የዓለም አቀፍ የጦር መሣሪያ ወጪ መቀነስ

በዓለም ደረጃ በአጠቃላይ ለጦር መሣሪያ ግዢ የሚወጣው ገንዘብ ከበፊቱ ጋር ሲነፃፀር በትንሹ ዝቅ ብሏል። ይህም የሆነበት ምክንያት ትናንት ስቶኮልም ላይ ይፋ የወጣው አንድ ጥናት እንደሚያመላክተው ዮናይትድ ስቴትስ ለኢራቅ ጦርነት የምታወጣው ገንዘብ በመቀነሱ ነው።