ጥር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ ከተሞች ሥር የሰደደውን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ ይረዳል የተባለ የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባ ረቂቅ አዋጅ በፓርላማ ጸደቀ፡፡ አዋጁ በተበታተነና በልማዊ መንገድ ሲካሄድ የነበረውን የመሬት ባለቤትነት ይዞታ አሰራርን በዘመናዊ መልኩ እንዲካሄድ የሚያስችል ከመሆኑም በላይ የህዝቦችን እኩል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚረዳ ነው ተብሎአል፡፡ የመሬት ይዞታ መብት ይፋዊ ምዝገባ …

ጥር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወደዓረብ አገራት ዜጎች የሚያደርጉት ጉዞ ከ2003 ዓ.ም በኋላ በአስደንጋጭ መልኩ ከ4ሺህ ወደ 198 ሺህ ማደጉን ዶ/ር ዘሪሁን ከበደ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ይፋ አደረጉ፡፡ ሚኒስትር ዴኤታው ለንባብ በበቃው “ዘመን” ከተባለው መንግስታዊ መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፤ በ2002 ዓ.ም ሚኒስቴር መ/ቤቱ መሰረታዊ የሥራ ሂደት ጥናት አጥንቶ ተግባራዊ ሲደርግ …

ጥር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ለኢሳት መረጃ በመስጠት ድርጅቱን ከውስጥ ሆነው የሚቦረቡሩ ሃይሎች አሉ በማለት እርስበርስ መወዛገባቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። አቶ በረከት ለሚኒስትሮችና ለኢህአዴግ  ከፍተኛ አመራሮች ያደረጉት ንግግር በኢሳት ከተለቀቀ በሁዋላ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች እርስ በርስ እየተወነጃጀሉ ነው። የኢህአዴግ አንዳንድ ከፍተኛ አመራሮች ውስጣችን ማጥራት አለብን በሚል ትናንትና ዛሬ …

ጥር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከጥር 16-18 ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀው የአፍሪካ ሚኒስትሮችና አምባሳደሮች ስብሰባ  የአማራ ክልል ም/ቤት በቻይና ድጋፍ ባሰራው አዲስ አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል፡ ህብረቱ አፍሪካ በ2063 ስለምትከተለው አቅጣጫ ይነጋገራል ተብሎአል። የአፍሪካ ህብረት ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ የኢትዮጵያ ከተሞች ስብሰባ ሲያዘጋጅ  የመጀመሪያው ይሆናል።

በምስራቅ ትግራይ የምተገኝ ወረዳ ናት። በ2007 ሕዝብ ቆጠራ መሰረት፣ ከመቶ አሥር ሺህ በላይ ነዋሪዎች ያሏት ናት። የአጽቢ ወረርታ ወረዳ ተብላ ትታወቃለች። በወረዳዋ መሃከል የምትገኝዉ ከተማ የአጽቢ ከተማ ናት። ከመቀሌ70 ኪሎሜተር በስተሰሜን፣ ከአዲግራት 94 ኪሎሜተር በስተደቡብ፣ ከዉቅሮ 20 ኪሎሜተር በስተ ምስራቅ የምትገኝ ናት። የዚህ ከተማ ነዋሪዎች በከፍተኛ ዉሃ እጥረት ምክንያት ከሕወሃት/ባለስልጣናት ጋር ትልቅ ዉዝግብ ላይ ናቸው። […]

የአንድነት ፓርቲ በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉዳይ ላይ እየሆነ ያለው፣ ሕዝብ በይፋ እንዲያወቀው መደረግ አለበት ሲል፣ ለአማራዉ ክልል አስተዳዳሪ ደብዳቤ አስገባ። ፓርቲዉ የአገርን ሉዓላዊነት በተመለከተ በሚደረጉ እንቅስቅቅሴዎች ዙሪያ፣ በሌሎች የዉጭ ሜዲያዎች በስፋት እየተነገረ፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ ግን መደበቁ ትልቅ ችግር እንደሚፈጠር በማሳሰብ፣ ጉዳዩ በአስቸኳይ ምላሽ እንዲያገኝና ለሕዝብ ይፋ እንዲደረግ አሳስቧል። ግልጽነትና ተጠያቂነት በሌለበት መልኩ በሚስጠር የሚደረግ ማናቸውም ስምምነቶች፣ […]

  የቤተ ክርስቲያን ዘርፈ ብዙ ችግር ለማረም በሚደረገው ጥረት ኹሉ በግንባር ቀደምነት መሰለፍ የእኛም የወላጆቻችንም ጽኑ አቋም ነው፡፡ አያሌ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ሙስናና ብልሹ አስተዳደርን እስከ መታሰር ደርሰው እየታገሉት ነው፡፡ ፓትርያርኩ ሙስናና ብልሹ አስተዳደርን ለማረም የሚያደርጉት ጥረት ታሪክ የሚዘግበውና መዘገብም ያለበት እውነት ነው፡፡ ሰንበት ት/ቤቶች የጨቅላ አእምሮዎችና የሥራ ፈቶች መጠራቀሚያ ሳይኾን ካህናትና ዲያቆናት፣ የሥነ መለኰት …

በየቀኑ ኢትዮጵያውያን ከ 3 እስከ 4 በሚደርሱ ጀልባዎች የመን እየገቡ ነው ። እነዚሁ የመን የደረሱ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ለእንግልት ና ለልዩ ልዩ ስቃይ መዳረጋቸውን ዘጋቢያችን አስታውቋል ።

የአደረጃጀትና አሠራር ለውጡን በመደገፍ በቅ/ሲኖዶስ ጸድቆ ተግባራዊ እንዲኾን የሚጠይቁት የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፣ ከአንድ ሚልዮን በላይ አጠቃላይ ብዛት ያላቸውን የሀ/ስብከቱን ወጣቶች የሚወከሉና ከ140 ሰንበት ት/ቤቶች የተውጣጡ ናቸው፡፡ በሀ/ስብከቱ፣ በክፍላተ ከተሞች ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶችና በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት መዋቅርና አደረጃጀት ውስጥ ሰንበት ት/ቤቶችን በማደራጀትና በማጠናከር ተልእኳቸውን እንዲወጡ ማድረግ ከዋነኛ ዓላማና ተግባራት መካከል አንዱ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያንን ሐዋርያዊ ተልእኮ …

ሁለት የጎዳና ልጆች የገና ዋዜማ አመሻሽ ላይ፣ ጎዳና ዳር ቁጭ ብለው አላፊ አግዳሚው ለዓመት በዓሉ ሲራወጥ ያያሉ፡፡ ዶሮ ያንጠለጠለ፣ በግ የሚጎትት፣ ቄጤማ የቋጠረ፣ በሬ የሚነዳ፣ እህል ያሸከመ፣ ‹የገና ዛፍ› የተሸከመ፣ አብረቅራቂ መብራት የጠቀለለ፣ ዋዜማ ሊቆም ወደ ቤተ ክርስቲያን ነጭ ለብሶ የሚጓዝ፣ ምሽቱን በዳንስ ሊያሳልፍ ሽክ ብሎ ወደ ጭፈራ ቤት የሚጣደፍ፣ ብቻ ምኑ ቅጡ፣ ከተማዋ ቀውጢ ሆናለች፡፡

እነርሱ ደግሞ የተበጫጨቀች ልብስ ለብሰው፣ የደረቀ ዳቦ ይዘው፣ በቢል ቦርድ ላይ የተለጠፈውን የጥሬ ሥጋ ሥዕል እያዩ፣ መጣሁ መጣሁ የሚለው የገና ብርድ እያቆራመዳቸው፣ የቆሸሸ ሰውነታቸውን እየፎከቱ፣ የቀመለ ፀጉራቸውን እያከኩ፣ በታኅሣሥ 15ና በታኅሥ 29 መካከል ያለው ልዩነት ጠፍቷቸው፣ የበግ ድምጽ እንጂ ሥጋው ርቋቸው፣ የበሬው ፎቶ እንጂ ሥጋው ጠፍቶባቸው፣ ያገኙትን ወረቀት እያነደዱ ጎዳናው ዳር ተቀምጠዋል፡፡

‹‹ቆይ ግን ገና ምንድን ነው?›› አለ አንደኛው ሰውነቱን እየፎከተ፡፡

‹‹የክርስቶስ ልደት ነዋ፤ በማይክራፎን ሲሰብኩ የሰማሁት እንደዚያ ነው››

‹‹የት፣ መቼ፣ ለምን ተወለደ?››

‹‹እነርሱ የሚሉት ቤተልሔም በምትባል ከተማ፣ በእኩለ ሌሊት፣ በብርድ ወቅት፣ ራቁቱን፣ እናቱ በከተማዋ ማደሪያ የሚሰጣት አጥታ፣ በተናቀው ቦታ በከብቶች በረት ውስጥ ተወለደ፡፡ በጣም ስለበረደውና ራቁቱን ስለነበር ከብቶቹ በትንፋሻቸው አሞቁት፤ ሌላ ሰው ስላልነበረ እረኞቹ መጥተው ዘመሩለት፡፡ እንዲህ ነው የሰማሁት፡፡››

‹‹እኛምኮ እንደርሱ የሚያስጠጋን አጥተን ነው ጎዳና የወደቅነው፡፡ እንደርሱ ራቁታችንን ነን፤ እንደርሱ የሚበላ የለንም፤ እንደርሱ እኛንም የሚያሞቁን እነዚህ ውሾች ናቸው፤ እንደርሱ እንደርሱ እኛም በተናቀው ቦታ ላይ ነን›› አለ ሁለተኛው ልጅ ውሻውን እየደባበሰ፡፡

‹‹የሚገርምህ ነገር ጌታ የተወለደው በከብቶች በረት ዋሻ ውስጥ ነው፡፡ ያኔ ጥድ የለም፤ በረት እንጂ፡፡ ጌታኮ ጫካ ውስጥ አልተወለደም፡፡ ያኔ ከረሜላ የለም፤ ያኔ ጥጥ የለም፣ ያኔ ፖስት ካርድ የለም፣ የሰብአ ሰገል ወርቅ፣ ዕጣንና ከርቤ እንጂ፡፡ አሁን ይኼን ሁሉ ከየት እንዳመጡት እንጃ፡፡ ይልቅስ ራቁታችንን ሆነን፣ የሚበላ ናፍቆን፣ በእንግዶች ማረፊያ ሥፍራ የሚሰጠን አጥተን፣ ከእንስሳት ጋር ተኝተን እኛ አለንላቸው፡፡ ገናኮ መከበር የሚገባው ከእኛ ጋር ነበር፡፡ ገና የሀብታሞች ሳይሆን የድኾች፣ የተከበሩ ሳይሆን የተዋረዱ፣ ቤት ላላቸው ሳይሆን ማደርያ ያጡ፣ ዘመድ ያላቸው ሳይሆን ወገን ያጡ ሰዎች በዓል ነው፡፡ ገና የሚወርዱበት እንጂ የሚወጡበት በዓል አልነበረም፡፡››

‹‹እኔም እሱን እያሰብኩ ነበር፡፡ ተመልከት ያኔ የዘመሩትን እረኞች አሁን ማንም አያስታውሳቸውም፡፡ ያኔ የቤተልሔም ሰዎች በጥጋብና በዕንቅልፍ ተወስደው አላስጠጋው ሲሉ በረታቸውን የሰጡት ከብቶች ነበሩ፡፡ አሁን የእነርሱ ዋጋ መታረድ ሆነ፡፡ በዓሉኮ የከብቶች በዓል ነበረ፡፡ እኔ ከብቶች ውለታ በዋሉበት፣ ከሰው የሚበልጥ ሥራ በሠሩበት በገና ቀን መታረዳቸው ይገርመኛል፡፡››

‹‹አይግረምህ፤ በሰው ልጅ ታሪክ ሁሉ እንደዚህ ነው፡፡ ታሪክ የሠሩትና መሥዋዕትነት የከፈሉት ምንጊዜም መሥዋዕት እንደሆኑ ናቸው፡፡ በኋላ የሚጠቀመው ታሪክ ሠሪው አይደለም፤ ታሪክ ተራኪው ነው፡፡ ‹የበሬን ምስጋና ወሰደው ፈረሱ› የተባለው ዝም ብሎ እንዳይመስልህ፡፡ አንተ በሠራኽው ታሪክ አንተን አርደው ያንተን በዓል የሚያከብሩ ሞልተዋል፡፡››

‹‹እርሱማ አታይም እንዴ፤ በኛ በድኾች ስም ይለመናል፤ ብር ይሰበሰባል፤ እኛ በፊልም እየተቀረጽን ታሪኩን እንሠራዋለን፤ በኋላ ግን እኛው ራሳችን በድህነት ቢላዋ እንታረድና የኛን በዓል ሌሎች ያከብሩልናል፡፡ ታሪኩን የሚሠሩት እረኞች፣ አበሉንና ደመወዙን የሚበሉት ግን የቤተልሔም ሰዎች፡፡ አንተ ፖስት ካርድ ብቻ ሆነህ ትቀራለህ፡፡ እስኪ የገናን በዓል ተመልከት፡፡ እረኞቹ የታሉ፤ በረቱ የታለ፤ ከብቶቹ የታሉ፤ ከሩቅ ሀገር የመጡት የጥበብ ሰዎች የታሉ፤ ጌታ የተኛበት የእንጨት ርብራብ የታለ፡፡ ሁሉም የሉምኮ፡፡ የእረኞቹን ቦታ ተኝተው የነበሩት የቤተልሔም ሰዎች ወስደውታል፤ የበረቱን ቦታ የገና ዛፍ ወስዶታል፤ የጥበብ ሰዎችን ቦታ የገና አባት ተረክቦታል፤ የከብቶቹን ታሪክ ሰባኪዎቹና ዘማሪዎቹ፣ ፓስተሮቹና ቄሶቹ ወስደውታል፤ የመላእክቱ ዝማሬ በጭፈራ ቤቶቹ ዘፈን ተተክቷል፡፡ ከብቶቹንም፣ እረኞቹንም፣ ሰብአ ሰገልንም፣ በረቱንም፣ መላእክቱንም፣ የምታገኛቸው ፖስት ካርድ ላይ ብቻ ነው፡፡››

‹‹የሚገርመኝ ምን እንደሆነ ታውቃለህ፤ በዚህ መንገድ ዳር በተሰቀለ ትልቅ ቴሌቭዥን ላይ ሳይ፣ የሃይማኖት አባቶች ‹በዓሉን ከተቸገሩት ጋር በማክበር አሳልፉት› ሲሉ እሰማለሁ፡፡ አንዳቸውም ግን ከመናገር ባለፈ ከተከበረ መንበራቸው ወርደው ከእኛ ጋር ሲያሳልፉ አይታዩም፡፡ ‹ክርስቶስ ከሰማያት ወረደ› ማለት እንጂ መውረድ ለካስ ከባድ ነው፡፡››

‹ካመጣኸውማ ገናኮ የመውረድ በዓል ነበር፡፡ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት ወረደ የሚባልበት በዓል ነበር፡፡ አሁን ግን የሚወጣ እንጂ የሚወርድ የለም፡፡ ወደ እኛ የሚወርድ የለም፡፡ ሰው አምላክ መሆን ቢያቅተው አምላክ ሰው ሆነ ይላሉ፡፡ እኛ እንደነርሱ መሆን አቅቶናል፤ ታድያ ምናለ እነርሱ እንደኛ ቢሆኑ፡፡ በጣም የሚገርመው ሰብአ ሰገል ስጦታ የሰጡት ራቁቱን ለነበረው፣ ቤት ላጣው፣ የቤተልሔም ሰዎች አላስጠጋ ላሉት፣ ከሰው ወገን ጠያቂ ላልነበረው ለክርስቶስ ነበረ እንጂ ሁሉ በእጃቸው፣ ሁሉ በደጃቸው ለሆኑት ለቤተልሔም ሰዎች አልነበረም፡፡ ዛሬ ግን ስጦታው ለቤተ ልሔም ሰዎች ሆነ፡፡››

‹አንድ ቀን አንድ ሰው ሲያስተምር ምን ሰማሁ መሰለህ፡፡ ክርስቶስ ‹ተርቤ አላበላችሁኝም፣ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝም› ይላል፡፡ የሰሙት ሰዎች ‹የት አግኝተን እናብላህ እናጠጣህ› ቢሉት ‹ለታናናሾቹ ካላደረጋችሁ ለእኔ አላደረጋችሁትም፣ ለታናናሾቹ ካደረጋችሁ ለእኔ አድርጋችሁታል› አላቸው አሉ፡፡ ታድያ ከኛ የባሰ ታናሽ ማን አለ? ያኔምኮ ክርስቶስ ተራ፣ ድኻ፣ እዚህ ግባ የማይባልና የተናቀ መስሎ ስለመጣ ነው የቤተልሔም ሰዎች ያላስጠጉት፡፡ ዛሬስ ድንገት ከእኛ መካከል ቢኖርስ፣ እዚህ ጎዳና ዳር ከውሾቹ ጋር ተኝቶ ቢሆንስ፤ በገዛ የልደቱ ቀን ሰዎች እርሱን ንቀው እያለፉ፣ ተጸይፈው እያለፉ፣ በጽድና በከረሜላ፣ በበግና በዶሮ፣ በጠላና በጠጅ፣ በፖስት ካርድና በስጦታ የራሱን በዓል እያከበሩለት ቢሆንስ፤ ››

‹ማን ያውቃል ወዳጄ፤ ሰው እንደሆነ በዓሉን እንጂ ራሱን ክርስቶስን የሚፈልገው አልመሰለኝም፡፡ ቢፈልጉት ኖሮማ አንድ ጥድ የሚገዙበት እኛን አልብሶ ‹ታርዤ አላለበሳችሁኝም› ከሚለው ያወጣቸው ነበር፤ የአንድ ፖስት ካርድ ዋጋ ለኛ የወር የቤት ኪራያችን ነበር፤ በጉን በልተው እንኳን ቆዳውን ቢሰጡን ለኛ የዓመት ቀለብ ነበር፤ ለከረሜላው የሚወጣው ገንዘብ የኛን የዓመት ጤና ይጠብቅ ነበር፡፡ አሁንማ የበዓሉ ምክንያት ተረስቶ በዓሉ ብቻ ቀርቷል፡፡››

‹‹እና አሁን ገና እየተከበረ ይመስልሃል››

‹‹ምን እየተከበረ ነው፤ እየተቀበረ ነው እንጂ››

© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት የወጣ ነው

አንድነት ፓርቲ ለአማራ ክልል እና ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ የኢትዮ ሱዳን ድንበር ማካለል ጉዳይ በአጭር ግዜ ውስጥ ለህዝብ ግልፅ እንዲሆን በደብዳቤ አሳሰበ። ዝርዝር ዘገባ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ !

የኦነግ መስራቾችና አንጋፋ መሪዎች፣ እነ ዶር ዲማ ነግዎ፣ አቶ ሌንጮ ለታ የመሳሰሉት፣ የኦሮሞ ጥያቄ የመገንጠል ሳይሆን የዴሞክራሲ ጥያቄ ነዉ በሚል፣ ራሳቸውን ከኦነግ አግልለው፣ የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፎረም (ኦዴፍ) የሚባል ድርጅት ማቋቋማቸው ያታወሳል። ኦዴፍም በኢትዮጵያ አንድነት እንደሚያምን ያረጋገጠ ሲሆን፣ ለኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮዮጵያዉያን ሁሉ እንቆማለን የሚል አቋም ፣ ድርጅቱ በተመሰረተ ሰሞን በስፋት ሲያንጸባርቅ ነበር። እንደዉም በፓልቶክ በተደረጉ […]

ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ አማካሪ የሆኑት አቶ በረከት ስምኦን ለመንግስት ሚኒስትሮችና ለከፍተኛ የኢህአዴግ አመራሮች በተዘጋጀው የምርጫ ውይይትና ግምገማ ላይ ባቀረቡት ንግግር ላይ እንደገለጹት አርሶ አደሩ እስካሁን በተሰረላት ስራ በመርካቱ ” መንግስት ሰላማዊ ሰልፍ ውጣ ቢለው ይወጣል፣ መንግስት ተኛ ቢለው ይተኛል፣ ግፍ ብንፈጽም አርሶአደሩ ይህን መንግስት ምንም አይለውም፣ …

ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦክስፋምን ጥናት መነሻ በማድረግ ረዩተርስ እንደዘገበው በምግብ አቅርቦት፣ በምግብ ጥራትና በምግብ ዋጋ ኢትዮጵያ ከ125 አገራት ከቻድ በመቀጠል የመጨረሻውን ደረጃ ይዛለች። በአለም ላይ የተመጣጠነ ምግብ በማቅረብ፣ በምግብ ዋጋና በጥራት ሆላንድ አንደኛ ሆና ስትመረጥ ፈረንሳይና ስዊዝርላንድ ይከተላሉ። አሜሪካ 21ኛ ደረጃ ስትይዝ ከአንድ እስከ 10 ያሉትን ደረጃዎች የአውሮፓ አገራት ይዘውታል። የኦክስፋም …

ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አሶሸትድ ፕሬስ እንደዘገበው የቻይና የአፍሪካ ህብረት ተወካይ የሆኑ አንድ ባለስልጣን ኢትዮጵያን በመጎብኘት ላይ ያሉትን የጃፓኑን ጠ/ሚ ሽንዞ አቤን ችግር ፈጠሪ ብለዋቸዋል። በአይቮሪኮስት፣ ሞዛምቢክና ኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ወደ አፍሪካ የመጡት ጠ/ሚ አቤ ለአፍሪካ አገራት ከፍተኛ የእርዳታ ገንዘብ ለመለገስ ቃል በመግባት የቻይናን ተጽእኖ ለመቋቋም ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውን …

ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአገሪቱ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ያለው የውሀ አቅርቦት አሳሳቢ እየሆነ ባለበት ሰአት በመቀሌና በአዳማ የሚታየው ከፍተኛ የውሀ እጥረት ነዋሪዎችን በእጅጉ እያስመረረ ነው። በመቀሌ አንዳንድ አካባቢዎች ካለፉት 4 ወራት ጀምሮ ውሀ ተቋርጧል። በአዳማም እንዲሁ አንዳንድ አካባቢዎች ለረጅም ቀናት ውሃ በመቋረጤ ነዋሪዎች ምሬታቸውን እየገለጹ ነው ። መንግስት የአገሪቱ የንጹህ …

ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሁለቱም ተፋላሚ ሃይሎች በአዲስ አበባ የሰላም ድርድር እያደረጉ ቢሆንም፣ ጦርነቱ ግን በመሬት ላይ እየተካሄደ መሆኑን የሚወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ። ከቀናት በፊት በነዳጅ ሀብቱ የበለጸገው አፐር-ናይል ስቴት የተበላውን ግዛት ዋና ከተማ ማላካልን መቆጣጠራቸውን  የመንግስት ሃይሎች ቢያስታውቁም፣ የአማጽያኑ መሪ የሆኑት ሪክ ማቻር ከተማዋን መልሰው መቆጣጠራቸውን አስታውቀዋል። የአማጽያኑ የድል ወሬ እንደተሰማ …

ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡት የግብጹ መሪ ሙሀመድ ሙርሲ በወታደሮችና በተቃዋሚዎች ድጋፍ ከስልጣን ከተወገዱ በሁዋላ የሽግግር መንግስቱ አዲስ ህገመንግስት በማርቀቅ ድምጽ እንዲሰጥበት አድርጓል። ባለፉት ሁለት ቀናት በተሰጠው ድምጽ አብዛኛው ህዝብ አዲሱን ህገመንግስት ይደግፋል ተብሎ ይጠበቃል። በአዲሱ ህገመንግስት አንድ ፕሬዚዳንት ለ2 ጊዜ ብቻ የሚመረጥ ሲሆን ፓርላማውም ፕሬዚዳንቱን ከስልጣን የማንሳት መብት …

ሰሞኑን በስፋት የሚወራው ስለ አዲሱ የአንድነት ሊቀመንበር ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው ነዉ። ነገር ግን የአንድነት ፓርቲ በተለያየ ጊዜ አባላቱና ደጋፊዎች ሲናገሩ እንደሚሰማዉ የአንድ ሰው ድርጅት ሳይሆን በርካታ ጠንካራ አመራር አባላት ያሉትብ ደርጅቱ መሆኑን ነዉ። ኢንጂነር ዘለቀ ረዲ ይባላሉ። በሲቪል ኢንጂነሪንግ ባችለር ኦፍ ሳይንስ ዲግሪ ያላቸው ሲሆን፣ በኢንተርናሽናል ሪሌሽንስ ሁለተኛ ባችለር ኦፍ አርት ተቀብለዋል። በአድንነት ጠቅላላ ጉባኤ […]

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ለአንድነት ፓርቲ ባቀረበው ጥሪ መሰረት የፓርቲው ስራ አስፈፃሚዎችና ከ22 ከሚበልጡ የህብረቱ ሀገራት ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውን የአንድነት ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ክፍል አስታወቀ፡፡ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው ለፍኖተነፃነት እንዳስታወቁት ትላንት ጥር 6 ቀን 2006 ዓ.ም በተደረገው በዚህ ውይይት የአንድነት ፕሬዝዳንት ፣የህዝብ ግንኙነትና የውጪ ግንኙነት ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡ በውይይቱ ወቅት […]

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች እሁድ ጥር 4 ቀን 2006 ዓ.ም ቅሊንጦ ማረሚያ ቤት በመሄድ የሙስሊም ማህበረሰብ የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴን ጎበኘ፡፡ ዝርዝር ለማንበብ እዚህ ያጫኑ!

ፋሲል የኔዓለም  Engi. Gezachew Shiferawግርማ ካሳ
የኢሳት ባልደረባ አቶ ፋሲል የኔዓለም “የአንድነት ፓርቲ የመጪው ጊዜ ፈተና” በሚል ርዕስ የጻፉትን ዘ-ሐበሻ ድረገጽ ላይ አነበብኩ። አቶ ፋሲል ጽሑፉን ያቀረቡት እንደ ግል አስተያየት እንደመሆኑ፣ ኢሳትን በዚህ ውስጥ ጣልቃ አላስገባም። የአንድነት ፓርቲ አዲሱ ሊቀመንበር፣ ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው፣ ሀገር ውስጥ ለሚታተመው ሪፖርተር ጋዜጣ ከሰጡት ቃለ ምልልስ፣ የሚከተለውን በመጥቀስ ነበር አቶ ፋሲል ጽሑፋቸውን የጀመሩት፤ 

ሙሉውን አስነብበኝ …

Ethiopians in Saudiየተመላሾች ጉዳይ …
ነቢዩ ሲራክ
ከሳውዲ ወደ ሀገር ቤት የተመለሱ ዜጎችን በሚመለከት የጀርመንና የአሜሪካ ራዲዮን ጨምሮ በርካታ የመገናኛ ብዙኀን አንድ አይነት የሚመስል መረጃ ግፉአን ተመላሾችን እማኝ እያደረጉ መረጃ አቀብለውናል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በተለምዶ እሩቅ ምስራቅ ተብሎ በሚታወቀው የኢሲያ ክ/ዓለም ከጃፓን ባህር በስተምስራቅ በሰላማዊ ውቅኖስ፣ በደሴት መልክ የምትገኘው ጃፓን ስያሜዋም እራሱ በእነርሱ ቐቐ አተረጉዋጎም የጸኃይ መነሻ እንደማለት ነው።

አንዱዓለም አራጌ Andualem Aragieግርማ ካሳ

“በሕገመንግሥቱ የመደራጀት መብታቸው የተጠበቀላቸው ፓርቲዎችን አልከሰስንም። ፓርቲዎችን ግን ሽፋን አድርገው ሥርዓቱን ወይንም ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን ለመናድ እንንቀሳቀሳለን የሚሉ ኃይሎችን ግን ዛሬም፣ ነገም፣ ሕጉን የማስከበር ግዴታና ኃላፊነት ስላለብን ከመከሰስ አያመልጡም ማለት ነው።”

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጀርመን ፤ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የጸጥታ መረጃ ልውውጥን በተመለከተ አዲስ ስምምነት ለማድረግ የምትሻ ሲሆን ፤ በዚህ ረገድ የወደፊቱ ግንኙነት ምን መሆን እንደሚገባው ፤ የህዝብ እንደራሴዎቿን ም/ቤት ዛሬ አከራክሯል።

ውዝግብ ያዳቀቃት የማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ የሽግግር ምክር ቤት እንደራሴዎች ባለፈው ሳምንት የወረዱትን የቀድሞ ፕሬዚደንት ሚሼል ጆቶዲያን የሚተካ ለመመረጥ ጉባዔ ጀመሩ።

ይድነቃቸው ከበደ Yedenekachew Kebedeይድነቃቸው ከበደ

“ሕዝቡ እኔ ማን እንደሆንሁ ይላል?” በማለት እየሱስ ክርስቶስ መረጃ ይጠይቃል፤ ደቀመዛምርቶችም ስለሱ የተባለውን አንድም ሳያስቀሩ ይነግሩታል። እሱም መልሱ እንዲህ ይላቸዋል “እናንተስ እኔ ማን እንደሆንሁ ትላላችሁ?” አላቸው። እነሱም መለሱለት። ሙሉ ታሪኩ ሉቃስ ም.9 ቁ.18 ላይ ይገኛል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ግርማ ሞገስ
ኢትዮጵያ ከውጭ ወረራ ረጅም የነፃነት ዘመን እንዳላት የሀገር ተወላጅ እና የውጭ ሀገር የታሪክ ተመራማሪዎች ያረጋግጣሉ። ይሁን እንጂ በሥልጣኔ ግን ብዙም እንዳልገፋች ይኸው ዛሬ የእኛም ትውልድ ሳይቀር የሚያየው ሕቅ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ኡስታዝ አቡበከር አህመድ የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ዛሬ ረቡዕ እንዲቀርቡ የተደረገ ሲሆን በ 2004 በመኪና ሰው ገጭተው አምልጠዋል በሚል ክስ እንደተመሰረተባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡

ኡስታዝ አቡበክር አህመድ ፍርድ ቤት ከቀረቡ ቡሃላ አቃቤ ህጉ ክሱን ለፍርድ ቤቱ በንባብ ያሰማ ሲሆን ሀምሌ 8 2004 ላይ በተለምዶ ሶማሌ ተራ በሚባለው አካባቢ ላይ በንብረት እና በሰው ሂወት ላይ አደጋ ሊያስከትል በሚችል መልኩ ከተገቢው ፍጥነት በላይ አሽከርካሪውን በማሽከርከር በአንድ ሰው የእጁ አውራ ጣት ላይ የስብራት አደጋ አድርሰው ጥለውት ሄደዋል የሚል ክስ እንዳቀረበባቸው ተዘግቧል፡፡

ይህም ድርጊት ተፈፀመ የተባለው ሃምሌ 8 ቀን የደህንንንት ሃይሎች የኮሚቴውን አመራሮች ከመንገድ ላይ በማገት ወደ ሚፈልጉት ቦታ የብልግና ስድብ እየሰደቡ ይዘዋቸው በሚወስዱበት ሰአት መሆኑ ታውቋል፡፡ በዚህ ቀን መታቂያቸውን አናሳይም ያሉት ደህንነቶች ጋጠወጥ በሆነ መልኩ ብልግና እየተሳደቡ ለማገት ያደረጉትን ሙከራ በማክሸፍ ወደ ታላቁ አንዋር መስጂድ አምልጠው መግባታቸው ይታወሳል፡፡ በዚህ ወቅት ነው ሰው ገጭታችሁ አምልጠሃል በሚል በሃሰት ወንጀል የቀረረበባቸው፡፡

ኡስታዝ አበቡበከር አህመድ ከዚህ ቀደም በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የወንጀል መርማሪ ፖሊሶች ወደሳቸው በመሄድ ይህን ወንጀል ፈፅመዋል በሚል ቃላቸውን እንዲሰጡ ተጠይቀው የነበረ ሲሆን ኡስታዝ አቡበከርም የተባለውን ድርጊት አለመፈፀማቸውን በወቅቱ መኪና ሲያሽከረክሩ እንዳልነበር፣መኪናውም የሌላ ሰው እንደነበር እና በሹፌር ሲሄዱ እንደነበር ብሎም ከፊት ለፊት በነበረው የመኪና መቀመጫ ላይም ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ተቀምጠው እንዳልነበር እና በደህንነቶች ጋጠ ወጥ በሆነ መንገድ የእገታ ወንጀል ሲፈፅምባቸው ከወንጀል ድርጊቱ ማምለጣቸውን በዝርዝር ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡

ይህንንም በማስመለከት ዛሬ ፍርድ ቤት በቀረቡበት ሰአት ፍርድ ቤቱ ቃላቸውን ሰጥተው እንደሆነ ለማረጋገጥ የጠየቃቸው ሲሆን ኡስታዝ አቡበከር አህመድም ቃላቸውን መስጠታቸውን እና የዚህ አይነት ድርጊት በወቅቱ አለመፈፀሙን ብሎም የሚያውቁት ጉዳይ እንደሌለ አስረድተዋል፡፡

ፍርድ ቤቱም ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የሚባሉ አካላት ፍርድ ቤት መቅረባቸውን የጠየቀ ቢሆንም አለመገኘታቸው የተገለፀ ሲሆን ምስክር የተባለ አንድ ግለሰብ ብቻ ግን ችሎት የቀረበ ሲሆን ሁሉም ተሟልተው እንዲቀርቡ ለጥር 28 ቀነ ቀጠሮ እንደተሰጣቸው ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

ይህ ክስ ሆን ተብሎ የኡስታዝ አቡበከር አህመድን ፅናት ለመፈታተን እና ተስፋ ለማስቆረጥ ሆን ተብሎ የተደረገ ተግባር ሲሆን በተጨማሪም ኮሚቴው በእስር ላይ ሆነው ባወጡት መግለጫ በመበሳጨታቸው እና የተፈጠረው መነቃቃት ወደሌላ አቅጣጫ ሆን ተብሎ ለማስቀየስ መሆኑን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

ግርማ ካሳ
ጆን ኬሪ (ግራ)፣ ቴዎድሮስ አድኀኖም (ቀኝ) John Kerry (L) Tedros Adhanom (R)ኢቲቪ በቅርቡ አንድ፣ በአንድ በኩል አሳዛኝ፤ በሌላ በኩል አስቂኝ ዶኪሚንተሪ ለተመልካቾቹ አቅርቧል። በርካታ ጉዳዮች ተነስተዋል። በዚህ ጽሑፍ የፌዴራል ከፍተኛ አቃቤ ሕግ የሆኑት፣ አቶ ብርሃኑ ወንድማገኝ፣ አንጋፋው ጋዜጠኛ እስክንደር ነጋን በተመለከተ፣ በተናገሩት ላይ ጥቂት ሃሳቦችን ለመገልጽ እወዳለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

(ውስጥ ውስጡን ድመትም ነብር ናት) ክፍል 1
ይድረስ ታሪክ ለምትንሻፈፉ እና በብሔር ለማጋጨረት ለምትጠሩ ሁሉ
ቶሎሣ በቀለ

አባቴ አንድ ነገር ሳይጥማቸው ሲቀር “ኪሳ ኬሳ አዱሬን ቢኒሳ” ይላሉ። በኦሮምኛ፤ “ውስጥ ውስጡን ድመትም ነብር ናት” ማለት ነው። ይህ የኦሮሞን አባባል የተጠቀምኩት የኦሮሞ ልጆች ላይ ነብር መስለው ድመት የሆኑ የተገላበጠ ገመና ያላቸው እንደ እባብ ቆዳቸውን እየሸለቀቁ ወደ እሳት የሚገፉት ስንኩል ሰዎች ስላሉ ነው። ለእነዚህ የታሪክ ዝቃጮች ጥያቄ ማቅረብና እና እውነታውን ማሳየት እፈልጋለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

የኢትዮጵያ መንግስት የሆነው ህወሃት በሀገራችን ሰላምና ፍትህ፣ ልማትና እድገት እየመጣ ነው እያለ የተረጋጋ መሆኑን በማስመሰል በየጊዜው ይናገራል። ነገርግን የሀገሪቱን ገንዘብ በተዘዋዋሪ በውጪ በሚኖሩ የስርአቱ አግልጋዮች ስም የቦታና የንግድ ግዢ በውጪ ሀገር የማድረግ ስራ በሰፊው እየተፋፈመ መሆኑን የውስጥ ዜና ምንጮቻችን ገልፀዋል።

በተለይም በአሜሪካን ሀገር በሚገኙ የተለያዩ ግዛቶች በጉብኝት ስም ታማኝ ሰዎችን በመላክ የሀገሪቱን ገንዘብ በማሸሽ ቦታና የንግድ ማእከሎችን እንዲገዙ እየተደረገ ነው። ህወሃት ራሱ ያልተረጋጋ እና አደጋ ያንጃበበት በመሆኑ ውስጣቸው መረጋጋት እንደሌለበት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ።

ታዲያ ይህንን ፍርሃት በመሸፈን በበላይነት የህወሃት ኤፈርት ከፍተኛ አመራሮች ይኼን ገንዘብ የማሸሽን ዘዴ እንደ አንድ አማራጪ ወስደው ራሳቸውንና ንብረታቸውን ለማሸሽ እየተዘጋጁ ነው ሲል መረጃውን የላከልን ዘጋቢያችን አስታውቋል። በቅርቡ ከሁለት ወር በፊት የኤፈርት ልኡክ ቡድን ወደ አሜሪካ ተልእኮ እንደነበርም አስረድቷል። ከዚህ ዜና ጋር በተያያዘ የህወሃት ባለስልጣኖች ገንዘባቸውን በማሸሽ ላይ ናቸው ሲል የግንቦት 7 ሬዲዮ በቅርቡ መዘገቡ ይታወሳል። (አባይ ሚዲያ)

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ለአንድነት ፓርቲ ባቀረበው ጥሪ መሰረት የፓርቲው ስራ አስፈፃሚዎችና ከ22 ከሚበልጡ የህብረቱ ሀገራት ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውን የአንድነት ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ክፍል አስታወቀ፡፡ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው ለፍኖተነፃነት እንዳስታወቁት ትላንት ጥር 6 ቀን 2006 ዓ.ም በተደረገው በዚህ ውይይት የአንድነት ፕሬዝዳንት ፣የህዝብ ግንኙነትና የውጪ ግንኙነት ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት የተለያዩ ሀገራትን የወከሉት የህብረቱ ዲፕሎማቶች አሁን ስለሳለው አጠቃላይ የሀገራችን የፖለቲካ ሁኔታ፣አንድነት እንደ ፓርቲ ያለበትን ሁኔታ በዝርዝር ለማወቅ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት የፓርቲው ፕሬዝደንት በፕሮጀክተር የታገዘ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አንድነት ከግንኙነት ስትራቴጂ አንፃር በሀገር ውስጥ እንዲሁም በውጪ ማለትም ከኢትዮጵያ ዳያስፖራና ከአለም አቀፉ ህብረተሰብ ጋር ስለሚኖረው ግንኙነት የተብራራ ምላሽ ተሰጥቷቻዋል፡፡

ኢንጅነት ግዛቸው አንድነት በሚመለከት ባቀረቡት ገለፃ የፓርቲውን ርዕይ፣ተልዕኮና አላማ በሰፊው አብራርተዋል፡፡በመቀጠልም ስለአንድነት ፖሊሲዎችና መርሆዎች ጥልቅ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ አክለውም የአንድነት ፓርቲን ተቋማዊ አደረጃጀት በሚመለከት ገለፃ ሰጥተዋል፡፡ የሀገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ በሚመለከትም የኢህአዴግ መንግስት ባለፉት አመታት አንዳችም አይነት የለውጥ አዝማሚያ እንዳላሳየ ይልቁኑም ተቋማዊ የአፈና ስርአትን እያጠናከረ እንደሚገኝ ፕሬዝዳቱ ማሳያዎችን በመጥቀስ አብራርተዋል፡፡

የኢህአዴግ መንግስት የተዘፈቀበትን ሙስና ግዝፈት የዘረዘሩት ኢንጅነር ግዛቸው የፀረሽብር ህጉ ከመንግስት የተለየ የፖለቲካ አቋም ያላቸውን ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ለማጥቃት የተቀመጠ መሆኑን በአንድነት አመራሮችና በሌሎች የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችም ላይ የደረሰውን እስርና እንግልት በማሳያነት አስረድተዋል፡፡ አንድነት ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት ጋር መልካም ግንኙነት እንዳለውና በበርካታ ሀገራትም የተቋቋሙ የአንድነት ድጋፍ ሰጪ ቻፕተሮች እንዳሉጠቁመዋል፡፡

ወደፊትም በተጠናከረ ደረጃ በሀገራቸው ፖለቲካ ላይ በቀጥታ የሚሳተፉበትን መንገድ እንደተቀየሰና የዲያስፖራው አባላትን በአባልነትና በድጋፍሰጪነት በንቃት ለማሳተፍ መታቀዱን ፕሬዝደንቱ ተናግረዋል፡፡ በውይይቱ ላይ ከፓርቲው ፕሬዝደንት ከኢንጅነር ግዛቸው ሽፈራው ጋር የተገኙት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ሀብታሙ አያሌውና የውጪ ግንኙነት ሀላፊው ኢ/ር ዘለቀ ረዲ ተጨማሪ ማብራሪያ መስጠታቸውም ታውቋል::

የጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ አማካሪ የሆኑት አቶ በረከት ስምዖን በቅርቡ ከሚኒስትሮች እና ከኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ባደረጉት ውይይትና ግምገማ ላይ «ህዝቡን ለመምራት የሚነደፉ ንድፈ ሀሳቦች ( ቲዮሪዎች) በየጊዜው ካልተሻሻሉ የሚዝጉ በመሆናቸው አብዮታዊ ዲሞክራሲ በልማታዊ ዲሞክራሲ እንዲተካ ተደርጓል» ብለዋል። «የኢህአዴግ መንግስት ይበልጥ የሚገለጸው በአብዮታዊ ዲሞክራሲ አስተሳሰብ ሳይሆን በልማታዊ ዲሞክራሲ አስተሳሰብ ነው» በማለት አቶ በረከት ገለጽዋል።

አቶ በረከት አብዮታዊ ዲሞክራሲ በልማታዊ ዲሞክራሲያዊ መንግስት ከመተካቱ በፊት ፣ ግንባሩ ለ3 ተከፍሎ እንደነበር ገልጸዋል። አንደኛው የአመራር ወገን «ችግራችን የውስጥ ነው እና በቅድሚያ የውስጥ ችግራችንን እንፈትሽ የሚል» አቋም ሲይዝ ፣ ሌላው ወገን ደግሞ ዋናው ችግራችን ሻዕቢያ በመሆኑ በቅድሚያ ሻዕቢያን እንውጋ የሚል አቋም ይዞ እንደነበር፣ እና ሻእቢያን ከወጋን በኋላ ወደ ውስጥ ችግራችን እንመልከት የሚለው ሶስተኛው አማራጭ አሸንፎ መውጣቱን ገልጸዋል። «በ1997 ዓ.ም ዋናው የአመጽ ሀይል የነበረው ስራ ያጣውና ተስፋ የቆረጠው ወጣት ነው» በማለት የገለጹት አቶ በረከት ለወጣቱ ስራ ካልተፈጠረለት በመንግስት እና በአገር ላይ እንደሚያምጽ ገልጸዋል። መንግስት የምርጫ 97ትን አመጽ ያስነሱት ተቃዋሚዎች ናቸው ብሎ ሲከስ መቆየቱ ይታወቃል።

ኢህአዴግ ከባለሀብቱ ነጻ የሆነ መንግስት ለመመስረት መነሳቱን የገለጹት አቶ በረከት፣ ስልጣን ላይ የሚያመጣን አርሶአደሩና በከተማ ያለው ጭቁኑ ህዝብ ነው እንጅ ባለሀብቱ አይደለም ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግስት በባለሀብቱ ገንዘብ የሚተዳደር አይደለም ያሉት አቶ በረከት፣ ገንዘብ ከፈለገ ከባላሀብቱ በግብር መልክ መውሰድ እንደሚችል ተናግረዋል። ይህ መንግስት ለህልውናው የራሱ የገቢ ምንጭ እንዳሉት የጠቀሱት አቶ በረከት፣ አየር መንገድን ባንኮችን እና መብራት ሀይልን በምሳሌነት አንስተዋል። የመንግስትን አስተዳደር ያለምንም ችግር ለማስኬድ የባለሀብቱም የውጭ ድጋፍም እንደማያስፈልግ አቶ በረከት አክለዋል።

አቶ በረከት፣ ኢህአዴግ ምርጫውን ያለባለሀብቶች ድጋፍ ማሸነፍ እንደሚችል እየገለጹ ባለበት ጊዜ በድንገት የመንግስት ተቋሞችን በመግለጽ በቂ ገንዘብ አለን ማለታቸው ተሰብሳቢዎችን ማስገረሙን ስብሰባውን የተከታተሉት አንድ ከፍተኛ የኢህአዴግ አመራር ገልጸዋል። አመራሩ እንዳሉት ኢህአዴግ ለምርጫ ማስኬጃ ከመንግስት ገንዘብ እንደሚወሰድ የአቶ በረከት ንግግር በቂ ማሳያ ነው ።

መንግስት የራሱ ገንዘብ ከሌለው እንደምእራብ የአፍሪካ አገራት ይሆናል ያሉት አቶ በረከት፣ የኮትዲቩዋር ሚኒስትሮች ደሞዛቸውን የሚወስዱት ኮትዲቯር ከሚገኘው የፈረንሳይ ኢምባሲ ነው ይላሉ። በኬንያም ሁኔታው ተመሳሳይ መሆኑን አቶ በረከት አክለዋል ኢህአዴግ በ2002 በተደረገው ምርጫ ከግል ባለሀብቶች ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡ ይታወቃል። በባቡር ግንባታ፣ በመንገድ ቁፋሮና በትራንሰፖርትና እጥረት የተነሳ በአዲስ አበባ መኖር ያስጠላል ያሉት አቶ በረከት ያም ቢሆን ግን ህዝቡ ልማት ነው በሚል እንደሚቀበለው ገልጸዋል።ኢሳት ዜና