በደቡብ ሱዳን ለወራቶች ከዘለቀ ከፍተኛ ግጭትና ጦርነት በኋላ፤ የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳል ቫኪርና ተቀናቃኛቸዉ የቀድሞዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪኤክ ማቸር የተኩስ አቁም ስምምነት ተፈራረሙ። ይህ ትናንት ምሽት የተደረሰዉ ስምምነት፤ በተፈረመ በ24 ሰዓታት ዉስጥ ተግባራዊ እንደሚሆን ተገልፆአል።

ፓትርያርኩ ዛቻ ያሰሙበትን ድንገተኛ ስብሰባ ያስተባበሩት የፅልመታዊው ቡድን ቀንደኞች እነንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ፡- ‹‹ቅዱስ አባታችን አይዞዎት፤ እኛ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ እንድንገኝ መድረክ ይፍጠሩ፤ እስከ መጨረሻው እንታገላለን›› በማለት አጋርነታቸውን ገልጸውላቸዋል፡፡ የቅ/ሲኖዶሱ ጽ/ቤት የፓትርያርኩ አካሔድ የምልዓተ ጉባኤውን ውሳኔ እንደሚጋፋ በመጥቀስ የተቃወማቸው ሲኾን የጠቅ/ቤተ ክህነቱ ዋ/ሥራ አስኪያጅም ለኹለት ዓመት የዘገየው የደንቡ ማሻሻያ ረቂቅ በመጪው ምልዓተ ጉባኤ ጸድቆ …

በእዮብ መሳፍንት

  1. በህቡዕ መደራጀት

በህቡዕ መደራጀት ወንጀል ነው???
በኢፌድሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 31

“ማንኛውም ሰው ለማንኛውም አላማ የመደራጀት መብት አለው፡፡ ሆኖም አግባብ ያለውን ህግ በመጣስ ወይም ህገመንግስታዊ ስርአቱን በህገወጥ መንገድ ለማፍረስ የተመሰረቱ ወይም የተጠቀሱትን ተግባራት የሚያራምዱ ድርጅቶች የተከለከሉ ይሆናሉ”

 ይላል፡፡ ከዚህ አንቀፅ በግልፅ እንደምንረዳው በህቡዕም ሆነ በግልፅ መደራጀት መብት ነው፡፡ መደራጀት የሚከለከለው “ህግ በመጣስ ወይም ህገመንግስታዊ ስርአቱን በህገወጥ መንገድ ለማፍረስ” ከሆነ ብቻ ነው፡፡
ስለሆነም “ፖሊስ” (በተግባር ከሳሹ ኢሃዲግ ቢሆንም) በዞን 9 ጦማሪያን ላይ ባቀረበው ክስ በህቡዕ መደራጀትን በራሱ ወንጀል ለማስመሰል መሞከሩ ከህግ አግባብ ውጪ ብቻ ሳይሆን ህገመንግስቱን የሻረና የናደ ተግባር ነው፡፡ አላማውም ማንኛውንም መደራጀት ማስፈራራትና ሰዎችን ከመደራጀት እንዲቆጠቡ ማድረግ እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡ ሲጀመር ዞን9 የጦማሪያን ስብስብ እንጂ ህጋዊ ሰውነት ያለው የተደራጀ አካል ወይም ድርጅት አይደለም፡፡ ለዚህም ነው አቃቤ ህግ ዞን 9ን በቀጥታ ሊከሰው ያልቻለው (በህግ መሰረት ህጋዊ ሰውነት የሌለውን አካል መክሰስ ስለማይቻል)፡፡ መሰባሰብን እና መደራጀትን በቅድሚያ መለየት ያስፈልጋል፡፡ ሁሉም ስብስብ መደራጀት አይደለም፡፡
ከዚህ በፊት በልጆቹ ላይ ፖሊስ መስርቶት የነበረውን “ራሱን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ብሎ ከሚጠራ ድርጅት ጋር አብሮ መስራት” የሚለው ክስ እንደማያዋጣ እንደገባው ሁሉ አሁንም ይሄኛው ክስ አያዋጣም፡፡

      2.    ሁለተኛው የክሱ ነጥብ “ከሽብርተኛ ቡድን ጋር አብሮ መስራት”
ይህ ሽብርተኛ የተባለው ቡድን የትኛው እንደሆነ ባይገለፅም በኢትጲያ ውስጥ ሽብርተኛ የተባሉት ግንቦት 7፣ ኦነግ፤ ኦብነግ እና አልቃይዳ ብቻ ናቸው፡፡ ስለዚህም ልጆቹ ከነዚህ ድርጅቶች ከአንዱ ጋር ሰርተዋል ብሎ ፖሊስ ካመነ ማስረጃ ሊኖረው ይገባል መለት ነው፡፡ ስለዚህም ማስረጃ ላሰባስብ በሚል ፖሊስ ተጨማሪ ጊዜ መጠየቁ አስቂኝ ነው፡፡ መጀመሪያ አስሮ ማስረጃ ማሰባሰብ ማለት ወንጀል መፈብረክ እንጂ ወንጀልን መክሰስ ዐያደለም፡፡
ከነዚህ ከላይ ከጠቀስኳቸው ድርጅቶች ውስጥ አንደኛው የውጭ ሀገር ድርጅት ሌሎቹ ሁለቱ ደግሞ ብሄር ተኮር ድርጅቶች ስለሆኑ ፖሊስ ሊል ያሰበው ምናልባት ግንቦት 7ን ሊሆን ይችላል ወይም ባለፈው ክስ “ራሱን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ብሎ ከሚጠራ ድርጅት” ያሉትን ድርጅት ደረጃውን ወደ አሸባሪ ድርጅት ከፍ አርገውት ሊሆን ይችላል፡፡ እኔ በግሌ ልጆቹ በብሎጋቸው የፃፉት ሰላምን፤ አንድነትን፤ ፍቅርን፤ የሰባዊ መብት መከበርን፤ ዶሞክራሲን እንጂ አንድም ቀን ሽብርን ሲፅፉ አይቼ አላውቅም፡፡ እነዚህ ነገሮች ሽብር ከተባሉም ሽብር መልካም ነገር እንጂ መጥፎ ነገር አይደለም፡፡
ስለዚህም እጠይቃለሁ የዞን 9 ጦማሪያን ወንጀል ሰርተዋል ብዬ አላምንምና ባስቸኳይ ይፈቱ፡፡ Zone9
‪#‎freezone9bloggers‬

ሄኖክ የሺጥላ
አዲሱን ( የነበረውን ግን ሰሞኑን የሾረውን ) የ ” ኦሮሞ ወጣቶች ” ግድያ። በነገራችን ላይ ለምንድን ነው ” የኢትዮጵያ ወጣቶች ” የማንለው ? ማለት ስለማንፈልግ ? ወይስ ብንል ባንል ምን ይጠቅማል ( ምንስ ይጎዳል በሚል ሃሳብ ?) ሁለቱንም ያዙልንና እንቀጥል። ሰሞኑን አምቦ ላይ የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ ወዳጆች ” ልጅ ሄኖክ በዚህ ጉዳይ ላይ አንድ ነገር በል እንጂ” ጠላቶች ደሞ ” አንተ ምንትስ አማራ አሁን አማራ ቢሆን ኖሮ ይሄ ሁሉ መከራ የደረሰበት አምሳ ገጽ ጽፈህ ፣ ነገሩን ለውጠሕና ለጥጠህ ባቀረብከው ነበር ” የሚሉ መልዕክቶችን አስቀምጠውልኛል። እኔም እንደ ለገዳዲ ሬዲዮ ” ጦማሪዎችች ሆይ ምልእክታችሁ ደርሶኛል ለሁሉም እንደነገሩ ለመመለስ እንሆ–“

ሙሉውን አስነብበኝ …

Fekahmed Negash, Director of Transboundary Rivers of Ethiopia commenting on Abdel-Fatah El-Sisi’s statement regarding river Nile and cooperation between Ethiopia and other African countries

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ካራቱሪ የተባለዉ የህንድ ኩባንያ ጋምቤላ ዉስጥ ለእርሻ ሥራ የተሰጠዉን አንድ መቶ ሺህ ሄክታር መሬት ማልማትን ትቶ ከቀረጥ ነፃ የገቡ ማሽኖችን በማከራየት ሥራ መጠመዱን ሠራተኞች አመለከቱ።

በኦሮምያ ክልል ለአዲስ አበባና ለኦሮምያ ልዩ ዞኖች የተዘጋጀውን ማስተር ፕላን በመቃወም ባለፈው ሳምንት ሰልፍ በወጡ በተለያዩ የኦሮምያ ክልልየሚገኙ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ላይ የተወሰደውን እርምጃ በመቃወም ዛሬ ጠዋት በርሊን ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ።

ሁለት በጀርመን የሚኖሩ ወጣቶች በተለይ ኢትዮጵያ ለሚገኙ የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ተማሪዎች የሚሆን አንድ የትምህርት መማሪያ ድረ ገፅ ሰርተዋል።ስለዚህ የትምህርት ድረ ገፅ አላማ እና አጠቃቀም መስራቾቹ በዛሬው የወጣቶች ዓለም ይገልፁልናል።

የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች ለዛሬ እንደተቀጠረዉ ለፊት ለፊቱ ዉይይት አዲስ አበባ ገብተዋል። ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር ዛሬ ከቀትር በፊት መድረሳቸዉ ሲገለፅ፤ የቀድሞ ምክትላቸዉና የአማፅያኑ መሪ ሪክ ማቻር ደግሞ ትናንት ማምሻዉን ነዉ አዲስ አበባ ገብተዉ ያደሩት።

ጫቱን ሲያስገቡ የተያዙት የሦስት ዓመት እስራት ይጥበቃቸዋል
በሕገወጥ መንገድ ከሎንዶን ወደ ስዊድን ሲግባ የተያዘ ጫት Chat, Foto: Scanpix

Ethiopia Zare (ዓርብ ግንቦት 1 ቀን 2006 ዓ.ም. May 9, 2014)፦ 816 ኪሎ ጫት ከሎንዶን በስዊድንዋ የወደብ ከተማ ጉተምበርግ በኩል በመርከብ ተጭኖ ሲገባ አፕሪል ላይ መያዙንና ሁለት ሰዎችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ሜትሮ ጋዜጣ በዛሬው ዕትሙ አስነብቧል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ባለፈው ጊዜ በተከታታይ የዴር ሡልጣንና ከዚያም ጋር የሚያያዙ ጉዳዮችን ስናነሣ ነበር፡፡ ምን መደረግ አለበት በሚለውም ዙሪያ ስድስት ነጥቦችን አንሥተናል ዛሬ የመጨረሻውን ክፍል እነሆ፡፡

7. ዲያስጶራውን ማንቀሳቀስ

ወደ ኢየሩሳሌም ቅዱሳት መካናትን በመሳለም ረገድ ዲያስጶራ ኢትዮጵያውያን ብዛታቸው እየጨመረ ነው፡፡ በውጭ የሚገኙት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናትም ቁጥር ከዓመት ዓመት እጨመረ ይገኛል፡፡ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን እንዲሆን ለኢትዮጵያ ታሪክ፣ ቅርስና ዝና ተቆርቋሪ የሆኑትን ሌሎች ወገኖች በማስተባበር ዲያስጶራው የዴር ሡልጣንን  ይዞታ በማስጠበቅ፣ ዲፕሎማሲያዊ ሥራ በመሥራትና የሕግ ድጋፍ በማድረግ ተግባራት ላይ እንዲንቀሳቀስ ማድረግ ይገባል፡፡

አንዳንድ በአሜሪካን ሀገር የሚገኙና ከሲኖዶሱ የተለዩ ወገኖች ክፍፍሉን ወደ ኢየሩሳሌም ለማዝመትና በቅድስቲቱ ሀገር እርስ በርሳቸው የማይስማሙ ሁለት ማኅበረሰቦችን ለመፍጠር፣ ጥንታዊው ቦታም ተረስቶ እንዲቀር የሚያደርጉትን ጥረት በመግታት በኢየሩሳሌም ቅዱሳት መካናት ጉዳይ የተባበረ እና የማይከፋፈል የኢትዮጵያውያን ድምጽ እንዲኖር ማድረግ ያሻል፡፡

በእሥራኤል የሚገኙ የኢትዮጵያ ቅዱሳት መካናትን በተመለከተ ዓለም ዐቀፋዊ ሲምፖዝየምና የውይይት መድረክ በማዘጋጀት፣ ዐውደ ርእዮችን በማቅረብ፣ ግብጾች በገዳሙ ላይ የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ በዓለም ዐቀፍ መድረኮች በመገዳደር፣ ጉዳዩ የዓለም ዐቀፍ ሚዲያዎችን ትኩረት እንዲያገኝ በማድረግ፣ የዴር ሡልጣን መነኮሳት እየኖሩበት ያለው የአኗኗር ሁኔታ ከዓለም ዐቀፍ የሰዎች የመኖርና የመኖሪያ ቦታ መብት አንጻር ያለበትን ደረጃ በማሳየት፣ የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች ለመነኮሳቱ የመኖርና ለመኖር የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች የማግኘት መብት እንዲሟገቱ በመወትወት ዲያስጶራው የማይናቅ አስተዋጽዖ ሊያደርግ ይችላል፡፡

8. ቤተ እሥራኤላውያንን ማንቀሳቀስ

ኢትዮጵያ ውስጥ ለሺ ዓመታት የኖሩ ቤተ እሥራኤላውያን ዛሬ በእሥራኤል ይገኛሉ፡፡ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ፍቅርና ክብር ያላቸው፣ ጉዳያችንንም ጉዳያቸው የሚያደርጉ ቤተ እሥራኤላውያንም አሉ፡፡ የሩሲያ ቤተ ክርስቲያን ከሩሲያ በመጡ ቤተ እሥራኤላውያን የምታገኘውን ድጋፍ ምሳሌ ያደረገ ድጋፍ እንዲያደርጉ ቤተ እሥራኤላውያንን ማስተባበር ይቻላል፡፡

በእሥራኤል ፓርላማ ጉዳዩ እንዲታይ፣ የግብጻውያን ጫና እንዲቀንስ፣ የኢትዮጵያውያን መነኮሳት የመኖር መብት እንዲከበር፣ የቦታው የባለቤትነት ክርክር እንዳለ ሆኖ ነገር ግን በእሥራኤል የኑሮ ደረጃ ለአንድ ሰው የሚያስፈልጉት መሠረታዊ ፍላጎቶች ለዴር ሡልጣን መነኮሳት እንዲሟሉ፣ በዴር ሡልጣን በሚገኙት የሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ማኅበረሰቦች መካከል መለስተኛ ውይይቶች እንዲጀመሩ በማድረግ ረገድ ቤተ እሥራኤላውያን የማይተካ ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ፡፡

9. ጠንካራ የገዳም ሕግ ማውጣት

በእሥራኤል የሚገኙት የኢትዮጵያ ገዳማትና ገዳማውያንን የሚመለከት ጠንካራ ገዳማዊ ሕግ ያስፈልጋል፡፡ ትምህርትና፣ አገልግሎትን፣ ሥራን፣ ጸሎትን፣ የንብረት አስተዳደርን፣ ከገዳም መውጣትንና መግባትን፣ ሀብትን፣ የዲሲፕሊን ሕጎችንና ሌሎች ጉዳዮችን የተመለከቱ ሕጎች ያስፈልጋሉ፡፡ ለመሆኑ ቅዳሴ በፍላጎት ነው የሚከናወነው? ሰው የሚጠፋበት ጊዜ የለም? የሌሊቱ አገልግሎትስ ሰላም ነው? አንድ መነኮስ ጠዋት ኪዳን ካደረሰ ወይም የአገልግሎት ተረኛ ካልሆነ ምን ሲሠራ ነው መዋል ያለበት? ለአስጎብኝነት ተግባርስ የሚመድበው ማነው? ወደ ሌሎች አገሮች የሚደረገው ጉዞስ እንዴት ነው መፈቀድ ያለበት? አንድ መነኮስ ንግድ ማካሄድ ይችላል? ለመሆኑ ሁሉን መነኮሳት የሚመለከት የጸሎት መርሐ ግብር አለ? ወይስ ለጸሎት የሄዱ መነኮሳት ሰሞነኛ መሆን አለባቸው? ገዳሞቻችን ጠንካራ የዲስፕሊን ሕግ ያስፈልጋቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ መነኮሳትን በተመለከተ የኢየሩሳሌም ተሳላሚ አውሮፓውያን የጻፏቸው መዛግብት ሁሉ ለጸሎት፣ ለትምህርትና ለፍጹማዊ ምናኔ የሚሰጡትን ቦታ በአድናቆት የሚያነሡ ናቸው፡፡ በ18ኛው መክዘ በሊባስ የነበረ አንቶንዮ የተባለ ፍራንቺስካን ስለ ኢየሩሳሌም መነኮሳት በጻፈው አንድ የጉዞ ማስተዋሻ ላይ ‹‹ወደ ጎልጎታ በሚወስደው መንገድ ላይ በአነስተኛ ቤተ መቅደሶች የሚገለገሉ ኢትዮጵያውያን ይገኛሉ፡፡ እነዚህ መነኮሳት ወደ ሊባኖስ በየዓመቱ ይዘልቃሉ፡፡ እነርሱ ሲመጡ ለመባረክ የኛ ምእመናን ሳይቀሩ ትተውን ይሄዳሉ፡፡ ልብሳቸው አዳፋ ነው፡፡ አንዳንዶቹም ቆዳ ይለብሳሉ፡፡ ሕዝቡ ልብሳቸውን ቀድዶ ይወስደዋል፡፡ ለእነርሱም የሚበቃቸውን እህል ይሰጧቸዋል፡፡ የሚመጡበት ወቅት እዚህ በጉጉት ነው የሚጠበቀው›› ይላል፡፡ ይኼ ነገር ዛሬ እንጥፍጣፊውስ አለ?

10. የተቀናጅ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ

ዴር ሡልጣንንና ሌሎች በቅድስት ሀገር የሚገኙ ቦታዎቻችንን በተመለከተ የሚነሡ ነገሮች ሁሉ ድንገቴዎች ናቸው፡፡ አሁን ባሳለፍነው የትንሣኤ በዓል እንኳን ስምንት መቶ ሺ ዶላር ስለሚያወጣ ቦታ ግዥ ሲነገር ነበር፡፡ ከዚህ በፊትም ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ የተጠመቀበትን ቦታ ስለመግዛት ይነሣ ነበር፡፡ ጃንደረባው የተጠመቀበት ቦታ ግዥ የት እንደደረሰ ሳይታወቅ አሁን ደግሞ ሌላ ሃሳብ መጣ፡፡ የዚህኛው ግዥም ቢሆን ዝርዝር ፕሮጀክቱ አልተገለጠም፡፡ እንዴው ብቻ ገንዘብ አዋጡ ነው የተባለው፡፡

የኢየሩሳሌም ቅዱሳት መካናትን በተመለከተ ሊኖረን የሚገባው አሠራር የተቀናጀና የታሰበበት ስትራቴጂያዊ ዕቅድን የተከተለ መሆን አለበት፡፡ አባቶች በተቀያየሩ ቁጥር የማይቀየር፣ በሚገባ ታስቦበት ቢያንስ ለዐሥር ዓመት እንዲያገለግል ሆኖ የተዘጋጀ፣ የሁሉንም ተሳትፎ ያካተተ መሆን ይገባዋል፡፡ አንዱ ተነሥቶ ይህንን እንገንባ፣ ሌላው ተነሥቶ ያኛውን እንግዛ፣ ሌላው ተነሥቶ ይህን እናሠራ ማለት የለበትም፡፡ የገዳሙ የወደፊት ዕድገት፣ ያሉበት ችግሮች፣ ችግሮቹን እንዴት በቅደም ተከተል መፍታት እንደሚቻል፣ ለዚህ የሚያስፈልገው ወጭ፣ ወጭው ከየት እንደሚሸፈን፣ የሚሠራው ነገር የአስተዳደሩ ጉዳይ፣ በሚገባ ሊመለሱ ይገባቸዋል፡፡

በጣም የሚገርመው ነገር ኢየሩሳሌም ላይ ሕዝቡን አስተባብሮ ዘመን የሚሻገር ሥራ መሥራት ሲቻል ምእመናን ሁልጊዜ የሚነገራቸው በአልዓዛር ለሚገኙ አረጋውያን ጋቢ እንዲያመጡ ነው፡፡ ለምን ዘላቂ በሆነ መንገድ ችግራቸውን አንፈታውም? ዛሬ ወጣት መስለው የሚታዩት መነኮሳትስ ነገ እዚያ አይደለም እንዴ የሚጦሩት? ያ ሁሉ ጋቢ እዚያ ምን እንደሚሠራ መድኃኔዓለም ይወቀው፡፡

በአሁኑ ጊዜ አስጎብኝዎቹ በዝተዋል፡፡ ሁኔታውን ስናየው የማስጎብኘቱ ሥራ ከመጀመሪያው ትውልድ ወደ ሁለተኛው ትውልድ እየተሸጋገረ ነው፡፡ ከዛሬ አርባና ሃምሳ ዓመታት በፊት ማስጎብኘቱን የጀመሩት አካላት በአዳዲስ ትኩስ ኃይሎች እየተተኩ ነው፡፡ ይህንን ዕድል በተቀናጀ ስትራቴጂ መምራት ያስፈልጋል፡፡ እያንዳንዱ አስጎብኝ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ዐውቆ፣ ለዚያም ተዘጋጅቶ እንዲሠራ ያደርገዋል፡፡ ለተሳላሚነት የሚመጣው ሕዝብም በየዓመቱ በተሠራው ላይ እየተወያየ በቀረው ላይ እየጨመረና የራሱን ኃላፊነት እየወሰደ እንዲያበረክት ያደርገዋል፡፡ አንድ ትውልድ ሲያልፍ አሻራውን አስቀምጦ እንዲያልፍም ያደርጋል፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ወደ ኢየሩሳሌም በአዲስ መንገድ ጉዞ የተጀመረበትን ሃምሳኛ ዓመት እያከበርን ባለንበት ዘመን ላይ ሆነን የሠራነውን ሥራ ብንገመግመው ሕዝብ ከማጓጓዝ የዘለለ ውጤት አናገኝበትም፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ገዳሞቻችን የዕጣን መቀመሚያ፣ የሻማ መሥሪያ፣ የጠበል ማሸጊያ፣ የቅብዐ ቅዱስ ማዘጋጃ፣ የቅዱሳት ሥዕላት ማተሚያ፣ የቅዱሳት መጻሕፍት ማዘጋጃ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ያ ሁሉ ተሳላሚ ወደ ገዳሞቻችን ሲሄድ የሚገዛው ቅብዐ ቅዱስ፣ ዕጣንና ጠበል ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት በርካሽ ተገዝቶ የሚከፋፈል እንጂ በኛው ቤተ ክርስቲያን የተዘጋጀ አይደለም፡፡ ይህ አሳዛኝም አሳፋሪም ነው፡፡ ሁሉም ነገር እያለ፣ የሰው ኃይሉም ተከማችቶ፣ ለመሥሪያ የሚሆን ቦታ ሳይጠፋ የሰው ንብረት ማከፋፈያ እንደመሆን ያለ አሳዛኝ ነገር አልነበረም፡፡

ሲሆን የኢየሩሳሌም ገዳማት ለሀገር ውስጥ አብያተ ክርስቲያናት መትረፍ ነበረባቸው(‹ጳጳሱ ቄስ ናቸው ወይ ቢሉ ተርፏቸው ለሰው ይናኛሉ› እንደተባለው) ካልሆነ ደግሞ ቢያንስ ለራሳቸውና ለተሳላሚዎች የሚተርፍ ነገር መኖር ነበረበት፡፡ በጣም የሚገርመው ነገር በገዳሞቻችን የገዳማቱን ታሪክ እንኳን የሚገልጥ በራሪ ወረቀት አይገኝም፡፡ ፖስት ካርድማ በሥዕለትም አታገኙ፡፡ በሌሎቹ አብያተ ክርስቲያናት ያያችሁ እንደሆነ እስከ 11 በሚደርሱ ቋንቋዎች የተዘጋጁ ገዳማቱን የሚገልጡ ወረቀቶች ታገኛላችሁ፡፡ አንድ ሸክል(የእሥራኤል ገንዘብ) አስቀምጡና ውሰዱ ይሏችኋል፡፡ ሞያ ከጎረቤት መማር ለምን እንዳቃተን እንጃ፡፡

ባለፈው በክፍል አንድ ላይ ይህንን ሃሳብ በመጠኑ ተነሥቶ ነበር፡፡ የገዳሙ መነኮሳት በምሳ ሰዓት ተሰብስበው በወሰኑት መሠረት በሰጡት መልስ ግን የኛ ሥራ ጸሎት እንጂ ተግባረ ዕድ አይደለም ብለዋል፡፡ ለዚህ እኔ መልስ ከምሰጣቸው የመነኮሳት አባቶች ከሚባሉት አንዱ አባ ስልዋኖስ ያደረገውን ልንገራቸው፡፡ አንድ ወንድም አባ ስልዋኖስን ለማየት ወደ ደብረ ሲና ወጣ፡፡ በዚያ የሚገኙ ወንድሞችም ተግተው ሲሠሩ ተመለከተና ለአባ ስልዋኖስ ‹‹ለሚጠፋ ምግብ አትድከሙ፣ ማርያምስ የማይቀሟትን ዕድል መረጠች ተብሏል›› አለው፡፡ አባ ስልዋኖስም ዘካርያስ የተባለ ረድኡን ጠርቶ ‹‹ይህንን ወንድም መጽሐፍ ስጠውና በበኣት ውስጥ አስቀምጠው›› አለና አዘዘው፡፡

ያ እንግዳ ወንድምም ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን ምናልባት አንድ ሰው ለማዕድ ይጠራኝ ይሆናል ብሎ ጠበቀ፡፡ የጠራው የለም፡፡ የሚጠራው ሲያጣ ወደ አባ ስልዋኖስ ሄደና ‹‹ዛሬ ወንድሞች ምግብ አይመገቡም እንዴ›› ሲል ጠየቀው፡፡ አባ ስልዋኖስም ተመግበው መጨረሻቸውን ነገረው፡፡ ያ ወንድምም ‹‹ታድያ እኔን ለምን አልጠሩኝም›› አለው፡፡ አባ ስልዋኖስም ‹‹አንተ መንፈሳዊ ስለሆንክ ይህንን መሰሉን ምግባር አትፈልገውም ብለን ነው፤ እኛ ግን ሥጋውያን ስለሆንን እንመገባለን፡፡ የምንሠራውም በዚህ ምክንያት ነው፡፡ አንተ ግን የማይቀሙህን ዕድል መርጠሃልና ቀኑን ሙሉ መጽሐፍ ብቻ ታነባለህ፡፡ አላፊ ጠፊ ምግብ አያስፈልግህም›› አለው፡፡ ይህንን ሲሰማ ያ ወንድም በግንባሩ ተደፍቶ ‹‹ይቅር በለኝ›› አለው፡፡ አባ ስልዋኖስም ‹‹ለማርያም ማርታ ታስፈልጋታለች፤ ማርያም የተመሰገነችው በማርታ ምክንያት ነውና ለማርታ ምስጋና ይግባት›› አለው፡፡

ከትናንት ብንዘገይ ከነገ መቅደም አለብንና ስንፍናውን አስወግደን ዛሬ ብንነሣ እንደርሳለን፡፡ በገዳማቱ ውስጥ ነገሩ እንደ እግር እሳት የሚለበልባቸው፣ ለተልዕኮ ለመፋጠን የማይሰለቹ፣ ገዳማቸውን ከሌሎች እኩል ሆኖ ለማየት የሚተጉ ብርቱ መነኮሳት መኖራቸውን ማንም ያየዋል፡፡ ምንም ጥቂት ቢሆኑ፡፡ እነርሱን አንቀሳቃሽ ሞተር አድርጎ ሥራውን መሥራት ነው፡፡ ኢየሩሳሌም ላይ እንደዚህ የተቀናጀና መሥመር ያለው ሃይማኖታዊ ሥራ መሥራት የሀገር ቤቶቹን ገዳማትና አድባራት መንፈስም የሚቀሰቅስ ይሆናል፡፡ እነዚህ አባቶች ነገ በቤተ ክርስቲያኒቱ ታላላቅ ኃላፊነት ላይ ሲመደቡም በኢየሩሳሌም የለመዱትን እዚህ ሀገር ቤትም እንዲተገብሩት ያደርጋቸዋል፡፡

ማጠቃለያ

የኢየሩሳሌም ገዳማት ጉዳይ በማንም እጅ ላይ አይደለም፡፡ በራሳችን እጅ ላይ ነው፡፡ የደከምነውም እኛ ነን የምንበረታውም እኛው ነን፡፡ ግብጾች በደንባራ በቅሎ ላይ ቃጭል ይጨምራሉ እንጂ ደንባራዋን በቅሎ አያመጧትም፡፡ በብኾር ላይ ቆረቆር ያመጣሉ እንጂ ብኾሩ የኛው ነው፡፡ እኛን ለመጥረቢያ እጀታ ሆኖ የፈጀን የራሳችን ጠማማ ነው እንዳሉት ዛፎች ችግሩ እኛው ነን፡፡ ስለዚህም ቁጭ ብሎ መነጋገር፣ መፍትሔ መፈለግና ዕቅድ ማውጣት ያስፈልጋል፡፡ ዓለም በፈጣን ሁኔታ እየተቀያየረ ነው፤ ሁል ጊዜ እየየ አያዋጣም፡፡ የሚያዋጣው መንፈሳዊ ሆኖ፣ ሠርቶ፣ ተግቶና ዓለምን አሸንፎ መለወጥ ነው፡፡ ለጊዜው እኔም በዚሁ ላብቃ፡፡ ጽሑፉ ከተጀመረ በኋላ የገዳሙ መነኮሳትና ሌሎች ምእመናን የላኩልኝን ሰነድና መረጃ አጠናክሬ ደግሞ ሌላ ጊዜ እመለሳለሁ፡፡ ቸር ይቆየን፡፡

የደቡብ ሱዳን አማጽያን መሪና የቀድሞው ምክትል ፕሬዘዳንት ሪያክ ማሻር ከሀገሪቱ ፕሬዘዳንት ሳልቫ ኪር ጋር ለሚያደርጉት የፊት ለፊት ውይይት አሁን ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል።

ይህ የፊት ለፊት ግጭቱ ከተቀሰቀሰ ከአራት ወራት ወዲህ የመጀመሪያው ይሆናል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል የሚባለው ዓለምአቀፍ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ደቡብ ሱዳን ውስጥ በመዋጋት ላይ ያሉት ሁለቱም ወገኖች በሲቪሎች ላይ አስከፊ ጭካኔ ፈፅመዋል ብሏል።

ጥቃቱ ዘር ተኮር ሲሆን በሰብዕና ላይ የተፈፀመ ወንጀል ደረጃ ላይ የደረሰ ነው ሲል አምነስቲ አስገንዝቧል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ናይጀሪያ ውስጥ ቦኮ ሃራም በሚባለው ፅንፈኛ ቡድን የተጠለፉ ወደ 300 የሚጠጉ ልጃገረዶችን ለመፈለግ ለሚደረገው ዓለምአቀፍ ጥረት ድጋፍ ለመስጠት የዩናይትድ ስቴትስ ቀዳሚት እመቤት ሚሼል ኦባማ ሃሽታግ ብሪንግ ባክ አወር ገርልስ (#BringBackOurGirls) – ልጆቻችንን መልሱ የሚል መልዕክት ይዘው የተነሱትን ፎቶግራፍ ትናንት በትዊተር ለቅቀዋል፡፡

የናይጀሪያ ሴቶች የሴቶች መብቶች ጉዳይ ነው ብለው በሚያምኑት በዚህ እንቅስቃሴ ውስጥ ሚስ ኦባማ ያደረጉትና ከጎናቸውም መቆማቸው ልባቸውን የነካው መሆኑን እየገለፁ ነው፡፡

አንዳንድ የፀጥታ ተንታኞች ደግሞ የዩናይትድ ስቴትስ በጉዳዩ ውስጥ መግባት ከሚኖረው ፋይዳ ይልቅ ጉዳቱ ሊያይል ይችላል የሚል ሥጋት እያሰሙ ነው፡፡

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ዋና ጽ/ቤቱ በሰሜን ጀርመን በገኧቲንገን ከተማ የሚገኘው በዓለም ዙሪያ በጭንቅ ላይ ለሚገኙ ሕዝቦች ተቆርቋሪ መሆኑ የሚነገርለት ማሕበር(GFBF) በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ የሰብአዊ መብት ይዞታ አስመልክቶ ትናንት ጋዜጣዊ መግለጫ አወጣ።

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ናይጀሪያ ውስጥ ፤ እስላማዊው አክራሪ ቡድን ቦኮ ሃራም፤ ከምንጊዜውም የበለጠ አሁን ተጠናክሮ ይገኛል። በሳምንቱ መግቢያ ላይ አገሪቱን ከካሜሩን ጋር በሚያዋስነው ድንበር፣ እንደገና አንድ መንደር ከቦ ጥቃት ማድረሱ ታውቋል።

በደቡብ ሱዳን ካለፈው ታህሳስ ወር ወዲህ በመንግሥቱ ጦር እና በዓማፅያኑ መካከል በቀጠለው ውጊያ ስቃይ ውስጥ ያለው ተፈናቃዩ ሲቭል ሕዝብ ወደ የማሳው በመለስ ዘር እንዲዘራ እና ወደ ዕለታዊ ተግባሩ እንዲመለስ ለማስቻል በምሥራቅ

የሩስያ ፕሬዚደንት ቭላዲሚር ፑቲን ትናንት በሞስኮ ከአውሮጳ የፀጥታ እና ትብብር ድርጅት ሊቀመንበር ዲድየ ቡርክሀልተር ጋ ስለ ዩክሬይን ውዝግብ ከመከሩ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በምሥራቅ ዩክሬይን መፍቀሬ ሩስያ ቡድኖች

ሚያዝያ 27፤ 73ኛው የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች በዓል በአራት ኪሎ የድል አደባባይ በደማቅ ስነ- ስርዓት ተከብሯል። በተለይ በብሄራዊ ትያትር አባት አርበኞች፤ ህጻናት ቲያትረኞች፤ ሙዚቀኞች የተሳተፉበት ሥነ-ስርዓት እጅግ የደመቀና ታሪክና ባህልን ያካተተ መሆኑ ተነግሮለታል።

የዞን 9 ጦማርያንን የጊዜ ቀጠሮ ሊያይ ተሰየመው ችሎት ዛሬ ሌላ አሰቃቂ ዜና አብሮ ሰምቷል፡፡ ሁለቱ የዞን9 አባላት በፍቃዱ ሃይሉና አቤል ዋበላ በማእከላዊ መመታታቸውን እና ውስጥ እግራቸው ላይ ግርፋት እንደተፈጸመባቸው የገለጹ ሲሆን ፓሊስ ማስረጃ የላቸውም ሲል ተከራክሯል፡፡ ለክርክሩ ምላሽም ውስጥ እግራቸውን ለፍርድ ቤቱ ማሳየት እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ቶርቸር ህግ መንግስታዊ አይደለም ሲል “አስተያየቱን” ሰጥቷል፡፡ እነደትላትናው ሁሉ በተመሳሳይ ምክንያቶች የተነሳ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው ሲሆን ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ 10 ቀናትን ለምርመራ ፈቅዶአል፡፡
በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ለተከሳሾቹ ጭብጨባ እና ፉጨት ማሰማት የተከለከለ ሲሆን ተከሳሾች ሲወጠ ባሳዩት አጋርነትም ከዛሬ በሁዋላ ካጨበጨባችሁ እነዳትገቡ እናደርጋለን የሚል ማስፈራሪያም ተሰጥቷል፡፡ ወ/ ሮ ስንታየሁ የተባሉ የሬጅስትራር ሰራተኛ ጭብጨባውን እና ፉጨቱን ለዳኛ በመንገር (በተለመደ ቋንቋ በማቃጠር) አጋርነት እያሳዩ የነበሩትን ወጣቶች ተግባር ለማስቆም ሞክረዋል፡፡
ዞን 9 በድጋሚ የዞን 9 አባላት ያወሰድዋቸው ምንም አይነት የአሸባሪነት ስልጠና እንደሌላ እያረጋገጠ በህገ መነግስቱ አንቀጽ 18 መሰረት ማንኛውም ሰው ጭካኔ የተሞላበት ኢሰብአዊ ከሆነ ክብሩን ከሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት የመጠበቅ መብት አለው ቢልም በታሰሩ አባላቶቻችን ላይ የደረሰውን ግርፋት አጥብቆ ያወግዛል፡፡
በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች በመደወል እንዲሁም ኢሜሎችን በመላክ ለሚመለከታቸው አካላት ጥያቄያቸወን በማቅረብ አጋርነታችሁን እንድታሳዩ እንጠይቃለን፡፡

  • ፍትህ ሚኒስትር Ato Desalyn Terasa 0115-51-50-99 /ext/286 0115-15 35 28
  • እምባ ጠባቂ Ato Liul Seyum / Ato Gezagegn Tsfaye ,Public Relations 0111-58-06-52/ 0115-54-33-36 0115-53 20 73
  • የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር Ato Aidsu Petros 0116293040, 0116293071
  • የፕሬዘዳንቱ ቢሮ Ato Gebru Abreha / Ato Adnew Abra 0111-22-67-67 , 0111-24-46-14

0115-51-20-41

  • ፌደራል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት +251115512744
  • የኢትዩጲያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን 0 11-550-41-14

‪#‎FreeZone9bloggers‬ ‪#‎FreeEdom‬ ‪#‎FreeTesfalem‬ ‪#‎FreeAsemamaw‬ ‪#‎Stoptourture‬

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

የኢትዮጵያ ፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአራዳ ምድብ ችሎት ፣ ፖሊስ ከ10 ቀናት በፊት በታሰሩት በ6 ድረገጽ ጸሐፍት ጉዳይ ላይ ዛሬ የጠየቀውን የ15 ቀናት የምርመራ ጊዜ ወደ 10 ቀናት ዝቅ አደርጓል።

የመረጃ ፤ የዕውቀት ማካማቻውና ማከፋፈያው ጋን ከተከፈተ ከጥቂት ዐሠርተ ዓመታት ወዲህ፤ የምርምር ውጤቶቻቸውን በኢንተርኔት ይፋ የሚያደርጉ ጠበብት ቁጥር እየጨመረ ሄዷል። ስለሆነም፤ ዕውቀትን ባፋጣኝና በቀላሉ ለመቃኘትም ሆነ ለመቅሰም የሚያስችል ሁኔታ መፈጠሩ የሚያጠራጥር አልሆነም።

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የአዲስ አበባ ከተማን ለማስፋት በሚል የተነደፈዉን አዲስ የከተማ ልማት እቅድ በመቃወም ሰልፍ የወጡ ተማሪዎች ላይ የደረሰዉን የህይወት ህልፈት፣ ድብደባና እስራት በመቃወም፤

የቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ የቻይና እና የአፍሪቃ የንግድ ግንኙነት ይበልጥ በእኩልነት ላይ የተመረኮዘ እንደሚሆን ተናግረዋል። የቻይናእና የአፍሪቃ ፤ በተለይም የቻይናና የኢትዮጵያ የንግድ ግንኙነት እንዴት ይገመገማል?

ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ በዛሬው ዕለት ምክር ቤታዊ ምርጫ ተካሄደ። በዚሁ የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዚደን ኔልሰን ማንዴላ ከሞቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገሪቱ በተካሄደው ምርጫ የአፍሪቃውያኑ ብሔረተኞች ኮንግረስ፣ «ኤ ኤን ሲ » እንደሚያሸንፍ እና መሪው ፕሬዚደንት ጄኮብ ዙማም ለቀጣዮቹ አምስት ዓመትትም በሥልጣናቸው እንደሚቆዩ ይጠበቃል።

የሰባት ፓርቲዎች ስብስበ የሆነው ትብብር በአንድነት እና በመኢአድ መካከል ፖለቲካ ፕሮግራሞቻቸው ተመሳሳይ እንደመሆናቸው መዋሃድ እንዳለባቸው ማሳሰባቸው አገር ቤት የሚታተመው ሰንደቅ ጋዜጣ ገለጸ። ስብሰቡ ሁለቱ ፓርቲዎች ከተዋሃዱ በኋላ እነርሱም ያንን ዉህደት እንደሚቀላቀሉ፣ የትብብሩ ሊቀመንበር መናገራቸውን ሰንደ አክሎ ዘግቧል። መኢአድ እና አንድነት የማይዋሃዱ ከሆነ ግን ትብብሩ፣ ከአንዳቸው ጋር እንደሚዋሃድ ሰንደቅ የትብብሩን ሊቀመንበር ጠቅሶ አትቷል። በዚህ ጉዳይ ላይ […]

ሰንደቅ – አባ ዱላ በተገደሉ ተማሪዎች ዙሪያ “የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ ጥያቄ ፍትሐዊና ሕጋዊ ነው” በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉትን በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ዉስጥ የሚተዳደሩ ከተሞችን ከአዲስ አበባ ጋር በማስተባበር በጋራ ለማልማት የወጣዉን የተቀናጀ መሪ እቅድ በመቃወም ሰሞኑን በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች የተካሄደው ተቃውሞ ተከትሎ በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል። በአዳማ፣ በድሬዳዋ፣ በጅማ፣ በመደወላቡ፣ በአምቦ፣ በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲዎችና በጠቅላላው በ11 […]

«የሃይለማሪያም ደሳለኝ ቁልቁለቶች» በሚል በተመስገን ደሳለኝ ከጻፈው የተወሰደ (ክፍል 4) ግንባሩ ‹‹ባለራዕይ›› በማለት ካቆለጳጰሰው የቀድሞ ሊቀ-መንበሩ አቶ መለስ ህልፈት በኋላ፣ በጠባብ ብሔርተኞችና ጥቅመኞች በመሞላቱ መተካካቱን ተከትሎ ይፈረካከሳል የሚል ከውስጥም ከውጪም የሚሰማ ሹክሹክታ ነበር፡፡ በርግጥም የኃይለማርያም ወደ መንበሩ መምጣት ‹‹በአማራና ኦርቶዶክስ የምትመሰለው ሀገር፣ የአናሳውም ሆናለች›› ከሚለው የአቦይ ስብሐት እንቶ ፈንቶ ውጪ፣ ከተጠበቁት ሁነቶች ብዙዎቹን (በተለይ ሥርዓታዊ […]

«የሃይለማሪያም ደሳለኝ ቁልቁለቶች» በሚል በተመስገን ደሳለኝ ከጻፈው የተወሰደ (ክፍል 4) ጠቅላይ ሚንስትሩ ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት፣ አቶ ግርማ ሰይፉ መንግስት የኤርትራንና የኢትዮጵያን ሕዝብ ለማቀራረብ የሚያደርገውን ጥረት አስመልክቶ ያለውን አቋም በተመለከተ ላነሳው ጥያቄ፣ የሰውየው ምላሽ ከእውነታው ፍፁም ያፈነገጠ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ የኃይለማርያም ማብራሪያ ሁለቱ ሕዝቦች የቀድሞ ግንኙነታቸውን መልሰው እንዲያጠናክሩ ‹‹ኢትዮጵያውያን የኃይማኖት አባቶች እና ምሁራኖች ለሚያደርጉት ጥረት መንግስት ድጋፍ […]

«የሃይለማሪያም ደሳለኝ ቁልቁለቶች» በሚል በተመስገን ደሳለኝ ከጻፈው የተወሰደ (ክፍል 3) አቶ ኃይለማርያም በስድስት ወር (በጥር) ለተወካዮች ም/ቤት ማቅረብ የነበረበትን ሪፖርት በዘጠኝ ወሩ ባለፈው ሳምንት ባቀረበበት ወቅት፣ ከምርጫው በፊት የፖለቲካ ማሻሻያ መጠበቁ የዋህነት እንደሆነ የጠቆመን፣ የም/ቤቱ አባል አቶ ግርማ ሰይፉ የጠበበው ምህዳርን አስመልክቶ ላቀረበለት ጥያቄ ‹‹ዲሞክራሲ በአንድ ሳምንት ተበጥብጦ አይጠጣም (ፓርቲው ሥልጣን ከያዘ በቀጣዩ ወር ሃያ […]

«የሃይለማሪያም ደሳለኝ ቁልቁለቶች» በሚል በተመስገን ደሳለኝ ከጻፈው የተወሰደ (ክፍል 2) አቶ ኃይለማርያም በስድስት ወር (በጥር) ለተወካዮች ም/ቤት ማቅረብ የነበረበትን ሪፖርት በዘጠኝ ወሩ ባለፈው ሳምንት ባቀረበበት ወቅት፣ ከምርጫው በፊት የፖለቲካ ማሻሻያ መጠበቁ የዋህነት እንደሆነ የጠቆመን፣ የም/ቤቱ አባል አቶ ግርማ ሰይፉ የጠበበው ምህዳርን አስመልክቶ ላቀረበለት ጥያቄ ‹‹ዲሞክራሲ በአንድ ሳምንት ተበጥብጦ አይጠጣም (ፓርቲው ሥልጣን ከያዘ በቀጣዩ ወር ሃያ […]

« የሃይለማሪያም ደሳለኝ ቁልቁለቶች» በሚል በተመስገን ደሳለኝ ከጻፈው የተወሰደ ((ክፍል 1) ) በ2005 ዓ.ም መጀመሪያ አቶ ኃይለማርያም “ጠቅላይ ሚኒስትር” ተደርጎ በኢህአዴግ ሲሾም፤ በፓርቲው ውስጥ አክራሪ ብሔርተኛ የአመራር አባላት ከመኖራቸው አኳያ፤ መቼም ቢሆን “ራሱን ችሎ ይቆማል” ብሎ መጠበቁ ተምኔት እንደሆነ በርካታ የፖለቲካ ተንታኞች መናገራቸው ይታወሳል፡፡ ይህ ኃይል እንኳን እንደ ኃይለማርያም ላለ የድል አጥቢያ መሪ ቀርቶ፣ ከድርጅቱ […]