ኬሳ ኬሳ አዱሬን ቢነሳ
(ውስጥ ውስጡን ድመትም ነብር ናት) ክፍል 1
ይድረስ ታሪክ ለምትንሻፈፉ እና በብሔር ለማጋጨረት ለምትጠሩ ሁሉ
ቶሎሣ በቀለ
አባቴ አንድ ነገር ሳይጥማቸው ሲቀር “ኪሳ ኬሳ አዱሬን ቢኒሳ” ይላሉ። በኦሮምኛ፤ “ውስጥ ውስጡን ድመትም ነብር ናት” ማለት ነው። ይህ የኦሮሞን አባባል የተጠቀምኩት የኦሮሞ ልጆች ላይ ነብር መስለው ድመት የሆኑ የተገላበጠ ገመና ያላቸው እንደ እባብ ቆዳቸውን እየሸለቀቁ ወደ እሳት የሚገፉት ስንኩል ሰዎች ስላሉ ነው። ለእነዚህ የታሪክ ዝቃጮች ጥያቄ ማቅረብና እና እውነታውን ማሳየት እፈልጋለሁ።