ሰበር ዜና – አባላቱ በሀብታም እና ድኻ መከፈላቸውን የተቃወመው የሰሚት መድኃኔዓለም ሰንበት ት/ቤት በአለቃው ታሸገ፤ ‹‹ምርጫው ይለፍና አሳስራችኋል፤ ልክ አስገባችኋለኹ›› እያሉ ሲዝቱ ሰንብተዋል
- ርምጃው የሀ/ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ፣ አመራሩ እንዲቀየር የጻፉትን ደብዳቤ መነሻ ያደረገ ነው
- ለጥያቄአቸው ምላሽ ባለማግኘታቸው በፓትርያርኩ ላይ ቅሬታቸውን በመዝሙር ገልጸው ነበር
- ከ200 በላይ አባላት የሚማሩበት አዳራሽና የሰንበት ት/ቤቱ ጽ/ቤት ቁልፎች ተሰብሮ ታሽግዋል
- የደብሩ ስምንት አመራሮች ከመሳለም በቀር ወደ ደብሩ ገብተው እንዳይሰበሰቡ ተከልክለዋል
* * *
- በካህናትና በምእመናን አንድነት መመራት ባለበት ደብር የአለቃው ዓምባገነንነት ሰፍኖበታል
- ሰበካ ጉባኤ የለም፤ በአቋሜ አይስማሙም ያሏቸውን ብዙኃኑን የሰበካ ጉባኤ አባላት አግደዋል
- ሦስት የሰንበት ት/ቤቱ አመራሮች የፖሊቲካ ፓርቲ አባላት ናቸው በሚል ለቀናት ታስረው ነበር
- ክሣቸው ተነሥቶ የሀብታም በሚል የተለየው ጉባኤ እንዲቀር የተሰጠው ትእዛዝ አልተፈጸመም
- በደብሩ አቅራቢያ የሚገኘው የጎሮ ፖሊስ ጣቢያ አለቃው እንዳሻቸው የሚያዙበት ነው ተብሏል
* * *
- በፀረ ሙስና እና ፀረ ኑፋቄ ንቅናቄው የተደናገጡ አማሳኞች የሐሰት አቤቱታ እያሰባሰቡ ነው
- ‹‹ተሐድሶ የለም›› በሚል የሰንበት ት/ቤቶችን አመራሮች ለመከፋፈል እየተፍጨረጨሩ ነው
- የማደራጃ መምሪያው ዋና ሓላፊና በሙስና የተጨማለቁ የሀ/ስብከቱ ሓላፊዎች ይተባበሯቸዋል
- መላው የሰንበት ት/ቤቶች አባላት የአንድነቱን የወሳኝ ፍልሚያ ጥሪ በንቃት እየተጠባበቁ ነው

