ማንም ኢትዮጵያዊ ሰልፉን እንዳይቀር – ግርማ ካሳ

ዛሬ ሚያዚያ 13 ቀን በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን በአዲስ አበባ ሰልፍ አድርገዋል። ህዝቡ በራሱ አነሳሽነት ነበር ሰልፍ የወጣው። የተወሰኑ ቦታዎች የወያኔ ታጣቂዎች ሰልፈኛዉን ደብድበዋል። በብዙ ቦታዎች መንገድ እየዘጉ ሰልፈኛው እንዳያልፍ ያከላከሉበትም ሁኔታ ነበር። ያው የታወቀ ነው። እነሱ የሚበረቱት ሁልጊዜ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ነው።

የሕዝቡን ስሜት፣ ሐዘን እና ንዴት የተረዳው ወያኔ፣ ነገ «በበመስቀል አደባባይ ሰልፍ ይደረጋል» ብሎ ጥሪ አቅርቧል። ወያኔ ሕዝቡ ስሜቱን እንዲገልጽ መተባበሩን በአዎንታዊነት ወስጄዋለሁ። ወያኔም ባይጠራም ኖሮ ዛሬ እንደተደረገው፣ ህዝቡ መውጣቱ አይቀሬ ነበር።

ይሄንን አጋጣሚ በመጠቀም፣ የሰማያዊ ፓርቲ ሰልፉን እንደሚቀላቀል የገለጸ ሲሆን፣ ሕጋዊነቱን በወያኔ የተጠነጠቀው፣ ግን መዋቅሩን ጠብቆ ያለው የአንድነት አባላትና ደጋፊዎችም ሰልፉን ይቀላቀላሉ ተብሎ ይጠበቃል። በአስሩም ክፍለ ከተማ፣ እንዲሁም እንደ ናዝሬት/አዳማ፣ ደብረ ብርሃን፣ አምቦ ባሉ የአዲስ አበባ አካባቢ ከተሞች የምንኖርም ኢትዮጵያዉያን የነገዉን ሰልፍ በመቀላቀል ድምጻችንን እናሰማ። ይሄ የፖለቲካ ጉዳይ አይደለም። ይሄ የአገር ጉዳይ ነው።

በዚህ በደቡብ አፍሪካ፣ በሊቢያን በየመን ለሞቱት ወገኖቻችን ጥቁር በመልበስ ሃዘናችንን እንገልጻለን። ጥቂቶችን ሚሊየነሮች እያደረገ ብዙሃኑን ያደኸየው፣ ብዙዎች አገራቸውን ጥለው እንዲሰደድ ያደረገዉን ስርዓትን እንቃወማለን። አገዛዙ ሽብርተኞች እያለ ሰላማዊ ዜጎችን ማሰሩን አቁሞ፣ ያሰራቸውን በአስቸኳይ ፈትቶ፣ እንደ አይሰስ እና አልሻባብ ያሉ ሽብርተኖች መዋጋት እንዲጀመር እንጠይቃለን። ከሁሉም በላይ ደግሞ በሊቢያና በየመን እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ ችግር ላይ ያሉ ወገኖቻችን ለማዳን የወያኔ መንግስት አስቸኳይና ግልጽነት ያለው ርብርብ እንዲያደረግ እንጠይቃለን።

ረእቡ ሚያዚያ 14 ቀን።
ሐሙስ ሚያዚያ 15 ቀን ትምህርት፣ ሥራ፣ ንግድና ትራንስፖርት አይኖርም። የሐዘን እና የተቃዋሞው ቀኑን በጸሎት እናሳልፋለን።10408890_10206295278891618_5792838664246267972_n