ብፁዕ አቡነ አብርሃም የባሕር ዳር ከተማ ሀገረ ስብከትን እንዲመሩ ተመደቡ

abune-abraham-archbishop-of-the2

ብፁዕ አቡነ አብርሃም

 የምዕራብ ጎጃም – ፍኖተ ሰላም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃምየባሕር ዳር ከተማ ሀገረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መደባቸው፡፡

ምልዓተ ጉባኤው ብፁዕነታቸውን የመደበው፣ የባሕር ዳር ከተማ የአዊ እና መተከል ዞኖች ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሚያዝያ ፱ ቀን በድንገተኛ ሕመም ማረፋቸውን ተከትሎ ነው፡፡

ለብፁዕነታቸው መልካም የሥራ ዘመን እንመኝላቸዋለን፡፡