የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ርካሽ ፖለቲካ ዉሸት ሲጋለጥ
ሌባ ለአመሉ ዳቦ ይልሳል ሆነና ነገሩ ይህንን እንኩአን እዉነቱን ሊነግሩን አልፈለጉም:: በጎነት እና አስተዋይነትን ወደ ርካሽ ፖሎቲካ አዞሩትና እንዴት ብሎ መጠየቅ ልማዱ ላልሆነው ህዝብ "በቅርቡ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳድራ 20 ሚልዮን የአውስትራልያ ዶላር ተሸለመች" ብለዉት እርፍ::
ቅሌት!
በሪቱን ለማናገር የማሰነው ቡድን ከጎሮቤትም ሆነ ከቅርብ ቤተዘመድ ያገኘዉት ምላሽ የ20 ሚሊዮን ዶላሩን ታሪክ እና በሪቱ አሸነፈች ስለተባለዉ አዋርድ የሚያዉቁት ነገር እንደሌለ ነዉ:: ዛሬም ከአንድ ፖለቲከኛ አፍ የሚወጣውን ሁሉ ምንም ሳያጣራ ልክ ከላይ ከጸባዖት እንደመጣ ቃል ጋቢ አንጥፎ እየሰገደ በእልልታ የሚቀበል ምስኪን ሰው በዚህ በመረጃ ዘመን መኖሩ ያሳዝናል :: እዉነቱ ወዲህ ነዉ::
ነገሩን የመልቦርን ነዋሪ እና በሪቱ ጃለታን በቅርበት የምያዉቃት ጃራ ቦሩ (jaarraa boru) እንዲህ ይገልፀዋል::
ታሪኩ እንዲህ ነው᎗ ባሪቱ ጃለታ(ከመሃመድ አህመድ እና ከክሚያ የተወለደች: የምልኬሳ እና ዳሜሳ እህት:) ከምትኖርበት ሜልበርን ልዩ ስሙ ወራቢ (Werribee) ከምባል ከተማ ለእረፍት ከቤተሰቦችዋ ጋር ሃገር ቤት ሄዳ በነበረችበት ወቅት በመንግስት ምንም ትኩረት ያልተሰጠበትን የጋራ ሙለታን አከባቢ ትምህርት ቤቶች ለመጎብኘት እድሉን ታገኛለች:: ያንን ጉብኝት ካደረገች በኋላ መንፈሷ እረፍት ያጣል:: ነብሷ ትጨነቃለች:: ወደምትኖርበት ሜልበርን (ወራቢ) ስትመለስ በዚሁ ጉዳይ ትታመማለች:: ትምህርቷን መከታተል ይሳናታል:: በየሳይካያትሪስቱ ብትወሰድ ለመንፈሷ ጭንቀት ምንም መፍትሔ ታጣ:: በመጨረሻም በሽታውን ያልተናገረ መፍትሄ አያገኝም በምለው ፕሪንስፕል በመመራት ለትምህርት ቤቷ ፕሪንስፓል (ዳይሬክተር) "ኢትዮጵያ ያሉት ልጆች በሚያፈስ ቤት ውስጥ እንደዚያ አፈር ላይ ተቀምጠው በተጨናነቀ ሁኔታ ሲማሩ አይቼ ደስታ ራቀኝ፣ እንቅልፍ አጣሁ፤ ምግብ እንኳ መብላት አልቻልኩም::" ብላ ስታለቅስባቸው ጊዜ የተለያዩ ገንዘብ የማሰባሰቢያ ፕሮግራሞች ተካሂዶ የተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑድርጅቶች ተረባርበው የዚህችን ሲበዛ ሰብዓዊነት የተሞላባትን ታዳጊ ወጣት መንፈስ ለመታደግ ባሳዩት ርብርቦሽ አንድ ትምህርት ቤት ለመስራት የሚያስችል ፈንድ ይገኝላታል:: ታዲያ ዶክተሩ እንደዚያ በስንት እንባ፣ ህመም እና ደጅ መጥናት የተገኘውን ገንዘብ የኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች ከውጭ ለሚጎበኛቸው እነኒያ በመንግስት ቸል የተባሉት ትምህርት ቤቶች ምን ያህል ሰዉን እንደሚያስለቅሱ ላለማንሳት እና ፖለቲካቸውን ለማሳመር እንዲመቻቸው ነው የሃያ ሚልዮኑን ቲዎሪ ይዘው ከች ያሉት::
አቶ ቴዎድሮስ ድፍን የሜልበርን ህዝብ የሚያውቀውን ታሪክ መልኩን ስለምን ለመለወጥ ፈለጉ:: የሆነ ሆኖ ዶክተሩን ሳላመሰግናቸው ላልፍ የማልፈልገው ግን ፈንዱን ወደ ትግራይ ሳያዞሩ እንደታቀደው ወደ ጋራ ሙለታ እንዲላክ መወሰናቸውን ነው:: በሪቱን እንኳን ደስ ያለሽ ልንላት ይገባል:: ያበባ እቅፍ ቱላማሪን አየር ማረፊያ ይጠብቃታል:: ዶክተር እርስዎን ግን ታዘብናችሁ::
Dagim Ahunim
