አዲሱ የጀርመን ጥምር መንግሥት

የጀርመን የህዝብ እንደራሴዎች ምርጫ አሸናፊ የክርስቲያን ዲሞክራት ህብረት ፓርቲ መሪ አንጌላ ሜርክልም ዛሬ ቃለ መሃላ በመፈፀም የመራሄ መንግሥትነቱን መንበር ለ3ተኛ የስልጣን ዘመን በይፋ ተረክበዋል ። የጀርመን የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ፣ በሰጠው ድምፅ የመረጣቸው ሜርክል ትልቁን ተጣማሪ መንግሥት ለሚቀጥሉት አራት አመታት ይመራሉ ።