ፓትርያርኩ: የረዳት ሊቀ ጳጳሱን የባንክ ሒሳብ የማንቀሳቀስ ሓላፊነት ያለቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ ቀየሩ፤ ‹‹ተጠያቂነት እና መንፈሳዊ መከባበር የሌለበት የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኹኔታ አፋጣኝ መፍትሔ የሚያሻው ነው›› /ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ/
- አስተዳደሩን፣ የገንዘብ እና ንብረት እንቅስቃሴውን የመቆጣጠር ሕጋዊ ሓላፊነታቸው ተገድቧል
- በዕቅድ ባልተያዙ ከፍተኛ ግዥዎች እና የወጪ ሰበቦች ምዝበራ ሊፈጸም እንደሚችል ተጠቁሟል
- በቅ/ሲኖዶስ የተመደቡትን ረዳት ያጣው ሀ/ስብከቱ ከ50 ሚልዮን በላይ ተቀማጩ ለአደጋ ተጋልጧል
* * *
- የሠራተኞች ደመወዝ እና አይቀሬ የኾኑትን ዕለታዊ የሥራ ማስኬጃ ወጪዎች እንዳይወጡ ፈቃደኛ ያልኾንኩበት እና ሥራዎች እንዲጓተቱ ያደረግኹበት ወቅት እስከ ዛሬ ድረስ የለም፡፡
- በተመደቡት ሥራ አስኪያጅ እና በእኔ መካከል ያለው የሥራ ግንኙነት እና ሓላፊነት ከቃለ ዐዋዲው እና ከሕገ ቤተ ክርስቲያኑ አንጻር ታይቶ እና ተለይቶ በትክክል ባለመተግበሩ ሓላፊነቴን ለመወጣት በእጅጉ እቸገራለኹ፡፡
- በሀገረ ስብከቱ የተረጋጋ እና ሰላማዊ የሥራ ግንኙነት እንዲኖር፤ ሓላፊነት፣ ተጠያቂነት እና መንፈሳዊ መከባበር ባለው ኹኔታ በሕጋዊ አሠራር ሥራዎችን ለማከናወን የሚያስችል የሥራ መመሪያ እንዲኖር ቅዱስነትዎ ትኩረት ይስጠው፡፡
/ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ/
