ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬ፣ ጥቅምት ፲፭ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. አራተኛ ቀን ውሎው የድሬዳዋና ምዕራብ ሐረርጌ ሊቀ ጳጳስ የኾኑት ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም፣ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ ኾነው እንዲሠሩ የምደባ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ምልአተ ጉባኤው ውሳኔውን ያሳለፈው፣ ከግንቦት ፳፻፭ ዓ.ም. ጀምሮ የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ ኾነው በነበሩት ብፁዕ አቡነ ዳንኤልና በማኅበሩ መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ዙሪያ ከመከረ በኋላ ነው፡፡ ቅዱስ …

ቅ/ሲኖዶሱኻያ ኹለት የስብሰባ አጀንዳዎችን በማጽደቅ መወያየት ጀምሯል በሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያው ሥልጣናቸውን የማጠናከር ውጥን አላቸው የማኅበረ ቅዱሳን ደንብ አጀንዳ እንዳይኾን መቃወማቸው ውድቅ ተደርጓል ሊቃነ ጳጳሳቱን ባዘለፉባቸው ሕገ ወጥ ስብሰባዎች ይቅርታ ጠይቀዋል የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን በራሱ የሚመራው ሊቀ ጳጳስ ይመደብለታል በደቡብና ምዕራብ ኢትዮጵያ የቤተ ክርስቲያን ጸጥታ ጉዳይና የተሐድሶ መናፍቃን የሚፈጥሯቸው ችግሮች በአጀንዳነት ተይዘዋል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ …

በቃለ ዐዋዲው ደንብ መሠረት፣ በካህናት እና ምእመናን አንድነት በየደረጃው የተዋቀረውና የቤተ ክርስቲያናችንን አስተዳደር ለመምራት ከፍተኛ የሥራ አስፈጻሚነት ሥልጣን የተሰጠው አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ፣ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ደረጃ ያካሔደውን ፴፫ኛ ሀገር አቀፍ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ ጥቅምት ፰ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ቀትር ላይ የአቋም መግለጫ በማውጣትና የውሳኔ ሐሳብ በማቅረብ አጠናቅቋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን መዋቅር …

ቃለ ጉባኤ፡- የበጀት ዓመቱ የሥራ አፈጻጸም ዘገባዎች ትኩረት ከሰጧቸው ዝርዝር ነጥቦች ውስጥ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን የሥራ እንቅስቃሴ የሰፈረው የጉባኤተኛው ቃል (ገጽ 12) የአቋም መግለጫና የውሳኔ ሐሳብ፡- የማኅበራትን ታላቅ አስተዋፅኦ ስለማወቅና ችግሮቻቸውን በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ስለ መፍታት የተያዘው የጋራ አቋምና የቀረበው የውሳኔ ሐሳብ (ገጽ 20)

አማሳኞቹ በአጠቃላይ ጉባኤው የሚሳተፉት በታዛቢነት ብቻ ኾኖ ሳለ የውይይት መድረኩን ተጠቅመው የፓትርያርኩን ‹‹የቅኝ ገዥ ነው!›› ቅስቀሳ ለማጠናከርና ፀረ – ማኅበረ ቅዱሳን መግለጫ እንዲወጣ በዋና ሥራ አስኪያጁ ላይ የሚያደርጉት ጫና እንደማይወክላቸው የአዲስ አበባ ልኡካን እየገለጹ ነው፡፡ ‹‹ሰሞኑን መቅሠፍት አለ›› በሚል ከንቱ ማስፈራሪያ በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ላይ በተለያየ መንገድ ጫና ከመፍጠር አልፈው አካላዊ ጥቃት ለማድረስም እየተሰናዱ …

ኑፋቄያቸውና ሕገ ወጥ ጥቅማቸው እንዳይጋለጥ የሚሰጉ አካላት ያስተባበሩት ነው የብፁዓን አባቶች ስም እየተጠቀሰ የወረደው የስድብ ናዳ በእጅጉ አሳዝኖናል በፈቃዳችንና በነፃ የምንፈጽመውን የአገልግሎት መብታችንን የሚፃረር ነው ግለሰቦቹ በስም ማጥፋት ዘመቻቸው ከቀጠሉ ማኅበሩ በሕግ ይጠይቃቸዋል *               *               * የስም ማጥፋት ድርጊቱን የፈጸሙበት ግለሰቦች÷ ራሳቸውን ደብቀው የምንፍቅና ዓላማን ያነገቡና ማኅበሩ ለዓላማቸው መሳካት ዕንቅፋት እንደኾነባቸው የሚያምኑ፤ የቤተ …

ጥቂት አማሳኞች በማንጨብጨብ ሲከተሏቸው፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን ጨምሮ ብዙኃን ጉባኤተኞች በድንጋጤና በተደምሞ አዳምጠዋቸዋል፡፡ ፓትርያርኩ በቀቢጸ ተስፋ ውስጥ እንዳሉም አመላካች ኾኗል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን÷ በጉባኤያት፣ በኅትመትና በኤሌክትሮኒክስ የስብከተ ወንጌል ስርጭት፣ በቅዱሳት መካናት ልማት፣ በአብነት ት/ቤቶችና በካህናት ማሠልጠኛዎች ድጎማና ሞያዊ እገዛዎች ያከናወናቸው ተግባራት በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ሪፖርት በስፋት ተዳስሰዋል፤ ጉባኤተኞች ማኅበሩ ላስመዘገባቸው የሥራ ፍሬዎች ደማቅ ድጋፋቸውን ገልጸዋል፡፡ …

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ በጥቅምት ወር መጀመሪያ ላይ የሚካሔደው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ መደበኛ ስብስባ ዛሬ ይጀመራል፡፡ ዘንድሮ ለ፴፫ኛ ጊዜ የሚካሔደው ይኸው ዓመታዊ ስብሰባ፣ ከጥቅምት ፭ – ፯ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. የሚቆይ ሲኾን ከ50 አህጉረ ስብከት የተውጣጡ ከ800 ያላነሱ ልኡካን ይገኙበታል፡፡ የመንበረ ፓትርያርኩ መቀመጫ ከኾነው ከአዲስ አበባ፣ የሀገረ ስብከቱን ተወካዮች ጨምሮ …

ስብሰባው ፓትርያርኩ ‹‹አጥፍቸው እጠፋለኹ›› ባሉት ማኅበረ ቅዱሳን ላይ ቅስቀሳ በማካሔድ በቅዱስ ሲኖዶሱ ላይ ጫና ለማሳደርና ለኃይል ርምጃ ምቹ ኹኔታ ለመፍጠር ያለመ ነው፡፡ *         *        * ‹‹ባላወጣነውና ባላጸደቅነው ሕግ ማኅበራትን መፈረጅና ሕገ ወጥ ማለት አንችልም፡፡›› ‹‹አቡነ ጳውሎስ በአማካሪዎች ክፋት ዕድሜያቸውን አሳጥረዋል፤ ቅዱስነትዎም ያስቡበት፡፡›› ‹‹ከአለቆችና ጸሐፊዎች ጋራ የተደረገው ውይይት አባቶች የተዘለፉበትና ያዘኑበት ነው፡፡›› ‹‹ለእገሌ ሚኒስትር እናገራለኹ፤ ለእገሌ …

ከሥልጠናው ተሳታፊዎች ከፍተኛ ተቃውሞ አጋጥሟቸዋል፤ ከሥራ ባልደረቦቻቸውም ጠንካራ ጥያቄ ቀርቦባቸዋል፡፡ ‹‹በሴኩላሪዝም ሰበብ ማዕተብኽን በጥስ ማለት ሃይማኖትን ከማስካድና እንደ ሰቃልያነ አምላክ አይሁድ መስቀሉን ለመቅበር ከመሞከር ተለይቶ አይታይም፡፡ ሃይማኖት፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን እና ታሪካዊ ትውፊት እንዳይፋለስ የመጠበቅና የማስጠበቅ ሓላፊነት ያለበት ቅዱስ ሲኖዶስ በጥንቃቄ ሊከታተለው ይገባል፡፡›› /የሥልጠናው ተሳታፊዎች/ ‹‹ፈትል አንድነት እየሸረቡ ለክርስትና ሕይወት መግለጫ በክርስትና ጥምቀት ጊዜ አንገት …

ሦስት ቀለማት ያላቸው ክሮች የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ሲኾኑ አንድ ላይ መፈተላቸው ወይም አንድ መኾናቸው ቅድስት ሥላሴ ማለት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በመለኰት በህልውና አንድ አምላክ መኾናቸውን ያመለክታል፡፡ ጥቁሩ፡- ክርስቲያን ስለ ሃይማኖት የሚቀበለው መከራ የሚሸከመው መስቀል፣ ቀዩ፡- በሰማዕትነት ደም የማፍሰስ ሲኾን ቢጫው ደግሞ የክርስቲያን ተስፋ የሃይማኖት ምልክት ነው፡፡ ክርስቲያን ለክርስቶስ ታማኝ በመኾኑ በነፍሱ ሞግዚት …

ትክክለኛ የቋሚና አላቂ ንብረት ምዝገባና አስተዳደር፣ ተቀባይነት ያለውና እምነት የሚጣልበት የገንዘብ ገቢና ወጪ እንቅስቃሴ፣ ግልጽና ወጥነት ያለው የግዥ አፈጻጸም፣ ብቁ የቁጥጥር ሥርዐት ባለመዘርጋቱ የቤተ ክርስቲያናችን ጥቅል ሀብት አይታወቅም፡፡ በማንኛውም ሕጋዊና ዘመናዊ የሒሳብ ምርመራ አሠራር እጅግ ኋላ ቀር በኾነው በነጠላ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ እና በሞዴላሞዴሎች አሠራር የቤተ ክርስቲያንን ገንዘብ እና ንብረት ከብኩንነት፣ ከመዘረፍ እና ከመጭበርበር ለማዳን …

የሕወሐት ታጋይ ጄ/ል ዮሃንስ ገ/መስቀል ቦሌ ቴሌ መድሃኒያለም ባለ6 ፎቅ ህንፃ እንዳስገነቡ የቅርብ ምንጮች አጋለጡ። ከ95ሚሊዮን ብር በላይ በሚደርስ ወጪ እንደተገነባ የተነገረለት ይኸው ባለ6 ፎቅ ዘመናዊ ህንፃ ለተለያዩ የግልና የመንግስት ባንኮች፣ ኢንሹራንስ ድርጅቶች፣ ንግድ ቤቶችና የተለያዩ ድርጅት ቢሮዎች እንደተከራየ የጠቆሙት ምንጮቹ በወር ከ2.1 ሚሊዮን ብር የሚገመት ኪራይ ጄኔራሉ እንደሚሰበስቡ አስታውቀዋል።

ሌ/ጄ ዮሃንስ በግላቸው ባለ6 ፎቅ ዘመናዊ ህንፃ በከፍተኛ ወጪ በማስገንባትና ከፍተኛ የኪራይ ሂሳብ በየወሩ በመሰብሰብ ከሌሎቹ በቢዝነስ ከተሰማሩ የሕወሐት/ኢህአዴግ ጄኔራል መኮንኖች የተለየ እንደሚያደርጋቸው ምንጮቹ አመልክተዋል። በአገር መከላከያ ሚኒስቴር የመረጃ ዋና መምሪያ ሃላፊ ሆነው ለረጅም አመታት ሲሰሩ የቆዩት የህወሐቱ ጄኔራል ዮሃንስ ገ/መስቀል ከ1995ዓ.ም ጀምሮ ከጄ/ል ሳሞራ የኑስ ጋር የከረረ ቅራኔ ውስጥ ገብተው እንደቆዩና በሁለቱ የህወሀት ጄኔራሎች መካከል የተፈጠረው ቅራኔ እየተባባሰ ሄዶ ጄ/ል ዮሃንስ ከሃላፊነት እንዲነሱ መደረጉን ያስታወሱት ምንጮቹ የሁለቱ ቅራኔ ሙስናን መሰረት ያደረገ እንደነበረ አስረድተዋል።

(በወቅቱ ስለግጭታቸውና መለስ ዜናዊ ዘንድ ቀርበው ስለተነጋገሩት በኢትኦጵ ጋዜጣ መረጃው ይፋ ተደርጐዋል) ጄ/ል ዮሃንስ ከመከላከያ ሃላፊነታቸው እንዲነሱ የተደረጉት በጄ/ል ሳሞራ መሆኑን ያስታወሱት ምንጮቹ በወቅቱ “ጡረታ” በሚል እንደተነሱና ሲነሱም በሜ/ጄኔራል ማእረግ እንደነበሩ አስታውቀዋል። በሙስና ባገኙት በመቶ ሚሊዮን የሚገመት ገንዘብ ሕንፃ ወደማስገንባት የግል ቢዝነስ የተሰማሩት ጄ/ል ዮሃንስ ከአራት አመት በኋላ በመከላከያ የሌተና ጄኔራልነት ማእረግ ባሳለፍነው ሰኔ ወር ተሰጥቷቸው በደቡብ ሱዳን የሚሰማራውን የተመድ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት በጦር አዛዥነት እንዲመሩ መመደባቸው አስገራሚ ነው ያሉት ምንጮቹ ምክንያቱም ጡረታ ተብለው የተሰናበቱት ዮሃንስ የሌተና ጄኔራል ማእረግ እድገት ተሰጥቷቸው መመለሳቸው በመከላከያ ታሪክ የመጀመሪያው ሊያደርጋቸው ስለሚችል ግርምት ሊፈጥር ችሏል ብለዋል። ዮሃንስ የአገር መከላከያ ሚ/ር የሌ/ጄኔራል ማእረግ እንዲሰጣቸውና በተመድ እንዲመደቡ የተደረገው በአሜሪካ ትእዛዝ መሆኑን ምንጮቹ አመልክተዋል። በቦሌ ለንደን ካፌ ፊት ለፊት ዘመናዊ መኖሪያ ካስገነቡት ጄኔራሎች አንዱ ናቸው።

(በፎቶው ጄ/ል ዮሃንስ ገ/መስቀል)


በሶፍት ኮፒ ተሰርቶ በኢንተርኔት የተሰራጨውን መጽሐፍ አሁን አንብቤ ጨረስኩት (ነሐሴ 27፡ ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ ማለቴ ነው)፡፡ መጽሐፉ በስውር አልደረሰኝም፡፡ እዚሁ ፌስቡክ ላይ Book for All ከሚባለው ግሩፕ ነው ያገኘሁት፡፡ እርግጥ የደረሰኝ ኮፒ ለህትመት የተዘጋጀው ሳይሆን የመጽሐፉ የመጀመሪያ ረቂቅ ይመስለኛል፡፡

ያም ሆነ ይህ መፅሐፉን አነበብኩት፡፡ ሆኖም በመጽሐፉ ያነበብኩት ነገር ብዙም አላስደነቀኝም፡፡ የቀድሞው ም/ሚኒስትር ስናየው፣ ስንሰማውና በግሉ ፕሬስ ስናነበው የነበረውን ነው መልሰው የጻፉት፡፡ ያ ማለት ግን ዋሽተውናል ማለት አይደለም፡፡ አቶ ኤርሚያስ ለጊዜው ያልተናገሯቸው በርካታ ነገሮች ሊኖሩ እንደሚችሉ ብረዳም አሁን የጻፉት ነገር በኢህአዴግ አባላት ሲነገረን ከነበረው በምንም መልኩ የሚለይ አይደለም፡፡ አቶ መለስ ዜናዊን ጨምሮ ሌሎች አንጋፋ የኢህአዴግ መሪዎች በልዩ ልዩ የግምገማ መድረኮች ሲያወጧቸው የነበሩት ሪፖርቶች ከዚህ ቢብሱ እንጂ ከዚህ የሚያንሱ አይደሉም፡፡ ለአብነትም አቶ መለስ “ቦናፓርቲስታዊ የመበስበስ አደጋዎች” እና “ድርጅታችን ከእንጥሏና ከጭንቅላቷ መግማት ጀምራለች” በሚሉ ርዕሶች የጻፏቸውን ሪፖርቶች መጥቀስ ይቻላል፡፡

የአቶ ኤርሚያስ መጽሐፍ መልዕክቱ ለኢህአዴግ ተቃዋሚዎች አልመሰለኝም፡፡ ከዚህ ይልቅ አቶ ኤርሚያስ ለኢህአዴግና ለአባላቱ ማስጠንቀቂያ ያስተላለፉበት የተቆርቋሪነት ድርሳን ሆኖ ነው ያገኘሁት፡፡ አቶ ኤርሚያስ በጥቅሉ “ድርጅቱ የተመሰረተበትን ዓላማ እየሳተ በስህተት ላይ ስህተት እየጨመረ ሄዷል፤ ለወደፊቱ በዚሁ መንገድ ከቀጠለ የህልውናው ነገር አጠያያቂ ይሆናል፤ ሀገሪቷም አደጋ ላይ ተወድቃለች፤ ስለዚህ አመራሩና አባላቱ የድርጅቱን ህልውና ማስቀጠል ከፈለጉ ተገቢ የማስተካከያ እርምጃዎችን በጊዜ መውሰድ አለባቸው” የሚል መልዕክት ነው ያስተላለፉት፡፡

ይህ የአቶ ኤርሚያስ ስጋት በአቶ መለስ ዜናዊ በተለያዩ ጊዜያት ተንጸባርቋል፡፡ አቶ መለስ “የቆሰለው ጅብ ታሪክ”ን እያነሱ “ኢህአዴግ ራሱን እያረመና እያስተካከለ ካልሄደ እንደቆሰለው ጅብ ራሱን በልቶ ይጨርሳል” በማለት ጽፈዋል፡፡ በሌላ ጊዜም “የኢህአዴግ ዋነኛ ጠላቱ ተቃዋሚው ሳይሆን ኢህአዴግ ራሱ ነው፤ ኢህአዴግ ራሱን ካልጠበቀ ህልውናው ለአደጋ ይጋለጣል” በማለት በአደባባይ ተናግረዋል፡፡ ስለዚህ የኢህአዴግ አባላትና ደጋፊዎች ሰውየውንና መጽሐፉን ከማጥላላት ይልቅ የአቶ ኤርሚያስን ምክር በአዎንታዊነት ተመልክተው ለተግባራዊነቱ ሊንቀሳቀሱ ይገባል እላለሁ፡፡

—–

በአንጻሩ ግን አንድ ጥያቄ አለኝ፡፡ “እነኝህ በስልጣን ማማ ላይ ከቆዩ በኋላ ወደ ውጪ እየኮበለሉ የኢህአዴግን እኩይነት የሚያወጉን ባለስልጣናት ራሳቸው ምን ያህል ንጹህ ናቸው?” የሚል፡፡ እንዲህ የምለው ከኢህአዴግ አፈንግጠው ወደ ወጪ ከሚጠፉት ባለስልጣናት መካከል የብዙዎቹ ግለ-ታሪክ የተበላሸ መሆኑን ስለማውቅ ነው፡፡ ለምሳሌ የኦህዴድና የኢህአዴግ ፖሊት ቢሮ አባልና የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደርና ጸጥታ ሃላፊ የነበሩት አቶ ዮናታን ዲቢሳን እንውሰድ፡፡ እኝህ ግለሰብ በየካቲት 1993 ከተሰደዱ በኋላ ኢህአዴግ የሰራቸው ወንጀሎች በማለት ብዙ ነገር ለፍልፈዋል፡፡ ነገር ግን በወቅቱ ስልጣን ላይ ከነበሩት የኦህዴድ (ኦፒዲኦ) መሪዎች መካከል የርሳቸውን ያህል በወንጀል የተነከረ ግለሰብ ያለ አይመስለኝም፡፡ በታችኛው እርከን (ዞን፣ ወረዳ፣ ቀበሌ) የነበሩት የኦሮሚያ ክልል አስተዳደር አካላት ተጠሪነታቸው ለርሳቸው ነበር፡፡ በመሆኑም በኦሮሚያ ክልል የሚካሄዱ እንቅስቃሴዎችን በቅርበት ይቆጣጠሩ ነበር፡፡ በዚህ ስልጣናቸው ተጠቅመው የከወኗቸው ብዙ ጉዶች አሉ፡፡

እኝህ ግለሰብ በሺህ የሚቆጠሩ የኦሮሞ ልጆች በኦነግ ደጋፊነት ተከስሰው እንዲታሰሩ፣ እንዲገደሉ፣ እንዲሰደዱና ደብዛቸው እንዲጠፋ የተደረገበትን ኦፕሬሽን ካቀናበሩትና ካስፈጸሙት አንዱ ናቸው፡፡ የኦሮሚያ መሬቶችን አላግባብ እየቆረሱ ለጎረቤት ክልሎች ሰጥተው ካበቁ በኋላ በሌሎች ክልሎች የተከለሉ ኦሮሞዎች “ወደ ኦሮሚያ ክልል መጠቃለል እንፈልጋለን” የሚል ጥያቄ ሲያነሱ አይቀጡ ቅጣት እንዲቀጡ አድርገዋል፡፡ በኦሮሚያ ክልል በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ በተካሄዱ የመግደል፣ የማስደንበርና የማፈናቀል ዘመቻዎችም አውራ ተሳታፊ እንደነበሩ በሰፊው ይታወቃል (ወደ ውጪ ከኮበለሉ በኋላ በወለጋ ክፍለ ሀገር ከሆሮ ገድሩ አውራጃ ለተናፈቀሉ የአማራ ተወላጆች ተቆርቋሪ ሆነው የአዞ እምባ ማንባታቸው በጣም አስደምሞኛል)፡፡

አቶ ዮናታን በተለይም ለሃያ ዓመታት የግጭት ቀጣና በሆነው የአዋሽ-ቦርዶዴ-ሚኤሶ-አፍደም መስመር ላይ (የባቡር ሐዲድን ተክትሎ ባሉት ከተሞች) በኦሮሞና በሶማሌ ወንድማማች ህዝቦች መካከል በየሶስት ወሩ ለሚቀጣጠለው ግጭት ኢ-ፍትሐዊ ሽፋን በመስጠት ግጭቱ እንዳይረግብ ከሚያደርጉ ግለሰቦች ዋነኛው ነበሩ፡፡ ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚንቀሳቀሱ የዞንና የወረዳ ስራ አስፈጻሚዎችን አስረዋል፤ ከስራ አባረዋል፡፡ በግጭቱ የምንጊዜም ተጠቂ የሆኑት የአሰቦትና የሚኤሶ አርብቶ አደሮች ራሳቸውን የሚከላከሉባቸውን የጦር መሳሪያዎች በመንጠቅ ከሩቅ አካባቢ በሚመጡ ቆለኛ የከብት ዘራፊዎች በተደጋጋሚ እንዲገደሉና እንዲዘረፉ አድርገዋል፡፡ በዚህ ጥቃት የተንገበገቡት የሀረርጌ ሽማግሌዎች ለአቤቱታ ወደ ጨፌ ኦሮሚያና የፌዴራል መንግሥት ሲሄዱ ሰድበው በማዋረድ መልሰዋቸዋል፡፡
እኝህ ነውረኛና ወንጀለኛ ግለሰብ ናቸው እንግዲህ ወደ ውጭ ሄደው የኢህአዴግን አውሬነት የሚያረዱን፡፡ በልዩ ልዩ ሚዲያዎች ቀርቦ ሲጠየቅ “ለኦሮሞ ህዝብ ስለተቆረቆርኩና ኢሕአዴጎች በነጻነት ስላላሰሩኝ ሀገር ጥዬ ወጣሁ” ብሎናል፡፡ የሚገርመው ደግሞ ለኦሮሞ ህዝብ እታገላለሁ የሚለው ኦነግ “የኦነግ ደጋፊዎች ናችሁ” በሚል ስም የኦሮሞ ወጣቶችን ቁምስቅላቸውን ሲያሳይ የነበረውን ነውረኛ ግለሰብ በሁለት እጆቹ መቀበሉ!! አይ ፖለቲካ!! ውቢቷ እመቤት!!

አቶ ዮናታን ከሀገር የጠፉት በወቅቱ ኦሮሚያን በስውር ይመራ ከነበረው ሰለሞን ተስፋይ (ጢሞ) ጋር በመጣላታቸው ነው እንጂ ለኦሮሞ ህዝብ በመቆርቆራቸው አይደለም፡፡ ከሰለሞን ጋር በጥቅም ተጋጩ፤ ከርሱ የሚሰጣቸውንም ትእዛዝ አልቀበልም እያሉ ማስቸገር ጀመሩ፡፡ በመሆኑም “ቆይ! የሚል ዛቻ ደረሳቸው፡፡ በዚህም ቀን ከሌሊት እንቅልፍ አጡ፡፡ በመሀሉ እርሳቸውን የሚወዱ ሰዎች ለአጭር ጊዜ ስልጠና ወደ አውሮጳ ላኳቸው፡፡ ዮናታንም በዚያው ኮበለሉ፡፡ ታሪካቸው ይኸው ነው፡፡ (በነገራችን ላይ በመጋቢት 1993 ህወሐት ለሁለት ሲከፈል አቶ ሰለሞን ተስፋይ ከነ ስዬ አብረሃ ጋር ከድርጅቱ ተባረዋል፤ አቶ ዮናታን የሰለሞንን ዛቻ ችሎ ለአንድ ወር ቢቆይ ኖሮ ከሀገር ባልኮበለለም ነበር)፡፡

—–

የመጽሐፉ ፀሐፊ የሆኑት አቶ ኤርሚያስ ወንጀለኛ እንዳልሆኑ አምናለሁ፡፡ እኔም ወንጀለኛ ናቸው ከሚል አይደለም ይህንን የጻፍኩት፡፡ ነገር ግን ወደ ውጭ የኮበለሉት ባለስልጣናት ጠቅላላ ታሪካቸው መጠናት አለበት ባይ ነኝ፡፡ ሰውዬው እንደ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ከፖለቲካ ተሳትፎው ውጪ በግል የሰራው ወንጀል ከሌለ እሰየው! አሰላለፉን መቀየር ይችላል፡፡ ሰውየው እንደ ዮናታን ዲቢሳ በደም የጨቀየ ዶሴ በእጁ ላይ እያለ የኢህአዴግን እኩይነት የሚዘበዝብልን ከሆነ ግን በጭራሽ አንቀበለውም፡፡ ወንጀለኛ ምንጊዜም ቢሆን ወንጀለኛ ነው፡፡ የፖለቲካ አሰላለፍ ለውጥ ወንጀለኛነትን አይፍቀውም፡፡ አንድ ሺህ አንድ ነጥብ!!!

“..እንዲህ አይነት ጥያቂዎችን እነማን እንደሚጠይቁ እናውቃለን ደንቆሮ ዝቃጭ ..” ደብረጺሆን
“በስልጠናው ላይ ሰራተኛው ለኢሕአዴግ ያለውን ጥላቻ በሰፊው አሳይቶበታል። ” የካድሬዎች ሪፖርት
ይህን ሰሞን ለምርጫ የሚሆን ድጋፍ እና አዳዲስ አባላትን ለመመልመል የወያኔው ጁንታ የመንግስት ሰራተኞችን እና የዩንቨርስቲ ተማሪዎችን የመልካም ልማታዊ አስተዳደር በሚል ሽፋን ለፖለቲካ አጀንዳነት ሊጠቀምባቸው በማሰብ እያደረገ ያለው ስልጠና ከአለመግባባት አልፎ እስከ ስድብ መድረሱ ሰልጣኞችን አስቆጥቷል።

በዚሁ መሰረት የኢትዮ ቴሌኮም ሰራተኞች ለስልጠና የጠራው የወያኔ ቡድን ካድሪዎቹ የሰራተኛውን ጥያቄ መመለስ ስላቃታቸው ወደ ደብረጺሆን ያስተላለፉት ሲሆን ዶክተር (በተገዛ ዲግሪ ) ደብረጺሆን በከፍተኛ ቁጣ በተቀላቀለበት ሁኔታ ሲመልሱ ተስተውሏል። ሰራተኞቹ የሃይማኖት ነጻነት እና ሙስሊሞች ፣ ዞን 9 ፣ የኦሮሞ ተማሪዎች ፣ የኑሮ ውድነት ፣ የዘረኝነት መስፋፋት ፣ የሃገሪቱ ታሪክ ማበላሸት እና የሃገር ዳር ድንበር ፤ የሚታሰሩ ዜጎች እና የተቃዋሚዎች ሮሮ …. ፣ ወዘተ ያቀረቧቸው ጥያቂዎች ከደብረጺሆን ጋር ካለመግባባት በስድብ እና በቁጣ የታጀቡ እንደነበሩ ታውቋል።

በወያኔ ካድሬዎች ዘንድ ከፍተኛ መደናገጥ የታየበት ይህ የኢትዮ ቴሌኮም ስልጠና ዶክተር የሚባሉት ደብረጺሆን በከፍተኛ ቁጣ በሺዎች የሚቆጠረውን ሰልጣኝ የመንግስት ሰራተኛ …..ቁጣ በተቀላቀለበት አምባገነናዊ መንፈስ ድንጋጤን ተላብሰው ….. ደንቆሮ …..ደደብ … የዘቀጠ .. በሚሉ የስድብ አጀቦች ጥያቄዎቹ የነማን እንደሆኑ እናውቃለን .. በሚል ማስፈራሪያ ሰራተኛውን ማሰልታን ሳይሆን ማስጠንቀቅ በሚል እንዲሁም ለመጪው ጊዜ እርምጃ እንደሚወሰድ መል እክት በሚያስተላልፍ መልኩ ሲዝቱ ሲሳደቡ ተስተውሏል።

ዶክተር በሚባሉት ደብረጺሆን መልስ ሰራተኛው ከፍተኛ ቁጣ ይሰማ ሲሆን ከአሁን በኋላ በሚደረጉ የስልጣና ቀኖች ላይ ምንም ጥያቄ ላለመጠየቅ እና አስተያየት ላለመስጠት ሰራተኛው አድሞ ወደ ስልጠናው እንደገባ ሲታወቅ የወያኔ ካድሬዎች የሰራተኛውን ድፍርት እና በጥያቄዎች መግነን ተከትሎ ድንጋጤ የፈጠረባቸው ቢሆንም ከጀርባ ግን ሰራተኛውን ሲያበረታቱ ተስተውሏል።
ከስልጠናው መልስ ካድሪዎች ለአለቆቻቸው የሚያቀርቡት ሪፖርት እንደሚጠቁመው የመንግስት ሰራተኛውም ይሁን የዩንቨርስቲው ተማሪ ለኢሕአዴግ ያለውን ጥላቻ የሚያሳይ መሆኑን እንደሆነ ከፓርቲው ጽ/ቤት የተገኙ መረጃዎች ያሳያሉ።ሚኒሊክሳልሳዊ

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

ላለፉት 23 ዓመታት ህወሓት/ኢህአዴግ ስራዬ ብሎ ካዳከማቸውና ጉዳዬ ከማይላቸው ዘርፎች ውስጥ የሚመደበው የትምህርት ስርዓቱ ሲሆን ይህም ከኢህአዴግ ስህተቶች ሁሉ ዋነኛው እና አሳፋሪ ተግባሩ ነው፡፡ ለሁለት አስርት አመታት ትውልዱን በማምከን በሀገሩ ተስፋ እንዲቆርጥ ከገፉት ጉዳዮችም ግንባር ቀደሙ የህወሓት/ኢህአዴግ የተምታታበት የትምህርት ፖሊሲ መሆኑም ይታወቃል፡፡ ትምህርት ለአንድ ሀገር እድገት የጀርባ አጥንት መሆኑ እየታመነ የትምህርት ስርዓቱ ሆን ተብሎ በንቀት እና በዝርክር አሰራር እንዳያድግና ጥራት እንዳይኖረው ኢህአዴግ እየተጋ አሁን ድረስ ዘልቋል፡፡

በዚህ አይነቱ አጥፊ አካሄድ ምክንያትም ሀገራችን በዓለም ደሃ ሀገራት ተርታ ቀዳሚዋ ሆናለች፡፡ የተማረ እየተገፋ በስራ አጥነት ሲንከራተት እና ለስደት ሲዳረግ በካድሬነት የስርዓቱ አገልጋይ መሆን ደግሞ በተቃራኒው ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል፡፡ በተለይም ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው የገዢው ፓርቲ አባል እንዲሆኑ ሲገደዱ መቆየታቸውና የኢህአዲግ አባል ካልሆኑም ስራ ሊያገኙ እንደማይችሉ እየተነገራቸው በፍራቻ ለአባልነት የተመዘገቡ ብዙዎች እንደሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ በዚህ ሳያበቃ አሁን አሁን ደግሞ የገዢውን ፓርቲ ያረጀና ያፈጀ ኋላቀር አስተሳሰብና ርዕዮተ-ዓለም በተማሪዎች ላይ ለመጫን በየዓመቱ መጀመሪያ ‹ስልጠና› በሚል ፈሊጥ በጀት በጅቶ በግድ ሊግታቸው እየሞከረ ይገኛል፡፡

በዚሁ በያዝነው ወርም በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎች እንዲሰበሰቡና ስልጠና እንዲወስዱ ጥሪ የተላለፈ ሲሆን ስልጠናውን ያልተከታተለም መደበኛ ትምህርቱን እንደማይቀጥል ማስፈራሪያ አይሉት ማሳሰቢያ በገዢው ፓርቲ በኩል ተላልፏል፡፡ ሌላው አስገራሚ ዜና ደግሞ ተማሪዎቹ በግድ ስልጠናውን እንዲወስዱ መገደዳቸው ሳያንስ ወደ ግቢ ከገቡ በኋላ ተመልሰው መውጣት እንደማይችሉ መሰማቱ ነው፡፡ ይህም ኢህአዴግ ካድሬዎቹን የሚያሰለጥንበት ዝግ የስብሰባ ስልት መሆኑ ጉዳዩን የበለጠ አስገራሚ ያደርገዋል፡፡

ህወሓት/ኢህአዴግ ይህንን ስልጠና ሲያካሂድም፡-

1. ህግን በጣሰ መልኩ የትምህርት ማዕከላትን የፖለቲካ ማራመጃ እና የአንድ ፓርቲ ርዕዮተ-ዓለም ማስፈፀሚያ አድርጓል፡፡

2. ይህን ፋይዳ ቢስ ስልጠና በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎችና ከ800.000 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች በሚሰጥበት ወቅት ከፍተኛ የህዝብ ሀብት እያባከነ ይገኛል፡፡

3. ተማሪዎች የእረፍት ጊዜያቸውን በነፃነት ማሳለፍ ሳይችሉ በአስቸኳይ ወደ ዩኒቨርስቲዎች እንዲመለሱ ተገድደዋል፡፡

4. በሚሰጠው ስልጠናም ላይ በአክራሪነት በብሔርተኝነትና በመሳሰሉት ጉዳዩች ሽፋን በተማሪዎች ዘንድ መርዛማ ጥላቻን እየረጨ ይገኛል፡፡

5. በአጠቃላይ በስልጠናው ወቅት ርካሽ የፕሮፖጋንዳ ስልትን በመጠቀም መጪውን ምርጫ በማምታታት ለማለፍ እየሞከረ ሲሆን ይህም በአምባገነንነቱ ቀጥሎ ህብረተሰቡን አማራጭ ለማሳጣትና ሀገሪቷን ወዳልተፈለገ አለመረጋጋት ሊወስድ እየሞከረ መሆኑን ያሳያል፡፡

በመሆኑም ሰማያዊ ፓርቲ ይህን የገዢው ፓርቲ ህገ ወጥ አድራጎት አጥብቆ እያወገዘ ጉዳዩን እየተከታተለም አቋሙን ይፋ የሚያደርግ መሆኑንን ይገልፃል፡፡ ተማሪዎችም በዚህ ህገ ወጥ ተግባር ሳይደናገጡ ያለምንም ፍርሃት ህጋዊ በሆነ መንገድ ይህን ካድሬያዊ ስልጠና በማውገዝ፣ የገዢውን ፓርቲ ድብቅ ሴራ በማጋለጥ እና ለህወሓት/ኢህአዴግ የተለመደ አጥፊ ፕሮፖጋንዳ ባለመታለል ተማሪዎች በአንድነት እንዲቆሙ ሰማያዊ ፓርቲ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ነሀሴ 15/2006 ዓ.ም ሰማያዊ ፓርቲ

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ከኢትዮጵያ ሀገሬ የደቀቀ ኢኮኖሚ ላይ በማን አህሎኝነት ወጪ ተደርጎ፣ ቅጥ ባጣ መልኩ በመላ አገሪቱ እየተከበረ ስላለው የቀድሞ አምባገነን ጠ/ሚኒስትር ሁለተኛ ሙት ዓመት ዝክርም ሆነ ሰውየውን ዛሬም በአፀደ-ህይወት ያለ ለማስመሰል እየሞከሩ ላሉት ጓዶቹ አንዲት ምክር ብጤ ጣል ማድረጉ ተገቢ ነው ብዬ ስለማስብ በአዲስ መስመር እንዲህ እላለሁ፡-

አብዮታዊው ገዥ-ግንባር ግንቦት ሃያ፣ የህወሓት ምስረታ፣ የብአዴን አፈጣጠር፣ የኦህዴድና የደኢህዴን ውልደት፣ የብሔር ብሔረሰቦች በዓል፣ የባንዲራ ቀን፣ የመከላከያ ሳምንት፣ የፍትሕ ሳምንት፣ የሕዳሴ ግድብ መሰረት ድንጋይ የተጣለበት… ጅኒ-ቁልቋል እያለ ዓመቱን ሙሉ በማይጨበጥ ተራ ፕሮፓጋንዳ ማሰልቸትን መንግስታዊ ኃላፊነት አድርጎታል፡፡ ይህ እንግዲህ ለቁጥር የሚያታክቱ፣ በነጭ ውሸት የታጨቁ እና በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ቅኝት የተንሸዋረሩ ‹ዶክመንተሪ ፊልሞቹ›ን ረስተንለት ነው፡፡

ይህ ሁሉ ያልበቃው ‹‹ጀግናው›› ኢህአዴግ ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህልፈት ወዲህ፣ ወርሃ-ነሐሴንም እንደ ግንቦት ሃያው ሁሉ የሟቹን ታጋይነትና አብዮታዊነት፤ ሕዝባዊነትና አርቆ አስተዋይነት፤ የርዕዮተ-ዓለም ተራቃቂነትና የአየር ንብረት ተካራካሪነት፤ በፖለቲካ ቢሉ በኢኮኖሚ ቁጥር አንድ ጠቢብነትና ባለራዕይነት፤ ፍፁም ፃድቅነትና ሰማዕትነት…. የሚተረክበት ሲያደርገው ቅንጣት ታህል ሀፍረት አልተሰማውም፡፡ ሰሞኑን በ‹‹ኢትዮጵያ›› ቴሌቪዥን ግድ ሆኖብን ተመልክተንና ሰምተን በትዝብት ካሳለፍናቸው ‹‹መለስ፣ መለስ›› ከሚሉ የከንቱ ውዳሴ አደንቋሪ ድምፆች በተጨማሪ፣ የኦሮሞን ባሕላዊ ልብስ ሲያለብሱት፣ ሐረሪዎች ጋቢ ሲደርቡለት፤ በደቡብ የሚገኙ ብሔሮች የየራሳቸውን ባሕል የሚወክሉ አልባሳት ሲሸልሙት፣ ስለወላይታነቱ ሲመሰክሩለት… ደጋግመን ለመመልከት ተገደናል፤ ይሁንና ድርጅቱ ስለ ቀድሞ ሊቀ-መንበሩ አልፋና ኦሜጋነት ለመስበክ ዙሪያ ጥምዝ ከዳከረለት ከእንዲህ አይነቱ የተንዛዛ ፕሮፓጋንዳ ይልቅ፣ በዚሁ የቴሌቪዥን መስኮት የቀረበ አንድ ጎልማሳ ‹‹መለስ ሁሉም ማለት ነው›› ሲል የሰጠው አስተያየት፣ ቅልብጭ አድርጎ ይገልፅለት ነበር ብዬ አምናለሁ፡፡ የዚህ አይነቱ ምጥን አስተያየትም በጥራዝ ነጠቅነት ዘላብዶ የኋላ ኋላ በሀፍረት ከማቀርቀር ያድናል፡፡ ለምሳሌ እናንተ የግንባሩ ካድሬዎች ስለመለስ ምሁርነት ለመናገር ስትዳዱ ሁሌ የምትደጋግሙት፣ ያንኑ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ አርቃቂነቱ እና የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ኀልዮት አዋቃሪነቱ ነው፡፡ ግና፣ ይህ ‹‹ንድፈ-ሃሳብ›› ተብዬ ራሱ በርዕዮተ-ዓለምነት ለመጠራት የማይበቃ የተውሸለሸለ ጭብጥ ስለመሆኑ በርካታ ምሁራን በጥናቶቻቸው ከማስረገጣቸው ባሻገር፣ አገሪቷን ለከባድ ኢኮኖሚያዊ ድቀት፣ ሕዝቧን ደግሞ ለጥልቅ ድህነት መዳረጉን ብቻ ማስታወሱ በቂ ይሆናል፡፡ ስለልማታዊ መንግስት አዋጭነት በብቸኝነት እንደተከራከረ ተደርጎ የሚለፈፈውን እንኳን ንቆ መተው ሳይሻል አይቀርም፡፡ ከታንዲካ ማካንደዋሬና መሰል የፅንሰ-ሃሳቡ አበጂዎች የዘረፋቸውን መከራከሪያዎች ማን ዘርዝሮ ይዘልቀውና፡፡ ‹መለስን ቅበሩት› የምለውም፣ እንዲህ ያሉ አስነዋሪ ማንነቶቹን ማስታወስ ስለሚያም ነው፡፡

እናም እውነት እውነት እላችኋለሁ፡- ስለሰውዬው የምትነግሩን እና የምታስቀጥሉት ‹ሌጋሲ›ም ሆነ የምትተገብሩት ረብ ያለው አንድም ራዕይ የለምና ዝም፣ ፀጥ ብላችሁ የምራችሁን ቅበሩት፡፡ እስቲ! ኦጋዴንን ተመልከቱ፤ ካሻችሁም ወደ አኝዋኮች ተሻገሩ፤ ያን ጊዜ እናንተ በአርያም የሰቀላችሁት ሰው፣ ለነዚህ ሁለት ብሔሮች የቀትር ደም የጠማው ጨካኝ መሪ እንደነበር፣ በክፋት ትዕዛዞቹ ጥፋት ከተረፈ ጠባሳ ትረዱታላችሁ፡፡ ለአቅመ-ሔዋን ያልደረሱ ህፃናት በሰልፍ የሚደፈሩባት፣ ወጣቶች እንጀራ ፍለጋ በተስፋ-ቢስነት ጥልቁን ውቅያኖስ ሰንጥቀው ለመሰደድ የማያመነቱባት፣ የጤና ኬላ ማግኘት ተስኗቸው በልምሻ የሚባትቱ ብላቴኖችን በአቅም-የለሽነትና በቁጭት የምናስተውልባት ደካማ አገር አስረክቦን እንዳለፈ ከወዴት ተሰወረባችሁ? ከቀዬዎቻቸው በጉልበት ለተፈናቀሉ ወገኖች በመቆርቆር ‹‹ሕግ ይከበር!›› ባሉ በየጉራንጉሩ ወድቀው እንዲቀሩ የተፈረደባቸው ጎበዛዝትን ሬሳ እንድንቆጠር ያደረገን ደመ-ቀዝቃዛ ‹መሪ› እንደነበረስ ስንት ጊዜ እያስታወስን እንቆዝም? ቀደምት አባቶች ወራሪውን ፋሽስት ለማንበርከክ የተዋደቁባቸው ጢሻና ኮረብቶች በዚህ ዘመን የዜጎች ወደሞት አገራት መሸጋገሪያ ጽልማሞቶች የሆኑት በማን ሆነና ነው? ከሕግ ተጠያቂነት ቢያመልጥ፣ ከታሪክ ተወቃሽነት ልትታደጉት የምትችሉ ይመስላችኋልን?

…ይልቅ እመኑኝ! ፀጥ ብላችሁ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ጥልቅ ጉድጓድ ቆፍራችሁ ቅበሩት! ላይመለስ በመሄዱም እንደ ግልግል ቆጥራችሁት እርሱት!! መቼም በገዛ ራሱ ሕዝብ ላይ ትውልዶች ይቅር ሊሉት የሚሳናቸውን ይህን መሰሉ መከራ ላዘነበ ሰው በአፀደ-ስጋ ሳለም ሆነ በበድን የሙት መንፈሱ ስር በየዓመቱ ለአምላኪነት መንበርከክ፣ የናንተን አልቦ ማንነት እንጂ ሌላ አንዳች የሚነገረን ቁም ነገር ጠብ ሊለው አይችልም፡፡ ይህም ሆኖ ለመለስ አምልኮ እጅ መስጠት አሳፋሪነቱ፣ ለካዳሚዎቹ ብቻ መሆኑን መስክሮ ማለፉ የቀሪዎቻችን ዕዳ እንደሆነ መገንዘብ አለብን፡፡

Image

በሆዳችን አንገዛም !!!!! የተማሪው የዛሪው መሪ መፈክር
“እየተቃውመ የሚሰለጥን እያጉረመረመ የሚበላ ትውልድ ……… ከሰልጣኞቹ ይልቅ አሰልጣኞቹ ጥያቄ የሚያጭር ንግግር እያደረጉ ተቃውሞውን ያባብሱታል ” ከወያኔ ካድሬዎች አንዱ በስካይፒ

ምንሊክ የዘመናዊ ኢትዮጵያ አባት ነው ።……… ኢትዮጵያዊነት በስር መሰረት ሲተላለፍ የመጣ ስለሆነ በዘረኝነት አይናድም።….. አናካሽ እና ከፋፍለህ ግዛ የሚለውን ሰነዳችሁን አቃጥሉት ።… ስልጠናው ይቁም ።….
የተትረፈረፈ ምግብ አምጥታችሁ በሆዳችን ልትገዙን ከሆነ አትሞኙ ። ምግቦች ከመትረፍረፍ የተነሳ እየተደፉ ነው ለምን ለጎዳና ተዳዳሪዎች አይሰጡም።……. ለምን ስንበላ በፖሊስ እንታጀባለን ? ………
የህዝብ ገንዘብ የገዢውን ፓርቲ ፕሮፓጋንዳ ለመርጨት ያላግባብ እየተጠቀማችሁበት ነው።፣…………..
ሕዝብን እየተሳደባችሁ እድሜያችሁ የሚረዝም እንዳይመስላችሁ …. 2007 ምርጫ ድጋፍ ለማግኘት ትባዝናላችሁ ……የሃገር ሃብት ለናንተ ፖለቲካ አጀንዳ እየዋለ እናንተ በቻይና ብድር ታራውጡናላችሁ። ………….ለሕዝብ ጥቅም የዋለ የሃገር ሃብት የለም። …የሚያሳዝነው ሕዝቡ መሮታል የሚመራው አጥቶ ነው እንጂ ….ሰበብ እየፈጠራችሁ ንጹሃንን እያሰራችሁ ተቃዋሚዎችን ወህኒ እየከተታችሁ ሌላውን እያሳደዳችሁ ምርጫ የሚኖር ይመስላቹሃል? …. ከ እናንተ ጋር የሚወዳደር ያለ ይመስላችኋል።
Image

ሰልጣኝ ተማሪዎች ስልጠናው ግጭትን የሚያስነሳ በመሆኑ እንዲቆም ጠየቁ ።ሰልጣኞቹ ፌስ ቡክ እንዳይጠቀሙ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) VIA ነገረ ኢትዮጵያ / Negere Ethiopia
ከነሀሴ 9 ጀምሮ በደብረማርቆስ ከተማ በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፣ ተክለኃይማኖት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ቤተ መንግስት፣ መምህራን ኮሎጅና የደብረ ማረቆስ መሰናዶ ትምህርት ቤት ተከፋፍለው በአራት የሥልጠና ቦታዎች እንዲሁም 45 የውይይት ቡድኖች ስልጠና እየወሰዱ የሚገኙት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስልጠናው ከፋፋይና ለትውልዱ ጎጅ በመሆኑ ሊቆም እንደሚገባ ማሳሰባቸውን ሰልጣኞቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡

ተማሪዎቹ በተለይም ‹‹የኢትዮጵያ ህዝቦች ትግልና የአገራችን ህዳሴ›› በሚል ህዝብን ከህዝብ ያጋጫል ያሉትን ያሉት ሰነድ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ እንዳሰሙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ተማሪዎች ‹‹እስር በእስር ለማናከስ የተዘጋጀ ሰነድ ነው፡፡ በመሆኑም ሰነዱ ሊቃጠል ይገባዋል፡፡ በቀጣይ ወደ ዩኒቨርሲቲ ስንገባ የሚያጋጨን ስለሆነ ስልጠናው በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል፡፡ የኦሮሚያ ተማሪዎችን አመጽ የቀሰቀሰው በዚህ የኢህአዴግ ከፋፍለህ ግዛ ሴራ ነው፡፡ ሰነዱ እንደሚለው ኢትዮጵያ ከታናሽንት ወደ ታላቅነት ሳይሆን ከታላቅነት ወደታናሽነት ነው የወረደችው፡፡ ለዚህ ከፋፋይ ሰነድ በርካታ ወጭ ወጥቶ እርስ በእርሳችን ለማናከስ ከሚጣር በገንዘቡ በየጎዳናው የወደቁ ኢትዮጵያውያንን ከርሃብ መታደግ ይችል ነበር፡፡›› በሚል ጠንካራ ተቃውሞ ማሰማታቸውን ገልጸውልናል፡፡

ተማሪዎቹ አክለውም ‹‹አጼ ምኒልክ በጊዜያቸው መልካም ስራ ሰርተዋል፡፡ ስህተት ሰሩ እንኳ ቢባል የዘመኑ ወጣቶች ያ ስህተት ላይ ተሳታፊዎች ባለመሆናችን የእኛም ስህተት ተደርጎ ከሌሎቹ ጋር ለማናከሻነት መዋል የለበትም፡፡ በዚህ ዘመን ህወሓት፣ ብአዴንና ሌሎቹ የኢህአዴግ አባላት እንጅ ህዝብ ነፍጠኛ ሊባል አይገባም፡፡ ብአዴን አማርኛ ተናጋሪውን አይወክልም፡፡›› ማለታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተለይ ኢህአዴግ ስኬታማ እንደሆነ በሚገልጸው የሰነዱ ክፍል ላይ ካድሬዎች በየ እምነት ተቋማት ጣልቃ እየገቡ በመሆኑ የእምነት ነጻነት እንደሌለ፣ ጋዜጠኞች እየሰደዱ መሆንንና ሚዲያዎች በመዘጋታቸው ሀሳብን በነጻነት መግለጽ እንዳልተቻለ፣ የመድብ ፓርቲ እንደሌለና የኢህአዴግ አፋኝ መሆኑን በመግለጽ ሰነዱ ላይ የተጠቀሱት ስኬቶች በተግባር እንደሌሉ ተከራክረዋል፡፡

ትምህርትን በተመለከተ ሰነዱም ሆነ ኢህአዴግ በየጊዜው ያብጠለጥላቸዋል ያሏቸውን አጼ ምኒልክ ‹‹እኔ ቤት እንጀራ የለም፡፡ እንጀራ ያለው ትምህርት ቤት ነው ፡፡›› ብለው እንደነበር በማውሳት ከመቶ አመት በፊት ከነበረው ስርዓትም ያነሰ መሆኑን የተከራከሩ መኖራቸውን ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም የትምህርት ስርዓት ከመቼውም ጊዜ በባሰ መውደቁ፣ ተማሪዎች ተመርቀው በተማሩት ዘርፍ ሳይሆን ኮብልስቶንን ጨምሮ ያልተማሩትን እንዲሰሩ መገደዳቸውንና ስራ አጥ መሆናቸውን በመግለጽ የትምህርት ስርዓቱን ውድቀት አስረድተዋል ተብሏል፡፡ በስልጠናው ወቅት ከኢህአዴግ ስኬት በስተጀርባ ዋናው ተዋናኝ ሆነው የቀረቡት አቶ መለስ ዋነኛ የመወያያ ርዕስ እንደነበሩና ተማሪዎችም ‹‹አማርኛ ተናጋሪውን አቶ መለስ አከርካሪውን መትተነዋል ብለዋል፡፡ አከርካሪውን ከተመታ አሁን ሌላ ከፋፍለህ ግዛን የሚያሰፍን ስልጠና ለምን አስፈለገ? የመለስን ራዕይ አሳካለሁ የሚለው ብአዴን አማርኛ ተናጋሪውን አይወክልም፣ ህዝቡን የሚሳደቡ ባለስልጣናት ምንም አይነት እርምጃ የማይወሰድባቸው ስርዓት ለህዝብ ንቀት ስላለው ነው፣ ኢህአዴግ ራሱ ዘረኛ ነው፡፡›› በሚል ተቃውሟቸውን ገልጸዋል፡፡

ስልጠናው ወጣቱ ኢህአዴግ የያዘውን የተሳሳተ መስመር ለማስያዝ የሚጥርና የማይጠቅም በመሆኑ ሊቆም እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ በውይይቱ ወቅት ዝምታን የመረጡ ተማሪዎችም እንደ ወጣት ማንም አውቅልሃለሁ ሳይላቸውና ሳይፈሩ ስህተቱን እንዲቃወሙ ማሳሰባቸው ታውቋል፡፡ በስልጠናው ወቅት አሰልጣኞች ተማሪዎች ፌስ ቡክ ውሸት በመሆኑ እንዳይጠቀሙ፣ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ፌስ ቡክን በመጠቀማቸውና በፌስ ቡክ አማካኝነት በሚነሳ ብጥብጥና ሌሎች ችግሮች ምክንያት መንግስት በሚወስደው እርምጃ ተጎጅ እንደሚሆኑ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላት ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ ተማሪዎች በስልጠናው እንዳይሳተፉ ጥረት ተደርጓል ያሉት ሰልጣኞቹ ‹‹አክራሪና አሸባሪ የሚባሉ አካላት መሳሪያ እንዳትሆኑ፣ ለእነዚህ አካላት መሳሪያ በመሆናችሁ የእርምጃው ሰለባ ትሆናላችሁ፡፡ መንግስት ተጠያቂ አይሆንም፡፡›› የሚል ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል፡፡

በስልጠናው ወቅትም ተቃዋሚዎች፣ ጋዜጠኞች፣ ፌስ ቡከኞች፣ መንግስት በእምነታቸው እንዳይገባ ኢትዮጵያውያን በአጥፊነት መፈረጃቸውንና ተማሪዎች ከእነዚህ አካላት መራቅ እንዳለባቸው ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክት መተላላፉን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ተማሪዎች በበኩላቸው ‹‹በአሁኑ ወቅት ኢህአዴግ ሚዲያውን እያፈነ ነው፣ ተቃዋሚዎችን እያሰረ ነው፣ በእምነት ጉዳይ ጣልቃ እየገባ ነው፣ የሚቀጥለውን ምርጫ ወቅት የእነዚህ ሁሉ ጭቆና ወደ አመጽ ቢያመራ ተጠያቂው ማን ነው? ለምን እንደ ሻዕቢያ በግልጽ አምባገነን መሆናችሁን አታውጁም? ህዝቦችን በየ አካባቢው እያፈናቀላችሁ ለምን ምኒልክን ትከሳላችሁ? ብሄራዊ እርቅን ለምን ትፈራላችሁ? የስልጠናው በጀት ይነገረን? ትራንስፎርሜሽኑ አልተሳካም፣ አባይ ግድብ የኢህአዴግ ፕሮጀክት ነው እና ሌሎችንም ጥያቄዎችና አስተያየቶች ማንሳታቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በደብረማርቆስ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በአሰልጣኝነት ከተመደቡት መካከል አብዛኛዎቹ የገዥው ፓርቲ የካቢኔ አባላት እንደሆኑና በተለይ ታሪክ ላይ ያተኮረው የስልጠናው አካል በብአዴን አባላት ጭምር ቅሬታ እንዳስነሳ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ነሃሴ 9 የጀመረው ስልጠና በሁለት ዙር ለ15 ቀናት የሚሰጥ ሲሆን በዋናነት የኢትዮጵያ ህዝቦች ትግልና የአገራችን ህዳሴ፣ የታድሶ መስመርና የኢትዮጵያ ህዳሴ፣ ልማታዊ ዴሞክራሲ ስርዓትና ፈተናው እንዲሁም ህገ መገንስታዊ መርህና የሰላማዉ ትግል ስልት የተሰኙ አራት ጥራዞችን ያካተተ እንደሆነ ታውቋል፡፡ በቀጣይ ቀናት ከሰልጣኞቹ የተላኩትን የስልጠኛ ሰነዶችና መረጃዎች እየተከታተልን ለአንባቢያን የምናደርስ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

‹‹ይድረስ ላንቺ››

ተፃፈ ከስድስተኛ ተከሳሽ በዘላለም ክብረት

ወዳጄ ልቤ ከቶ እንደምንድን ነሽ? እውን እኔና አንቺ በአለም ስንኖር ሌላ የመገናኛ ዘዴ አጥተን ወደ snail mail እንመላለሳለን ብለሽ አስበሽ ታውቂያለሽ? ለማንኛውም እንዲህ ሆነ፡፡ ጥጋበኛ ሰው ያስቀናኝ ጀምሮልሻል፣ ጥጋበኛ እንዲህ የሚለው ትዝ አለኝ፡፡

‹‹ ….ደብዳቤ ቢጽፉት እንደ ቃል አይሆንም፣

እንገናኝ እና ልንገርሽ ሁሉንም….››

የደላው! ቢያሻው በደብዳቤ፣ ሲፈልግ በአካል እያማረጠ እኮ ነው፡፡ ለእኔ አሁን ባለሁበት ሁኔታ ሁለቱም ቅንጦት ነው (ወይ ደብዳቤው አይደርስሽም ወይም አንቺን ማየቴ ሊገደብ ይችላል)፡፡ቆይ ትንሽ የጎን ወሬ ላዋራሽና ምክንያቱን እነግርሻለሁ፡፡ ‹‹አንቺ›› ተብለሽ በዚህ ደብዳቤ ስለተጠቀስሽው ‹‹አንቺ››ና ይሄን ደብዳቤ ለሚያነቡ ወዳጆች የዕምነት ክህደት ቃሌን በትንሹ ላስፍር፡፡

እመቤት ሲልቪያ ፓንክረስት የኢትዮጵያ ፍቅረኛ (Ethiopian by choice) ዱቼ ሞሶሎኒ እትዮጵያን በወረረ ጊዜ፤ ወራሪው ሃይል በመላው ኢትዮጵያ ‹‹ የኢትዮጵያን ስም እያነሱ መፃፍ ክልክል ነው›› የሚል ያልተፃፈ አዋጅ አውጆ እንደነበር ይነግሩናል፡፡ በዚህም ምክንያት ፀሀፍቱና አዝማሪያኑ ስውር መጠሪያ መጠቀም ስላስፈለጋቸው እስከ ዛሬ ድረስ ተወዳጁ ሕዝባዊ ዘፈን አንቺ ልጅ አንቺ ልጅ እንደ ስውር የፍቅር ዘፈን ተበርክቷል፡፡ በዘፈኑ ‹‹አንቺ ልጅ ›› የተባለችውም ኢትዮጵያ ናት፡፡ እኔስ በዚህ ዘመን ‹ይድረስ ለባለ ታሪኩ›፣ ‹ይድረስ ለባለ ንብረቱ›… እንደሱ የሀዘን ደብዳቤ ርእስ ‹ይድረስ ለኢትዮጵያ › በማለት ፋንታ ‹ይድረስ ለአንቺ› ለማለት ስውር መጠሪያ ተጠቅሜያለሁ? ፤ በፍፁም! ጌቶች እንደሚሉት ሕገ መንግስቱ የመናገር ነፃነቴን ሙሉ ለሙሉ አስከብሮልኛልናi

ቧልቱ ይቆየንና በዚህ ደብዳቤ ርዕስ ዙሪያ ያለማንም አስገዳጅነት የእምነት ክህደት ቃሌን ላስፍር አንቺ የተባለችው ኢትዮጵያ አይደለችም፡፡ ‹አንቺ› የኔዋ ሀቢቢ ግን ባለሽበት ይድረስሽ፡፡ ውዴ እንግዲህ በዚህ ደብዳቤ ያለፈውን እያነሳሁ እነግርሻለሁ፡፡ወይ ትስቂያለሽ (ሳቅሽ እንዴት ያምራል?) ወይ ደግሞ ታዝኛለሽ (እኔን!)

ይህንን ደብዳቤ የመፃፍ መብት

እነሆ ላንቺ ስለሆነው ሁሉ ላጫውትሽ ስጀምር፤ በመነሻው ያሰብኩት ነገር ይሄን ደብዳቤ የመፃፍ ሕጋዊ መብት አለኝን? የሚለውን ጥያቄ ነው፡፡ ለዚህም መነሻዬ አሁን ያለሁበት ሁኔታ ነው፡፡ በመጀመሪያ “ሕገ-መንግስታዊ ስርአቱንና ሕገ-መንግስቱን በሀይል ፣በዛቻና በአድማ ለመናድ በመምከር/ በመናድ” ወንጀል ተጠርጥሬ የታሰርኩ ቢሆንም፤ በታሰርኩ በ23ኛው ቀን ወንጀል ወንጀልን፤ ጥርጣሬ ሌላ ጥርጣሬን እየወለደ የተለያዩ የሽብር ተግባራትን ለመፈፀም ለማሴርና ለማነሳሳት ወንጀል ተጨማሪ ጥርጣሬ በፓሊስ ዘንድ በማሳደሬ የክፋት ልኬ ከፍ ያለ ሲሆን፤ በመጨረሻም ሕገ-መንግስቱን እንደ እያሪኮ ግንብ ለመናድ በመሞከር፤ ሕብረተሰቡን ደግሞ ከሚተነፍሱት የሰላም አየር ለማቆራረጥ ከማሰብ የተለያዩ የሽብር ተግባራትን ለመፈፀም ሲንቀሳቀስ ተይዟል በሚል ወንጀሎች ተከስሼ በማረፊያ ቤት እገኛለሁ፡፡ ይሄን ሁሉ የምነግርሽ ‹ለ አንቺ› አዲስ ነገር ነው በማለት አይደለም፡፡ ይልቁንስ ያለሁበት የእስር ሁኔታ ደብዳቤ ካንቺ ጋር እንዳልፃፃፍ ይከለክለኛልን? የሚለውን ለማስረዳት በማሰብ ነው፡፡

መቼም አሁን ያለሁበት ሁኔታ ተገቢ ነው ብዬ ባላምንም ‹ ዋስ ጠበቃዬ ነውና› ስለመብቴ ስናገር ያን የፈረደበት ህግ መጥቀሴ አልቀረም፡፡ ታዲያስ በእስር ላይ ያለ ሰው ከወዳጁና በሕይወቱ ጋር ደብዳቤ ሊፃፃፍ ምን ገደብ አለበት? ይላል ስል፤ ስለፌደራል ታራሚዎች አያያዝ የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 138/1999 በአንቀፅ 18 ላይ “ታራሚዎች (ተጠርጣሪዎች) ከማረሚያ ቤቱ (ከማረፊያ ቤቱ) ውጭ ካሉ ሰዎች ጋር መፃፃፍ ይፈቀድላቸዋል፡፡ ሆኖም ለጥበቃ ስራ ተቃራኒ የሆነ ተግባር እንዳይፈፀም በፅሁፎቹ ላይ ቁጥጥር ይደረጋል” በማለት የኔና አንቺ ደብዳቤ መፃፃፍ በሕግ የተፈቀደ ነገር እንደሆነ ደንግጎልናል፡፡ አሜን! (እንዲያው ይሄ ልጅ አሁንስ ተስፋዬ.. ማነው ? ሕጉ አይደለምን… የሚል የጅል ዘፈኑን አላቆምም እንዴ ብለሽ እንደማታሾፊብኝ እምነቴ ነው) ጓድ ሌኒን በዛች የፒተርስበርግ እስር ቤት ውስጥ ደብዳቤ መፃፃፍ አትችልም ተብሎ ተከለከለ እርሱ ግን የ Russia Social Democratic Party ን ፕሮግራም መፅሀፍ ውስጥ በየመስመሮቹ መሀል በ Invisible Ink በመፃፍ ታሪክ ስራ፡፡ እነሆ እኔ ግን በትናንት ሌኒኒስቶች (ፋና)፤ በዛሬ አሳሪዎቻችን መልካም ፈቃድ ደብዳቤ የመፃፃፍ ሕጋዊ መብቴ ተከብሮልኝ ይሔው በነጩ ወረቀት ላይ እንደ ሕዳሴው ባቡር እፈነጭበታለሁ፡፡

እንዲህ ሆነልሽ

አበባዬ- አፄ ሀይለስላሴ ከማንኛውም ባለስልጣን በሕይወት ዘመናቸው የበለጠ የቀረቧቸው የነበሩት ከ1934-1948 ድረስ ለ14 ዓመታት በፅህፈት ሚንስትርነት ያገለገሏቸውን ፀሀፊ ትዕዛዝ ወልደ ጊዎርጊስ ወልደ ዮሀንስን እንደ ነበር ነግሬሻለሁ? ወዳጅነትና ፍቅር ያልፋልና ሀይለስላሴና ወልደ ጊዎርጊስ ተጣሉ፡፡ የአፄ ሀይለስላሴ መንግስት መፅሀፍ ፀሀፊ አቶ ዘውዴ ረታ የወልደጊዎርጊስን መጨረሻ ሲተርኩ፡፡

‹‹ ፀሃያማው ሚያዚያ 17/1948 ቀን ለ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሀንስ እንደ ሌሎቹ ቀናት ብሩህ ሁና ነበር የነጋችው፡፡ ብሩህ ሁና እንደምታመሽም አልተጠራጠሩም ነበር፡፡ ምን ያደርጋል! ያች ክፉ ሰኞ የወልደጊዎርጊስ ከፍተኛ ስልጣን መጨረሻ ሆነች፡፡ በእኩለ ቀን ገደማ ቤተ መንግስት ተጠርተው ከፅህፈት ሚንስተርነታቸው ተነስተው የአሪሲ ጠቅላይግዛት ደረሳቸው››

(መፅሀፉ አጠገቤ ስለሌለ ቃል በቃል አልጠቀስኩም)

ወልደጊዮርጊስ ተሽረው ከቤተ-መንግስት እንዲርቁ የተደረገበት ምክንያት የሀይለስላሴን ወንበር በሰዒረ መንግስት ለመገልበጥ አስበዋል በሚል ምክንያት ነበር፡፡ወልደጊዎርጊስን እዚህ ጋር ማንሳቴ የሚያዚያ 17 ስለት እኔም ጋር በመድረሷ ነው፡፡ ውዴ! የእኔዋን ሚያዚያ 17/2006 ዓ.ም ውሎ እንደ ዘውዴ ረታ ስተርክልሽ ይሔን መሳይ ይሆናል፡፡

‹‹ ፀሃያማዋ ዓርብ ሜያዚያ 17/2006 ዓ.ም አጀማመር እንደ ወትሮው አልነበረም፡፡የጠዋት ትምህርት ክፍለ ጊዜ እንዳይረፍድብኝ እየተቻኮልኩ ወደማስተምርበት (የመጨረሻ ክላስ ነበር) አምቦ ዩንቨርሲቲ ስሄድ፤ ተማሪዎች አዲስ የተዘጋጀውን የአዲስ አበባ ከተማ መሪ እቅድ ‹ሕገ-መንግስታዊ አይደለም በሚል መነሻ የተለያዩ መፈክሮችን እያሰሙ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው ነበር፡፡ ሰልፉ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተካሂዶ እንደተጠናቀቀ በሰልፍ ምክንያት የቀረውን የመጨረሻ ክላስ ሚያዚያ 18/2006 ዓ.ም ለማካሄድ ተማሪዎቼ ጋር ቀጠሮ ይዤ ብለይም ‹ሰው ያቅዳል ፣ እግዜር ይስቃል› እንደሚባለው ሆነና በዛች ሚያዚያ 17/2006 ዓ.ም ማምሻ ላይ እንደ ወልደጊዎርጊስ ወልደ ዮሃንስ ‹የመንግስትን ዙፋን በሕዝባዊ አመፅ ልትነጥቅ አሲረሀል› በሚል ክስ በቁጥጥር ስር እንደዋልኩ የደህንነት ግሪሳዎች (8 ወይም 9 የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አባላት ) አበሰሩኝ፡፡

) ነገ ጠዋት 3 ሰዓት እንዲገኙ ብለው በስልክ ቢጠሩኝ ‹እሺ ነገ ሶስት ሰአት ላይ ክላስ አለኝ ከክላስ ወደ 9 ሰዓት አካባቢ አመጣለሁ › ብዬ የምቀርበውን ሰው ይሔን ሁሉ ሀይል ከሁለት መኪና ጋር በመመደብ ላከበረኝ መንግስቴ ‹ጉዳት› ባሰብኩ ግዜ ነው፡፡ ላክባሪዬ ውለታ መላሽ ያርገኝ i

ዓለሜ- ደብዳቤዬን እያነበብሽው እንደሆነ ተስፋ አለኝ፡፡ በቁጥጥር ስር ውሏል የምትለው ሀረግ ድሮም ትንሽ ፈገግ ታደርገኝ ነበር፤ አሁን ደሞ እኔን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከአዲስ አበባ የመጣው የደህንነት ቡድን መሪ የመሰለኝ እድሜው ትንሽ ገፋ ያለ ሰው አንድ ሶስቴ ስልክ እየደወለ (ለማን ይሆን) ‹በቁጥጥር ስር አውለነዋል› እያለ መልክት ሲያስተላልፍ ስሰማ ፈገግ ማለቴ አልቀረም፡፡ ሀሳቤ ልቤ ፣ ይሄውልሽ ከስራ ቦታዬ ‹ሀገር ሰላም› ሕዝባዊ አመፅ ለመቀስቀስ አስበሃል በሚል ጥርጣሬ በቁጥጥር ስር የዋልኩት እንዲህ እንደገለፅኩት ነበር፡፡ ከሚያዚያ 17/2006 -ሀምሌ 11/2006 ዓ.ም ያሉት 84 ቀናት የተደጋገሙና ሕይወት አልባ በመሆናቸው እንዲሁ ከማሰለችሽ 5 ሁነቶችን ልፃፍልሽና ዘና በይ፡፡ ከሁነቶቹ በፊት ግን ስለ 84 ቀናቱ አጭር መግለጫ ልስጥሽ፡፡

የመጀመሪያዎቹን 75 ቀናት በፌደራል ወንጀል ምርመራ ዘርፍ (ማዕከላዊ) ጥብቅ ጥበቃ ክፍል (Siberia) ውስጥ 5 ቁጥር የተባለ 4 ሜትር በ5 ሜትር የሆነችና 5 ፍራሾችን በምትይዝ ክፍል ውስጥ ከረምኩ፡፡ ክፍሉ የተፈጥሮ ብርሀን በምንም አይነት መንገድ (ቀንን ጨምሮ) የማይገባበት ሲሆን፣ ለ24 ሰዓታት የመብራት ብርሀን ይበራበታል፣ መብራት ሲጠፋ በጄኔሬተር ሀይል ይተካል፡፡ ጄኔሬተሩ ነዳጅ ሲጨርስ ደግሞ ቀንም ሆነ ማታ ጨለማ ነው ባትሪ፣ ሻማ፣ ማንኛውንም አይነት ሰዓት መያዝ አይቻልም፡፡ ጠዋት 12 ላይ ለ10 ደቂቃ ፤ ማታ ከ10 ሰዓት አስከ 12 ሰዓት ለ 10 ደቂቃ ሽንት ቤት ለመጠቀም የክፍላችን በር የሚከፈት ሲሆን፤ በቀን ውስጥ ከ15 – 20 ደቂቃ ለሚሆን ጊዜ ደግሞ ከክፍላችን በየተራ ወጥተን ነፋስ/ፀሀይ እናየለን፡፡ ከዛ ውጭ በቀን ውስጥ ከ23 ለሚበልጠው ሰዓት የክፍሉ በር ዝግ ሲሆን ጮክ ብሎ ማውራትና መዝፈንም ቅጣት ያስከትላል፡፡

ወዳጄ በነዚህ 75 ቀናት ስንት ‹አሸባሪ› ወዳጆችን አፈራሁ መሰለሽ፡፡ መንግስቴ የ 15 እና የ14 ዓመት ልጆችን በአሸባሪነት ጠርጥሮ እንደሚያስርም ለመረዳት ችያለሁ፡፡ አብረውኝ በእስር የነበሩት ወዳጆቼ ጥርጣሬ አጅግ የተለየ ነው፡፡ ከአል-ሸባብ አስከ ኦብነግ እስከ ኦነግ እስከ የቤኒሻንጉል ጉምዝ ሕዝቦች ነፃ እውጭ ግንባር እስከ አቂዳ(አዲስ የሽብር ቡድን)… ስቃይን መማር ጥሩ ነውና ሁለት ለሚሆኑ ቀናት ብቻዬን በመታሰሬም solitary confinement ን experience ለማድረግ ‹ታድያለሁ›፡፡ በርግጥ ብቻዬን ታስሬ ነበር ከምል ካንቺ ሀሳብ ጋር ታሰርኩ ብል ይቀለኛል፡፡

አምስቱን ሁነቶች ዘንግቼ ስለ ስቃዬ ተንዛዛሁብሽ ይሆን? ለዚህ ተግባሬ በእስረኛ ቋንቋ ‹ተፀፅቻለሁ›፡፡ በቃ ወደ ጉዳዮቹ፡፡ ከዚህ በታች የምገልፃቸው ሁነቶች የ84 ቀናቱ የእስር ወቅት (የምርመራ) ጊዜ ምን እንደሚመስል እንደነበር ያስረዱሻል ብዬ አስባለሁ፡፡ (ሁሉም በእውነት እኔ ላይ የደረሱ ጉዳዮች ናቸው)፡

1.

ሚያዝያ 17/2006 ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ ከምኖርበት አምቦ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ከደህንነቶች ጋር በቤት አውቶሞቢል እየተጓዝኩ ነው፡፡ አንድ ልጅ እግር ደህንነት ጠየቀኝ

‹‹ዘላለም የህግ መምሕር ነህ አይደል..››

እኔ

ማለትህ እጅግ ያሳዝናል፡፡ ለማንኛውም እንኳን ተማሪዎቹን ሳታበላሻቸው በጊዜ በቁጥጥር ስር ዋልክ፡፡ ኧረ ለመሆኑ ከውጭ ስንት ሽህ ደላዮችን አግኝተሻል? Any way በልማታችን ቀልድ የለም” አለኝ፡፡ (እኔም ባስተማርኩባቸው 4 አመታት ስንት ተማሪዎችን ‹እንዳበላሸሁ › እያሰብኩና ልማታችን በወለደው የአስፋልት መንገድ ፏ ብዬ ከምሽቱ 3፡50 ላይ ማዕከላዊ ከቸች፡፡

2.

እመቤቴ – መንግስት ሕዝባዊ አመፅ ለመቀስቀስ አሲራችኋል፤ ለዚህም በቂ ማስረጃ አለኝ በማለት ያሰረን ቢሆንም መንግስት ሀሳቡ እውነት ይሆንለት ዘንድ የእኛን ‹አዎ አሲረናል› የሚል መልስ በማባበልና በሀይል ለማግኘት ከመሞከር ውጭ ሌላ ያቀረበው አንዳችም ማስረጃም ሆነ መረጃ(በጠ/ሚንስትሮች ቋንቋ) አልነበረም/የለምም፡፡ ለዚህም ይመስላል በማእከላዊ የቆየሁባቸው ቀናት ምርመራው በሙሉ ‹አላማችሁ ምንድን ነው በሚል ሕይወት አልባና አሰልቺ ጥያቄ የተሞላው፡፡ እኔም የዚህ ጥያቄ ሰለባ ሁኜ ከረምኩልሽ፡፡ እንዲህ ላጫውትሽ፣

መርማሪ ፖሊስ (በተደጋጋሚ) – እንደ ዞን 9 አላማችሁ ምንድን ነው?

እኔ

መርማሪ ፖሊስ፡ እሱ ሽፋን ነው፤ እውነተኛ ዓላማችሁን ተናገር?

እኔ

መርማሪ ፖሊሱ እንድንመልስለት የሚፈልገው ‹ከበላይ አካል› ይዞ እንዲመጣ የታዘዘውን መልስ፤ “አላማችን እንደ ጭቃ ተረግጦ፤ እንደ ገል ተቀጥቅጦ የሚገኘውን ጭቁን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከተጫነበት ቀንበር ነፃ ማውጣት ነው፡፡ ለዚህም መሳካት ሕዝባዊ አመፅ ማደራጀትን እንደ ዋነኛ ዓላማ አድርገን ነው የተቋቋምነው፡፡”

ሲሆን ይህ ደግሞ ከአላማችን ጋር የማይገናኝ መንግስታዊ ፍላጎት በመሆኑ እንዲህ አይነት መልስ ከእኔ ማግኘት እንደማይችል የተረዳው መርማሪ በተደጋጋሚ አስብበት በማለት ይሰናበተኝ ነበር፡

3.

የእኔ ፅጌሬዳ አላማችን እንደ ቡድን ባይጠይቁኝ ኑሮና የግል ዓላማዬን ቢጠይቁኝ አላማዬ ‹አንቺ› እንደሆንሽ ከመናገር ወደኋላ እንደማልል ታውቂያለሽ አይደል? የሆንሽ ‹አሸባሪ› ነገር፡፡ Any way ምርመራዬ ቀጥሎልኛል፡፡ ሁለት መርማሪዎች እየተፈራረቁ ገራሚ ገራሚ ጥያቄዎችን እየጠየቁኝ ነው፡፡ እነሆ ፡

መርማሪ ፖሊስ፡ ከአለም መሪዎች ማን ማንን አግኝተህ ታውቃለህ?

እኔ

መርማሪ ፖሊስ፡ እኛ እኮ ያለመረጃ አይደለም እየጠየቅን ያለነው፡፡ ጉድ ሳይመጣብህ ብትናገር ይሻላል፡፡

እኔ፡ እስኪ አስታውሱኝና ምን እንደተነጋገርን ልናገር፡፡ በርግጥ ባለፈው የኔልሰን ማንዴላ ማስታወሻ ፕሮግራም በ አፍሪካ ህብረት በተከበረበት ወቅት ጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ አግኝቻቸዋለሁ፡፡ ሌላ የማስታውሰው የለም፡፡

መርማሪ ፖሊስ፡ ህም! እሺ ዘንድሮ ኦባማ ፊት ንግግር ለማድረግ ከተመረጡ 3 ኢትዮጵያውያን አንዱ አንተ አይደለህም?

እኔ፡ ‹‹እንዴ ኦባማ ፊት ንግግር ነው ያልከኝ? ድንገት ከታሰርኩ በኋላ ተመርጬ (በማሾፍ ድምፀት) ከሆነ አላውቅም፡፡ወይ በስም መመሳሰል ሊሆን ይችላል፡፡ አሜሪካ በአፍሪካ ጉዳይ ምን አግብቷት ነው? ላልከኝ ግን ወጣቶችን Empower ማድረግ ችግር ያለው አይመስለኝም ፤ ደግሞ በረሀቡም በድርቁም ጊዜ ርዳታ የምታደርገው እኮ አሜሪካ ነች፡፡ ምን አግብቷት ነው የምትረዳው አይባልም መቼም?!››

መርማሪ ፖሊስ፡ አሁን ዘመኑ የልማት ነው፤የምን ረሀብ ነው የምታወራው? በል ተወው፡፡

(‹ፈሪ ውሃ ውስጥ ያልበዋል› ሰምተሻል ውቤ? መንግስቴ ብቻውን እየሮጠም ፍርሃቱና ስጋቱ ብዛቱ፡፡ የሚቆጨኝ ነገር ከዓለም መሪዎች ማን ማንን አግኝተሃል? ‹ስባል› ከሲሪላንካ ፕሬዜዳንት ጋር ተገናኝቼ ወደ ደቡብ አሜሪካ ፔሩ በመጓዝ ማቹፒቹን ጎብኝቻለሁ ብዬ ብናገር ኑሮ፤ ክሳችን ላይ ‹ከሲሪላንካ መንግስት ባገኘው የገንዘብና የመሳሪያ ድጋፍ ወደ ፔሩ በመጓዝ ሕገ-መንግስት እንዴት እንደሚናድ በማቹፒቹ ኮረብታ ስልጠና ወስዶ ተመልሷል፡፡ ለዚህ እንደ ማስረጃ ይሆን ዘንድ ላፕቶፔ ውስጥ የተገኙት ከ300 በላይ የቼጉቬራ ምስሎችና Machu Pichu: The Mecca of Hippies” የሚል ባለ 22 ገጽ ‹ሰነድ› አብሮ ይያዝልኝ ነበር፡፡ ሲያበሳጭ

4.

ፍቅር አደከምኩሽ አይደል?! ልጨርስ ስለሆነ ትንሽ ታገሺኝ፡ በዛውም ‹ፍቅር ታጋሽ ነው› የሚለውን Paulian ወንዴነት፤ ‹ፍቅር ታጋሽ ናት› በሚል ማስተካከያ እንድናርመው፡፡ የዚህ የምርመራ ነገር እኮ አላልቅልኝ አለ፡፡ በእስሬ ወቅት ሌላው በተደጋጋሚ እንዳስረዳ ስጨቀጨቅበት የነበረው ጉዳይ ‹ኒዮ-ሊብራልነቴና ልማትና ዲሞክራሲ ጎን ለጎን አብረው ይሄዳሉ ማለቴ ነበር፡፡

መርማሪ ፖሊሶቹ እየተቀያየሩ ስለኢህአዴግ የፖሊሲ ትክክለኛነት ‹ያስረዱኝ› ነበር፡፡ “አንተ ምን ጎደለብኝ ብለህ ነው ነጭ አምላኪ የሆንከው ? ትንሽ የተስፋ ጭላንጭል ስናይ አንተና ጓደኞችህ አይናችሁ ለምን እንደሚቀላ እስኪ ንገረን ? ይህች አባቶቻችን ‹በደምና በጾም› ያቆዩልንን አገር አንተና ያንተ ትውልድ ግን ውበቷ እና ድንቅነቷ ላስጎመጃቸው ነጮች ለመሸጥ መደራደር ጀመራችሁ….” እያሉ ‹በባንዳነት› ሲከሱኝ ከረሙ፡፡ የሀገሪቱ ውበትና የነጮች በውበቷ መጎምጀት ነገር ሲነሳ ጊዜ ‹አንቺ› ትስቂ ዘንድ የሚከተለውን አንቀፅ አሻግሬ ታደሰ የተባሉ ፀሐፊ ከ 50 ዓመት በፊት ‹እኔና አንተ› ካሉት ጽሁፋቸው ላይ እጠቅስልሻለሁ

“ኢትዮጵያ እጅግ ያማረች፤ የተዋበች ፤የተደነቀች፤ላያት ሁሉ የምታማልል፤የምታዘናጋ…….ናት፡፡ ዓይኗ የብር አሎሎ መለሎ ከአጥቢያ ኮከብ የተፎካከረ….. ነው፤ አገራችን ኢትዮጵያ ፅጌረዳ መስላ የሰኔን ቡቃያ ትመስላለች፡፡ የመስከረም አበባ ሆና በሩቅ ትስባለች፤የመስህቧ ኃይል ማግኔት ምስጋን ይንሳው፡፡ አገራችን ኢትዮጵያ ጥርሷ እንደ በረዶ ሆና ለፈገግታ ያህል ትንሽ ከንፈሯን ስትገልፀው እንኳንስ ለሰው ግብዙ መልዓክ ያብዳል፡፡ ኢትዮጵያ ፀጉሯ የሀር ነዶ ነው፤ኢትዮጵያ አጠረች ፤ረዘመች፤ወፈረች፤ብሎ ስለአካሏ መናገር አይቻልም፡፡ እንዲያው ዝም ይሻላል፡፡ በጠቅላላው ኢትዮጵያ ውበቷ ሰነፉን ይገድላል፡፡ ብርቱውን አነሁልሎ ያሳብዳል፡፡ እግዚአብሔር፤ኢትዮጵያን ሲፈጥር በብዙ ተራቋል፤ተጠቧል፤ ውበቷ በሩቅ ይስባል፤ አጥንትም ይሰብራል፤አዕምሮን ይሰውራል፡፡ ይገርማል!” ይላሉ፡፡

ምንም እንኳን ውበት እንደተመልካቹ ነው ቢባልም፤ መርማሪዎቹ በዚህ ዓይነት Vulgar Natioanlism ሰክረው እኔና የእኔ ትውልድ ሀገሪቱን ‹በውበቷ ለሰከሩ› ነጮች ልንሸጣት እንደተዋዋልን እየነገሩኝ ነው፡፡ ይገርማል! ዲሞክራሲን ከልማት እኩል ማስኬድ ነውር የለበትም፤ ተገቢም ነው ማለት እንደ አገር ሽያጭ ውል የሚቆጠርበት ብሎም ‹ሩቅ አስባ ሩቅ ለማደር እየተጋች ያለችን አገር› መንገድ ላይ በጠረባ ለመጣል የተደረገ ሙከራ ተደርጎ የሚወለድባትና ‹አሸባሪ› የምንሰኝባት፣ ‹ለፈገግታ ያህል ትንሽ ከንፈሯን ስትገልጠው እንኳን ሰውን ግብዙን መልዓክ የምታሳብደው ኢትዮጵያ!

ሊቁ ገብረሕይወት ባይከዳኝ ‹ልማትን ሲተች› “እውቀት በሌለው ሕዝብ አገር መንገድና የምድር ባቡር ቢሰራ ሕዝቡ እንዲደኸይ ያፋጥናል እንጂ አይጠቅመውም፡፡ ጥቅሙ ከርሱ ጋር የሚገበያዩ አዋቂ ሕዝቦች ነው” በማለት ‹ልማት ብቻውን ዋጋ የለውም› ሲል ይበይናል፡፡ ገብረሕይወት የእኛው ትውልድ አባል ቢሆን ኖሮ “የኢኮኖሚ እድገቱን በመካድ፤ ሕዝቡ በአዕምሮ መናወጥ ምክንያት የዘረጋነውን የባቡር ሀዲድ ፈነቃቅሎ እንዲጥልና ሌሎች የሽብር ተግባራትን እንዲፈፀም በማነሳሳት ‹ወንጀል›” መመርመሩና መከሰሱ አይቀሬ ነበር፡፡

ውዴ! ያን ‹አሸባሪ› ሳቅሽን ሳስብ በፀረ-ሽብር ሕጉ መሠረት ጉዳይሽ ሊታይ ይችላል የሚል ስጋቴ የበዛ ነው፡

5.

እንዲያው ለዚህ 84 ቀናት ውስጥ የሆንኩትን ሁሉ እንዳልፅፍልሽ እንዳትሰለችብኝ ፈራሁ፡፡ እያንዳንዱን ሁነት በ Diary መልክ ከትቤ እንዳልክልሽ በነዛ ቀናት ውስጥ ብዕርም ሆነ ነጭ ወረቀት ይዞ መገኘት ‹ከፍ ብሎ አንገትን፣ ዝቅ ብሎ ባትን› ባያስቆርጥም ዛቻና ዱላን ማስከተሉ አይቀርም ነበርና ልከትብ አልቻልኩም፡፡ እንዲሁ በደፈናው ግን አንዳንድ ጉዳዮችን ብዘረዝርልሽ፡

በነዛ ክፉ ቀናት ከምሽቱ 12 ሰዓት እንቅልፍ መተኛትን ለመድኩ፡፡ ይሔም ነገር መልካም እንደሆነ አየሁ፡፡ ምክንያቱም ሌሊት ከእንቅልፍ ተቀስቅሰው ራቁታቸውን ሲደበደቡ አድረው ከ 3 እና 4 ሰዓታት ቆይታ በኋላ በነፍስ ወደ መኝታ ክፍላችን የሚመጡ የእስር ጓደኞቼን (Cellmates) ስቃይና ሰቆቃ ላለመስማት፡፡በ2004 ዓ.ም የፌዴራል ፖሊስ ‘Cyber crime Laboratory’ ተቋቁሟል መባሉን ሰምቼ ‹እንግዲህ cyber criminal ሁሉ የት ትገቢ? አለቀልሽ!› ብዬ ነበር፡፡ በጊዜ ቀጠሮ ጊዜ እንደተረዳሁት ደግሞ ‹ያለችን አንዲት ኮምፒውተር ናት የእነዚህ ልጆች ዳታ በአንድ ኮምፒውተር መርምረን መጨረስ ስላልቻልን የጊዜ ቀጠሮ ይሰጠን› ሲባል ነው፡፡ አረ እንዲያውም ‹እስኪ Anti-virus ካለህ ኮምፒውተሬ ላይ ጫንልኝ› ተብዩ ሁሉ ነበር፡፡ ‹ለሽብር ተግባራት› መመርመሪያ ያልሆነ ‘Cyber crime laboratory’ ለመች ሊሆን ነው?

– ‹አንተ ከየት ነው የመጣኸው?› (አንድ ተማሪ ወዳጄን)

– ‹ከሀሮማያ ዩኒቨርስቲ›

– ‹አሀ እናንተ ናችኋ…..›

****

– ‹አንተኛውስ ከየት ነው የመጣኸው?!›

– ‹ከወለጋ ዩኒቨርስቲ›

– ‹አሁን ኦሮሚያ ብትለማ ምን የሚያስከፋ ነገር አለው?!….›

*****

– ‹አንተስ ከየት ነው የመጣኸው› (እኔን ነው)

– ‹ከአምቦ ዩኒቨርስቲ›

– ‹ሕዝቡን እርስ በርስ አጋጭታችሁ ከተማዋን በደም ያጠባችኋት እናንተ….›

– ‹አረ እኔ ከግጭቱ በፊት ነው የታሰርኩት›

– ‹በእውነት ነው የምልክ እድለኛ ነህ፡፡ የኦሮሚያን ልማት ተቃወመ ተብለህ በታሪክ አለመስፈርህ በጣም እድለኛ አድርጎሀል፡፡›

(ለመሳቅ ሁላችንም የጎልማሳውን ከክፍል መውጣት እየተጠባበቅን እኮ ነው ውዴ) – ሁሉ ቧልት የሆነበት ሀገር!

በነዚህ ሁሉ የጉድ ቀናት ለምን እንደታሰርኩ ትክክለኛውን ምክንያት የሚነግረኝ አካል ፍለጋ ሁሌም አስብ ነበር፡፡ መታሰሬ ግን አያስገርመኝም፤ አያስከፋኝም! ደስታን በሔድኩበት ሁሉ እፈልጋለሁ፤ የእድል ነገር ሆኖ ደስታም ከእኔ አይርቅም፡፡ ፍቅሬ ለረጅም ዘመናት ‹የሰው የመኖር አላማ ማወቅ ነው› የሚለውን Aristotlian (አሪስቶትሊያን) አስተምህሮ በልቤ ይዤ እኖር ነበር፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ‹የመኖር ዓላማ መደሰት ነው› የሚለው አስተምህሮ በአርስቶትሉ ‹የማወቅ ዓላማ› ደባልቄ ይሔው እየተደሰትኩልሽና እያወቅሁልሽ እገኛለሁ፡፡ ‹አንች› የደስታዬ ምንጭ፡

‘‘Thanks to you….For you exist’

Clézio

ስለክሴና ስለተስፋዬ ሌላ ደብዳቤ እፅፍልሻለሁ፡፡

P.S አሳሪዬ ሆይ ልብ ይስጥህ!

ያንችው ዘላለም

ከብዙ ፍቅር ጋር!

እኛ ኢትዮጵያውያን የዚያ ብሔር ወይም የዚያ ጎሣ አባል ሆነን የተፈጠርነው የሆነ ቅጽ ሞልተን ወይም ዕጣ ተጣጥለን አይደለም፡፡ ተፈጥሮ ነው፡፡ በባለጠበንጆቹ ወያኔዎች የተነጠቅነውን መብትና ግዴታን በማስከበር፣ ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን መገንባት የምንችለው ግን እንደ ብሔር ወይም ብሔረሰብ አባል ብቻ ታስረንና ጠበን ሳይሆን፣ እንደ አንድ አገርና ሕዝብ በጋራ ስንቆምና እጅ ለእጅ ስንያያዝ ነው፡፡

ኢትዮጵያዊነት እንዳያብብ የሃገር መልካም ታሪክ እንዳይወራ ጠንክረው የሚሰሩት ወያኔዎችን የማሳፈር እቅዳቸውን የማደባየት ግዴታው የኛ የኢትዮጵያውያን ነው:: የዓለም፣ የአኅጉራዊና የአገራዊ ፈተናው እየከበደ በሄደ ቁጥር የኢትዮጵያዊነት መለኪያና የጥንካሬው ማረጋገጫ እየጨመረና እየከበደም መጥቷል፡፡ እስካሁን ድረስ ያለው ኢትዮጵያዊነታችን ጠንካራ አይደለም ወይ? የሚል ጥያቄ ሊነሳና አነጋጋሪ ሊሆን ይችላል፡፡ በግልጽ እንነጋገር ከተባለ ግን ኢትዮጵያዊነታችን ደካማ ነው አንልም እንጂ፣ ካለው የኢትዮጵያዊነት ስሜት በላይ እጥፍ ድርብ ጠንካራ የሆነ ኢትዮጵያዊነት ያስፈልገናል ብለን ግን በድፍረትና በእምነት እንናገራለን፡፡

አንድነት እና ጥንካሬ በዜጎች መሃል እንዳይሰርጽ በወያኔ የሚሰራውን ደባ የማክሸፍ ሃገራዊ ግዴታ አለብን:: ኢትዮጵያዊ ሚናችንን በአግባቡ ለመወጣት እንኳ ጠንካራ አንድነትና ኢትዮጵያዊነት ያስፈልገናል፡፡ ይህ ጠንካራ ኢትየጵያዊነት ነው ሚና እንድንጫወት ዋስትና የሚሆነው፡፡

ልድገመው !!!
እኛ ኢትዮጵያውያን የዚያ ብሔር ወይም የዚያ ጎሣ አባል ሆነን የተፈጠርነው የሆነ ቅጽ ሞልተን ወይም ዕጣ ተጣጥለን አይደለም፡፡ ተፈጥሮ ነው፡፡ ይህ እንዳለ ተቀብለን የብሔራችንን ባህልና ቋንቋ እናከብራለን፤ እናሳድጋለን፤ ይህንን ማድረግ ማንንም አይጐዳም፡፡ ሁላችንን ግን ይጠቅማል፡፡ ይህን እያከናወንን ግን ከድህነት በመላቀቅ፣ በመበልፀግ፣ ሰላምና መረጋጋትን እውን በማድረግ፣ መብትና ግዴታን በማስከበር፣ ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን መገንባት የምንችለው ግን እንደ ብሔር ወይም ብሔረሰብ አባል ብቻ ታስረንና ጠበን ሳይሆን፣ እንደ አንድ አገርና ሕዝብ በጋራ ስንቆምና እጅ ለእጅ ስንያያዝ ነው፡፡

ከዚህ ውጪ ሌላ መንገድ ወይም አማራጭ የለም፡፡
https://www.facebook.com/minilik.salsawi

በአለባበስ እና በአመጋገብ በክርስቲያንና በሙስሊም ተማሪዎች መካከል አድልዎ ይፈጸማል በተማሪዎች ዲኑ ማንአለብኝነት ተማሪዎች የፍልሰታ ለማርያምን ጾም ለመጾም ተቸግረዋል የጅማ የማኅበረ ቅዱሳን ማዕከል ምእመኑን በማስተባበር ለተማሪዎቹ ድጋፍ እያደረገ ነው ቅ/ሲኖዶስ ሃይማኖታዊ መብታቸውን የሚያስከብር አቋም እንዲወስድ ተማሪዎቹ ጠይቀዋል ‹‹ኦርቶዶክሳዊ ሥርዐተ እምነትን በማንአለብኝነት ለይቶ የመጋፋት አካሔዱ፣ አኹን በደረሰበት ደረጃ አሳሳቢ የሃይማኖታዊል ነፃነት መረገጥ እንጂ የመብል ጉዳይና የአንድ ዩኒቨርስቲ …

(አለቃ አያሌው ታምሩ) በኢትዮጵያ እመቤታችንን መውደድ በልማድ እንደ ተረት በማይታይ ዓይነት ኹኔታ ተስፋፍቶ የኖረ አይደለም፡፡ ወንድም ሴትም ቢኾኑ እንዳላቸው የእምነት መጠን በእመቤታችን ስም ጸሎት ጸልየው፣ ስእለት ተስለው፣ ምጽዋት አድርገው፣ ዝክርዋን ዘክረው፣ ስምዋን ጠርተው፣ በአማላጅነትዋ ተማፅነው ዐሳባቸው እየተፈጸመላቸው፣ የጎደለው እየሞላላቸው፣ የጠመመው እየተቃናላቸው፣ ድውያን ፈውስ በማግኘት፣ ሠራተኞች ለሥራቸው የተቃና መንገድ በማግኘት፣ መምህራን በሚያስተምሩበት፣ ቅዱሳን ገድላቸውን በሚፈጽሙበት ጊዜና …

በመንግስት ተቋማት ውስጥ ተቀጥሮ መስራት በፈቃደኝነት ድህነትን ለመውረስ ዝግጁ መሆን ማለት ነው፡፡ የመንግስት ተቋማቶች ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች ድርቅ ተመትተዋል፡፡ ተስፋ የቆረጡ፤በሙያቸው የማይተማመኑ ወይም ሙያ አልቦዎች፣ በሠራተኛው ገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ ያልሆኑ የእውቀት የክህሎት፣ የዝግጅት እና የተነሳሽት ድኩማኖች መናኸሪያ እየሆኑ መጥተዋል፡፡ አማራጭ አጥቶ የመንግስትን ቤት ሙጥኝ ያለ ፈጻሚ እንኳንስ አገር ሊገነባና የአፍራሽነት ሚና ነው የሚጫወተው፡፡ መንግስት በክህሎት አልቦ እና በሙያ ለምኔ ፈጻሚዎች ተከብቦ እንዴትስ ህዝብን ማገልገል ይችላል? የግሉ ዘርፍ በሰው ኃይል አደረጃጀቱ በልጦት ከተገኘ መንግስት የግሉን ዘርፍ መምራት ቀርቆ መንግስት በግሉ ዘርፍ ይመራል፡፡

http://minilik-salsawi.blogspot.com/201 … ost_3.html

Image

በሐሰት መንግስታዊ ማጭበርበሮች ሳንታለል በጋራ በመታገል ቀጣይ ድሎችን እናረጋግጥ !!!
#Ethiopia #EPRDF #UDJ #Blueparty #Ginbot7 #Medrek #MinilikSalsawi

ህዝብ መንቃቱን መረዳት እስኪያቅተው ድረስ ወያኔ ማላዘኑን ተያይዞታል።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

በሃገሪቱ ያለውን ሁኔታ በትክክለኛው መንገድ የማያስቀምጡ የወያኔ ፕሮፓጋንዲስቶች እርስ በእርሳቸው የሚጋጩ ዘገባዎችን በመስራት እና እውነትን ለመሸፋፈን በመትጋት የሕዝቦችን የማወቅ መብት ያለርሕራሄ እየተጋፉ ይገኛል። ይህ በወያኔ የፕሮፓጋንዳ አካላት የሚፈጸም ማጭበርበር እና ማደናገር የገዢውን ፓርቲ ውስጣዊ ዝርክርክነት በይፋ ያሳብቃል።ያለለውን እንዳለ ድሮ ተግንብቶ የታደሰውን እንደ አዲስ እንደተገነባ ፤ ያልተሰራውን እንደተሰራ ሕዝቡ የማያገኘውን አገልግሎት እንደሚያገኝ ወዘተ በማድረግ በሁለት እና ሶስት እጥፍ በማባዛት በመቶኛ በማስላት በመደመር በማባዛት ያሌለውን ምስል በመፍጠር ሕዝቡን እያደናበሩ ይገኛሉ።

በአለም ላይ ካሉ መንግስታት በተለየ ሁኔታ ዜጎቹን እያጭበረበረ ወደ ድህነት አዘቅት እየከተተ ያለ መንግስታዊ አስተዳደር ነኝ የሚል ቢኖር ወያኔ እና ወያኔ ብቻ ነው። የወያኔ የማይሳኩ እና የሚያደሐዩ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ፖሊሲዎች መነሻቸው የተሳሳቱ ፕሮፓጋንዳዎች ናቸው። ማንኛውንም ፖሊሲ ይሁን አዋጅ መመሪያ ይሁን ደንብ ወያኔ ሲያወጣ በተቆጣጠራቸው ሚዲያዎቹ እያጋነነ የሕዝብን ልብ ለመስቀል በመሞከር እደርስበታለው ያለው ግብ ምንግዜም እየተኮላሸ ተጨባጩን ሁኔታ ባለማገናዘብ እየካደ ስለሚጓዝ የሃገር ኢኮኖሚ የጨው ክምር በመሆኑ እየተናደበት ይገኛል።

ሕዝቡ ትክክለኛ አስተዳዳሪ ባለማግኘቱ ምክንያት እየተንገላታ በየቦታው ምሬት በበዛበት በአሁኑ ሰአት ተገቢውን አገልግሎት እንዳገኘ በማድረግ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ በመርጨት ለማሳሳት እየተሞከር ሲኦን በቀረቡ መዝገቦች ላይ ውሳኔ መስጠት አቅቶት ወይም በቸልተኝነት አልወስንም ብሎ የሚኮፈስ ቢሮክራሲ ዜጎችን ሲያስለቅስ በአደባባይ እየታየ መፍትሔ እየተገኘ ነው የሚል ማደናገሪያ ሲቀርብ ያሳዝናል፡፡ ያሳፍራል፡፡በፍትሕ ሥርዓቱ አካባቢም ሲታይ እየወጡ ያሉ መግለጫዎችና ሪፖርቶች የሚያስገርሙ ናቸው፡፡ ፍትሕ ዘገየብን፣ ፍትሕ ተነፈግን የሚሉ በርካታ ዜጎች ባሉበት አገር ውስጥ የፍትሕ ሥርዓቱ ተደራሽነት ወደር የለውም ዓይነት ሪፖርቶች ይቀርባሉ፡፡ ሕዝቡ በየፍርድ ቤቱ በተጓደለ ወይም በተነፈገ ፍትሕ ምክንያት ከላይ ታች ሲቅበዘበዝ እየታየ የማይመስል ነገር ይነገራል፡፡ በዚህ መስክ ያለው ማደናገር ራስ ያሳምማል፡፡

በኑሮ ውድነት በትራንስፖርት በውኃ በኤሌክትሪክና በስልክ አገልግሎቶች አለመሟላት እና መቆራረጥ ምክንያት ሥራውና ኑሮው አሳር እያየበት ያለው ሕዝብ የአገልግሎቱ ተደራሽነት በዚህን ያህል በመቶ አደገ ወይም ደረሰ ሲባል ቀልድ የተያዘ ይመስለዋል፡፡ ለሳምንታት ውኃ አጥቶ የሚንከራተት ሕዝብ የውኃ ተደራሽነት ከዘጠና በመቶ በላይ ሆኗል ተብሎ ሲለፈፍበት እንዴት ይቀበላል? በኤሌክትሪክ ኃይል እጦት ምክንያት ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው ማምረት እያቃተውና ሕዝቡ በጨለማ ሲሰቃይ ተደራሽነቱ ይህን ያህል ደርሷል ሲባል ማን ያምናል? በሌሎች ዘርፎችም ተመሳሳይ ማደናገሪያዎች ሞልተዋል፡፡ከመሃል አገር እና ከተለያዩ ክፍለሃገሮች ገበያዎች የተገኙ ተብለው የሚቀርቡ የእህል ዋጋዎች መጋጨት የሚያስገርሙ ናቸው፡፡ ጤፍ፣ በርበሬ፣ ጥራጥሬና የተለያዩ የግብርና ምርቶች ዋጋ በወያኔ መገናኛ ብዙኃኑ ሲተነተን፣ በፍፁም ገበያ ውስጥ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ አያሳይም፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ማደናገሪያ ማንን እንደሚጠቅም አይገባንም፡፡ ህዝብ መንቃቱን መረዳት እስኪያቅተው ድረስ ወያኔ ማላዘኑን ተያይዞታል።

ስለዚህ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አንዱ ለሌላው መረጃዎችን በማስተላለፍ ወያኔ እና ሚዲያዎቹ የሚጠቀሙበትን የማደናበሪያ ስልት በማጋለጥ እና ሊደናበር የሚችለውን የዋሁን ኢትዮጵያዊ በማስረዳት የዜግነት ግዲታችንን እየተወጣን በጋራ በመታገል ይህንን ውሸታም እና አጭበርባሪ አደናባሪ ስርአት ልናስወግደው እና ለመጪው ትውልድ እውነትን የተሞላች አገር የማስረከብ ሃላፊነት እንዳለብን ለማሳሰብ እወዳለሁ። በጋራ በመታገል ቀጣይ ድሎቻችንን እናረጋግጣለን!!1 #ምንሊክሳልሳዊ

በጥርጣሬ/ግምት ካልሆነ በቀር አስራ አራቱ መኮንኖች የት እንደገቡ አይታወቅም።
ሁለት ከፍተና የጦር መሃንዲስች ዱካቸው ደብረዘይት ከሚገኘው እስር ቤት ተገኝቷል።
ወደ መቀሌ ከዲያስፖራው ጋር ለዘረፋ የንግድ ሽርክና ኢንቨስተሮች ለመመልመል ያመሩት ጄኔራሎች ሳይቀሩ በምን እንደመጡ በማይታወቅበት ሁኔታ አዲስ አበባ ደርሰው የመሃል አገር መኮንኖች መጥፋትን ተከትሎ ያመጣውን ውጥረት በስብሰባ ሲያሹት እና ከተለያዩ ወታደራዊ ደህንነቶች መረጃ ሲሰበስቡ እንደዋሉ ታውቋል።

በሰራዊቱ ውስጥ አለመተማመን የተፈጠረው ከምን የመነጨ ነው የሚል ጥናት በዚህ ሳምንት በተካሄደበት የመሃል አገር መከላከያ መምሪያዎች ውስጥ አጋጣሚ በተገኘ መረጃ 16 ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የት እንደገቡ አይታወቅም ሲል ሪፖርት ያቀረበው የወታደራዊ ደህንነት ቡድን የቀረበለትን ጥቆማ ለበላይ አካላት ሪፖርት ሳያድርግ ፍተሻውን አጧጡፎት የነበረ ቢሆንም ምንም አይነት ፍንጭ ባለማግኘቱ ትላንትና የተነገረው የበላይ አካል በከፍተኛ ድንጋጤ ተውጦ የዋለ መሆኑን ለጦር ክፍሎቹ ቅርብ የሆኑ ምንጮቻችን ከመከላከያ ያደረሱን መረጃ ጠቁሟል።

ከመሃል አገር በተለያየ የጦር መምሪያ ውስጥ ተመድበው ይሰሩ የነበሩት እና የአንድ ኮርስ ምሩቅ ናቸው የተባሉት ወታደራዊ መኮንኖች ውስጥ የሕወሓት ጄኔራሎች ላይ ጥርሱን እንደነከሰ የሚነገርለት ኮሎኔል አለም የሚባለውን የተንቤን ተውላጅ ጨምሮ አስረ አንዱ ወደ ደቡብ ሱዳን ዘልቀው ገብተዋል የሚል መረጃዎች ቢኖሩም እስካሁን ማረጋገጥ እንዳልቻለ ለመከላከያ ደህንነት ቢሮ ምንጮቻችን የገለጹ ሲሆን የሶስቱ ዱካ አለመገኘቱን እና ሁለት ከፍተኛ የጦር መሃንዲሶች ከየት ታፍነው በማን ታፍነው እንደተወሰዱ ሳይታወቅ በደብረዘይት የምድር ውስጥ እስር ቤት እንደሚገኙ ተረጋግጧል።

የሕወሓት ጄኔራሎችን ያመሳቸው ጉዳይ የተንቤን ተወላጆች ሌሎች የደቡብ እና የአማራ ተወላጆች ተያይዞ መጥፋት ሲሆን እንዲሁም በጦር ሰራዊቱ ውስጥ እየላላ መጥቷል ሲሉ የደነፉበት የወታደራዊ ደህንነት ቁጥጥር መላላት ለነገው የስልጣን እድሜያቸው ከፍተኛ ስጋት እንዳጠላበታ ያሳያል ሲሉ መረጃውን የላኩልን የመከላከያ ምንጮቻችን ተናግረዋል። በሙሉ የሃገሪት እዞች ከፍተኛ ቁጥጥር እና ፍተሻ እንዲካሄድ በዛሬው ስብሰባ ጥብቅ ትእዛዝ ያስተላለፉት የሕወሓት ጄኔራሎች በደቡብ እና በምእራብ ድንበሮች አከባቢ ያሉ እንቅስቃሴዎች እንዲፈተሹ በወጪ ገቢው ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እንዲደረግ እና የየቀኑ ሪፖርት እንዲላክ እንዲሁም በመሃል አገር ያሉ የቶር መኮንኖች በየቀኑ ለቅርብ አለቃቸው ዝርዝር የአባላት እንቅስቃሴ ሪፖርት እንዲያቀርቡ ጥብቅ ትእዛዝ አውርደዋል።እንዲሁም ተጨማሪ ወታደራዊ ደህንነቶች በየእዙ እንዲመደቡ አዘዋል።

በዚህ ዙሪያ ያለውን ጉዳይ በተመለከተ የወታደራዊ ደህንነት ሪፖርቶቹን እየተከታተልን የምናቀርብ መሆኑን ቃል እንገባለን።
#ምንሊክሳልሳዊ

ዛሬ በኢትዮጵያ መሬት ላይ ያለ አሸባሪ ወያኔና ወያኔ ብቻ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎችን በፖለቲካ አመለካከታቸው፣ መንግስት በመተቸታቸው በግልጽ በመጻፋቸውና በአደባባይ በመናገራቸው ከዚህም አልፎ በጥርጣሬ በተለይም በብሄረሰብ ማንነታቸው እያሳደደ የሚያፍን የሚያሰቃይና የሚገል የሽብር ተቋም ካለ ወያኔ ብቻ ነው። በኢትዮጵያ መሬት ላይ ሰላማዊ ዜጎችን ኢላማ ያደረገ የተቃውሞ ሃይል በተግባርም ሆነ በአስተሳሰብ ከወያኔ ውጪ አንዳች ሃይል የለም።

አፋኙ የወያኔ ስርአት በተለየም የህዝቡን ሀብትና ንብረት እየዘረፉ የሚቀማጠሉት የህወሃት መሪዎችና ሎሌዎቻቸው የተቃውሞ ድምጽ በሰሙ ቁጥር እንደሚሸበሩና እንቅልፍ አጥተው እንደሚያድሩ ይታወቃል። አፍነውና ዘርፈው ገለው የሚገዙት ህዝብ ግፍ በዛብኝ ብሎ በተናገረ ቁጥር የሚሸበሩት እነሱ ብቻ እንጂ ህዝቡ አይደለም።
በኢትዮጵያ ምድር ያለው አሸባሪ ወያኔ ብቻ መሆኑን ሺ ምሳሌዎችን ጠቅሶ ማስረዳት ይቻላል። ሶስት አመት ሙሉ የሰላም እጃቸውን እየዘረጉ ከልመና ባልተለየ ሁኔታ መብታቸውን የጠየቁና ድምጻችን ይሰማ ያሉት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ማንንም ዜጋ አላሸበሩም። የተገላቢጦሽ እነሱ አሸባሪ ተብለው የግፍ ሰቆቃ ይፈጸምባቸዋል።

ጋዜጠኞችና ጦማሪዎቹ መንግስት ያወጣውን ህግ እንዲያከብር ስለጠየቁ በአደባባይ ስለጻፉ ግፍ ይፈጸምባቸዋል። እነሱ ያሸበሩት ሀገርና ህዝብ የለም። ከመንገድ ላይ ጎትተው እንደ እባብ ቀጥቅጠውና ፈነካክተው በማግስቱ ፍርድ ቤት ያቀረቧት ወየንሸት ሞላ የተባለች ባለ ተስፋ ወጣት የወያኔ አረመኔዎች በሙስሊሙ ህዝብ ላይ የሚሰሩትን ጭፍጨፋ እግር ጥሏት ከማየትና ከመታዘብ ውጪ ያሸበረችው ሰው፣ ሀገር የለም። በየወህኒ ቤቱ እና አፈና ጣቢያው ታስረው የሚቀጠቀጡት የኦሮሞ ልጆች ለጥያቄያቸው መልስ ሲጠብቁ ከመጨፍጨፍ ያለፈ የፈጸሙት እብሪት የለም። በየክልሉ ቀና ብለህ ባለስልጣን ተናገርክ፣ ጥያቄ ጠየቅክ፣ ባለስልጣን ደፈርክ፣ ተሰብስበህ አየንህ ወዘተ እየተባለ የሚገረፈው እንደ እንስሳ እየተገደለ የሚጣለው ገበሬ የሰራው ወንጀል የለም። አሸባሪም አይደለም! በየቦታው ቦንብ እየቀበረ አፈንድቶ ንጹሃንን ገድሎ ሊያፈነዱ ሲሉ ፈንድቶባቸው ራሳቸውን ገደሉ ብሎ በአደባባይ የሚሳለቀው አሸባሪው ህወሃት እንጂ ንጹሃኑ አይደለም።

የኛ መሪ አንዳርጋቸው ከልጅነት እድሜው ጀምሮ ራሱን ለህዝብ ነጻነት የሰጠ አርበኛ እንጂ አሸባሪ አይደለም። በተመሳሳይ ውንብድና ከጎረቤት ሀገር ድረስ በአለም አቀፍ የወረበሎች ውንብድና መንገድ ወያኔ እያፈነ የገደላቸው አሮሞዎችና፣ ሱማሌዎች፣ አኙዋኮች፣ አማሮችና ሌሎችም ነጻነት ከመፈለግ ውጪ ያሸበሩት ህዝብና ሀገር የለም።
በኢትዮጵያ ምድር የነጻነት ድምጽና ኮሽታ በሰማ ቁጥር የሚሸበረው ህወሃትና በለሟሎች ብቻ ናቸው። ይህ የነጻነት ድምጽ ደግሞ እየጎላ መሄዱ የማይቀር ነውና ወያኔ ሰፈር ሽብር ይሆናል።

የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ! ወጣት፣ ሴት፣ ሽማግሌ፣ ገበሬ እና በየቦታው ያላችሁ የኢትዮጵያ ልጆች ሁሉ! አሸባሪህ ወያኔና ወያኔ ብቻ መሆኑን አውቀህ በገዛ ሀገርህ ላይ ነጻነት በተመኘህና በጠየቅህ ጊዜ ሁሉ ለሽብር ጥቃቱ ኢላማ ያደረጉህን ወያኔ ተባብረን ከላያችን ለማውረድ ተነስ! በያለህበት እምቢ በል! ለወያኔ የሚጠቅም የመሰለህን ነገር ሁሉ አታድርግ! አትተባበር! ሸቀጣቸውን አትግዛ! ወያኔዎችን ከማህበራዊ ሂወትህ አግል! የቻልክ ሁሉ ደግሞ የነጻነት አርበኞችን ዛሬ ነገ ሳትል አሁን ተቀላቀል!!! ነጻነታችን ያለው በእጃችን ላይ መሆኑን አትዘንጋ። ግንቦት 7 ሁልጊዜም ከመቼውም ጠንክሮ ከጎንህ ነው።

የወያኔን ሽብር በተባበረ ሃይል እናቁመው!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
ግንቦት7

የትግራይ ስብስቡ በጂጁ ሆቴል እቅዳቸው የህወሓትና የደህንነት ሰዎች ባሉበት ኣውጥተዋል ::
ሕወሓት በትግራይ ከዚህ ቀደም በሚደረጉ ምርጫዎች ካለምንም ተወዳዳሪ በብቸኝነት ተወዳዳሪ ሲመጣ ደሞ ስም በማጥፋት እና በጉልበት በመደቆስ በብቸኝነት ምርጫዎችን እያሸነፈ ላለፉት 23 አመታት ዘልቋል። ካለፉት 6 አመታት በኋላ አረና ትግርያ ብሎ የሚጠራ ተቀናቃኝ የፖለቲካ ፓርቲ ተመስርቶ በትግራይ ውስጥ እንቅስቃሴውን እያስፋፋ ባለበት ሰአት በመጭው ምርጫ እሸነፋለሁ ሕዝቡ በድምጹ ይጥለኛል የሚል ከባድ ስጋት ስላለበት ከአረና ፓርቲ ጋር ይመሳሰላልኛል ያለውን ተለጣፊ ፓርቲ ለመመስረን እንቅስቃሴ መጀመሩን ታውቋል።

http://minilik-salsawi.blogspot.com/201 … -post.html

ድብደባ እና ህግ አስከባሪው ፖሊስ ሚና

ድብደባ ከድሮም ባህላችን የነበረ ባል ሚስቱን መደብደብ፣ አባት ልጁን መግረፍ፣አስተማሪ ተማሪውን መጠፍጠፍ፣ለኛ ኢትዮጵያውያን የታዘዘልን ባህላዊ ህክምናዎች ኣንዱ ይማስለኛል፣ በሀሳብ እና ንግግር ችግርን ክመፍታት ይልቅ ጉልበት አለኝ የሚለው አካል በሀይል አስገድዶ የራስን ፍላጎት መጫን በመሀበረሰባችን ውስጥ ያለ እውነታ ነው። እናስ መንግስት የማህበረሰቡ ውጤት ነውና ክድሮም ጀምሮ በተለያዩ ገዢዎቻችን ስንጠፈጠፍ ኖረናል አሁንም አለም ስለ ሰብአዊ መብቶች የተሻለ ግንዛቤ አለባት በምንልበት ወቅትም እኛና ድብደባ ላንፋታ የተጋባን ይመስል የድብደባ ሌጋሲያችንን እያስቀጠልን ነው። በቅርቡም ባሎች ሚስቶቻቸውን በመደብደብ የሶስተኛ ማእረግነት አግኝተናል እንዲሁም፣ በቅርቡ በመንግስት በኩልም በሺህ የሚቆጠሩ ምእመናን እና ከጉዳዩ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ሰዎች በጅምላ በፌድራል ፖሊስ ለመደብደብ ታቅዶ ታልሞ የሰለጠኑ በሚመስል ሁኔታ ብዙ ሺህ ሰዎች ፅሎት ሊያደርጉ በሄዱበት እንዲሁም ነጋዴዎች እና ገበያተኞች እንደ አንበጣ ወረሽኝ በድንገት ተወረው ተደብድበዋል።
Image

አድማ መበተን ወይስ ድብደባ

እንደ ፈረደብን ሌላ ሀገር ምሳሌ ላርግና ህዝብ የተለያዩ ጥያቄዎች ሲኖሩት ሰልፍ መውጣት የተለመደ ነው። ነገሩ ከፍቶም ችግር ከተፈጠረ አድማ በታኝ ፖሊሶች መተው ሰልፉን መበተን እንዲሁም ከተቃውሞ አድራጊዎቹ ወገን እንደ ድንጋይ እና ሀይል መጠቀም ከተጀመረም በተለያዩ መንገዶች መበተን አዲስ አይደለም። ነገር ግን ባለፈው አርብ በአንዋር መስጊድ እና መርካቶ አካባቢ የታየው ሁኔታ ግርም የሚል ነው።

ምክንያት፡~
1 ድብደባው የተጀመረው የተቃውሞ ሰልፉ ሳይደረግ በፊት እየተሰገደ ነበር።
2 የተቃውሞ ስልፈኞቹ መሀል በገቡ ደህነነቶች እና ምልምል ካድሬዎች ሰልፉ ሰላማዊ እንዳይሆን አስቀድመው ህዝቡ መሀል ድንጋይ በመወርወር እንዲረበሽ አስደርገዋል።
3 በሌላ ሀገር እንደምናየው ህዝቡ እንኩዋን ከፖሊስ ሀይል ጋር ሊጋጭ ይቅርና አንድ ፖሊስ በያዘው ዱላ ብቻ እስክ ሀምሳ ሰዎችን የሚሆኑ እያሩዋሩዋጠ ሲዥልጥ ነበር።ህዝቡም እራሱን ለመከላከል ያደረገው በአለም የምንተወቅበትን እሩጫ ብቻ ነበር።
4 እናም የፖሊስ ተልእኮ አድማ መበተን ሳይሆን መግረፍ ይመስል ነበር።
5 መርካቶ አካባቢ ደጅ ላይ በልብስ ስፌት የሚተዳደሩ ወጣቶች ስራቸውን እየሰሩ ባሉበት ሰአት ከየት እንደመጣ እንኩዋን ያላዩት የፖሊስ መንጋ መቶ አናት አናታቸውን ሲፈልጣቸው ማሽናቸውን ጥለው እግሬ አውጪኝ ሲሉ ባለሱቆች ሱቃችሁን አልዘጋችሁም ተብለው እንግልት እና ድብደባ ተደርጎባቸዋል።

ፖሊስ መታሁ ስትል የሰማሁዋት አንዲት ልጅ ብቻ ነች ምክንያትዋን ስታስረዳም” መስጊድ ውስጥ ታግተን እንዳለ አንዱ ፖሊስ መጣና ከአጠገቤ የቆሙትን አሮጊት በያዘው ዱላ ወገባቸውን ሲላቸው አላስቻለኝም ለምን እኔን አይመታም እንዴት እኝህን ሴትዮ አልኩና ጫማዮን አውልቄ አናቱን ብየው ወደ ህዝቡ ውስጥ ስገባ ቆይ በሁዋላ ላግኝሽ እያለኝ ተሰወርኩበት። ” በተረፈ አንድ ተጎድቶ የተኛ የፖሊስ ምስል እዚሁ ፌስቡክ ላይ የተለቀቀ አይቻለሁ እሱንም በግርግሩ መሀል መኪና የገጨው መሆኑን ተረድቻለሁ።

ከአንዋሩ ድብደባ በሁዋላ መስጊድ ውስጥ የታገቱ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች እስከ ምሽቱ አራት ሰአት ድረስ ታግተው ወደ ተለያዩ ቦታዎች በትልልቅ መኪኖች እንደ ሰርዲን ታጭቀው ተወስደዋል።

በየማቆያ ጣቢያዎቹ የነበረው ሁኔታም የተለያየ ነበር በጉለሌ አካባቢ የታሰሩት ሰዎች በተለያዩ ኮማንደሮች ልማታዊ የምክር አገልግሎት ተሰጥቶዋቸው የተወሰደባቸው ሞባየሎቻቸው ተመልሶላቸው ከለሊቱ ዘጠኝ ሰአት አካባቢ ተለቀዋል።

ወደ ኮልፌ ያለው የፌድራል ፖሊስ ማሰልጠኛ የተወሰዱት ግን ያዩት አበሳ አሳዛኝና ዘግናኝም ነበር የሴቶችን መከናነቢያ ማቃጠል ለሊቱን ሙሉ የሰልጣኝ ፌድራል ፖሊሶች ድብደባ እንዲሁም ሞባየሎቻቸውን ቅሚያም ነውር አልነበረም። ሞባየል ሲነ’ጥቁ ቆምንለት ከሚሉት የህግ ማስከበር አላማ በተፃራሪ እንደቆሙ የሚያገናዝብ ህሊናም አልነበራቸውም። እንዲሁም ድብደባው ይደረግ የነበረው ቀጥታ አናት አናት ላይ ብቻ ያተኮረ መሆኑ ደግሞ ሰዎቹ ጭንቅላት እና ከበሮን መለየት ይችላሉ ወይ ያስብላል።

አንዱ ሽማግሌ ሲያጫውቱኝ እኔ ስብሰባ ይሁን ምን የማውቀው ታሪክም አልነበረም በቃ ከባንክ የሰው አርባ ሺ ብር ቼክ አውጥቼ በዛው ልሰግድ አንዋር ሄድኩ የገጠመኝ ግን ድብደባና ዝርፊያ ነበር። በግርግሩ መሀል ስሮጥ ብሩ ተበተነ ካጠገቤ የደረሱትም ፖሊሶች “የአሸባሪ ብር ፥የአሸባሪ ብር “እያሉ ብሩን ወደ ኪሳቸው መዶል ጀመሩ እኔንም አንዴ አናቴን ሲሉኝ ነብሴን ለማዳን ፈረጠጥኩ።እንዲሁም ልጆቻቸው የታሰረባቸው ቤተሰቦችን አንዳንድ ፖሊሶች ልጆቻችሁን እንድናስለቅቅላችሁ እያሉ እስከ ሁለት ሺ ብር መጠየቅም ተጀምሮ ነበር።

እናም ህግ አስከብራለሁ የሚለው ፖሊስ እና መንግስት አሸባሪ ሆነው ህዝቡ ደግሞ ሲሸበር ዋሉ ለማጠቃለያም የዛሬ አመት እንዲሁ በኢድ ሰላት ላይ ድብደባ ተደርጎ ነበር፣ እናም አንድ ገጠመኝ አጫውቼያችሁ ልሰናበት ልጁ ፖሊሶች እንደ ለመዱት አናት አናቱን በዛ ዱላቸው ሲያራውጡት የጨነቀው እርጉዝ ያገባል እንደሚባለው ሆኖበት “ወላሂ እኔ ክርስትያን ነኝ” አላቸው።

እስከ ልዩ ጽ/ቤት የተዘረጋው የአማሳኞች ሰንሰለት ለአለቃው መነሣት ተጠያቂ ኾኗል ምእመናን፣ በተነሡት አለቃ ምትክ የሚደረግ ምደባን እንደማይቀበሉ አስጠንቅቀዋል ፓትርያርኩ ለክብረ በዓል ወደ ቁሉቢ ሲያልፉ ለማነጋገር ዝግጅት እየተደረገ ነው የኦዲት ሪፖርቱ የድሬዳዋ አገልጋዮች እና ምእመናን በአንድነት እንዲሰለፉ አድርጓል ‹‹የአለቃው መነሣት ሙስናን ለሚዋጉ ሌሎች አስተዳዳሪዎች ዋስትና የሚያሳጣ ነው፡፡›› ‹‹ፓትርያርኩ በቋሚ ሲኖዶስ የተወሰነውን ስለማይቀበሉና መፍትሔ ማምጣት ስላልተቻለ ሕዝቡ …

አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብስባ ለመጥራት ታቅዶ ነበር በተሳሳተ አካሔዳቸው ከቀጠሉ ቋሚ ሲኖዶሱ አብሯቸው አይሠራም በአ/አበባ የአድባራት አለቆች ዝውውር ስሕተት መሥራታቸውን አምነዋል ‹‹የኔ ቃልና የነሱ ቃል በዓላማ አንድ ስለኾነ፣ የሚያመጡት ሐሳብ ስለሚመቸኝ ነው፡፡››          /ፓትርያርኩ በሰብሳቢነት የሚመሩትንና አብረው የሚወስኑበትን የቋሚ ሲኖዶስ መመሪያዎች ከአማሳኞች ጋራ እየመከሩ ስለሚገለብጡበት አካሔድ በቋሚ ሲኖዶስ ለተጠየቁት የመለሱት/ /ምንጭ፡- ፋክት፤ ቅጽ …

በ፲፱፻፹፯ ዓ.ም. ዳግመኛ ከተከፈተ ወዲህ የተመረቁት ደቀ መዛሙርት ብዛት 2175 ደርሷል የተቋማዊ ነፃነት ዕጦትና የበጀት እጥረት ‹‹ጥናትና ምርምር ላይ እንዳላተኩር አድርጎኛል፡፡›› መሠረቱ የወጣው ሕንፃ ሥራ እንዲቆም በጀቱም እንዲመለስ የተላለፈው ትእዛዝ አወዛግቧል ወደ ዩኒቪርስቲ ደረጃ የማሸጋገሩ ሒደት በግንባታ ላይ የሚገኘውን ሕንፃ መጠናቀቅ ይጠብቃል ‹‹ከዛሬው ደስታችኹ የሚበልጥ ደስታ ከፊታችኹ ስለተዘጋጀ ደስታችኹ ዕጥፍ ድርብ ነው፡፡›› /ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ/ …

ቋሚ ሲኖዶሱ የካህናቱንና ምእመናኑን አቤቱታ በመቀበልና የፓትርያርኩ ጥያቄ እንዲጣራ በማዘዝ፣ በሓላፊነታቸው እንዲቀጥሉ የወሰነላቸው ውጤታማው የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል አስተዳዳሪ መልአከ ብርሃናት ቀሲስ ክብሩ ገብረ ጻድቅ፣ ውሳኔውን የሚፃረር የዝውውር ደብዳቤ በአባ ማትያስ ትእዛዝ ተጽፎባቸዋል፡፡ የፓትርያርኩን አግባብነት የሌለው ትእዛዝ በመቃወም የደብሩን ሀብት ከአማሳኞች ሰንሰለታዊ ምዝበራ ለመከላከል እንዲሁም የቋሚ ሲኖዶሱ ውሳኔ በማስከበር የደብሩን ሰላም ለማስጠበቅ መንፈሳዊነት በተሞላው አኳኋን …

    ቋሚ ሲኖዶስ ዛሬ በጉዳዩ ላይ እንደሚወያይ ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ትላንት ጥዋት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ለተሰለፉ ከአንድ ሺሕ ለማያንሱ ካህናትና ምእመናን አስታውቀዋል፤ የቋሚ ሲኖዶሱ ውሳኔ የካህናቱንና ምእመናኑን ቀጣይ ርምጃ ይወስናል፡፡     ፓትርያርኩ በጥቂት አማሳኞች ምክር ላይ የተመሠረተ የሙስና ክሣቸውን በማስረጃ አስደግፈው እንዲገልጹላቸው የተማፀኗቸውን፤ ለአቤቱታ በሕዝብ ማመላሻ አውቶቡሶች፣ ታክሲዎችና የቤት …

ፓትርያርኩ እና አማሳኝ አማካሪዎቻቸው÷ ለቅዱስ ሲኖዶሱ የመልቀቂያ ጥያቄ ካቀረቡት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ጋራ የተቋማዊ ለውጥ ጥናቱን በመደገፍ በቅርበት የሠሩት ውጤታማው የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ብርሃናት ክብሩ ገብረ ጻድቅ ከሓላፊነታቸው እንዲነሡ በሀገረ ስብከቱ ሓላፊዎች ላይ ግፊት አድርገዋል – ‹‹ታዝዤ ነው፤ የፓትርያርኩ ጭቅጭቅ አላስቀምጥ አለኝ፡፡›› (ዋ/ሥ/አስኪያጁ ሊቀ አእላፍ በላይ መኰንን)   የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ …

ከምኒልክ ሳልሳዊ
በወያኔ መኮንኖች እና በኢትዮጵያ የመከላከያ ስራዊት መኮንኖች መካከል በፖለቲካ እና በጥቅማ ጥቅም ጉዳዮች ዙሪያ ውስጥ ውስጡን እየተካረረ የመጣው አተካራ ከባድ ውጥረት መፍጠሩን በእዙ የሚገኙ መኮንኖች የተገኘው መረጃ ጠቁሟል። ሕገመንግስታዊ ጥያቀዎችንእና ወታደራዊ ጥቅማ ጥቅሞችን የሚተይቁ መክንኖች ከየክምፑ ተለቅመው ወደ ሰሜን እዝ እና ወደ ሶማሊያ ከሄደው ጦር ጋር እንዲቀላቀሉ ከተደረገ በኋላ ውጥረቱ እየሰፋ መምጣቱ ታውቋል።

ከዚህ ቀደም የተነሱ ሕገመንግስታዊ ጥያቄዎችን የሕወሓት ከፍተኛ መኮንኖች የጥያቄው ባለመብቶችን ወደ ሌላ አከባቢ በመቀየር የቀሩትንም በጥቅም ለመያዝ ቢሞክሩም ያላዋጣቸው ሲሆን ክመሃል ሃገር ሰልጥነው የተመደቡትም ወታደራዊ ደህንነቶች የአንድ ብሄር አባላት ስለሆኑ የመከላከያ ሰራዊቱ የበታች መኮንኖች በጥርጣሬ ስለሚመለከቷቸው የተላኩበትን ግዳጅ በብቃት መፈጸም ባለመቻላቸው ምንም አይነት ውጤት አለማምታታቸው ችግሩ ዳግም እንዲያገርሽ ሆኗል።
በወታደራዊ ደህንነቶች አማካኝነት እንቆጣጠረዋለን ብለው የምስራቅ እዝ ከፍተኛ የሕወሓት መኮንኖች ያሰቡት ጉዳይ ዳግም ውጥረት መፍጠሩ በድንበሩ አከባቢ ስጋት ስለፈጠረ ወደ አከባቢው አዲስ የመከላከያ ሰራዊት አንድ ሻለቃ ጦር እንዲመደብላቸው ጠይቀዋል።
የምስራቅ እዝ ምኮንኖች አብዛኛው ስራቸው የኮንትሮባድ ተግባራትን መፈጸም መዝረፍ እና ሴቶችን መድፈር መሆኑ ይታወቃል። የሕወሓት መኮንኖች ሌላውን አስፈላጊውን ሕግ የሚፈቅደውን ጥቅማ ጥቅም በመከልከል ከፍተኛ በድል እያደረሱ ሲሆን በሶማሊያ ክልል ውስጥ በዘረጉት ከፍተኛ የቢዝነስ ስራ ውስጥ ማንም ሌላ ሰው እንቅስቃሴ ማድረግ የማይችል ሲሆን እነሱ በሚሰሩ ቢዝነስ ውስጥ የሚገባ ንብረቱ እንደሚወረስ ታውቋል፡፤ የሞባይል ቀፎዎችን እና የኢሌክትሮኒስ ዕቃዎችን በሕገወጥ መንገድ ጭነው ካለፍተሻ ወደ መሃል ህገር በማምጣት በይርጋ ሃይሌ ሕንጻ ካሉ ወኪሎቻቸው ጋር በመተባበር በመላው ሃገሪቱ እንደሚያከፋፍሉ ታውቋል።

ኢትዮጵያን የሚገዛው ጉጅሌ ሀገራችንን እየወሰደበት ያለው አደገኛ አቅጣጫ አሳሳቢ ከመሆን አልፎ የአደጋውን መራራ ፍሬ ማየት ከጀመርን ሰነበትን። የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ወሳኝ ከሆነው የወደፊቱ የጋራ ጥቅማቸውና ህልውናቸው በበለጠ ልዩነታቸውና ያለፈ ታሪካቸው እንደዋናው ነገር እየተቆጠረ ለሚሰበከው ስብከት የኢትዮጵያ ህዝብ አስተዋይ ባይሆን ኖሮ እስካሁን ብዙ ጥፋት በደረሰ ነበር።
ህወሃት በህዝቡ ውስጥ የኖረውን ልዩነት የጠብ፣ የግጭትና የመፈራራት መሰረት በማድረግ በሥልጣን ላይ ለመቆየት ካለው ምኞት የተነሳ በመደዴ ካድሬዎቹ አማካኝነት ለዘመናት አብሮ የኖረውን ህዝብ በማቃቃር እኩይ ተግባር ላይ ተጠምዶ ይገኛል።
ህወሃት ይህን የማጋጨት ስራ በተለይ በስልጣን የመቆየት ፍርሃት ባባነነው ቁጥር የሚጠቀምበት መሳሪያ አድርጎታል። በባህርዳር ላይ የብሄረሰቦች ኳስ ጭዋታ ውድድር ምክንያት አድርጎ፣ መደዴ ካድሬዎቹን አሰማርቶ ስታዲዮም ውስጥ ኦሮሞዎች እንዲሰደቡ ካደረገ በኋላ ነገሩን ከማረጋጋት ይልቅ በኦሮሞኛ የቴሌቪዥንና ሬድዮ፣ ኦሮሞዎች በአማራዎች ተሰደቡ ብሎ ያስነገረው ለምንድን ነው? ከዚያ በኋላ በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ቁጣና ጠብ ለመቀስቀስ ብሎም በዚህ ጠብ ውስጥ ገላጋይ በመምሰል የአንዱ ብሄር ጠባቂ መስሎ ለመታየት ጉዳዩን ባልተረዱ የዋሆች ውስጥ ለመግባት ይፈልጋል። በአማራ ተወላጆች አካባቢ እኛ ከሌለን ኦሮሞ ይፈጇቹኋል፤ በኦሮምያም በሶማሊያም እንዲሁ በተዘጋ በር ውስጥ በተቃራኒው ዘረኝነትንና መከፋፈልን በመስበክ ንጹሃኑ ህዝብ ከፍርሃት ተነስቶ ተገዥ ደጋፊዎቹ እንዲሆኑ በማድረግ ላይ መሆኑንም ያልገባቸው የዋሆች ይኖራሉ። ህወሃትንና ባህርዩን በቅጡ ለምናውቀው ወገኖች ግን ይህ ተንኮሉ ትልቅ ሚስጥር አይደለም።
የጉጅሌው ቡድን የራሱን ስልጣንና የዝርፊያ ኢኮኖሚ ኮርቻ ለማደላደል እስከረዳው ወይም የሚረዳው መስሎ እስከታየው ድረስ ደሃ ገበሬዎችን ማፋጀትን፣ ህዝብን እርስበርስ ማናከስን፣ የቂም መርዝ መዝራትን የሚያየው እንደ ፖለቲካ ጥበብ ነው።
ጉጅሌው ብልጠት መስሎት የጎሰኝነትንና የማንነትን ደመነፍስ የሚነካ ፕሮፖጋንዳ በህዝቡ ውስጥ በመንዛት ሊያደርስ የፈለገው ጥፋት በአብዛኛው ህዝብ ዘንድ ስላልሰራለት የራሱን ሎሌዎችና ተካፋይ መደዴ ካድሬዎችን በማሰማራት የጭካኔ ስራዎችን በማካሄድ ላይ መሆኑን በብዙ መረጃዎች አረገጋግጠናል። በአሁኑ ወቅት በየቦታው የሚካሄደውን የህዝብ ማፈናቀልና ግጭት የሚመራው ራሱ ህወሃት ያሰማራቸው ካድሬዎች እንጂ በራሱ በህዝቡ ተነሳሽነት እንዳልሆነ ሁላችንም ልናውቅ ይገባል። በዚህ ሳይጣናዊ አካሄድ ለምትደርሰው ለያንዳንዷ ጉዳት ሀላፊነት የሚወስደውም ራሱ ህወሃት መሆኑን ግንቦት 7 አጥብቆ ያምናል።
ህወሃት መቃብር አፋፍ ላይ ሆኖ የሚደግስልንን የጥፋት ድግስ ለማምከን የየብሄረሰቡ ልሂቃን ሁሉ አንድ ላይ ሆነን ህዝባችንን እንድንታደግ ግንቦት 7 ለሁሉም የነጻነት ሃይሎች ጥሪውን ያቀርባል።
ግንቦት 7 በዚህ የህወሃት የጨለማ መንገድ ላይ የሚያበራውን የብርሃን ችቦ ይበልጥ በማብራት ላይ ይገኛል። ሁላችንም በምናገኘው የብርሃን ሃይል ጨለማው ላይ እያበራን ከማሳየት አልፈን ወደ መቃብሩ ልንገፋው ይገባል።
ግንቦት 7 በኢትዮጵያ የማንነትና የብሄር ብሄረሰብ ጉዳዮች በሰለጠነ መንገድ እና በመደማመጥ ሁሉንም ተጠቃሚ በሚያደረግ መንገድ መፍታት እንደሚቻል ያምናል። ይልቁንም የወደፊቱ የህዝባችንና የሀገራችን ጥቅም ይበልጥ የሚከበረው በስብጥርነታችን ላይ በምንገነባው አንድነት መሆኑን ያምናል።
የተከበራችሁ የአገራችን ዜጎች የነጻነታችን ጊዜ ቅርብ ነው። ህወሃት መቃብር አፋፍ ላይ ሆኖ ያዘጋጀልንን የጥፋት ድግስ፣ ሀገራችን የጋራ ጠላት በመጣባት ጊዜ ሁሉ እንደምታደርገው በአንድ ላይ ታግለን የጋራ ታሪክ እንሰራ ዘንድ የዘወትር ጥሪያችን እናቀርባለን።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!

በአማራ ክልል ለሚገኙ አመራሮችና አባላት የተደረገውን ስልጠና አስመልክቶ ከብአዴን ጽህፈት ቤት በቁጥር ብአዴን 145/10/ኢህ/06 ለኢህአዴግ ጽ/ቤት አዲስ አበባ በሚል የተጻፈው ደብዳቤ “አብዛኛው ህዝብ አሁንም ለመንግስት ከፍተኛ ጥላቻ” ማሳየቱን ገልጿል።
የብአዴን አመራር እና አባላቱ ከሰላም የዘለለ የልማት ለውጥ አለመምጣቱን፣ ኢህአዴግ ቢቀጥል ባይቀጥል ግድ እንደሌላቸው፣ እንዲሁም መንግስትን በትክክለኛ ዋጋው ሳይሆን በፍርሃት እንደሚያመሰግኑ በሰነዱ ላይ ተዘርዝሮ ቀርቧል።
“የኢትዮጵያ ህዝቦችና አገራዊ ህዳሴያችን” በሚለው የማጠቃለያ ግምገማ ሰልጣኞቹ ” ስለአገራቸው ታሪክ ብዙ ትምህርት መቅሰማቸውን፣ የህዳሴውን ጉዞ ለማሳካት ድርጅቱ እየከፈለ ያለውን መስዋትነት፣ የኢትዮጵያ ገናና ስልጣኔ ለምን እንደወደቀ፣ የህዳሴ ጉዞውን ሊያሳካ የሚችል መንግስት ያለ መሆኑን፣ የብዝህነትና እኩልነት ሀገራዊ ጠቀሜታ ፣ የአማራ ገዢ መደብ ሌሎች ብሄሮችና ብሄረሰቦችን ብቻ ሳይሆን አማራውን ጭምር እንደጨቆነ” የሚያሳይ ትምህርት መውሰዳቸውን ሰነዱ ያመለክታል።
በስልጠናው የብአዴን ታሪክ አብሮ መቅረቡንና ሰልጣኞችም የብአዴንን ታሪክ በማወቃቸው መርካታቸውን ሰነዱ አክሎ ይዘረዝራል።
“ግልጽነት ያልተያዘባቸውና በተግባራዊ እንቅስቃሴ ተከታታይ ውይይትና ስራ የሚጠይቁ ጉዳዮች ምንድን ናቸው?” በሚለው ንጹስ ርእስ ስር ደግሞ ” አሁንም ድረስ ብአዴንን የማይቀበሉ እና ከ97 ጋር በተያያዘ በመንግስት ላይ ተቃውሞ የሚያሰሙ ድምጾች አሉ፣ ነገር ግን የመንግስትን የሃይል እርምጃ ተከትሎ በፍራቻ እንዲኖሩ ማድረግ ተችሎአል።” ሲል አስቀምጧል።
“በውይይቱ ወቅት የታዩ የአመለካከት ችግሮች ምንድን ናቸው?” በሚለው ንዑስ ርዕስ ስር በርካታ ችግሮች ተዘርዝረው ቀርበዋል። ” በ1989 ዓም የነበረው የመሬት ክፍፍል ለቢሮክራቶች ለምን 4 ቃዳ መሬት ተሰጠ? በአማራ ክልል ብቻ የአርሶ አደር መሳሪያ ለምን ተነጠቀ? ልማቱ ወደ ትግራይ ይሄዳል፣ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት አስመራንና አሰብን መያዝ ነበረብን” የሚሉት ጥያቄዎችና አስተያየቶች በሰልጣኞች መቅረቡን ያወሳል።
ሰነዱ በስልጠናው የታዩ ደካማና ጠንካራ ጎኖችንም ይዘረዝራል። ሰልጣኙ እርስ በርስ በመተጋገዝ፣ በመማማር ተሞክሮውን በማካፈልና በመተራረም የነበረው ሁኔታ በሚለው ንጹስ ርእስ ስር ደግሞ ” አሁንም ለመንግስት ህዝቡ በአብዛኛው ጥላቻ ማሳየቱ” የሚል ሰፍሮአል።
የብአዴን አመራርና አባላት ” በአብዛኛው ከሰላም የዘለለ የልማት ለውጥ የለም ” ብለው እንደሚያምኑ፣ “ኢህአዴግ ቢቀጥል ባይቀጥል ደንታ እንደማይሰጣቸው”፣ እንዲሁም “መንግስትን በትክክል ዋጋ ሳይሆን በፍርሃት እንደሚያመሰግኑ” በሰነዱ ማብቂያ ላይ ተገልጿል።
ሰነዱን ለኢሳት የላኩትን የኢህአዴግን ከፍተኛ አመራሮች እንደወትሮው ሁሉ በህዝብ ስም ለማመስገን እንወዳለን።
ሰኔ ፲፯(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና

በነገረ‬-ኢትዮጵያ ጋዜጣ የተስተናደ
Image

ይስጥልኝ!! እንደምን ሰነበቱልኝ፡፡ ዛሬ ከካሳንቺስ ስድስት ኪሎ በቤተ-መንግስቱ አጥር ስር እያለፍን እናወራለን፡፡ እንቀጥል፡፡ ከካዛንቺስ ስድስት ኪሎ ለመሄድ የታክሲ ሰለፍ ይዣለሁ፡፡ እንደ በረሃ ዘንዶ የተጥመለመለው ሰልፍ የቤተ-መንግስቱን አጥር ታኮ ፊት በር ሊደርስ የጥቂት ምስኪን ተሰላፊዎችን ከኋላ መሆን ብቻ ይጠባበቃል፡፡ ትንሽ ክብዶ(ማካበድ) ስንጨምርበት ደግሞ ከኋላ በተሰለፈውና በቤተ-መንግስቱ ጠባቂ መካከል ያለው ርቀት አንድ መትረየስ አያሥጠምድም፡፡ አንድ ሰዓት ላይ የማልቀርበት ብርቱ ቀጠሮ 6 ኪሎ አካባቢ ይጠብቀኛል፡፡ ሳላረፍድ ለመድረስ 11 ሰዓት ካዛንቺስ ታክሲ መያዣ ደርሸ የመሰለፍ ግዴታየን መወጣት ይኖርብኛል፤ ወይም ይህን ሰልፍ ትቸ የአንድ ሰዓት የእግር ጉዞ በቤተ መንግስት አጥር ስር አንገቴን ደፍቸ ማለፍ ይጠበቅብኛል፡፡በዚህ ቤተ-መንግስት ለሚያልፍ ሰው አንገቱን ደፍቶ ማለፍ ግድ ይለዋል፡፡ ይህን ማድረግ ያልቻለን አስገድደው አንገት የሚያስደፉ ስልጡን ጠባቂዎች እንደ ግሪሳ ወፍ ወረውታል ቤተ-መንግስቱን፡፡ የሆነ ነገር ፈልገው ወይም የሚያሳክክ ነገር ቢገጥምዎት እንኳን ቀና ማለት ውጉዝ ነው፡፡ ይህን ካደረጉ ደግሞ ቁጭ በል ተነስ፤ቁም ሂድ የሚል ግልምጫ ሊከተልዎት ይችላል፡፡ አለፍ ካለና ጥበቃዎቹ እጅና እግራቸውን ማፍታታት ካስፈለጋቸው ደግሞ ጡጫ ነገርም ሊቀምሱ ይችላሉ፡፡ ለምን ብሎ ጥያቄ የለም፡፡ ምክንያቱም ይህ ቤተ-መንግስት ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ ሽር ማለት የሚችል መንግስት እንጅ እንደ እኔ አይነት አመዳም ድሃ አይደለምና፡፡ እድለ ጠማማ ከሆንክ ደግሞ አንዱ የአፍሪካ ነፍሰ ገዳይ አምባገነን መሪ ከቦሌ አየር ማረፊያ እየመጣ ስለሆነ ጀርባህን ሰጥተህ ቁም ልትባል ትችላለህ፡፡ በደርግ ጊዜ ነው አሉ እንዲህ እንዳሁኑ ሊቀመንበሩ ሲያልፉ ፊትህን አዙረህ ቁም ይባል ነበር፡፡ ይህ ድርጊታቸው ስልችት ያላቸው ሴትዮ ‹‹ሰውየውን የሚጠብቁት ከአይን ነው ወይስ ከጥይት›› አሉ ይባላል፡፡ ስለዚህ ይህን አካባቢ ፈጥን ብሎ በታክሲ ላፍ ማለት ይበጃል፡፡
በዚህ ደዲቃዎችን ሳይሆን ሰዓታትን በሚጠይቀው ሰልፍ ላይ የተደረደሩት ምስኪን የሀገሬ ዜጎች ሰማያዊ ታክሲ ላይ ትኩረት አድርገው አይናቸውን ላይ ታች ያቅበዘብዛሉ፡፡ በዚህ ሰልፍ ላይ የሌለ የሰው አይነት የለም፡፡ ከወፍራም እስከ የኔ ቢጤ ሲንብሮ፡ከሰማይ ቅርቡ ሞጋጋ እስከ እንቅፋት የመሰለ ድንክ፡ከምሁራን እስከ መሰረተ-ትምህርት ምሩቅ ብቻ ሁሉንም ሊያስማማ ከሚችለው መመዘኛ ከድህነት ውጭ ሰልፉ የሰው ማህበራዊ ነው ማለት ይቻላል፡፡ በነገራችን ላይ እንዲህ ታክሲዎች የመስቀል ወፍ በሚሆኑበት አጋጣሚ እንደ እኔ አይነት ቀጫጫዎች ተወዳጅነታቸው ይጨምራል፡፡ ቀጫጫዎችን በአንድ ወንበር እስከ ሶስትና አራት ሰው ለመጫን ስለሚመች፡፡ በመሆኑም እርስዎ ታክሲ ይሳፈራሉ እርስዎን ሌላ ሰው ተሳፍሮዎት ይጓዛሉ፡፡ ለምን ብሎ ጥያቄ የለም ምክንያቱም ይህ ጽሀዩ መንግስታችን ያመጣው ልማት ውጤት ነውና፡፡ በፈረንጅ ሀገር ወፍራም ሰዎች ተጨማሪ ክፍያ ይጠየቃሉ ሲባል ብሰማ መንግስቴን አጥብቄ አመሰገንኩት፡፡ እንዴት ብለው ከጠየቁኝ፤እንዲህ እመልሳለሁ፡፡ ሀገሬ ፍትሀዊነት የሰፈነባት በመሆኗ ወፍራሙም ቀጫጫውም እኩል የታክሲ ታሪፍ ስለሚከፍል፡፡ ደግሞ ኢቲቪ እንዳይማኝ፡፡ ኢቲቪ ከሰማ ግን እንዲህ ነው የሚዘግበው፡፡ ሀገራችን በታክሲ ታሪፍ ፍትሃዊነት በምስራቅ አፍሪካ አንደኛ ናት፤ አክሎም የታክሲ ሰልፈኛው ፈዛዛነት ለጎረቤት ሀገራት ምርጥ ተሞክሮ ሊቀመር የሚችል ነው ሲሉ አንዳንድ የታክሲ አሽከርካሪዎች ተናግረዋል!! ማለቱ አይቀርም ኢቲቪ ነፍሴ፤ ነፍሱ ይጥፋና፡፡ ጎበዝ በስንቱ አንደኛ ሆንን ተብሎ ይዘለቃል፡፡ ሌሎቹ ሀገራ ስራ አቆሙ እንዴ?!! በአንድ ወቅት አቶ መለስ ስለ ፍትሀዊ የገቢ ክፍፍል ሲናገሩ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከኖርዌይ ቀጥላ ሁለተኛ ናት ሲሉ ሙድ ይዘው ነበር፡፡ ከደረጃ ጋር በተያያዘ የሆነ ወቅት ላይ ሚስተር ኦባማ የአለም መሪዎችን ሰብስበው ተወያዩ ሲባል የሰማ ካድሬ መሪዎቹ በጉብዝናቸው ነው የተመረጡት ሲል አወራለት፡፡ ጓደኛየ ካድሬውን እንዲህ ጠየቀው ‹‹የመረጣው መስፈርት አንድ ከላይ አንድ ከታች ነው እንዴ››ብሎ ነበር፡፡ በታችኛው መመዘኛ የገባው ማን እንደሆነ መቸም ገምታችኋል፡፡ የእኔ ነገር የተነሳውበትን ነገር ስቸ ወዴት ተሰነቀርኩ፡፡ ወደ ቀደመ ነገሬ ልመለስና ስለ ታክሲ ሰልፌ ላውራ፤ ሰልፍ ሰልፍ ሰልፍ………….ኡፍፍፍፍፍፍ……….
ለምንና እስከ መቸ እንዲህ እንደምንሰለፍ ባይገባኝም፡የወገኔ ድካም ግን እጅጉን ያመኛል፡፡ ተሰላፊው የሰውነቱን ክብደት መሸከም አቅቶት እግሩ የዛለው ወገቡን ይዞ፤የባሰበት እየተቀመጠ፤የቀናው ደግሞ ከጎኑ የተሰለፈችን ኮረዳ እያሽኮረመመ ሰማያዊ ታክሲ ይጠባበቃል፡፡ ኮረዳ አሽኮርማሚው እንኳ ታክሲው ባይመጣም ግድ አይሰጠውም፡፡ በስንት ደቂቃ ልዩነት ብቅ የምትለው ታክሲ ከአስራ አምስት ሰው በላይ ጭና ላፍ ትላለች፡፡ ቀሪዎቹ ሰዎች ሰማያዊ ታክሲ መጠበቃችን እንደቀጠለ ነው፡፡ ፍቅረኛው ‹‹ሰማያዊ ልብስ ለብሸ እመጣለው ያለችው ጎረምሳ በታክሲ ይደነብራል›› እንደሚባው ሰማያዊ ነገር ባየን ቁጥር እናንጋጥጣለን፡፡ እንዲህ ወደ ታክሲው ያንጋጠጥነውን ያክል ወደ ቤተ-መንግስቱ ብናጋጥጥ መና ይወርድልን ነበር አልላችሁም መቸም፡፡ ታዲያ ቤተ-መንግስት ምን የሚወርድ ነገር አለ እንዳላችሁ ገብቶኛል፡፡ ‹‹ሆድ ይፍጀው›› አለ ሰውየው ብየ አልፈዋለው፡፡ በአሁኑ ጊዜ እኮ ስለ ቤተ-መንግስቱ የማይሆን ነገር ማሰብ አሸባሪነት ነው፡፡ ቀድማ የሄደችው ታክሲ የምትመለሰው ሾፌሩና ረዳቱ መቶ ግራም ገለምሶ ካኘኩ በኋላ ነው፡፡ ከስንት ሰዓት በኋላ እንደምንም እየተንፋቀቅን በሀይለ ስላሴ ጊዜ የተገዛች ከርካሳ ታክሲ ላይ ተጭነናል፡፡ መኪናዋ በጣም ከማርጀቷ የተነሳ ግጭት ቢደርስባት ቲታነስ ሊገድለዎት ይችላል፡፡ የብሄራዊ ሙዚየም ድክመት ነው እንጅ ታክሲዋ መገኛዋ እዛ ነበር፡፡ ለማንኛውም ጠጋ በል ከሚል የወያላ ንዝንዝ ለመዳን ስል ጋቢና መሳፈር እወዳለሁ፡፡ በእዛውም ቶሎ ለመድረስ ጋቢና መቀመጥ መፍትሄ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በታክሲ ፈልፍ ያባከንኩትን ጊዜ ያካክስልኛል ብል በአለም የመጀመሪያው ውሸታም አልሆንም፡፡
ሰው እንደ ቲማቲም ግጥግጥ ብሎ ተጭኗል…….ተሳፋሪዎች ጥቅጥቅ ብለው እንደገቡ ሴታ ሴት መሳዩ ሾፌር ገብቶ የመኪናውን ሞተር ቆሰቆሰው፡፡ ሞተሩ ተረክ ብሎ ተነሳ፡፡ በመቀጠል የተወዳጇ አስቴር አወቀ ተስረቅራቂ ድምጽ ከእስፒከሩ ወደ ጆሯችን ፈሰሰ፡፡ ‹‹ወይ ኑሮ ወይ ኑሮ›› ትላለች አስቱ የዛን ዘመን ኑሮ ዳገት ለመተረክ፡፡ የተዘፈነበትን ዘመን ሳይሆን ዛሬን የሚሰብከው የአስቴር ዘፈን ኑሮ እንዴት ከባድ እንደሆነ ለማስረዳ ያጣጥራል፡፡ ዘፈኑ በዚህ ዘመን ተዘፍኖ ቢሆን ምን ሊባል ኑሯል፡፡ ይህ ዘፈን ሲዘፈን የአንድ ኩንታል ጤፍ ዋጋ በአሁኑ የአንድ ምግብ ዋጋ ጋር እኩል ነበር፡፡ አስቱ አሁን ሪሚክስ አድርጋ ብትዘፍነው እንደ ብሄራዊ መዝሙር ሁሉም ሰው ተቀባብሎ ይጫወተው ነበር፡፡በዚህ በሀል አንዱ ተሰፋሪ በኑሮ ይማረር በምን እሱ ያውቃል፤ከሙዚቃው ድምጽ በላይ 11.2% ጮክ ብሎ ሙዚቃውን ቀንሰው ሲል ደነፋ፡፡ እንደ ተንቤን ኮረዳ ሹርባ የተሰራው ሴታሴት ሾፌር ድንገት ወንዳወንድ ሆኖ አልቀንሰውም ሲል መለሰለት፡፡ ቀጠል አድርጎም ተሳፋሪው ላይ የትችት ማዕበል አወረደበት፡፡‹‹ታክሲ ውስጥ ብቻ ነው መብትህ ትዝ የሚልህ?››ከሁለት ሰዓት በላይ ተሰልፈህ ስትቆይ ለምን ብለህ አልጠየቅክም? ወይስ አሁን ነው ሰው መሆንህ የገባህ? በሚሉ ሞጋች ጥያቄዎች ያፋጥጠው ጀመር፡፡ ሁሉም ተሳፋሪ በሾፌሩ መልስ በመገረም ጸጥ አለ፡፡ አሁንም ሾፌሩ መናገሩን ቀጥሎ ‹‹እኛ ላይ የምትጮኸው ጠብ-መንጃ ስለሌለን ነው›› ሲለው የኮረኮሩኝ ያክል አሳቀኝ፡፡ ሌላው ተሳፋሪም አብሮ ሳቀ፡፡ ሰውየውም ሂሱን ውጦ ዝም አለ፡፡ ‹‹ጠብ መንጃ ስለሌለን›› ድንቅ አባባል፡፡ ተናጋሪው ሰውየ ድንገት የተቃዋሚዎች ስብሰባ እንደታደመ ካድሬ ቅስሙ ተሰብሮ ጸጥ አለ፡፡ ወደ ውስጤ አሰብኩ የሹፌሩ ነገር ትክክል ነበር፡፡ ከሁለት ሰዓታት በላይ ታግሶ መሰለፍ የቻለ ሰው እንዴት የሙዚቃ ድምጽ በዛ ብሎ ለመቃወም ወኔ አገኘ፡፡ ያውም ለስለስ ብሎ የተከፈተን ሙዚቃ ካቀነስክ በሚል ጥያቄ፡፡ በነገራችን ላይ ከመጠን በላይ የሚለቀቁ ሙዚቃዎች አግባብ ናቸው የሚል መከራከሪያ የለኝም፡፡
ታክሲዋን ቀና ብየ አየኋት፡ጥቅሶች ተንጠልጥለዋ፡፡ ዙሪያ ገባዋ በአብዮተኛ ጥቅሶች ተሞልታለች ያች ከርካሳ ታክሲ፡፡ ትኩረቴን የሳበችኝ ግን ‹‹መብትህን ከታክሲ ስትወርድም ጠይቅ!!›› የምትለዋ ነች፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ ሾፌሩን አደነቅኩት፡፡ ሳትፈራ ጠይቅ ነው ያለው ሾፌሩ፡፡ የጥበብ መጀመሪያው መጠየቅ ነው!! እንዲል የእኔ ፍልስፍና የመጨረሻው ምዕራፍ፡፡ ትክክል መስሎ ያልተሰማንን ነገር መጠየቅ፤ያላመንበትን ላለማድረግ እንቢ ማለትን መለማመድ ይጠበቅብናል፡፡ እኛ ኢትዮጵያዊያን ስንባል ትልቁ ችግራችን ክፉ ቀንን ታግሎ ከማሸነፍ ይልቅ ችግሩን መለማመድ ይቀለናል፡፡ ልመደው ሆዴ የዘወት እንጉርጎሯችን ነው፡፡ ‹‹ክፉ ቀንን እና ቅዝምዝምን ጎንበስ ብሎ ማሳለፍ ነው›› ስንል እንተርታለን፡፡ ‹‹ቀን ሲያልፍ ተናገር ወንዝ ሲጎድል ተሻገር›› እንላለን፡፡ በአባቶቻችን ተረት የምንኖር በተረት እንኳን እራሳችንን ያልቻልን ምስኪኖች፡፡ ‹‹ቻለው ሆዴ ልመደው በዘዴ››ን በአደባባይ የምዘፍን………
የተንዘላዘለውን ሰልፍ ለማስቀረት ከምንዘይደው ይልቅ የምንለምድበትን ዘዴ እንፈጥራለን፡፡ ኑሮ ማለት ሰልፍ እስኪመስለን ድረስ ለዳቦ እንሰለፋለን፡ለታክሲ ሰልፍ፡ሲያስለቅሰን ለኖረ ሰው የሀዘን ሰልፍ፡ለሰልፋችን መንስኤ የሆነን አምባገነን ለመቅበር ሰልፍ፡በአጠቃላይ ኑኗችን ሰልፍ የሆንን ድንጉጦች….!! በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ከእድገት በህብረት ዘመቻው ሰልፍ ቀጥሎ ረጅሙ ሰልፍ የታክሲ ሰልፍ ሳይሆን አይቀርም፡፡ የዚህ ሁሉ ሰልፋችን መንስዔ የሆነውን መንግስት እንፈረዋለን፡፡ ከፍርሀታችን የተነሳም መንግስትን ለማማረር እንኳ በራችን በደንብ መዘጋቱን እርግጠኛ የምንሆን ስንቶቻቻን ነን?፡፡ እንዚህን ሰልፎች አንድ ቀን አንዱ ወፈፌ መፎክር ያስያዛቸው እለት ምን ሊሆን እንደሚችል መገመቱ ከባድ አይሆንም፡፡ ‹‹መንግስት ባቡሩ ሲያልቅ ችግሩ ይቀረፋል እስከዚያው ድረስ ባቡሩን መስላችሁ ተሰለፉ›› እያለ ጥሩምባውን ይነፋል፡፡ ድሃ በህልሙ ቅቤ ባይበላ ኖሮ እከክ ይበጣጥሰው ነበር እንዳሉት አይነት ነው፡፡እኔ የምጠቀመው የስድስት ኪሎ ታክሲ ስለሆነ ችግሬ አይቀረፍምና ዝም አልልም፡፡ ወይም እንደተባለው ተስፋ ማድረግ ይቻላል፡፡ ለነገሩ ዝም ባንልስ ምን እናመጣለን፡፡ እኛ ጠብ-ምጃ የለን ማን ይፈራናል፡፡ ከታክሲው በሰላም ወርጃለው፤የቀጠርኩት ወዳጀም ከፊት ለፊቴ ይታየኛል፡፡ የሾፌሩ ድምጽ ግን አሁንም ይከተለኛል፡፡ ‹‹እኛ ጠብ-መንጃ ስለሌለን ነው የምትጮኸው››?!! ትልቅ አባባል!!
ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል!!

አዲስ አበባ እና መቀሌ ላይ በተከታታይ እየተካሂዱ ያሉ ስብሰባዎች ውጥረቱ ያመለክታሉ። እያንዳንዱን እንቅስቃሴያችንን የሚከታተሉ እና የሚያጨልሙን ሰላዮች ተመድበውብናል ሲል መቀሌ ያለው የሕወሓት አንጃ አኩርፏል። ከመሃል አገር የፌዴራል መንግስቱን በመቆጣጠር እያሾረው ያለው የሕወሓት አመራሮች ቡድን መቀሌ በሚገነው አንጃ ላይ ሰላዮችን አሰማርቷል ሲሉ በትግራይ ክልል ያሉ የሕወሓት ባለስልጣናት እየከሰሱ ነው፡፤ ይህንን ተከትሎ የተነሳው ኩርፊያ እና አለመግባባት ሕወሓቶችን ዳግም ወደ ቀድሞው ሽኩቻ እና ቅራኔ ውስጥ እንዳይከታቸው ያሰጋል ሲሉ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ጠቁመዋል።

በግንቦት ሃያ በአል ምክንያት ወደ አውስትራሊያ ተጉዘው የነበሩት አለቃ ፀጋይ በርኸ እና ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ ብምካከላቸው በተነሳ አለምግባባት በተለያየ በረራ ወደ አገር ቤት መመለሳቸው የሚታወስ ሲሆን አለቃ ጸጋይ አብረውን በተጓዙ ጭፍሮቹ ያሰልለናል ሲሉ የቡድኑ አባላት ሲናገሩ ተደምጧል። አለቃ ጸጋይ ሰክረው የሰው ሚስት ሊያሽኮርምሙ ሲዳዳቸው በቡጢ መዘረራችው ይታወቃል።

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

የመንበረ ፕትርክናው ነጻነት በተገኘበትና ብሔራዊ ቅዱስ ሲኖዶስ በተቋቋመበት ባለፈው ግማሽ ምእት በተነሡ ቅዱሳን ጥናትና አሠያየም ላይ ትኩረት ይሰጣል፡፡ ቀኖናው ተደጋጋሚ ራእይና ተኣምራት በማሳየት የተመሠረተውን የቤተ ክርስቲያናችንን የቅዱሳን አሠያየም ትውፊት ሲኖዶሳዊ በማድረግ የሚያጠናክር ነው ተብሏል፡፡ የኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ ወቅዱስ ፖፕ አቡነ ቄርሎስ ስድሰተኛንና ሊቀ ዲያቆን ሐቢብ ጊዮርጊስን በቅድስና ለመሠየም በምታደርገው ዝግጅት ቅድስናቸውን ዐውቃላቸዋለች፡፡ ኹለተኛው …

‹‹መመሪያው በኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች ላይ በማተኮር በአድሏዊነት ይፈጸማል›› /ተማሪዎቹ/ ‹‹መንግሥት ለሙስሊም ኾነ ለክርስቲያን ተማሪዎች በልዩ ኹኔታ ምግብ እንዲዘጋጅ ፈቅዷል›› /የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሚያዝያ ፳፻፮ ዓ.ም. የመመሪያው አጸፋዊ ማብራሪያ/ ‹‹ዩኒቨርስቲው ያወጣው መመሪያ ላይ እንዲህ የሚል የለም፤ ሴኩላሪዝም ባለበት ዩኒቨርስቲና በዩኒቨርስቲው የሴኔት ሕግ መሠረት የሰኔን ጾም ይኹን ሌላውን ጾም የማጾም ግዴታ የለብንም፤ ዩኒቨርስቲው የራሱ ፕሪንስፕልና መመሪያ አለው፡፡›› /በአድሏዊነት …

‹‹ዕውቅናችን ሕጋዊ ነው፤ ቅሬታችን በአግባቡ አልተስተናገደም፡፡›› /የኅብረቱ አመራሮች/ በየሀገረ ስብከቱ ለተበራከቱት ማኅበራት መመሪያ እንዲዘጋጅላቸው ተጠይቋል (ኢትዮ-ምኅዳር፤ ቅፅ ፪ ቁጥር ፸፪፤ ረቡዕ፣ ሰኔ ፲፩ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.) በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር የተደራጀው ‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ወጣቶችና ጎልማሶች ማኅበራት ኅብረት›› የአገልግሎት ፈቃድ በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ መታገዱ ተገለጸ፡፡ የእግድ ውሳኔው ለኹሉም ማኅበራት በማዕከል ተዘጋጅቶ …

በኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች በቀረቡ ዘገባዎችና ጽሑፎች ላይ ተመሥርቶ በሚ/ር ዴኤታው አቶ ሙሉጌታ ውለታው በተመራው የሚኒስቴሩ ግምገማ፣ የተላለፉት መረጃዎች ሐሰት እንደሌለባቸውና እነዶ/ር ሺፈራው በፀረ አክራሪነት ትግሉ አያያዝ ላይ ድክመት እንዳለባቸው ማሳየቱ ተጠቁሟል፡፡ የግንባሩ አመራሮችና አባላት ጭምር የተቃወሙት የእነዶ/ር ሺፈራው ማኅበሩን በማዳከም ቤተ ክርስቲያንን የማቀጨጭ የአክራሪነት ፍረጃና መፍቀረ ፕሮቴስታንታዊ ብሎግ መር ትንታኔ የግንባሩን ድርጅታዊ መዋቅር ለማይቀለበስ አደጋ …

በአብዮቱ መባቻ ዓመታት ከደርጉ ‹‹የለውጥ ሐዋርያት›› ጋራ በቁርኝት ሠርተዋል ከደርግ ጋራ አብሮ በመሥራትና ደርግን በማውገዝ መካከል የሚታዩት የፓትርያርኩ የአቋም ጽንፎች ፀረ አማሳኝ መስሎ የአማሳኞች ከለላ ኾኖ የመገኘት ፍፃሜ ነው!! (ፋክት መጽሔት፤ ቅጽ ፪ ቁጥር ፵፱፤ ግንቦት ፳፻፮ ዓ.ም.) ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቤተ ክርስቲያኒቱና መሪዎቿ ከመንግሥት ጥገኝነት ነፃ ሊኾኑ እንደማይችሉና መንግሥት በቤተ ክርስቲያኒቷ የአስተዳደር …

ጠቅላላ ጉባኤው በየዓመቱ የሚካሔድበት በዓለ ጰራቅሊጦስ ‹‹የሰንበት ት/ቤቶች ቀን›› ነው ሰንበት ት/ቤቶች ከአማሳኞች ጋራ የገቡበት ግጭትና አፈታቱ የጠቅላላ ጉባኤው ትኩረት ነው ጥያቄያቸው በአግባቡና በወቅቱ ባለመፈታቱ ወጣቶች በየቦታው እየተንገላቱና እየታሰሩ ነው ከ፳ ሚልዮን በላይ ወጣቶች በሰንበት ት/ቤቶች የታቀፉት ከ፬ ሚልዮን አይበልጡም 60 ሺሕ ወጣቶች በ102 ማኅበራት የተደራጁበት የአ/አ ወጣቶች ማኅበራት ኅብረት ፈቃድ ታገደ (ምንጭ፡- አፍሮ ታይምስ፤ …

ጳጳሳት የፓትርያርኩን የማኅበረ ቅዱሳን ደንብ ማሻሻያ ቅድመ ኹኔታ አልተቀበሉትም ‹‹ቅድመ ኹኔታው የማኅበሩን አገልግሎት የሚያቀጭጭ በሒደትም የሚያስቆም ነው፡፡›› /ታዛቢዎች/ ማኅበሩ የመተዳደርያ ደንቡ ማሻሻያ ረቂቅ እስኪጸድቅ በነባሩ ለመመራት ይገደዳል (አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፫ ቁጥር ፯፻፶፤ ቅዳሜ ግንቦት ፳፫ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን መተዳደርያ ደንብ ማሻሻያ ረቂቅን እንደ አንድ አጀንዳ የያዘው የዘንድሮው …

በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ መሠረት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚመራው በቅዱስ ሲኖዶስ በተሾመ ኤጲስ ቆጶስ ወይም ሊቀ ጳጳስ እንጂ በፓትርያርኩ የምደባ ምክረ ሐሳብ አለመኾኑን በመጥቀስ ነው ጥያቄአቸው ተቀባይነት ሳያገኝ የቀረው፡፡ ከዚህም ባሻገር የብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ከሓላፊነት መልቀቅ ምክንያታዊ ማብራሪያ እንደሚያስፈልገው ምልዓተ ጉባኤው ፓትርያርኩን በማሳሰቡ ለአ/አበባ ሀ/ስብከት የሊቀ ጳጳስ ምደባ አልተደረገም፡፡ ምልዓተ ጉባኤው ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በሓላፊነታቸው …

ከግንቦት ፭ – ፲፱ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ለ16 ቀናት የተካሔደውን የምልዓተ ስብሰባ ውሳኔዎች በ17 ነጥቦች የዘረዘረውና ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ላይ የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በፓትርያርኩ ቢነበብም የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ በማኅበረ ቅዱሳን መተዳደርያ ደንብ ላይ የተጀመረው ውይይት ቀጥሎ ውሳኔ እንደሚያሳልፉ ተናግረዋል፡፡ በመግለጫው ተ.ቁ.(12) ላይ የማኅበረ ቅዱሳን መተዳደርያ ደንብ ማሻሻያ ረቂቅ በተመለከተ በ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. …

ፓትርያርኩ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ከጨለማው ቡድንና ፖለቲከኞች ጋራ የመከሩበትን የራሳቸው ያልኾነ ሐሳብና አጀንዳ የተቃወሟቸውን የምልዓተ ጉባኤውን አባላት ‹‹በገንዘብ የተገዛችኹ›› እያሉ በመዝለፍ ቅዱስ ሲኖዶሱን ተዳፍረዋል፡፡ አቡነ ማትያስ ለአጥኚ ኮሚቴው የላኩት ባለ24 አንቀጽ ድንጋጌዎችና ግዴታዎች ሳይቀነሱና ውይይት ሳይደረግባቸው በደንቡ ካልተካተቱና ረቂቁ በሌላ ኮሚቴ ዳግመኛ ካልታየ በሚል አጀንዳውን በራሳቸው አቋም ብቻ ለመቋጨት ያደረጉት ሙከራ በፍጹም አንድነት በቆሙት ብፁዓን …