ከሓምሌ ወር 2007 ዓ/ም ጀምሮ መብራት በተደጋጋሚ በመቆራረጡና በመጥፋቱ ምክንያት ባለ ድርጅቶች ለኪሳራ መጋለጣቸው ተገለፀ።ምንጮቻችን እንደገለፁት በአዲስ አበባ ከተማ ካለፈው ሓምሌ ወር 2007 ዓ/ም ጀምሮ መብራት በተደጋጋሚ በመቆራረጡና በመጥፋቱ ምክንያት። በኤሌክትሪክ ሃይል የሚሰሩ የተለያዩ ድርጅቶች ለኪሳራ መጋለጣቸውን የገለፀው መረጃው መንግስት መፍትሄ እንዲሰጥበት በማለት ባለድርጅቶቹ ለሚመለከታቸው አካላት ጥያቄ ቢያቀርቡም። ችግሩን አይቶ መፍትሄ የሚሰጥ አካል ባለመገኘቱ ምሬታቸውን […]

በኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች የዝናብ ስርጭቱ በእጅጉ ዘግይቶ በመጀመሩ፤ በከብት እርባታ የሚተዳደሩ የአፋርና ኢሳ አካባቢዎች መጎዳታቸውን የማህበረሰቦቹ ተወካዮች ገለጹ። በድርቁ የተነሳ በአንዳንድ አካባቢዎች የሰዎች ህይወት መጥፋቱንና በርካታ እንስሳት መሞታቸውን፤ የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ከአፋርና ኢሳ ማህበረሰቦች መሪዎች ካገኘው መረጃ ለመረዳት ተችሏል። የፌዴራልና …

የክረምት ዝናብ ዘግይቶ መጀመሩ አሳሳቢ ሆኗል፤ በአፋርና ኢሳ አካባቢዎች ለ5 ወራት የዝናብ እጥረት ተከስቷል Read more »

ብክነቱን በአውራነት በማጋለጣቸው የታገዱት ተቆጣጣሪ የከፈሉትን መሥዋዕትነት አድንቋል የብር 110 ሚሊዮን ጭማሪ ሲደረግ ሀገረ ስብከቱ አያውቀውም፤ ሊቀ ጳጳሱም አልፈቀዱትም የብር 103 ሚ. ጠቅላላ በጀት በሚመደብበት ተቋም በብር 110 ሚ. አለመወሰኑ አነጋጋሪ ነው ግለሰቦችን በመጥቀም ራሱን ያበለጸገው አለቃው፣ አድባራትን ባለዕዳ በማድረግ ይታወቃል *           *           * የደብሩ ዋና ጸሐፊ በሀገረ ስብከቱ በዋና …

አርበኞች ግንቦት ሰባትን በ አሸባሪነት በምዕራባዊያን ዘንድ ለማስፈረጅ ያደረገው ከንቱ ውትወታ ያልሰመረለትና በተቃራኒው ጫናው የበረታበት ወያኔ የነጽነት ኮከቡን አንዳርጋቸው ጽጌ ሰውሮ ካስቀመጠበት ያፈና እስር ቤት ወደ ቃሊቲ ተዛውሮ መታየቱ ታወቀ። ከየመን አየር ማረፊያ ትራንዚት ላይ በወያኔ ደህንነቶች የታፈነው ታጋይ አንዳርጋቸው …

አንዳርጋቸው ጽጌ ቃሊቲ ማራሚያ ቤት ታዬ! Read more »

በምህራብ ዞን የሚገኙ የእስታፍ ሰራተኞች ወታደራዊ ሚስጥር አባክነዋል በሚል ለ8 ቀናት በስብሰባ ላይ ተጠምደው መሰንበታቸው ታወቀ።በምእራብ እዝ፤ በባህርዳር መኮድ በተባለው ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ የስርዓቱ የሰራዊት አባላት ወታደራዊ ምስጢር አባክናችኋል በሚል ሰበብ ለ 8 ቀናት ስብሰባ ላይ መቀመጣቸው የገለጸው መረጃው ነገር ግን በተካሄደው ስብሰባ ምንም አይነት ፍንጭ እንዳልተገኘና አመራሮቹ በራሳቸው ጥርጣሬ ብቻ ለ6 ሰው በቁጥጥር ስር […]

ዓለምአቀፍ ጉዞ ላይ ሳሉ ከየመን ዋና ከተማ ሰንዓ አይሮፕላን ጣቢያ ተጠልፈው ወደ ኢትዮጵያ የተወሰዱትና አሁን እሥር ላይ የሚገኙት የቀድሞ የግንቦት ሰባት ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲለቀቁ ለማድረግ እየጣረ መሆኑን ሪፕሪቭ የሚባለው ድርጅት ዳይሬክተር አስታውቀዋል፡፡ የሞት ፍርደኞችን ለማገዝና ለመደገፍ የሚሠራው …

አንዳርጋቸውን ለማስለቀቅ ሪፕሪቭ የሚባለው ድርጅት እየጣረ ነው – VOA Read more »

ዳግማዊ አቡነ ጴጥሮስ !እየመጡ ነው ! አቡነ መቃሪዮስ <<ልጆቼን ለማበረታታት ወደ በረሃ እደምወርድ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ ::>> ማለታቸውን ሰማን ::እኛም የዩንቨርስቲ ተማሪዎችን ከቅድስተ ማሪያም ቤተክርስቲያን በማስወጣት ለአግአዚ ክፍለጦር ካስረከቡት…ቢዮንሴ ለምትባል እራቁት ዳንሰኛ እና ዘፋኝ ታቦት አስወጥተው እሷንም በቤተ መቅደሱ ውስጥ ካንሸራሸሩት ሀውልት ከቆመላቸው አቡነ ጳውሎስና ለገፍዓን ጥብቅና ይቆሙ ይመስል የሚመለከታቸውን የቁልቢ ገብርኤል ያመት ንግስ ትተው የግብረ […]

ነኅሴ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተቃውሞው ሰልፍ መንስኤ ከገንዘብ ምንዛሬ ጋር የተያያዘ ሲሆን፣ ዛሬ ከቀኑ 8 ሰአት ተኩል ላይ በተፈጠረው ተቃውሞ ቁጥራቸው በውል ያልተወቀ ሰዎች ተደብድበው ሆስፒታል ገብተዋል። በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች በነጋዴዎች በኩል የሚልኩትን ገንዘብ ለማስቀረት ከፌደራል የመጡ ፖሊሶች እርምጃ መውሰዳቸው፣ ለተቃውሞ ሰልፉ መነሻ ምክንያት መሆኑን የሚናገሩት የአካባቢው ተወላጆች፣ …

ነኅሴ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢህአዴግ የድርጅት አባለት ግምገማ መጠናቀቁን ተከትሎ የግምገማ ውጤት እየወጣ ሲሆን፣ በዚህም ግምገማ መሰረት በርካታ የከተማዋ ወረዳ አመራሮች ከሃላፊነታቸው እንደሚነሱ ታውቋል። በጉለሌ ክ/ከተማ ስር ከሚገኙ ወረዳዎች ከ50 በላይ አመራሮች ፣ ከአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ደግሞ ከ20 በላይ የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ከሌሎች ክ/ከተሞች ከፍተኛ ቁጥር …

ነኅሴ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሩዝ በማምረት የሚታወቀው የፎገራ መስክ ለሸንኮራ አገዳ ተክል ሊውል ነው መባሉን ተከትሎ ፣ ሩዝ በማምረት ኑሮአቸውን የሚገፉ አርሶአሮች ስጋት ላይ ወድቀዋል። በጣና ሃይቅ ዳር የሚገኘው ሰፊው የፎገራ ረግራጋማ ሜዳ ከማዳበሪያ ነጻ ሆነ ሩዝ በማምረት የሚታወቅ ቢሆንም፣ ገዢው ፓርቲ በአገሪቱ የሚታየውን የስኳር እጥረት ለመፍታት በሚል ሰበብ አርሶአደሮችን …

ነኅሴ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢህአዴግ መንግስት በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ለመያዝ በሚል ስሌት የሚሰጠው የቤት መስሪያ ቦታ፣ ተመሳሳይ ጥያቄ ላቀረቡ ፣ በአገር ውሰጥ ለሚኖሩ ዜጎች ባለመስጠቱ፣ ቅሬታ እየተፈጠረ መሆኑን ዘጋቢአችን ገልጿል። መንግስት የዲያስፖራ ቀን ለማክበር በሚል ሰሞኑን በክልሎችና በአዲስ አበባ እንቅስቃሴ የጀመረ ሲሆን፣ ይህን ተከትሎ በተነሱት ውይይቶች ላይ ይህ የቅሬታ …

ነኅሴ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የብሔራዊ የሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ ኤልኒኖ ከግንቦት ወር 2007 ዓ.ም ጀምሮ በመከሰቱ በኢትዮጵያ በአብዛኛዎቹ አካባቢዎች የዝናብ ስርጭት መዛባት መከሰቱን፣ ከዚሁ ችግር ጋር ተያይዞ በቀጣይ ሁለት ወራትም የዝናብ መዛባቱ እንደሚቀጥል ይፋ አድርጓል። የኤጀንሲው ሃላፊዎች ትላንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በግንቦትና በሰኔ ወራት በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የተሻለ ዝናብ የነበረ ቢሆንም በሐምሌ …

ነኅሴ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከምርጫው ማግስት ከአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በፖሊስ ተይዘው የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እያንዳንዳቸው የ15 ሺህ ብር ዋስ ተጠይቆባቸዋል፡፡ አመራሮቹ ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ አራት ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፣ ፖሊስ በሽብርተኝነት ወንጀል እንደጠረጠራቸው ሲገልጽ ቆይቷል፡፡ ፖሊስ ‹‹ለግንቦት 7 አባላትን እየመለመሉ ይልካሉ፣ኤርትራ ድረስ ሄደው ስልጠና ወስደዋል፡፡›› የሚል ክስ …

ነኅሴ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ቅዳሜና እሁድ በተካሄደው አፍሪካ ፎረም ፌስቲቫል ላይ የተገኘው አስተባባሪ ኮሚቴ፣ ከምግብ፣ ከቡና፣ ከመጠጥ ሽያጭና ከተለያዩ ገቢዎች ያገኘውን ገንዘብ በኢሳት አካውንት ማስገባቱን ገልጿል። በእለቱ የኢሳት አላማ ለውጭ አገር ዜጎች ከማስተዋወቅ በተጨማሪ፣ ለኢሳት በቋሚነት ድጋፍ የሚያደርጉ አባላትንም መዝግቧል። በምግብ ዝግጅት ሴቶች ከፍተኛ ተሳትፎ ማድረጋቸውን የገለጸው አስተባበሪ ኮሚቴው፣ …

በቦረና ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን በኖኖ-አሎ ቀበሌ በሚኖሩ ዜጎች ላይ ባካባቢው የመንግሥት ባለሥልጣናትና ጥቂት ተባባሪዎቻቸው ብሄር-ተኮር ጥቃት ደርሶባቸዋል ሲል ሰ መ ጉ የተሰኘው የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ገለጸ። ጥቃቱ ብሄር-ተኮር ይሁን እንጂ የብሄር ግጭት አይደለም ሲሉ የ ሰመጉ ጽሕፈት ቤት …

በቦረና ክልል በኖኖ-አሎ ቀበሌ በሚኖሩ ዜጎች ላይ ጥቃት ተፈጸመ ሲሉ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድን ሀላፊ ተናገሩ Read more »

በከባድ ሙስና የተጠረጠሩ የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ባለሥልጣን በቁጥጥር ሥር ዋሉ

በመቶ ሚሊዮን ብሮች ተጠርጥረዋል

በከባድ ሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ላለፉት ሁለት ወራት ሲፈለጉ የቆዩት የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ቢራቱ፣ ነሐሴ 3 ቀን 2007 ዓ.ም.  በአዳማ ከተማ በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡

አቶ ወንድሙ በቁጥጥር ሥር የዋሉት በፌዴራልና በኦሮሚያ ክልል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽኖች ጥምረት ነው፡፡ በሁለቱ ፀረ ሙስና ኮሚሽኖች የተዋቀረው ግብረ ኃይል ተጠርጣሪውን ግለሰብ ነሐሴ 4 ቀን 2007 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ወንጀል ምድብ ችሎት በማቅረብ፣ የ14 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ ቢጠይቅም ፍርድ ቤቱ የ11 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

አቶ ወንድሙ የተጠረጠሩት የኦሮሚያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ በነበሩበት ወቅትና ከዚያ በኋላም የኦሮሚያ ክልል ብድርና ቁጠባ ተቋም ምክትል ኃላፊ ሆነው በሠሩባቸው ጊዜያት፣ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር የመንግሥት ገንዘብ በመመዝበር  የሙስና ወንጀል ነው፡፡

የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የሥነ ምግባር፣ ትምህርትና ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ አሰፋ፣ አቶ ወንድሙ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውንና በቁጥጥር ሥር ሊወሉ የቻሉት መንግሥት ማግኘት የነበረበትን በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ አሳጥተዋል በሚል ምክንያት መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

ከክልሉና ከፌዴራል ፀረ ሙስና ኮሚሽኖች የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው፣ አቶ ወንድሙ ምንጩ ያልታወቀ ከፍተኛ ሀብት፣ ለመንግሥት ገቢ መሆን የነበረበት ግብርና ታክስ፣ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ግዙፍ ኩባንያዎች የሰበሰቡትን ቫት ሆን ብለው ለመንግሥት ገቢ እንዳይሆን በማድረግና ጉቦ በመቀበል ወንጀል ተጠርጥረው ነው በቁጥጥር ሥር የዋሉት፡፡ ግለሰቡ የፌዴራል መንግሥትና የኦሮሚያ ክልል ማግኘት ያለባቸውን ገቢ አሳጥተዋል ተብለው ስለተጠረጠሩ ሁለቱ የፀረ ሙስና ኮሚሽን በትብብር መሥራት መጀመራቸው ታውቋል፡፡ ነገር ግን ተጠርጣሪውን ግለሰብ ለፍርድ ለማቅረብ በሚሞከርበት ወቅት ተጠርጣሪው በመሰወራቸው ከሁለት ወራት ፍለጋ በኋላ በአዳማ ከተማ መያዛቸው ታውቋል፡፡

አቶ ወንድሙ በራሳቸውና በቤተሰባቸው ስም ከፍተኛ ንብረት ማካበታቸው ምርመራ እንዲደረግባቸው መንስዔ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ ለሁለቱም የፀረ ሙስና ኮሚሽኖች በተለያዩ ጊዜያት በርካታ ጥቆማዎች ደርሰዋል ተብሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በተለይ በሻሸመኔና በምሥራቅ ሐረርጌ ቦርዶዴ አካባቢ የሚገኙ የጫት ኬላዎች ከግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን መንግሥት ማግኘት ያለበትን ገቢ ለግል ጥቅም ሲያውሉ ቆይተዋል የሚል ጥርጣሬ መኖሩን፣ የፀረ ሙስና ኮሚሽኖቹ መረጃ ያመለክታል፡፡

አቶ ወንድሙ የሥራ ጊዜውን ባጠናቀቀው የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት (ጨፌ) አባል ነበሩ፡፡ ኦሕዴድ አቶ ወንድሙን በ2007 ዓ.ም. ጠቅላላ ምርጫ ዕጩ አድርጎ እንዳላቀረባቸው ታውቋል፡፡ በዚህ መሠረት አቶ ወንድሙ ያለመከሰስ መብት የሌላቸው በመሆኑ የፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር እንዳዋሏቸው ተገልጿል፡፡

አቶ ወንድሙ የኦሮሚያ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ሆነው ለአምስት ዓመታት ሠርተዋል፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት የኦሮሚያ ብድርና ቁጠባ ተቋም ምክትል ኃላፊ ሆነው ሲሠሩ ቆይተው፣ ከ30 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ሕገወጥ ግዥ ተጠርጥረው ከወራት በፊት ከምክትል ኃላፊነታቸው መነሳታቸው ታውቋል፡፡

 

የወያኔ ብሔራዊ መረጃ የተባለ ጽንፈኛ ቡድን የነጻነት ታጋዮችን ስም በተልያየ መንገድ ለማጥቃት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የሚጠቁሙ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ። በተለይም በዉጭዉ አለም ላይ የሚገኙ ስደተኞችን ቀንደኛ ተጠቂ ለማድረግ የተነሳዉ የብሐራዊ መረጃ ቡድን በትናንትናዉ እለት መጋለጡን የዉስጥ ምንጮች ጠቁመዋል። ከዚህ ቀደም ብሎ በደረሰን መረጃ መሰረት ህዝባዊ ወያኔ ሔርነት ትግራይ ብሔራዊ መረጃ ቡድን የነጻነት ታጋዮችን ለማጥቃት ከሚጠቀምባቸዉ መንገዶች […]

የ 11 % ዲጂታል እድገት ውጤቱ ይህ ነው እንዴ? ወይ ልማታዊ መንግስት  ህዝብን ያላሳተፈ እና በጥቂት ራስ ወዳድ አምባገነን እና ዘረኛ የግለሰቦች ቡድን የምትማራ ሃገር እድገቷም ለጥቂቶች ሆዳሞች እንጂ ለመላው ህዝብ አይደለም Nightly News   |  August 12, 2015 Food crisis in Ethiopia Aug. 5: Hunger is once again threatening vast swathes of Africa because of drought […]

ስብሰባው ከአርባ ሰባት ሃገራት የተሰባሰቡ የኦሮሞ የዲያስፖራ አባላትን የአርባ ሰባቱ ሃገሮች ዲፕሎማቶች በተገኙበት ተካሂዷል ። መንግስት የኦሮሞ ዲያስፖራ ሳምንት ብሎ የሰየመውን ሳምንት በማስመልከት: ከመላው አለም ያሰባሰባቸውን የኦሮሚያ ዲያስፖራ አባላት: በሚሊኒየም አዳራሽ ጠቅላይ ሚስትሩ በተገኙበት ደማቅ የአቀባበል ስነ ስርዓት ካደረገላቸውና : ለሶስት ቀናት ያክል ሃገሪቷን ካስጎበኛቸው በኃላ : በአዳማ ገልማ አባገዳ አዳራሽ በመሰብሰብ : የተለመደ ፕሮፓጋንዳውን […]

ከሳምንታት በፊት ልደታ ፍርድ ቤት በአንድ ችሎት በአጋጣሚ ሁለት የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎችን ተከታተልኩ፡፡ ሁለቱም እስረኞች ዝዋይ ሆነው በፕላዝማ ይግባኝ እየጠየቁ ነው፡፡ አንዱ ህፃን ደፍሯል ተብሎ 2 አመት ከምናምን ብቻ ተፈርዶበታል፣ ሌላኛው ደግሞ በህፃን ላይ መድፈር የሚመስል ወንጀል ፈፅመሃል ተብሎ አራት አመት ተፈርዶበታል፡፡ መጀመሪያ ህፃን ደፍረሃል ተብሎ 2 አመት መፈረዱ ገረመኝ፡፡ ህፃን ላይ መድፈር የሚመስል ወንጀል […]

የፖለቲካ አመራሮች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በጻፉት ደብዳቤ አቶ አንዳርጋቸው ለብቻቸው 24 ሰአት የተፈጥሮ ብርሀን በማያገኙበት ሁኔታ እስር ላይ መሆናቸውን እንደጠቀሱ አልጀዚራ በብቸኝነት ማግኘት ችያለሁ ያለውን መረጃ ዋቢ በማድረግ አስነብቧል። ለኢትዮጵያ መንግስት ጥያቄያቸው ያቀረቡት እነዚህ አካላት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የያዙበት ሁኔታ አሳሳቢ እና በሀገሪቱን ከአለም አቀፍ ማህበረሰብ የሚነጥል እንደሆነ ገልጸዋል። በአሜሪካ የውጪ ጉዳዮች ኮሚቴ አባል እና የካሊፎርኒያ […]

ሞኒካ ራየንስ በአሜሪካ የደቡብ ካሮሊና ነዋሪ ስትሆን ባለፈው አርብ አንድ በህግ ጥላ ስር የሚገኝ ወዳጇን ለመጠይቅ ወደ ዩኒየን እስር ቤት መጽሐፍ ቅዱስን ይዛ ጎራ ትላልች ። የ24 አመቷ ሞኒካ የእግዜአብሔር ቃላት ያለበት ፣ በሃዘን እና በመከራ ወቅት አጽናኝ የሆነው መጽሐፍ ቅዱስን ይዛ እስረኛው ዘመዷን መጠየቋ የተባረከ ሐሳብ ነበር ። በተጠቀለለ ወረቀት ሽፋን ላይ “መጽሐፍ ቅዱስ […]

በዘንድሮው ክረምት የተፈጠረው የዝናብ እጥረት አሉታዊ ተፅዕኖዎችን እያሳደረ ነው

ለከብቶች መሞትና ለሰብል ውድመት ምክንያት ሆኗል

-ችግሩ አሳሳቢ በመሆኑ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ ብሔራዊ ኮሚቴ ተቋቁሟል

በአገሪቱ አብዛኛዎቹ አካባቢዎች በዘንድሮው የክረምት ወቅት የተከሰተው የዝናብ እጥረት አሉታዊ ተፅዕኖዎችን እያሳደረ መምጣቱን፣ የብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ ይፋ አደረገ፡፡

ዘግይቶ የመጣው የነሐሴ ዝናብ ሥርጭት መሻሻል እንደሚታይበት ገልጿል፡፡

ችግሩ ስለመከሰቱ ለመንግሥት ካሳወቀ ከሁለት ወራት በኋላ በይፋ በሰጠው መግለጫ የዝናብ እጥረቱ በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍሎች መታየቱን ገልጾ፣ ይህም በእርሻ ሥራ አጀማመር፣ የዘር ጊዜን በማስተጓጎልና የሰብል ውኃ ፍላጎትን ባለማሟላትና በመሳሰሉት ተፅዕኖዎቸ እንዲጠናከሩ አድርጓል በማለት አስታውቋል፡፡ 

ነሐሴ 5 ቀን 2007 ዓ.ም. በኤጀንሲው የሥራ ኃላፊዎች በተሰጠው በዚሁ መግለጫ የዝናብ እጥረቱ ተፅዕኖ በሰብል ልማት ላይ ብቻ ሳይሆን፣ በተለይ በክረምት ወቅት በአገሪቱ ግድቦች መግባት የነበረበት ውኃ እንዲቀንስ ምክንያት መሆኑን አስታውቋል፡፡ የዝናብ እጥረት በየወንዞቹ የሚፈሰው ውኃ ዝቅ እንዲል፣ እንዲሁም በሜዳማና በረግረጋማ መሬት ላይ መተኛት የነበረበት የውኃ መጠን መቀነስ ጎልተው ከታዩ ክስተቶች ውስጥ እንደሚካተቱ ተጠቅሷል፡፡ 

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈጠነ ተሾመ እንደገለጹት፣ በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍል የታየው የዝናብ እጥረት በተለይ በሐምሌ ወር ጎልቶ ታይቷል፡፡ በሰኔ ወር የነበረው የዝናብ አጀማመር የተሻለ መጠንና ሥርጭት ቢኖረውም፣ በሐምሌ ግን የተዳከመ ገጽታ ስለነበረው በበርካታ የአገሪቱ አካባቢዎች ላይ ዝናብ እጥረት መከሰቱን፣ ይህም አሉታዊ ተፅዕኖዎች እንዳሳደረ ገልጸዋል፡፡

የዝናብ እጥረቱ ስላሳደረው ተፅዕኖ የኤጀንሲው ኃላፊዎች ዝርዝር ማብራሪያ ባይሰጡም፣ የዝናብ እጥረቱና የታየው ድርቅ ለሰብል መጥፋትና ለእንስሳት ሞት ምክንያት መሆኑን ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ ከአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በ31 ወረዳዎች ላይ ድርቅ ተከስቷል፡፡

በአንዳንድ ወረዳዎች እስከ 240 የሚደርሱ ፍየሎችና ግመሎች መሞታቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች እንደደረሰም የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ባለሙያ አቶ ኡስማን ኢድሪስ ሙሳ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅትም አደጋውን ለመከላከል የክልሉ መንግሥት፣ በፌዴራል መንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በጥምረት የፈጠሩት ኮሚቴ እየተንቀሳቀስ ነው ተብሏል፡፡ የተወሰኑ አርብቶ አደሮችም ከብቶቻቸውን የተሻለ አየር ንብረት ወዳለበት አካባቢዎች እየወሰዱ ነው፡፡ 

የብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በአፋር አካባቢ ስለተከሰተው ችግር ሲያብራሩ፣ ‹‹በአፋር ክልል ዝናብ ማግኘት በነበረበት ወቅት አላገኘም፡፡ ይህ ትክክል ነው፤›› ብለዋል፡፡

‹‹አሁን ግን በሥርጭትም በሽፋንም የተሻለ ዝናብ በመኖሩ እዚያ አካባቢ ባሉ ግድቦች ውኃ ለመያዝ ያስችላል፡፡ ይህም ከዚህ በኋላ ሊመጣ የሚችለውን ተፅዕኖ መቀነስ የሚያስችል ነው፤›› ሲሉም አክለዋል፡፡ 

በሌላ በኩል ከዝናብ እጥረት ጋር ተያይዞ በተፈጠረው ችግር ተጎጂ ከሆኑ አካባቢዎች መካከል የአርሲ ዞን ዶዶታ ወረዳ አንዱ መሆኑን የሪፖርተር የመስክ ቅኝት አመላክቷል፡፡ ከሌላው ጊዜ በተለየ የተፈጠረው የዝናብ እጥረት በወረዳው ውስጥ ያሉትን ቀበሌዎች በሙሉ ያዳረሰ መሆኑን የወረዳው ግብርና ቢሮ ገልጿል፡፡ የዝናብ እጥረቱ በግንቦት ወር ከ2,370 ሔክታር በላይ በቆሎ የተዘራበት ማሳ እንዲጠፋ ምክንያት እስከመሆን መድረሱንም፣ የወረዳው የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ጀማል ኑራ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

በዝናብ እጥረቱ ምክንያት ለከብቶች መኖ እጥረት በመፈጠሩ አብዛኛዎቹ አርሶ አደሮች ለመጠባበቂያ ያስቀመጡትን መኖ እንዲጠቀሙ አስገድዷቸዋል፡፡ አንዳንዶችም በዚህ ወቅት ለከብቶቻቸው ይሆን የነበረው ሣርና የበቆሎ አገዳ በዝናብ እጥረቱ ምክንያት ባለማግኘታቸው፣ መኖ ወደ መግዛት እንዳስገባቸው ሪፖርተር ያነጋገራቸው አርሶ አደሮች ገልጸዋል፡፡

የዘንድሮው የክረምት ወቅት ዓለም አቀፍ ክስተት የሆነው የኤልኒኖ ተፅዕኖ ሥር በመውደቁ የተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የዝናብ እጥረት ማጋጠሙን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ እጥረቱም በቦታ በጊዜና በመጠን የተለያየ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡ አሁን ግን የተስተካከለ ዝናብ እየተገኘ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ተመሳሳይና አንድ ዓይነት እጥረት እንዳላጋጠመ፣ በአንፃራዊነት የተሻለ ዝናብ ያገኙ አካባቢዎች እንዳሉ ሁሉ በዚያው ልክ እጥረት ያጋጠማቸው እንዳሉ ለመገንዘብ እንደተቻለ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡ የኤጀንሲው የሚቲዎሮሎጂና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ድሪባ ቆርቻ፣ በዚህ ወቅት የተፈጠረው ችግር ከኤሊኒኖ ጋር የተያያዘ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከዚህ በኋላ በቀጣዮቹ ሁለት ወራት የተሻለ ዝናብ ቢጠበቅም በአሁኑ ጊዜ እየተጠናከረ ከመጣው የኤልኒኖ ክስተት ጋር ተያይዞ በቀሪዎቹ ነሐሴና መስከረም በመደበኛ ሁኔታ የሚኖረው የዝናብ መጠንና ሥርጭት የተዛባና ያልተስተካከለ እንደሚሆንም፣ ኤጀንሲው ባወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡ 

የዝናብ እጥረቱ ተከስቶባቸዋል ብለው በምሳሌት ከጠቀሷቸው አካባቢዎች መካከል በትግራይ፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በአፋር፣ በሱማሌ አንዳንድ ቦታዎች እጥረቱ በቀጥታ ከኤልኒኖ ጋር በተያያዘ የተፈጠረው ችግር እንደሆነም ታውቋል፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ ተመሳሳይ የአየር ንብረት ያላቸውና በምድር ወገብ አካባቢ ባሉ አገሮችም የታየ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ 

 በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍሎች የተከሰተውን የዝናብ እጥረትና ሥጋት የታወቀው ቀደም ብሎ ቢሆንም፣ መረጃው ዘግይቶ መነገሩ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ በተለይ ብሔራዊ ሜቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ አሁን የሰጠው መረጃ የዘገየ ነው የሚል ጥያቄ አስነስቶበታል፡፡ የኤጀንሲው ኃላፊዎች ግን መረጃው ዘግይቷል የሚለውን ትችት አልተቀበሉትም፡፡ ኤጀንሲው የክረምቱን ወቅት የተመለከተ ዝርዝር መረጃውን በግንቦት ወር መስጠቱን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ከመረጃው በኋላም ላለፉት ሁለት ወራት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ሲሠሩ መቆየታቸውን አስረድተዋል፡፡ 

ምክትል ዳይሬክተሩ አቶ ዱላ ሻንቆ ኤጀንሲው እያንዳንዱን መረጃ በተለያዩ መንገዶች ሲያቀርብ ስለነበር መረጃውን ለመስጠት መዘግየት ታይቷል የሚለውን ሐሳብ ሳይቀበሉት ቀርተዋል፡፡ ችግሩ መኖሩን በግንቦት ወር ማስታወቃቸውንና የየዕለቱን የአየር ፀባይ መረጃ በመመዝገብና በቀጣይ ሊኖር የሚችለውን ሁሉ በማጠናቀር፣ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ጀምሮ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት በሙሉ ማሠራጨቱንም ገልጸዋል፡፡

በዚሁ በመረጃ መሠረት ያለውን ሥጋት እንዴት ለመፍታት እንደሚቻልና መንግሥት ዝግጅት እያደረገ መቆየቱን፣ በብሔራዊ ደረጃ የአደጋ መከላከል ኮሚቴም መቋቋሙ ተገልጿል፡፡ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሚመራው ይህ ብሔራዊ የአደጋ መከላከል ኮሚቴ ውስጥ በዋናነት የተካተቱትም ብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ፣ ግብርና ሚኒስቴር፣ የአደጋ መከላከል ዝግጁነትና የምግብ ዋስትና ቢሮ፣ የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ናቸው፡፡ ይህ ኮሚቴ ሰፊ ርቀት መጓዙን አቶ ፈጠነ ገልጸው፣ ‹‹ጉዳዩ በደንብ ታስቦበት እየተሠራበት ነው፤›› ብለዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ከችግሩ አሳሳቢነት አንፃር ኤጀንሲው በየክልሉ ያሉት የቅርንጫፍ የሥራ ኃላፊዎቹ ከየክልሉ ፕሬዚዳንቶች ጋር በቀጥታ በመገናኘት መረጃ እንዲሰጡ ጭምር እየተደረገ ነው ተብሏል፡፡ በይፋ ጋዜጣዊ መግለጫ አልተሰጠበትም እንጂ ሊኖር የሚችለውን ችግር በቅድሚያ በማሳወቅ በጋራ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ሊከሰት ይችላል ተብሎ ከተተነበየው መረጃ አንፃር መንግሥት ሰፊ ዝግጅት እንዲያደርግ ኤጀንሲው መምከሩን፣ የግብርና ዘርፎች በየደረጃው በመዋቅራቸው መሠረት አርሶ አደሮች ዘንድ እንዲደርሱም ከፍተኛ ጥረት መደረጉን ገልጸዋል፡፡ 

የኤጀንሲው ዋና ተግባር ትንበያና የምክር አገልግሎት መስጠት መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ቅድመ ማስጠንቀቂያዎችን ጉዳዩ የሚመለከታቸው የውሳኔ ሰጪ አካላት እንዲጠቀሙበት እያደረገ ነው ብለዋል፡፡

አሁን የታየው የአየር ለውጥ የሚያሳርፈው ተፅዕኖ ቀላል ያለመሆኑን ለመግለጽ፣ ‹‹ተፅዕኖው በአንድ አርብቶ አደርና በአርሶ አደር ላይ የሚገለጽ ሳይሆን በጤና ረገድም የራሱ የሆነ ተፅዕኖ ያሳድራል፤›› ብለዋል፡፡ 

የሚታየው ሙቀት እየተጠናከረ በሚሄድበት ጊዜ በአየር ለውጡ ምክንያት የሚወለዱ በሽታዎችን ጭምር የሚያስፋፋ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ፣ ከጤና ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ጋር ኤጀንሲው እየሠራ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡ 

የዝናብ እጥረቱም ሆነ የአየር ለውጡ ሌሎች ተፅዕኖዎችን ሊያሳድሩ እንደሚችሉ የኤጀንሲው ኃላፊዎች አስረድተዋል፡፡ የአየር መዛባቱ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከባድና ቅፅበታዊ ዝናብ፣ ጎርፍና የወንዞች ሙላትን አስከትሏል ተብሏል፡፡ 

በቀጣይ ወራትም ተመሳሳይ ችግር ሊኖር የሚችልበት ዕድል አንደሚኖር ያመለከቱት ዶ/ር ድሪባ፣ በአንዳንድ አካባቢዎች በአጭር ቅጽበት ከ50 እስከ 80 ሚሊ ሊትር ዝናብ መመዝገቡን አስታውሰዋል፡፡ በቀጣዮቹ ሁለት ወራት በተለይ በነሐሴ ወር የተሻለ ዝናብ ሊኖር ይችላል የሚል ግምት ያላቸው ዶ/ር ድሪባ፣ በበጋ በአንድ በኩል ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በደረሱ ሰብሎች ላይ ተፅዕኖ እንደሚኖረው፣ በሌላ በኩል ግን ዝናቡ አዎንታዊ ገጽታ እንደሚኖረውም ያስረዳሉ፡፡ አሁን በተተነበየው መረጃ መሠረት በመጪው በጋ ዝናቡ የሚኖረው ደግሞ የጎርፍና የወንዞች ሙላትን ሊያስከትል እንደሚችልም ተገልጿል፡፡ 

ከኤልኒኖ ወይም ከሌሎች ክስተቶች ጋር ተያይዞ በአገሪቱ ሊከሰቱ የሚችሉትን ከመደበኛ ወጣ ያሉ የአየር ሁኔታና ፀባይ፣ ክስተቶችንና ተፅዕኖዎችን የዕለት ተዕለት ክትትል በማድረግ መረጃዎችን ለተጠቃሚዎች እንደሚሰጥም ኤጀንሲው አስታውቅል፡፡ አሁን ያለው ችግር ተፅዕኖ ያለው መሆኑ ባይካድም፣ ሰሞኑን የታየው ዝናብ ፍራቻ ያሳደረውን ድርቅ እንዲቀንስ ያደርጋል የሚል ተስፋ እንዳለ ኃላፊዎቹ ጠቁመዋል፡፡ 

ሰሞኑን የታየው ዝናብ ተስፋ ሰጪ ቢሆንም አሁንም እስከታች ድረስ ሊከናወኑ ይገባቸዋል የተባሉ ጥንቃቄዎችም ተጠቁመዋል፡፡ በተለይ የሚገኘውን ውኃ በተቻለ መጠን መያዝ አስፈላጊ ነው ተብሏል፡፡ ኤጀንሲው ሊፈጠር የሚችለውን ሥጋት ሲገልጽ፣ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ሰብሎቻቸውና እንስሳቶቻቸው እንዳይወድሙና እንዳይሞቱ ለምን አልተደረገም ለሚለው ጥያቄ፣ በኤጀንሲው ኃላፊዎች ምላሽ ሳይሰጥበት ታልፏል፡፡ 

 

ሰባት ደላሎች በቁጥጥር ሥር ሲውሉ በአንዱ ላይ ክስ ተመሠረተ

ወደ ተለያዩ ዓረብ አገሮች የሚሄዱ ኢትዮጵያውያንን ሞት፣ አካል መጉደልና እንግልትን እየደረሰባቸው በመሆኑ መንግሥት እንዳይሄዱ ዕግድ የጣለ ቢሆንም፣ በተለይ ቀደም ብሎ ስደት በማይታወቅባቸው ገጠራማ አካባቢዎች ቁጥራቸው

ከፍተኛ የሆኑ ወጣቶች በሕገወጥ መንገድ እየተሰደዱ መሆኑን፣ መንግሥት ሐምሌ 4 ቀን 2007 ዓ.ም. አስታወቀ፡፡

ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ተከላካይ ብሔራዊ ምክር ቤት የ2007 ዓ.ም. ዕቅድ አፈጻጸምን አስመልክቶ ባደረገው ግምገማ፣ በፌዴሬሽን ምክር ቤት ተሰብስበው ለነበሩ ባለድርሻ አካላት እንደተገለጸው፣ ሕገወጦችን መከላከል የሚያስችል እስከ ሞት ድረስ ቅጣት የሚጥል ሕግ ከማውጣት ባለፈ፣ ለማስፈጸም ተግቶ የሚሠራ አካል ባለመኖሩ ችግሩን ማቆም እንዳልተቻለ ተገልጿል፡፡

በአማራ፣ በትግራይ፣ በኦሮሚያና በደቡብ ክልሎች በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ ጥሩ ሥራ የተሠራና የተሻለ ውጤትም የታየበት መሆኑን የገለጹት የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኰንን፣ የሕገወጥ ደላሎች አሠራር በየጊዜው ስለሚቀያየር የዜጐች ጉዳት እየጨመረ መምጣቱንና የተደረገውም ጥረት አርኪ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዜጐች ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳትና አደጋ የሚመጥን እንቅስቃሴ አለመደረጉን የተናገሩት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህ የሚያሳየው የሕገወጥ ደላሎቹ መተላለፊያ የሆኑት ክልሎች፣ መንግሥትና ኅብረተሰቡ ባለመግባባታቸው ነው ብለዋል፡፡ በአገራቸው ሠርተው መለወጥ የሚችሉ በርካታ ዜጐች ለከፋ ጉዳት እየተዳረጉ መሆናቸውንም አክለዋል፡፡ በዜጐች ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት የአገርን ገጽታ ጭምር የሚያበላሽ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ 

በቱሪስት ቪዛ እየተሰደዱ ያሉት ዜጐች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱንና ዕግድ በተጣለባቸው ኳታርና የመን ሕጋዊ ሽፋን እየተሰጣቸው ለከፋ አደጋ እየተጋለጡ የሚገኙ ዜጐች ጉዳይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የገለጹት ደግሞ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ሰለሞን ተስፋዬ ናቸው፡፡ ሕገወጥ ደላሎችን ወደ ሕግ ለማቅረብ የተቀናጀ አሠራር የሚያስፈልግ ቢሆንም፣ እስካሁን ክልሎችም ሊተገብሩት ባለመቻላቸው አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ጠቁመዋል፡፡

አቶ ደመቀ ሕገወጥ ደላሎች ባለሁለት ፎቅ ሕንፃ በመገንባት ሀብታቸውን ሲያፈሩ፣ በሕገወጥ ደላሎችና የጉዞ መስመር የሄዱ ወጣቶች ግን የአውሬ ሰለባ እየሆኑ እንደሆነ ጠቁመው፣ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ተባብሮ ሊታገል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ መንግሥት በተለይ በኢትዮጵያውያን ላይ የሳዑዲ ዓረቢያ ዜጐች ግድያ፣ አካል ማጉደልና ከፍተኛ እንግልት ካደረሱ በኋላ በሕጋዊ መንገድ ፈቃድ አውጥተው የውጭ አገር ሥራና አሠሪን የሚያገናኙ ኤጀንሲዎች ሥራቸውን እንዲያቆሙ በመደረጉ፣ በከፍተኛ ችግር ውስጥ መሆናቸውን እየገለጹ ይገኛሉ፡፡

መንግሥት በአጭር ጊዜ አሠራሩን አስተካክሎ ኤጀንሲዎቹ ሥራቸውን እንደሚቀጥሉ የገለጸ ቢሆንም፣ የቤት ኪራይና የሠራተኛ ደመወዝ እየከፈሉ ከነገ ዛሬ ሥራ እንደሚጀምሩ የሚጠባበቁ ቢሆንም፣ መንግሥት ስለነሱ ምንም ሳይባልና የስብሰባው አካልም ሳያደርጋቸው መቅረቱ እንዳሳዘነው የኤጀንሲዎች ማኅበር ገልጿል፡፡ ብሔራዊ ምክር ቤቱ እንዳረጋገጠው፣ በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ ዜጐች እየተሰደዱ መሆኑን የሚናገሩት ኤጀንሲዎቹ፣ ሕንፃ መገንባት ብቻ ሳይሆን ሌሎች ከፍተኛ ሀብቶችን ሕገወጥ ደላሎች እያከማቹ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ሥራ በመሰማራት የተጠረጠሩ ሰባት ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ፖሊስ አስታውቋል፡፡ የፌዴራል ፖሊስ ከዓለም አቀፍ የፖሊስ ድርጅት (ኢንተርፖል) ጋር በመተባበር ባደረገው ክትትል ኬንያ፣ ታንዛኒያና ሱዳን ውስጥ የነበሩት እነዚህን ሕገወጥ ደላሎች ወደ ኢትዮጵያ እንዳስመጣ ተገልጿል፡፡ በሌሎች አገሮች በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሕገወጥ ደላሎች አገር ውስጥ ካሉ ደላሎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ በሕገወጥ መንገድ በርካታ ዜጐችን ወደ ተለያዩ አገሮች ይልኩ እንደነበር የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ዘርፍ የሕገወጥ ሰዎች ዝውውር ወንጀል ምርመራ ዲቪዚዮን ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ወንድሙ ጨማ ተናግረዋል፡፡

በቦሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ ነዋሪ መሆኑ የተገለጸው አቶ መሐመድ ሐሰን የተባለ ተጠርጣሪ ደላላ ደግሞ፣ ሰባት ወጣቶችን በሱዳንና በሊቢያ አድርጐ ወደ አውሮፓ እንደሚልካቸው በማነጋገር፣ ከጅግጅጋ ወደ አዲስ አበባ አምጥቷቸው አዲስ አበባ ላይ በቁጥጥር ሥር ውሎ ክስ ተመሥርቶበታል፡፡ ግለሰቡ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ሁለተኛ ወንጀል ችሎት ስምንት ክሶች የተመሠረተበት ሲሆን፣ የዋስትና መብቱን ተነፍጐ በማረሚያ ቤት እንዲቆይ ተደርጓል፡፡ 

ግለሰቡ ሐረር ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ግብረ አበሮቹ ጋር በመቀናጀት፣ ሰባቱን ወጣቶች ከጅግጅጋ ወደ አዲስ አበባ አስመጥቶ ካዛንችስ አካባቢ በአንድ ሆቴል ውስጥ አልጋ ከያዘላቸው በኋላ፣ ማንም ቢጠይቃቸው ኢትዮጵያዊ እንዳልሆኑ እንዲናገሩ በማስጠንቀቅና ኢትዮጵያዊ መሆናቸው ከታወቀ ለስደት የመጡ መሆናቸው እንደሚታወቅና ሊታሰሩ እንደሚችሉ በመንገር፣ መታወቂያቸውን መፀዳጃ ቤት ውስጥ እንዲከቱ ማድረጉን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡ 

ዓቃቤ ሕግ ስምንት ክሶችን የመሠረተበት አቶ መሐመድ፣ ወጣቶቹን ለመምከርና ለማስጠንቀቅ ያደረገው ሙከራ ብዙም ቀናት ሳይጠቀምበት በቁጥጥር ሥር መዋሉን ክሱ ይገልጻል፡፡ በሱዳንና ሊቢያ አድርገው ጣሊያን እንደሚገቡ የተነገራቸው ወጣቶቹ፣ ለጉዞው የሚጠበቅባቸውን ክፍያ ሊቢያ ሲደርሱ ለቤተሰቦቻቸው በመደወል፣ እንዲልኩላቸው እንደሚያደርጉ ተስማምተው እንደነበር ክሱ ይገልጻል፡፡ ተከሳሹ ድርጊቱን እንዳልፈጸመ የገለጸ ቢሆንም፣ ዓቃቤ ሕግ አራት ምስክሮችን አሰምቶ ፍርድ ቤቱ እንዲከላከል ብይን በመስጠት፣ ለጥቅምት 30 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጥሮታል፡፡      

 

ነኅሴ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን በኖኖ አሎ ቀበሌ የሚገኙ ባለስልጣናት እና የጸጥታ ሃላፊዎች ‘ እናንተ የዚህ አካባቢ ተወላጆች ሳትሆኑ ሀብት እያፈራችሁ የአካባቢው ተወላጆች ግን ከናንተ ያነሰ ገቢ ነው ያላቸው…ይህን ገቢ ያገኛችሁት በኛ መሬት ነው፤ ስለዚህ የክልሉ ተወላጆች ባለመሆናችሁ ክልሉን ለቃችሁ ውጡ’ በማለት ቤታቸውን በማቃጠልና ንብረታቸውን በመንጠቅ …

ነኅሴ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስር የሚታተመው ሳምንታዊ የሰብአዊ እርዳታ መጽሄት እንደዘገበው መንግስት በአገሪቱ ውስጥ የታየውን የምግብ እጥረት ለመቅረፍ ለጋሽ አጋራት አስቸኳይ እርዳታ እንዲለግሱ ጥሪ አቅርቧል። ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ ሊፈጠርባቸው ይችላል ተብሎ ለተሰጋባቸው ቦታዎች መንግስት 700 ሚሊዮን ብር መመደቡን አስታውቋል። ዞን 3 በሚባለው የአፋር አካባቢ እንዲሁም ስቲ ዞን …

ነኅሴ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አይ ኤስ አይ ኤስ በኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመውን አሰቃቂ ግድያ ለመቃወም መንግስት በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ሰበብ የታሰሩት እነ ማቲያስ መኩሪያ፣ ፖሊስ በጊዜ ቀጠሮ ወቅት ‹‹የቪዲዮ ማስረጃም አለን›› በማለቱና ተከሳሾቹ ‹‹ቪዲዮው ይቅረብልን፣ የቪዲዮ ማስረጃው ለእኛም የመከላከያ ምስክርነት ይጠቅመናል›› ብለው በመጠየቃቸው፣ ፍርድ ቤቱ የቪዲዮ ማስረጃው መቅረብ እንዳለበትና እንደሌለበት ብይን …

ነኅሴ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሽብር ወንጀል ተከሶ ቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኘው አበበ ካሴ ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመበት ታወቀ አበበ ካሴ፣ በማእከላዊ እስር ቤት የሁሉም ጣቶቹ ጥፍሮች ተነቅለው፣ በዘር ፍሬው እና በመላ አካላቱ ላይ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞበት መረጃ ለማውጣት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቶ በመጨረሻ ቂሊንጦ እስር ቤት ከተወረወረ በሁዋላ፣ የደረሰበትን ችግር ሁሉ ዘርዝሮ …

ነኅሴ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ባለስልጣናትና የሶማሊያ መንግስት ባለስልጣናት በሂራን ክልል ቡሎ ቡርዴ እና በለድ ወይኔ ከተማ ውስጥ ከአካባቢው የአገር ሽማግሌዎች ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ሽማግሌዎቹ፣ ከአምስት በላይ ንፁሃን የሶማሊያ ዜጎች በኢትዮጵያ ወታደሮች በግፍ መገደላቸውን ተናግረዋል። የሶማሊያ ምክትል የመከላከያ አዛዥ መሀመድ አደን ግድያው መፈፀሙን አምነው የአፍሪካ ህብረት ባለስልጣናት ይቅርታ …

ኢሳት ዜና :-በትግራይ እና በአማራ ክልል ገዢዎች መካከል ያለው አለመግባባት በተለያዩ አጋጣሚዎች ከፍ ዝቅ ሲል ቆይቶ ፣ ሰሞኑን ኢህአዴግ በአካሄደው ግምገማ ላይ እንደገና አገርሽቶበታል። የትግራይ ክልል ገዢ አቶ አባይ ወልዱ የተወሰኑ የህወሃት ደጋፊዎችን በመያዝ በሁለቱ ክልሎች መካከል ስላለው አወዛጋቢ መሬት ፣ ከአማራ ክልል ገዢ ጋር በድንበር አካበባ ያደረጉት ውይይት፣ በዘለፋና በጸብ ከተቋጨ ከወራት በሁዋላ፣ በሰሞኑ […]

የወያኔ መንግስት ወታደራዊ ደህንነት ቢሮ ከፍተኛ ስጋት ላይ መዉደቁን እናዳሳወቀ ከዉስጥ የወጣ መረጃ አመለከተ። በተለይም በትግራይ እና በሱዳን በኩል እየተጠናከረ የመጣዉ የአርበኞች ግንቦት 7 እና የኦነግ ጥንካሬ በተለይም ዉስጥ ለዉስጥ የሚደረጉ ሽምቅ ዉጊያዎች እየተበራከቱና የትጥቅ ትግሉን የመረጡ እነዚህ ሐይሎች በአጭር …

የወያኔ መንግስት ወታደራዊ ደህንነት ቢሮ ከፍተኛ ስጋት ላይ መዉደቁን እናዳሳወቀ ከዉስጥ የወጣ መረጃ አመለከተ Read more »

-በኣራት ቀና ዝግጅቱ ላይ ተሳታፊ የሚሆኑ ሰዎች መሬት ይሰጣችዋል -የኮንዶሚንየም ቤት እና ሌሎችንም ጥቅሞች ታገኛላችሁ የሚል ፕሮፓጋንዳ በመንግስት ካድሬዎች በስፋት እየተካሄደ ነው ይህን ልፈፋ የሰሙ ታዛቢዎች ቤት ያጡ በየጎዳናውና በችግር የሚኖሩ ብዙ ዜጎች እያሉ ስብሰባዬን ኣጫፈራችሁ ተብሎ ይህ ነገር በመባሉ ስር፡ኣቱ ሆዳሞች በጥቅም ከመሰብሰብ በቀር እየሞተ እንዳለ እና ኣላማ እንደሌለው ሲናገሩ ተደምጠዋል ይህ የዲያስፖራ ቀን […]

የምዕራብ ጎጃም የብአዴን አመራርና አባላት ከሀምሌ 29 እስከ ነሀሴ 1 2007 ዓ.ም ባካሄዱት ስብሰባ ላይ ነው መከፋፈሉ ሊከስት የቻለው፡፡ የምዕራብ ጎጃም የብአዴን የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ሀብታሙ፣ የዞኑ ምክትል ከንቲባ አስፋው ገበየሁና የወረዳው የብአዴን ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አላምር ተሻለ የተባሉ የህወሓት አገልጋይ የመሩት በዱላ ቀረሽ ስድድብ፣ እርስበርስ መወነጃጀልና የተደበቀ ገመናን በመነስነስ ታጅቦ ለሦስት ቀናት የዘለቀው ስብሰባ […]

በትግራይ እና በአማራ ክልል ገዢዎች መካከል ያለው አለመግባባት በተለያዩ አጋጣሚዎች ከፍ ዝቅ ሲል ቆይቶ ፣ ሰሞኑን ኢህአዴግ በአካሄደው ግምገማ ላይ እንደገና አገርሽቶበታል። የትግራይ ክልል ገዢ አቶ አባይ ወልዱ የተወሰኑ የህወሃት ደጋፊዎችን በመያዝ በሁለቱ ክልሎች መካከል ስላለው አወዛጋቢ መሬት ፣ ከአማራ ክልል ገዢ ጋር በድንበር አካበባ ያደረጉት ውይይት፣ በዘለፋና በጸብ ከተቋጨ ከወራት በሁዋላ፣ በሰሞኑ የኢህአዴግ ጉባኤ […]

ኢሳት (ነሐሴ 4፣ 2007 ዓም) 200 የሚጠጉ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች በማላዊ እስር ቤቶች የጤንነታቸው ሁኔታ አሳሳቢ በሆነ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ አንድ አለምአቀፍ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ገለጠ። ኢትዮጵያዉያኑ ከባለፈው አመት ታህሳስ ወር ጀምሮ በማላዊ መዲና ሊሎንግዌ በእስር ላይ መሆናቸውን ዶክተርስ ዊዝ አውት ቦርደርስ (Doctors Without Borders) የተሰኘ የፈረንሳይ ድርጀት አስታውቋል። በማላዊ የበጎ አድራጎት ድርጅት ተወካይ የሆኑት ኒኮሌት ጃክሰን …

ኢሳት ዜና (ነሐሴ 4፣ 2007) ሰሞኑን በአፋር ክልል የተከሰተው ድርቅ ተባብሶ በመቶዎች የሚቆጠሩ የቁምና የቤት እንስሳት መሞታቸውን አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። የአካባቢው ነዋሪዎች በበኩላቸው፣ በክልሉ በክረምት ወቅት የሚጠበቀው ዝናብ በሚፈለገው መጠን ባለመዝነቡ ምክንያት ህይወታቸው አደጋ ላይ መውደቁን በመግለፅ ላይ መሆናቸው ታውቋል። ከአዲስ አበባ ወደ አፋር ክልል መዲና በሚወስደው ዋናው አስፋል መንገድ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ …

ኢሳት ዜና (ነሐሴ 4፥ 2007) የአሜሪካ ፤ የብሪታኒያ እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት የፖለቲካ አመራሮች አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር እንዲፈቱ ለጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ደብዳቤ መላካቸውን አልጀዚራ የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘገበ። የፖለቲካ አመራሮች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በጻፉት ደብዳቤ አቶ አንዳርጋቸው ለብቻቸው 24 ሰአት የተፈጥሮ ብርሀን በማያገኙበት ሁኔታ እስር ላይ መሆናቸውን እንደጠቀሱ አልጀዚራ በብቸኝነት ማግኘት ችያለሁ ያለውን መረጃ ዋቢ በማድረግ …

ነኅሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በትግራይ እና በአማራ ክልል ገዢዎች መካከል ያለው አለመግባባት በተለያዩ አጋጣሚዎች ከፍ ዝቅ ሲል ቆይቶ ፣ ሰሞኑን ኢህአዴግ በአካሄደው ግምገማ ላይ እንደገና አገርሽቶበታል። የትግራይ ክልል ገዢ አቶ አባይ ወልዱ የተወሰኑ የህወሃት ደጋፊዎችን በመያዝ በሁለቱ ክልሎች መካከል ስላለው አወዛጋቢ መሬት ፣ ከአማራ ክልል ገዢ ጋር በድንበር አካበባ ያደረጉት ውይይት፣ …

ነኅሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ ኢህአዴግ ባደረገው ግምገማ ፣ ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ እርሳቸውንና ቤተመንግስቱን ከሚጠብቁ የደህንነት ሃይሎች ጋር ተስማማተው መስራት አልቻሉም የሚል ትችት ከቀረበባቸው በሁዋላ፣ ግንኙነቱ ወደ ባሰ ደረጃ መውረዱን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። አቶ ሃይለማርያም “በቤተሰቦቼና እና በእኔ ላይ በሚደረገው አላግባብ ክትትል ተሰላችቻለሁ” የሚል ንግግር በሁለተኛው ዙር የኢህአዴግ ሂስ እና ግለ …

ነኅሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደብዩብ ሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ልዩነት እየሰፋ መሄዱን ተከትሎ ኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን መንግስት ተደራዳሪን ከአገሯ አስወጥታለች። እርመጃው የተወሰደው የደቡብ ሱዳን መንግስት አንድ የተቃዋሚ አባል ወደ አዲስ አበባ እንዳይሄድ ማገቱን ተከትሎ ነው። ደቡብ ሱዳን የድርድሩ ቦታና አደራዳሪው ስዩም መስፍን እንዲቀየር የጠየቁ ሲሆን፣ ለዚህ የሰጡት ምክንያትም፣ አዳራዳሪዎቹ ራሳቸው በአገራቸው …

ነኅሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስአበባ ዓለም አቀፍ መስፈርት የሚያሟሉ ሆቴሎችን ደረጃ ለመመደብ በተካሄደው ጥናት 98 ያህል ሆቴሎች ከደረጃ በታች ሆነው መገኘታቸው ይፋ ሆኗል። በዓለም አቀፉ ቱሪዝም ድርጅት ከፍተኛ ባለሙያዎች ተጠንቶ ባለፈው ቅዳሜ ይፋ በተደረገው ውጤት መሠረት ለውድድር ከቀረቡት 136 ያህል ሆቴሎች ደረጃ ማግኘት የቻሉት 38 ያህሉ ብቻ ናቸው፡፡ በዚህ መሰረት ባለ5 …

ነኅሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአውስትራሊያ የሜልቦርን የአርበኞች ግንቦት7 ጽ/ቤት ” ሀገራችን ስላለችበት ሁኔታ እንምከርበት” በሚል በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለ2ኛ ጊዜ የተዘጋጀው ስብሰባ በስኬት ተጠናቋል ብሎአል። የድርጅቱ የሜልቦርን ከተማ ተጠሪ አቶ ነብዩ መላኩ ፣ “የድርጅት አጥር ሳይከልለን ትግሉን እንርዳ” የሚል መልእክት ሲያስተላልፉ፣ ዶ/ር ታደሰ ብሩ በስካይፕ ባስተላለፉት መልእክት ደግሞ ” ትግሉ …

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ላንድሮቨር ማዞሪያ፣ መሳይ ካባ በተባለ ቦታ ነው ወጣቶቹ ህይወታቸው አልፎ የተገኙት ተብሏል፡፡ በአካባቢው ለመንገድ ስራ ድንጋይ ለማውጣት የተቆፈረ ከ7 እስከ 9 ሜትር ርዝመት ያለው ጥልቅት መለስተኛ ሐይቅ ፈጥሯል፡፡ ሁለቱ 20 አንዱ ደግሞ 25 አመታቸው ነው የተባሉ 3 ወጣቶች የገቡበት ምክንያት ባይታወቅም የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር […]

ነጻነትን ለአለም ጥቁር ህዝብ እዳላጎናፀፍን ዛሬ በባንዳ ልጅ ነጻነታችን ተገፎ ሀገራችን ተዋርዳ ዜግነታችን ተንቆ ሀይማኖታችን ተደፍሮ ፍትህ ጠፍቶ ህዝባችን እኩልነትን አጥቶ ስቃይ በዝቶ እሰራት ግርፋቱ ከፍቶ ርሃብ ጥማቱ… ተባብሶ የሰውልጅ መብት ተጥሶ መቶ/100/በማይሞሉ የባዳ ልጅ መሰቃየቱ ይብቃ !! ተነስ አባቶቻችን ጣሊያንን ከሃገር ሲአስወጡ ሲደመስሱ ዘመናዊ መሳሪያ ተጠቅመው አልነበረም ስለዘህ አሁን ሁሉ ተዘጋጅቶል ተነስ ታጠቅ እስከመቸ […]

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ እንደዘገበው አርበኞች ግንቦት 7 ጦርነት በከፈተባቸውና አሁንም እየተፋለመባቸው በሚገኙ አካባቢወች የሚኖሩ ደሀ ገበሬዎች ለንብረታቸው መጠበቂያ ጥረው ግረው ጥሪታቸውን በማሟጠጥ በገንዘባቸው ገዝተው በፈቃድ የታጠቁት የጦር መሳሪያ በህወሓት አገዛዝ እየተወሰደባቸው ይገኛል፡፡ ሰሞኑን በታች አርማጭሆ የተጀመረው ትጥቅ የማስፈታት የህወሓት መሰሪይ ተግባር ላይ አርማጭሆንም ጨምሮ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በአጠቃላይ በአርማጭሆ እና በወልቃት ምድር ሰፍሮ የሚገኘው ህወሓት […]

አርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ እንደዘገበው የባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 11 አባይ ማዶ ወጣቶች አንድ አካባቢ ላይ ተሰባስበው በመጫወት ላይ እያሉ ፖሊሶች ድንገት መጥተው “ለምን አንድ ላይ ተሰብስባችሁ ቆማችሁ?” በማለት አምባጓሮ በመፍጠራቸው ነበር ግጭቱ የተነሳው፡፡ ፖሊሶቹ ወጣቶችን ከቆሙበት በኃይል አባረው ወደየቤታቸው ለማስገባት ሲሞክሩ ወጣቶቹ በፖሊስ ላይ የአጸፋ እርምጃ በመውሰዳቸው አንድ ፖሊስ ለከፋ ጉዳት እንደተዳረገ ታውቋል፡፡ የህወሓት […]