የኢህኣዴግ መዝገበ ቃላት (እንደወረደ) ******* “የልማት ሰራዊቱ” እንደየኣስፈላጊነታቸው ሊጠቀምባቸው የሚገባ የተመረጡ ቃላቶች፥
ፀረ ሰላም ሃይሎች
የፀረ ዲሞክራሲ ሃይሎች
የፀረ ልማት ሃይሎች
ኣሸባሪዎች
ነውጠኞች
ነጭ ለባሾች
የደርግ ርዝራዦች
ያለፉት ስርዓት ቅሪቶች
የኣፄው ስርዓት ናፋቂዎች
ኣደገኛ ቦዘኔዎች
ኪራይ ሰብሳቢዎች
የግል ጥቅም ኣሳዳጆች
ጥገኞች
ትምክህተኞች
ነፍጠኞች
የስልጣን ጥመኞች
ተስፈኞች
ጠባቦች
እንክርዳዶች/ጉርዶች
መሃል ሰፋሪዎች
ኣድሃሪያን
የቀለም ኣብዮተኞች
የሻዕቢያ ቅጥረኞች/ ጋሻጃግሬዎች
ኣክራሪ ቡድኖች
የሰለፊ/ወሀቢ እምነት ኣራማጆች
ፅንፈኞች
ቆ… ሻሻ (እደግመዋለሁ ቆ… ሻሻ!)
የበከተ/የገማ/የበሰበሰ ኣስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች
ዝቃጮች
ሁከተኞች
ፀብ ኣጫሪዎች
ተቸካዮች
ተንበርካኪዎች
ጥራዝ ነጠቆች
ስግብግብ ነጋዴዎች
ተለጣፊዎች/ተነጣፊዎች
የኢንተርሃምዌ ኣራማጆች
ሗላቀር ኣስተሳሰብ የተጠናወታቸው ሃይሎች
ህገ መንግስቱን በጉልበት ለመናድ የሚዶልቱ ሃይሎች
ኣንዳንድ ኣርቆ ማሰብ የተሳናቸው ዜጎች (ዘገምተኞች )
•
•
•
(ደከመኝ በነጠብጣብ ልለፈው )
*****
የቀረ የለም። ምሁር ነሽ፡ ፖለቲካ ኣያገባኝም የምትይ መሃል ሰፋሪ ነሽ፤ የእምነት ሰው ነሽ፡ ነጋዴ ነሽ፡ ምንድነሽ ሁልሽም ቅጥያ ኣለሽ!
የልማት ሰራዊቱ ከሁሉም ጋር ስለማይስማማ (ከራሱም ጭምር) ለሁሉም ቅጥያ ኣዘጋጅቷል፤ ባንዳች የስድብ ምትሃታዊ ሃይል ነው ስርዓቱ የቆመው ማለት ሳይሻል ኣይቀርም።