ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ወጣትነት ከመቼውም ጊዜ በላይ በርካቶች ሱስ የሚያሲይዙ ነገሮች ለመሞከር የሚፈተኑበት ጊዜ ነው። ከገቡበት ደግሞ ፤ የቻሉ በራሳቸው ኃይል ያልቻሉ ደግሞ እድሜ ልካቸውን ለሱስ አስያዦች ጥገኛ ሆነው ይቀራሉ። የዛሬው የወጣቶች ዓለም እንግዳችን ራሱን ከሱሰኝነት አላቋል። ልደት አበበ አነጋግራዋለች።

እ ጎ አ ከ 1980 ዓ ም አንስቶ በሱዳን በኩልና በቀጥታም ከኢትዮጵያ ወጥተው በተለያዩ ጊዜያት እሥራኤል የገቡ፣ ቤተ እሥራኤል በመባል የታወቁ ኢትዮጵያውያን አይሁድ፣ በአንዳንድ መግለጫዎች መሠረት ወደ 80 ሺ ይጠጋሉ ፤ ከ 100 ሺ በላይ

የጀርመን ፍሪድሪኽ ኤበርት ድርጅት (እሽቲፊቱንግ) ፣ አዲስ አበባ ውስጥ ትናንት በሒልተን ሆቴል ባዘጋጀው ስብሰባ፤ የክርስትናና እሥልምና የዘመናት የመቻቻል ታሪክ ትኩረት እንደተደረገበት ተገለጠ። ድርጅቱ ፤ ከፓሪስ ዩንቨርስቲ ፣ በአፍሪቃ ቀንድና

ናይሮቢ ኬንያ ዉስጥ ዛሬ በደረሰ ፍንዳታ ቢያንስ አስር ሰዉ ሳይገደል እንዳልቀረ ተገለጸ። በርካቶችም ተጎድተዋል። የኬንያ ብሄራዊ የአደጋ መከላከል ዘመቻ ማዕከል ፍንዳታዉ የደረሰዉ በህዝብ ማመላለሻ መለስተኛ አዉቶቡስና ገበያ ዉስጥ መሆኑን ገልጿል። ለፍንዳታዉ እስካሁን ኃላፊነት የወሰደ አካል የለም።

“ሽፈራው - ሞሪንጋ” በአበራ ለማ "Shiferaw - Moringa" by Aberan Lemmaጋዜጠኛ፣ ገጣሚና ደራሲ አበራ ለማ “ሽፈራው – ሞሪንጋ” የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ አሣተመ። ሞሪንጋ ወይም ባገራችን “ሽፈራው” እያልን በስፋት የምንጠራው ዕጽ፣ እጅግ እውቅናን አግኝቶ የኖረው በእስያ ውስጥ ነው። ሕንዶች ኦሊፌራ የተሰኘው ዝርያ ባለጸጎች በመሆናችው በብዙ መልኩ ሲጠቀሙበት ኖረዋል። ዛሬ ኦሊፌራ የተሰኘው ዝርያ፣ በሰሜንና ደቡብ አሜሪካ፣ በካሪቢያን ደሴቶች፣ በአፍሪካና በኦሴኒያ ውስጥ በብዛት እየለማና እየተስፋፋ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ዘረኛው አገዛዝ የመጨረሻ የሚመስል ከልክ ያለፈ የዘረኝነትና የፍጅት ተግባሩን ቀጥሏል። ሕዝብን ከሕዝብ ማባላቱ የስርአቱ አይነታ ስልት መሆኑን እስካሁንም ያልተረዱ መኖራቸው ያሳዝናል። በአለፉት ፪፫ አመታት ተወልደው ያደጉና በሰላሳወቹ ውስጥ ያሉ ዜጎች ብዙወች የስርአቱ ሰለባወች ሆነዋል። አገርና ሕዝብ ለወያኔ ደናቁርት ምንም ማለት አይደለም። በመሆኑ የአገር ልሂቃን፤ የፖለቲካና የሰበአዊ መብት ተሟጋች የሆኑ ዜጎች ክንዳቸው እንዲጠነክር መተባበርን ይጠበቅባቸዋል። ወያኔ […]


ከታሰሩ 22 ቀናትን ስቆጠሩት የዞን ዘጠኝ አባላትና ጋዜጠኞች በቤተሰብም ሆነ በሕግ ባለሞያ የመገናኘት መብታቸውን ለማግኘት 19 ቀናት ፈጅቶባቸዋል፡፡ ከታሰሩ እስከ 17 ቀን ድረስ ማንም የቤተሰብ አባል ሳይጎበኛቸውና በወዳጅ ዘመዶች ሳይጠየቁ የከረሙ ሲሆን ከጠበቆች ጋር ለመገናኘት ደግሞ 19 ቀናት ፈጅቷል፡፡ አሁንም ከጠበቆቻቸው ጋር መገናኘት ያልቻሉ ቀሪ እስረኞች አሉ፡። 
በተለምዶው እነደሚደረገው የፓሊስ ማእከላዊ ምርመራ የቤተሰብ ጉብኝትን አይቻልም በሚል ቀላል ቃል የከለከለ ሲሆን ለጠበቆች ስብሰባ ላይ ነን የሚል ምክንያት ሲሰጥ ከርሟል፡፡ ይህ በመሆኑም የተነሳ የተያዙ ሰዎች መብት የሆነው የህገ መንግስቱ አንቀጽ 19 ሁለት ላይ ያለው የተያዙ ሰዎች ያለመናገር መብት ( the right to remain silent) በይፋ ተጥሶ ያለማንም የህግ ባለሞያ ምክር ለብዙ ቀናት ምርመራ ሲደረግባቸው ቆይቷል፡፡
ምርመራቸውን ጨርሰዋል ተብለው የታሰቡ ታሳሪዎቸን ካልሆነም በስተቀር በምርመራ ወቅት የህግ ባለሞያ ለማግኘት አልተፈቀደላቸውም፡፡
መሰረቱ መሰረታዊ የሆነው ያለመናገር መብትና የሕግ ባለሞያ የማግኘት መብት መከልከሉ የተለመደውን ማእከላዊ ምርመራ የሚታማበትን የማስገደድ ምርመራ እውነተኛነት የሚያጋልጥ ነው፡፡ በተጨማሪም የአካልና የስነልቦና ጉዳት የማድረስ ምርመራ ሲፈጸምባቸው እነደነበረ የተያዙ የዞን ዘጠኝ አባላት በተናገሩበት ወቅት ፍርድ ቤቱ የነዚህን ጉዳቶች መከልከል ላይ አስተያየት ከመስጠት ውጪ ይሄ ነው የሚባል እርምጃ እና ማጣራት ለመውሰድ አልሞከረም፡፡
ማዕከላዊ ምርመራ ከዚህ በፊት የሚታወቅበት ድብደባ፣ ምግብና እንቅልፍ መከልከል፣ የስነልቦና ጫና እና ማስፈራሪያ የተለያዩ ዛቻዎች ሁሉም በተያዙ የዞን ዘጠኝ አባላትና ጋዜጠኞች ላይ በተለያየ መልኩ እነደደረሰ ተረድተናል፡፡ ይህም ምርመራውን ተከትሎ የሚመጣውን ማንኛውንም ማስረጃ በሕግም በሞራልም ተቀባይነት እነዳይኖረው እነደሚያደርግ እናውቃለን፡፡
ከታሳሪዎች የሚገኙ ማንኛውም መረጃዎች በከፍተኛ ተጽእኖ ስር እንደተሰጡ አንዲሁም ዝም የማለትና የሕግ ባለሞያ ምክር የማግኘት ሕገ-መንግስታዊ መብቶቻቸው ተጥሰው የተገኙ እንደሆኑ ዞን ዘጠኝ ያምናል፡፡ በወንጀል ህግ ስነስርአት መሰረት እነዚህ ያለህግ ባለሞያ ጉብኝት ያለመናገር መብታቸው (የህገ መንግስቱ አንቀጽ 19) ተጥሶ የተገኙ መረጃዎች በዚህ ምክንያት ብቻ ተቀባይነት እነደማይኖራቸውም የአገሪትዋ ሕግ ይደነግጋል፡፡
በመሆኑም መንግስት ታሳሪዎቹን አንደፈታ እና ጉዳያቸው ሕገ መንግሰታዊ እና የወንጀል ህግ ሥነ-ስርአት ሕጉን ተከትሎ አንዲሆን እንዲያደርግና ሌሎች እንዲያከብሩ የሚጠይቀውን ሕግ መንግስት ራሱን በማክበር አንዲጀምር አሁንም በድጋሚ ጥሪ እናቀርባለን ፡፡
ህገ መንግስታዊ መብታቸው ተጥሶ ማእከላዊ ምርመራ የሚገኙ የዞን ዘጠኝ አባላት እና ጋዜጠኛ ወዳጆቻችን ያለንን ክብር እና ፍቅር እየገለጽን ጽናታቸው አስተማሪ ሲሆን በሚከተሉት ቀናት በሚኖሩት ማንኛውም የህግ ሂደቶች ውስጥ የሚኖሩትን አዳዲስ መረጃዎች ለዞን ዘጠኝ ነዋሪያን እንገልጻለን፡፡ነገ ቅዳሜ ግንቦት 9 እና እሁድ ግንቦት 10 የሚደረጉ የፍርድ ቤት ሄደቶችን አራዳ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት ጠዋት በመገኘት መከታተልና አጋርነታችሁን ማሳየት ትችላላችሁ፡፡
የዞን ዘጠኝ ስብስብ አባላቶቹ ምንም አይነት ህገ ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው እንደማያውቁ በድጋሚ ለማረጋገጥ ይወዳል፡፡

የኢትዮ ሱዳን ዳር ድንበር በግልፅ የተከለለ እንዳልሆነ ይታወቃል። የኢትዮጵያ አርሶአደሮች የሚጠቀሙት መሬት የኢትዮጵያ እንደሆነ ሲወሰድ ሱዳናውያን የሚገለገሉበትም የሱዳን ነው ተብሎ ይታሰባል። ከቅርብ ግዜ ወዲህ ግን የኢህአዴግ መንግስት ኢትዮጵያውያን አርሶአደሮችን ከቀያቸው እያፈናቀለ ለሱዳን ማስረከቡ ይታወቃል። ብዙ የኢትዮጵያ አርሶአደሮች ተፈናቅለዋል፣ የተወሰኑ ተለዋጭ መሬት ሲሰጣቸው ምንም ያላገኙም አሉ። ድንበሩ ብዙ ዉዝግብና ተቃውሞ ያለው ሲሆን የኢህአዴግ መንግስት ከሱዳኖች ጋር […]

እንደተለመደው ዘወትር በየቀኑ እንደማደርገው ሁሉ – ማክሰኞ ምሽት አካባቢ (ግንቦት 5፣ 2006) የኢትዮጵያን ጠረንና ሙቀት በመሻት፡ የሃገር ቤት ወቅታዊ ዜናዎች ገጾችን ሳፈላልግ/ሳገላብጥ – በቤት ማስተላለፍ ሂደት የሚታየውን የኪራይ ሰብሳቢነት ተግባር ለማስወገድ እርምጃ እየተወሰደ ነው የሚለው በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) የተጻፈው አርዕስት ላይ ዐይኔ በድንገት አረፈ። አገራችን ምርጫ ዋዜማ ላይ ስለሆነች፡ በየመሥሪያ ቤቱ ባለሥልጣኖች ያልሆነውን ሆነ፡ […]

መድረክ በአሁኑ ወቅት የኢህአዴግ መንግስት ሰላማዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችን በኃይል ለማፈን የሚወስዳቸው የኃይል እርምጃዎች እና ተፅዕኖዎች በአስቸኳይ ቆመው የሀገራችን ወቅታዊ እና መሰረታዊ ችግሮች በሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ አግባብ እንዲፈቱ መንግስትን በሰላማዊ ሰልፍ ለመጠየቅ ግንቦት 10 ቀን 2006 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ 7 ሰዓት የሚካሄድ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቷል፡፡ ስለዚህም የአዲስ አበባ እና የአከባቢዋ ነዋሪዎች ልክ በተጠቀሰው ቀንና […]

ለመረጃ ያህል አሁን እየተሰሙ ያሉ ነገሮች በጣም አስፈሪና አሳዛኝ ናቸው:: ለመሆኑም ይህንን በዝምታ ማለፍ አይቻልም፤ በጥቂቱም ቢሆን እየተሳካለት የሚገኘውን ህዋህት/ኢህዴግ ከመነሻው ጀምሮ ለሀገር ማሰቡ የሚባል ነገር ወደ ጎን በመተው የስልጣን ማርዘሚያ ዘዴዎችን በመቀየስ ይህው 23 ዓመት ሀገሪቱን በጎሳ፤ በጎጥ፤ በብሔር፤ በሀይማኖት ሲከፋፍል ከርሞአል። በመጀመሪያ እሱ በቀደደው ቁምጣ የቡሄር ብሔረሰቦች መብት፤ በማለት ሰራ ግን ከጭፈራ ያልዘለለ […]

 

ዝዋይ እሥር ቤት የሚገኙ የ19 ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችና አንድ ጋዜጠኛ ቤተሰቦችን ጠቅሶ የወጣ የአንድ ጋዜጣ ዘገባ ታሣሪዎቹ አካሄዱ የተባለውን የረሃብ አድማ ተከትሎ ከባድ ድብደባ እንደተካሄደባቸው ይገልፃል፡፡

ድብደባ ብቻ ሳይሆን አንዳንዶቹ በጋለ ኮንቴይነር ውስጥ ተይዘዋል መባሉን አትቷል፡፡

ጉዳዩን ለማጣራት ሰሎሞን ክፍሌ ወደ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ፅ/ቤትና ወደ አንድ የታሣሪ ቤተሰብ አባል ስልክ ደውሏል፡፡

የወኅኒ ቤቱን ባለሥልጣናት ለማግኘት ቢሞክርም ለጊዜው አልተሣካለትም፡፡

 

በሥልጣን ላይ ያሉ የመንግሥታት መሪዎች በሥራ ላይ ባሉባቸው ዓመታት የሕግ ከለላ እንዲደረግላቸው ስለሚቻልበት መንገድ ለመምከር ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በኅብረቱ ፅ/ቤት ስብሰባ አድርገው ተወያይተዋል፡፡

ስብሰባውን ለመከታተል የሄደው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን መለስካቸው አምሃ ግን በሥራ ላይ እንዳለ በኅብረቱ የፀጥታ ኃይሎች ታግቶ ከቆየ በኋላ ተለቅቋል፡፡

ከመለስካቸው አምሃ ጋር ያደረግነውን ቀጥታ ቃለ-ምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

የዓለም የምግብ ድርጅት በዘንድሮዉ ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት 2014 ለ6,5 ሚሊዮን ኢትዮጵያዉያን የምግብ ርዳታ ለመስጠት መዘጋጀቱን የጠቀሰ ዘገባ ሰሞኑን ይፋ ሆኗል። በኢትዮጵያ ግብርና ሚኒስቴር የምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሀገሪቱ የምግብ ርዳታ የሚያስፈልገዉ ሕዝብ ከ2,7 ሚሊዮን እንደማይበልጥ ያመለክታሉ።

የሰዎች ፍልሰት ለህብረተሰባዊ እና ለኤኮኖሚያዊ ዕድገት ፣ እንዲሁም ፣ በዓለም ድህነትን በመቀነሱ ረገድ የሚኖረው ሚና ትናንት በስዊድን መዲና ስቶክሆልም የተከፈተው በፍልሰት እና በልማት ላይ ያተኮረ ዓለም አቀፍ መድረክ

ጦርነት በቀጠለባት ደቡብ ሱዳን ለረሃብ አደጋ ለተጋለጠው ህዝብ አስቸኳይ እርዳታ ለማቅረብ ለጋሽ ሃገራት ገንዘብ እንዲለግሱ ተጠየቁ ። ኦክስፋም የተባለው የብሪታኒያ ግብረ ሰናይ ድርጅት ለችግሩ ከወዲሁ አፋጣኝ መልስ ካልተሰጠ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ደቡብ ሱዳናውያን ህይወት አደጋ ላይ እንደሚወድቅ አስጠንቅቋል ።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ታስቦ የዋለዉን የእናቶች ቀን በማስመልከት በርካታ ኢትዮጵያዉን በተለያዩ የማሕበራዊ ደረ-ገፆች እናትን የሚያወድስ እናትን የሚያመሰግን የተለያዩ ስነ-ፅሁፎና ግጥሞች ተለዋዉጠዋል። በተለይ በፊስቡክ ማህበራዊ ድረ መገናኛ ገፅ ላይ የእናቶቻቸዉን ፎቶ ግራፎች በማስቀመጥ እናቶቻቸዉን ያመሰገኑ ኢትዮጵያዉያን እጅግ ብዙ ናቸዉ።

በሩስያና በምዕራባውያን መካከል የተፈጠረው ቅራኔ ተካሯል ። በሩስያ ላይ የኤኮኖሚ ማዕቀብ የመጣሉ ዛቻ አሁንም እንደቀጠለ ነው ። የሩስያ የኤኮኖሚ እድገት እምርታ ቀደም ካለ ጊዜ አንስቶ ቀንሷል ። በአሁኑ ቀውስ ደግሞ እድገቱ ተገቷል ። ይህ ደግሞ በጀርመን የውጭ ንግድ ላይ ተፅእኖ እያሳደረ ነው ።

እሥራኤላውያን እንዲህ ይተርካሉ፡፡

በኢየሩሳሌም ከተማ የሚኖሩ ሁለት ወንድማማቾች ነበሩ፡፡ አንደኛው ባለ ትዳርና የቤተሰብ አስተዳዳሪ፣ ሌላኛው ደግሞ ላጤ ነበሩ፡፡ ሁለቱም የሚተዳደሩት በአንድ የእርሻ መሬት ነው፡፡ ጠንክረው በጋራ በመሥራት ያመርቱና ምርቱን በእኩል ይካፈላሉ፡፡ በሥራና በኑሮ ያላቸው መተጋገዝና መጠቃቀም ለአካባቢው ሰዎች ሁሉ እጅግ የሚያሰቀና ነበር፡፡ አንደኛው ለሌላኛው የሚያስበውን ያህል ለራሱ አያስብም ነበር፡፡

አንድ ቀን ላጤው ለባለ ትዳር ወንድሙ እንዲህ አሰበ፡፡ ‹‹ወንድሜ የቤተሰብ ኃላፊ ነው፡፡ ባለቤቱን፣ ልጆቹን፣ የባለቤቱን ወላጆችና የቤቱን ሠራተኞች ማስተዳደር አለበት፡፡ ምርቱን ከእኔ ጋር እኩል መካፈል የለበትም፡፡ እርሱ ከእኔ የሚበልጥ ምርት ማግኘት አለበት፡፡ ነገር ግን አሁን ከእኔ የተሻለ እህል ውሰድ ብለው አይቀበለኝም፡፡ ስለዚህ በሌላ መንገድ መርዳት አለብኝ፡፡››

አውጥቶ አውርዶም በጎተራ ካለው የእርሱ እህል እየወሰደ ማታ ማታ ተደብቆ በወንድሙ ጎተራ ውስጥ ለማስቀመጥ ወሰነ፡፡ ማታ ማታ ተደብቆ በመውጣት ከራሱ ጎተራ ወደ ወንድሙ ጎተራ እህል ይገለብጥ ነበር፡፡ ነገር ግን ጠዋት ጎተራውን ሲያየው እንኳንስ ሊጎድል ካለፈው የበለጠ ሞልቶ ያገኘው ነበር፡፡ ይህም እጅግ ይገርመው ነበር፡፡ ፈጣሪ በጎ ሥራዬን አይቶ እየባረከኝ ነው ብሎም አመሰገነ፡፡

ባለትዳሩም እንዲሁ ለብቻው ‹‹ወንድሜ እንደ እኔ አላገባም፡፡ ለወደፊትም ከባድ ኃላፊነት ይጠብቀዋል፡፡ ትዳር መመሥረት አለበት፣ልጆች መውለድ አለበት፡፡ ለዚህ ደግሞ አሁን የሚያገኘው ምርት በቂው አይደለም፡፡እኔ የራሴን ኑሮ አደላድያለሁ፡፡፡ እርሱ ግን ገና አዳጊ ነው፡፡ አሁን እርሱን የሚበልጠውን ምርት ውሰድ ብዬ ብነግረው አይቀበለኝም፡፡ ስለዚህ በድብቅ ልረዳው ይገባኛል›› ብሎ አሰበ፡፡

ወንድሙ ለእርሱ የሚያደርገውን ያላወቀው ባለ ትዳሩ ወንድምም ሊነጋጋ ሲል እየተነሣ ከራሱ ጎተራ ወደ ወንድሙ ጎተራ እህል ይጨምር ነበር፡፡ ጠዋት ሲነሣ ግን ጎተራው ሳይጎድል ያገኘዋል፡፡ ይህም ሁልጊዜ ይገርመዋል፡፡ መስጠቴን ተመልክቶ ፈጣሪ ነው የሞላልኝ እያለም ያመሰግን ነበር፡፡

እንዲህ እያደረጉ ለብዙ ጊዜ ከኖሩ በኋላ በአንድ ሌሊት አንደኛው እህሉን ተሸክሞ ወደሌላው ጎተራ ሲሄድ በድንገት መንገድ ላይ ተገናኙ፡፡ ሁለቱም በነገሩ ተገርመው ተቃቅፈው እየተላቀሱ የነበረውን ነገር ተነጋገሩ፡፡ ከበፊቱ ይልቅም ፍቅራቸው እጅግ ጸና፡፡ እግዚአብሔርም ተገኝቶ ለዚህ ፍቅራቸው መታሰቢያ እንዲሆን በእነርሱ የእርሻ ቦታ ላይ ቤተ መቅደሱ እንደሚሠራ ቃል ገባላቸው፡፡ ንጉሥ ሰሎሞን ታላቁን ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም ውስጥ የሠራው በእነዚህ ወንድማማቾች የእርሻ ቦታ ላይ ነው ይባላል፡፡

ከፍቅር መገለጫዎች ዋናው መሟላት ነው፡፡ ታላቁ ኢትዮጵያዊ ፈላስፋ ዘርዐ ያዕቆብ ሰው ማለት የሚሟላ ፍጡር ነው ይላል፡፡ ሙሉ እንዲሆን እንጂ ተሟልቶ አልተፈጠረም፡፡ ለመሟላት ሌላ ሰው ያስፈልገዋል፡፡ ሰው የፈለገውን ያህል የበቃ የነቃ ቢሆንም ሙሉ ሰው ለመሆን ግን ሌላ ሰው ያስፈልገዋል፡፡ ሰውን በመተቸት፣ ስሕተቱን በመግለጥ፣በመውቀስና ጎደሎነቱን በማሳየት ከምናርመውና ከምናስተካክለው በላይ የጎደለውን በመሙላት እናስተካክለዋለን፡፡ የምንወደው ሰው፣ የምናስብለት ሰው፣ የምናወቀው ሰው፣ ማለት የምናሟላው ሰው ማለት ነው፡፡

በወዳጅና ወዳጅ ባልሆነ መካከል ያለው አንዱ ዋና ልዩነት አብሮ ከመብላት፣ አብሮ ከመጠጣት፣ ልቅሶና ደስታ ከመደራረስ፣ ከመደዋወልና ከመጠያየቅ፣ ከመዛመድና አብሮ ከመኖር የሚመጣ አይደለም፡፡ ሰውን ለምን እናውቀዋለን? ለምንስ ማወቅ እንፈልጋለን? ለምንስ እንቀርበዋለን? ሰው ስለሆንን፣ የሚጠይቅ ኅሊና የሚያስብ ልቡና ስላለን ማወቅ የመጀመሪያው ነው፡፡ ይህንን መከላከል አንችልም፡፡ የግድ ከልዩ ልዩ ምንጮች ስለ አንድ ሰው እናውቃለን፡፡ ይህ ማወቅ ግን መተዋወቅን አይፈልግም፤ መቀራረብንም የግድ አያመጣም፡፡ ሁለተኛው ደግሞ መተዋወቅ ነው፡፡ ይኼኛው መቀራረብን ያስከትላል፡፡ መስተጋብርን ይፈጥራል፡፡ በዚህ መልኩ የምናገኘው መተዋወቅ ኃላፊነትን ይወልዳል፡፡ የመሟላትን ኃላፊነት፡፡

መተዋወቅ ለመሟላት ካልሆነ ስለ ሰዎች ያለንን ፋይል መቀነስ ያስፈልገናል፡፡ ዐወቅኩት፣ ቀረብኩት፣ እገሌንኮ ዐውቀዋለሁ፣ እቀርበዋለሁ ለማለት መተዋወቅ አያስፈልገንም፡፡ ግንኙነታችን መሟላትን የማያመጣ ከሆነ ዕውቀት መቀነስ ታላቅ ብልሃት ነው፡፡ ከሰዎች ጋር ያለንን ግንኙነት በሦስት መልኩ ብናደርገው ግንኙነታችን የታሰበበትና የተሟላ ይሆንልናል፡፡

የማናውቃቸው ሰዎች፡፡ እነዚህ ሰዎች ከኛ ጋር ለመተዋወቅም ሆነ በእኛ ለመታወቅ ዕድል የሌላቸው ወይም ዕድል የሌለን ናቸው፡፡ የሚበዙትም እነርሱ ናቸው፡፡ በማወቃችን የምናተርፈው ወይም የሚያተርፉት ነገር ከሌለ አለማወቃችን ምንም ጉዳት የለውም፡፡ ያገኙትን ሰው ሁሉ ስልክ የሚቀበሉ፣ ደግመው የማያገኙትን ሰው የሚተዋወቁ ሰዎች ሊያውቋቸው በማይገቡ ሰዎች ፋይላቸውን የሚያጨናንቁ ናቸው፡፡

ሁለተኛዎቹ የምናውቃቸው ሰዎች ናቸው፡፡ እነርሱ ሊያውቁንም ላያውቁንም ይችላሉ፡፡ ያ ደግሞ የእነርሱ ፋይል ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች የሥራ ባልደረቦቻችን፣ ጎረቤቶቻችን፣ ታዋቂ ሰዎች፣ ደንበኞቻችን፣ ዕውቀትን የምንሸምትባቸው ሰዎች፣ በልዩ ልዩ ምክንያት የምናገኛቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ከእነርሱ የምንፈልገው፣ ለእነርሱም የምንሰጠው ነገር ስላለ እናውቃቸዋለን፡፡ አንዳንዶቹንም ማወቅ የግድ ይለናል፡፡ ሌሎቹን ደግሞ አለማወቅ አንችልም፡፡ እነዚህን ሰዎች የግድ መቀራረብ፣ መተዋወቅ፣ ወይም የተለየ ተግባቦት መፍጠር ላያስፈልገን ይችላል፡፡ ግንኙነታችን አንድን ጉዳይ፣ ተግባር፣ ኃላፊነት፣ መሥመር ወይም ደግሞ ሁኔታ መሠረት ያደረገ ነውና፡፡

ሦስተኛው መተዋወቅ የሚባለው ነው፡፡ መቀራረብንና መግባባትን የሚያመጣው፡፡ በውስጡም መዋደድ ያለበት፡፡ ከላይ በሚገኙት ሁለቱ መውደድ እንጂ መዋደድ የለባቸውም፡፡ የማናውቃቸውንም ሰዎች፣ የምናውቃቸውንም ሰዎች ልንወዳቸው እንችላለን፡፡ ግንኙነት የሚያመጣው መዋደድ ግን ላይኖር ይችላል፡፡ እኛ ስለ እነርሱ እናስብ ይሆናል፣ እነርሱ ስለ እኛ እንዲያስቡ አይጠበቅምና መተሳሰብ ላይኖር ይችላል፡፡ በመተዋወቅ ውስጥ ግን ሦስቱም አሉ፡፡ መግባባት፣ መተሳሰብና መዋደድ፡፡ እነዚህ ሦስቱ ነገሮች ወዳጃዊ ኃላፊነትን ያስከትላሉ፡፡ አንዱ ለሌላው በጎ መሆን፣ ስኬትና ደኅንነት ኃላፊነት ይሰማዋል፡፡ ይህ ኃላፊነት ከመጠየቅ፣ ከመለመን ወይም ከመወትወት የሚመጣ አይደለም፡፡ ከመተዋወቅ የሚመጣ ራስ ወሰድ ኃላፊነት ነው፡፡

ለሌላው ሕይወት የማይገደን ወይም ኃላፊነት የማይሰማን ከሆነ የተሻለው መንገድ ዕውቀት መቀነስ ነው፡፡ ለምን እንቀራረባለን? ለምን እንወያያለን? ለምንስ የማንሸከመውን የሰው ‹ውስጥ› እናውቃለን? ለምንስ የማንጋራውን የሰው ችግር እናውቃለን? ለምንስ የማንሞላውን ጉድለት እንሰማዋለን? ለምንስ የማናክመውን ቁስል እንመረምረዋለን? አንዳንድ ሰው አመል ሆኖበት ‹‹ይህ ነገር አይመለከተኝም፣ ይህ ነገር ልሸከመው አልችልም፣ ይህንን ነገር መስማት የለብኝም፣ ይህ ነገር የሰውየው የራሱ ብቻ ነው›› ማለት አይችልም፡፡ በሁሉም ነገር ውስጥ ይገባል፣ ሁሉም ነገር ይመለከተኛል ይላል፣ ሁሉንም ነገር በዝርዝር ያውቃል፣ የሁሉም ሰው ጓዳ ዘው ይላል፡፡ ነገር ግን ምንም ዓይነት ኃላፊነት አይወስድም፡፡ ከማወቅና ሲወራ አብሮ ከማውራት፣ ባስ ሲልም ‹ገመናን ከማጋለጥ› ያለፈ ሚናም የለውም፡፡ መሸሽ እንዲህ ካለው ሰው ነው፡፡

የሰሎሞን ቤተ መቅደስ በእነዚህ በመሟላት በሚኖሩ ወንድማማቾች እርሻ ላይ እንደተገነባው ሁሉ የኛም የትዳር፣ የወዳጅነት፣ የጓደኛነት፣ የሥራና የጉርብትና መቅደሳችን በመሟላት ላይ ቢመሠረት ኖሮ፣ ተባብሮ ከመውደቅ ተባብሮ ወደ ማደግ፣ ተያይዞ ከመጠፋፋት፣ ተያይዞ ወደ መመንደግ፤ ጥሎ ከማለፍ ይዞ ወደማለፍ ይሸጋገር ነበር፡፡ ይኼው ሦስቱንም ታላላቅ እምነቶች(እስልምና፣ ይሁዲነትንና ክርስትና) አስተሳሥሯል የሰሎሞን መቅደስ፡፡ ሁሉም እዚያ ቦታ አለው፤ ልብም አለው፡፡ ሁሉም እዚያ ይጸልያል፤ ሁሉም ያንን ቦታ ያከብራል፡፡ መግባባትን ከመነጋገር በላይ ይበልጥ የሚያጠነክረው ‹መሟላት› ነው፡፡ አብሮ መኖርን አብሮ ከመሥራት በላይ ‹መሟላት› የተሟላ ያደርገዋል፡፡ ወዳጅነትን አብሮ ከመብላት በላይ ‹መሟላት› ያጸናዋል፡፡

መሟላት መጓደልን የሚያጠፋ ነው፡፡ በመሟላት የሚኖሩ ወዳጆች የሚሞሉትን ያህል ይሞላላቸዋል፡፡ ሳያጎድሉ መስጠት የሚቻለው በመሟላት ነው፡፡ አንድ ኢትዮጵያዊ ተረት እዚህ ላይ ትዝ አለኝ፡፡ በወዳጁ ሀብት የሚቀና አንድ ጎረቤት ከወዳጁ አሞሌ ጨው ይበደራል፡፡ብድሩን ክፈል ሲባል ‹‹አሞሌውኮ ድንጋይ ሆነብኝ›› ብሎ ይመልሳል፡፡ ያ ጎረቤትም ተንኮሉን ቢያውቅም የሚያደርገው ስላልነበረው ዝም ብሎ ኖረ፡፡ አንድ ቀንም ‹እባክህ ሴት ልጅህ ባለቤቴን የድግስ ሥራ ታግዛት›› ብሎ ለመነውና የጎረቤቱን ሴት ልጅ ወሰደ፡፡ ልጂቱም ትመጣለች ተበላ ብትጠበቅ በዚያው ቀረች፡፡ ልጂቱን የወሰደው ጎረቤትም ‹‹ልጂቱማ ዝንጀሮ ሆነችብኝ›› ብሎ መለሰ፡፡ ያም ድሮ በአሞሌው ላይ የሠራውን ያውቅ ነበርና ውጦ ዝም አለ፡፡

ከብዙ ጊዜ በኋላ ሁለቱም ጠዋት ከብት አውጥተው ሲያሠማሩ ተገናኙ፡፡ አስቀድሞም ልጁ ዝንጀሮ ሆነች የተባለበት አባት እንዲህ ብሎ አንጎራጎረ፡-

‹‹ወይ ዘንድሮ ወይ ዘንድሮ

ልጄ ሆነች ዝንጀሮ››

አሞሌው ድንጋይ የሆነበትም

‹‹ወይ ጉባይ ወይ ጉባይ

አሞሌ ሆነ ድንጋይ››

ሲል መለሰ፡፡

የልጂቱ አባትም

‹‹አሞሌስ አለ ከጎታ

የልጄን ነገር እንዴታ›› ሲል ጠየቀ፡፡

የአሞሌው ጌታም፡-

‹‹አሞሌስ ካለ ከጎታ

ልጂቱም አለች ካጎቷ›› ሲል አበሠረው ይባላል፡፡ ስንሟላ እንጂ ስንባላ አናድግም፡፡

© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው፡፡

ቅጥረኛው አምባገነን መለስ ዜናዊ ወያኔ በ1983 አዲስ አበባ ሲገባ እግረ መንገዱን የገበሬውን ልጆች፣ ጋዳፊና የአረብ ሀገር ከበርቴዎች ባስታጠቁት ዘመናዊ ታንክና መሣሪያዎች፣ እያጨደ በሬሳቸውና በደማቸው ላይ እየተረማመደ እንደነበር መሪር የቅርብ ትዝታ ነው። በቅጥረኛው አምባገነን መለስ ዜናዊ ይመራ የነበረው ጎጠኛው የወያኔ መንግሥት፣ የኢጣልያ ፋሺስት ያወጣውን በተለይ በአማራና በኦሮሞ ላይ ያነጣጠረውን የከፋፈለህ ግዛው ፖሊሲ ኮርጆ በመከተል፣ የአፄ ምኒልክ […]

እንደተለመደው ዘወትር በየቀኑ እንደማደርገው ሁሉ – ማክሰኞ ምሽት አካባቢ (ግንቦት 5፣ 2006) የኢትዮጵያን ጠረንና ሙቀት በመሻት፡ የሃገር ቤት ወቅታዊ ዜናዎች ገጾችን ሳፈላልግ/ሳገላብጥ – በቤት ማስተላለፍ ሂደት የሚታየውን የኪራይ ሰብሳቢነት ተግባር ለማስወገድ እርምጃ እየተወሰደ ነው የሚለው በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) የተጻፈው አርዕስት ላይ ዐይኔ በድንገት አረፈ። አገራችን ምርጫ ዋዜማ ላይ ስለሆነች፡ በየመሥሪያ ቤቱ ባለሥልጣኖች ያልሆነውን ሆነ፡ […]

ቅጥረኛው አምባገነን መለስ ዜናዊ ወያኔ በ1983 አዲስ አበባ ሲገባ እግረ መንገዱን የገበሬውን ልጆች፣ ጋዳፊና የአረብ ሀገር ከበርቴዎች ባስታጠቁት ዘመናዊ ታንክና መሣሪያዎች፣ እያጨደ በሬሳቸውና በደማቸው ላይ እየተረማመደ እንደነበር መሪር የቅርብ ትዝታ ነው። በቅጥረኛው አምባገነን መለስ ዜናዊ ይመራ የነበረው ጎጠኛው የወያኔ መንግሥት፣ የኢጣልያ ፋሺስት ያወጣውን በተለይ በአማራና በኦሮሞ ላይ ያነጣጠረውን የከፋፈለህ ግዛው ፖሊሲ ኮርጆ በመከተል፣ የአፄ ምኒልክ […]

ካድሬዎች ወጣቶቹን እያደራጁ በአማርኛ ተናጋሪዎች ላይ ግድያና ድብደባ እንዲፈጽሙ እያደረጉ ነው፡፡ ትናንትና ማታ የኦህዴድ ካድሬዎች ቤታቸውን በእሳት ሲያቃጥሉባቸው አምሽተዋል፡፡ ህጻናት ሳይቀር ተቃጥለዋል፡፡ አብዛኛዎቹ ከተደበቁበትና ቤታቸው ያልተቃጠለባቸውም ከሰፈራቸው ለመውጣት አልቻሉም፡፡ በርካቶቹ ተደብቀው በምግብ እጦት ላይ ናቸው፡፡ ካድሬዎች አስረኛ እና አስራ ሁለተኛ ክፍል ያቋረጡ ወጣቶቹን እያደራጁ በአማርኛ ተናጋሪዎች ላይ ግድያና ድብደባ እንዲፈጽሙ እያደረጉ ነው፡፡ ወጣቶቹ ከከተማ በመውጣት […]

በነቀምቴ በሚገኘው የወለጋ ዩንቨርስቲ የሚማሩ የኦሮሞ ተማሪዎች ባነሱት ተቃውሞ የወያኔ ፖሊሶች አጸፋውን የወሰዱ ሲሆን በዚሁም አጸፋ የተጎዱ በርካታ ተማሪዎች ወደ ህክምን ጣቢያ ሄደዋል። ከተደበደቡት ተማሪዎች በከፊል ምስሎቻቸውን ይመለክቱ። እነዚህ የምታይዋቸው ተማሪዎች በዛሬው የተቃውሞ ሰልፋቸው ላይ ይተጎዱ ናቸው።

«ኢትዮጵያዉያን ከኦሮሚያ ይዉጡ» የሚል መፈክር በማሰማቱ የሚታወቀውና በቅርቡ የተቋቋመው፣ የኦሮሞ ሜዲያ ግሩፕ ቴሌቭዥኝ ጀርባ ዋናው ሰው ተብሎ የሚገመተው፣ ጃዋር ሞሃመድ፣ ኢሳትን ከኢቲቪ ጋር የሚሰሩ ሲል ክስ አቀረበ። በጊምቢ የሚኖሩ ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያዊያን ላይ ጥቃት ጥቃት እየተደረሰ እንደሆነ ኢሳት ሜያ 12 ቀን የዘገበዉን የተቃወመው ጃዋር፣ የኢሳትን ዘገባ የተጋነነ ብሎታል። ኢሳት የጊምቢ ነዋሪዎችን ሁሉ ሳይቀር በማነጋገር፣ አክራሪዎች […]

ይሁንና በመኻሉ 450 ገደማ የሚሆኑትን ለማትረፍ ተችሏል። ማኒሳ በተባለው ክፍለ ሀገር ፤ ሶማ በተባለው ጣቢያ በሚገኘው የድንጋይ ከሰል ማውጫ ጉድጓድ አደጋ በደረሰበት ቅጽበት፤ ወደ 800 የሚጠጉ ሠራተኞ ች እንደነበሩ ተገልጿል።

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ኦልሜርት ጉቦ በመቀበል በቀረቡባቸው በሁለት የክስ ጭብጦች ከ6 ሳምንታት በፊት የጥፋተኝነት ብይን ተላልፎባቸው ነበር ። ኦልሜርት ላይ ትናንት ውሳኔ የተላለፈው ለሁለት ዓመታት ከተካሄደ የፍርድ ሂደት በኋላ ነው ። ኦልሜርት 160 ሺህ ዶላር የሚደርስ ጉቦ ተቀብለዋል ሲል ፍርድ ቤቱ አስታውቋል ።

የወደፊቱን የሰው ቀጣይ ህልውና ለማረጋገጥ ፤ ከወዲሁ ስለፕላኔታችን አያያዝ ጠንቀቅ ማለት እንደሚገባ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ያተኮሩ ምሁራን አጥብቀው ይመክራሉ። አንዳንዱ መግለጫቸው እንዲያውም አደናባሪም፤ ተስፋ አስቆራጭም የሚመስልበት ሁኔታ አለ።

«አፍሪቃ የምትፈልገዉ ተግባር ነዉ፤ አፍሪቃ ወደ ተግባር እንድትገባ ከተፈለገ፤ አፍሪቃ የራስዋን ወይም ደግሞ ሀገሮች፤ የራሳቸዉን ፍላጎት፤ ሌሎችን በመጠበቅ ሳይሆን፤ በራሳቸዉን መወሰን መቻል አለባቸዉ» የኤኮነሚ ጉዳይ ምሁሩ ደምስ ጫንያለዉ፤ የአፍሪቃን ዓመታዊ የኤኮነሚ ዘገባን በተመለከተ የተናገሩት ነዉ።

በወለጋ ከኦሮምኛ ተናጋሪዎች ዉጭ ያሉ ኢትዮጵያዉያን ላይ ከፍተኛ ጥቃት እየተደረገ እንደሆነ ከመኢአድ አካባቢ የደረሱን ምንጮች ገለጹ። «በወለጋ ክፍለ ሃገር ከፍተኛ የሆነ ችግር ተፈጥሮል፡፡ በተለይ በጊምቢ ከተማ ኗሪ የሆኑ ከኦሮሞኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ዉጭ ያሉ ይደበደባሉ ይሰደዳሉ፣ ይገደላሉ» ያሉት የመኢአድ መንጮቻችን ፣ አቶ ፍሬዉ አያሌዉ የተባሉ የከተማዋ ነዋሪ በአክራሪ ኦሮሞዎች እንደተገደሉም ይገልጻሉ። ኦሮሞ ያልሆኑ ዜጎች ንብረትና ሱቅ […]

«አበሾች አዲስ አበባን በመጠቀም የኦሮሚያን መሬት እየወረሩ ነው» በሚል በቅርቡ ይፋ የሆነውን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በመቃወም በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተቃውሞ ማሰማታቸው ይታወቃል። ከተቃዉሞው ጋር በተገናኘ በርካታ ዜጎች የሞቱ ሲሆን፣ በንብረትም ላይ ከፍተኛ ጥፋት ደርሷል። በተነሳው ቀውስ ሰለባ ከሆነቸው ከተማ አንዷ የጊምቢ ከተማ ናት። ከጊምቢ የተላኩ ፎቶዎችን ይመልከቱ

ጥንታዊቷ የአምቦ ከተማ ፣ የኢትዮጵያን ዋና ከተማ አዲስ አበባ ከምእራቡ የኢትዮጵያ ክፍል የምታገናኝ ከተማ ናት። አገዛዙ በሚወስዳቸው ዘረኛ ፖሊሶዎች ምክንያት፣ አምቦ ብዙ የተረሳችና ሰፋፊ የልምታ እንቅስቃሴዎች የማይታዩባት ከተማ ነበረች። በከተማዋ ሶስት ፎቆች ብቻ የነበሩ ሲሆን፣ አገዛዙከፍተኛ አፈና ከሚያደርግባቸው ቦታዎች አንዷ ነበረች። ሰሞኑን በተነሳው ረብሻ ብዙዎች የተገደሉ ሲሆን፣ በከተማዋ የነበሩ ሶስት ትላልቅ ፎቆች ወድመዋል። የወ/ር አበበች […]