ነኅሴ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአንድ እስከ አራተኛ ክፍል በሚተገበረው የክላስተር ፖሊሲ በተለይ በኦሮምያ ፤ ሶማሌ እና ደቡብ ክልሎች ከአንድ እስከ አራተኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች የማንበብ እና የመፃፍ ክህሎታቸው ከዜሮ ነጥብ በታች መሆኑን ከትምህርት ሚኒስትር የተገኘው መረጃ አመልክቷል፡ የተማሪዎቹ የሂሳብ ማስላት ችሎታ መዳከሙን፣ በሳይንስ ትምህርት ላይ ለውጥ እንዲመጣ የተጣለው ግብም አለመሳካቱን …

ነኅሴ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለእናቶችና ህጻናት ጤንነት ታስቦ ከተለያዩ ለጋሽ ሃገራት በእርዳታ የተገኙትን አምቡላንሶች ከታሰበላቸው አገልግሎት ውጭ ለተለያዩ ፖለቲካዊ ስራ በመመደብ ሲጠቀሙባቸው እንደነበር በምዕራብ ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ የሚገኙ አንድ የስራ ኃላፊ ገለጹ፡፡ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉት ኃላፊ እንደተናገሩት የወረዳ አስተዳዳሪዎች በቂ በጀት እንዲመድቡ መመሪያ ቢሰጣቸውም ችላ በማለት አገልግሎት መስጠት የነበረባቸው …

ኢሳት ዜና (ነሐሴ 15 ፣ 2007) ሰሞኑን በኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞ አውሮፕላን ውስጥ በእቃ መጫኛ ውስጥ ተደብቆ በስዊድን ጥገኝነትን የጠየቀው ኢትዮጵያ በአየር መንገድ ውስጥ በአንድ ብሄር የበላይነት የሚደርሰው በደልና ግፍ ለህዝብ ለማጋለጥ ሲል ድርጊቱን መፈጸሙን ከኢሳት ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ አስታወቀ። የ 24 አመቱ ወጣት ይርጋሸዋ ማሽላ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ ለመናገር የሚከብድ የአንድ ብሄር …

‹‹እንሰሳት በዋሉበት እየቀሩ ነው›› ነዋሪዎች በሀገሪቱ በተፈጠረው የዝናብ እጥረት ምክንያት በተለይ በአፋር፣ በሶማሊና በሌሎች አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ ጎጃም ውስጥም በመከሰቱ በርካታ እንሰሳት እየሞቱ መሆኑንና ሰውም ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለፁ፡፡ በተለይ ድርቁ በሶማ፣ አራራ፣ እነገ እና ሰንጠርጌ ቀበሌዎች ለበርካታ እንሰሳት ሞት ምክንያት ከመሆኑም ባሻገር ነዋሪዎችም ለከፍተኛ ችጋር ተጋልጠዋል ተብሏል፡፡ ድርቁ አስከፊ ደረጃ […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ በቀጣይ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ላይ የተመረጡ እና የተለመዱ ፊቶችን ስብስበው ጥያቄ ሲያቀርቡና ማብራሪያ ሲሰጡ ነበር፡፡የእኔን ቀልብ የሳበው ግን አውቀውም ይሁን ሳያውቁት ወጣቶችን እየበላ ያለ ስርዓት ባለቤት እና መሪ መሆናቸውን የገለፁበት አስተያየት ከታዳሚው ሞቅ ባለ በተደጋጋሚ ጭብጨባ መታጀቡ ነው፡፡ ባለፈው የኦባማ ጉብኝት ወቅት ዲሞክራሲ ማላት ምርጫ በስላም ማጠናቃቅ ብቻ አይደለም፡፡ ጋዜጠኞችን አክቲቪሰቶችን […]

ከታሳሪ የህሊና ሰዎች መካከል አብጦ ሊፈነዳ የተቃረበውን የፖለቲካ ድባብ ለማስተንፈስ ሲባል ወዳጄን፣ ጓዴንና የቀድሞ ባልደረባዬን አብርሀ ደስታን፣ የሽዋስ አሰፋን፣ ሐብታሙ አያሌውን፣ ዳኤል ሽበሽንና አብሃም ሰለሞንን «በነፃ» መለቀቅ በሰማሁ ጊዜ ደስታ ቢሰማኝም፤ ንጹሓኑ «በነጻ» መለቀቃቸው ከጠባቡ ጓንታናሞ ወደ ሰፊው ጓንታናሞ መዛወራቸው እንጂ አሁንም ነጻ አለመሆናቸውን፤ እንዴውም አሁን ያለንበት በነጻነት የመናገርና የመጻፍ ሁኔታ እነሱ ከመታሰራቸው በፊት ከነበረው […]

 

በነሶሊያና ሺመልስ የክሥ መዝገብ ብይን ሲጠብቁ የነበሩት አራቱ የኢንተርኔት አምደኞች ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል፡፡

ክሣቸው ተቋርጦ በነፃ የተሰናበቱትም በኤግዚቢትነት ተይዘው የነበሩ ንብረቶቻቸው እንደተመለሱላቸው ተናግረዋል፡፡

በኮምፕዩተሮቻቸው ውስጥ የነበሩ ልዩ ልዩ ሠነዶች ግን በመጥፋታቸው ማዘናቸውን ገልፀዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

ዛሬ ነሐሴ 13/2007ዓም በ8:00 ሰዓት የጠቅላይ ፍርድ ሰበር ሰሚ ችሎት ወሳኔ ለመስጠት ሲያነጓትተው የነበረውን የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የሰበር አቤቱታ ላይ ዛሬ ውሳኔውን አስተላልፏል። ፍርድ:- ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ ከዚህ ቀደም የእስር ፈርድ ቤቱ የሰጠው የ 3 አመት ፍርድ አግባብም ትክክልም ነው፣ ስለዚህ የስር ፈርድ ቤቱ ካስተላለፈው ውሳኔ ውጪ አይደለንም ፍርዱን አፅንተነዋል ፍርዱ ልክ ነው ምንም […]

በመረጃ መረብ ሰንሰለቱ አማካኝነት ወደ መንግስት መዋቅር ዘልቆ በመግባት ያገኘው የታማኝ ምንጮች መረጃ እንዳረጋገጠው በሙስሊሙ ዑማ ላይ ከፍተኛ በደልና ጭቆና የፈፀመው ህወሓት መራሹ መንግስት በአሁኑ ሰዓት የሙስሊሙ ማህበረሰብ አጠቃላይ ሁኔታ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ዘፍቆታል ። በአሁኑ ሰዓት ሙስሊሙ ማህበረሰብ የትግል ስልቱን ቀይሮ ውስጥ ለውስጥ በመደራጀት አንድነቱን እያጠናከረ እና በተናጠልና በቡድን በመሆን ስለ ቀጣይ ትግሉ እየተወያየ […]

ርዕዮት አለሙ፤ ከአዲስ አበባ ልጆች ሆነን “እከሌ (እከሊት) አክራሪ ነዉ (ናት)” ሲባል ይሰጠን የነበረዉ ትርጉም እና አሁን አክራሪነት እየሰጠ ያለዉ ትርጉም ለየቅል ይመስለኛል፡፡ ያኔ አንድ ሰዉ በአክራሪነት ሲጠራ ከብዙሃኑ በተለይ ሁኔታ ሃይማኖቱን ወይም የሚያምንበትን አንዳች ነገር አጥብቆ መያዙን እና በሚያምንበት ነገር ላይ …

አክራሪና አሸባሪዉ ኢህአዴግ ወይስ የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት? – ርዕዮት አለሙ Read more »

ነኅሴ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በወረ ጃርሶ ወረዳ በሚገኙ በፋጂ ኢጀርሳ፣ ላንቱ ወላርጊ እና ምእራብ ኮርጎጎ ቀበሌዎች የሚኖሩ ከ300 በላይ አርሶአደሮች ከሰኔ 28 ቀን 2007 ዓም ጀምሮ ኢጀርሳ መንደር ውስጥ በሚገኝ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ታስረው እየተደበደቡ መሆኑን ቤተሰቦቻቸውና እስራቱን ለማምለጥ የተደበቁ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። …

ነኅሴ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው ከሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ ከአንድ ዓመት በላይ በተንዛዛ የፍርድ ቤት ቀጠሮ በእስር ሲማቅቁ የነበሩት አራቱ የፖለቲካ እስረኞችን ጨምሮ ሌሎች ሁለት ተጠርጣሪዎች፣ የልደታው ፍርድ ቤት 19ኛ የወንጀል ችሎት፣ ዛሬ ነሃሴ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ተከሳሾችን አሰናብቷል። በዘላለም ወርቅአገኘሁ የክስ መዝገብ የተከሰሱት የቀድሞው …

ነኅሴ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰንደቅ ጋዜጣ ይዞት በወጣው ዘገባ በፓትሪያርክ አቡነ ማትያስ መመሪያ የተቋቋመው አጥኚ ቡድን የመሬትና ሕንፃዎች ኪራይ ተመንን አስመልክቶ በ51 የአዲስ አበባ አድባራት ባካሔደው ጥናታዊ ሪፖርት፣ በየወሩ 100 ሚሊዮን ብር፣ በዓመት ደግሞ 1 ቢሊዮን 500 ሚሊዮን ብር በሙስና እንደሚዘረፍ ገልጿል። ቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ እና ሰፊ የመሬት …

ነኅሴ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ነዋሪዎች እንዳሉት ሰኔ 15 እና 16 የክረምቱ ዝናብ ከዘነበ በሁዋላ፣ ዝናብ ለተከታታይ ስድስት ሳምንታት አልዘነበም። ሃምሌ 29 ቀን ደግሞ ለአንድ ጊዜ ዘንቦ በመጥፋቱ ፣ ህዝቡ በከፍተኛ ሃዘን ውስጥ ገብቶ ነበር። ይሁን እንጅ ትናንት ከምሽቱ 11 ሰአት ከ30 ደቂቃ ላይ መዝነብ የጀመረው ዝናብ እስከ 12 ሰአት …

ነኅሴ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባና የኢህአዴግ የስራ አስፈጻሚ ኮምቴ አባል አቶ ድሪባ ኩማ የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብና ተግባር በከተማዋ መቀነስ ያልቻለው መመሪያዎችን በቁርጠኝነት መፈጸም የማይችል አመራር በመኖሩ ነው ሲሉ በስራቸው የሚገኙ አመራሮችን ወቅሰዋል፡፡ ከንቲባው ይህን የተናገሩት በሰኔ ወር 2007 የተጠናቀቀውን የአምስት ዓመት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸምና በቀጣይ ዓመት …

በፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በሽብርተኝነት ክስ ተመሥርቶባቸው በእስር ላይ የቆዩት የቀድሞ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)፣ የሰማያዊና የአረና ፓርቲ አመራሮችና ሁለት ተከሳሾች በነፃ እንዲሰናበቱ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ነሐሴ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ወሰነ፡፡ የአንድነት ፓርቲ የቀድሞ …

የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ሀብታሙ አያሌውና ዳንኤል ሺበሺ፣ የአረና ፓርቲ አመራር አብርሃ ደስታ፣ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር የሺዋስ አሰፋና ሌሎች 2 ተጠርጣሪዎች በነፃ እንዲሰናበቱ ተወሰነ Read more »

በተባበሩት መንግሰታት የሰብአዊ ድጋፍ ቢሮ ይፋ ባደረገው አዲስ ሪፖርት በኢትዮጵያ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር በያዝነው ወር 4.5ሚልዮን መድረሱን ይፋ አድርጓል፡፡ የ2015 ግማሽ አመት የሰብአዊ ድጋፍ ተፈላጊነት ከተገመገመ በኋላ ሪፖርቱ ይፋ ሲደረግ ለጋሽ አገራትና የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዩች በስፍራው መገኘታቸውን መረጃው ጨምሮ ጠቁሟል፡፡ ሪፖርቱ በተጨማሪ ለምግብና ምግብ ነክ ላልሆኑ ነገሮች የሚያስፈልገው የእርዳታ መጠን በጃንዋሪ(ጥር)ወር ተተንብዮ ከነበረው […]

ዛሬ ነሃሴ 14/2007 ዓ.ም የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የተከሰሱትን 2ኛ ተከሳሽ ሀምታሙ አያሌው፣ 3ኛ ተከሳሽ ዳኤል ሽበሽ፣ 4ኛ ተከሳሽ አብርሃ ደስታና 5ኛ ተከሳሽ የሸዋስ አሰፋ እንዲሁም 7ኛ ተከሳሽ አብሃም ሰለሞን በነፃ እንዲለቀቁ ወስኗል፡፡ በአንፃሩ አንደኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ ከአሁን ቀደም ተከሶበት በነበረውና ከ15 አመት በላይ እንደሚያሳስር የሚታወቀው የፀረ ሽብር ህጉ አንቀፅ አራት ‹‹ማሴር፣ […]

የአርበኞች ግንቦት 7 ህዝብ ግንኙነት የህወሓት አገዛዝ የደህንነት ቢሮ ጮርቃ ህፃናትን በሰላይነት እያሰለጠነ እንደሚገኝ ታወቀ፡፡ የህወሓት ብሄራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮ በርካታ ህፃናትን ከየአካባቢው መልምሎ አዲስ አበባ ውስጥ የስለላ ትምህርት በስውር እያስተማረ ይገኛል፡፡ ብሄራዊ መረጃና ደህንነት ህፃናቱን አገዛዙን ብቻ በታማኝነት እንዲያገለግሉ የሚያመቻች የስለላና ሌሎች ተያያዥ ትምህርቶችን ለረጅም ጊዜ በተከታታይ በመስጠት አስተሳሰባቸውን በመግራት አእምሯቸውን በሚፈለገው መልኩ ለመቅረፅ […]

የተመሠረተበትን 35ኛ ዓመት በታላቅ ፌሽታ ለማክበር ደፋ ቀና በማለት ላይ የሚገኘው የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ በረከት ስምኦን ንቅናቄው ሰሞኑን በሚያካሂደው ጉባዔ ላይ እንደማይመረጡ ምንጮች ጠቆሙ፡፡ ህወሃትም በተመሳሳይ ሁኔታ የሟቹን የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍንን ያሰናብታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የብአዴን ምንጮች እንደሚሉት ኢህአዴግ ባስቀመጠው የመተካካት ስርዓት መሠረት […]

ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ድንበር አቋርጣችኋል የተባሉ ኢትዮጵያዊያን ማላዊ ውስጥ በእሥር ላይ ይገኛሉ። እነዚህ 232 ኢትዮጵያዊያን የሚገኙበት ሁኔታም እጅግ አስከፊና ጤንነትንም የሚጎዳ መሆኑን እዚያው ኗሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል። ከእነዚህም አንዷ ዋና ከተማይቱ ሊሎንግዌ ውስጥ ከሃያ ዓመታት በላይ የኖሩት ወ/ሮ …

ማላዊ ውስጥ 232 ኢትዮጵያዊያን ታስረዋል Read more »

ነኅሴ ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተመሠረተበትን 35ኛ ዓመት በታላቅ ፌሽታ ለማክበር ደፋ ቀና በማለት ላይ የሚገኘው የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ በረከት ስምኦን ንቅናቄው ሰሞኑን በሚያካሂደው ጉባዔ ላይ እንደማይመረጡ ምንጮች ጠቆሙ፡፡ ህወሃትም በተመሳሳይ ሁኔታ የሟቹን የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍንን ያሰናብታል ተብሎ …

ነኅሴ ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ፣ ኢሰመጉ የአሁኑ ሰመጉ ባወጣው 137ኛ ልዩ መግለጫ፣ ከምርጫ 2007 ጋር በተያያዘ 6 ሰዎች መገደላቸውንና 83 የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች መታሰራቸውን በስም ዘርዝሮ አቅርቧል። በደብረማርቆስ ከተማ ሰኔ 8 ቀን 2007 ዓም የተገደለው ወጣት ሳሙኤል አወቀ፣ በፖለቲካ አመለካከቱ ምክንያት የተገደለ መሆኑን የቅርብ ቤተሰቦቹ …

ነኅሴ ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር ባወጣው ሪፖርት በኢትዮጵያ ውስጥ የመኸርና የክረምት ዝናብ ወቅቱን ጠብቆ ባለመጣሉና በመዘግየቱ ምክንያት በተፈጠረው ድርቅ ሰለባ ለሆኑ ከ4 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያን ግምቱ ከ386 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወይም ከ7 ቢሊዮን 700 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ አፋጣኝ የሆነ የሕይወት አድን የምግብና ሌሎች …

ኢሳት ዜና (ነሐሴ 12 ፣ 2007) በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን የዞኑ አስተዳደር ህገ ወጥ ግንባታ ናቸው ያላቸውን መኖሪያ ቤቶች ለማፍረስ መሞከሩን ተከተሎ ነዋሪዎች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተው በርካታ ሰዎች ለእስር መዳረጋቸውና መደብደባቸው ተገለጠ። በሳምንቱ መገባደጃ በዞኑ በምትገኘው የቦሎሶሶሬ ወረዳ በተቀሰቀሰ በዚሁ ግጭት ከ20 በላይ ነዋሪዎች በላይ ነዋሪዎችና ህገ-ወጥ ናቸው የተባሉትን ግንባታዎች ለማፍረስ የተሰማሩ ከ10 በላይ አፍራሽ …

(ስሉሥ ወልደሂወት) “ማንም የቆመ የሚመስለው ቢኖር እንዳይወድቅ ይጠነቀቅ”! መጽሓፍ ቅዱስ የሰው ልጅ ፍላጎት ሁሌ የሚያድግና የማይሟላ በመሆኑ የለውጥ ጥያቄን ለመመለስ ሁሌም ሰለተሻለ አማራጭ፣ ስለተሻለ ዘዴ ወይም ስትራቴጂ ማሰቡና መነጋገሩ ተገቢና ጤናማ መሆኑ የማይታበል እውነት ነው፡፡ በዲሞክራሲያዊ ማህበረሰብ ዘንድ የተቀደሰና ከነቀፋና ትችት የፀዳ የፖሊሲ አቋም ወይም የፖሊሲ አፈፃፀም የማይኖር መሆኑም እንደዚሁ። ዜጐች በግልም ይሁን በተደራጀ መልኩ በነፃነትና ከማንኛውም ተጽእኖ በጸዳ መልኩ የፖሊሲ አማራጮችን መተቸችና የመልካም አስተዳደር ግድፈቶችን ነቅሶ ማውጣት የሚችሉበት ሁኔታ ከተፈጠረ ያ ማህበረሰብ የታደለ ነው ማለት ይቻላል፡፡ የፖለቲካ መሪዎች በዓቅም ውስንነት፣ በግንዛቤ እጥረት፣ የግል ፍለጎት በማሰቀደም ወይም በቅንነት እጦት ምክንያት የሕዝቦችን ጥቅም አደጋ ውስጥ ሊከቱ የሚችሉበት እድል ሰፊ ነው። በመሆኑም የፖሊሲ አማራጮችንና የአፈፃፀም ግድፈቶችን ከመተቸት ባላፈ ፖሊሲውን ለማስፈፀም ሃላፊነት የወሰዱ የፖሊቲካ ድርጅቶች አመራር፣ ውስጣዊ ድርጅታዊ ህይወትና የአመራሩ የግል ማንነት ሳይቀር አብጠርጥሮ ማወቅና መተቸት በሰለጠነው ዓለም የተለመደና ውጤታማ የሆነ የዲሞክራሲ ባህል ነው፡፡ ከሰሞኑ አቶ ዳዊት ገብረ እግዚአብሔር የተባሉ ዜጋ በተለየ ሁኔታ በህወሓትና ህወሓት በሚመራው የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የልማትና መልካም አስተዳደር ፖሊዎችና አፈጻጸም ላይ የሰላ ትችት በመሰንዘር ላይ ይገኛሉ፡፡ የአቶ ዳዊት ትችት ከግል ገጠመኝና ትዝብት በመነሳት በአጠቃላይ በስርዓቱ፣ ስርዓቱ በቆመባቸው ምሰሶችና የማስፈፀምያ ፖሊሲዎች ስትራቴጂዎች እንደዚሁም የድርጅቱና የድርጅቱ አመራር ዓቅምና ህዝባዊነት ላይ ጥያቄ አስነስቷል፡፡ ቀደም ብዬ እንዳልኩት ከፖሊሲ የተሻለ ፖሊሲ፣ ከተሻለው ፖሊሲ እጅግ የተሻለ ፖሊሲ መኖሩ የማይቀር ስለሆነ፤ አቶ ዳዊት ስለተሻለ አመራር፣ […]

በሕዝብ ሃብት መቀለድ ተይዟል::ሰበታ አከባቢ ያልተጠናው የባቡር ሃዲድ እየፈረሰ ነው:: ሰበታ አካባቢ ያለ የባቡር ሃዲድ መስመር በወያኔ ባለስልጣናት ትእዛዝ እየፈረሰ ነው በምስሉ እንደሚታየው አሁን ከተገነቡት መሀል አንዱ ሲሆን ምክንያትቱ ሳይታወቅ ሁኔታ በ24 ሰአት አንዲፈረሰ ትዕዛዝ ተሰጥቷል በተለያዩ የአዲስ አበባ አከባቢዎች በርካታ የሆኑ የባቡር መስመሮች የሚፈርሱ እንዳሉ የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል::ይህ ያልተጠና እና በሕዝብ ሃብት ላይ እየተቀለደ […]

ዛሬ በዞን 9 ጦማሪያን የፍርድ ቤት ውሎ የገረመኝ ዛሬ ረፋድ ላይ፤ ናቲ፣ አጥናፍ፣ በፍቄና አቤል በፊት ለፊት በር ችሎት ከገቡ በኋላ፣ እኛም ችሎቱን እንታደማለን ብለን ስንጠብቅ፤ ለጠበቃቸው ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱ ተነገረ፡፡ ጦማሪያኑንም በጓሮ በር በማስወጣት ‹‹አንበሳ ቤት›› እንዲቀመጡ ተደረገ፡፡ በፊት ለፊት አስገብቶ በጓሮ በር ማስወጣት ምን ይባላል? ለምንስ ይሆን? በስፍራው የተገኙ የእስረኛ ቤተሰቦች፣ ዘመዶች፣ ጓደኞች፣ […]

የቀድሞው የብሥራተ ገብርኤል፣ የመካኒሳ ሚካኤል እና የገርጂ ጊዮርጊስ አለቆች ተጠቅሰዋል ከግለሰቦች ጋር የሕገ ወጥ ጥቅም ተጋሪ በመኾን አድባራቱን ለዕዳ የዳረጉ አለቆች ይገኙበታል የመኪና እና የኮንዶሚኒየም ቤት ቁልፍ ሽልማት በፓትርያርኩ ሳይፈቀድ እንዳይሰጥ ተወስኗል ቤተ ክርስቲያኒቱን ወደ ጥንተ ክብሯ የሚመልስ የፀረ ሙስና እንቅስቃሴ ይደረጋል ተብሏል በጥናታዊ ሪፖርቱ፣ ‹‹አስገራሚ እና ለምዝበራ የተመቸ›› በተባለ አሠራር፣ የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል …

በኢትዮጵያ ከሚገኙት ከ30 ከሚበልጡት የመንግሥት እና በብዛት ከተከፈቱት የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ዘንድሮ ከ90 ሺህ የሚበልጡ ተማሪዎች ተመርቀዋል። ዩኒቨርሲቲዎቸች እና የኮሌጆች ምሩቃን የቀሰሙትን እውቀት እና በሥልጠና ያገኙትን ሙያዊ ክሂሎት የተሻለ ኑሮ እድል ከፋች አድርገው ተመልክተውታል። ይሁንና፣ ገሀዱ እንደጠበቁት ሆና ሳያገኙት …

ምሩቃን እና የሥራ ዕድል Read more »

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መንጌ ወረዳ የመንግስት ሃይሎች አርብ እለት በሰነዘሩት ጥቃት 12 ሰዎች ተገደሉ። ከሟቾቹ ውስጥ 5ቱ ህይወታቸው ያለፈው እስር ቤት ከተወሰዱ በኋላ በምግብ ተመርዘው እንደሆነ የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ አስታወቀ። የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ (ቤሕነን) ሊቀመመንበር አቶ አብዱልዋህድ መሃዲ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት አርብ ነሐሴ 8 ቀን 2007 የመንጌ ወረዳ ነዋሪዎች በስርዓቱ ላይ […]

በኬንያ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር የዋሉት 100 ኢትዮጵያዊያን ትናንት አመሻሽ ላይ ነው፡፡በወጣትነት የእድሜ ክልል የሚገኙት ታሳሪዎቹ በተፋፈነ ሁኔታ በአንድ ትልቅ መኪና ተሳፍረው ወደ ናይሮቢ በመገስገስ ላይ እንዳሉ በፖሊሶች በተደረገ ፍተሻ መያዛቸው ታውቋል፡፡ታሳሪዎቹ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለማቅናት አቅደው የነበሩ መሆናቸውም ተነግሯል፡፡ እንደ ዴይሊ ኔሽን ዘገባ ከሆነም ስደተኞቹ በሞያሌ በኩል በድብቅ በማለፍ ወደ መሩ ካውንቲ ማምራታቸውን መረጃ የነበራቸው የኬንያ ፖሊሶች በቀላሉ በቁጥጥር ስር ሊያውሏቸው […]

ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአለፈው ምርጫ ጋር ተያይዞ ፣ የአካባቢው ህዝብ የስርዓቱ ደጋፊ አይደለም፣ በምርጫውም ለመሳተፍም ሆነ ከመንግስት ጎን ለመቆም ፍላጎት አላሳየም በሚል የበቀል እርምጃ እንደተወሰደባቸው የአካባቢው ተወላጆች፣ የልዩ ሃይል አባላት በወሰዱት የጭካኔ እርምጃ እስካሁን በመንጌ ወረዳ 11 ሰዎች መገደላቸውን ገልጸው፣ ግጭቱ ወደ ዳቡስ አካባቢም የተዛመተ በመሆኑ የሟቾቹ ቁጥር ከፍተኛ …

ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ወሎ ለጋምባ ወረዳ ከዩኒቨርስቲ ግንባታ ጋር በተያያዘ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ወጣቶች ተይዘው መታሰራቸውን የደረሰን ዜና አመልክቷል። ከታሰሩት መካከል 6 ያክሉ የመንግስት ሰራተኞች ናቸው። ዩኒቨርስቲው ይገነባበታል ተብሎ እቅድ ተይዞ በነበረበት በቱሉ አወሊያ አንድ ፖሊስ ተደብድቦ አቀስታ ሆስፒታል ገብቷል። በአካባቢው የሰፈረው የፌደራል ፖሊስ ወጣቶችን …

ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት የመኢአድ ፓርቲ የአመራር አባላት በእስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው የአይን እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል። ወጣት ተስፋየ ታሪኩ፣ ቀድም ብሎ በእስር ቤት ውስጥ እየተደበደቡ መሆኑን ለፍርድ ቤት ማመልከቱን ተከትሎ ፣ ፖሊሶች ዘቅዝቀው በጠመንጃው ሳንጃ በሽፋኑ ጀርባውን ደብድበውታል፣ እጁና እግሮቹም ተጎድተዋል። ተስፋየን …

ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ ሬዲዮ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ አስመልክቶ በሰራው ዘገባ ፣ የአገሪቱ ሰራተኞች በአለም ላይ እጅግ ዝቅተኛ የሆነ ክፍያ ከሚያገኙ አገሮች ቀዳሚ መሆናቸውን ጠቅሶ፣ የውጭ አገር ኩባንያዎች ሰራተኞቹን እንደ ባሪያ እንደያዙዋቸው ገልጿል። ከ11 ሚሊዮን በላይ ስራ አጥ ባለበት የሰራተኛውን የመጨረሻ የክፍያ ወለል ማስተካከል ፈታኝ መሆኑን የገለጸው ቢቢሲ፣ ወጣቱ በ50 …

ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ወታደሮች በሶማሊያ ሂራን ክልል ውስጥ ከአፍሪካ ኅብረት የሰላም አስከባሪ ጦር፣ አሚሶም ተልኮ ውጪ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን የአሚሶም ምድብ አራት የጦር አዛዥ የሆኑት አብዱራህማን አብዲ ዲምቢሊ ቅሬታቸውን አሰሙ። ጅቡቲያዊው የጦር አዛዥ ኮማንደር አብዱረህማን ፣ ካለ ህብረቱ ጦር ትእዛዝ በሂራን ግዛት የኢትዮጵያ ወታደሮች አልሸባብን ደምስሰው አካባቢውን ከተቆጣጠሩት በኋላ …

ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመላ ሃገሪቱ በ2001 ዓ.ም የተቋቋመው የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ የታሰበለትን ሃገራዊ ፋይዳ በተገቢው ሁኔታ ለማድረስ እንዳልቻለ የአማራ ክልል የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ የሽዋስ ተናገሩ፡፡ ዳይሬክተሩ በክልሉ በልዩ ልዩ ቦታዎች በተካሄደው ውይይት ለተሳታፊዎች እንደገለጹት በአመለካከትና ክህሎት ዙሪያ ሰፊ ክፍተት አለ ብለዋል። መዛኝ …

ነኅሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሚኒስትሩ ሚካኤል ማኩዊ የምስራቅ አፍሪካ በየነ መንግስታት ኅብረት ኢጋድ ዋና አደራዳሪ የሆኑትስዩም መስፍን በተደራዳሪዎች ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ ይሞክራሉ ሲሉ ወቀሳቸውን አሰምተዋል። ሚካኤል ማኩዊ ” የኢጋድ አደራዳሪዎች ደቡብ ሱዳንን የሙከራ ምድር ለማድረግ ይሞክራሉ።አንዳንዶቹ በጭራሽ ዓለማቀፋዊ ተቀባይነት የሌላቸው ናቸው።የግድ መፈረም አለባችሁ ብሎ ለተደራዳሪዎች አስገዳጅ ውል ማቅረብ፣ ካልፈረማችሁ እኛ …

የት እንዳሉ ሳይታወቁ ቀርተው የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በአባታቸው መጎበኘታቸው ተሰማ:: የአርበኞች ግንቦት 7 አመራር የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የመን ላይ ተይዘው ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፈው ከተሰጡ በኋላ አፍቃሪ የመንግስት ድረገጾች በፎቶ ሾፕ አንዳርጋቸው የአዳማን መንገድ ሲጎበኝ በሶሻል ሚድያዎች ለጥፈው ሲዋሹ ነበር:: ከዚህም በተጨማሪ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም አቶ አንዳርጋቸውን ልማቱን እያስጎበኘነው ነው ሲሉ በአሜሪካ ድምጽ ራድዮ […]

ኢሳት ዜና (ነሐሴ 12 ፣ 2007) በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መንጌ ወረዳ የመንግስት ሃይሎች አርብ እለት በሰነዘሩት ጥቃት 12 ሰዎች ተገደሉ። ከሟቾቹ ውስጥ 5ቱ ህይወታቸው ያለፈው እስር ቤት ከተወሰዱ በኋላ በምግብ ተመርዘው እንደሆነ የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ አስታወቀ። የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ (ቤሕነን) ሊቀመመንበር አቶ አብዱልዋህድ መሃዲ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት አርብ ነሐሴ 8 ቀን …

የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያን ህዝብ ንብረትና አንጡራ ሀብት በመመዝበር በአለም አቀፍ ደረጃ አሉ በሚባሉ ታላላቅ የንግድ ተቋማትና ባንኮች ላይ ባለድርሻ እየሆኑ ይገኛሉ ለጊዜዉ ስማቸዉን መጥቀስ አስፈላጊ የልሆኑ ከፍተኛ ባለስልጣናት በደቡብ አፍሪካ ዚምባብዌ ኡጋንዳ ቦትሱዋና ዉስጥ ትላላቅ ህንጻዎችን፣ እና የእንግዳ መቀበያ ሆቴሎችን ( gust houses ) ፣ መሬቶችና ሌሎችታላላቅ የንግድ ተቋማት ላይ እግራቸዉን እየተከሉ ይገኛሉ። […]

የመላው ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ( መኢአድ) የውጭ ግንኙነት ሀላፊ አብርሃም ጌጡ ሰኔ 12 /2007 ልደታ ፓሊስ መምሪያ ታሰረ ብዙም ሳይቆይ ወደ 5ኛ ፓሊስ ጣቢያ ተዛወረ ልደታ ፍርድ ቤት ሚያዝያ 13/2007 ዓም የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ወጣቶችን አደራጅተህ ሚያዝያ 14/2007 ዓም መንግስት የጠራውን ሠልፍ እንዲረበሽ አድርገሃል የሚል ክስ ቀረበበት ጊዜ ቀጠሮ ላይ እያለ ሳይቋጭ […]

_በፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና በምክትላቸው በአርበኛ መዓዛው ጌጡ የተመራው የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራር በኤርትራ በረሃ በተለያዩ የጦር ካምፖች የሚገኙትን የነጻነት ታጋዮችን ጎበኘ። አቶ ነዓምን ዘለቀና አቶ ኤፍሬም ማዴቦም ተገኝተዋል። ታጋዮቹ ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡ ከአመራሮቹም ጋር ተወያይተዋል። _ባለፈው ዓርብ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መንጌ ወረዳ ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የሚመራው መንግስት ሃይሎች በወሰዱት እርምጃ 17 ኢትዮጵያውያን ተገደሉ። ስርዓቱ በቃን […]

በሚሌ ወረዳ የሀርሲስ ቀበሌ ነዋሪዎች በድርቅ መጎዳታቸውን የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዘጋቢ ግርማይ ጋብሩ በአፋር ክልል ታዘዋውሮ ዘግቧል። Listen