የአፍሪቃ ኅብረት የሶማሊያ ሰላም አስከባሪዎች

በሶማሊያ የአፍሪቃ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል በእንግሊዝኛ ምሕፃሩ AMISOM ከሁለት ዓመታት በኋላ ወታደሮቹን ከሶማሊያ ለማዉጣት እቅድ እንዳለዉ ተነገረ። በተመድ የጸጥታዉ ምክር ቤት መርሃግብር መሠረት AMISOM በሶማሊያ የሚኖረዉ የሰላም ማስከበር ኃላፊነት በተጠቀሰዉ ዓመት ያበቃል።