካኔያቸውን (ኢ-

ሠብአዊነታቸውን) ወለል አድርገው የሚያሳብቁ ድርጊቶች መፈፀማቸውን አላቋረጡም፡፡ ለማሳያ ያህልም እስረኛው ከሌሊቱስድስት

ሰዓት ላይ በአንድ ድምፅ እንዲህ የሚል መፈክር እንዲያሰማ መገደዱን እዚህ ጋ መጠቀስ ይቻላል፡-

‹‹መለስ ዜናዊ ሐኖላዶ!›› (መለስ ዜናዊ ለዘላለም ይኑር!)

‹‹አብዲ ሑመድ ዑመር ሐኖላዶ!››

‹‹ኢትዮጵያ ሐኖላዶ!››

ኦብነግ ሐዳኦዶ!›› (ኦብነግ ይውደም!)ሌላው አስገራሚ ጉዳይ ቤተሰብ ታሳሪ ልጁ በሕይወት ይኑር ይሙት የሚያውቀውከማጎሪያው በስንት ጊዜ አንዴ የሚፈታ

ሰው ሲገኝ ብቻ የመሆኑ እውነታ ነው፡፡ እናም ድንገት በአንዲት ‹ዕድለኛ› ቀን አንድ ታሳሪ ከ‹‹ጄል-አዳብ›› የተለቀቀእንደሆነ ወሬው

ከመቅጽበት ይዛመትና ለሳምንታት አሊያም ለወራት የእስረኛው ቤት በእንግዶች እስከ አፍ-ገደፉ ጢም ብሎ ይውላል፡፡የተለመደ

ነውና እሱም ያለመታከት የቀረበለትን ጥያቄ በሚከተለው መልኩ ሲመልስ ይከርማል፡-

‹‹ኦ!… እገሌ ከሞተ እኮ ሁለት ዓመት አለፈው›› ፤ “እገሌማ ሲያሳዝን! ካረፈ ገና አንድ ወሩ ነው”፤ “ኦ! እገሌ ለወደፊቱ

እግዜር ይጠብቀው እንጂ እስካሁን በሕይወት ይገኛል…” ወዘተ ወዘተ. . .

የታሰሩ እንዲፈቱ በፖለቲካ ድርጅቶች ላይ የሚደረገው ወከባና ጫና እንዲቆም በመግለጫው ጠይቋል::
http://www.andargachewtsige.com/?p=343

Image

ህዝብን በማይሽር ቁስል አየጎዱ በፕሮፓጋንዳ ማከም አይቻልም:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EthioMuslims‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ ሽብር ግድያ እስር ድብደባ እንግልት በጅምላ አፈሳ ዘረፋ ንጥቂያ እና ከፍተኛ የሆነ ኢሰብአዊነት እና ጭፍጨፋ በመንግስት ነኝ ባይ ሃይሎች በይፋ በአደባባይ ተፈጽሟል::ይህንን መንግስታዊ ሽብር የማይሽር ጠባሳ በመላው ኢትዮጵያውያን ላይ ጥቁር ነጥብ አስቀምጧል:: የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ጥያቄና የኮሚቴው መፈታት ጥያቄ በአስቸኳይ ሊመለስ ይገባል::ሙስሊም ወገኖቻችን ለሃገራቸው እና ለነጻነታቸው ምን ያህል ቀናኢ መሆናቸውን በተግባር አስመስክረዋል::
http://minilik-salsawi.blogspot.com/201 … ost_9.html

Image

Image
አምባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት ሰላማዊ ታጋዮችና በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ማሳደዱን አሁንም ቀጥሎበታል። የዘጠኙ ፓርቲዎች ትብብር ለህዳር 27 ጠርተውት በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በመንግስት ኃይሎች የተወሰደውን እጅግ አረመኔያዊ የሆነ ህገ ወጥ እርምጃ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ (አንድነት) ፓርቲ በጥብቅ ያወግዛል።

እነዚህ ፓርቲዎች የሀገሪቱ ህገ መንግስት፣ የስብሰባና ሰልፍ አዋጁ በሚፈቅደውመሰረት ለአዲስ አበባ መስተዳድር ሰልፍ እንደሚያደርጉ ቀኑንና ቦታውን ጠቅሰውአሳውቀዋል፤ በአዋጁ መሰረት ደግሞ ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ እንጂ ፍቃድ መጠየቅ ግድ የሚል አይደለም። ነገር ግን ህገ ወጥ በሆነ ሁኔታ ህጉ በሚፈቅደው መሰረት ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ከሰማያዊ ፓርቲ ፅህፈት ቤት እየወጡ የነበሩትን ሰልፈኞች በመንግስት ኃይሎች ከፍተኛ የሆነ ድብደባ
እንዲፈፀምባቸው ተደርጓል።

ከዚህም ባሻገር የትብብሩ ፓርቲዎች አመራሮችና አባላት አፍሶ በመውሰድ በጨለማ ክፍል ውስጥ አስሯቸው ይገኛል። ወዳጅና ዘመድ እንዳይጠይቃቸው መደረጉም የአንድነት ከፍተኛ አመራሮች ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በትናንትናው ዕለት በአካል ተገኝተው አረጋግጠዋል።
የአዲስ አበባ አስተዳደር ይሄ ጉዳይ በአግባቡና ህጉ በሚፈቅደው መንገድ መፍታት ሲችል፤
በሚዲያ እርምጃ እወስዳለሁ ብሎ ማወጁና በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ግፍ
እዲፈፀም በማድረጉ ሀላፊነቱን መውሰድ አለበት። በተለይ ኢህአዴግ የ2007
ምርጫ እየቀረበ ባለበት ሁኔታ እንዲህ ዓይነቱ አፈናና ህገወጥ እርምጃ መውሰዱ
ምርጫውን ችግር ውስጥ የሚከት ጉዳይ መሆኑ ሊገነዘብ ይገባል። አንድነት
ፓርቲ ይሄ ጉዳይ በዝምታ የሚያየው ነገር አይሆንም፤ በቅርቡም አስፈላጊውን
መረጃዎች ሁሉ አሰባስቦ ጋዜጣዊ ይሰጥበታል።
የዘጠኙ ፓርቲዎች አመራሮችና አባላት በህገ መንግስቱ ላይ የተቀመጠውን
ሰላማዊ ሰልፍ የማድርግ መብት ከመጠቀም ውጪ ያጠፉት ምንም ዓይነት ነገር
ስለሌለ በአስቸኳይ ሊፈቱ ይገባል። ገዥው መንግስት ከህግና ከስርዓት ውጪ
በሰላማዊያን ዜጎች፣ በፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ላይ እየወሰደ ያለውን
አፈና፣ ድብደባና እስር እንዲያቆም፤ የህግ የበላይነትን፣ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ
መብቶችን እንዲያከብር አለም አቀፉ ማህበረሰብ ተገቢውን ጫና እንዲያሳድሩ
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ (አንድነት) ፓርቲ ጥሪውን ያቀርባል። በተለይ
ደግሞ የጉዳዩ ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ይህ ህገወጥና አረመኔያዊ
ድርጊት በዝምታ ሊያልፈው አይገባም፤ ኢህአዴግ በቃህ ሊለው ይግባል።
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ (አንድነት) ፓርቲ
ህዳር 29 /03 /2007
አዲስ አበባ

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር አመራሮች ‹‹ህገ መንግስቱን በኃይል በመናድ›› ወንጀል ተከሰሱ
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎AddisAbebaprotest‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎Blueparty‬ ‪#‎Miniliksalsawi‬
– ‹‹ህገ መንግስቱን ማየት አለብኝ›› ዳኛው
– በርካታ ህዝብ ተገኝቶ የነበር ቢሆንም እንዳይገባ ተከልክሎ ችሎቱ በዝግ ታይቷል፡፡
– የአብዛኛዎቹን ታሳሪዎች ቤት ሊፈትሽ እንደሚችልም ከፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
Minilik Salsawi
በሰላማዊ ሰልፉ ታፍሰው አዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ (ሶስተኛ) ታስረው የሚገኙት የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር አመራሮች፣ አባላትና የሰልፉ ተሳታፊዎች ‹‹ህገ መንግስቱን በኃይል በመናድ›› ወንጀል ተከሰው 14 ቀን ተቀጠረባቸው፡፡ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት፣ አቶ አርጫፎ ኤርዳሎ፣ አለሳ መንገሻና ሌሎቹም የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር አመራሮች፣ አባላትና በሰልፉ ላይ የታፈሱ ዜጎች አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው ለታህሳስ 13/2007 ዓ.ም ተቀጥሮባቸዋል፡፡

ችሎቱ በዝግ የታየ ቢሆንም ሶስተኛ ከሚገኙት ሴት ታሳሪዎች ጠይቀን ማረጋገጥ እንደቻልነው ‹‹ሁከት በመፍጠር ህገ መንግስቱንና ህጋዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ እና መንግስት ያልፈቀደው ሰልፍ በመውጣት›› የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡ ታሳሪዎቹ በበኩላቸው ‹‹እኛ ህጋዊና ሰላማዊ ታጋዮች ነን፡፡ በህጉ መሰረት ሰልፉን እንደምናደርግ አሳውቀናል፡፡ በመሆኑም የዋስ መብታችን ተከብሮ ልንለቀቅ ይገባል›› ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ አቃቤ ህግ ‹‹ምርመራዬን አልጨረስኩም፡፡ የምሰበስበው ተጨማሪ መረጃ አለ፡፡ መረጃዎችን ይደብቁብኛል፡፡ ሌሎች ተባባሪዎችም አሉ፡፡›› ሲል የጊዜ ቀጠሮ እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡ በሌላ በኩል ዳኛው ‹‹ህገ መንግስቱና ሌሎቹም ህጎች ለሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቅ እንጅ ማስፈቀድ አይጠበቅም የሚሉ ከሆነ ህገ መንግስቱንና ሌሎቹንም ህጎች ማየት አለብኝ፡፡›› ብለው 14 ቀጥረውባቸዋል፡፡ አቃቤ ህግ ‹‹የምሰበስበው ተጨማሪ መረጃ አለ፡፡›› ባለው መሰረት የአብዛኛዎቹን ታሳሪዎች ቤት ሊፈትሽ እንደሚችልም ከፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከታሳሪዎቹ መካከል 9ኝ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ ለየብቻቸው ቅዝቃዜ የበዛበትና ጨለማ ቤት ውስጥ እንደታሰሩ የታወቀ ሲሆን በምርመራ ወቅት ከፍተኛ ድብደባ እየተፈጸመባቸው እንደሆነም አቤቱታ አቅርበዋል፡፡ ሆኖም ዳኛው የቀረበውን አቤቱታ ትኩረት ሳይሰጡ እንዳለፉት ታሳሪዎቹ ገልጸውልናል፡፡ ታሳሪዎቹ አራዳ ምድብ ችሎት በቀረቡበት ወቅት ችሎቱ በበርካታ የፌደራል ፖሊስ ታጥሮ ታይቷል፡፡ የፍርድ ሂደቱን ለመከታተል በርካታ ህዝብ ተገኝቶ የነበር ቢሆንም እንዳይገባ ተከልክሎ ችሎቱ በዝግ ታይቷል፡፡

ኢህአዴግ የታገለለት የቡድን መብት በተግባር የታለ!?
ያቀረብነው ‹‹የሃይማኖት ነጻነት ይከበርልን›› ጥያቄ የዜግነትም የቡድንም መብት ቢሆንም ይኸው ሶስት ዓመት ሙሉ ምላሽ ተነፍጎታል!
ሰኞ ህዳር 29/2007

ሃገራችን ኢትዮጵያ ብዙ ብሄር ብሄረሰቦች በጋራ የሚኖሩባት እንደመሆኗ መጠን ህብር የተላበሰ ማህበረሰብን አቅፋለች። በተመሳሳይም ብዝሃ ሃይማኖትን መርህ አርርጋ ሃይማቶችን ከጥንስሱ ጀምሮ ተቀብላ ያስተናገደችም ሃገር ነች። ይሁን እንጂ ብሄር ብሄረሰቦችም ይሁኑ ሃይማኖቶች በሃገሪቱ አስተዳዳሪዎች በእኩል የታዩበት እና እንደዜጋ በተመሳሳይ መልኩ የተዳደሩበት የታሪክ አጋጣሚ አናሳ ነው። ያም ሆኖ ማህበረሰባችን እንደ ህዝብ የሚደርሱበትን የበላይ ተጽዕኖዎች ተቋቁሞ ለዘመናት አብሮ ኖሯል።

የታሪካችን ዳራ የሚያሳየው አብይ መገለጫ ይህን ቢመስልም ቅሉ የነበሩትን የበደል እና ኢ-ፍትሃዊነት ፈተናዎች መቋቋም ሲሳናቸው ለአማራጭ መፍትሄ የተነሱበት አጋጣሚ በርካታ ነው። በሃገራችን በከፍተኛ ህዝብ ቁጥር የሚወከሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ከማህበረ-ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ህይወት በስልት እና በግዳጅ ሲገለሉ ማስተዋል የተለመደ የታሪካችን ገጽታ ነው። ስለዚህም ነው መንግስት ለብሄር ጥያቄም ይሁን የሃይማኖት ነጻነትን ለሚሹ የህብረተሰባችን ክፍሎች ተገቢ ምላሽ መስጠት የሚያሻው። ይህ ባልሆነበት ግን ሁለቱም ቢሆን መብታቸውን ለማስከበር መነሳታቸው አይቀሬ ነው። ይህም በሃገራችን የቅርብ ጊዜ ታሪክ የተስተዋለ እውነታ ነው። ከእነኚህ ተገፊ የህዝብ አካላት መካከል የተወሰኑ ብሄር ብሄረሰቦች እና ሃይማኖታዊ ቡድኖች ቀዳሚዎቹ ሲሆኑ በስርዓተ ጾታ ተጽዕኖ ስር የወደቁ የሃገራችን ሴቶችም ተመሳሳይ መድሎ እና መገለልን አስተናግደዋል።

ይህ ሲባል አንድ የሃገራችን ሴት በሴትነቷ ከሚደርስባት ጫና ባሻገር በምታምንበት ሃይማኖት፣ ብሎም በወከለችው ብሄረሰብ መገለል ምክንያት ድርብርብ ግፍን ልታስተናግድ የምትችልበት እድል ሰፊ ነው። በእርግጥም ከተለመደው የስርዓተ ጾታ ጫና ባለፈ መንግስት በወሰደው የሃይል እርምጃ እና የሒጃብ ማገድ ጸረ-ሴኩላሪዝም ዘመቻ ብዙ ሙስሊም ሴቶች ሰለባ መሆናቸው ቀጥሏል። በአንጻሩም የአንድ እምነት ተከታይ በሃይማኖቱ ሰበብ ከሚደርስበት መገፋት ባለፈ በብሄሩ ምክንያትም ለመገለል የሚዳረግበት አሰራር ለዘመናት ተስተውሏል። በመሆኑም ከብሄራቸው እና ቋንቋቸው ጋር የተዛመደ መድልዎን ሲቃወሙ ከብሄር ጉዳይ ጎን ለጎን የሃይማኖት ነጻነት ጥያቄን አብረው ያነገቡ ቡድኖችን ማግኘት የተለመደ ይሆናል። በብዙዎቹ የሃገራችን ክፍሎች እንደሚስተዋለው የአንድ ብሄር ተወላጆች በአንድም ይሁን በሌላ የታሪክ አጋጣሚ ሙሉ በሙሉ፣ አልያም በአብዛኛው የአንድ ሃይማኖት ተከታይ ሊሆኑ ይችላሉና። የሃገራችን ነባራዊ ገጽታ እንደሚያስረዳው ተገፊ የሆኑ የሃይማኖት እና የብሄር መገለጫዎች በአንድ የህብረተሰብ ክፍል ውስጥ ተነባብረው የመገኘት እድላቸው ሰፊ ነው። ስለሆነም መንግስት የብሄር መብትን ማስከበር የሚችልበት ሁኔታ ሊፈጠር ቢችል እንኳን የሃይማኖት እኩልነትን እስካላረጋገጠ ድረስ እነኚህ የሃገራችን ህዝቦች በበደል አዙሪት ውስጥ ይኖራሉ ማለት ነው። ከዚህ መሰል የበደል ድግግሞሽ ለመላቀቅ ሁለቱንም የቡድን መብቶች ያለምንም መሸራረፍ በህገ-መንግስቱ መርሆች መሰረት ማረጋገጥ ብቸኛ አማራጭ ሆኖ ይታያል።

ይሁን እንጂ የኢህአዴግ መንግስት ‹‹ሴኪውላር (ዓለማዊ) መንግስት በመመስረት አስከብሬዋለሁ›› የሚለውን የሃይማኖት እኩልነት አጀንዳ መልሶ በቀን ብርሃን ሲንደው ተስተውሏል። ‹‹መንግስታዊ ሃላፊነትን ከሃይማኖታዊ ሚና ነጥያለሁ›› ያለው መንግስት በሃይማኖታችን አዛዥ ናዛዥ ከነበሩት ቀደምት ሃይማኖታዊ መንግስታት መሪዎች በምንስ ተለየ? ሌሎች አካላትን ‹‹የአጼውን ስርዓት ናፋቂ›› ሲል የሚያወግዝበትስ አቅም ይኖረዋልን? ለቡድን መብት መከበር የታገለ እና በተግባርም እውን መሆኑን የሚሻ ቢሆን ኖሮ ሙስሊሙን ከሃገራችን ሁለገብ የህይወት ዘርፍ ማግለልን እና ሃይማኖታዊ የቡድን መብቱን በጠራራ ጸሃይ መግፈፍን ጀብዱ አድርጎ ሊቆጥር ባልቻለ ነበር። መንግስት ለቡድን መብት ዘብ በቆመ ኖሮ ባለፉት ሶስት የትግል ዓመታት ላነሳናቸው ህገ መንግስታዊ የእምነት ነጻነት ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ በህጋዊ መንገድ ሊሰጥ በቻለ ነበር። ቀደም ካሉት ዓመታት ጀምሮ የእምነት ተቋሞቻችንን በመቆጣጠር በሃይማኖታችን ላይ የተፈጸመው ደረቅ ጣልቃ ገብነት ከጅምሩ የሃይማኖት እኩልነት ጥያቄን ‹‹ጥያቄ ምልክት ውስጥ›› ባላስገባም ነበር።

ሙስሊሙን የማጥቃቱ ዘመቻ ሙስሊም ሴቶችን እና ወጣት ተማሪዎችን በስመ ሴኩላሪዝም ከትምህርት በማፈናቀል እየተተገበረ ይገኛል። በመሆኑም የኢህአዴግ መንግስት ረጅም ዘመን ትግል ለሃይማኖትም ሆነ ለጾታ እኩልነት ከወሬ ያለፈ ቁርጠኝነት እና ለመርህ ተገዥነት እንዳላሳየ ሙስሊሙ ላነሳቸው የመብት ጥያቄዎች ጆሮ ከመንፈጉ እና ከዚህ ሙስሊም ሴቶችን አነጣጥሮ ከሚያጠቃው መንግስታዊ መድሎ የበለጠ ሁነኛ ማሳያ የለም። በተለይ ደግሞ መንግስት በደነገገው መመሪያ ምክንያት በርካታ እህቶቻችን ጦሳቸውን እያዩበት ያለው ሒጃብ ኢህአዴግ ‹‹እኩልነትን አጎናጸፍኳቸው›› በሚላቸው ብሄሮችም ዘንድ እንደ ባህል መዘውተሩ አንድ እውነታ ነው። እነኚህ ብሄሮች ባህላቸው እና ቋንቋቸው እውቅና ከተቸረው አለባበሳቸውንም በነጻነት ሊተገብሩ የሚችሉበት አጋጣሚ በአመት አንዴ በጭፈራ በሚከበረው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ብቻ ሊሆን አይገባም። የቡድን መብት የሆነው የብሄር እኩልነት እና የሃይማኖት ነጻነት ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ ከሚውልበት ከዚህች የአንድ ቀን የሚዲያ ሽፋን ሊያልፍ ይገባል። በዓመት አንዴ የሚደረግ ጭፈራ የእኩልነት ማሳያ እና መለኪያ ፈጽሞ ሊሆን አለመቻሉን መንግስት ራሱ የሚገነዘበው እውነታ ነው። በብሄር ብሄረሰቦች በዓል ላይ ሂጃብ መልበስ መብት እና ባህል ተደርጎ በትምህርት ተቋማት ግን መታገዱ ማን የት ላይ እንዲኖር እንደተሳበ የሚያረጋግጥ ነው፡፡

በዚህ ረገድ መንግስት በ‹‹ልዩ ድጋፍ›› ወደዩኒቨርስቲ አመጣሁ የሚላቸውን የ‹‹ታዳጊ›› ክልል ተወላጅ ሴቶች በአለባበሳቸው ምክንያት ብቻ መልሶ ከዩኒቨርስቲው በሃይል እያባረረ ነው። እውን ታዲያ የታዳጊ ክልሎችን እና በውስጣቸው የሚኖሩ ብሄሮችን የወደፊት እጣ ፈንታ ሊቀይሩ የሚችሉ የተማሩ የሰው ሃይሎችን እያፈናቀሉ ‹‹በልዩ ድጋፍ የክልሎችን ዓቅም ገነባን፣ ሴቶችን አበቃን›› ለማለት ያስደፍራልን? ይህ የመንግስት መድሏዊ አሰራር የሴቶችን፣ ሙስሊሞችን፣ ብሄር ብሄረሰቦችን (ባህሎችን) እና የታዳጊ ክልሎችን ተዋጽዖ የሚፈታተን ከመሆኑም በላይ በየትኛውም መልኩ የቡድን መብት ለብሄሮችም ይሁን ለጾታዎች፣ እንዲሁም ለሃይማኖቶች እንዳልተረጋገጠ የሚያመላክት አብይ ተጨባጭ ነው። በተለይ ይህ እውነታ በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ ጎልቶ የሚታይ መሆኑ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ‹‹የመንግስት የቡድን መብት ማስከበር ሂደት ሆን ተብሎም ይሁን በቸልታ ለምን እኛን አይመለከትም? ለምንስ መድልዎ ይፈጸምብናል?›› የሚል ጥያቄ እንዲያነሱ ይገፋል።

አዎን! የቡድን መብት አስከብራለሁ የሚለው መንግስት ከቃላት ጨዋታ ባለፈ በተግባር የታገዘ መሬት ላይ የሚወርድ መፍትሄ መሻት ግድ ይለዋል። በመርህም ይሁን በአፈጻጸም ረገድ የብሄር እና የእምነት ነጻነትን እና እኩልነትን ማረጋገጥ ያልቻለ መንግስት ህዝብን የማስተዳደር የሞራል ብቃት ሊኖረው አይችልም። በተለይም ለዘመናት ታገልኩለት ለሚለው እና ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ለሚደሰኩርለት የቡድን መብት ጥያቄ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ መፍትሄ ሰጥቶ ለጉዳዩ መቋጫ ያላደረገ መንግስት እንደምንስ ‹‹ለቡድን መብት ታጋይ እና ጠበቃ ነኝ›› ሊል ይቻለዋል!? ለሃገራችን ግማሽ ህዝብ መሰረታዊ የህልውና ጉዳይ የሆነውን የእምነት መብት ገርስሶ ‹‹ለሃይማኖት እኩልነት ሰራሁ›› ቢል ማንስ ይሰማዋል!? ‹‹ንግግርህን እንዳልሰማ ተግባርህ ይጮህብኛል›› እንዲል ብሂሉ ከንግግር በላይ ጮሆ የሚናገረው እና ሰሚ ጆሮ የሚያገኘው ተግባሩ አይደለምን!!? የቡድንም ይሁን የተናጠል መብቶች በቃላት ሽንገላ፣ በአሰልቺ ፕሮፖጋንዳ እና በሚዲያ ልፈፋ ሊመሰረቱ አይችሉም። ይህ ሁሉ መሬት ላይ ጠብ የሚያደርገው ምንም ፋይዳ የለውምና!! ህዝብ በዕለት ተዕለት ህይወቱ ሊያስተውል የሚችለውን እውነተኛ እኩልነት እና የመብት ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ይሻል። ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ግን መብትን ከመጠየቅ ይልቅ ከጠባቂነት ተላቆ ወደማስከበር ምዕራፍ ይሸጋገራል። ባለፉት ሶስት ዓመታት የተስተዋለው ህዝባዊ የመብት ማስከበር እንቅስቃሴ የሚያመላክተውም ይህንኑ ነው።

ዛሬ መንግስት ህዝብን ጆሮ ሰጥቶ ሊያደምጥ ግድ የሚልበት ጊዜ ላይ ተደርሷል። ህዝብ በተራ ሽንገላ የሚታለልበት ዘመንም አልፏል። ከሌላው የዓለማችን ክፍሎች በተለየ የሰለጠነ አካሄድ ‹‹መብቴን አላስነጥቅም›› ማለትን መርሁ አድርጓል። ይህ ህዝብ ‹‹መሪዎቹ›› ለዘመናት ታገልንለት ቢሉም በተግባር ግን እውን ላላደረጉለት የቡድን መብትም ይሁን ግለሰባዊ ነጻነቶች መከበር በሰላማዊ መንገድ መትጋቱን ይቀጥላል። ከገባበት ‹‹የመብቴ ይከበር›› ትግልም ምንም አይመልሰውም – የመብቱ በእውን መረጋገጥ ሲቀር!!

ህዝብ መርህን ባማከለ መልኩ እንደሚፈልገው መኖርን እንጂ እንዲኖር በተደረገው መልኩ ማሰብን አይሻም። ላለፉት ሁለት ዓስርት ዓመታት የተሰበከውን ሁሉ ጠንቅቆ ተረድቶ አፍረጥርጦ መጠየቅን እና ‹‹ለምን?›› ማለትን ተለምዶው አድርጎታል። ይህ የህዝብን የብስለት ደረጃ አመላካች ነው። መብት እና ግዴታውን ለይቶ የተረዳ ህዝብን ፈጽሞ እያታለሉ መኖር የማይቻል ሆኗል። አልገዛም ባይነት እና ለጭቆና እምቢተኝነትን በስብዕናው የተላበሰ ዜጋ በግዳጅ አምባገነንነትን ሊጭኑበት አይፈቅድም። ያለው የህግ መርር እንዲተገበር በህጋዊ መንገድ መጠየቁም አይቀሬ ነው፤ ማስተካከል የማይችል የስልጣን ጥመኛ ሲገጥመው ግን መብት እና ፍላጎቱን የሚያሟላበትን እና የሚያሟላለትን አማራጭ ለመፈለግ ይገደዳልና።

በእውን የቡድን መብት መከበሩን ማረጋገጥ ካስፈለገ በማህበረ-ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ፣ እንዲሁም ሌሎች ተቋማዊ አሰራሮች የሁሉንም አቻ ተሳታፊነት በተግባር ማሳየት የግድ ነው። በማህበራዊ ግልጋሎት ተደራሽ ያልሆነን፣ በልማት ፖሊሲ ያልታቀፈን፣ በአግላይ ፖሊሲ የተገፋን፣ በህግ ስርዓቱ ተበዳይ የተደረገን አንኳር የህዝብ ክፍል ይዞ ‹‹የብሄሮችን እኩልነት አረጋገጥኩ›› ብሎ በየዓመቱ መዘመር የብሄሮች እና የሃይማኖቶች እኩልነትን ከወረቀት ባለፈ ሊያረጋግጥልን አይችልም። በማደግ ላይ ባለች ሃገር ውስጥ ‹‹ታዳጊ›› የሚባሉ በርካታ ክልሎች እና ብሄረሰቦች ባሉበት ሁነት የብሄሮች እኩልነትን መረጋገጥ የሚያሳይ ተጨባጭ አስረጂም አይገኝም። በተለይ ደግሞ እነኚህ ክልሎች እና ብሄሮች በብዛት የአንድ ሃይማኖት ተከታዮች መሆናቸው ግምት ውስጥ ሲገባ እና በሌሎች ክልሎች እንደሚገኙት የእምነት ወንድሞቻቸው ሁሉ እነሱም በእምነታቸው ምክንያት በደል እና የሃይማኖት መብት ጥሰት ማስተናገዳቸው የሃይማኖት እኩልነትም እንዳልተረጋገጠ በቂ ማሳያ ነው።በመሆኑም እውነተኛ ፍትህ እና እኩልነት የሰፈነበት ሁለንተናዊ ህይወት በሃገራችን ላሉት ሁሉም ብሄሮች እና ብሄረሰቦች፣ እንዲሁም እምነቶች (ሃይማኖቶች) እንዲረጋገጥ ማድረግ ለነገ የማይባል አጣዳፊ የመንግስት ግዴታ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።

መንግስት ወደራሱ ዞር ብሎ የሚናገረውን እና የሚፈጽመውን ተዛምዷዊነት ፈትሾ በግልጽ ተግባሩን እንደ ቃሉ ማድረግ መጀመር ይጠበቅበታል፡፡ ይህን ካልፈቀደ ደግሞ ህዝብን ተግባር አልባ በሆነ ጮሌ ምላስ ለመሸንገል መታገሉን ትቶ በአዋጅ የመንግስት ፖለቲካዊ ማዕዘናትና እኩልነት ጽንሰ ሐሳቦች መፍረሳቸውን ሊያውጅ ይገባል!! ያኔ ህዝብም የ‹‹ህግ ይከበርልን›› ጥያቄውን ፍትህ እስኪሰፍን እና መብቱ እስኪከበርለት በቁርጠኝነት ይገፋበታል፤ አልያም ‹‹ፈጽሞውኑ ህግ የለም!›› ሲል ስለ ህጋዊነት ይሰብካል!!

ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምፃችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

Image