ኀዳር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አወዛጋቢው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን በመቃወም ከአመት በፊት አደባባይ የወጡ የኦሮምያ ክልል ወጣቶችና ተማሪዎች ህይወታቸው በመንግስት ታጣቂዎች ከተቀጠፈ በሁዋላ፣ ኢህአዴግ እቅዱን በድጋሜ ተግባራዊ ለማድረግ መንቀሳቀሱን ተከትሎ በአምቦ፣ በማንዲና በዙሪያ ከተሞችና ቀበሌዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ተቃውሞአቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው። ለኢሳት ደረሱት መረጃዎች እንደማለከቱት አካባቢው ከዚህ ቀደም እንደነበረው ሁሉ …

ኀዳር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በፎገራ ወረዳ፣ ወረታ ከተማ በቁሃር ሚካኤል ቀበሌ ነዋሪ የሆነው መንግስቴ ቢምር የተባለ የአካባቢ ሹም የህብረተሰቡን መሳሪያ በማስፈታት ከኢህአዴግ ጋር ሲሰራ ነበር በሚል መገደሉን ተከትሎ፣ እስካሁን በቁጥጥር ስር ያልዋሉት ገዳዮች በተገኙበት እንዲገደሉ መወሰኑን ምንጮች ገልጸዋል። ከሹሙ ግድያ ጋር በተያያዘ እየተፈለጉ ያሉትና ባለቡት ይገደሉ የተባሉት አርሶ አደር መንጋው …

መቀመጫዉን ዬኤስ አሜሪካ ኒዮርክ ከተማ ላይ ያደረገዉ ለጋዜጠኞች የሚሟገተዉ ድርጅት «ሲፒጄ» የተባለ ተቋም ለዞን ዘጠኝ ጦማርያን የ 2015 ዓ,ምን ዓለማቀፍ የፕሪስ ነፃነት ሽልማት አበረከተ።

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ጋዜጠኞች ከመንግስት አካላት መረጃ በማግኘት ረገድ ከፍተኛ ችግር እንዳለባቸዉ ተመለከተ። ይህ የተገለፀዉ የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር ዛሬ በሂልተን ሆቴል ባካሄደዉ የምክክር መድረክ ነዉ።

ሁለት ወጣቶች በሚንያፖሊስ ከተማ፣ ሚነሶታ መኪና ውስጥ በተኩስ ተገድለው መገኘታቸውንና ሶስተኛው ወጣት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት በሆስፒታል እርዳታ እየተደረገለት መሆኑ ታውቋል። ባለፈው እሁድ እአአ ሕዳር 22 2015 ምሽት ላይ ሁለት ወጣቶች በሚንያፖሊስ ከተማ፣ ሚነሶታ መኪና ውስጥ በተኩስ ተገድለው መገኘታቸውንና ሶስተኛው ወጣት …

በሚነሶታ ሁለት ኢትዮጲያውያን ሞቱ ፣ አንዱ ደግሞ የከፋ ጉዳት ደርሶበታል – ህዳር 25, 2015 Read more »

የአንከር ወተት ማስታወቂያ ታገደ

ከኢትዮጵያ መድኃኒት፣ ምግብና ጤና ክብካቤ አስተዳደር ቁጥጥር ባለሥልጣን ጥቅምት 29 ቀን 2008 ዓ.ም. ለብሮድካስት ባለሥልጣን በተጻፈ ደብዳቤ የአንከር ወተት የቴሌቪዥን ማስታወቂያ ኅዳር 2 ቀን 2008 ዓ.ም. እንዲታገድ

መደረጉን፣ የባለሥልጣኑ ሕዝብ ግንኙነት ማስተባበሪያ ኃላፊ አቶ ወርቅነህ ጣፋ ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

ሪፖርተር ከመድኃኒት አስተዳደርና ቁጥጥር ባሥልጣን ምንጮችና ከብሮድካስት ባለሥልጣን መረዳት እንደቻለው፣ ማስታወቂያው እንዲቋረጥ የተደረገው በሦስት ምክንያቶች ነው፡፡ የመጀመርያው ወተቱ ከኒውዚላንድ መጣ የሚለው የማስታወቂያው ነጥብ እየተነገረ እንዳለው ሳይሆን፣ እዚህ አገር የሚቀነባበርና የሚታሸግ መሆኑ መገለጽ አለበት የሚል ነው፡፡ 

ሁለተኛው ደግሞ ምንም እንኳ የወተቱ ማሸጊያ ላይ የተቀመጠ ቢሆንም፣ በቴሌቪዥን በሚነገረው ማስታወቂያ ወተቱን ሊጠቀሙ የሚችሉ የዕድሜ ገደብ ሊገለጽ ይገባል የሚል ነው፡፡ የመጨረሻው ከሰላሳ በላይ ንጥረ ነገሮች ያሉት ተብሎ መነገሩ የሚያሳየው ይህ ነው የሚባል ግልጽ ቁጥር ባለመኖሩ፣ በትክክል በውስጡ የሚገኘው ንጥረ ነገር መጠን መቀመጥ ይኖርበታል የሚል ነው፡፡ 

የኒውዚላንድ ሚልክ ፕሮዳክትስ ኢትዮጵያ ሼር ካምፓኒ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘኮ ኢብሮ ማስታወቂያው ሲነገር መገለጽ ነበረባቸው የተባሉት መረጃዎች በወተቱ እሽግ ላይ መገለጻቸውን በመጠቆም፣ በማስታወቂያው ያልተነገሩት በሰላሳ ሰከንድ ውስጥ ዋና ዋና ነገሮችን ለመግለጽ ሲባል መሆኑን ይናገራሉ፡፡ 

የወተቱ ዱቄት በእርግጥም የኩባንያው እናት ኩባንያ ከሆነው የኒውዚላንዱ ፍሮንቴራ ኩባንያ እንደሚመጣ ገልጸዋል፡፡ ያላቸው የንግድ ፈቃድም እዚህ አገር ለማደባለቅና ለማሸግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 

እሳቸው እንደገለጹት፣ የተጠቃሚዎች ዕድሜን ስለመግለጽና የወተቱን ‹ከኒውዚላንድ የመጣ› በሚል መተዋወቅን በሚመለከት፣ ከመድኃኒት አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን ጋር ተነጋግረው መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ ማስታወቂያውን ሲያሠራጭ ከነበረው ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ጋርም እንዲሁ ተነጋግረዋል፡፡ 

ወተቱ ምን ያህል ንጥረ ነገር አለው? (ትክክለኛ ቁጥር) የሚለውን ለማወቅ የላብራቶሪ ምርመራ እንዲደረግ ስምምነት ላይ ተደርሶ ናሙና ወደ ውጭ ተልኮ ውጤት በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን አቶ ዘኮ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ 

ማስታወቂያው እንዲቋረጥ የተደረገው ትክክለኛውን ምግብና ምግብ ነክ ነገሮች የሚተዋወቁበትን አግባብ ተከትሎ እንዲተዋወቅ ለማድረግ ሲባል እንደሆነ፣ በሚመለከታቸው የቁጥጥር ተቋማት ተገልጿል፡፡ 

በፋፋ ፉድስ ኢትዮጵያና በኒውዚላንድ ወተት አምራች ድርጅት ፎንቴራ የአሥር ሚሊዮን ዶላር የጋራ ኢንቨስትመንት፣ አንከር ወተት በዚህ ዓመት መጀመርያ ላይ ለገበያ መተዋወቁ ይታወሳል፡፡ 

 

በጦርነቱ ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች መሞታቸውና ንብረት መውደሙ ተገልጿል

በደቡብ ክልል ሸካ ዞን ይዞታቸው ለኢንቨስተር በመሰጠቱ ምክንያት ምትክ ቦታ እንዲሰጣቸው ጥያቄ በማቅረባቸው ‹‹ለሕግ ተገዢ አይደሉም›› በማለትና በሽፍታነት በመፈረጅ፣ በሸኮዎች ላይ ዕርምጃ ለመውሰድ ሸካዎችን በማስታጠቅና

የእርስ በርስ ጦርነት በማነሳሳት የተጠረጠሩ፣ የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪን ጨምሮ 12 ተሿሚዎች ክስ ተመሠረተባቸው፡፡ 

የደቡብ ክልል መንግሥት ፍትሕ ቢሮ ዓቃቤ ሕግ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተዘዋዋሪ አንደኛ ወንጀል ችሎት ኅዳር 9 ቀን 2008 ዓ.ም. ያቀረበው ክስ እንደሚያስረዳው፣ የሸኮ ብሔር ተወላጆችና የየኪ ወረዳ ፃኑ ቀበሌ ጉፍታ ንዑስ መንደር ነዋሪዎች ይዞታ ለኢንቨስተር ተሰጥቷል፡፡ ነዋሪዎቹ ለረዥም ዓመታት ምትክ ቦታና የንብረት ግምት እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡ ጥያቄያቸውን በመቀበል ምላሽ መስጠት ያልፈለጉት የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አዝመራ አንደሞና የሥራ ባልደረቦቻቸው፣ ‹‹ለሕግ ተገዢ አይደሉም›› በማለትና በወንጀለኛነትና በሽፍታነት በመወንጀል፣ በዞኑ ፖሊሶች ተይዘው እንዲታሰሩ ማድረጋቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ዘርዝሮ አቅርቧል፡፡ 

ሕጋዊ መብታቸውን በመጠየቃቸው ወንጀለኞች የሚል ስያሜ በመስጠት ነዋሪዎቹን በመተባበር በማሰርና የእርስ በርስ ጦርነት እንዲነሳ ያደረጉት ተጠርጣሪዎች የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አዝመራ አንደሞ፣ በዞኑ የደኢሕዴን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ፣ የየኪ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወርቁ ሻረው፣ የየኪ ወረዳ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አምሳሉ ከሴቶ፣ የቴፒ ከተማ ከንቲባ አቶ ሻሎ አድሎና ሌሎችንም ተጠርጣሪዎች ዓቃቤ ሕግ በክሱ ዘርዝሯል፡፡ 

ተጠርጣሪዎቹ ከ30 በላይ የፖሊስ አባላትን መሣሪያ በማስታጠቅ፣ ሚያዝያ 20 ቀን 2006 ዓ.ም. ወደ ፃኑ ቀበሌ ጉፍታ ንዑስ መንደር በመሄድ የሸኮ ብሔር ተወላጆችን ከበው መያዛቸውን የሚገልጸው የዓቃቤ ሕግ ክስ፣ ያልተያዙት የአካባቢው ነዋሪዎች በሁኔታው በመደናገጥና በመረበሽ ንብረታቸውንና ቤታቸውን ጥለው አጎራባች ወደሆነው ጋምቤላ ክልል ዶንቻዬ ቀበሌ መሰደዳቸውንም ያስረዳል፡፡ 

የሸኮ ነዋሪዎች ቀዬአቸውን ትተው ሲሰደዱ ተጠርጣሪዎቹ ‹‹አካባቢውን ተቆጣጥረነዋል›› በማለት አካባቢው ላይ ባንዲራ መትከላቸውንና ተመልሰው ሲመጡ ዕርምጃ ለመውሰድ የሚያስችላቸውን ንዑስ የፖሊስ ጣቢያ መክፈታቸውም ተገልጿል፡፡ በአካባቢው ምሽጎችን ቆፍረው ለውጊያ ቅድመ ዝግጅት ማድረጋቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ አካቷል፡፡ 

ድንገት በተፈጠረባቸው ወረራ ወደ አጎራባች ክልል የተሰደዱት ሸኮዎች ወደ ቀያቸው እንዳይመለሱ ሕገወጥ ድብደባና እስር በተጠርጣሪዎቹ ሲፈጸምባቸው ቆይቶ፣ ድርጊቱ ወደ እርስ በርስ ግጭት ተቀይሮ በሸኮዎችና በሸካ ብሔረሰቦች መካከል ጦርነት እንዲፈጠር ማድረጋቸውንም የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡ 

በሸኮዎችና በሸካ ተወላጆች መካከል በተደረገ የእርስ በርስ ጦርነት ስማቸው የታወቁ ስድስት ሰዎች መሞታቸውን ማረጋገጡን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ገልጿል፡፡ በተጨማሪም ስማቸውን ማወቅና መለየት ያልተቻለ በርካታ ሰዎች መሞታቸውን ባቀረበው ክስ ላይም ገልጿል፡፡ ከሰባት የሚበልጡ ነዋሪዎችም ከፍተኛ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸውና የገቡበት እንዳልታወቀም አክሏል፡፡ ጦርነቱ ከእነሱ አልፎ ወደ አጎራባች ቀበሌዎች እንዲስፋፋና በዞኑ የፀጥታ ችግር እንዲሰፍን ምክንያት መሆናቸውንም ዓቃቤ ሕግ በክሱ አስረድቷል፡፡ 

ተከሳሾቹ ‹‹ወደዳችሁም ጠላችሁም የዞኑና የወረዳው ቁልፍ ያለው በእኛ እጅ ነው›› በማለት በሁለቱ ብሔረሰቦች መካከል የተነሳው ግጭት ወደ ቴፒ ከተማ አስፋፍተዋል፡፡ በግንቦት ወር 2007 ዓ.ም. የቴፒ ከተማ ፖሊስ አባላት የሆኑ አምስት ፖሊሶች ወደ ጫካ ገብተው በነበሩ የሸኮ ተወላጆች እንዲገደሉ ማድረጋቸውንና ግጭቱ እስካሁን እንዲቀጥል ማድረጋቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡ ተከሳሾቹ የአካባቢው ነዋሪዎች ከቀዬአቸው እንዲፈናቀሉ ማድረጋቸውን፣ በሕዝብ ደኅንነትና ኑሮ ላይ ከፍተኛ ቀውስ ማስከተላቸውንና የእርስ በርስ ጦርነት የማነሳሳት ወንጀል መፈጸማቸውን ዓቃቤ ሕግ አብራርቷል፡፡ 

ተከሳሾቹ በተሰጣቸው ሥልጣንና ኃላፊነት ሕግና ሥርዓትን ተከትለው ኅብረተሰቡን ማገልገል ሲገባቸው፣ ሥልጣናቸውን ተገን በማድረግ ሆን ብለውና አስበው በሕገወጥ ተግባራት በመሰማራት በሕዝብና በመንግሥት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ አብራርቶ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡ ፍርድ ቤቱ የተከሳሾቹን ጉዳይ የሚያየው በተዘዋዋሪ ችሎት ቢሆንም፣ የሚቀጥለው ችሎት መቼ እንደሚሰየም አልታወቀም፡፡ 

 

ለሕመም ማስታገሻ የሚውለው ኮዴይን ጥቅም ላይ እንዳይውል ታገደ

የኢትዮጵያ የመድኃኒት፣ የምግብና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን እ.ኤ.አ. ኖቬምበር 1 ቀን 2015 ባሠራጨው ሰርኩላር፣ ኮዴይን የተባለው የሕመም ማስታገሻ ላልተወሰነ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ጥቅም ላይ እንዳይውል አግዷል፡፡ 

ባለሥልጣኑ ለክልሎችም ሆነ ለፌዴራል መንግሥት የጤና ቢሮዎች በላከው ደብዳቤ እንደገለጸው፣ ኮዴይን የተባለው መድኃኒት ለኢትዮጵያውያን የዘረ መል አወቃቀር (Genetic Makeup) የማይስማማ መሆኑንና ጥቅም ላይ ከዋለም እስከ ሞት ሊያደርስ እንደሚችል በጥናት መረጋገጡን አስታውቋል፡፡

ባለሥልጣኑ ዕገዳውን ያደረገው የአሜሪካ የምግብና የመድኃኒት አስተዳደር በኢትዮጵያና በሌሎች አገሮች ላይ አተኩሮ ባከናወነው ጥናት፣ ኮዴይን የተባለው የሕመም ማስታገሻ እስከ ሞት የሚያደርስ መሆኑን በማሳወቁ ነው፡፡ 

የተሠራው ጥናት እንዳመለከተው በዘረ መል አወቃቀር ምክንያት አንዳንድ ሰዎች ኮዴይን ሲወስዱ ወደ ሞርፊን እንደሚቀየር፣ በዚህም ምክንያት በደም ውስጥ የሚገኘውን የሞርፊን መጠን በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመር ለመተንፈስ ችግር ብሎም ለሞት እንደሚያደርስ ተገልጿል፡፡ 

በመሆኑም ማንኛውም የጤና ባለሙያና የጤና ተቋም ኮዴይን የተባለውን የሕመም ማስታገሻ በየትኛውም ዕድሜ ለሚገኙ ታካሚዎች በሕመም ማስታገሻነት ወይም ለብርድና ለሳል ሕመሞች እንዳያዙ ደብዳቤው የደረሳቸው የጤና ቢሮዎች፣ በሥራቸው ለሚተዳደሩ የጤና አገልግሎት ተቋማት እንዲያስተላልፉ አዟል፡፡ ዕገዳው የተደረገው ላልተወሰነ ጊዜ እንደሆነ ቢገልጽም፣ ላልተወሰነ የተባለበት ጊዜ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ደብዳቤው አይገልጸም፡፡ 

ጉዳዩን በተመለከተ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ተንቀሳቃሽ ስልክ ላይ በተደጋጋሚ ቢደወልም ጥሪውን አልመለሱም፡፡ የአሜሪካ የምግብና የመድኃኒት አስተዳደር ጥናት እንደሚያመለክተው፣ ምርመራ ከተካሄደባቸው 122 ኢትዮጵያውያን መካከል 29 በመቶ የሚሆኑት ወይም 35 ኢትዮጵያውያን የዘረ መል አወቃቀር ኮዴይን በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ሞርፊን የሚቀይር ኢንዛይም አላቸው፡፡ 

ይህ የጥናት ውጤት ከተገለጸ ስድስት ወራት ቢሆነውም የኢትዮጵያ የመድኃኒት፣ የምግብና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን ውሳኔ ሳይወስድ እስከተጠቀሰው ቀን ቆይቷል፡፡ በተመሳሳይ ጥናት የአዲስ አበባ የወተት አቅርቦት ለካንሰር የሚዳርግ አፍላቶክሲን የተባለ ውህድ እንዳለው ከተገለጸ ከስድስት ወራት በኋላ መረጃው በተለያዩ የማኅበራዊ ድረ ገጾች ሲለቀቅ፣ ባለሥልጣኑ የራሱን ተጨማሪ ጥናት እያከናወነ መሆኑን ሰሞኑን ለመገናኛ ብዙኃን መግለጹ አይዘነጋም፡፡ 

 

“የኢትዮጵያ ወታደሮች የኬንያን ድንበር ዘልቀው ሦስት የኬንያ ፖሊሶችን ገደሉ” ሲሉ የኬንያ ጋዜጦች ፅፈዋል፤ የሃገሪቱ ፖሊስ ግን ሰዎቹን የገደሉት የኢትዮጵያ ታጣቂ አማፂያን እንጂ የመንግሥቱ ወታደሮች አይደሉም ይላል፡፡

ኅዳር 8 ቀን 2008 ዓ.ም. ረቡዕ ለሐሙስ አጥቢያ ከጓንግዙ ቻይና ወደ አዲስ አበባ በመብረር ላይ የነበረ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ 777 አውሮፕላን ውስጥ የተሳፈረ መንገደኛ፣ በስካር መንፈስ ሁከት በመፍጠሩ በመንገደኞች ርብርብ በቁጥጥር ሥር ዋለ፡፡

የበረራ ቁጥር ኢቲ607 ከ300 በላይ መንገደኞች አሳፍሮ ከጓንግዙ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የተነሳው ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ነበር፡፡ አንድ ሰዓት ተኩል ከበረረ በኋላ በበረራ አስተናጋጆች አማካይነት ለመንገደኞች እራት ቀርቦ ካበቃ በኋላ፣ አብዛኛዎቹ መንገደኞች አሸልበው ነበር፡፡

በአውሮፕላኑ የተሳፈሩ መንገደኞች ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ከእንቅልፋቸው የነቁት በሰሙት ጩኸት ምክንያት ነበር፡፡ በኢኮኖሚ ክፍል የነበሩ የበረራ አስተናጋጆች እየተጯጯሁ ወደ ቢዝነስ ክፍል ሲሮጡ መመልከታቸውን መንገደኞች ተናግረዋል፡፡ ከእንቅልፋቸው ተደናግጠው የተነሱ የተወሰኑ መንገደኞች የበረራ አስተናጋጆቹን ተከትለው ሮጠዋል፡፡

‹‹የበረራ አስተናጋጆቹ ሊገለን ነው›› እያሉ እየሮጡ ወደ ቢዝነስ ክፍል መምጣታቸውን የገለጹት ተሳፋሪዎች፣ ዕድሜው በ30ዎቹ መጨረሻ የሚገመት ናይጄሪያዊ መንገደኛ በስካር መንፈስ ተገፋፍቶ የበረራ አስተናጋጆችን ለመደብደብ ሲያባርር መመልከታቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

በዚህን ወቅት በቢዝነስ ክፍል ውስጥ የተሳፈሩ አንድ ኢትዮጵያዊ ባለሀብት፣ በቢዝነስ ክፍል መግቢያ ላይ ጠብቀው ከሁከት ቀስቃሹ ናይጄሪያዊ ጋር ግብግብ ፈጥረዋል፡፡ ናይጄሪያዊው ግዙፍ ቢሆንም ኢትዮጵያዊው ባለሀብት እንደምንም ብለው መተናነቃቸውን ገልጸው፣ ሌሎች ናይጄሪያዊያን መንገደኞች ባደረጉላቸው እገዛ ግለሰቡን ከወለል ላይ ሊጥሉት ችለዋል፡፡ መንገደኞቹ ነውጠኛውን ተሳፋሪ በደረቱ በማስተኛት እጁን የኋሊት አስረውታል፡፡ ግለሰቡ መጠጥ መጠጥ ይሸት እንደነበር መንገደኞች ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሪፖርተር በላከው ማብራሪያ፣ ግለሰቡ በአውሮፕላኑ ውስጥ የአልኮል መጠጥ እንዳልቀረበለት ገልጿል፡፡ ለመንገደኛው የቀረበለት ለስላሳ መጠጥና ምግብ ብቻ እንደሆነ የጠቆመው አየር መንገዱ ግለሰቡ ግን ሰክሮ እንደነበር ይታመናል ብሏል፡፡

ሪፖርተር ያነጋገራቸው መንገደኞች ግለሰቡ አውሮፕላኑን ከመሳፈሩ በፊት፣ የአልኮል መጠጥ በብዛት ሳይወስድ እንዳልቀረ ግምታቸውን ተናግረዋል፡፡

የአውሮፕላኑ ሠራተኞች ነውጠኛው ግለሰብ በሌሎች ተሳፋሪዎችና በአውሮፕላኑ ላይ ጉዳት ሳያደርስ፣ ከሌሎች ተሳፋሪዎች ጋር በመተባበር ሁኔታውን መቆጣጠራቸውን አየር መንገዱ አስታውቋል፡፡

ግለሰቡ በቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ አውሮፕላኑ ለሰባት ሰዓታት ያህል በመብረር ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት በሰላም አርፏል፡፡ መንገደኞቹና የአውሮፕላኑ ሠራተኞች ግለሰቡን ለኤርፖርት ደኅንነት ሠራተኞች አስረክበዋል፡፡ ግለሰቡ ለፌደራል ፖሊስ ተላልፎ ከተሰጠ በኋላ፣ ፖሊስ ምርመራ እያካሄደበት መሆኑ ታውቋል፡፡

ከግለሰቡ ጋር ግብግብ የፈጠሩት ተሳፋሪዎች ለወደፊቱ ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈጠር በግለሰቡ ላይ ጠንከር ያለ ቅጣት ሊጣል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ ‹‹የፖሊስን ሪፖርት ተመልክተን በቀጣይ መደረግ ስላለበት ጉዳይ እንመክራለን፤›› ያለው አየር መንገዱ፣ የፖሊስ ምርመራ ከተጠናቀቀ በኋላ በግለሰቡ ላይ የወንጀል ክስ ይመሠረታል የሚል እምነት እንዳለው አስታውቋል፡፡

 

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

ኀዳር ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በወሎ፣ቆቦና ዋግ ህምራ አካባቢ የሚኖሩ አርሶ አደሮች የዘንድሮው ድርቅ ከ1977ቱ ያልተለየ ነው በማለት ለኢሳት ተናገሩ፡፡ ተጎጂዎች በድርቁ በርካታ ሃብት ንብረታቸውን በመጨረሳቸው ባዶ እጃቸውን እንደቀሩ ይናገራሉ፡፡የገዢው መንግስት ሚዲያዎች በድርቁ የሞተ ሰው የለም በማለት ለማስተባበል ቢሞክሩም ተጎጅዎቹ ‹‹ ከሃብታችን ባሻገር ልጆቻችን እየተነጠቅን ነው፡፡ ›› በማለት በተጨባጭ ያለውን የወቅቱን …

ኀዳር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ድርጊቱ የተፈጸመው ባለፈው መስከረም ወር ሲሆን የቀብሩ ስነስርዓት የተፈጸመው ግን ባሳለፍነው ሳንምት ነው። በመተከል ዞን በዳንጉር ወረዳ 12 የአማራ ተወላጆች ለቀን ስራ ተብለው ከተወሰዱ በሁዋላ በወረዳው አስተዳደሪ ትእዛዝ ኮከል ቀበሌ ላይ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ተረሽነዋል።አስከሬናቸው ተቆራርጦ በጆንያ ተጠቅሎ መገኘቱንና የቀብር ስነስርዓታቸውም መፈጸሙን ምንጮች ገልጸዋል። የተገደሉት ነዋሪዎች …

በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የቀጠለዉ ቁርቁስና፣ ፖለቲካዊ ዉዝግብ አሁን ደግሞ በስፖርቱ ላይ ጫናዉን ያሳረፈ መስሏል። ኢትዮጵያ ከሕዳር 11 ጀምሮ ለ 15 ቀናት በምታስተናግደዉ የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ ሀገሮች «ሴካፋ» የእግር ኳስ ሻምፒዮናን ኤርትራ እንዳትካፈል ኢትዮጵያ አግዳለች ሲል አሶሺየትድ ፕረስ ያወጣዉን ዘገባ ተከትሎ፤

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

በተለያዩ ርቀቶች 27 የዓለም ክብረ ወሰኖችን የሠበረውና በቅርቡም የምንጊዜውም የዓለም ምርጥ አትሌት ተብሎ የተመረጠው ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ከነገ በስቲያ እሁድ በይፋ ከአትሌቲክሱ ዓለም ይሰናበታል።

በኢትዮጵያ በዝናብ እጥረት የተነሳ በተከሰተው ድርቅ 8.2 ሚሊዮን ሰዎች የምግብ ዋስትና ችግር እንደገጠማቸው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምጣኔ ሀብት አማካሪ አቶ ንዋይ ገብረዓብ ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ገልጸዋል።

በተለያዩ የማላዊ እስር ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች በቅርቡ ወዳገራቸው እንደሚጓጓዙ፣ IOM-ዓለማቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅትና ማላዊ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለቪኦኤ ገለጹ። ይህ የተገለጸው ዋና ጽ/ቤታቸው ኬንያ-ናይሮቢ የሆነውና ማላዊንም የሚያካትቱት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በትናንቱ ዕለት ማላዊ ተገኝተው እዚያ ለሚገኙ የIOM, የMSF-ድንበር-የለሽ የሐኪሞች ድርጅትና የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ አባላት ባረረጋገጡበት ወቅት ነው።

ኀዳር ፲ (አስር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በጉጂ ዞን የሚኖሩ የተለያዩ ብሄረሰቦች በአንድ ላይ በመሆን ያቀረብነው የመልካም አስተዳደር እና የፍትህ ጥያቄ ካልተመለሰ የህዝባዊ እምቢተኝነት ተቃውሞአቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል። የዞኑ የአገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ሰዎችና የአካባቢው ባለስልጣናት በአንድነት ሆነው ኦሮምያ ክልል በመሄድ ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ መልስ ሊያገኙ አልቻሉም። ጥያቄያቸውን ይዘው ወደ ጠ/ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ማምራታቸውንም ጉዳዩን በቅርብ …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላንን በተመለከተ፤ የፌድራል መንግስትም ሆነ የኦሮሚያ ምክር ቤት፤ ሕዝብን ጠርቶ ያላወያየበት ምክንያት፤ የኦሮሞ ወይም የአከባቢ አርሶ አደሮችን አፈናቅለዉ መሬት ዘረፋ ላይ የተመሰረተ እንቅስቃሴ ለማድርግ በመታቀዱ ነዉ ሲሉ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ከፍተኛ አመራሮች ተናገሩ።

በፍቃዱ ዘ ኃይሉ

‹‹…ይወስዳል መንገድ፣ ያመጣል መንገድ 

አንድ የሚጠላ፣ አንድ የሚወደድ…››

ሕይወት መንገድ ነች፡፡ በየመንገዱ ከሰው ታወዳጀናለች፤ ከተወዳጀናቸው ታለያየናለች፡፡ እኔም በሕይወቴ ጎዳና በገጠመኝ የእስር ሕይወቴ ካፈራኋቸው ወዳጆቼ ዘላለም ወርቅአገኘሁ አንዱ ነው፡፡ ሁሌ ‹‹ለምን ሳንታሰር አልተዋወቅንም?›› እንባባላለን፡፡ ቀድሞ መተዋወቁ የተለየ ነገር ይፈጥር ይመስል፡፡

ዘላለም ወርቅአገኘሁ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋለው ሐምሌ 1፣ 2006 ነበር፡፡ ልክ ከእኛ ውስጥ (ከአቤል በቀር) ወንዶቹ ሁሉ ‹‹ሳይቤሪያ›› ከሚባለው ቀዝቃዛ የምድር ክፍል ወጥተን ‹‹ሸራተን›› ወደሚባለው አንፃራዊ ምቹ ክፍል የተዘዋወርን ዕለት ማለት ነው፡፡ እኛ ወደ‹‹ሸራተን›› የተዛወርነው ለካስ እሱን ጨምሮ ለነሀብታሙ አያሌው፣ አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ዳንኤል ሺበሺ፣ እንዲሁም ለነባሕሩ፣ ዮናታን፣ አብርሃም እና ሌሎችም ቦታ መልቀቅ ስላለብን ነበር፡፡ አንድም እንዳንቀላቀል፣ አንድም ምሥጢር እንዳንለዋወጥ መሆኑ ነው፡፡ ዘላለም ወርቅአገኘሁ የገባው፣ የኛው ዘላለም ክብረት ወደነበረበት 5 ቁጥር ነበር፡፡ እዚያ ግን ብዙ አልቆየም፡፡ ከዚያ ክፍል ወጥቶ ጭራሹኑ መብራት ወደሌለው እና ከአንድ ሰው በላይ በማያሳድረው ጭለማ ክፍል (ስምንት ቁጥር ) ውስጥ ገብቷል፡፡ ስምንት ቁጥር ውስጥ 41 ቀናት ቆይቷል፡፡

በጨለማ ቤት 24 ሰዓት፣ ለብቻ መቆየት ምን ያክል ከባድ እንደሆነ መገመት ይከብዳል፡፡ ለተወሰኑ ቀናት ከአብርሃ ደስታ ጋር ተጎራብተዋል፡፡ ከዚያ በፊት ባይተዋወቁም (ዘላለም በሥም ያውቀው ነበር) ግድግዳ እየደበደቡ ይነጋገሩና ማፅናኛ ቃላትም ይለዋወጡ እንደነበር ሁለቱም ነግረውኛል፡፡ ዘላለም ከታሰረ ዓመት ሲሞላው ‹‹በእስር ቆይታዬ የተረዳሁት የ24 ሰዓትን ርዝመት፣ የዓመትን እጥረት ነው›› አለኝ፡፡ ‹እንዴት?› አልኩት፤ ‹‹ስምንት ቁጥር እያለሁ 24 ሰዓት ማለት ፈፅሞ የማያልቅ ረዥም የጊዜ ዓይነት ነው፡፡ ዓመት ደግሞ በእስር ዓይን መለስ ብለህ ስትመለከተው በጣም አጭር ነው፡፡ አሁን ሳስበው የገባኝ የሁለቱ አያዎ (paradox) ነው›› አለኝ፡፡ እውነቱን ነው፡፡ ኔልሰን ማንዴላ ‹‹በእስር ቤት አንዱ ቀን ከሌላኛው ቀን፣ አንዱ ሳምንት ከቀጣዩ ሳምንት፣ ወሩ ከሚቀጥለው ወር ጋር አንድ ዓይነት ናቸው›› ብለው ጽፈዋል፡፡ እውነት ነው፤ ስለዚህ መለስ ብለው ሲመለከቱት ዓመቱ በጣም አጭር ይመስላል፡፡ ዘላለም የተረዳው ያንኑ ነው፤ የጨለማ ቤቷን ተሞክሮ የገለፀልኝ ደግሞ እኔ ልገልፀው ስቸገር የነበረውን ነው፡፡

ዘላለም ወርቅአገኘሁ ካየኋቸው ክሶች ሁሉ የተንዛዛ ክስ ነው የተመሠረተበት፡፡ ክሱ ብቻውን ዘጠኝ ገጽ ነው፡፡ ፌስቡክ ላይ ያደረገው ቻት፤ ቤቱ የተገኙ የትምህርት እና ሌሎችም ጽሑፎች በሙሉ ክሱ ውስጥ ተተንትነዋል፡፡ ማስረጃ ተብለው ተያይዘዋል፡፡ ከተያያዙበት የሰነድ ማስረጃዎች መካከል ጥቂቶቹን ለትዝብታችሁ ያክል ልንገራችሁ፡፡

አንድ ገጽ ሙሉ በእስኪርቢቶ የተጻፈ ጽሑፍ ነው፤ እንዲህ ይነበባል፣

“If Blogging is a Crime,

then I am a Blogger too.

Free Zone9 Bloggers”

እንዳየሁት በጣም ነበር የደነገጥኩት፡፡ ብዙ ሰዎች በእጃቸው ‹‹መጦመር ወንጀል ከሆነ እኔም ጦማሪ ነኝ፤ የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ይፈቱ›› የሚል ጽሑፍ ይዘው ፎቶ እየተነሱ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እየለጠፉ እንደነበር ሰምቻለሁ፡፡ ነገር ግን የሽብር ክስ ማስረጃ ሰነድ ሆኖ ይመጣል ብዬ ግን ጠርጥሬ አላውቅም፡፡ ኢሕአዴግ ብዙ ጊዜ ያስገርመኛል (surprise ያደርገኛል)፡፡ በዚህም አስገረመኝ ከማለት ውጪ ቋንቋ የለኝም፡፡

ሌላም በጣም አስገራሚ ሰነድ ‹‹የሠራኸውን ወንጀል›› ያስረዳል ተብሎ ቀርቦበታል፡፡ ሰነዱ አንዳንዶች እንደሚሉት ‹‹ለኢሕአዴግ ብሉይ ኪዳኑ ነው››፡፡ ሰነዱ “On the Questions of Nationalities in Ethiopia” ይላል፡፡ የብሔር ጥያቄን በወረቀት ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ አቀንቅኗል የሚባልለት የዋለልኝ መኮንን መጣጥፍ ነው፡፡ ታዲያ የዚህ መጣጥፍ ገጽ ዘላለም ወርቅአገኘሁ ክስ ላይ ማስረጃ ሰነድ ተብሎ ተያይዟል፡፡ ይህንን ሰነድ ምን ብለው ያስተባብሉታል?

እነዚህም ብቻ አይደሉም፡፡ ዘላለም በታሰረበት ወቅት በፐብሊክ አድሚኒስትሬሽን ማስተርሱን በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ እያጠና ነበር፡፡ ታዲያ በወቅቱ ያገላብጣቸው የነበሩ ጥናቶችም ማስረጃ ተብለው ከክሱ ጋር ተያይዘው ቀርበውበታል፡፡ ለምሳሌ የሚከቱሉት ርዕሶች ያሏቸው ጽሑፎች አሉ፤ “Academic freedom” (የትምህርት/ማስተማር ነጻነት)፣ “University for Society” (ዩንቨርስቲ ለማኅበረሰብ)፣ እና “Social Service” (ማኅበራዊ አገልግሎት)፡፡ እንግዲህ እነዚህ በይፋ የሚታወቁ ትምህርት ነክ የሆኑ አጀንዳዎችን የሚታወቁ ጥናቶችን ማስረጃ ብሎ የሽብር ክስ ላይ ማያያዝ አንድም የከሳሾቹን አላዋቂነት ያሳብቃል፡፡ ያውቃሉ ቢባል እንኳ እያወቁ አጥፊነታቸውን ይናገራል፡፡ በተጨማሪም፣ የኔልሰን ማንዴላ ‘Long Walk To Freedom’ የተሰኘውና ከዋናው እትም አጥሮ የተጻፈው መጽሐፍ ገጽ 25 ላይ የሰፈረው፣ ኔልሰን ማንዴላ ‹የሕንድ ብሔራዊ ኮንግረስ›፣ ፓርቲያቸው ‹የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ› ለሚያደርገው ትግል አርኣያ እንደሆነው የሚያትቱበት ጽሑፋቸው ዘላለም ላይ ማስረጃ ተብሎ ተጠቅሶበታል፡፡

ዘላለም በዐቃቤ ሕግ ምስክር ሳይቀር የተነገረበት አንዱ ‹‹በሽብር ተፈርዶበት ውጪ አገር ከሚኖር የግንቦት 7 አመራር ገንዘብ ተልኮለታል›› የሚለው አንዱ ሲሆን፣ ይህንኑ ያስረዳል ተብሎ የተያያዘው ሰነድ ግን የሚያስረዳው ሌላ ነገር ነው፡፡ ሰነዱ የሚያስረዳው ተድላ ደስታ የተባለ ሰው ሦስት መቶ ዶላር እንደላከለት ነው፡፡ ተድላ ደስታ የ‹ደ ብርሃን› ጦማር ጸሐፊ ሲሆን፣ የግንቦት 7 አመራር ቀርቶ አባል ስለመሆኑ ምንም መረጃ ያልቀረበ ከመሆኑም በላይ ‹‹የተፈረደበት›› የሚለው ገሀድ ውሸት ነው፡፡

እንዲህ እና መሰል ክሶችን ታቅፎ የቆየው ዘላለም ነሐሴ 14/2007 ቀድሞ የተከፈተበት አንቀጽ 4 (ሲያንስ 15 ዓመት፣ ሲበዛ ሞት የሚያስቀጣ) ተቀይሮለት በአባልነት ብቻ፣ ማለትም 7/1 (ቢበዛ 10 ዓመት የሚያስቀጣ) አንቀጽ ተደርጎለት እንዲከላከል ተወስኖበታል፡፡ የዛኑ ዕለት በእሱ መዝገብ የተከሰሱት አራቱ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና አብርሃም ሰለሞንም ‹‹ነጻ›› ተብለው ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ዐቃቤ ሕግ ይግባኝ በማለቱና የፍቺ እግድም ከጠቅላይ ፍ/ቤት በማሳዘዙ እስከዛሬ አልተፈቱም፡፡ ሌሎቹ የዘላለም ጓደኞች ባሕሩ እና ዮናታንም ቀድሞ በተከፈተባቸው አንቀጽ 7/1 እንዲከላከሉ ተበይኖባቸዋል፡፡ የዘላለም ጓደኞች የተያዙት ከዘላለም ጋር በመሆን ወደውጭ አገር በመጓዝ የኢንተርኔት ደኅንነት ሥልጠና ሊወስዱ በተለዋወጡት ኢሜይል ሳቢያ እንደሆነ ይገመታል፡፡ ሥልጠናውን እያመቻቸላቸው የነበረው በስደት ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ አርጋው አሽኔ ሲሆን፣ አርጋው በክሱ መዝገብ ላይ ‹‹የግንቦት 7 አመራር›› ተብሎ ነው የተጠቀሰው፡፡ አርጋው አሽኔም እንደ ተድላ ደስታ ሁሉ እንኳን የግንቦት 7 አመራር ሊሆን አባል መሆኑንም የሚያስረዳ ማስረጃ የለም፡፡ ዛሬ ዘላለምና አራቱ ፖለቲከኞች በወኅኒ 500ኛ ቀናቸውን ያከብራሉ፡፡ ያከብራሉ ይባላል ወይ ብላችሁ እንዳትጠይቁኝ! ሌሎቹም በዘላለም ሥም በሚጠራው መዝገብ ላይ ያሉ የሕሊና እስረኞች ከሰሞኑ 500 ቀን ይሞላቸዋል፡፡

እኛ ስንያዝ የተረፉ (እና የተሰደዱ) ጓደኞቻችን ሰው ሊረዳላቸው ያልገባቸው ፈተና ውስጥ እንደነበሩ ሲያደርጉ ከነበሩት እና ሲልኩብን ከነበሩ መልዕክቶች ሰምተናል፣ ተረድተናል፡፡ ፈረንጆች ይህ ዓይነቱን ጉዳይ ‘survival’s guilt’ (‹የተራፊዎች የጥፋተኝነት ስሜት› እንበለው?) ይሉታል አሉ፡፡ ከዚያ ደግሞ ድንገት ክሳቸው ተቋርጦ የወጡት አባሪዎቻችን እኛን የከዱን ዓይነት ስሜት ይንፀባረቅባቸው ነበር፤ ይኸው ‹የተራፊዎች የጥፋተኝነት ስሜት› ሳይሆን አይቀርም፡፡ ቀሪዎቹም ተራችን ደረሰና ተንጠባጥበን ስንወጣ እኔ የጓደኞቼን ሕመም በከፊልም ቢሆን የተረዳሁት የመሰለኝ ዘላለምን ተሰናብቼ ስወጣ ነው፡፡

ዘላለም እስሬን ካቀለሉልኝ ሰዎች ውስጥ ዋነኛው ነው፡፡ ውይይታችን፣ ንትርካችን ሁሉ የማይዘነጋ ነበር፡፡ ማታ፣ ማታ መታጠቢያ ክፍሉ ውስጥ ካለች ጠባብ ኮሊደር ውስጥ የባጥ የቆጡን እየቀባጠርን እስከ ሌሊቱ ሰባትና ስምንት ሰዓት የምንቆይበት ጊዜ ነበር፡፡ በተለይ አምስቱ አባሪዎቼ ድንገት የወጡ ጊዜ የነበረውን የሐሳብ ውዥንብር እና የእንቅልፍ መዋዠቅ ከእሱ ጋር በማውራት ነበር ሰውነቴን ያላመድኩት፡፡ በእስር ቤት ቋንቋ ገበታ በጋራ የሚቋደሱ ሰዎች፣ መቅዱስ ነበር የሚባሉት፡፡ ዘላለም መቅዱሴ ብቻ አልነበረም፡፡ ወኅኒ የሰጠኝ ጓደኛዬም ነው፡፡ አሁን እቤቴ ቁጭ ብዬ አስበዋለሁ፡፡ ሳያመሽ መተኛት አይችልበትም፤ በጣም ያመሻል፡፡ ለቆጠራ 12፡30 በራችን ሲንኳኳ ‹ሀንጎቨር› እንዳለበት ሰው ዓይኑ ቅልትልት ብሎ፣ ፎጣ ደርቦ ሲወጣ ይታወሰኛል፡፡ ኳስ ጨዋታ ሲኖር (እኔ ባልወድም) ከጎረምሳው ሁሉ ጋር ሲሟገት ይታየኛል፡፡ ሰው መንከባከብ ይችልበታል፤ ሲንከባከበኝ ትዝ ይለኛል ልበል? አዎ፣ እንደሚንከባከበኝ ስለማውቅ እኔም እቀብጥ ነበር፤ እሱም ሲንከባከበኝ አስገራሚ ነው፡፡

ዘላለም ወርቅአገኘሁ እና ጓደኞቹ (5 ሆነው) የመጪው ሰኞ፣ ሕዳር 13፣ 2008 ራሳቸውን ለመከላከል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ይቀርባሉ፡፡ እኔም እንደተመልካች ላያቸው እሄዳለሁ፡፡ አልጨብጣቸውም፡፡ እጄን የማውለበልብላቸው ከሆነ እንኳን ፈራ ተባ እያልኩ ነው፡፡ እኔ ከትልቁ እስር ቤት ሆኜ፣ እነርሱ ደግሞ ከጠቧቧ ሁነው ያዩኛል፡፡ ‹ሁላችንም ነጻ ካልወጣን፣ አንዳችንም ነጻ ወጣን ማለት አይቻልምና!›

መልካም ዕድል ከመመኘት በላይ ምን አቅም አለኝ፡፡ መልካም ዕድል፣ የክፉ ቀን ጓዴ! መልካም ዕድል!

Zelalem Workagenegu drawing by Melody Sundberg


ኀዳር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ማክሰኞ ሸዋ ሮቢት በቀወት ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የነበሩ እስረኞች በሙሉ ያመለጡ ሲሆን፣ እስረኞቹ እስካሁን አልተያዙም። አብዛኞቹ እስረኞች በህገወጥ መንገድ ትነግዳላችሁ ተብለው የተያዙ ነበሩ። እስረኞቹ ሌሊት ላይ የጭቃ ቤቱን ግድግዳ በውሃ አርሰው ከቀደዱት በሁዋላ ሁሉም በአንድ ላይ አምልጠዋል። ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ እስረኞችን ለመያዝ ፍተሻ በመካሄድ ነው። …

የዞን ዘጠኝ የድረ-ገጽ ጻሕፍት አባል የሆነው ዘላለም ክብረት የድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ተሟጋች ድርጅት ሽልማትን ለመቀበል ወደ ፈረንሳይ ለመጓዝ ሲሞክር ተከለከለ። በእስር ቆይተው ከተፈቱት ጋዜጠኞችና የድረ-ገጽ ጻሕፍት መካከል ፓስፖርቶቻቸው ያልተመለሰላቸው ወደ ቀድሞ የስራ ገበታቸው መመለስ የተከለከሉ መኖራቸውንም አስታውቀዋል።

ፈረንጅ ሆይ ናና ፈረንጅ ሆይ ናና አንተ ስትናገር ይታመናልና ፈረንጅ ሆይ ናና ፈረንጅ ሆይ ናና አንተ ስትናገር ትሰማለህና ፈረንጅ ሆይ፤ አንተ ገድላቱንና ድርሳናቱን፣ ዜና መዋዕሎችንና ታሪከ ነገሥቱን፣ የፍልስፍናውንና የጥበቡን፣ የመድኃኒቱንና የጠልሰሙን ነገር ከግእዝ ወደ እንግሊዝኛ ስትተረጉመው ሁሉም ያደንቅሃል፣ ያነብሃል፡፡ ይጠቅስሃል፡፡ …

ፈረንጅ ሆይ ናና – ዳንኤል ክብረት Read more »

ፓሪስ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ያለፈው ዓርብ የሽብር ጥቃቶች ከተካሄዱባቸው አካባቢዎች በየትኛውም ሥፍራ መቼም ሊገኙ ይችሉ እንደነበር እዚያው የሚኖሩ አንድ ኢትዮጵያዊ ገልፀውልናል፡፡

በራያና ቆቦ የሚኖሩ ገበሬዎች ከመንግስት በቂ የእህል እርዳታ ካላገኘን፥ ለከባድ የረሃብ አዳጋ እንጋለጣለን ብለው ይፈራሉ።

ኀዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-35ኛ አመት በአሉን በማክበር ላይ ያለው ብአዴን ፣ የመንግስት ሰራተኞች ፣ ተማሪዎች፣ ነጋዴዎችና በተለያዩ ሙያ የተሰመራዩት ሁሉ ስራቸውን አቁመውና ድርጅታቸውን ዘግተው በአሉን እንዲያከብሩ ተገደዋል። በበአሉ ላይ ባልተገኙት ላይ የተለያዩ ደረጃ ያላቸው ቀጣቶች እንደሚተላለፍባቸው የድርጅቱ ካድሬዎች ሲቀሰቅሱ መሰንበታቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል። በኮምቦልቻ፣ ደሴ ጎንደርና ሌሎችም ቦታዎች ህዝቡ ለብአዴን ሰልፍ …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

ኀዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ባለቤት አባት የሆኑት አቶ አሰፋ ሩዎ ሂወራ በሃዋሳ ከተማ የሚገኙ የተለያዩ ነዋሪዎችን የቤት ካርታ በመቀበል በአመት ከ25 ሺ እስከ 30 ሺ ብር እንደሚከፍሉ አስታውቀው የባንክ ብድር ከወሰዱ በሁዋላ፣ ብድሩን ለመመለስ ሳይችሉ በመቅረታቸው የቤታቸውን ካርታ ያስያዙ ሰዎች ቤታቸው በሃራጅ ሊሸጥባቸው መሆኑን ተናግረዋል። ነዋሪዎች …

የዓለም የጤና ድርጅት በአዳጊ ሃገራት የሚገኙ 225 ሚሊዮን የሚሆኑ ሴቶች እርግዝና እንዳይከሰት ለማድረግ ወይም ለማዘግየት ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን የወሊድ መከላከያ እንደማይጠቀሙ ያመለክታል።

ሀገራችን መሬት ላይ እንድ ሌላ ግዙፍ የርሀብና የችጋር ዳመና እያንዣበበ ነው። አንዳንድ ቦታም ግዳይ መጣል መጀመሩን እየሰማን ነው። ይህ ችግር በሰብዓዊ ዕውቀትና ሀይል የሚፈታ ሆኖ ለምንድነው እንዲህ እየተመላለሰ የሚጎበኘን? ሌሎች ሀገሮች ተመሳሳይ የአየር ሁኔታ ችግር እየገጠማቸው እንደኛ ለአዋራጅ ጉስቁልናና ልመና አልተዳረጉም። እኛ ጋ ምን የተሰወረብን ነገር አለ? የአፍሪካ የውሀ ሰገነት የምትባልና ከማንም የማይተናነስ የተፈጥሮ ጸጋ […]

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

የመልካም አስተዳደር መጓደል በልማት እንቅስቃሴ ላይ ትልቅ ማነቆ ነው። ሕዝብንም የልማት ውጤት ተጠቃሚ እንዳይሆን ያደርጋል፣ በሚል ሕዝብ እና መንግሥት አዘውትረው በቅሬታ ሲናገሩ ይሰማል።

የፕላስቲክ ቱቦዎችንና መገጣጠሚያ ማሽነሪዎችን ለማስመጣትና በአገር ውስጥ ለመገጣጠም ከኢትዮጵያውያን ጋር ባለድርሻ በመሆን ያቋቋሙትን ኩባንያ መጠቀሚያ በማድረግ፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኤልሲ ከፍተው ካገኙት የውጭ ምንዛሪ ውስጥ ከ62.2 ሚሊዮን ብር በላይ በውጭ ባንክ በመደበቅ የተጠረጠሩ ሁለት የውጭ ዜጐች ተከሰሱ፡፡

 

የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ክስ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ክስ የመሠረተባቸው ተጠርጣሪ ተከሳሾች፣ በትውልድ አሜሪካዊና በዜግነት ደቡብ አፍሪካዊ መሆናቸው የተገለጸው ሚስተር ማይክል ማትሰንርና እንዲሁም ግብፃዊ መሆናቸው የተገለጸው ሚስተር አይመን አብድል ሞተልብ ሙሳ ኢሳ መሆናቸው በክሱ ተገልጿል፡፡

ግለሰቦቹ የተከሰሱት በከባድ የማታለል ወንጀልና በሕገወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል መሆኑንም ክሱ ይጠቁማል፡፡

ተከሳሾቹ ድርጊቱን እንዴት እንደፈጸሙት ዓቃቤ ሕግ በክሱ እንደገለጸው፣ ኢትዮጵያውያንና ግብፃዊው ሚስተር አይመን በጋራ ባቋቋሙት ስታር ፓይፕና ፊቲንግስ ኩባንያ ውስጥ፣ ሚስተር ማትሰን ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው ይቀጠራሉ፡፡ ሚስተር አይመን ለብቻቸው ያቋቋሙት ጎልደን ትሬዲንግ ከሚባለው ኩባንያ በተጨማሪ ከሚስተር ማትሰን ጋር በጋራ ያቋቋሙት በዱባይ የሚገኝ ዋሶ ቴክኖሎጂ ግሩፕ የሚባል ኩባንያ አላቸው፡፡ በመሆኑም ተከሳሾቹ ከህንድና ከቻይና ወደ አገር ውስጥ እንደሚያስገቡ የገለጹትን የፕላስቲክ ቱቦና መገጣጠሚያ ማሽነሪዎችን፣ በኢትዮጵያ ንግድ መርከብ ለማጓጓዝ የተለያየ መጠን ያለው ዶላር ለማስጫኛ በመክፈል ዕቃዎቹን እንዳስገቡ መግለጻቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡ 

ተከሳሾቹ ከቻይናና ከህንድ ከ2004 ዓ.ም. እስከ 2005 ዓ.ም. ድረስ በኢትዮጵያ ንግድ መርከብ እያስጫኑ ዕቃውን ሲያስገቡ፣ ለማስጫኛ ያልተከፈለውን የገንዘብ መጠን፣ በሐሰተኛ የማስጫኛ ደረሰኝና የንግድ ሽያጭ ደረሰኝና በሐሰተኛ ማኅተም ተጠቅመው ወንጀሉን እንደፈጸሙ የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡

ተከሳሾቹ በቻይና የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ ወኪል የሆነው ‹‹የቻይና የውቅያኖስ አጓጓዥ ኤጀንሲ ሻንጋይ›› የሚል ሐሰተኛ የጭነት ደረሰኝ በማዘጋጀት፣ ‹‹የመጫኛ መነሻ ወደብ ሻንጋይ ቻይና፣ ጭነት ማራገፊያ ጂቡቲ የባህር ወደብ፣ መድረሻ ሞጆ ደረቅ ወደብና አጓጓዥ የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ›› የሚል ሐሰተኛ ሰነድ አዘጋጅተው የተለያየ መጠን ያለው ዶላር እንደተከፈለ በማስመሰል፣ ጠቅላላ ድምሩ 62,278,179 ብር ዱባይ ሚስተር ማይክልና ሚስተር አይመን በጋራ በዱባይ ማሽሩክ ባንክ በከፈቱት ‹‹ዋሶ ቴክኖሎጂ ግሩፕ›› ተብሎ በሚጠራው ድርጅታቸው አካውንት ውስጥ እንዲገባ ማድረጋቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡

ተከሳሾቹ የተጠቀሰውን ያህል ገንዘብ ዱባይ በሚገኘው የድርጅታቸው አካውንት ማሽሩክ ባንክ ያስገቡት፣ ለምሳሌ ዕቃውን ያስጫኑት በ19,000 ዶላር ከሆነ ኤልሲ ከፍተው የውጭ ምንዛሪ ከጠየቁት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቃሊቲ ቅርንጫፍ በሚያቀርቡት ሐሰተኛ ሰነድ 40,000 ዶላር እየተቀበሉ፣ ልዩነቱን ለግላቸው ማድረጋቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡ 

ቻይናና ህንድ ውስጥ ላለው ስታር ፓይፕና ፊቲንግስ ፋብሪካ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሲላክ ‹‹የተመረተበት አገር ቻይና፣ ለማሽነሪው ለአንዱ ብቻ የተከፈለ 385,370 ዶላር›› በማለትና ትክክለኛ ምርት ለማስመሰል ‹‹በስቴት ኦፍ ቴክሳስ ንግድ ምክር ቤት የተረጋገጠ›› የሚል ሐሰተኛ ሰነድ ማኅተም ተደርጐበት እንደቀረበ ክሱ ይገልጻል፡፡

በስቴት ኦፍ ቴክሳስ ንግድ ምክር ቤት በተመዘገበው የቻይና ኩባንያ የተመረተ እውነተኛ ምርት ለማስመሰል፣ ተከሳሾቹ ዋሶ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ፕሮፎርማ ሰብስቦ እንዳረጋገጠ የሚያሳይ የንግድ ደረሰኝ በማቅረብ፣ እውነተኛ አስመስለው በሐሰተኛ ሰነድ እየተገለገሉ፣ ከዘጠኝ ጊዜያት በላይ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የውጭ ምንዛሪ በመውሰድ የተጠቀሰውን ገንዘብ ዱባይ ወደሚገኘው አካውንታቸው ለማሸሽ መቻላቸውን ክሱ ያብራራል፡፡

ተከሳሾቹ ‹‹ለኢትዮጵያ ንግድ መርከብ በቻይና ውቅያኖስ ጉዞ ኤጀንሲ የተከፈለ የውጭ ምንዛሪ›› በማለት በሐሰት ባዘጋጁት የተለያየ ሰነድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያወጡትን የውጭ ምንዛሪ፣ ወደ ዱባይ ማሽሩክ ባንክ በመላክ ከባድ የማታለል ወንጀል መፈጸማቸውን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡

ሚስተር ማትሰን በቁጥጥር ሥር ሲሆን፣ በዋስትናው ላይ ብይን ለመስጠትና የክሱን ሒደት ለማስቀጠል ለኅዳር 8 ቀን 2008 ዓ.ም. ተቀጥሯል፡፡ ሚስተር አይመን ሊገኙ ባለመቻላቸው በጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግላቸው ትዕዛዝ ተሰጥቶ ለመጠባበቅ ለታኅሳስ 6 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡

ከሁለቱ የውጭ ዜጎች ጋር ክስ የተመሠረተባቸውና በ100,000 ብር ዋስ በውጭ ሆነው ክሳቸውን እንዲከታተሉ ትዕዛዝ የተሰጠባቸው ደግሞ አቶ ወሰንዓለም ገብረ እግዚአብሔር ይባላሉ፡፡

አቶ ወሰንዓለም የተጠረጠሩት ሚስተር ማትሰን የስታር ፓይፕና ፊቲንግስ ሥራ አስኪያጅ ሆነው ሳሉ፣ ከድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብ ውጪ ድርጅቱ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ካስቀመጠው ገንዘብ ውስጥ፣ ሦስት ሚሊዮን ብር ‹‹ለሚመለከተው ሁሉ›› ተብሎ በተሰጣቸው ውክልና በድርጅቱ ስም በማውጣታቸው መሆኑን ክሱ ያብራራል፡፡ በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈጸሙት በሌላ ሰው ጥቅም ላይ የሥራ አመራር ጉዳት ማድረስ ወንጀል መከሰሳቸውን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያብራራል፡፡     

 

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባባሪያ ቢሮ (OCHA) የአስቸኳይ መልስ ፋንድ ክፍል ሰርፍ (CERF) ለኢትዮጵያ ከገጠሙት ሁሉ የከፋ በሆነ ድርቅ ለተጎዱ ማህበረሰቦች የአስራ ሰባት ሚሊዮን ዶላር አስቸኩዋይ ርዳታ ትናንትና ሰጠ።

የወተቱ እንቆቅልሽ

አቶ ደረጀ ዳዲ በሰንዳፋ ከተማ ወተት አምራች ነው፡፡ የራሱን ብቻም ሳይሆን ከአካባቢው ገበሬዎች እየሰበሰበ አዲስ አበባ አምጥቶ ለአከፋፋዮች ያስረክባል፡፡ በቀን እስከ 800 ሊትር ወተት ያቀርብ የነበረ ቢሆንም፣ በቅርቡ የዓለም አቀፍ

የእንስሳት ምርምር ኢንስቲትዩት (IRLI) ጥናትን በመጥቀስ በአዲስ አበባና በአዲስ አበባ ዙሪያ ከሚገኙ ከተሞች በተሰበሰቡ ወተቶች ውስጥ አፍላቶክሲን የተሰኘ ኬሚካል መገኘት በመገናኛ ብዙኃን በመዘገቡ ምክንያት፣ ትልቅ ኪሳራ እንደደረሰበት አቶ ደረጀ ለሪፖርተር ገልጿል፡፡ በዚህም በአሁኑ ወቅት በቀን ከ300 ሊትር በላይ ማቅረብ አልቻለም፡፡ በወተት ውስጥ ለአፍላቶክሲን መገኘት ምክንያት የሆነው የሻገተ ፋጉሎ መሆኑ በጥናቱ ቢጠቀስም፣ ሪፖርተር በተለያዩ የሰንዳፋ ከተማ ወረዳዎች ተዘዋውሮ ያነጋገራቸው ወተት አምራቾች ፋጉሎን ለመኖነት መጠቀም ካቆሙ ዓመታት መቆጠራቸውን ገልጸዋል፡፡ ከኑግ ዘይት ሲጨመቅ ተረፈ ምርት የሆነው ፋጉሎ ዋጋ በኩንታል 800 ብር መሆኑም፣ ከዋጋ አንፃር ተመራጭ እንደማያደርገውም ያስረዳሉ፡፡ በበረህ ወረዳ ከዳቤ ቀበሌ ወተት አምራች የሆነው አቶ ይገዙ አሰፋም የአፍላቶክሲን መገኘት ዜና በእጅጉ ገቢያቸውን እንደጐዳው ገልጿል፡፡

ባለፈው ሳምንት ተቀባዮች ሙሉ በሙሉ ወተት እንዳልተረከቡት ይናገራል፡፡ እሱም በአካባቢው ፋጉሎን ለእንስሳት መኖ ጥቅም ላይ እንደማይውል፣ ይልቁንም ቢሾፍቱ ከተማ ከሚገኝ ዓለማ ካውዳይስ የእንስሳት መኖ ከተሰኘ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተመጣጠነ መኖ እየገዙ እንደሚጠቀሙ አስረድቷል፡፡ በበረህ ወረዳ ግራር ቀበሌ ኗሪና ለሰንዳፋ አካባቢ የእንስሳት መኖ አቅራቢና ወተት አምራች የሆነው አቶ ተሾመ መንግሥቱም፣ በአካባቢው ፋጉሎን ለመኖነት እንደማይጠቀሙ ይናገራል፡፡ እሱም በቀን እስከ 160 ሊትር ወተት ያቀርብ የነበረ ቢሆንም፣ ባለፈው ሳምንት ምንም ተረካቢ አለማግኘቱን ገልጿል፡፡ በወተት ንግዳቸው ላይ እንደዚህ ያለ ኪሳራ ያስከተለው መረጃ ትክክል አለመሆኑ በተደጋጋሚ በመገናኛ ብዙኃን ቢገለጽም፣ ብዙም የተቀየረ ነገር እንደሌለ አምራቾቹ ሪፖርተር ባነጋገራቸው ወቅት ገልጸዋል፡፡

ምርምሩ የተካሄደው ከአዲስ አበባ፣ ከቢሾፍቱ፣ ከሰበታ፣ ከሰንዳፋና ከሱልልታ ከተማ በተወሰዱ የወተት ናሙናዎች ላይ ሲሆን፣ አፍላቶክሲን በወተት ናሙናዎቹ ውስጥ (0.41 ማይክሮ ግራም በሊትር) መገኘት ዜና በኋላ ለወትሮ የወተት ገበያ ግርግር በነበረበት ሰንዳፋ ከተማ፣ ገበያው እረጭ ማለቱን ሪፖርተር በከተማው ተዘዋውሮ ካነጋገራቸው አምራቾች ማረጋገጥ ችሏል፡፡ አምራቾቹ ወጣ የተባለው ምርምር ገበሬውን ክፉኛ የጐዳ፣ በአገር ሀብት ላይም ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳደረ በመሆኑ ነገሮች ወደነበሩበት ይመለሱ ዘንድ መንግሥትና የሚመለከታቸው ሁሉ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ ጥናቱን በሚመለከት የመንግሥትንና ጥናቱን የሠራው የዓለም አቀፍ የእንስሳት ምርምር ኢንስቲትዩት አስተያየትን፣ እንዲሁም መንግሥት የወሰዳቸውን ዕርምጃዎች በሚመለከት የተጠናቀረው ዘገባ በማኀበራዊ ገጽ ላይ ይመልከቱ፡፡ (በዘገባው ሚሊ ግራም ተብለው የተቀመጡት መለኪያዎች ማይክሮ ግራም ተብለው እንዲነበቡ የዝግጅት ክፍሉ ያሳስባል)   

 

በ50 ሺሕ ብር ዋስ ይፈቱ የተባሉት መምህር ግርማ ይግባኝ ተጠየቀባቸው

በተጠረጠሩበት ሐሰተኛ ሰነድ መጠቀም ወንጀል ተጨማሪ ጊዜ ተጠየቀባቸው

የእሳቸው ተከታይና የሚሏቸውን ነገር ሁሉ ያደርጉ የነበሩን ግለሰብ ቤት በማሸጥና ገንዘቡንም እንዲፀለይበት በማለት ወስደዋል ተብለው ተጠርጥረው የታሰሩት መምህር ግርማ ወንድሙ፣ በ50,000 ብር ዋስ እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት በሰጠው ትዕዛዝ ላይ ፖሊስ ይግባኝ ማለቱ ታወቀ፡፡ 

የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ወንጀል ችሎት ለመምህር ግርማ የፈቀደውን የ50,000 ብር ዋስትና የተቃወመው ፖሊስ፣ ቅሬታውን ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ወንጀል ችሎት አቅርቧል፡፡ ፖሊስ ባቀረበው መከራከሪያ ነጥብ ላይ ብይን ለመስጠት ፍርድ ቤቱ ለኅዳር 13 ቀን 2008 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ 

ተጠርጣሪው ሐሰተኛ ሰነድ መጠቀማቸውን ገልጾ ፖሊስ ባቀረበው ክስ ምክንያት መምህር ግርማ ኅዳር 3 ቀን 2008 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀርበው የነበረ ሲሆን፣ እሳቸው ከቤተክህነት እንደተሰጣቸው የገለጹት ሰነድ በፎረንሲክ ተመርምሮ ሐሰተኛ መሆኑን እንዳረጋገጠ ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ ሌላ ተጨማሪ የሚመረመር ሰነድ እንዳለውና ተጨማሪ ሰነድ ሰጥተዋል የተባሉት የቤተ ክርስቲያን አባት በአገር ውስጥ አለመኖራቸውን በማስታወቅ፣ ተጨማሪ 14 ቀናት እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡ 

የመምህር ግርማ ጠበቆች ፖሊስ ያቀረበውን ማመልከቻና ተጨማሪ ቀናት በመቃወም፣ ደንበኛቸው በዋስ ተለቀው ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ጠይቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የጠበቆቹን ማመልከቻ በማለፍ የሰባት ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ለፖሊስ ፈቅዷል፡፡ 

 

አርሶ አደሩን በመግደል የተጠረጠረው ፖሊስ መሰወሩ ተጠቆመ

‹‹መያዣ አውጥተን እያፈላለግነው ነው›› ፖሊስ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሰያን ደብር ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ውስጥ፣ በአካባቢው የተመደበ ፖሊስ አርሶ አደሩን ገድሎ መሰወሩን የአካባቢው ነዋሪዎች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

ሟች አርሶ አደር ጌቱ ዘውገ የሚባል የ27 ዓመት ወጣት መሆኑን የገለጹት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ለመሞቱ ምክንያቱ የሆነው ጥቅምት 20 ቀን 2008 ዓ.ም. ከአንድ ሌላ አርሶ አደር ጋር በተፈጠረ አለመግባባት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የተጋጩበት ምክንያት ባይታወቅም ሟች አቶ ጌቱ ከአንድ የአካባቢው ሰው ጋር ሲጣላ የአካባቢው ነዋሪዎች ገላግለዋቸው ወደየቤታቸው የሄዱ ቢሆንም፣ በአካባቢው ግጭት እንደነበር ሪፖርት የደረሰው ተጠርጣሪ ምክትል ሳጅን ግርማ ብርሃኑ፣ ወደ  ሟች ቤት መምጣቱን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡ ተጠርጣሪው ምክትል ሳጅን ግርማ ሟችን ይጠራና ወደ ፖሊስ ጣቢያ ይዞት ለመሄድ በመነጋገር ላይ እያሉ ሌሎች ሁለት ፖሊሶች ይደርሳሉ፡፡ አንዱ ፖሊስ ሟች ላይ ድብደባ እየፈጸመበት እያለ፣ ምክትል ሳጅኑ በያዘው ክላሽኒኮቭ ጠመንጃ ተኩሶ እንደገደለው የአካባቢው ነዋሪዎች አስረድተዋል፡፡

በወቅቱ በተፈጠረው ግርግር ተጠርጣሪውን ማንም ሊይዘው እንዳልቻለና ወደ ላይ እየተኮሰ ከአካባቢው መሰወሩን የገለጹት ነዋሪዎቹ፣ በመተባበር በሟች ላይ ድብደባ የፈጸመበት ሌላው ፖሊስ መያዝና በሕግ መጠየቅ ሲገባው፣ ከአካባቢው ዞር ተደርጎ ሌላ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር መመደቡ የአካባቢውን ነዋሪዎች እንዳስቆጣ ተናግረዋል፡፡ ሟች በቅርቡ ትዳር የያዘ መሆኑንና ቤተሰቡን እንደሚረዳ፣ በአካባቢው ተወዳጅ ወጣት አርሶ አደር እንደነበር የሚናገሩት ነዋሪዎቹ፣ በቤተሰቦቹ ፊት በጠራራ ፀሐይ ገድሎት የተሰወረውን የፖሊስ ባልደረባ የክልሉና የፌዴራል መንግሥት ለሕግ እንዲያቀርቡት ጠይቀዋል፡፡

በአርሶ አደሩ ላይ ተፈጽሟል ስለተባለው የግድያ ወንጀል ማብራርያ እንዲሰጡ ሪፖርተር ያነጋገራቸው በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደነባ ወረዳ ፖሊስ መምርያ ኃላፊ ኢንስፔክተር መስፍን ደጉ ግድያው መፈጸሙን አረጋግጠዋል፡፡ ወንጀሉ እንደተፈጸመና ተጠርጣሪው ምክትል ሳጅን ግርማ ብርሃኑ ግን እንዳልተያዘ የገለጹት የመምርያ ኃላፊው፣ ፖሊስ ምርመራውን ጨርሶ መያዣ በማውጣት ተጠርጣሪውን ለመያዝ እየሠራ መሆኑንና ከኅብረተሰቡ ጋር ተባብረው በቅርቡ በቁጥጥር ሥር እንደሚያውሉት ተናግረዋል፡፡

ግድያው የተፈጸመው በሁለት ግለሰቦች መካከል በተነሳ ፀብ ምክንያት መሆኑን በተደረገው ምርመራ መረጋገጡን የገለጹት ኢንስፔክተሩ፣ ሟች ለሕግ አልገዛም በማለት በፖሊሶች ላይ ዕርምጃ ሊወስድ ሲል ግድያው ሊፈጸም እንደቻለ መረጃ ማግኘታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የአካባቢው ፖሊስና ነዋሪዎች ተስማምተውና ተከባብረው እንደሚኖሩ የገለጹት የመምርያ ኃላፊው፣ አንዳንድ ጊዜ ሳይታሰብ ወንጀል የሚፈጸም በመሆኑ ፈጻሚውን በሕግ ፊት ማቅረብ ግድ ስለሆነ፣ የተቻለውን ሁሉ በማድረግ ተጠርጣሪውን ይዞ ለማቅረብ አስፈላጊው ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ 

 

“ሃብት ያለው ሰው አይታሰርም። ተፈርዶባቸው እስር ቤት ያሉ ባለ ሃብት መንገድ ላይ ሲሄዱ ሌላ ሰው ገጭተው ሌላ ክስ ተመሠረተባቸው። አቃቤ ሕግ ምሥክር ማስፈራራት የሃሰት መረጃ ማስጠናት። በጥናቱ ካገኘናቸው ውስጥ ናቸው።” አቶ ተካ ገብረ የሱስ፤ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዲሬክተር።

    በቅርቡ የተቋቋመው የኩላሊት እጥበት ማዕከል፣ ለኩላሊት ሕመምተኞች የእጥበት ህክምና ለመስጠት በኤስ ኤም ኤስ እያሰባሰበ ያለው ገንዘብ፣ “ለታለመለት ዓላማ አልዋለም”፤ መባሉ እያወዛገበ ነው፡፡ ባለፈው አርብ ጥቅምት 26 ሬዲዮ ፋና ባስተላለፈው ዘገባ፣ ማዕከሉ ለኩላሊት ህመምተኞች የእጥበት አገልግሎት ለመስጠት ከህዝብ ከሚሰበሰበው የበጐ አድራጐት ገቢ፣ ኮሚሽን እየከፈለ መሆኑን ጠቅሶ ድርጊቱ ህገወጥ ነው ብሏል፡፡ 524 ሺህ ብር ኮሚሽን ተቀብያለሁ ያሉ ግለሰብም በዋቢነት ማቅረቧ ታውቋል፡፡ የማዕከሉ የቦርድ አባልና የገቢ አሰባሳቢ ኦፊሰር ደራሲና ዳይሬክተር አንተነህ ሃይሌ በበኩሉ፤ “የኩላሊት እጥበት ማዕከሉ በSMS ከህዝብ ከሰበሰበው 7 ሚሊዮን ብር ውስጥ 4 ሚሊዮን ብር ተመዝብሯል የሚል ዘገባ በሬዲዮ ፋና መሰራጨቱን ጠቁሞ፤ 7 ሚ. ብር የሚለውን ከየት አምጥቶ እንዳወራ አናውቅም ብሏል፡፡ “የፋና ሃሰተኛ ዘገባ የህዝቡን በጐነት የሚረብሽና የህሙማንን ህልም የሚያጨልም ነው፤” ሲልም ተችቷል፡፡“የፋና ዘገባ እውነትን ማዕከል ያደረገ አይደለም፤” ያሉት የማዕከሉ የቦርድ ሰብሳቢ ኢንጂነር ሳሙኤል ይርጋ፤ “ለሚሠራው ሥራ የሚከፈል ኮሚሽን የለም” ሲሉ አስተባብለዋል፡፡ማዕከሉ ከገራዶ ፊልም ፕሮዳክሽን ጋር ስለፈጸመው የሥራ ውል የተጠየቁት ሰብሳቢው፣ “ማዕከሉ ሥራ ሲጀምር ምንም ገንዘብና የሰው ሃይል ስላልነበረው የኤስኤምኤሱን አጠቃላይ ሥራ እንዲያከናውንና ለእድለኞች ሽልማት ከገቢው ከ10 በመቶ ያልበለጠ ሒሳብ እንዲወራረድለት ውል ፈጽመናል” ብለዋል፡፡ እያንዳንዱም ወጪ በደረሰኝ እንደሚገባና እንደሚወጣ ከቀሪው ጋር የሚያሳይ የባንክ ስቴትመንት እንዳለ ገልፀዋል፡፡ ሬዲዮ ፋና ያለ መረጃ ያሰራጨውን ዜና በተመለከተ፣ ይቅርታ እንዲጠይቀን ደብዳቤ አስገብተናል – ብለዋል ሰብሳቢው፡፡

ፓትርያርኩ ከካቶሊክ ጋር ያለን ሃይማኖታዊ ልዩነት “ጠባብ ነው” ማለታቸው እያነጋገረ ነው

    የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ ከካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጋር ያለን ልዩነት “ጠባብ ነው” ማለታቸው እያነጋገረ ነው፡፡ፓትርያርኩ ይህን የተናገሩት ባለፈው ሳምንት በዓዲግራት ሀገረ ስብከት ተገኝተው የደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያንን በመረቁበት ወቅት ሲሆን በሥነ ሥርዓቱ ላይ የትግራይ ክልል ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ተስፋ ሥላሴ መገኘታቸውን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ድረ ገጽ ዘግቧል፡፡
ፓትርያርኩ አቡነ ማትያስ፣ “ከካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጋር  ያለንን ጠባብ የሃይማኖት ልዩነት ጠብቀን፣ በዜግነታችንና በክርስቶስ ልጅነታችን በዋና ዋና የልማት ሥራዎች ዙሪያ በጋራ በመሥራት፣ ለክርስቶስም ለሰው ልጅም ደስታን የሚሰጥ አገልግሎት ማበርከት  ይጠበቅብናል፤” ብለዋል – ድረ ገጹ እንደዘገበው፡፡ይሁንና የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንና የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ያላቸው የእምነትና የሥርዓት አስተምህሮ ልዩነት መሠረታዊ መሆኑን የጠቀሱ አስተያየት ሰጪዎች፣ ፓትርያርኩ ሃይማኖታዊ ልዩነቱ ጠባብ እንደሆነ ተናግረዋል ተብሎ በሰፈረው ዘገባ ግር መሰኘታቸውን ጠቁመዋል፡፡

   በስፔናዊው ሚጌል ሊያንሶ ተፅፎ የተዘጋጀውና ከ60 በላይ በሚሆኑ ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫሎች ላይ ተሳትፎ፣ 10 ሽልማቶችን ያሸነፈው “Crumbs” (ስብርባሪ) የተሰኘው ሳይንሳዊ ልብወለድ ፊልም፤ ትላንት ምሽት በአቤል ሲኒማ ተመረቀ፡፡ ከዓለም ጦርነቶች ፍፃሜ በኋላ ምን ሊፈጠር እንደሚችል በሚያመለክተው በዚህ ፊልም ላይ ዳንኤል ታደሰ (ጋጋኖ) በመሪ ተዋናይነት የተጫወተ ሲሆን ባሳየው የትወና ብቃትም አድናቆት ተችሮታል ተብሏል፡፡ ለትወናው አምስት ሺህ ዩሮ (125ሺ ብር) እንደተከፈለው ጋጋኖ ለአዲስ አድማስ ተናግሯል፡፡ ፊልሙ በአውሮፓና በአሜሪካ በተለያዩ ከተሞች ለእይታ ቀርቦ አድናቆትን ያተረፈ ሲሆን ከ60 በላይ ዓለም አቀፍ ፊልም ፌስቲቫሎች ላይ ተሳትፎ፣ ከ10 በላይ ሽልማቶችን ማግኘቱን የፊልሙ ፕሮዲዩሰር አርቲስት ዮሐንስ ፈለቀ ገልጿል፡፡ “ክረምብስ” ፊልምን፣ ለመስራት 200ሺ ዶላር እንደፈጀ ተናግሯል፡፡   

ኀዳር ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለስድስት ከፍተኛ ጡረተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ለእያንዳንዳቸው በ25 ሚሊየን ብር ወጪ በስጦታ የሚለገሳቸው የመኖሪያ ቤት እየተገነባ መሆኑ ሰሞኑን በመገናኛ ብዙሃን ይፋ ከሆነ በሁዋላ በአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል፡፡ በተለይ በረሃብ ምክንያት ከ 15 ሚሊየን ያላነሱ ወገኖችን ችግር ላይ በወደቁበት፣ በከተሞች አካባቢ ከፍተኛ ኑሮ ውድነትና የስራ …