አለመተማመኑ በስፋት ነግሷል::ከትግራይ ክልል ብቻ የተመለመሉ ለደህንነት ስልጠና አዲስ አበባ ገቡ::
Minilik Salsawi እየተፍረከረከ ያለውና የመተማመን መንፈስ የጠፋበት የወያኔው ጁንታ ባለፈው ወር ያደረገውን የደህንነት ሃላፊዎች ስብሰባ ውስኔን ተከትሎ ከትግራይ ክልል ብቻ የተመለመሉ 2800 ሰዎች ለደህንነት ስልጠና አዲስ አበባ ገብተው መጠቃለላቸው ተሰምቷል::በደህንነት ሃላፊዎቹ ውሳኔ መሰረት በሌላው ክልል ዜጎች ላይ ያለው እምነት የሞተ ስለሆነ በደህነንቱ ስራ ላይ ስልጠና እንደማይሰጣቸው ታውቋል::ከክልሎች የደህንነት ተቋሙን የሚቀላቀሉ ማንኛቸውም ዜጎች እድሉ እንደማይሰጣቸው እና ያሉትንም ከደረጃቸው ዝቅ ያሉ ቦታዎች በመመደብ ሃገራዊ እና መንግስታዊ የምስጢር መረጃዎችን እንዳያገኙ መከላከል ያስፈልጋል የሚሉት የደህንነት ሃላፊዎቹ የደህንነት ተቋሙ ውስጥ መተማመን እንዲስፋፋ አድርገዋል ሲሉ ከክልሎች የመጡ ደህንነቶችን ወንጅለዋል::
መረጃውን የሰጡኝ ለኢሚግሬሽን እና ደህንነት ቢሮ ቅርብ የሆኑ ምንጮች እንዳሉት አዳዲስ ስልጠና ተሰቷቸው የሚመደቡ ደህንነቶች አስፈላጊውን ጥቅማ ጥቅም እና በፈለጉበት አገር ላይ ለወደፊት ኑሮ የሚሆን መኖሪያ ቤት ሳይቀር እንደሚገነባላቸው ቃል ተገብቶላቸዋል::በደህንነት ተቋም ውስጥ ከፍተኛ የሆነ አለመተማመን መንገሱን ያወሱት ምንጮቹ በገሃድ ከምናየው የባለስልጣናቱ ውንብድና በተጨማሪ የሃገር (የብሄራዊ ጥቅም)ምስጢር ሳይቀር ለውጪ ሃይሎች እየተሸጠ መሆኑን ገልጸዋል::እንዲሁም ህገመንግስቱን እና ተቃዋሚ ሃይሎችን በተመለከተ የሚነሱ ጥያቄዎች የደህንነት ሃላፊዎቹ በደህንነት አባላቱ ላይ ያላቸውን እምነት እንዲሸረሸር ያደረገ መሆኑን ሲናገሩ ራሳቸው ሃላፊዎቹ የሚፈጥሩት ጫና አለመተማመኑን አስፍቶት እያለ የትግራይ ተወላጆች ባልሆኑ ዜጎች ላይ መደፍደፉ እንደማያዋጣ ምንጮቹ ጠቁመዋል::
የሕወሓት የደህነንት ተቋሙ የትግራይ ተወላጆችን መልምሎ ወደ አዲስ አበባ ያመጣበት ሌላው ምክንያት ከዚህ ቀደም የደህነንት ተቋሙ አባላት የነበሩ የትግራይ ተወላጆች በጦር ሰራዊቱ እና በፖሊስ ሰራዊቱ ውስጥ ከተራ ወታደርነት እስከ መኮንንነት ማእረግ ተሰቷቸው ሰርገው እንዲገቡ የተደረገ መሆኑን ምንጮቹ ተናግረዋል::በተለይ በፖሊስ ሰራዊቱ ውስጥ የፖሊስ ሳይንስ ሙያ ሳያጠኑ በከፍተኛ የአመራር ቦታዎች ላይ እና በየፖሊስ ጣቢያ አዛዥነት ላይ የተመደቡ የደህንነት አባላቱ በዜጎች ላይ ከባድ የሆነ ሰቆቃ እየፈጸሙ መሆኑን ምንጮቹ ገልጸዋል::