እመቤት ግርማ ( 18 አመት ወጣት)፣ ንግስት ወንዳፍራዉ፣ መታሰቢያ ስዩም፣ ወይንሸት ንጉሴ፣ ምኞት መኮንን በሩጫ ወቅት ሁከት ፈጥራችሁላ ተብለው ከታሰሩ «የጣይቱ ልጆች» መካከል የሚገኙ ናቸው። የካቲት 30 2006 ዓ.ም እሑድ ቀን ነው። በተዘጋጀው የሴቶች የ500 ሩጫ በርካታዎች ይሮጣሉ። ቢጫ ኬኔቴራ ለብሰዋል። ሩጫዉ እንደተጀመረ ድምጾች መሰማት ጀመሩ። የስድብ፣ የክፉ አይደለም። «የጣይቱ ልጆችን ነን፤ የሚኒሊክ ልጆች ነን፣ […]

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

አምባሳደሯ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ከአቶ ሐይለማርያም ደሳለኝና ከተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለይም ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ያደረጉት ዉይይት የኢትዮጵያን የፓለቲካ የሠብአዊ መብትና የዴሞክራሲ ይዞታን፤ የእስረኞች ሁኔታን የሚመለከት እንደነበር የተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች ዘግበዋል

የእሥልምና ሥነ-ፅሁፍ ምሥራቅ አፍሪቃ ዉስጥ በሚነገሩ በተለያ ቋንቋዎች ለረጅም ጊዜ የተለያዩ አገልግሎቶች ሲስጥ እንደነበር አጥኚቹ ተናግረዋል።በተለይ ሐረር ከተማ የገኙ መዛግብትና መፃሐፍት የምሥራቅ አፍሪቃዉ ጥንታዊዉ የሙስሊሞች ሥልጣኔ ከዝነኛዋ የቲምቡክቱ (ማሊ) ሥልጣኔ ጋር ታሪካዊ ትስስር እንዳለዉ ተመራማሪዎቹ አስታዉቀዋል

ለሰወስት ወር በሚቆየዉ ጉባኤ ከአምስት መቶ የሚበልጡ የመንግሥት፤ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፤ የሐይማኖት ተቋማት፤ የኩባንያና የንግድ ድርጅት ተጠሪዎች፤የሰራትኞች፤ የሙያና የፆታ ማሕበራት ተወካዮች፤ የሥነ-ጥበብ ባለሙያዎችና ታዋቂ ግለሰቦች ተካፍለዋል

ኢትዮጵያ ዉስጥ በየአካባቢዉ እንደሚነገረዉ ቋንቋ የየግል መጠሪያ ቢኖረዉም በአብዛኛዉ ግን ሬት በሚለዉ ስሙ ይታወቃል። ብዙዎችም ዛሬም ቢሆን ለጡት አስጣይነት ይጠቀሙበታል። ለመብቀል ብዙ ክብካቤና ዉሃ አይፈልግም፤ በዉስጡ ግን በርከት ያለ ዉሃ የማጠራቀም ባህሪ አለዉ።

አቡነ ጳውሎስን ሲያሳስቱና ሲያጋጩ የነበሩ ጎሰኛ እና አማሳኝ ግለሰቦች አኹን ምናልባት ከዚያ ቦታ ሳይነሡ እርስዎንም ወደዚያ የጥፋት ሣጥን አስገብትዎት መውጫ አሳጥዎት ከኾነ እባክዎ ወደ ልቡናዎ ተመልሰው ቃል የገቡባቸውን የለውጥ ተስፋዎች ለመተግበር ይነቃቁ፡፡ የመንግሥት ፖሊቲካዊ ጫና ሳያስፈራዎ፣ መንፈሳዊ የለውጥ አባትነትዎን በተግባር ያሳዩን፡፡ የለውጥ ሥራዎ አብቦና ፍሬ አፍርቶ ለማየትና ለመጠቀም ጉጉት አለን፡፡ (ሪፖርተር፤ ይድረስ ለሪፖርተር፤ ቅጽ 19 …

በተለምዶ ሲኤም ሲ በሚባለው ሰፈር፣ በቦሌ ክፍለ ከተማ ሥር ካለው ክልል ወደ የካ ከተማ ክልል ለባቡር የተሠራውን መንገድ እንደ ጦጣ እየዘለልኩ በማቋረጥ ላይ ነበርኩ፡፡ ከእኔ ፊት ፊት ሁለት ሽማግሌዎች በምርኩዛቸው እየተረዱ እንደ ሽሪ ሚሪ የተከረተፈውን የባቡር መንገድ በጥንቃቄ ይሻገራሉ፡፡ ሽሪ ሚሪውን ተሻግረው የተነጠፈው ሐዲድ ላይ ሲደርሱ ልባቸው መለስ አለላቸው መሰል የአኩስም ጋቢ የመሰለ ፀጉር የለበሱት አንደኛው ሽማግሌ ‹‹እንዴው በቃ ይህንን ባቡር የሐበሻ መድኃኒት አደረጉት ማለት ነው?›› ብለው ጓደኛቸውን ጠየቁ፡፡

‹‹እንዴት እንዴት በል?›› አሉ ሪዛቸው እንደ ዝቋላ ጥድ ወደታች የወረደላቸው ሌላው አረጋዊ፣ በከዘራቸው የባቡሩን ሐዲድ ነካ ነካ እያደረጉ፡፡

‹‹ቆይ ይኼ ባቡር ምንድን ነው የሚመስለው? ባቡሩ ሲያልቅስ ይኼ መንደራችን ምን ይመስላል? መሳፈሪያው እንዴት ነው?በዚህ በመገናኛስ በዋሻ ያልፋል የሚባለው እንዴት እንዴት ሆኖ ነው? እንዴት የሁላችንን ሕይወት ዋጋ ያስከፈለ፤ ስንት ቤቶችን ያስነሣ፣ ስንት ሠራተኞችን ያስረፈደ፣ ስንት ሚሊዮን ብር የፈጀ፣ ለሀገራችንም እንግዳ የሆነ ነገር ሲሠራ፣ እንዴት አንድ ቦታ እንኳን ሥዕሉ አይለጠፍም? ቆይ ይህንን ሁሉ መሥዋዕትነት ከፍለን፣ ጠዋት አርፍደን፣ ማታ ተሠልፈን፣ የሃያ ሁለትና የዑራኤል ሆቴሎች ቀዝቅዘው፣ እኛም መሻገሪያ አጥተን በስተርጅና እንደ ጉሬዛ እየዘለልን የሚሠራው ባቡር ምንድን ነው የሚመስለው? ለመሆኑ ታውቃለህ?››

‹‹ይኼው የሀብታሙ ሁሉ ሕንጻ ሲሠራ ከፊት ለፊቱ ሥዕሉ በትልቁ ይሰቀል የለም እንዴ? እኛም ዐቅምና ዕድል ኖሮን ባንሠራም ቆመን ሥዕሉን አይተን እናደንቃለን፡፡ ሕንጻው ሲያልቅ ሠፈሩ ምን እንደሚመስልም እንገምታለን፤ እንደ ሽምግልናችንም ‹አልቆ ለማየት ያብቃን› ብለን እንመርቃለን፡፡ የከተማው ባቡርማ ለምርቃትም ለጸሎትም አስቸጋሪ ሆነኮ፡፡ እኛ የከተማ ባቡር አይተን አናውቅ፣ ምናለ በየሠፈሩ ሥዕሉን ቢለጥፉልን፤ ብናደንቅ፣ ሠሪዎችንም ብንመርቅ፣ እንዲያስፈጽመውም ብንጸልይ፡፡››

ሽማግሌዎቹ የባቡሩን መንገድ አቋርጠው ወደ ሲ ኤም ሲ ሚካኤል አቅጣጫ ተጓዙ፡፡ መንገዴን ትቼ ወጋቸውን ሽቼ ተከተልኳቸው፡፡
‹‹አይህ ወዳጄ እነዚህ የሃይማኖት ሰዎች ‹መንግሥተ ሰማያት ይህንን ትመስላለች› የሚሉትኮ ያለምክንያት እንዳይመስልህ፡፡ የሚደርስብህን ሁሉ መከራ የምትቋቋመው የምታገኘውን አስረግጠህ ካወቅከው ብቻ ነው ብለው ነው፡፡ መንግሥተ ሰማያትን ይስሉብህና ‹ለዚህች ልዩ ሀገር ስትል ዋጋ ክፈል፣ መከራውን በጸጋ ተቀበል፤ እስከ ጊዜው ነው ቻለው› ይሉሃል፡፡ ምነው እነዚህ ባቡር የሚሠሩ ሰዎች ከእነርሱ ቢማሩ፡፡ ለመሆኑ ይኼ ሁሉ ጉድጓድ ተቆፍሮ፣ መንገድ ተከልክሎ፣ ሠፈር ፈርሶ፣ ሐውልት ተነቅሎ፣ ማቋረጫ ጠፍቶ፣ መንገድ ተዘጋግቶ፣ ንግዱ ተቀዛቅዞ የምናገኘው ነገር ምንድን ነው? ምን ይመስላል? አሁን እኛ መሥዋዕትነት እየተቀበልን ያለነው ምን ለማግኘት ነው? ማንም አያውቅም፡፡ ምነው ግን ይህንን ባቡር የሐበሻ መድኃኒት አደረጉትሳ››

‹‹እኔም ሁልጊዜ የሚገርመኝ እርሱ ነው፡፡ መገናኛ ሄድኩ፣ ዑራኤል ሄድኩ፣ መስቀል አደባባይ ሄድኩ፣ ሜክሲኮ ሄድኩ፣ በቀደምም መርካቶ ሄድኩ፤ ሕዝቡ የመሰለውን ብቻ ነው የሚያወራው፡፡ አንዱ ኤሌክትሪኩ ከላይ ነው ይላል፣ ሌላው መሬት ውስጥ ተቀብሯል ይላል፤ አንዱ ማውረጃው ከላይ ነው ይላል፣ ሌላው መሬት ውስጥ ነው ይላል፤ አንዱ የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት አይመለስም፣ ቦታ የለውም ይላል፤ ሌላው ይመለሳል፣ ግን ከድሮው ሬዲዮ ጣቢያ አጠገብ ይተከላል ይላል፡፡ ይህንን ሁሉ ምን አመጣው? አንተ እንዳልከው የሐበሻ መድኃኒት ይመስል ምሥጢር ስላደረጉት ነው፡፡ እንጂማ ሲሆን እኛ ሽግሌዎቹም እንድናይ ከፍ ከፍ አድርገው፣ ካልሆነም ባቅም ባቅሙ ሥዕሉን መለጠፍ ነበረባቸው፡፡››

አሁን ሽማግሌዎቹ ወደ ሲኤም ሲ ሚካኤል እየገቡ ነው፡፡ ባርኔጣቸውን ሊያወልቁና እጅ ሊነሡ በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡

‹‹በቀደም አያ ተሰማ ምን አለኝ መሰለህ››

‹‹ምን አለህ ደግሞ፤ መቼም እርሱ ወግ አያልቅበትም፡፡››

‹‹የካና ቦሌ አሁን ነው ትክክለኛ ድንበር ያገኙት፡፡ ይኼው የባቡሩ መንገድ የማያገናኝ ድንበር አበጅቶላቸዋል፡፡ ካሁን በኋላ የምንገናኘው በሞባይል ብቻ ነው፡፡ ከመንገድ ማዶና ማዶ ሆነህ በስልክ እያወራህ በእጅ ሰላምታ መለዋወጥ ብቻ ነው›› አለኝ፡፡

‹‹እንዴ መሻገሪያ አያደርጉልንም እንዴ? እኛ ወዲያ ተሻግረን ሚካኤልን ላንሳለም፣ ሙስሊሞችም ወዲህ መጥተው ላይሰግዱ ነው ማለት ነው? ይህማ ደግ አይደለም››

‹‹ቢለጥፉትኮ ይኼ ጥያቄ ይመለስልን ነበር፡፡ ግን የሐበሻ መድኃኒት ነው፡፡ ያውም የወፍ መድኃኒት፡፡ ፌርማታው የት ጋ ነው? መንገዱንስ እንዴት አቋርጠን ነው የምንሳፈረው? ሰው ዘሎ ቢገባስ? እንዴው ተጨነቁ ብሎን የሚመስለንን ስንገምት እንውላለን፡፡ ቤት ስትሠራ እንኳን መሐንዲሱ የቤቱን መልክ በወረቀት ስሎ ይሰጥሃል፤ አንተም አይተህ ደስ ሲልህ ይህንንስ ወገቤን አሥሬ እሠራዋለሁ ትላለህ፤ ሰው ዛሬ ወደፊት የሚቀበርበትን ቦታ እንኳን ለማወቅ ፈልጎ በቁሙ መቃብር ያሠራል፤ ልብስ ሰፊ እንኳን ዋናው ልብስ እስኪደርስ በቾክ ጨርቁ ላይ ስሎየልብሱን መልክ ያሳይሃል፤ ደጋሽም ድግሱ እስኪደርስ ቅምሻ ብሎ ይጠራሃል፤ የሞሰቡን እንጀራም በእንጎቻው ትገምተዋለህ፤ ባቡሩን ግን እንዴት እንገምተው? ለመሆኑ ምን መልክ ይኖረዋል? እንዴት ነው የምንሳፈረው? ወጭውስ በኛ ዐቅም ይቻላል? እንደ ሰርዲን ታጭቀን ነው ወይስ ወንበር አለው? ለመሆኑ እንደ አውቶቡስ ቁጥር አለው? ሲሆን አንድ ቦታ ላይ ሠርተው እንደ ኤግዚቢሽን ቢያሳዩን፤ ‹አሃ ለካ እንደዚህ ነው› ብንል አእምሯችን ለምዶት ቢቆይ መልካም ነበር፡፡ ካልሆነም ሥዕሉን በየሠፈራችን ቢያኖሩት››

‹‹በቀደም ታናሿ ልጄ የምወልደውኮ ሴት ልጅ ነው አለችኝ››

‹‹ያቺ ነፍሰ ጡሯ››

‹‹አዎ፤ በምን ዐወቅሽው፣ የዛሬ ልጆች መጠንቆል ጀመራችሁ ወይ አልኳት››

‹‹ሐኪሙ አሳየኝ – አለችኝ››

‹‹ሆድሽን ከፍቶ አሳየሽ – ብዬ ቀለድኩባት››

‹‹አይደለም በመሣሪያ ማየት ይቻላልኮ – አለችኝ፡፡ ዛሬ ያልተወለደን ልጅ ወንድ ይሁን ሴት ማወቅ እየተቻለ እንዴት ነው እንዲህ ሠፈሩን ሁሉ አቋርጦ የሚሄደውን ባቡር መልክ ቀድሞ ማየት ያልተቻለው፡፡ ሲቆፍሩ፣ ሲገነቡ፣ ሲሚንቶ ሲሞሉ፣ አቧራ ሲያቦኑ ብቻ ነው የምናያቸው፤ የሐበሻ መድኃኒት አደረጉት አልክ፣ እውነትክን ነው፡፡››

አረጋውያኑ ወደ ሚካኤል ግቢ ዘልቀው ተሳለሙና አጥሩ ጥግ ዛፎቹ ሥር ዐረፍ አሉ፡፡

‹‹እኔ ግን ምን እንደሚመስለኝ ታውቃለህ?›› አሉ ሽበት ያጀባቸው ሽማግሌ

‹‹ምን ይመስልሃል?›› አሏቸው ሪዛሙ አረጋዊ

‹‹እኛ ብቻ ሳንሆን እነርሱም አሟልተው ያወቁት አይመስለኝም››

‹‹መጠርጠር እርሱን ነው›› አሉና መዳፋቸውን በመዳፋቸው መቱት፡፡

© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

… በማስመሰል ታጥሮ መሆን በጠፋበት
ምን አገባኝ የሚል በተከማቸበት
የባይተዋር መንፈስ ከሞላ ባገሩ
ዘመኑን ማወቂያ ይሄ ነው ሚስጥሩ
ይሄን ጊዜ ጠርጥር እንደጠፋ ዘሩ።
(ገጣሚ ደምሰው መርሻ/ያልታተመ)
አዎን፣ ገጣሚ ደምሰው እንዳለው እኔም በዚህ ዘመን “ዘሩ እንደጠፋ” አሊያም ሊጠፋ እንደተቃረበ እጠረጥራለሁ፡፡ ስለምን? ቢሉ …በኢትዮጵያችን ለህሊናው፣ ለሕዝብና ለሀገሩ የሚቆረቆር፣ የእውነት ተሟጋችና የሞራል ልዕልናን የተቀዳጀ ሙሉ ሰው ፈልጎ ማግኘት እጅግ አተካች ሆኗልና።

ሙሉውን አስነብበኝ …

የአንድት ፓርቲ የአዲስ አበባ ዞን ስራ አስፈፃሚ የተቃውሞ ሰልፍ ሊጠራ ነው እንደሆነ የፍኖት ጋዜጣ ዘገበ። «በአዲስ አበባ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣውን የውሃ፣የመብራትና የቴሌኮም አገልግሎት ጥራት መጓደልና የአገልግሎት መቋረጥ መንግስት በአፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥ ለመጠየቅ፣ የከተማዋን ነዋሪዎች በማነቃነቅ ደማቅ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ የአንድት ፓርቲ የአዲስ አበባ ዞን ስራ አስፈፃሚ መወሰኑን የዞኑ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ለፍኖተ ነፃነት […]

ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም

ወያኔ/ኢሕአዴግ ጥሩምባ ነፍቶ የብሔሮች፣ የብሔረሰቦችና የሕዝቦች ነጻነት ብሎ ከአወጀና ሁሉንም ለሃያ ሁለት ዓመታት በተስፋ ከአስፈነደቀ በኋላ ችግር ተፈጠረበት፤ ችግሩ ምንድን ነው? ችግሩ የቆጡንአወርድብላየብብቷንጣለች የሚባለው ነው፤ ችግሩ አፍ ከሚችለው በላይ ለመጉረስ ከራስ ጋር መተናነቅ ሆነ፤ ችግሩ የማሰብ ድርቀት ነው፤ ችግሩ ከአሜሪካና ከአውሮፓ መንግሥታት ጀምሮ እስከቀበሌ መዋቅር ያሉትን ሁሉ በአንድ ዘዴ እያባበሉና እያታለሉ ማደናበር ነው፤ ችግሩ በሃያ ሁለት ዓመታት ውስጥ ዘዴው ሻግቶ ዓላማው ደብዛው መጥፋቱ ነው፤ ቸግሩ የዘዴው መሻገትና የዓላማው መክሸፍ መጋለጡ ነው፤ ችግሩ ወያኔ የተቀመጠበት የሥልጣን ወንበር መቆርቆር መጀመሩ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ዘወትር ቅዳሜ ማታ ከደሳለኝ መኮንን ጋር፣ምርጥና አዳዲስ የካንትሪ ማለትም የአሜሪካ አገር ሰብእ፣ የሮክ፣ተሶል፣የፖፕ፣የአር-ኤን-ቢ፣ብሉዝ፣የሬጌና የሂፕ-ሃፕ ዜማዎችን እንዲያደምጡ ተጋብዘዋል።

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ጊዚያዊ ጥቅላይ ሚንስትሩ እንዳሉት የሩሲያ ጦር በሳቸዉ አገላለጥ ለክሪሚያ «ገንጣይና ከፋፋዮች» ከለላ መስጠቱ እዉነት ነዉ።የዚያኑ ያክል ያዜንዩክና ጓዶቻቸዉ በዩናይትድ ስቴስና በተባባሪዎችዋ እቅፍ ዉስጥ መሆናቸዉም ሐቅ።

ከዓለም የጦር መሣሪያ በመግዛት ብዛት ቻይና ፣ህንድ እና ፓኪስታን የመጀመሪያውን ስፍራ ይዘዋል ይላል የዓለም አቀፍ የጦር መሣሪያ ንግድን የሚመረምረው «የሰላም ጥናት ተቋም» በምህፃሩ «ሲፕሪ» ዛሬ ያወጣው ዘገባው።

በአንድነት እና መኢአድ የዉህደት እንቅስቃሴ ላይ አስተያይተ የሰጡት የፓርላማ እና የአንድነት ብሄራዊ ምክር ቤት አባል አቶ ግርማ ሰይፉ ምክር ቤቶቹ ይሄን ታሪካዊ ዉሳኔ ባሳለፉበት ወቅት የሚከተለውን ብለዋል፡ «ዛሬ በመኢህአድ ፅ/ቤት የመኢህአድ እና የአንድነት ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባላት የጋራ ስብሰባ አድርገው አንድ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሰዋል፡፡ ይህውም ለቀጣይ ሐሙስ መጋቢት 11/2004 ዓ/ም የቅድመ ውህደት ሰምምነት […]

በደቡብ ክልል፣ በጋሙ ጎፋ ዞን የምትገኝ ወረዳ ናት። ወደ 150 ሺህ የሚጠጋ ነዋሪ አላት። በዚያ ያሉ ገበሬዎች ከሚያርሱበት ቦታ በግድ እንዲፈናቀሉ ከመደረጉ በተጨማሪ፣ ብዙዎች ያታሰሩባት ወረዳ ናት። የቁጭ ወረዳ ትባላለች። በአንድነት ፓርቲ አነሳሽነት ለሕዝብ የፋ የሆነው የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት ትኩረት ከሰጠባቸው ወደ አሥራ የሚሆኑ አካባቢዎች አንዷ ቁጫ ናት። በቁጫ ሊደረግ የታሰበዉን ትእይነተ ሕዝብ በመደገፍ፣ […]

በምርጫ ዘጠና ሰባት ወቅት ጠንካራ ፓርቲ ይባሉ የነበሩት መኢአድ እና ኤዴፓ ነበር። ሁለቱን ፓርቲዎች የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት እና የመኢአድ ላዕላይ ምክር አባላት ቤት መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም አባላት በጋር ባካሔዱት ስብሰባ፣ ሁለቱ ፓርቲዎች የፊታችን ሐሙስ መጋቢት 11 ቀን 2006 ዓ.ም የቅድመ ውህደት ፊርማ እንዲያደርጉ መመሪያ ማስተላለፋቸውን ፍኖት ነጻነት ዘገበ። በምርጫ ዘጠና ሰባት ከመደረጉ […]

የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤትእና የመኢአድ ላዕላይ ምክር ቤት አባላት በጋር ባካሔዱት ስብሰባ ሁለቱ ፓርቲዎች የፊታችን ሐሙስ መጋቢት 11 ቀን 2006 ዓ.ም የቅድመ ውህደት ፊርማ እንዲያደርጉ መመሪያ ማስተላለፋቸውን ስብሰባውን የተከታተለው የፍኖተ ነፃነት ባልደረባ ዘገበ፡፡ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባላት እና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ላዕላይ ምክር ቤት አባላት ዛሬ መጋቢት 7 ቀን 2006 […]

የሰማያዊ ፓርቲ መንግስት ከህዝብ ጀርባ የሚያካሂደውን የኢትዮጵያ – ሱዳን ድንበር ማካለልን በመቃወም በጎንደር ከተማ የጠራውን ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ አጠናቋል በእለቱም የፓርቲው አስተባባሪ ለህብረተሰቡ በዚህ አስቸጋሪ ወቅትና አምባገንን ስርዓት ውስጥ ሆናችሁ የሀገራችን ጉዳይ ያገባናል ብላችሁ ስለመጣችሁ እናመሰግናለን በሚል ንግግር ፕሮግራሙን ከፍተው የሰልፉን አላማ አብራርተው የፓርቲውን ሊቀመንበር ወደ መድረክ ጋብዘዋል፡፡ የፓርቲው ሊቀመንበርም ለተሰላፊዎቹ ባስተላላፉት መልእክት ለወጣቶች የሀገራቸውን ክብር እንዲያስጠብቁ እራሳቸውንም ከፍርሀት እና ከስጋት በማላቀቅ ለራሳቸውም ለሀገራቸውም አለኝታ እንዲሆኑ፤ እንዲሁም ስርዓቱ ላይ ያሉት አስተዳደሮች ስልጣን ወቅታዊ መሆኑን አውቀው በኢትዮጵያ ድንበር ላይ እየተፈጸመ ያለውን ደባ እንዲያስቆሙ ከታሪክ ተጠያቂነት እንዲድኑ፤ ለልጆቻቸውም ውርደትን ሳይሆን ክብርን እንዲያወርሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ፓርቲውም የጠራውን ሰልፍ እና ማስተላለፍ የፈለገውን መልእክት በተሳካ ሁኔታ አስተላልፎ ፕሮግራሙን አጠናቋል፡፡ ፓርቲውም በአካባቢው የሚገኙ የፓርቲው አስተባባሪዎችን እንዲሁ የጎንደር እና የአካባቢው ህዝብን ለዚህ ሰልፍ መሳካት ላደረጉት አስተዋጽኦ ከፍ ያለ ምስጋና አቅርቧል፡፡

ዘወትር ቅዳሜ ማታ ከደሳለኝ መኮንን ጋር፣ምርጥና አዳዲስ የካንትሪ ማለትም የአሜሪካ አገር ሰብእ፣ የሮክ፣ተሶል፣የፖፕ፣የአር-ኤን-ቢ፣ብሉዝ፣የሬጌና የሂፕ-ሃፕ ዜማዎችን እንዲያደምጡ ተጋብዘዋል።

የምዕራብ ሀገራት ያወገዙት በዩክሬን ክሪምያ ልሳነ ምድር ህዝበ ውሳኔ ተጠናቀቀ። ለሞስኮ መንግስት የሚያደላዉ የክርምያ አስተዳደር ባለስልጣናት የህዝበ ዉሳኔዉ ዉጤት ከሩስያ ጋር ለመቀላቀል ማረጋገጫ የሰጠ መሆኑን በመግለፅ ላይ ይገኛሉ። ከክሪሚያ አስተዳደር በወጣዉ መግለጫ መሰረት 93 በመቶ መራጭ፤

የምዕራብ ሀገራት ያወገዙት ህዝበ ውሳኔ በዩክሬንክሪምያልሳነምድርተጠናቀቀ። ለሞስኮ መንግስት የሚያደላዉ የክርምያ አስተዳደር ባለስልጣናት ከሩስያ ህዝበ ዉሳኔዉ ዉጤት ከሩስያ ጋር ለመቀላቀል ማረጋገጫ የሰጠ መሆኑን በመግለፅ 93 በመቶ መራጭ የክሪምያ ልሳነ ምድር ከዩክሪይን እንዲገነጠል መወሰኑን እየገለፀ ነዉ።

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ፀረ ሰላም ሃይሎች
የፀረ ዲሞክራሲ ሃይሎች
የፀረ ልማት ሃይሎች
ኣሸባሪዎች
ነውጠኞች
ነጭ ለባሾች
የደርግ ርዝራዦች
ያለፉት ስርዓት ቅሪቶች
የኣፄው ስርዓት ናፋቂዎች
ኣደገኛ ቦዘኔዎች
ኪራይ ሰብሳቢዎች
የግል ጥቅም ኣሳዳጆች
ጥገኞች
ትምክህተኞች
ነፍጠኞች
የስልጣን ጥመኞች
ተስፈኞች
ጠባቦች
እንክርዳዶች/ጉርዶች
መሃል ሰፋሪዎች
ኣድሃሪያን
የቀለም ኣብዮተኞች
የሻዕቢያ ቅጥረኞች/ ጋሻጃግሬዎች
ኣክራሪ ቡድኖች
የሰለፊ/ወሀቢ እምነት ኣራማጆች
ፅንፈኞች
ቆ… ሻሻ (እደግመዋለሁ ቆ… ሻሻ!)
የበከተ/የገማ/የበሰበሰ ኣስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች
ዝቃጮች
ሁከተኞች
ፀብ ኣጫሪዎች
ተቸካዮች
ተንበርካኪዎች
ጥራዝ ነጠቆች
ስግብግብ ነጋዴዎች
ተለጣፊዎች/ተነጣፊዎች
የኢንተርሃምዌ ኣራማጆች
ሗላቀር ኣስተሳሰብ የተጠናወታቸው ሃይሎች
ህገ መንግስቱን በጉልበት ለመናድ የሚዶልቱ ሃይሎች
ኣንዳንድ ኣርቆ ማሰብ የተሳናቸው ዜጎች (ዘገምተኞች )




(ደከመኝ በነጠብጣብ ልለፈው )
*****

የቀረ የለም። ምሁር ነሽ፡ ፖለቲካ ኣያገባኝም የምትይ መሃል ሰፋሪ ነሽ፤ የእምነት ሰው ነሽ፡ ነጋዴ ነሽ፡ ምንድነሽ ሁልሽም ቅጥያ ኣለሽ!

የልማት ሰራዊቱ ከሁሉም ጋር ስለማይስማማ (ከራሱም ጭምር) ለሁሉም ቅጥያ ኣዘጋጅቷል፤ ባንዳች የስድብ ምትሃታዊ ሃይል ነው ስርዓቱ የቆመው ማለት ሳይሻል ኣይቀርም።

የሰውን ፣ ሰብአዊ መብት ለማክበር ፣ በኤኮኖሚ፤ በልማት መደርጀት ቅድመ ግዴታ አይሆንም። የትምህርት መሥፋፋት፣ እርግጥ እገዛ ሊያደርግ ይችላል። ሙሉ ወሳኝነት አለው ተብሎ ግን አይታሰብም።

Image
ምንሊክ ሳልሳዊ :- ህገመንግስታዊ ጥያቄ ባነሱ ከጄኔራልነት እስከ ሻምበልነት ማእረግ ባላቸው የቀድሞው የኢሕዴን ታጋዮች እና የአሁን የብኣዴን የጦር መኮንኖች እና በሕወሃት ጄኔራሎች መካከል ከፍተኛ የሆነ የመብት ጥያቄዎችን ያማከለ እና ህገመንግስታዊ ስርኣትን ተከትሏል የተባለለት ጥያቄዎችን ተከትሎ ከፍተኛ ውጥረት መከሰቱን የመከላከያ ምንጮቻችን ጠቁመዋል::

ባለፉት ሰሞናት የተደረጉት ስብሰባዎች በከፍተኛ አለመግባባት የተበተኑ ሲሆን በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ በስፋት የፓርቲ ስራዎች እንጂ ሃገራዊ ስራዎች እየተሰሩ አይደለም የሚሉ እንዲሁም የመከላከያ ሰራዊቱ ለህገመንግስቱ መከበር ተገኢ መሆን አለበት በአሁን ወቅት ለአንድ የፓርቲ አመራር እና ለፕሮፓጋንዳ ተገኢ ሆነናል የሚሉ ተመሳሳይ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን በሰራዊቱ ውስጥ ያለውን የእድገት የትምህርት እና የደምወዝ መብትን በተመለከተም ከፍተኛ ክርከር ቢደረግም ካለመግባባት መኮንኖቹ ጥርስ እንደተነካከሱ ወደየመጡበት ተበታትነዋል::

የሰራዊት አባላትን ለመቀነስ በተደረገው ጥናት መሰረት ለምን ሁለት ብሄር ላይ አተኮረ የሚሉ ጥያቄ እንዲሁም የስኮላርሺፕ አድሏዊነት በተመለከተ ጠንከር ያሉ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን እንዲሁም ከአንድ ብሄር ለትምህርት ተመርጠው የሚላኩ መኮንኖች በዛው ሳይመለሱ ይቀሩና ነገሩ ይድበሰበሳል የሚሉ አስጨናቂ ጥያቄዎች ተከታትለው ቢነሱም ከመድረኩ መልስ ሳይሰጥባቸው ተድበስብሰው አልፈዋል::ከአንድ ብሄር ብቻ ተመርጠው ለትምሕርት አውሮፓና አሜሪካ ከሄዱት መኮንኖች 80 ከመቶ ያልተመለሱ ሲሆን ይህ ጉዳይ ተድበስብሶ ሌላው ብሄር ስኮላሺፕ እንዳያገኝ ምክንያት እየተፈጠር በዚያው ስለምትከዱ ሃገር ውስጥ በቂ አካዳሚ ስላለ እዚህ እንድንማር ይደረጋል::ስኮላሺፕ የሚሰጣቸው ለማይመለሱ መኮንኖች ነው የሚሉ አቤቱታዎች ተሰምተዋል::ምንሊክ ሳልሳዊ

በሕወሓት ጄኔራሎች እና በብኣዴን ከፍተኛ የጦር መኮንኖች መካከል የተነሳውን ፍጥጫ ተከትሎ ጄኔራል አበባውን ወደ ሲችል ባለስልጣንነት ለማዘዋወር የታቀደ መሆኑን የገለጹት ምንጮሽች በአሁን ሰአት ጄኔራሉ እንደ ቁም እስረኛ አብዛኛው ጊዜያቸውን በመኖሪያ ቤታቸው እንደሚያሳልፉ እና ወደ ቢሯቸው አልፎ አልፎ እንደሚገቡ ታውቋል::

የሳሞራ የኑስን ስልጣን ይረከባሉ ተብሎ የሚጠበቀው ጄኔራል አበባው ጄኔራል ዮሃንስን ወደ ሳሞራ ሕወሓት በሹመት አቅርቦ ካመጣቸው በኋላ ይተለያየ ተጽእኖ እየተደረገባቸው ቢሆንም የብኣዴን ፓርቲ አመራሮች ሁኔታውን በቅርብ እየተከታተሉ ነው ቢባልም ምንም አይፈጥሩም የአሽከርነት ሚና ካልሆነ በስተቀር ሲሉ ምንጮሹ ገልጸዋል::የጄኔራል አበባው ስልጣን ማቆም እና ወደ ሲቭል ባለስልጣንነት መቀየር በሃገሪቱ የፖለቲካ ሂደት ላይ የሚያመጣው ለውጥ እንዳይኖር ሁኔታዎች እየተገመገሙ መሆኑ ታውቋል::ከዚህ ቀደም በተለያየ ወቅት ወደ ውጪ ለእረፍት ለመሄድ ጥያቄ ያቀረቡት ጄኔራል አበባው በተለያየ ምክንያት ሲሰናከልባቸው የቆየ ሲሆን እሳቸውን እና መሰላቸውን ከሰራዊቱ በዘዴ እና በብልሃት ገፍቶ ለማስወጣት በስፋት እየተሰራ መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል::ካሁን ቀደም ሜጄር ጄኔራል የነበሩት አባዱላ ገመዳ አቶ ተብለው ወደ ሲችል ባለስልጣንነት ሲዘዋወሩ ሁለት ከፍተኛ የጦር ጄኔራሎች ደግሞ ወደ እስር ቤት መወርወራቸው አይዘነጋም::ምንሊክ ሳልሳዊ

Image

ከ50 በላይ የሚሆኑ የቅማንት ብሔረሰብ አመራርና አባላት መታሰራቸው ተጠቆመ::
ሕገ መንግሥቱ በሚፈቅደው መሠረት እያቀረበ ባለው የማንነትና የራስ አስተዳዳርነት ጥያቄ ምክንያት፣ ከ50 በላይ የሚሆኑ አባላትና አመራሮቹ መታሰራቸውን የቅማንት ብሔረሰብ አመራር ኮሚቴ አስታወቀ፡፡

የካቲት 9 ቀን 2006 ዓ.ም. ‹‹ቅማንት የሚባል ሕዝብ የለም ያለ አካል ባይኖርም የራስ አስተዳደር ግን ሊፈቀድ አይችልም›› በሚል የክልሉ መንግሥት ተወካዮች ምክር ቤት ነሐሴ 30 ቀን 2005 ዓ.ም. ያስተላለፈውን ውሳኔ በመቃወም፣ በጎንደር ከተማ እስከ 300 ሺሕ የሚደርሱ ተወላጆች በተገኙበት ሰላማዊ ሠልፍ https://www.facebook.com/photo.php?fbid … =3&theater ማድረጉን ተከትሎ፣ በተለይ በአመራር ኮሚቴው ላይ ጫናና ወከባ ሲደርስበት መቆየቱን ገልጿል፡፡

በመሆኑም የክልሉ መንግሥት በተቀናጀ መንገድ በአባላቱና በአመራሩ ላይ በአድማ በታኝና ፖሊስ ሠራዊት በታገዘ ኃይል አማካይነት፣ ከየካቲት 28 ቀን 2006 ዓ.ም. እስከ መጋቢት 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ድረስ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ድረስ በድምሩ 50 አመራርና አባላት ከመኖሪያ ቤታቸው ተወስደው እንደታሰሩበት ኮሚቴው አስታውቋል፡፡ በመተማ ወረዳ ሰላማዊ ሠልፍ አድርገው በሰላም ካጠናቀቁ በኋላም የታሰሩ አባላት እንዳሉም አክሏል፡፡

የክልሉ መንግሥት በምን ምክንያት እንዳሰራቸው ግልጽ ባያደርግም፣ የታሰሩ አባላቱ በቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዳይጠየቁ፣ ከጎንደር በ80 እና 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኙ ዳባትና ደባርቅ ወረዳዎች ተወስደው መታተሰራቸው የሰብዓዊ መብት ረገጣ መሆኑን ኮሚቴው አስታውቋል፡፡

የቅማንት ብሔረሰብ ተወካይ ኮሚቴ በአባላቱና አመራሩ ላይ የአማራ ክልል መንግት ፈጽሞብኛል ስለሚለው እስራትና መንገላታት ማብራሪያ እንዲሰጥ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መምርያ ሲጠየቅ፣ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው ኮማንደር ሰኢድ መሐመድ ምንም መረጃ እንደሌላቸው ገልጸው፣ የሰሜን ጎንደር ዞን ፖሊስ መምርያን ለማብራሪያ ጠቁመዋል፡፡ የሰሜን ጎንደር ፖሊስ መምርያ ፖሊስ ባልደረባ የሆኑትና ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ፖሊስ፣ ‹‹እኛ ቅማንት የሚባል ብሔረሰብ አናውቅም፤ የምናውቃቸው አማራ መሆናቸውን ነው፤›› ካሉ በኋላ፣ በበኩላቸው የሰሜን ጎደር ዞን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወደ ኮማንደር ዘመነ አመሸ ቢጠቁሙም፣ የቢሮም ሆነ የግል ስልካቸውን ሊያነሱ ባለመቻላቸው የኮማንደሩን ምላሽ ማካተት አልተቻለም፡፡ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ምንጭ ረፖርተር ጋዘጣ

ሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ በአገሪቷ ዉስጥ ባሉ አሥራ ሰባት ከተሞች፣ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች እንደሚያደርግ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ ሕዝባዊ ስብሰባ በማድረግ የሚጀመር ሲሆን፣ በሌሎች ከተሞች ከአንድነት ጽ/ቤቶች ወደ አደባባይ በሚሄድ ትይንተ ሕዝቦች ይደረጋሉ። ላስ ቬጋስ፣ ኔቫዳ፣ ከአዲስ አበባ ጋራ ሶሊዳሪቲ በመመሰረት ፣ በዚያ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን፣ በአዲስ አበባ ለሚደረገዉ ሕዝባዊ ስብስበ የሚያስፈልገውን ወጭ ሙሉ ለሙሉ ለመሸፈን […]

ወደ ስድስት የሚጠጉ የፖለቲካና የየሲቪክ ማህበራት ስብስበ የሆነው የኢትዮጶያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት፣ በዚህ ሳምንት በዳያስፖራ ለተቋቋመው የሚሊዮኖች ድምጽ ግብረ ኃይል በጻፉት ደብዳቤ ፣ ድርጅታቸው፣ በአገር ቤት ከፍተኛ መስዋእትነት እየከፈሉ ላሉ ታጋዮች ያላቸዉን አድናቆትና አክብሮት በመገጽል፣ አገር ቤት እየተደረገ ያለዉን የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ ጎን እንደሚቆሙ አረጋገጡ። ድርጅቶቹ በደብዳቤ ድጋፋቸውን […]

ዘወትር ቅዳሜ ማታ ከደሳለኝ መኮንን ጋር፣ምርጥና አዳዲስ የካንትሪ ማለትም የአሜሪካ አገር ሰብእ፣ የሮክ፣ተሶል፣የፖፕ፣የአር-ኤን-ቢ፣ብሉዝ፣የሬጌና የሂፕ-ሃፕ ዜማዎችን እንዲያደምጡ ተጋብዘዋል።

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ወደ የማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ የተጓዙት የጀርመን የልማት ትብብር ሚንስትር ጌርድ ሚውለር ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የርስበርስ ጦርነት ያመሰቃቀላንት የማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ ሲቭል ሕዝብ ስቃይ የማብቃትበቸልት ማለፍ እንደማይገባው አሳስቡ።

ከዚህ በፊት ‘የትግራይ ሕዝብና ሕወሓት ምንና ምን ናቸው?’ ብዬ በጠየቅኩበት ጽሑፌ፤ እጅና ጓንት ናቸው ብዬ ነበር። ስለብዙኃኑ ትግራዋዮች እያወራን ከሆነ አሁንም ያው ነው መልሴ። በዚያ ጽሑፍ እዚህ ድምዳሜ ላይ የደረስኩት ሕወሓት በሚያገኘው ሙሉ ድምፅ አይደለም፤ ያንን የሚያክል ድምፅ አዲስ አበባ ውስጥም የትም ፈጭቶ የትም አግኝቶታል። ሕወሓትን የሚወዱት አማራጭ አጥተው ነው ብዬ ነበር የተከራከርኩት። ምክንያቱም ደግሞ ትግራዋይ ያልሆነው ሰው ሁሉ ትግራዋዩን በሕወሓት መነፅር ስለሚመለከተው ተገፍቶ ነው ባይ ነበርኩ በዚያ ጽሑፍ (በዚህ ጽሑፍ ደግሞ ‘ምን ዓይነት አማራጭ አጥቶ ነው?’ የሚለውን ነው የምጠይቀው) ።

እርግጥ ይሄ ብቻ በቂ ምክንያት አይደለም። ሕወሓት ለሁለት ዐሥርት ዓመታት የዘራው የጥርጣሬ ፕሮፓጋንዳ ትግራዋዮች ሕወሓትን ባይወዱት እንኳ ለሌሎች የሚኖራቸው ጥርጣሬ ከሱ ጉያ እንዳይወጡ ያስገድዳቸዋል። (ፀረ-ቅኝግዛት ተንታኞች የጥገኝነት አባዜ የሚሉት ዓይነት።)

ይህንን ድምዳሜ የእነአብርሃ ደስታን የግለሰብ እና አረና ፓርቲን የቡድን ቁርጠኛ ትግል አጣቅሶ ፉርሽ ለማድረግ የሚሞክር አይጠፋም ብዬ እገምታለሁ። ችግሩ፣ የአረና ተቀባይነት ከጥቂት የልሒቃን ትግራዋዮች አልፎ ብዙኃኑ ውስጥ ሰርጿል ወይ የሚለው ጥያቄ ሲመጣ ነው።

ወደ ጽሑፌ ርዕስ ስመለስ ‘ወዳጅ’ የሚለውን ቃል የተጠቀምኩበት ሕዝቡ የሚወደው ለማለት እንጂ ድርጅቱ የሚወደው ለማለት አይደለም። የአንድ ወገን ፍቅር ነው። አዎ፣ ሕዝብ ሆነን ስናስበው ሕዝቡ የሚወደው “የተሻለ” አማራጭ የለውም።

ሕዝብ ማለት (ቢያንስ ለዚህ ጽሑፍ) በደረሰበት የማኅበረሰባዊ ዕድገት (social evolution) ደረጃ ብቻ የሚያስብ፣ ስሜታዊ፣ ማኅበራዊ እንስሳ ማለት ነው። ሕዝብ ደምበጫ ውስጥ የኦሮሞ ስም ይዞ የመጣ ሰው አይመርጥም፣ ሰላሌ ውስጥ የትግራዋይ ስም ይዞ የመጣ ሰው አይመርጥም፣ አዲግራት ውስጥም እንደዚያው ነው። ይህ የወገን ፍለጋ እሳቤ የሰለጠኑት ዓለማትም ውስጥ የተቀረፈ ነገር አይደለም። አሜሪካ ውስጥ የሳኡዲ አረቢያ ስም የያዘ ፕሬዚደንት ቢያንስ በቅርቡ አይመረጥም። ስለዚህ ሕወሓት ለትግራይ ሕዝብ ይህን የሕዝብ ፍላጎት ያሟላል። ያውም ነፍጥ አንስቶ ሕዝቤን ነጻ አወጣለሁ ብሎ ለመታገል እስከሚደርስ ጀብደኛ ታሪክ (legend) በማሟላት። ስለዚህ ለአረና እና ሌሎችም አማራጭ ፖለቲካ ይዘው የትግራይን ሕዝብ ልብ ለመግዛት የሚታገሉ ፖለቲከኞች ዐብይ ፈተናቸው ይህንን የትግራዋዮች እና ሕወሓት የልብ ለልብ ግንኙነት የሚያሻክር ማስረጃ አሳይቶ፣
ከዚያ የተሻለ ነገር እንደሚያቀርቡ ማሳመን መቻል ነው። ይህንን ማድረግ ለጊዜው ከባድ ይመስላል።

ሕዝብ ጥቅሙን ወዳድ ነው። ፖለቲከኞችም የሚሟገቱት የሕዝብ ጥቅም በሟሟላት ስም ነው። ስለዚህ የሕዝብ ጥቅም በማሟላትም ረገድ ቢሆን የሕወሓት ተፎካካሪዎች ቀላል ፈተና አይኖራቸውም። ሕዝብ ቅቡልነት (legitimacy) የሰጠው መንግሥት የሚያደርገውን ሁሉ ለጥቅሜ ነው ብሎ ያምናል። ሕወሓት ደግሞ በትግራይ ውስጥ የብዙኃኑ ቅቡልነት ይጎልበታል ብሎ ለመከራከር የሚያስችል በቂ መረጃ የለንም። ስለዚህ ተቃዋሚዎች ለሕዝቡ ጥቅም የሚበጅ የተሻለ አማራጭ ይዘው ከመወትወታቸው በፊት በሕዝቡ ውስጥ ቅቡልነት ለማግኘት መድከም አለባቸው። ቅቡልነት ደግሞ ሕዝቡ ቀድሞ የተቀበለውን ቡድን ስም አፈር ድሜ በማስበላት ብቻ አይገኝም፤ እንዲያውም ይህንኛው ወደኋላ ሊባርቅ (backfire) ይችላል። ተፎካካሪ ፓርቲዎቹ ሕዝባዊ ወካይነታቸውን እና ሕወሓት ከሕዝቡ ጉያ ወጥቶ ርቆ መሄዱን የሚያስመሰክሩባቸው ብዙ መንገዶችን መፍጠር አለባቸው።

ሌላውና የማይናቀው ሕወሓትን የተሻለ አማራጭነት በትግራይ ውስጥ የሚያጎላው ደግሞ ጉልቤነቱ ነው። የሕወሓት በኢሕአዴግ ውስጥም ሆነ በፌዴራል መንግሥት ውስጥ ከዕኩልነት የበለጠ ኃይል ሌላውን ሕዝብ፣ አራማጆችን ወይም የሕግ የበላይነት የሚያሳስባቸውን ሰዎች ያሳስብ እንደሆነ እንጂ ብዙኃኑ ትግራዋዮችን አያሳስብም። ሕዝብ ይወክለኛል የሚለው ቡድን የበላይ ኃይል ሲኖረው አይጠላም። የአረና ፈተናም ይኸው ነው። የትግራይ ሕዝብ አረና ከሕወሓት የተሻለ ፖለቲካዊ አማራጭ ይዞ መጥቷል ቢሎ ቢያስብ እንኳ ሕዝቡ በሌሎች ሕዝቦች ላይ የሚኖረውን [የጦር] ኃይል የበላይነት ያስነጥቀኛል ብሎ ካሰበ ለመምረጥ ይቸገራል። ይህ የትግራይ ሕዝብ የተለየ ባሕርይ አይደለም፣ የሁሉም ሕዝቦች ባሕርይ ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ በአገራት መካከል ያሉ ሽኩቻዎችም ባብዛኛው በዚሁ የበላይነት ጥያቄ እንጂ የዕኩልነት ጥያቄዎች የተነሱ አይደለም።

ከላይ የተዘረዘሩት በሙሉ የሕዝብን የጋራ የአስተሳሰብ ፍሰት እንጂ የሕወሓትን እውነተኛ ወካይነት ያረጋግጣሉ ብሎ መደምደምም አይቻልም። ሕወሓት የሚደነቀው የሕዝቡን ሥነ ልቦና በመረዳት መጠቀሚያ ማድረጉ ነው። በዚህ መሐል ግን በርካታ ለማረም የሚቸግሩ ስህተቶችን ሰርቷል። ከስህተቶቹ ሁሉ የከፋው በፌደራሊቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ሌሎች ሕዝቦች የትግራይን ሕዝብ በሕወሓት ዕዳ እንዲጠመድ (በጥርጣሬ ዓይን እንዲታይ) ማድረጉ ነው፣ በምላሹም የትግራይ ሕዝም ሌላውን የማያምን የሕወሓት ጥገኛ አድርጎታል። እነአረናም ይህንን ክፍተት በመሙላት እና የሁሉም ወገን ሕዝቦች ለዘመናት የነበራቸውን ትስስር ባለበትና በተሻለ የዕኩልነትና ወዳጅነት ስሜት ለማስቀጠል የሚያስችል ፕሮግራም መቅረፅ ይጠበቅባቸዋል። እስከዚያው ድረስ ግን ሕወሓት የትግራይ ሕዝብ የቅርብ ወዳጅ መስሎ መኖሩን ይቀጥልበታል።

ዘወትር ቅዳሜ ማታ ከደሳለኝ መኮንን ጋር፣ምርጥና አዳዲስ የካንትሪ ማለትም የአሜሪካ አገር ሰብእ፣ የሮክ፣ተሶል፣የፖፕ፣የአር-ኤን-ቢ፣ብሉዝ፣የሬጌና የሂፕ-ሃፕ ዜማዎችን እንዲያደምጡ ተጋብዘዋል።

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

በርካታ ናይጀሪያውያን ቦኮሃራም የሚያደርሰውን ጥቃት በመሸሽ እየተሰደዱ ነው ። አብዛኛዎቹ የሚፈናቀሉት በተለይ ባለፈው ዓመት በግንቦት ወር መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከደነገገባቸው ከሰሜን ምሥራቅ ናይጀሪያ ግዛቶች ነው ። በዚህ ሰበብ የሃገር ውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥር እየጨመረ መሄድ በተለይ በትላልቅ ከተሞች አሉታዊ ተፅእኖ አሳድሯል ።

ምርመራው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ ተባርኮ ታቦቱ ከመግባቱ በፊት ይከናወናል የጠ/ቤ/ክህነቱ የቁጥጥር አገልግሎት ከምእመናኑ ጥረት ጎን በመቆም ከፍተኛ ድጋፍ አድርጓል በሀ/ስብከታቸው አስተዳደር ጣልቃ መገባቱን ሊቀ ጳጳሱ ለቋሚ ሲኖዶስ አባላት አስታውቀዋል መዝባሪዎቹ ‹‹አንመረመርም›› በሚል በሊቀ ጳጳሱና በደብሩ አስተዳዳሪ ላይ እየዛቱ ናቸው የጠ/ቤ/ክቱ ምሕንድስና ዘርፍ ሓላፊ ኢ/ር ሰሎሞን ካሳዬ ብቃት እንዲመረመር ተጠይቋል ለቤተ ክርስቲያናችን የታቀደውን የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ …