ገበሬዎች ቤታቸው እየተፈተሸ እየተዘረፉ እየታሰሩ እየተገደሉ እየተሰደዱ ነው::ህዝቡ በጣም ተማሯል::

– ምርጫ በመጣ ቁጥር እንክብካቤው ሰልችቶናል::ህክምና አተን ስንገላታ መች ደረሳችሁልን::የአዊ ነዋሪዎች
– የመኢአድ አመራሮች ከወያኔ የምርጫ ሜዳ ራሳቸውን እያወጡ ነው::ድርጅቱ ምርጫውን ጥሎ ይወጣል::

‪#‎Miniliksalsawi‬ – በምእራብ ጎጃም ዞን ወንበርማ ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮችን በማዳበሪያ እዳ ምክንያት ፓሊስና የወረዳው አመራር ያለ ፍቤት ትእዛዝ ቤታቸውን እየፈተሸ ከብት ንብረታቸውን እየዘረፉ መሆኑን አንድ ወዳጀ አሁን አስታውቆኛል።አርሶ አደሮቹንም ወደ ማጎሪያ እስር ቤት እየከተቱዋቸው ነው።

ጉልበት ያለውም ቤተሰቦቹን ይዞ በመሰደድ ላይ ነው እንደ ታማኝ ምንጮች ገለፃ ህዝቡ በጣም ተማሯል::።ከ50 ሰዎች በላይ እንደታሰሩ ከአንድ ቀበሌ ብቻ "የርግን" ከምትባል ቀበሌ ለጊዜው ቁጥራቸው የማይታወቁ ሰዎች ሀገር ጥለው ሸሽተዋል::አንድ "ወገዳድ"በሚባል ቀበሌ የሚኖር ሰው እስር ቤት ክቆየ በሁአላ እንደወጣ በድብደባ ብዛት መሞቱ ታውቋል::
የታሳሪዎች ስም:-
1.አርሶ አደር ወርቄ
2. " አዝመራው
3. " ስለሽ

የመኢአድ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ኢንጅነር ሽፈራዉ ከምርጫዉ ራሳቸዉን ያገለሉበትን ምክንያት አሳወቁ::
የሰሜን ቀጠና ሃላፊ የሆኑት ኢንጅነር ሽፈራዉ ሑሉንም ነገር ወያኔ በተቆጣጠረበት በምርጫ መሳተፍ ለአባገነንነቱ ሕጋዊ እዉቅና ከመስጠት ባሻገር ሰላማዊ ትግል እየተባለ ሕዝብን ከወዲሁ ዉጤቱ በታወቀ ላይ ማድከም እና ሌሎች የሰላማዊ ትግሎች ላይ እንዳያተኩር ማዘናጋት በመሆኑ ነው ብለዋል:: ኢንጅነር ሽፈራዉ ባለፈዉ ትብብሩ በጠራዉ ሰልፍ ላይ በማስተባበር ላይ እንዳሉ ለአንድ ሳንምንት በወያኔ ደህንነቶች ታፍነዉ ተወስደዉ ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈጠመባቸዉ ይታወቃል::ለጊዜው ስማቸው ይፋ ያልሆነ አመራሮች ራሳቸውን ከወያኔ የምርጫ ሜዳ ያገለሉ ሲሆን ድርጅቱ ይህን ተከትሎ ምርጫውን ጥሎ ይወጣል ተብሎ እየተጠበቀ ነው::

በተያያዘ ዜና በአዊ ዞን ኮሶበር ከተማ መንግስት ምርጫውን ምክናያት በማድረግ እስካሁን ተኝተው ከርመው አዊ ዩኒቨርስቲን የመሰረት ድንጋዪ አስቀመጡ በተመሳሳይ የኮሶበር ሆስፒታልንም በቶሎ ቶሎ ድንጋይ አስቀምጠዋል::የካቲት አንድ ቀን ህብረተሰቡ ግን እስከዛሬ የት ነበራችሁ ልጆቻችን ተምረው ዩንቨርስቲ መግቢያ ውጤት አምጥተው እሩቅ ቦታ ሲመደቡ አቅም አንሶዋቸው እዚሁ እንደኛው ገበሬ ሆነው ሲቀሩ ልጆቻችንና ባልተበቶቻችን ህክምና አጥተው በመንገድ ሲቀሩ እንዲሁም ምራጫ በመጣ ቁጥር ቃል የገባችሁልን ከዚህ በፊት የት አሉ ብሎዋቸዋል::