ፓትርያርኩ የጠቅላላ ጉባኤውን ተሳታፊዎች ለማነጋገር ፈቃደኛ አልኾኑም፤ መላው ሰንበት ት/ቤቶች የአንድነቱን ቀጣይ የንቅናቄ ጥሪ በንቃት እየተጠባበቁ ነው
ከመሰብሰቢያ አዳራሹ ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ ያመሩት የጠቅላላ ጉባኤው ተሳታፊዎች ፓትርያርኩ እንዲያነጋግሯቸው በመጠየቅ ከአርባ ደቂቃዎች በላይ እየዘመሩ ጠብቀው ነበር
- ፓትርያርኩ ጠቅላላ ጉባኤው በላካቸው ብፁዓን አባቶች እና ተሳታፊዎች ላይ በራቸውን ዘጉ
- የፓትርያርኩን ዳተኝነት በማጋለጥ ፍትሕን የሚጠይቁ የዐደባባይ ሰላማዊ ሰልፎች ይካሔዳሉ
- በአማሳኞች እና በተሐድሶ መናፍቃን ላይ የሚደረገው ተጋድሎ በየአጥቢያዎቹ ይቀጣጠላል
- ማስረጃ የተገኘባቸውን አማሳኞች በአገሪቱ ሕግ ለመጠየቅ የባለሞያዎች ቡድን ተቋቁሟል
* * *
፬ኛው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ባለ18 ነጥቦች የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል፤ ከመግለጫው ነጥቦች፡-
- በአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ የቀረበው ጥያቄ የኹሉም አህጉረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤያት የጋራ አቋም በመኾኑ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጠው ተጠይቋል፤
- የቤተ ክርስቲያን ሀብት እና ንብረት ለግል ጥቅማቸው በማዋል የቤተ ክርስቲያንን አቅም የሚያዳክሙ አማሳኞች ማስረጃ ተጠናቅሮ በአገሪቱ ሕግ መሠረት ለፍርድ እንዲቀርቡ ተጠይቋል፤
- አንዳንድ የገዳማት እና አድባራት ሓላፊዎች ‹‹የተሳሳተ አመክንዮ›› ሳቢያ በሰንበት ት/ቤቶች ላይ እየደረሰ ያለው እስር፣ እንግልት እና ወከባ እንዲቆም ተጠይቋል፤
- የመንግሥት የፍትሕ አካላት ከአጥፊዎች ጋራ በመተባበር የሰንበት ት/ቤት አባላትን ከማሰር እና ከማንገላት እንዲቆጠቡ ይደረግ ዘንድ ተጠይቋል፤
- በቤተ ክርስቲያን ተልእኮ አፈጻጸም ላይ ተጽዕኖ እየፈጠረ ያለውን የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ለማጋለጥ ከሀገር አቀፍ አንድነት እስከ አጥቢያ ማስረጃ የማሰባሰቡ ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል፤
- ማስረጃ በቀረበባቸው ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲሰጥ እና ውሳኔውንም ተግባራዊ ለማድረግ ኹሉም የቤተ ክርስቲያን አካላት አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስዱ ተጠይቋል፤
ተጨማሪ መረጃዎችን ይከታተሉ