አንድነት ፓርቲን በተመለከተ መልስ ለኢሳቱ ፋሲል የኔዓለም
ግርማ ካሳ
የኢሳት ባልደረባ አቶ ፋሲል የኔዓለም “የአንድነት ፓርቲ የመጪው ጊዜ ፈተና” በሚል ርዕስ የጻፉትን ዘ-ሐበሻ ድረገጽ ላይ አነበብኩ። አቶ ፋሲል ጽሑፉን ያቀረቡት እንደ ግል አስተያየት እንደመሆኑ፣ ኢሳትን በዚህ ውስጥ ጣልቃ አላስገባም። የአንድነት ፓርቲ አዲሱ ሊቀመንበር፣ ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው፣ ሀገር ውስጥ ለሚታተመው ሪፖርተር ጋዜጣ ከሰጡት ቃለ ምልልስ፣ የሚከተለውን በመጥቀስ ነበር አቶ ፋሲል ጽሑፋቸውን የጀመሩት፤