እውነት ከመንበርህ የለህማ!
ምነዋ መንግሰተ ሰማይ! የምህረትሽ ቀን ራቀ? ምነው ትንግርትሽ ረቀቀ ? ምነው ኪዳንሽ ታጠፈ … ወዝሽ ወዘናሽ ነጠፈ? እንደ ዳጉሳ ድፍድፍ … ላቦትሽ ተንጠፈጠፈ አሳርሽ ጠሎ አሰፈፈ ምነው እርሾው ተማጠጠ …. ጎታው ጎተራው ታጠጠ ረሀብ ላንቃው ፈጠጠ….ያዳም ልጅ አፅሙ ገጠጠ ምነው ጭር አለ ቀየው! ሀሩር ነዲዱ በረታ ኮርማው ጥማዱ ተረታ ምነው ነበልባሉ አየለ … ማሳው ተንቀለቀለ […]![]()