በአማሳኞች በደል እና በፍትሕ ዕጦት የተመረሩ ምእመናን ርምጃ መውሰድ ጀመሩ፤ በቦሌ ቡልቡላ መድኃኔዓለም ሓላፊዎችን በማስወጣት እና መኪኖቻቸውን በማገት ጽ/ቤቱን ተቆጣጠሩ
- አስተዳደሩ፣ በሕገ ወጥ ኪራይ የደብሩን ጥቅም ለሦስተኛ ወገን አሳልፎ በመስጠት ይታወቃል
- ጽ/ቤቱን አስበይደው በማሸግ የተቆጣጠሩት ምእመናኑ የተመሩት በሰንበት ት/ቤቱ አባላት ነው
* * *
- በመ/ፓ ቅ/ቅ ማርያም፣ የሒሳብ ፈራሚነቱን ለቄሰ ገበዙ ለማሳለፍ የተደረገው ጥረት ከሽፏል
- ሒሳብ ሹሙ ‹‹ጉረሮዬን ዘግተኽ አትኖርም›› እያለ በምእመኑ ተወካይ ላይ ሲዝት ሰንብቷል
* * *
- በደ/ሲና እግዚአብሔር አብ ያለደንቡ የታሰበው የሰ/ት/ቤት አመራር ለውጥ በውጥኑ ታርሟል
* * *
- የታሰሩ የሰ/መድኃኔዓለም ምእመናን በሃይማኖት ሰበብ ሕዝብን ማሳመፅ በሚል ፍ/ቤት ቀረቡ
- በሊ/ማ የማነ ላነጋግራችኹ አልፈልግም የተባሉት ቤተሰቦች ከጽ/ቤቱ በር በጥበቃ ተመልሰዋል
* * *
የፀረ ሙስና እና የፀረ ኑፋቄ ንቅናቄው በተቀናጀ ስልት ወደ ተግባራዊ ርምጃ ተሸጋግሯል!
አማሳኞች እንዲጠይቁ፣ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጆች እንዲወገዱ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና እንዲከበር እና ውሳኔዎቹ እንዲተገበሩ በየደረጃው ጩኸታቸውን ሲያሰሙ የቆዩት ማኅበረ ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤቶች በየአጥቢያቸው የተቀናጀ ርምጃ መውሰድ ጀምረዋል!
በሙስና፣ በአስተዳደር በደል እና በፍትሕ ዕጦት የተመረሩት ማኅበረ ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤቶች፣ በየአጥቢያቸው በአማሳኝ ሓላፊዎች ላይ የጀመሩት የፀረ ሙስና እና ፀረ ኑፋቄ ተግባራዊ ንቅናቄ÷ በእብሪት፣ በጥቅመኝነት እና በጎጠኝነት ለታወረው እና ለደነቆረው የፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስተዳደር የማንቂያ ደወል ነው!