የሰሜን ሱዳን የፖለቲካ ተጽእኖና ፤ የዐረብ ባህል ጫና አንገሽግሾት 22 ዓመታት መሪር ትግል ያካሄደው የደቡብ ሱዳን ህዝብ፤ ነጻነት ባወጀ በ 2 ዓመት ከመንፈቅ ገደማ ወደ አስከፊ የእርስ በርስ ውጊያ እንዳያመራ አሥግቷል። ባለፈው እሁድ በመዲናይቱ

በፍልሰት ሳቢያ በሚከሠቱ ችግሮች ላይ በማትኮር የተለያዩ አጣዳፊ የርዳታ ዓይነቶችን የሚያቀርበው ዓለም አቀፍ ድርጅት (IOM) ከስዑዲ ዐረቢያ ተገደው የተመለሱ ኢትዮጵያውያንን በመርዳት ላይ ሲሆን የተረጂዎቹ ቁጥር ከፍ በማለቱ ተጨማሪ እርዳታ እንዲቀርብለት መማጸኑ ተመልክቷል።

ሶስት ወጣቶች ናቸው። ማገዶን ከ50 ከመቶ በላይ ሊቆጥብ የሚያስችል ምድጃ እና የከሰል ማሽን በመሥራት ራሳቸውን አደራጅተው ሥራ የጀመሩ። እነዚህ ወጣቶችም በቅርቡ በታዳሽ ኃይል መስክ ለተሰማሩ ድርጅቶች እውቅና ከሚሰጠው የ(ኤስ ኢ ኢ ዲ ኢኒሽዮቲቭ) የ 2013ቱ ተሸላሚ ሆነዋል።

የኤሌክትሪክ ግንባታ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኤሌክትሪክ አገልግሎት ደግሞ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገግሎት ኩባንያዎች እንዲመራ መደረጉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፓሬሽን የህዝብ ግንኑነት ሃላፊ አቶ ምስክር ነጋሽ ለዶቼቬለ ተናግረዋል ።

የአውሮጳ ህብረት ለመጀመሪያ ጊዜ የጦር ተልዕኮ ለማካሄድ የወሰነው በአፍሪቃ ቀንድ የሚታየውን የባህር ላይ ውንብድናን ለመታገል ቆርጦ በተነሳበት ጊዜ ነበር። « አታላንታ» በሚል መጠሪያ የሚታወቀው እና ከአምሥት ዓመት በፊት የተጀመረው ይኸው የኅብረቱ ፀረ የባህር ላይ ወንበዴዎች ተልዕኮ የተሳካ ውጤት ማስገኘቱ ነው የሚነገረው።

ለህዝብ መረጃ በማቅረብ ሰፊ አገልግሎት በመስጠት ከታወቁት ዋና -ዋና ዘርፎች ፣ማለትም ሬዲዮ ፣ ቴሌቭዥን፤ ጋዜጣና መጽሔት ሌላ ፣ ማህበራዊ የህዝብ መገናኛ ዘዴዎች ፣ ፈጣንና ማራኪ ሁለገብ መረጃ ማቅረብ እንደሚችሉ በማሥመስከር ላይ ናቸው። ማሕበራዊ ድረ

አንዲት ትውልደ ኬንያት በቆዳ ቀለሟ ምክንያት እዚህ ጀርመን የደረሰባት አድልዎ የብዙዎችን ትኩረት የሳበ የሰሞኑ መነጋገሪያ ሆኗል ። የተላከላትን ጥቅል እቃ ለመቀበል ወደ አንድ የፖስታ አገልግሎት ሰጭ ድርጅት ባለፈው ሳምንት ጎራ ያለችውን ወይዘሮዋን የድርጅቱ ሠራተኛ ጥቁር ስለሆንሽ አልሰጥም ብላ ትከለክላታለች ።

ለሶስት አስርተ ዓመታት ከመድረክ ርቆ ቆይቶ፤በቅርቡ እጅግ አስደናቂ የተባሉትን እንብሮቹን ይዞዳግም ብቅብሎአል። በ1970ዎቹ ታዋቂ በነበረው ዋሊያስ ባንድ ውስጥ በጃዝ እና በሶልስልት የተቀነባበረ ሙዚቃን በመጫወት ዕውቅናን ያገኘው ኃይሉ መርጊያ።

እ ጎ አ ታኅሣሥ 17 ቀን 2010 ዓ ም፤ ቅጠላ ቅጠልና ፍራፍሬ በመሸጥ ይተዳደር የነበረው ሙሐመድ ቡዓዚዚ የተባለው ጎልማሳ ቤንዚን አርክፈክፎ ራሱን ሲያቃጥል፤ ቤን አሊንና ዘመዶቻቸውን ከሥልጣን ለማፈናቀል አልሞ አልነበረም። ይሁንና የቡዓዚዚ በገዛ

የአውሮጳ ህብረት ለመጀመሪያ ጊዜ የጦር ተልዕኮ ለማካሄድ የወሰነው በአፍሪቃ ቀንድ የሚታየውን የባህር ላይ ውንብድናን ለመታገል ቆርጦ በተነሳበት ጊዜ ነበር። « አታላንታ» በሚል መጠሪያ የሚታወቀው እና ከአምሥት ዓመት በፊት የተጀመረው ይኸው የኅብረቱ ፀረ የባህር ላይ ወንበዴዎች ተልዕኮ የተሳካ ውጤት ማስገኘቱ ነው የሚነገረው።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደሚለዉ ፕሬዝዳት ኪየር የሚወለዱበት የዲንካ እና ማቼር የሚወለዱበት የኑዌር ጎሳዎች መልክ እና ባሕሪ የያዘዉ ዉጊያ ፈጣን መፍትሔ ካላገኘ አደገኛ ነዉ።ደቡብ ሱዳን፥ ነፃነት ያወጀችበትን ሁለተኛ ዓመት-ከመንፈቅ፥ ከረጅም ጦርነት የተላቀቀችበትን ሥምንተኛ ዓመት፥ እነሆ በጦርነት ልታከብር ዉጊያ ጀምራለች።

የደቡብ አፍሪቃን ፀረ የዘር መድልዎ ሥርዓት (አፓርታይድ) በመታገል ህዝቡ ለድል የበቃው፤ በሕይወት ቢኖር ኖሮ በዛሬዋ ዕለት 67ኛ ዓመቱን ማክበር ይችል በነበረው ስቲቭ ቢኮን በመሳሳሉ የጥቁሩን ሕዝብ ንቃተ ሕሊና ከፍ ለማድረግ ዘመቻ ባካሄዱ ጠንካራ

የሱዳን ዋና ከተማ ጁባ ከእሁዱ መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ በኋላ ዛሬ መረጋጋትዋ ተዘግቧል ። ነዋሪዎች ዛሬ ከቤታቸው መውጣት ጀምረዋል ። አልፎ አልፎ ተኩስ መሰማቱ ግን አልቆመም ። መንግሥት እንዳስታወቀው ከመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ 10 ሰዎችን አስሯል ።

በፓሪስና በኒው ዮርክ የሚገኙት ፣ ድንበር አያግዴው የጋዜጠኞች ድርጅት (RSF) እና ለጋዜጠኞች ህልውናና መብት ተሟጋቹ ፤ (CPJ)፣ በዓለም ዙሪያ የጋዜጠኞችን ፍዳ የሚዘረዝረውን ዓመታዊ መግለጫቸውን ይፋ አደረጉ። ለመገባደድ 2 ሳምንት ገደማ በቀረው 2013 ጎርጎሪዮሳዊው ዓመት

ለዘመናት ከድህነት ወለል በታች ተፈርጃ መቆየቷ በሚነገርላት ኢትዮጵያ ምንም እንኩዋን መንግስት እና ኣንዳንድ ዓለም ዓቀፍ ተቐማትም ቢሆኑ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ፈጣን እድገት እያስመዘገበች መሆኗ ቢሰማም የድህነቱ ጥልቀት ግን እንዲህ በቀላሉ የሚቀረፍ ኣለመሆኑን ሁሉም ወገኖች ይስማሙበታል።

በመካከለኛዉ ምሥራቅ በሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ሥደተኞችን ችግር ለመግታት የተቀናጀና መጠነ-ሠፊ ጥረት መደረግ እንዳለበት ዋሽግን-ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ በጉዳዩ ላይ የተነጋገሩ ተሰብሳቢዎች አስታወቁ። ባለፈዉ ቅዳሜ በተደረገዉ ዉይይት ላይ የተካፈሉ ምሑራን፥ የሕግ ባለሙያዎችና የማሕበራት መሪዎች ጥናታዊ ፅሑፍ አቅርበዉ ነበር።

የማሊ ሕዝብ ባለፈው እሁድ ሁለተኛውን ዙር ምክር ቤታዊ ምርጫ አካሂዷል። የሀገሪቱ የፀጥታ ሁኔታ አሁንም አሳሳቢ የሆነበት ድርጊት በምርጫው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳረፉ አልቀረም። እንደታየው፣ ሕዝቡ በምርጫ ለመሳተፍ ፍላጎት ያለው አይመስልም። ከማሊ በተገኙ ዘገባዎች መሠረት፣ ድምፁን ለመስጠት የወጣው መራጭ ሕዝብ ቁጥር በጣም ዝቅተኛ ነበር።

የዓማዓቱን የልማት ግብ ከማሳካት አኩዋያ በርካታ የኣፍሪካ ኣገሮች ኣበረታች ውጤት እያስመዘገቡ መሆናቸው ተመለከተ።
የጸረ ድህነት ግብረ ኃይል የተሰኘው ቡድን ይፋ ባደረገው የ2013 ዓመታዊ ዘገባ በሰረት ኢትዮጵያን ጨምሮ አምስት የኣፍሪካ ኣገሮች የዓመዓቱን የልማት ግብ ከማሳካት አኩዋያ የቀዳሚነቱን ስፍራ ይዟል።

የተመድ ከፍተኛ የዉሃ እጥረት እንዳለባቸዉ ከሚገልጻቸዉ ሃገራት አንዷ ኬንያ ናት። ካለፈዉ መስከረም ወር አንስቶ ግን በድርቀቱ በሚታወቀዉ ቱርካና ግዛቷ የኬንያን ይህን መሰል ታሪክ የሚቀይር አጋጣሚ ተከስቷል።

የጀርመን የህዝብ እንደራሴዎች ምርጫ አሸናፊ የክርስቲያን ዲሞክራት ህብረት ፓርቲ መሪ አንጌላ ሜርክልም ዛሬ ቃለ መሃላ በመፈፀም የመራሄ መንግሥትነቱን መንበር ለ3ተኛ የስልጣን ዘመን በይፋ ተረክበዋል ። የጀርመን የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ፣ በሰጠው ድምፅ የመረጣቸው ሜርክል ትልቁን ተጣማሪ መንግሥት ለሚቀጥሉት አራት አመታት ይመራሉ ።

አርሰናል በማንቸስተር ሲቲ 6 ለ3 ተረቶ ግስጋሴው ጋብ ሲል፤ ሊቨርፑል ቶትንሐም ሆትስፐርን 5 ለ ባዶ በማንኮታኮት አርሰናልን ተናንቆታል። አርሰናል በሻምፒዮንስ ሊጉ ኃያሉ ባየር ሙንሽን ይጠብቀዋል። ሌሎች ዘገባዎችንም አሰናድተናል።

በደቡብ ሱዳን ትላንት የተሞከረው የመንግስት ግልበጣ መክሸፉን የኣገርቱ መንግስት ኣስታወቀ።

በቀድሞው ም/ፕሬዝደንት ማቻር የተመራው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ የከሸፈው ለፕሬዝደንት ሳልቫኪር ታማኝ የሆኑ ወታደሮች የበላይነትን በማግኘታቸው ነው ተብሏል።

ፍልስጤም-እስራኤሎች፥ ዋሽንግተን፥ ሞስኮዎች፥ ዋሽንግተን፥ ቤጂንግ፥ ዋሽንግተን ቴሕራኖች፥ ዋሽንግተን ሐቫናዎች፥ አስመራ-አዲስ አበቦች፥ ኢሕአዲግ ተቃዋሚዎች፥ ሶማሌዎች፥ ሶሪያዎች፥ ብዙ ናቸዉ። ቁጥራቸዉን መዘርዘሩ ያታክታልም። ከማንዴላ ምግባር ጥቁቱን፥ ከዴክላክ ድፍረት ትንሹን እንኳን ገቢር አለማድረጋቸዉ በርግጥ ያጠያይቃል

በጀርመን ምክር ቤታዊ ምርጫ ከተካሄደ ከሶስት ወራት በኋላ የክርስቲያን ዲሞክራቲክ ህብረት፣ በምሕፃሩ ሲ ዲ ዩ እና የክርስቲያን ሶሻል ህብረት፣ በምሕፃሩ ሲ ኤስ ዩ፣ እንዲሁም፣ የሶሻል ዲሞክራት ፓርቲ፣ በምሕፃሩ ኤስ ፒ ዲ አንድ ትልቅ ጥምር መንግሥት ለመመሥረት የሚያስችላቸውን ሰነድ ዛሬ ተፈራረሙ።

ሻምበል ጉታ ዲንቃ በአፄ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግስት ኔልሰን ማንዴላ ለትጥቅ ትግል ስልጠና አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በቆዩበት ወቅት ጠባቂያቸው ከነበሩ መኮንኖች መካከል አንዱ ናቸው። የማንዴላ የቀብር ስርዓት ላይ እንዲገኙ ለማድረግ በመላው ዓለም ያሉ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል። ይህ ጥረት ከምን ደረጃ ላይ ደረሰ?

የነፃነት እና የፀረ-ዘረኝነት ታጋዩ ኔልሰን ማንዴላ ስርዓተ ቀብር እሁድ ታኅሣሥ 6 ቀን 2006 ዓም ደቡብ አፍሪቃ ኩኑ በተባለችው የትውልድ መንደራቸው ተፈፀመ። ለማንዴላ ክብር በቀብር ስርዓቱ 21 ጊዜ መድፍ የተተኮሰ ሲሆን፤ የጦር ጀቶች ከዕድምተኛው በላይ ሲያንዣብቡም ታይተዋል።

የነፃነት እና የፀረ-ዘረኝነት ታጋዩ ኔልሰን ማንዴላ ስርዓተ ቀብር እሁድ ታኅሣሥ 6 ቀን 2006 ዓም ደቡብ አፍሪቃ ኩኑ በተባለችው የትውልድ መንደራቸው ተካሄደ። ለማንዴላ ክብር በቀብር ስርዓቱ 21 ጊዜ መድፍ የተተኮሰ ሲሆን፤ የጦር ጀቶች ከዕድምተኛው በላይ ሲያንዣብቡም ታይተዋል።

የቀድሞው የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚደንት እና ዋናው የፀረ አፓርታይድ ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ ሞት የሀገሪቱን ጥቁሮች እና ነጮች ዜጎች አቀራርቦዋል። በሀዘኑ ሰበብ የተፈጠረው ይኸው የመቀራረብ መንፈሥ ባለፉት

በኢትዮጵያ ተወልደው፣ በ 3 ዓመታቸው እሥራኤል በመግባት ፤ በዚያ ያደጉ የተማሩና የፓርላማ (ክኔሰት) አባል የሆኑት ፔኒና ታማኖ-ሻታ የተባሉት የ 32 ዓመት ወ/ሮ ፣ ከትናንት በስቲያ ደም ለመለገሥ ተዘጋጅተው ፤ በጤና ጥበቃ ሚንስቴር መመሪያ

የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ ትላንት አዲስ ጠ/ሚ መሰየማቸው ተዘገበ። ፕሬዝደንት መሐሙድ የቀድሞውን ጠ/ሚ ካባረሩ ሳምንታት ቢቆጠሩም ጠ/ሚ ሺርዶን ግን ኣሻፈረኝ ብለው ቆይተው ነበር። የሶማሊያው ም/ቤት የመተማመኛ ድምጽ ከነፈጋቸው በኃላ ግን ሺርዶን ስልጣን መልቀቃቸው ታውቐል።

የስፖርት አዋቂዎች እንደሚሉት ማንዴላ ከዓለማችን ፖለቲከኞችና የመብት ተሟጋቾች በተለየ ስፖርትን በሰላም መሣሪያነት ተጠቅመዋል ። ለስፖርት ትልቅ ቦታ ይሰጡ የነበሩት ማንዴላ በተለያዩ ዓለም ዓቀፍ የስፖርት ተቋማትና በስፖርት ዓዋቂዎች ዘንድ ትልቅ ከበሬታ አላቸው ።

የኢትዮጵያ መንግሥት ዋነኛ ተቃዋሚ ፓርቲ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ፣ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሰላማዊ ትግል መንገድ እየተዘጋ ነዉ አለ፦ ህዝቡን ወደ ትጥቅ ትግል እንዳይወስድ እንደሚሰጋ አስጠነቀቀም።

የሳውዲ አረቢያ መንግስት ህገወጥ ስደተኞች ያላቸውን የውጪ ዜጎች ከኣገሩ ለማስወጣት በጀመረው መጠነ ሰፊ ዘመቻ አኩዋያ የኢትዮጵያ መንግስትም 30 000 ያህል ዜጎችን ወደ ኣገራቸው ለመመለስ መገደዱን ባለፈው ወር ማስታወቁ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት ጥርጣሬ ካሰራቸዉ የኢትዮጵያ የሙስሊሞች ጉዳይ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ መሪዎች፥ አባላትና ተባባሪዎች መካካል አስራ-ሁለቱ በነፃ እንዲለቀቁ ተወሰነ።

ከግማሽ ም/ዓመት በፊት አንጋፋው የደቡብ ኣፍሪካ የነጻነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ ኢትዮጵያ ውስጥ ስልጠና ላይ በነበሩበት ወቅት የተቃጣባቸውን የግድያ ሙከራ ያከሸፉት ኢትዮጵያዊ ወታደር በቀብራቸው ለመገኘት እያሰቡ ነው።

ኬንያ የምሥራቅ አፍሪቃ የዕድገትና መረጋጋት ሞተር መሆኗ ነው የሚነገርላት።ፕሬዚዳንት ዑሑሩ ኬንያታና ምክትላቸው ዊልያም ሩቶ በሄግ ፤ ኔዘርላንድስ ዓለም አቀፍ የጦር ወንጀለኞች መርማሪ ፍርድ ቤት፤ ቢከሰሱም፤ አገራቸው፤ እ ጎ አ በ 2010 አዲስ