ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

በቦስተን የመካነ ሕይወት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በሊቢያ እና በተለያየ ቦታዎች በግፍ ለተጨፈጨፉት ወገኖች በትናንትናው ምሽት የጸሎት እና የሻማ ማብራት ስነ ስርአት በርካታ ኢትዮጵያውያኖች በተገኙበት፤ በደማቅ ስነ ስርዓት ተካሄደ!! የመካነ ሕይወት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በጠራው የሻማ እና የጸሉት ስነ ስርዓት ላይ በቦስተን እና አካባቢዋ የሚገኙ ኢትዮጵያውያኖች፤ የመካነ ሕይወት ቤተ ከርስቲያን እና የመካነ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን […]

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን ‹‹ርትዕት ሃይማኖቶሙ ለቅዱሳን አበዊነ = የአባቶቻችን ሃይማኖት የቀናች ናት›› ራሱን እስላማዊ መንግሥት (አይ ኤስ አይ ኤስ) እያለ የሚጠራው የጨካኝ አረመኔዎች ስብስብ፣ በግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ላይ ያካሔደው ዘግናኝ ግድያ ሳይበቃው ይህን እኩይ ድርጊቱን በልዩ ልዩ ምክንያት ከአገር ተሰድደው በሊቢያ በነበሩ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን …

በሶሻል ሚዲያ (ፌስ ቡክ) Ahamab muhamad oromo የሚባል ሰው ከብሄር ጋር የተያያዙ ጠንከር ያሉ መልእክቶችን በአማርኛና በኦሮምኛ ሲያስተላልፍ ቆይቷል፡፡የኢትዮጵያን ባንዲራ ሲረግጥ የሚያሳይ የራሱን ምስልም በመለጠፍ ጥላቻውን ማሳየቱን ብዙዎች ያስታውሱታል፡፡ ግለሰቡ የፕሮፋይል ምስሉ የአሜሪካ መንትያ ህንጻዎች ሲጋዩ የሚያሰይ ፎቶ ግራፍ ካደረገም ረዘም ያሉ ግዜያት ተቆጥረው ነበር፡፡ ወንድሞቻችን በሜድትራንያን ባህር አካባቢ በአይ ኤስ አይ ኤሶች ግድያ ከተፈጸመባቸው […]

  ማምሻውን ፖሊሶችና ፌድራል ፖሊሶች ጨርቆስ ቤተክርስቲያን ውስጥ በመግባት በምእምናን ላይ ድብደባ መፈጸማቸውን ጉዳት የደረሰባቸው  ገለጹ ህወሃት መራሹ ኢህአዴግ የእምነት ቦታዎችን በማርከስ ከዚህ ቀደም በገዳማት በመስጅዶች ውስጥ በመግባት በምእምናን ላይ ድብደባ ሲፈጸም መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን በዛሬው እለት በጨርቆስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ድረስ በመዝለቅ ከፍተኛ ድብደባ መፈጸማቸውን በቦታው ላይ ድብደባ የተፈጸመባቸው  ገልጸዋል፡፡… በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ከሚስቱ ጋር እንደነበር […]

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን፡፡ ‹‹ኢትዮጵያዊ መልኩን ነብር ዝንጉርጉርነቱን ሊለውጥ ይችላልን? ልጆቻችን የምንኮራባቸው መጻሕፍቶቻችን፣ የምንማርባቸው ዩኒቨርስቲዎቻችን ናቸው፤ አስተምረውናል፤ አኩርተውናል፤ አስከብረውናል›› (ብፁዕ አቡነ ሉቃስ፤ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፤ የሰቲት ሑመራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ) የልጆቻን የኃይለ ሚካኤል(ኢያሱ ይኵኖ አምላክ) እና የኃይለ ኢየሱስን(ባልቻ በለጠ) ነፍስ ይማርልን፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን የሐዘን ዳርቻ ያድርግልን፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን የቤተሰቡን …

ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ‹‹እስመ በእንቲኣሁ ይቀትሉነ ኲሎ አሚረ፡፡ ወኮነ ከመ አባግዕ ዘይጠብሑ = ስለ አንተ ቀኑን ኹሉ እንገደላለን፤ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን::›› (መዝ.43÷22) *       *       * ራሱን እስላማዊ መንግሥት (IS) እያለ በሚጠራው ዓለም አቀፋዊው አሸባሪ ድርጅት በይፋ በኢንተርኔት ባሰራጨው የቪዲዮ መረጃ፣ በኹለት የተለያዩ ቦታዎች በአሠቃቂ ኹኔታ የገደላቸው ወንድሞቻችን የተገኘባቸው አበሳ ወይም ወንጀል ክርስቲያን ኹነው …

የቀድሞው የግብፅ ፕሬዚዳንት መሐመድ ሙርሲ የሃያ ዓመታት እስራት ፍርድ

ለግብፅ አምስተኛው ፕሬዚዳንት ናቸው፡፡ በግብፅ ታሪክም የመጀመርያው በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የፕሬዚዳንትነቱን መንበር የጨበጡ ሲቪል መሪ ነበሩ፡፡

ግብፅን ለሦስት አሥርት ያህል የገዟትን ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ከገረሰሰው የግብፅ አብዮት በኋላ፣ እ.ኤ.አ. በሰኔ 2012 ሥልጣን የያዙት የቀድሞ የግብፅ…

Abune Elias. ብፁዕ አቡነ ኤልያስ

Ethiopia Zare (ረቡዕ ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. April 22, 2015)፡- ዛሬ ማምሻውን ከ12 ሰዓት (18፡00) ጀምሮ ለሁለት ሰዓታት በስቶክሆልም በደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን በሊቢያ ለተገደሉት ወገኖቻችን በብፁዕ አቡነ ኤልያስ የምስራቅ አፍሪካና የአውሮጳ ሊቀጳጳስ የተመራ ሥርዓተ ጸሎት ተደረገ። በርካቶች ሲያለቅሱ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በአይሲሲ እና በደቡብ አፍሪካ ለተገደሉት ኢትዮጵያዊያን በኖርዌይ ስታቫንገር የመድሐኒያለም ቤተክርስቲያን የፀሎት ስነ ስርዓት ተደረገ በአይሲሲ እና በደቡብ አፍሪካ ለተገደሉት ኢትዮጵያዊያን በኖርዌይ ስታቫንገር መድሐኒያለም ቤተክርስቲያን የፀሎት ስነስርዓት ተደረገ። የማጽናኛ ትምህርት በቤተክርስቲያን አባቶች ተሰጠ  እንዲሁም የማች ቤተሰቦች የመጽናኛ ፀሎት እና የጣፍ ማብራት  ስነስርዓት የተደረገ ሲሆን ከዛም በመቀጠል አይሲሲ እና ደቡብ አፍሪካን በመቃወም በስታስታቫንገር ሴንትሩም የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ። ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ […]

ከምሺቱ ፫ ሰሃት ጀምሮ በድፍን አዲስ አበባ አሸባሪው የወያኔ መንግስት መብራት በማጥፋት በ  በተገደሉት ወገኖቻችንና ለህዝቡ ግድ የሌለው የወያኔን ጉጂሌ በመቃወማቸው በዚህም የተበሳጨው የወያኔ መንግስት በለሊት ህዝቡን ከየቤቱ እያፈሰና በመኪና እያጋዘ ይገኛል ብዙ ወገኖቻችን ኣሁን ባደረሱኝ መረጃ መሰረት የከተማዋ መብራት በማጥፋት ልባቸው በሃዘን የተቃጠሉትን ወገኖቻችንን በጂምላ እያፈሰ ነው የትም እንዳደረሳቸው አልታወቀም ተብላል። posted by Aseged […]

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ኢስላሚክ ስቴት ወይም ISIS/ISIL በመባል የሚታወቀው አሸባሪ ድርጅት በሊቢያ በኢትዮጲያውያንን ክርስቲያኖች ላይ የፈፀመውን ግድያ ቪድዮ ባለፈው እሁድ ማሰራጨቱን ተከትሎ፤ ድርጊቱን ለማውገዝ ዛሬ ሰልፎች ተካሂደዋል፡፡ ያንን አስመልክቶ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ሚኒስተር ሬድዋን ሁሴን ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ከጽ/ቤቱ ያገኘነውን የመግለጫው ጭማቂ ጽሑፍ ከዚህ በታች አትመነዋል፡፡ 1) የተሳካ ሰልፍ ተካሂዷል፣ * ህዝቡ ከጫፍ ጫፍ ወጥቷል፣ * በሰላማዊ መንገድ በጋራ ሀዘኑ ዙሪያ፣ በቀጣይ የጋራ ጥረቶች ዙሪያ ያጠነጠነ መልዕክቱን አስተጋብቷል፣ * አንድነቱን በማጉላት ሽብርተኞች ለመፍጠር የፈለጉትን የመከፋፈል ሴራ ሙስሊም ክረስቲያን ሳይል በጋራ ተሰልፎ በመምጣት አክሽፏል፣ * ሽብርተኝነት ሃይማኖታዊ መሰረት እንደሌለው በማንኛውም ሃይማኖት ጀርባ መሸሸሸግ እንደማይገባ አረጋግጧል፣ * ISIS ማንኛውንም ሃይማኖት እንደማይወክል ፅንፈኝነትና አክራሪነትን እንዲሁም የሽብር ተግባርን ብቻ እንደሚወክል ስለዚህም የጋራ ጠላት መሆኑን በአንድ ድምፅ አስረግጧል፡፡ * የፀረ ሽብርና አክራሪነት ትግሉን ከመንግስት ጎን ቆሞ ለማጧጧፍ ያለውን ፅኑ አቋም አስተጋብቷል፡፡ * ህገ ወጥ ስደትን በመላ ህዝቡ ተሳትፎ ማስወገድ እንደሚገባ በቁጭት ገልጿል፣ * በሀገራችን ሰርቶ መለወጥ የሚቻልበት ዕድል እየተፈጠረ በመሆኑ ከነክብራችን በሀገራችን ሰርተን እንለወጥ የሚል ፅኑ አቋም አስተጋብቷል፣ * የሃይማኖት አባቶችንና የመንግስትን መልዕክት በጥሞናና በትእግስት አዳምጦ የቀጣይ ትግል ባለቤትነቱን አረጋግጧል፣ * በመሆኑም መንግስት የከበረ ምስጋና ያቀርባል፣ * ከህዝቡ በተጨማሪም የሀገራችን ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ከአንዳንዶች በስተቀር የደረሰው አደጋ በሰው ልጆች ላይ የተቃጣ ኢሰብአዊ ድርጊት መሆኑንና የኢትዮጵያውያን የጋራ ሀዘን መሆኑን፣ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት በሚደረገው ጥረትም የበኩላቸወን ድርሻ የሚወጡ መሆኑን በፓርቲዎች […]

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2007(ኤፍ.ቢ.ሲ) ባሳለፍነው እሁድ በሊቢያ ውስጥ በአሸባሪው አይ ኤስ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ኢተዮጵያውያን ማንነት በመለየት ላይ ይገኛል።

በዚህም መሰረት በርካታ የሟች ቤተሰቦች የልጆቻቸውን ሞት ተረድተው ሀዝን በመቀመጥ ላይ ይገኛሉ።

ቀደም ብሎ ኢያሱ ይኩኖአምላክ እና…

መንግስት ራሱ በጠራው ሰልፍ ላይ በተገኙት ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ድብደባ ፈጸመ:: ፎቶች ይዘናል ይመልከቱ፤ የBBN ድምጽ ዘገባ እዚህ በመጫን ያዳምጡ ህዝቡ ካለማንም ነጋሪነት ካለማንም ተቃዋሚ ጣልቃ ገብነት ራሱ በራሱ የሚከተሉትን መፈክሮⶭ አስምቷል። * የፈሰሰው ደም የውሻ አይደለም * መከላከያ ስራህ ምንድነው * የወያኔ ጉልበት እኛ ላይ ብቻ * ና ና መንግስቱ ናና * አባረዋቸው አሳረድዋቸው […]

IS ወይም ISIS/ISIL በመባል የሚታወቀው አለም-ዓቀፍ አሸባር ቡድን አል ፉርቃን በተባለ ሚዲያ በኩል “የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን አባላት የሆኑ የመስቀሉ ተከታዮችን” በአረመኔያዊ አኳኋን የገደለበትን ቪዲዮ መልቀቁ ይታወሳል፡፡ ቪዲዮውን መሰረት በማድረግ እንደሚከተለው ለመዳሰስ ተሞክሯል፡፡ ዋና ዋና ነጥቦች፡- * ነሳራ (Christians/The people of the book) * ኢብን ቴይሚያ (Ibn Teymiyyah) * ጂዝያ (ያላመኑ ላይ የሚጣል ግብር) * የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን አባላት የሆኑ የመስቀሉ ተከታዮች (The Oriental Orthodox Church (Ethiopia & Egypt)) ይሀ ቪዲዮ የ29 ደቂቃ ርዝመት ያለው ሲሆን በጥቅሉ በነሳራ/በክርስትያኖች (The people of the book) ላይ ያተኮረ ነው፡፡ በዚህም ነሳራን በአራት ክፍሎች ያስቀምጣል፡፡ 1/Western Catholic Church (Europe & other Eastern countries). 2/ The Oriental Orthodox Church (Ethiopia & Egypt). 3/ The Eastern Orthodox Church (Russia, Greece, Many Mediterranean states). 4/ The Protestant Church (Germany, America, Scotland, Norway and Holland) ከዚህ ቪዲዮ አላማ አንፃር ሲታይ ይህ ቪዲዮ ያነጣጣረው የኢትዮጵያና ግብጽ የጋራ መለያ በሆነው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ላይ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡ ለዚህም ነው የግድያውን ምክንያት “ጠላት የሆነችው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን መስቀል ተከታዮች” በማለት የገለፀው፡፡ ከ22፡30 – 23፡40 ባሉት ደቂቃዎች ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን አባላት የሆኑ የመስቀሉ ተከታዮች ሁለት (2) መሰረታዊ መልዕክት ያላቸውን ለማስተላለፍ የሞከረው፡፡ እነኝህም፡ 1/የኢስላሚክ ኢስቴት (IS) አገዛዝ ስርዓትን እስልምናን በመቀበል እንዲቀላቀሉ ጥሪ ማቅረቡ 2/ ከባርነት ወደ ነጻነት እንዲሸጋገሩ – አንድ ግዛትና አንድ መሪን በመቀበል ከ24፡00 […]

በሳውዲ፣ የመን፣ ደቡብ ኣፍሪካና ሊብያ በኢትዮጵያውያን ላይ ችግር ባጋጠመ ጊዜ በቦታው የሌሉ ብዙ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ መንግስት በነዛ ኣገራትና ቡድኖች ላይ እንዲወስደው የሚጠብቁት እርምጃ ኣርበኛዊ እርምጃ ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ደግሞ ጥሎበት (በባህሪው) ኣርበኛዊ ዲፕሎማሲ ኣያራምድም፡፡ ቢያንስ መንግስት በኣንዳንድ ወገኖች የሚነሳበትን የ”ወኔ-ቢስነት” ክስ ለመከላከልና ለዜጎቹ እንደሚቆረቆር ለማሳየት ያክል እንኳን (ባያደርገዉም) በቴሊቪዥን ብቅ ብሎ ዘራፍና ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት ኣይሆንለትም ወይም ኣያምንበትም፡፡ ይሄ ማለት ግን መንግስት ምንም ኣይነት እርምጃ ኣይወስድም ማለት ኣይመስለኝም ፡፡ በኢትዮጵያውያን ላይ ችግርና ጥቃት በደረሰ ቁጥር እኛ ዜጎች እንደምናሳየው ኣይነት ቁጣ የመንግስት ፊት (ግንባር) ላይ ባናየዉም በጊዜው እንደየሁኔታው የተሻለ የሚለው እርምጃ ይወስዳል የሚል ግምት ኣለኝ፡፡ ይሄንን ባህሪው ተቃዋሚዎቹ የፖለቲካ ነጥብ ለማስቆጠር ኣንዳንድ ደጋፊዎቹ ደግሞ የሚደግፉትን ፓርቲ/መንግስት ባህርይ በደንብ ካለመረዳት ኣሊያም በስሜትና ሃዘኑና ጥቃቱ በሚፈጥርባቸው ተፅእኖ ምክንያት መንግስትን ይወቅሳሉ፡፡ ለነገሩስ የኛን ስሜትና ምክር እየተከተለ እርምጃ የሚወስድ መንግስት ቢሆን ኖሮ ይሄኔ ከሱዳንና ግብፅ (በኣባይ ምክንያት)፣ ከሳውዲ ኣረቢያ (በዜጎች ምክንያት)፣ ከኤርትራ (በሄሊኮፕተር ምክንያት) እንዲሁም ከሌሎች ኣገሮች ጋር ጦርነት ውስጥ እንገባ ኣልነበር ? የሰሞኑ የ ISIL ጉዳይ ግን ትንሽ ስሜትን ይፈታተናል፡፡ ድህነት ኣንገሽግሽዋቸውና የቤተሰቦቻቸውን ኑሮ ለመቀየር የሰሃራ በረሃን ኣቋርጠው የመሞትና የመትረፍ ኣጋጣሚው እኩል የሆነበትን የሜዲትራኒያን ባህር የጀልባ ጉዞ ለማድረግ የተዘጋጁትን ወጣት ወገኖች በኣደባባይ ኣንገታቸው ሲቀላና ሰረሸኑ ማየትን የሚያክል ዘግናኝ ነገር የለም፡፡ ህዝባችን በሃዘንም በቁጭትም ኣደባባይ ወጥቶ ሆ ቢል፣ እስቸኳይ የኣጸፋ እርምጃ እንዲወሰድ ቢጠይቅ ኣይገርምም፡፡ ጥያቄው […]

ምነዋ መንግሰተ ሰማይ! የምህረትሽ ቀን ራቀ? ምነው ትንግርትሽ ረቀቀ ? ምነው ኪዳንሽ ታጠፈ … ወዝሽ ወዘናሽ ነጠፈ? እንደ ዳጉሳ ድፍድፍ … ላቦትሽ ተንጠፈጠፈ አሳርሽ ጠሎ አሰፈፈ ምነው እርሾው ተማጠጠ …. ጎታው ጎተራው ታጠጠ ረሀብ ላንቃው ፈጠጠ….ያዳም ልጅ አፅሙ ገጠጠ ምነው ጭር አለ ቀየው! ሀሩር ነዲዱ በረታ ኮርማው ጥማዱ ተረታ ምነው ነበልባሉ አየለ … ማሳው ተንቀለቀለ […]

በተለያዩ የባለ ሥልጣናትና የእምነትመሪዎች መግለጫዎች ላይ በሊቢያ ምድር የተሠዉትን ሰማዕታት በኢትዮጵያዊነታቸው ወይም በስደተኛነታቸው ብቻ አደጋ እንደደረሰባቸውተድርጎ እየተነገረ ነው፡፡ እነዚህ ክቡራን ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ የተሠዉትም እምነታቸውን አንለውጥም ስላሉ ነው፡፡አይሲስ የሠዋቸው በኢትዮጵያዊነታቸው አይደለም፡፡ አይሲስኮ ዜግነት የለውም፡፡ ዐረቦች፣ አውሮፓውያን፣ አፍሪካውያን እስያውያን የተቀላቀሉትአሸባሪና አሰቃቂ ድርጅትና አስተሳሰብ ነው፡፡ እንዲያውም ባለፈው ሰሞን ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከእንግሊዝ ወደ አይሲስ ለመግባትያደረጉትን ጥረት በመገናኛ ብዙኃን […]

ወጣቱ የቪኦኤ ጋዜጠኛ ስሙን እንዲደብቅለት ከተማፀነ በኃላ እንዲህ አለ – ”….እኔ ያለሁት ትሪፖሊ ውስጥ ነው።አሁን ከግማሽ ሰዓት በፊት ፊታቸውን የተሸፈኑ ሰዎች እኔ ወደምኖርበት ግቢ ገቡ እና ወደ 40 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንን ይዘው በመኪና ሄዱ።ከተወሰዱት ውስጥ በቅርቡ ኦፕራሲዮን የሆነች እና ነፍሰ ጡር አለችበት። እነማን እንድሆኑ ማወቅ አልቻልኩም።እኔ ተደብቄ ነው ያመለጥኩት። እዚህ እስላም እና ክርስቲያን ኢትዮጵያውያንን ሊለያዩን ሞክረው […]

አሁን ከማልታ ባገኘሁት መረጃ በቀደም ከተሠዉት ወንድሞቻችን ጋር የነበረ ፣በእግዚአብሔር ቸርነት አምልጦ ትሪፖሊ የገባ ወንድም አግኝቼ ነበር፡፡
 

እርሱ እንደነገረኝ በአጅዛቢያና ቤንጋዚ መንገድ ላይ የአይሲስ አራጆች የሊቢያ መንግሥት ወታደሮችን ዩኒፎርም  ለብሰው በዚያ የሚያልፉትን ለመያዝ ይጠብቃሉ፡፡ በአካባቢው ወደ ትሪፖሊ የሚጓዙ መንገደኞችን ሲያገኙ ይይዛሉ፡፡ ሱዳኖችንና ሶማልያውያንን ሙስሊሞች ናቸው ብለው ስለሚያስቡ ወዲያው እንዲሄዱ ይለቋቸዋል፡፡ ኤርትራውያንና ኢትዮጵያውያንን ግን ለብቻ ይይዛሉ፡፡ ከዚያም ሙስሊሞችን ለብቻ ክርስቲኖችን ለብቻ ያሰልፏቸዋል፡፡ በመቀጠልም ክርስቲያኖችን በኮንቴይነር ውስጥ ከትተው ወዳልታወቀ ሥፍራ ይወስዷቸዋል፡፡ ሙስሊሞችን ደግሞ ይለቋቸዋል፡፡

በቀደም ዕለት አይሲስ በባሕር ዳርቻ የሠዋቸው ክርስቲያኖች በሰውነታቸው ላይ የመስቀል ምልክት የነበረባቸውን መርጦ ነው፡፡ እነርሱን በተለየ ኮንቴይነር አስቀምጧቸው ነበር፡፡ ይኼንን መረጃ የነገረኝ ሰው ሊገደሉ ተመርጠው ከተለዩት ወገን ነበረ፡፡ ሌሎች በኮንቴይነር ያስቀመጣቸው ክርስቲያኖችም አሉ፡፡ ምናልባት ከዚህ የከፋ ዜና እንሰማ ይሆናል፡፡ አምላክ ይጠብቀን፡፡ አሁንም የአይሲስ አራጆች የመንግሥት ወታደሮችን ልብስ ለብሰው ሌሎች ስደተኞችን እየያዙ ነው፡፡

ይኼ መረጃንውን ያደረሰኝ ሰው ሊያመልጥ የቻለው ሌሎች ክርስቲያኖችን በጨለማ ወደ ኮንቴይነሩ ለማስገባት ኮንቴይነሩን በከፈቱበት ጊዜ ነው፡፡ የተወሰኑ ተያዦች አምልጠው ነበር፡፡ አንዳንዶች ተያዙ፡፡ ሦስቱ ግን አመለጡ፡፡ ሁለቱ የት እንደደረሱ አያውቅም፤ እርሱ ግን በእግዚአብሔር ቸርነት አምልጦ ትሪፖሊ ገብቷል፡፡
እባካችሁ ባገኛችሁት አጋጣሚ ሁሉ ሰሞኑን ለመጓዝ የተነሡት ቢያንስ ለጊዜው ይታገሡ፡፡ ሱዳን ያሉትም ከሱዳን አይውጡ፡፡ መንገዱ በአይሲስ አራጆች ተይዟል፡፡ ለማታለልም የመንግሥት ወታደሮችን ልብስ ለብሰው ድንበር ጠባቂ ይመስላሉ፡፡
እግዚአብሔር በእጃቸው የተያዙትን እንዲታደግ እንጸልይ፡፡

Ethiopian martyrs in Libyaበተለያዩ የባለ ሥልጣናትና የእምነት መሪዎች መግለጫዎች ላይ በሊቢያ ምድር የተሠዉትን ሰማዕታት በኢትዮጵያዊነታቸው ወይም በስደተኛነታቸው ብቻ አደጋ እንደደረሰባቸው ተድርጎ እየተነገረ ነው፡፡ እነዚህ ክቡራን ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ የተሠዉትም እምነታቸውን አንለውጥም ስላሉ ነው፡፡ አይሲስ የሠዋቸው በኢትዮጵያዊነታቸው አይደለም፡፡ አይሲስኮ ዜግነት የለውም፡፡ ዐረቦች፣ አውሮፓውያን፣ አፍሪካውያን እስያውያን የተቀላቀሉት አሸባሪና አሰቃቂ ድርጅትና አስተሳሰብ ነው፡፡ እንዲያውም ባለፈው ሰሞን ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከእንግሊዝ ወደ አይሲስ ለመግባት ያደረጉትን ጥረት በመገናኛ ብዙኃን ሰምተን ነበር፡፡ አይሲስ አገር የለውም፡፡

እነዚህ ወንድሞቻችንማ ማተብ የሚያደርጉበትን አንገት ለእምነታቸው ሲሉ የሰጡ ቅዱሳን ሰማዕታት ናቸው፡፡ እኛ በቃል ብቻ የምንናገረውን ሰማዕትነት በ21ኛው ክፍለ ዘመን በተግባር ያሳዩ የተግባር ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ ምናልባት ባለ ሥልጣናቱና ሚዲያዎቹ ይህንን ለመናገር የከበዳቸው ሌሎች አማኞችን እናስከፋለን ብለው አስበው ይሆናል፡፡ እውነት ለመናገር ግን በግድ ሃይማኖታቸውን ወደ እስልምና (ያውም አይሲስ ወዳጣመመው የእስልምና አመለካከት) መቀየር ነበረባቸው ብሎ የሚከራከር ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ይኖራል ብዬ አላምንም፡፡ ቢኖርም አመለካከቱን እንዲፈትሽ ማድረግ እንጂ እርሱን ላለማስቀየም እውነቱን መካድ አያስፈልግም፡፡ የአይሲስን ሐሳብ ተቀብለው፣ እምነቱን አራምደው፣ ከእርሱ ጋር ተቀላቅለው ለተወሰነም ጊዜ ቢሆን እድሜ ለማራዘም ቢፈልጉ መንገዱ ነበረ፡፡ ወላዋዮች፣ ለእምነት ግድ የለሾ፣ እምነታቸው እንደ ሸሚዝ ለመቀያየር የሚፈልጉ አቋም የለሾች ቢሆኑ ኖሮ ሞት ሩቅ ነበረ፡፡ እነ ኢያሱ፣ እነ ባልቻ፣ እነ ተስፋየና እነ ዳንኤል ግን እንደዚያ አልነበሩም፡፡ በእምነታቸው ጸኑ፤ በክርስቲያንነታቸው ታረዱ፣ ሰማዕትነትንም ተቀበሉ፡፡ይኼንን እውነታ መካድ ሰማዕታቱን ሁለት ጊዜ መግደል ነው፡፡ ከሞታቸው በላይ የሞቱበትን ክቡርና ቅዱስ ዓላማ መካድ አብልጦ ይገድላቸዋል፡፡ደግሞም ስደተኛነታቸው ለአደጋው ምክንያት ሆነ እንጂ የተሠዉት በስደተኛነታቸው አይደለም፡፡ ስደተኞችም ሆነው እምነታቸውን ለመለወጥ ቢፈልጉ ኖሮ ይችሉ ነበር፡፡ የተሠዉት በክርስትናቸው ነው፡፡ ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ አንገታቸውን የሰጡት ለክርስቶስ ነው፡፡ እንደ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ አነጋገር ‹እንደ ንጹሕ መገበሪያ ስንዴ ሆነው› ለአምላካቸው ነው በመሥዋዕትነት የቀረቡት፡፡ እነርሱ አንገት የሰጡለትን ክርስትና እኛ ለመናገር ለምን ፈራነው?

(Click here for PDF)

በማለዳው አነሳሴ እንደለመድኩት በስደቱ ዙሪያ ገብ የሆነውንና እየሆነ ስላለው ልሞነጫጭር ፣ ልብተከተክ አልነበረም … ከትናንት ከትናንት በስቲያ ጠዋት ፣ረፋድና ተሲያት ፣ ምሽት ፣ በደረቁ ሌሊት እያቅበጠበጠኝ ስልኬን አንስቸ ወደ ሊቢያ ዋና ከተማ ትሪፒሊ ወደ ማትረጋው ቢንጋዚና ሚስራታ የደዋወልኳቸውን ስልኮች ተመለከትኩ ። ከወዳጆቸ የደረሱኝን ሁለት ሶስት አድራሻዎችና እዚህ ጅዳ ያለ ሊቢያዊ ጓኛየ አድራሻቸውን አፈላልጎ የሰጠኝን ሌሎች […]

በነገው እለት በመስቀል አደባባይ የሚደረገው ሰልፍ ላይ ከአንድ ሚሊዮን ህዝብ በላይ ይወጣል ተብሎ ይገመታል። ከአዲስ አበባ እና አካባቢው ያለ ህዝብ በነቂስ እንደሚወጣ የሚደርሱን መረጃዎች ይተቁማሉ። ይህንን ሰላማዊ ሰልፍ ሰማያዊ ፓርቲ እና አንድነት ፓርቲንን ጨምሮ በርካታ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ደግፈውታል። አላማው በኢትዮጵያውያን ላይ አይሲስ የፈጸመውን ግድያ ለመቃወም ነው ተብሏል። በዛሬው እለት የታፈነው የአኢትዮጵያ ህዝብ አደባባይ ወጥቶ ድምጹን […]

‹‹. . . ዓይኔ በእንባ ደከመ፣ አንጀቴም ታወከ፡፡ ስለ ወገኔ ሴት ልጅ ቅጥቃጤ አንጀቴ በምድር ላይ ተዘረገፈ፡፡ አቤቱ የሆነብንን አስብ፣ ተመልከት ስድባችንንም እይ . . .፡፡›› ሰቆ. ፪፣፲፩ ፤ ፭፣፩ ፡፡ ይህን ቃል የተናገረው በመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን ዘንድ ‹‹አልቃሻው፣ ባለ ሙሾው ነቢይ›› በመባል የሚታወቀው አይሁዳዊው ነቢዩ ኤርምያስ ነው፡፡ ይህንን ነቢይ እንዲህ እንደ ርኁሩኋ እናት አንጀቱን […]

ዛሬ ሚያዚያ 13 ቀን በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን በአዲስ አበባ ሰልፍ አድርገዋል። ህዝቡ በራሱ አነሳሽነት ነበር ሰልፍ የወጣው። የተወሰኑ ቦታዎች የወያኔ ታጣቂዎች ሰልፈኛዉን ደብድበዋል። በብዙ ቦታዎች መንገድ እየዘጉ ሰልፈኛው እንዳያልፍ ያከላከሉበትም ሁኔታ ነበር። ያው የታወቀ ነው። እነሱ የሚበረቱት ሁልጊዜ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ነው። የሕዝቡን ስሜት፣ ሐዘን እና ንዴት የተረዳው ወያኔ፣ ነገ «በበመስቀል አደባባይ ሰልፍ ይደረጋል» ብሎ […]

በጎንደር ከተማ የሚገኙ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች፣ የመንፈሳውያን ወጣቶች ማኅበራትና የማኅበረ ቅዱሳን የጎንደር ማዕከል አባላት በላኩት መግለጫ በአሸባሪውና አረመኔው አይሲስ በኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ላይ የተፈጸመውን ጭካኔ አውግዘዋል፡፡ በመግለጫው ላይ እንደተገለጠው ‹‹‹‹ISIS›› የሽብር ቡድን 30 ኢትዮጵያውያንን ክርስቲያን በመሆናቸውና ሃይማኖታችንን አንቀይርም በማለታቸው ርህራሄ በጎደለው ሁኔታ አንገታቸውን በሰይፍ በመቅላትና በጥይት በመደብደብ የፈጸመው ዘግናኝ ተግባር ኢትዮጵያዊነትን የሚፈታተን፣ ታላቅ ኀዘንን በክርስቲያኖች ላይ ፈጥሯል፡፡›› ብሏል፡፡ በማያያዝም እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነታቸው ሊደረጉ ይገባል ያሏቸውን አራት ሐሳቦች ለሀገረ ስብከቱ አቅርበዋል፡፡ የመግለጫውን ሙሉ ቃል ቀጥሎ መመልከት ይቻላል፡፡ ይህንን በመጫን መግለጫውን ያንብቡ

ክንፉ አሰፋ

Eyassu Yukunualem and Balecha Belete, ISIS massacred them in Libya. የአይሲስ ሰለባዎቹ እያሱ ይኩኑዓምላክ እና ባልቻ በለጠ

ወጣት እየሩሳሌም አስፋው እንደወትሮው ቴሌቭዥን ከፍታ እየተመለከተች ነው። ብርቱካንማ ቱታ የለበሱና፣ እጆቻቸው የፍጢኝ የታሰሩ ወጣቶች በአሸባሪዎች ታጅበው ሲጓዙ ያሳያል ቴሌቭዥኑ። ለእርድ ከተሰለፉት ወገኖች ፊት ለፊት ላይ ያለው የእየሩሳሌም ወንድም ነበር። ሌላኛው ወንድሟም ከበስተኋላ ተሰልፏል። እያሱ ይኩኑዓምላክ እና ባልቻ በለጠ፤ ሁለቱም በዚያች ቅጽበት ክቡር ነብሳቸውን በግፈኞች ተነጠቁ። ከሁሉም የከፋ የሚያደርገው ደግሞ ወዳጅ ዘመዶች የነዚህን ወገኖች አስከሬን አግኝተው ለመቅበር እድል እንኳን ባለማግኘታቸው ነው። የሁሉንም ልብ የሚሰብር ክስተት!

ሙሉውን አስነብበኝ …

Senakriem Mekonnen. ሰናክሬም መኮንንክንፉ አሰፋ

“አሜሪካ ይዞን ከሄደ በኋላ በዋሽንግተን ዲሲ አንድ የገበያ አዳራሽ (ሞል) ውስጥ ጥሎን ጠፋ … ፖሊስ ሁለት ግዜ ይዞን ነበር … በርሃብ ተቀጣን፣ ርሃብ ጸንቶበት ሆስፒታል የገባም ልጅ አለ። … በየሬስቶራንቱ እየዞርን ለምነናል።” ይላል አንድ የ11 ዓመት ሕጻን ሳይንቲስት። ሂውስተን ቴክሳስ ያሚገኘውን ናሳ የጠፈር ምርምር ተቋም ለመጎብኘት ከአዲስ አበባ ሄደው ነው አስሩ ሕጻናት ዲሲ ላይ የሚሰቃዩት።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በእኔ ዲ/ን አብርሃም ወርቁና ዲ/ን ዮሴፍ አባይ አስተባባሪነት ስድስት ብፁአን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ይዘን በሰማዕታቱ በነኢያሱንና ባልቻ መኖርያቤት ከቀኑ 10:45 ሄደን አፅናንተን ተመልሰናል ቅዱስ ፓትርያርኩን ይዘን ለመሄድ ያደረግነው ሙከራ በኘሮግራም መደራረብ ምክንያት አልተሳካም ነገር ግን ልጆች ናቸው ብለው ሰሰይንቁን ማፅናናት ኃላፊነት አለብን ብለው ጥሪአችንን አክብረው 1ኛ/ብፁዕ አብነ ሉቃስ የሲኖዶሱ ዋና ፀሐፊና የሁመራ ሀ/ስ ሊቀ ጳጳስ […]

ሚያዝያ ፲፫(አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሊቢያ በአሸባሪዎች ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ለተገደሉት ወጣቶች ኢያሱ ይኩኖአምላክና ባልቻ በለጠ ቤተሰቦች ሀዘናቸውን ለመግለጽ ከተለያዩ አቅጣጫዎች  በማምራት ላይ የነበሩ ወጣቶች ስሜታቸውን መቆጣጠር ተስኖአቸው ተቃውሞአቸውን ሲያሰሙ ውለዋል። በሺ የሚቆጠሩ ወጣቶች መንግስትን የሚያወግዙ መፈክሮችን እያሰሙ ወደ ቤተመንግስት በማቅናት ላይ እያሉ ሂልተን ሆቴል አካባቢ በብዛት የተሰባሰቡት የፌደራል ፖሊሶች አስቁመዋቸዋል። ወጣቶች …

ሚያዝያ ፲፫(አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድምጻችን ይሰማ፦”ኢ–ሰብአዊነትንና ሽብርን ደግመን እናውግዝ! ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን እንታደግ!”በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ በደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያውያን እና ሌሎችም አፍሪካውያን ዜጎች ላይ አሰቃቂ የግድያ ወንጀል እየተፈጸመባቸው እንደሚገኝ በመጥቀስ፤ ሰቅጣጩ የጭካኔ ምግባር አፍሪካዊያን ላይ በአፍሪካዊያን የሚፈፀም መሆኑ ደግሞ ይበልጥ አሳዛኝ ያደርገዋል ብሏል። ከአስርት ዓመታት በፊት ምእራባዊያን ደቡብ አፍሪካዊያን የሚያደርጉትን የፀረ-አፓርታይድ ትግልና …

አንዱዓለም ተፈራ

Revolution. መማር እንችላለን ወይ?

ከ፲፱፻፷፮ ዓመተ ምህረቱ የየካቲት ሕዝባዊ መነሳሳት ጀምሮ፤ ለመብት፣ ለነፃነትና በሰላም ሠርቶ ለመኖር ያለው ትግል፤ ሳያርፍ በተከታታይ አሁንም እየተካሄደ ነው። በነዚህ ባለፉት ፵ ዓመታት፤ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን፤ በትግሉ ከሕዝብ ጎን ተሰልፈው ሕይወታቸውን ሠጥተዋል። ቆራጥ የሕዝብ ጠበቃዎች ወጥተዋል፤ ሕይወታቸውን ላመኑበት ዓላማ በቆራጥነት በመሥጠት በጀግንነት ተቆጥረዋል። ትውልድ አልፎ ትውልድ ተተክቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ሚያዝያ ፲፫(አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ የአለማቀፍ የስደተኞች ኮምሽነር ቃል አቀባይን  ጠቅሶ እንደዘገበው ሰሞኑን በሜዲትራኒያን ባህር በሰጠመችው ጀልባ ከነበሩ ከ800 በላይ የተለያዩ አገር ዜጎች መካከል 350 ኤርትራውያን ናቸው ተብሎ እንደሚገመት ገልጾ፣ ቀሪዎቹ ደግሞ ከኢትዮጵያ፣ ሶሪያ፣ ሶማሊያ፣ ሴራሊዮን፣ ማሊ፣ ሴኔጋል፣ ጋምቢያ፣ አይቮሪኮስት እና ባንግላዲሽ የመጡ መሆናቸውን ዘግቧል። አይ ኦ ኤም የተባለው አለማቀፍ የስደተኞች …

Donald N. Levine. ፕሮፌሰር ዶናልድ ሌቪን ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ነጻነት ለሀገሬ)

ፕሮፌሰር ዶናልድ ሌቪን፡ የልሂቃን ሁሉ ልሂቅ

ፕሮፌሰር ዶናልድ ሌቪን በዚህ ባሳለፍው ጥር ወር ኢትዮጵያን ለመጎብኘት የነበራቸው የረዥም ጊዜ ዕቅድ በህመማቸው ምክንያት የተጨናገፈ መሆኑን በኢሜይል መልዕክት ልከውልኝ ነበር። በዚያ አስበውት በነበረው ጉብኝት የሚከተሉትን ሶስት ዓላማዎች የማሳካት ዕቅድ ነበራቸው። እነርሱም፣

ሙሉውን አስነብበኝ …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

በነገው የአ/አበባ ነዋሪዎች የመስቀል ዐደባባይ ሰልፍ ቤተ ክርስቲያን መልእክቷን ታስላልፋለች ራሱን አይ ኤስ እያለ የሚጠራው አሸባሪ ቡድን፣ በንጹሐን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች ላይ በፈጸመው ግፍ ለገደላቸው ወገኖቻችን በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጸሎተ ፍትሐት እና ጸሎተ ወንጌል ለማድረግ ለነገ ከጠዋቱ 2፡30 – 4፡30 የወጣው መርሐ ግብር ለኀሙስ ጠዋት፣ ሚያዝያ 15 ቀን 2007 ዓ.ም. […]

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሊቢያና ደቡብ አፍሪቃ ዉስጥ ሰሞኑን በግፍ የተገደሉ ኢትዮጵያዉያንን ለማሰብ የሠወስት ቀን ብሕራዊ ሐዘን አወጀ።ምክር ቤቱ ዛሬ ባደረገዉ ሥብሰባዉ በሁለቱም ሥፍራዎች የተፈፀሙትን ግድያዎች አጥብቆ አዉግዟል።

ራሱን እስላማዊ መንግስት «አይ ሲስ» ብሎ በሚጠራው አክራሪ ቡድን ሊቢያ ላይ ከተገደሉት ኢትዮጵያውያን መካከል የእያሱ ይኩኖአምላክ እና ባልቻ በለጠ ቤተሰቦች አዲስ አበባ በተለምዶ ቂርቆስ በሚባለው ሰፈር ድንኳን ጥለው ሃዘን ላይ ናቸው።