Tag: Ethiopia
የጠቅላይ ሚኒስትሩ እጅ እጅ ያለዉ ዶሮ ወጥና ፖለቲካ
http://www.eaglewingss.com/%E1%8B%A8%E1 … %E1%8C%A5/
የጠቅላይ ሚኒስትሩ እጅ እጅ ያለዉ ዶሮ ወጥና ፖለቲካ
Samson K.
Posted By Samson K.
በቅርቡ ተጠቅላይ ሚንስትሩ ሃይለማሪያም ደስ አለኝ ዓረብ ሐገር ያዩትን ወገንና አዉሮፓ መጥተዉ ያዩትን የወገን ችግር፣በምፀት ሲገልፁ- ብዙ እንቶ ፈንቶ ተናግረዉ ነበር ፈረንጆቹ bla -bla ይሉታል ፣ ከዛ ዉስጥ ግን አንድ አነጋገራቸዉ ቀልቤን ስባ ሌላም ነገር አስታወሰችኝና ትንሽ ልበል ብዬ እኔም ብዕሬን አነሳዉ ።
ምን ሆነዉ ነው እንደዚህ በሰዉ ሐገር እሚሰቃዩት -ሐገራቸዉ ቢሆኑ ጠግበዉ መብላት እንደሚችሉ, ስደተኛዉን ኢትዮጵያዊም ሆነ ያገሪቷን ክብር በወረደ ቃላት ሲዘባበቱበት ከራሳቸዉ አንደበት ሰማሁና ፣ ታዲያ ይሔን ግዜ ምን አሰብኩ እኝህን ጠቅላይ ሚንስትር በዙሪያቸዉ ያሉ የድሮ ማርክሲስት ኤሊትሶች ይህን እንዲናገሩ እና እንዴት ከጨወታ እያስወጡዋቸዉ እንደሆነና መጨረሻቸዉም ከግዜሩም ከሰይጣኑም እንዳይሆኑ ተደርጎ የስርዓቱ የተሞላ አሻንጉሊት ሲሆኑ ማየቱ እንደዜጋም እንደሰዉም ስላሳዘንኝም ነዉ ።
ባንድ ዎቅት በፈረንሳይ ዓብዮት የፈረንሳይ የተራቡ ጭሰኞች በ፩፯፯፭ 1775 በፈረንጆቹ አቆጣጠር ባነሱት የዳቦ ጥያቄ ልዕልቲቷን ማሪይ አንቶይነት Marie Antointte ዳቦ ከሌለ ለምን ኬክ አይበሉም ዎይንም ደግሞ ኬክ ይብሉ ብላ የተናገረችዉን በወቅቱ የነበረዉ ምሁር ዓብዮተኛ የልዕልቲቷን አባባል በሁለት መንገድ ሰንጥቆ የህዝብ ቁጣ public plight መቀስቀሻ ተደርጎ በወቅቱ የነበረዉን የቡርዥዋ የመደብ አርስቶክራሲ aristocracy ችግር በማሣየትና እና የልዕልቲቷን ኦስትሪያዊነት ከፈረንሳይ ሞናርኪ ሉዊስ ፩፮ኛLouis XVI. ለመገንጠል የርስዋን አባባል ለፖለቲካ ትርፍ ተጠቅመዉበታል ።(ላንባቢያን- እንደማስታወሻ እንደምርቃትም ትሆነን ዘንዳ በዚች ዙሪያ ትንሽ ብናክል)-በነገራችን ላይ እዚህ ጋር አንባቢያን ስለዚህ አባባል በተለያዩ የታሪክ ፅሁፎች ዉስጥ ለምን ኬክ አይበሉም ያለችዉ ማሪያ ተረዝ Maria Therese ትባል የነበረች የፈረንሳዩ የሉዊስ ፩፬ኛ XIV ሚስት የነበረችዉን እንደሆነም ይነገራል ይህንንም የፃፈዉ ለመጀመሪያ ግዜ ዤን ዣኹዊዝ Jean -Jacques Rousseau ይባል የነበረ የፖለቲካ ፈላስፋ ‘ኑዛዜ’ ዎይንም ‘ኮንፌሽን confession ‘ብሎ ባሳተመዉ መፅሐፉ ዉስጥ እንዳሰፈረ የተለያዩ መጣጥፎች ይናገራሉ በዚ ጉዳይ እስካሁን ብዙ የታሪክ ፀሐፍት ለሁለት እንደተከፈሉ ነዉ ፤አንደኛዉ ወገን Marie Antoinette የማሪዬ አንቶይነት አባባል ሲል ሌላኛዉ ደግሞ የማሪያ ተሬዝ Maria Thereseነዉ እንዳለ ነዉ ። Louis XVIIሉዊስ ፩፰ኛም በራሱ ብዕር በ፩፯፱፩ (1791) አጠናቅሮ እንደፃፈና ኣባባሉም የማርያ ተረዝ መሆኑን የፃፈዉ ማስረጃም እንዳለ እሚተርኩ አሉ )
እናም ታዲያ ወደተነሳሁበት ርዕስ ስመለስ የኙ ጠቅላይ ሚንስትር ሐይለማሪያም ደስ አለኝ የጀርመን German ጉብኝት ወገን በመጠለያ ካምፕ ዉስጥ ባዶ ዱቄት ሲበላ አይተዉ የተናገሩት የማሪዬን Marie A.ዎይንም ማሪያ ተረዝ Maria Therese አባባል ስላስታወሰኝ እና መጨረሻቸዉም ስላሳዘነኝም ነዉ። ዱቄት ለምን ይበላሉ ዶሮ እያለ ከሆነ አባባላቸዉ ለኛ ሐገሩ ሐይለ ማሪዬ Marie የዘመናችን ያበሻ አባባል phrase ሆና እንዳትቀር ያስፈራል ፤ ከሆነ እንግዴ ሳንወድ በግድ ከ ማሪዬ Marie .A እና ከ ማሪያ Maria Therese ጎን ሌላ ያበሻ ሃይለ ማርዬ Marie ልንጨምር ግድ ይላል ማለት ነዉ- አጃኢብ ነዉ ። ለኛ ሐገርም ራሳቸዉን ለለዩ የመደብ ማርኪሲስት aristocrats መካከልና በቅዠት እሚኖረዉን የምንዱባን ህይዎት ባጠቃላይ ባያሳይልንም በከፊል ግን የሳቸዉ አባባል ያለዉን የመንግስትና የህዝብ ክፍተት ፍንትዉ አድርጎ ያሳያል – ልብ ያለዉ ልብ ይበል።
ብዙዉን ግዜ ያንድ ሐገር ጠቅላይ ሚንስትር ባገር ጉዳይ ስራ ላይ በሚሆንበት ግዜ የራሱ ያነጋገር ዘይቤዎች፣ የሚናገራቸዉ የሚጠቀማቸዉ ቃላትና አባባሎች ዕጅግ ጥንቃቔ ይደረግባቸዋል ፤ያም እሚሆነዉ የባለስልጣኑ አነጋገርና አካሔድም ሆነ አቀማመጥ ፕሮቶኮል የመላዉን ህዝብ እና ሐገር ስለሚወክል ነዉ ። ስለዚህ የራሱ የሆኑትን ልማዶችና ዕምነቶች በህዝብ ፊት ዎይንም በማንኛዉም የሚዲያ መገልገያ አዉታሮች ላይ ዕንዳይጠቀም የስራዉ ሃላፊነትና የስልጣኑ ደረጃ ባያስገድደዉም ፣ነገር ግን ብያንስ ግድ ይሏል። ይሔም ማለት በቀላል አገላለፅ ክብርንና ደረጃን ሐገርንና ህዝብን በሚመጥን መልኩ ማለት ነዉ፤ ፕሮቶኮል ጠባቂ ዎይንም ደምብ ጠባቂ ሹሙ ቢቻል ቀድሞ ይቀርፀዋል፤ ካልሆነም ቀድሞ ምክር ይሰጣል ። የዶሮ ወጥ ይዞ ስለመጉዋዝና ስለግርድና ስራ፣ ስለ ወገን ሰደተኝነት ማብጠልጠልና ተራ አነጋገርና ቃላትን መጠቀም ትርፉ ራስንና አገርን ማዋረድ ካልሆነ በቀር ሌላ የፖለቲካ ትርፍ አለዉ ቢባል ጅልነት ነዉ።
ለዛዉም ደግሞ ሲደተኞቹ የጦር ምርከኞች ሳይሆኑ ጥገኝነት ጠያቂዎች ሆነው የጀርመን መንግስትም ወስዶ ማስጎብኘቱ ሌላዉ ልብ ያላሉት እና ያልተዘጋጁበት ይመስላል ፤ ይህም ቢሆን ባዉሮፓ የስደተኞች አያያዝ ህግ መሰረት ለጀርመን መንግስትም ቢሆን የፖለቲካ ኪሳራ ነዉ ፤የታደጉዋቸዉን ሰደተኞች ለገዳያቸዉ ዎይ ደግሞ አሳዶ ላስወጣቸዉ መልሰዉ ካስጎበኙም የሚያሳዝን ነዉ። ይልቅ የዶሮ ወጡን ይዘዉ የመጡት ለዘመዶችዎ ከሆነ እና እዛዉ ጣቢያ ዉስጥ በስደተኛ ስም ለልዩ ስራ የተመደቡ ከሆነ ዕርግጥ ነዉ እነዚያ ሰዎች ምን ጎሎአቸዉ እና ምን አጥተዉ አንደሆነ እኛም አናውቅም እርሶንም ያ ከሆነ ያንገበገቦ ሚስኪኑን ትክክለኛ ስደተኛ ሳይደርቡ ለይተዉ ቢነግሩን ጥሩ ነበር።
በጀርመናዉያንም ጓደኞቻቸዉ ‘ኸይም’ heim (መጠለያ) ትርጉሙ ተነግሮአቸዉ’ እተዘጋጀ የስደተኞች ጣቢያ ተኪዶ ወገንን -ያንድ ሐገር ጠቅላይ ሚኒስትር ቆሞ ሲያሾፍና ሲዘባበት ያንን በህዝብ የመገናኛ ጣቢያ እንደ ትልቅ የፖለቲካ ትርፍ ወሰደዉ መደስኮሩ ፣ ፖለቲካ ሳይሆን ተራነትንና መደዴነትም ነዉ። ያገር ክብር የህዝብ ክብርን ከምንም በላይ ተምሳሌት ሆኖ እሚገለፀዉ በመሪዉ ነዉ ይሔን ክብር ነዉ ፈረንጆቹም DIGNITYዲግኒቲ እሚሉት ሐገር ህዝቡ ቢደኸይም በምንም ዓይነት ግን የራስ ክብርን dignityዲግኒቲ አሳልፎ አንድ ያገር ጠቅላይ ሚኒስትር እራሱንና ህዝቡን ባደባባይ አያዋርድም ። በጠቅላይ ሚኒስትሩ የክርስቲያን ሃይማኖት መፅሐፍ ቅዱስ ዉስጥም ሙሴ ያንን በባርነት ስር የነበረዉን ወገኑን አዝኖ አከበረው እንጂ አላዋረደዉም ፤ ክብር ለሰዉ በሰዉነቱ ፣ክብር ለህዝብ በማንነቱ፣ ክብር ለወገን በወገንነቱ ፣መስጠት ልማታዊ ባያረግም ነገር ግን ስልጡን ያረጋል ሙሉ ስብዕናንም ያላብሳል።
ጉብኝቱን የፈቀደልዎት የጀርመን መንግስት ዘመዶችዎ በመጠለያ ጣቢያዉ እንደነበሩ አሳዉቀዉ ከሆነ ፣ይኼም ቢሆን ለራስዎ የፖለቲካም ሆነ የሞራል ኪሳራ ሲሆን ለመላዉ ኢትዮጵያዊ ግን ዉርደት ነው። የጀርመን መንግስት ለርስዎ ጣቢያዉን ማስጎበኘቱም ባለም አቀፍ የስደተኞች አያያዝና የደህንነት ህግ አንቀፅ ጥሰት ሊያስጠይቀዉ እንደሚችል ሊያዉቁትም በተገባ ነበር ፤ ይሔንንም ባደባባይ ሲያወሩ ባዶ አማኝና ባዶ ፖለቲከኛ መሆንዎን ነው የሚያሳየዉ ።ለዚህም ነዉ የፕርቶኮል አስፈላጊነት በመሪ ደረጃ እንዲህ ያሉ ተቀጣጣይ የሆኑ አነጋገሮችን ቀድሞ እሚያርመዉ፤ ያለበለዚያ ራስንም አገርንም ተኩሶ እንደመምታት ነዉ ። ጠቅላይ ሚኒስትራችን የፊንላንድ finish ተማሪም ሆነዉ ኸይም heim ምን ማለት እንደሆነ አለማወቆን በሚድያ መናገርም በዉነት የፖሊቲካ አሽሙርም (political sarcasm) አለያም ደግሞ መሞዳሞድ( humor) ሊሆን አይችልም፤ ይልቅ ትዝብት ዉስጥ ነዉ የጣሎት።ጠቅላይ ሚኒስትራችን በፊኒሽ Finish ምድር የዉሃ ጥናት ትምህርቶን ሲወስዱ master ማስተር አድርገዉ የወጡት በዉሃ ላይ መንሳፈፍን ብቻ ይመስላል ለዚህም ነዉ በፖለቲካዉም ከሞራሉም አኳያ ራስዎን ሳይሆኑ እንደብርቅዬዋ የፊንላንድ ዳክዬ ተንሳፈዉ የሚታዩት the whooper swan ።
ለዚህ ርዕስ መነሻ የሆነን የሰሞኑ ትኩስ የመነጋገሪያ ኣጀንዳ የሆነዉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንጝግር ነዉ። ዋናዉ መልክታችን የሰዉየዉ የራሳቸዉን ህዝብ ማሳነሱና መዝለፉ ላይ ሳይሆን ሰዎቹ የተዘለፉበትን ምክንያቶች ላይ ትንሽ ለማለትና ምናልባትም ጠቅላይሚኒስትሩ ራሳቸዉንና ሰርዓታቸዉን ዞር ብለዉ ቢያዩበት ከሚል ነዉ።
ዛሬ በኢትዮጵያ ስለሚታየዉ የወጣት ሰቶች፣ ወጣት ዎንዶች ፣ የባለሙያ ምሁራን ስደት ዋናዉና ትልቁ ምክንያቱ የኢኮኖሚ ምኪንያት ሳይሆን ባገሪቱ ያለዉ የሰርዓት ኣልበኝነትና ስርአቱ ባመጣዉ የፖለቲካ ጫና ነዉ ።
ዛሬ ያለዉ የገዢዉ ሥርዓት በሰዉ ፍልሰት ንግድ በግልፅ በመሰማራቱና ባሰማራቸዉና ስርዓቱ በዘረጋዉ ዘመናዊ የሰዉ ንግድ ቀለበት ዉስጥ አንዲገቡ በተደረጉ ዜጎችና በተለይ ድግሞ ሆን ተብሎ በዘዴ የመሬት ንጥቂያና ዝርፊያዉ ባልተማሩና ምንም አይነት የስራ ሙያ ትምህርትና ልምድ በሌላቸዉ ሚስኪን የገበሬ ልጆች ከብቶቻቸዉን እና ያላቸዉን ጥሪት በዘዴ እንዲሸጡ እየተደረገ ገበሬዉን ያለዓምራች ሃይል እንዲሆን በማድረግና ያገሪቱን መሬት እና አንጡራ ሃብት ለዉጭ ባለሃብቶች አየተሰጠ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ዉስጥ ስዉም መሬቱም እኩል እየተሸጠ እንዲሰደድ በማስገደድና የመኖሪያ ቦታ በማሳጣትም ጭምር ነዉ።
እንዲሁም ዜጋዉን መሬት አልባና አገር አልባ በማድረግ ስደተኛ የሚል ተቀፅላ ስም ዎይንም መጠሪያ እንዲሸከም በመደረጉ ነዉ። ሰደተኛ በሚያደርገዉ የሥርዓቱ ዉጤት የዜጎች ስቃይና ያለፍላጎት የተሸከሙት ስደተኛ የሚለዉን ስም ነዉ ።
ዛሬ ያንድ ኢትዮጵያዊ የስደት ጉዞዉን እና አገር ለቆ የሚወጣበትን ሚክንያቶች በቅጡ ለተገነዘበ ሰዉ ኢትዮጵያዉያኖች ባገራቸዉ ያለዉን ከባድ ስራ ንቀዉ ሳይሆን ባገራቸዉ ያለዉን ከባድ የፖለቲካ ጫና፣ አፈና፣ ግድያ፣ እስር፣ የስራ ዕጦት፣ የምግብ ርሃብ፣ እና የነፃነት ርሃብና ፣ የቁም ቅዠት የሆነዉን የኑሮ ልዩነት ሽሽት የፍትሕ አለመኖር መሆኑ ግልፅና የማያከራክር ነዉ ።
እዚም በረንጆቹ አገር ዛሬ ያበሻን ስደተኛ በለበጣ ለተሻለ ሕይዎት ስደትን የሚመርጥ የስደት ገበያተኛ የሚል ቅፅል ስም አስከማዉጣት ተደርሶአል ፤በዚሁ አገር አባባል እንደወረደ አሲል ሾፐርስ asyl kjopers ፡ በንግሊዝኛዉ አሳይለም ሾፐር ASYLUM SHOPER ማለት ነዉ ። የዚን ወገን ህዝብ እመራለሁ የሚሉ ያገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሐይለማሪያም ደሳለኝ የዶሮ ዎጥ ይዘዉ መምጣታቸዉ ካዉሮፓ ዱቄት ሰፋሪዎች ጋር ሆነዉ የራስ ወገንን ችግር እያዩ ማላገጡ የሚያስከብር ሳይሆን ራስን እሚያዋርድና ራስንም መስደብ መሆኑን ልብ ሊሉት ይገባል ።ዱቔት ሲያቦኩ እና የሰዉ መኪና ተደግፈዉ ፎቶ እሚልኩ ያልዋቸዉ ወገኖች ናቸዉ በያረብ ሃገር ፣ባዉሮፓ፣ ባሜርካ ፣ኤሲያ ሌት ተቀን እየሰሩ ባገራችን ያለዉን የዘመናት ድህነት ለመቀንስና ቢያንስ የየራሱን ቤተሰብ በመደጎም ዙሪያ በዉጭ ያለዉ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ነዉ ትልቁን የለት ተዕለት ኑሮን በመሸፈን ላይ ያለዉ እንጂ መንግስት አደለም ዜጎቹን እየደጎመና እያኖረ ያለዉ ፣ መንግስት ይልቅ በተቃራኒዉ ህዝቡን ኣዋርዶ በያገሩ እየሔዱ ልመናን ስራዬ ብሎ ተያይዞታል ።
ባሁንዋ ኢትዮጵያ ዉስጥ መሬቱንና ልጁን በዘዴ ከተቀማዉ ያብዛኛዉ ማህበረሰብ ክፍል የሚገኘዉ ወጣት ስደተኛ ሴትም ሆነ ዎንድ በዓረብ ሐገራት ተበትኖ በግርድናም ይሁን በሞያ ስራ ላይ የተሰማራዉ ወገን ፡ በያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ቤተሰብና ማህረሰብ ከዛም አልፎ በዚያች አገር በተለይም የኢኮኖሚዉ ግንባታና የለት ተዕለት የህብረተሰቡ ኑሮ ዉስጥ ከፍተኛዉን ድጋፍና ተሳትፎ አያረገ ያለዉ ይኸዉ ባረብ ሐገራትና በሌላዉ ዓለም የተበተነዉ ሰደተኛ የተባለዉ ኢትዮጵያዊ ወገን ነዉ ።ይህ ደግሞ ሊያስመሰግነዉና ተበረታቶ ትክክለኛዉን የዜግነት ክብሩንና መብቱን ሊከበርለትና ዋስትና ሊኖረዉ ሲገባ ፤አሁን ያለዉ መንግስት በራስ ወገን ስቃይና ደም ፡ንግድ ዉስጥ ተገብቶ በራስ ዙሪያና ለራስ ብቻ እየተኖረ ወገንን ፡አገር አልባ አድርጎ የተበላሸ የዶሮ ወጥ ባዉሮፓና ባረብ አገር ይዞ መዞሩ ከሙቀቱ ወደ በረዶ – ከበረዶዉ ወደ ሙቀቱ ወጡን ይዘዉ ቢያጉዋጉዙ ትርፉ የዶሮ ወጡን ብቻ ሳይሆን ጠቅላይ ሚንስትራችንንም ሆነ ፖለቲካቸዉን እጅ እጅ እንዲሉ አድርጎዋቸዋል ።
ጠቅላይ ሚንስትሩ ስርዓታቸዉ ጠቅልሎ ባመጣዉ ችግር መልሰዉ ራሳቸዉ በራስ ወገን እና ዜጋ ላይ ማላገጥ አዋቂነት ሳይሆን ራስንና አገርን ማዋረድ ነው ። በጀርመን ሐገር የሚገኘዉን ‘ኸይም ‘ Heim መጠለያ ጣቢያ ሂደዉ፣ ዱቔት ሲፈጩ ባዩት ከማላገጥ የሰሩትን ዶሮ ወጥ በትኩሱ ባገር ቤት ጠርተው የበተኑትን ወገን ሊያበሉት ቢሞክሩ ምንኛ በመጠናቸዉ ፣ዶሮ ወጥ ሰርተዉ ባገሪቱ ጎዳና በየቦታዉ ለወደቁ ህፃናትና አረጋዊያን ቢያበሉ ምንኛ በመጠናቸዉ ፣የሰሩበትን ያመታት ጥሪት በገዛ አገራቸዉ በጉምሩክ ፈታሽና በግዜዉ ባለስልጣኖች የተዘረፉት ሴት እህቶቻችን በየመንገዱ ቀን ለቀን ባዶአቸዉን ግራ ገብቷቸዉ ያሉትን ፣እንደገና ዳግም ለመከራ ስደት መንገድ ላይ ያሉትን -በሰዉ ሐገር ያለዉን ከሚጎበኙ በገዛ አገሩ ሰደት ዉስጥ ያለዉን ቢጎበኙ ምንኛ መልካም ነበር።
እርግጥ ነዉ በዚ ልማታዊ መንግስት ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ የፈረንሳይ የታሸገ የመአድን የተጣራ ዉሃ french evian mineral water ገዝቶ የሚጠጣ ባለግዜ የደሃ ሃገር ቡርዥዋ እንዳለ ሁሉ ከቆሻሻ ገንዳ ከዉሻ ጋር እየተጋፋ በተራቡ እና በደከሙ ጣቶች የቁሻሻ ገንዳ ዉስጥ ሲቆፍሩ የሚዉሉም አሉ ፤ይኼንን ሃይማኖተኛዉና ፖለቲከኛዉ ጠቅላይ ሚንስትራችን ምናልባት ከየትኛዉ የስራ ዘርፍ ዉስጥ እንደመደቡት ባናውቅም ዛሬ ያ ሚስኪን ወገን ወስፋቱን መዝጊያ ለማግኘት ፡ከጠዋት እስከማታ ከተራቡ ዉሾች ጋር መከራዉን ሲቆፍረዉ እየኖረዉ ነው ፣ ጠቅላይ ሚንስትራችን ሰደተኛዉን ባገሪቱ ዉስጥ ያለዉን ከባድ ስራ ሸሸተዉ የወጡ ብለዉናል ፤ እንዴት አይሸሽ ከባዱስ ስራ የትኛዉ ይሆን?? ለጠቅላይ ሚንስትራችን ፣ ሰዉ ተሰልፎ በቁሙ ለጉርሻ ትርፍራፊ ምግብ ባደባባይ ሲሰለፍ ፣ ህፃናት በጎዳናና በመማሪያ ክፍል መሃል ከተማ ዉስጥ እየተራቡ ፣ ወገን በቁሙ በየበረሃው በቁሙ እየተበለተ፣ ወገን በየሃይቁ እንደሳርዲን ታጭቆ ፡ በመጨረሻም እንደ ጉማሬ ተነፍተዉ ዉሃ አንሳፎ እየተፋቸዉ በመላዉ ዓለም እየታየ፣ እንደዕባብ በሰዉ አገር እየተቀጠቀጡ ፣ እንደዓሳ በዘይት ፊታቸዉ እየተጠበሰ ፣ በጠራራ ፀሃይ መህል ከተማ ዉስጥ ወጣት ሴት ልጅ በግፍ ተድፍራ ስትገደል ሴቶች እንዴት ሸሽተዉ አይሰደዱ ?? ተነግሮ የማያልቀዉን መከራና ስቃይ ሲጋት እሚኖረዉ በዝቶ እያለ፣ጠቅላይ ሚንስትራችን ይሔን የማህበራዊና የኢኮኖሚ የፖለቲካ ቀዉስ ስደተኛዉ ላይ ደፍድፈዉ በራስ ጥጋብና ምርጫ ህዝቡ እንዳመጣዉ ተደርጎ መዘባበት ትናንት እንደተባለዉ ከርስዎ በፊት በነበሩት ጠቅላይ ሚንስትር ስለድርጀቶ የተነገረዉን መንቀዝና የፖለቲካ የመጨረሻዉ ብስባሴ ባንድ ዎቅት አሰምተዉን ነበር አሁን ማን ይንገረን ? ?
ከሞራልም አኳያ ቢሆን በየትኛዉም የዕምነት መፅሐፍ ቅዱስ ዉስጥ እንዲህ አይነቱን ስብዕናና ክፋት – በሀይማኖት የቅዱስ መፅሐፎቻቸዉ መገሠጭያውንም ማስተማሪያዉንም ከትበዉ ይዘዋል ፤ያን ላንባቢያን እንደምርጫቸዉ ስንተወዉ ለሞራልና ለግብረግብ እንዲሁም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የዕምነት አባቶች ግን የሳቸዉን አነጋገርና ትዕቢት ክፍተቱን ከሞራልና ከክርስትና አኳያ እንዴት እንደሚሞሉት በማስተዋል እንጠብቃለን ፣ሰማይ አይታረስ ንጉስ አይከሰስ ከሆነም ከነማብራሪያቸዉ እንጠብቃለን።
ጠቅላይ ሚኒስትራችን እንዴት እንደሚረዱትና እንደሚያዩት ባናውቅም ዛሬ ያለዉ ሃበሻ ኢትዮጵያዊ ባሜሪካም ሆነ ባዉሮፓ ያለዉ ሂስፓኒክ አደለም ፣ዛሬ ባረብ አገር ያለዉ ሃበሻ- ኢትዮጵያዊ ፡ ይሁዲ አዶለም ይሔንን እሳቸዉ ተምረዉ ባደጉበት የፖለቲካም ሆነ የሃይማኖት ትምህርት የህዝብ የራስ ወገንን ክፍተኛ ፍልሰት exodus ለያይተዉ ማየት አለመቻላቸዉ ምናልባትም ያገዛዙ ዋና ኤሊትሶች ፈረንጆቹ horse hood ሆርሰ ሁድ የሚሉትን ለሳቸዉም ባንገታቸዉ አጥልቀዉላቸዉ ይሆን ? እንዲህ ግራ ቀኙን እንዳያዩ አድርገዉ እሚጋልቧቸዉ? ፣እጅ- እጅ ብሎ እጅ- እጅ ካለ የዶሮ ዎጥ ጋር ዝም ብሎ መጋለብ ፣ አሳፋሪም አስነዋሪም ነዉ።
ተፃፈ – ስለ- ክብር፤ ለመላዉ ስደተኛ ኢትዮጵያዊ ሁሉ እንዲሁም በህይዎት ለሌሉ እና ባገራቸዉም ካገራቸዉ ዉጭ በግፍ ላለቁ ሁሉ።
በድሬዳዋ አየር ሃይል ውጥረት የበዛበት ግምገማ ተካሄደ
ታኀሳስ ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አራት ከፍተኛ ማእረግ ያላቸው የአየር ሃይል አብራሪዎች መጥፋታቸውን ተከትሎ በድሬዳዋ የአየር ሃይል ምድብ ሲካሄድ የነበረው የ3 ቀናት ግምገማ ሃሙስ እለት ተጠናቋል። በግምገማው ላይ አብራሪዎች፣ አሰልጣኞች፣ ቴክኒሻኖችና ሰራተኞች የተገኙ ሲሆን፣ ሰራተኞቹ ስለጠፉት አብሪዎች የተሰማቸውን ስሜት እንዲናገሩ፣ የሚያውቁትን ሚስጢር እንዲያወጡ ሲገደዱ ሰንብተዋል። ብዙዎች ” ስለጠፉት አብራሪዎች ምን ትላላለችሁ?’ እየተባሉ …
ምእራባዊያን ኢህአዴግን ከተቃዋሚዎች ጋር ለማቀራረብ ላይ ታች እያሉ ነው
ታኀሳስ ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው ችግር እየከፋ መሄዱ ለህዝባዊ አመጽ በር ሊከፍት ይችላል የሚል ስጋት ያደረባቸው ምእራባዊያን በአሜሪካ ፊት አውራሪነት በአገር ውስጥና በውጭ ያሉትን ተቃዋሚዎች ከኢህአዴግ ጋር ለማቀራረብ እየተሯሯጡ መሆኑን የዲፕሎማቲክ ምንጮች ገለጹ። እንደምንጮች ገለጻ በአገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ከሚታገሉት ድርጅቶች ውስጥ አንዳንዶችን በማካተት፣ በውጭ ከሚገኙ ገዢውን መንግስት በሃይል …
ደርግ ከ 26 ኣመት በፊት በትግራይ-በሀውዜን ላይ በፈጸመው ጭፍጨፋ የእስራ ዔል እጅ አለበት ሲሉ የህወሀት መስራች የሆኑት አቶ ስብሀት ነጋ ተናገሩ።
ታኀሳስ ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰንደቅ ጋዜጣ እንደዘገበው፣የቀድሞው የህወሀት ሊቀመንበር አቶ ስብሀት ነጋ ይህን ያሉት የህወሀትን 40ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ሰሞኑን ወደ ትግራይ ለተንቀሳቅቀሱት ጎብኝዎች የደርግ 604ኛ ኮር የተደመሰሰበትን ወታደራዊ ሳይንስ አስመልክቶ በሽሬ ከተማ በተሰናዳ መድረክ ላይ ባደረጉት ገለጻ ነው። “የቀዝቃዘውን ጦርነት ማክተም ተክትሎ ታላቋ ሶቪየት ህብረት መፈራረስ ጀመረች ያሉት አቶ ስብሀት፤ክስተቱን …
የተቃዋሚ መሪዎች ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጠባቸው
ታኀሳስ ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የተከሰሱት 6 የተቃዋሚ ድርጅቶች አመራሮችና ሌሎች ዜጎች በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ 19ኛው ወንጀል ምድብ ችሎት ሁለት ተለዋጭ ቀጠሮ እንደሰጠባቸው ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰማያዊ፣ የአንድነትና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች የሆኑት አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና አቶ …
በሜሮን ጌትነት ግጥም የተናደደው ሆድ አደር የህውሃት ካድሬ ያለቀሰው ለቅሶ
ፍ/ቤቱ በተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች ላይ ሁለት ተለዋጭ ቀጠሮዎችን ሰጠ
ለጥር 7 እና ለጥር 26/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቷል በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮችን ጨምሮ 10ሩም ተከሳሾች በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ 19ኛው ወንጀል ምድብ ችሎት ሁለት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠባቸው፡፡ ዛሬ ታህሳስ 24 ቀን 2007 ዓ.ም ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰማያዊ፣ የአንድነትና የአረና […]
ሰማያዊ ፓርቲ ከተመሰረተ ሦስተኛ ዓመቱ ነው፣ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች እንኳን አደረሰን !
ከምንም በላይ ግን ያኔ ከመነሻው ለአገር እና ለህዝብ የሚጠቅም ፓርቲ እንመስርት ብለን፣ገንዘባችን፣ ጊዜያችን፣ እውቀታችን ሳንሰስት በመስጠት፤በወቅቱ ፓርቲ እንመስርት ማለታችን ትክክል እንደነበር የዛሬ ውጤታችን ምስክር ነው !
—————————- YIDNEKACHEW KEBEDE ——————————————
ሰማያዊ ፓርቲ ከተመሰረተ አሁን ሦስተኛ ዓመቱ ነው፣የአገራችን አሉታዊ እና አዎንታዊ ፖሊቲካ ድርጊቶችና ክስተቶችን በመመርመር የመፍትሔ አካል ለመሆን በአገር ወዳድ ኢትየጵያዊያን ታህሳስ 22/2004 ዓ.ም በይፋ ተመሰረተ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በእውነት እና በእውቀት ላይ የተመሠረተ ሰላማዊ ትግል በማድረግ ፣የዜጎች የሥልጣን ባለቤትነት ለማረጋገጥ አባላቱ እና ደጋፊዎችሁ እያሣየነው ያለው ቁርጠኝነት እና ታማኝነት ለፓርቲያችን ጥንካሪ ዋንኛ መሠረት ነው፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ ከምስረታው ጀምሮ ያስመዘገባቸው አኩሪ ድሎች፣ በአገራችን እየተንቀሳቀሱ ከሚገኙ ቁጥራቸው ከበዛ ፓርቲዎች ተርታ፣ በግንባር ቀደምትነት ከሚጠሩ አንዱ ለመሆነ ችሎአል፡፡ፓርቲያችን ከተመሠተር እና ወደ እንቅስቃሴ ከገባ አጭር ጊዜ ቢሆነውም ፣በኢትዮጵያዊያን ካለው ተቀባይነት እና በገዥው መንግስት ላይ እያሣደረ ያለው አስጨናቂ ተፅኖ በመመልከት አንዳንድ ታዛቢዎች ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ ? በማለት ይጠይቃሉ፣ መልሱ ግን አጭር ነው፡፡ እሱም ጠንከራ ጓዳዊ ትስስር ፣ጥልቅ የሆነ የአገር ፍቅር ስሜት፣ለዓላማ መሞት፣ በእውቀት እና በእውነት ላይ የተመሰረት ሰላማዊ ትግል ተግባሪዊ ማድረግ ፣ለፓርቲያችን ውጤት የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል፡፡
ይህ ማለት ግን ፓርቲያችን ሊደርስበት ካሰበው ደረጃ እጅግ በጣም ትንሽ መሆኑ ሁላችንም የምንረዳው ሃቅ ነው፡፡ የሁላችንም የጋራ ዓላማ፣ ህዝብ የአገሩና የሥልጣን ባለቤትነቱ እንዲረጋገጥ ማድረገግ ነው ! ይህን ለማሳካት አሁን ላይ ፓርቲያችን ያስመዘገበው ድል የዋናው ትግላችን ውጤት ማሣያ መለኪያ እንጂ ፍፃሜ አይደለም፡፡ እርግጥ ነው ከትግሉ ጅምሮ አንስቶ የጠልፎ መጣል የተለመደው አዙሪት ፓለቲካ፣ ፓርቲያችን ፈተና ውስጥ የከተተው ቢሆንም በአመራሩ ጠንካራ ውሳኔ ከገጠመው ፈተና በብቃት ለመወጣት የተቻለው ሲሆን፣ወደፊትም እንዲኸ ዓይነቱ ክስተት እንዴት መወጣት እንዳለበት ት/ት ያገኘበትም መልካም አጋጣሚ ጭምር ነው፡፡
ፓርቲያችን ከሌሎች በአገር ውስጥ ከሚንቀሣቀሱ የዲሞክራሲ ኃይሎች ጋር በመተባበር መጪው አገር አቀፍ ምርጫ 2007፣ ፍታሓዊ እና ዲሞክራሳዊ እንዲሆን ጠንክሮ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን፣በ2005 ዓ.ም ሊካሄድ ታስቦ የነበረ የአካባቢ ምርጫ፣ ገዥው መንግስት በቻውን ተወዳድሮ ብቻውን ያሸነፈበት የይስሙላ ምርጫ መሆኑን የ33 ፓርቲዎች ጠንካራ ትብብር ያስገኘው ውጤት ነው ! የዚህም ውጤት ባለቤት ከሆኑ ፓርቲዎች ውስጥ ሰማያዊ ከዋናዎቹ አንዱ ነው፡፡አሁንም ወደፊትም ለአገር እና ለህዝብ ጥቅም ሲባል ፓርቲያችን በጥናት ላይ የተደገፈ ከእውነተኛ የዲሞክራሲ ኃይሎች ጋር የሚያደርጋቸው ማናቸውም ዓይነት ግንኙነት በፓርቲያችን ደንብ መሠረት ገደብ የተጣለበት አይደለም፡፡
ገዥው መንግስት የፓርቲያችንን ጥንካሪ በአግባቡ በመረዳት፣በምናደርጋቸው ሰላማዊ ትግል ምክንያት በመፍጠር በተደጋጋሚ ከሚወስዳቸው የእስራት እና ደብዳባ እርምጃ ባለፈ ፓርቲያችንን ለማፍረስ በግልፅ እና በስውር እየተነቀሣቀሰ ይገኛል፡፡ከዚህም በላይ የፓርቲያችን ሰላማዊ ተጋይ አቶ የሺዋስ አሰፋ ከአ/አ፣ አቶ በፍቃዱ አበበ ከአርባምንጭ እና አቶ አግባው ሰጠኝ ከሰሜን ጎንደር በሽብርተኝነት ከሱ እያሰቃያቸው ይገኛሉ፡፡ይሁን እንጂ የጀመረነው ሰላማዊ ትግል ከዚህም በላይ ዋጋ እንደሚያስከፍል ቀድመን የተረዳነው ስለሆነ ወደፊት እንጂ ወደ-ኋላ ማለት በእኛ ዘንድ ነውር መሆኑ ጠንቅቀን እናውቃለን !
ፓርቲያችን ባሣለፈው ሦስት ዓመታ ውስጥ የገጠመው ውስጣዊ እና ውጫዊ ችግሮች ማንኛወም ጠንካራ ፓርቲ ሊገጥመው ከሚችለው የተለይ ነገር አይደለም ፡፡ሆኖም ግን ያጋጠሙት ችግሮች ለመፍታት የተሄደበት መንግድ ማንኛውም ፓርቲ እና የፓርቲ አባላት ከሚሄዱበት በአንፃራዊ እጅግ በጣም የተሻለ ነበር ፡፡አሁንም ወደፊትም ችግሮች መኖራቸው የማይቀር መሆኑ ታሣቢ በማድረግ፣ የፓርቲው አባል የሆን ጥልቅና ዝርዝር ውይይት በግልፅ በማካሄድ ክፍተቶቻችን እንደምንሞላ ተስፋ አድርጋለው፡፡
ከምንም በላይ ግን ያኔ ገና ከመነሻው ለአገር እና ለህዝብ የሚጠቅም ፓርቲ እንመስርት ብለን፣ገንዘባችን፣ ጊዜያችን፣ እውቀታችን ሳንሰስት በመስጠት፤በወቅቱ ፓርቲ እንመስርት ማለታችን ትክክል እንደነበር የዛሬ ውጤታችን ምስክር ነው !ለዚህም በመብቃታችን መስራች አባላት ለሆን እንኳን ደስ አለን፣አላችሁ! ለማለት እወዳለው፡፡
የጀመራችሁት አገር የማዳን ትግል የእናተ የመስራቾች ብቻ ሳይሆን የእኛም ጭምር ነው !በማለት ከፓርቲው ምስረታ ጀምሮ እስካሁን ሰማያዊን በመቀላቀል በአመራርነት እና በአባልነት በማገልገል ፣አኩሪ የትግል መሰዋትነት እየከፈላችሁ ለምትገኙ ለገዥው ለወያኔ መንግስት የእግር እሳት ለሆናችሁ የእኔ ትውልድ ጓዶች እንኳን አደረሳችሁ !
ፓርቲያችን አሁን ላይ ያለበት ደረጃ እንዲደርስ በአሳብ እና በገንዘብ እየረዳችሁ ለምትገኙ በአገር ውስጥ እና በውጪ የምትገኙ ድጋፍ ሰጪዎቻችን ፣ድካማችሁ ፍሬ እያፈረ በመሆኑ የሚሰማችሁ ደስታ ለተጫማሪ ድጋፍ እንደሚነሳሳችሁ ተስፋዬ የበዛ ነው !ከምንም በላይ ግን ሁሌም ለማይለይን የሃሳብ እና የገንዘብ ድጋፋችሁ አገራዊ ግዴታችሁ ቢሆንም፣ በቀናነት እና በአገር ወዳድነት ለምታደርጉት ድጋፍ ምስጋና ተገቢ ነው፡፡ምስጋናውን ከአክብሮት ጋር እንድትቀበሉ በመጠየቅ ፣ለዚህ በመብቃታችን እንኳን አደረስን በማላት የ3ኛ ዓመት የእንኳን አደረስን የግል መልእክቴን በዚህ አጠቃልላለው፡፡
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !
ሁለት ሰዎችን አብነት አካባቢ የገደለው ወጣት በ20 ዓመት እስራት ተቀጣ Man who killed two people around Abinet hotel sentenced to 20 years in pirson
በቂም በቀል ተነሳስቶና ስለት ታግዞ በሁለት ሰዎች ላይ ከባድ…
ምክር እስከመቃብር – (ከኣልፎ ሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ) – በእውቀቱ ሥዩም
የቤት ኣከራየ የጋሽ ጣሰው ኣገር እየመጣሁ ነው፡፡ ወደ ኣዲስ ኣበባ እየመጣሁ ነው፡፡እናቶች ኣባቶች ልጆች ኦርጅናሎች ሰልቫጆች! እኔ ሳልመጣ ውጊያውን እንዳትጀምሩት ኣደራ፡፡ ኣጭርና ጣፋጭ ይሁን እንጂ በማንኛውም ትግል ላይ ለመሳተፍ ዝገጁ ነኝ፡፡የጥይት መከላከያ ቆብ ሹራብና ሱሪ እንዲሁም ፈንጅ የማይበትነው ጫማ ከተሰጠኝ ኣንድ ሻለቃ እመራለሁ፡፡ኣነሰ ከተባለ ኣንዲት ኮረብታ እቆጣጠራለሁ፡፡ በጦር ምህንድስና ላይ እሳተፋለሁ፡፡ ባሩድ ኣገነፋለሁ፡፡ የታንክ ጎማ እነፋለሁ፡፡በሰላሙ ቀን ለሞባይል፤ በቀውጢው ቀን ለሽጉጥ ማስቀመጫ የሚሆን ሰገባ እሰፋለሁ፡፡
‹‹እንደ ኢህአዴግ ያለ አሸባሪ የለም›› አብርሃ ደስታ (ከቂሊንጦ እስር ቤት)
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር ‹‹እንደ ኢህአዴግ ያለ አሸባሪ የለም›› አብርሃ ደስታ (ከቂሊንጦ እስር ቤት) “እዚህ እስር ቤት ውስጥ በሽብር ስም የገባ ሰው በፈጠራ ወንጀል እንደገባ ነው የሚታመነው፡፡ ስለዚህ የሽበር ክስ ተመስርቶባቸው የታሰሩትን ሰዎች ማንም ወንጀለኛ አድርጎ አይመለከታቸውም፡፡ በእርግጥም አሸባሪ የለም፤ የፈጠራ ክስ ነው ያሳሰራቸው፡፡ አሸባሪ አለ ከተባለም እንደ ኢህአዴግ ያለ አሸባሪ የለም፡፡ ነጻ መውጣት ያለበት ቡድን […]
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ጃንዩወሪ 01, 2015
የፕሮግራም መግለጫ
ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡
የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡
ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና
ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና
ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ
ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት
ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)
ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና
ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡
ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡
የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡
ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡
የ2015 አቀባበል በዓልና መልዕክቱ
2014ን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ፓን ጊ ሙን የተስፋ አድማስ የጨለመበት ነበር ያሉት-ባለፈዉ መስከረም።
2014 እና የሁለት ሙዚቀኞች ዕረፍት
ሁለቱ አንጋፋ ሙዚቀኞች ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸዉ ከተሰማ በኋላ በአዉሮጳ በተለይም በጀርመን ሙዚቃዎቻቸዉ በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃኖች ከፍ ብለዉ መሰማት ጀምረዋል፤ በተወዳጅ ሙዚቃ መጠይቅ መዘርዝርም የአንደኝነቱን ቦታ ይዘዋል። ኦስትርያዊዉ ሙዚቀኛ ኡዶ ዮርገንስና፤ ብሪታንያዊዉ ሙዚቀኛ ጆ ኮከር!
“በሐውዜን ድብደባ፤ የእሥራኤል እጅ አለበት” አቦይ ስብሃት ነጋ

ከ26 ዓመታት በፊት የደርግ መንግሥት በትግራይ ክልል በሐውዜን ሕዝብ ላይ ያካሄደው የአውሮፕላን ድብደባ በስተጀርባ የእሥራኤል መንግሥት እጅ እንዳለበት የቀድሞ የህወሓት ሊቀመንበር አቶ ስብሃት ነጋ ይፋ አደረጉ።
አቶ ስብሃት ይህን የገለፁት በሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ የደርግ 604 ኮር የተደመሰሰበትን የወታደራዊ ሳይንስ ጥበብ አስመልክቶ ሰሞኑን በሽሬ ከተማ በተሰናዳ የውይይት መድረክ ላይ ነው።
አቦይ ስብሃት ሲያስረዱ፣ “የቀዝቃዛው ጦርነት ማክተምን ተከትሎ ታላቋ ሶቪየት ሕብረት መፈራረስ ጀመረች። ይህን ክስተት ተከትሎ ሶቪየት ሕብረት ከኢትዮጵያ እየወጣች መጣች። በእሷ እግር የተተካውም የሩሲያ ፌዴሬሽን ለደርግ አገዛዝ ከዚህ በፊት ይደረግ የነበረውን ወታደራዊ እርዳታ አቋረጠ። ይህን ዓለም ዓቀፍ የፖለቲካ ዳይናሚዝም ተከትሎ አሜሪካ መራሹ የምዕራብ ዓለም እና የእሥራኤል መንግስት ከደርግ ጋር ወዳጅ ሆኑ። የደርግ አገዛዝን መውደቅን ተከትሎ ሊፈጠር የሚችለውን የጂኦ-ፖለቲካል ኃይል አሰላለፍ በመፍራት የምዕራቡ ዓለምና እሥራኤል ደርግን ወዳጅ አድርገው በእኛ የትግል እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ እርምጃዎች መውሰድ ጀመሩ” ብለዋል።
አያይዘውም፣ “በወቅቱ ሕወሓት ወታደራዊና ፖለቲካዊ አቅሙ እየጠነከረ እየመጣ በመሆኑ አሜሪካና እሥራኤል ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ገብተዋል። የአዲስ አበባው መንግስት ወዳጅ ስለሆኑ እንዴት ከተጀመረው የትጥቅ ትግል ሊያድኑት እንደሚችሉ ብዙ መንገዶችን ሞክረዋል። በጊዜው ደርግን ለማትረፍ ያልሞከረ የምዕራብ ሀገር አልነበረም። ሁሉም የሚችለውን አድርጓል። አሜሪካ ለማደራደር ስትሞክር እሥራኤል ግን የተለየ ሚና ወሰደች” ሲሉ ወንጅለዋል።
“አሜሪካ አንዴ ወደ ሮማ ሌላ ጊዜ ወደ ለንደን እንድንመጣ ጠራችን። ሮማ ላይ ጂሚ ካርተር አስጠርቶን የነበረ ቢሆንም፣ የደርግ ልዑካን ቡድን እናንተ ስለኢትዮጵያ ምን ያገባችኋል አሉን። ወደ ለንደን ተጠርተን ስንሄድ ግን ሁሉን ነገር ስለጨረስን ደርግን ጥለን ነበር” ብለዋል።
እስራኤል ግን ወደ ሮማ ከመሄዳችን በፊት፣ ደርግን በጦር መሳሪያ በማስታጠቅ ጀምራለች። ደርግ የታጠቀውን የክላስተር ቦምብ እ.ኤ.አ ጁን 22 ቀን 1988 ሐውዜን በገበያ ቀን ህዝቡ ላይ አዘነበው። በጥቃቱም ከ2ሺ 500 በላይ ህዝብ ማለቁን ተናግረዋል። አያይዘውም፤ “ይህ ሁሉ የህዝብ ዕልቂት በእሥራኤል አስታጣቂነት የተፈጸመ ነበር” ሲሉ አቦይ ስብሃት ለተሰብሳቢው በሃዘን ተውጠው አስረድተዋል።
የቀድሞ የደርግ መንግሥት ርዕሰ ብሔር የነበሩት ኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማሪያም ወደ ዙምባቡዌ የሸሹት በምዕራብ ሀገሮች ድጋፍ መሆኑ ሲነገር ነበር። ኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማሪያም በኢትዮጵያ ፍርድ ቤት በዘር ማጥፋት ወንጀል የሞት ፍርድ ቢተላለፍባቸውም አንዳቸውም የምዕራቡ ሀገራት የዙምባቡዌ መንግስት አሳልፎ እንዲሰጥ ግፊት አድርገው አያውቁም።
በ ፋኑኤል ክንፉ – www.sendeknewspaper.com
ገዥው ፓርቲ ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ የህዝቡን ሰላም ለማደፍረስ ስለሚያደርገው እንቅስቃሴ›› መረጃ ስጡኝ በሚል ለህዝቡ ቅጽ እያደለ ነው

የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለይም ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹በሰላማዊ ሰልፍ ስም የህብረተሰቡን ሰላም ለማደፍረስ እያደረገ የሚገኘውን እንቅስቃሴ በተመለከተ›› መረጃ እንዲሰጡት ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቅጽ እያከፋፈለ መሆኑ ታወቀ፡፡
ምንም እንኳ በቅጹ ላይ ዜጎች ስለ ሰማያዊ ‹‹ጥሩና መጥፎ›› አስተያየት እንዲሰጡ ቢልም መጀመሪያ ላይ ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ በሰላማዊ ሰልፍ ስም የህብረተሰቡን ሰላም ለማደፍረስ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ በተመለከተ›› ሲል ፓርቲው የህዝብን ሰላም እያደፈረሰ ነው ሲል ፈርጆታል፡፡
ቅጹ ከተሰጣቸው መካከልም አንድ የኮልፌ ቀራኒዮ ነዋሪ ቅጹን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቀው ሲል ለኢትዮ ምህዳር የላከ ሲሆን ‹‹ይህንን አስገራሚ ቅጽ እንድንሞላ በአንድ ክ/ከተማ በተገኘንበት ስብሰባ ላይ ለተሰብሳቢው ሁሉ ታደለ፡፡ ታዲያ ሁሉም ቅጹን ወስዶ ወደ ቤቱ ሄደ፡፡ እኔም የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቀው ለጋዜጣችሁ ዝግጅት ክፍል ልኬዋለሁ፡፡ አይገርምም ሕገ-መንግስት የሚፈቅደው ሰላማዊ ሰልፍ አንቀጽ በመንግስት አስፈጻሚዎች ሲጣስ›› በሚል አስተያየታቸውን አስፍረዋል፡፡
ነባር ተመዝጋቢዎች በቅርቡ ይተላለፋሉ በተባሉ ኮንዶሚኒየም ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ተደናግጠዋል Condominium registrants shocked by the new draw guidelines
ተጻፈ በ ታምሩ ጽጌ
‹‹በተከታታይ ስድስት ወራት ያልቆጠቡና ቆጥበው ያቆሙ…
ኢንጅነር ግዛቸው የአመቱ ምርጥ ሰው ተብለው ተመረጡ
መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው ኢትዮጵያን ሪቪው የተባለው ድረገፅ ኢንጅነር ግዛቸውን የአመቱ ምርጥ ሰው ብሎ መረጣቸው፡፡ ድረገፁ በየአመቱ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ተፅእኖ ያሳረፉ ፖለቲከኞችን የሚመርጥ ሲሆን በተጠናቀቀው የፈረንጆች አመት ላይ ኢንጅነር ግዛቸውን የአመቱ ምርጥ ሰው ብሎ መርጧቸዋል፡፡ ምርጫው የራሱ መስፈርቶች ያሉት ሲሆን በዋናነት ኢትዮጵያን ለማሻሻል ለተጉ እና ለነፃነት በሚደረገው ትግል አስተዋፅኦ ላበረከቱ ሰዎች ከግምት ያስገባ መሆኑን ድረገፁ […]
አርማጮ በአማራ ንቅናቄ ሰራዊት እና በወያኔ ሰራዊት በውጊያ ተወጥራለች::
አርማጮ በአማራ ንቅናቄ ሰራዊት እና በወያኔ ሰራዊት በውጊያ ተወጥራለች::
Minilik Salsawi : በአርማጮ አከባቢ በአማራ ንቅናቄ ሰራዊት እና በወያኔ ሰራዊት መካከል ከባድ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን የንቅናቄው ምንጮች ከአከባቢው አስታወቁ::የህዝቡ ተሳትፎ በከፍተኛ ደረጃ እየታየ ባለበት እና ህዝቡ እና የንቅናቄው ወታደሮች በመቀናጀት ዱር ቤቴ ብለው ወደ ጫካ መግባታቸው ሲታወቅ በመተማ ሸዲ አከባቢ በትላንትናው እለት በወያኔው ጦር ላይ ጥቃት አድርሶ ወደቦታው የተመለሰው የአማራ ንቅናቄ ሰራዊት ከሕዝቡ ጋር በመተባበር እጅግ በርካታ የጦር መሳሪያዎችን እንደማረከ ምንጮቹ ተናግረዋል::
ካለፈው አርብ ጀምሮ የተነሳው ውጊያ በአሁን ወቅት ቀጥሎ ያለ ሲሆን በዛሬው ለሊት ከፍተኛ የቶክስ እሩምታዎች እና የከባድ መሳሪያ ድምጾች በአከባቢው እየተሰሙ መሆኑ ታውቋል::በአብድራፊ አብሃጂራ ሶረቃ ግጨው ማርዘነብ ማይጸማር ሃሙስ ገበያ ዳንሻ ማይካድራ እና አከባቢው ጦርነቱ ይስፋፋባቸዋል የሚል ከፍተኛ ስጋት ስላደረ በአከባቢው የወያኔ ሰራዊቶች በብዛት መስፈራቸው ሲታወቅ አዳዲስ ታንኮችን የጫኑ ከባባድ መኪኖች በቦታው ደርሰዋል:: እንዲሁን ወደ ሱዳን ክልል ዘልቀው የገቡ እና ከሱዳን ወታደሮች ጋር አሰሳ የሚያደርጉ ወያኔዎችን እንዳጠቁ የአማራው ንቅናቄ ወታደሮች ተናግረዋል::
በአርማጮ እና አከባቢው የተከሰተውን ግጭት በተመለከተ የአማራ ንቅናቄ ሰራዊት መግለጫ ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል::
4 የኢትዮጵያ አየር ሀይል ከፍተኛ መኮንኖች አምልጠው ኬንያ ገቡ
http://www.mereja.com/video/watch.php?vid=311c44a25
በደብረማርቆስ ከተማ ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል! – ፍኖተ-ነፃነት
በርካታ ወጣቶች በፌደራል ፖሊስና በደህነት ሀይሎች በመታሰር ላይ ይገኛሉ! በደብረማርቆስ ስልጠና ላይ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃና የመሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በመንግስት ላይ ጥያቄ ማንሳታቸውን ተከትሎ እየታሰሩ እንደሚገኙ የፍኖተ-ነፃነት ምንጮች አስታወቁ፡፡ ተማሪዎቹ በመንግስት በኩል የሚሰጠውን ስልጠና ማውገዛቸውን እና በመንግስት በኩልም ቤተሰቦቻቸው ኢህአዴግን እንዲመርጡ እንዲያግባቡ መደረጋቸውን የገለፁት ምንጮች ተማሪዎቹ ይህን በመቃወም የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት ላይ የነበሩ ቢሆንም በፖሊስ […]
በጋምቤላ ክልል ተፈጥሮ በነበረው ግጭት 79 ሰዎች መገላቸውን መንግስት ገለጸ
ታኀሳስ ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት በጋምቤላ ክልል በጎደሬ ወረዳ ከመጋቢት እስከ ጳጉሜ በነበሩት ግጭቶች የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከ12 አይበልጥም በማለት በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቢቆይም፣ አቃቢ ህግ የክልሉን ባለስልጣናት ለመክሰስ ባቀረበው የክስ ቻርጅ ላይ 79 ሰዎች መገደላቸውን ፣ 273 ቤቶች መቃጠላቸውን ከ13 ሺ በላይ ዜጎች እንዲፈናቀሉ ማድረጋቸውን ገልጿል። አንዳንድ ወገኖች የተገደሉት ሰዎች …
የእስቴ መምህራን ተቃውሞ አሰሙ
ታኀሳስ ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ጎንደር እስቴ ወረዳ የሚገኙ መምህራን ለ3 ቀናት የሚቆይ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ስብሰባ እንዲካፈሉ ቢጠሩም፣ መምህራኑ በስብሰባው ላይ ከተገኙ በሁዋላ፣ በአንድ ድምጽ ስብሰባ ኣንሳተፍም በማለት ጥለው ወጥተዋል። መምህራኑ መንገድ የመሳሰሉ የመሰረተ-ልማቶች አልተሟሉም፣ ለመምህራን በቂ የሆነ ክፍያ አይሰጥም በማለት ተደጋጋሚ ቅሬታ ሲያቀርቡ ቆይተዋል። በዚህ ሁኔታ ውስጥ የተጠራው ስብሰባ …
በሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ ኅልፈት ‹‹ሐዘኑ የቤተ ክርስቲያን ነው›› /ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ/
‹‹…ወንድማችንን እናውቃቸዋለን፤ በእውነቱ ለፌ ወለፌ የማይሉ ደረቅ ሊቅ ናቸው፤ በሃይማኖቱ ዘርፍ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን፣ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንዲቱም ነጥብ እንዳትዛባ ከወንድሞቻቸው ጋራ ብዙ ትግል ያደረጉ አለኝታ ሊቅ ነበሩ፤ እርሳቸውን ማጣታችን ትልቅ ጉዳት ነው፤ ሐዘኑ የልጆቻቸውም አይደለም፤ ሐዘንተኛዋ ቤተ ክርስቲያን ናት፤ እግዚአብሔር ለዚኽች እናት ቤተ ክርስቲያን እርሳቸውን የመሰለ ይተካልን ከማለት በቀር ምንም ማድረግ አንችልም፡፡›› ከዘመናችን የቤተ …![]()
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ዲሴምበር 31, 2014
የፕሮግራም መግለጫ
ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡
የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡
ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና
ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና
ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ
ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት
ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)
ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና
ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡
ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡
የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡
ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡
የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መሰደድና «ሲ ፒ ጄይ»
ባለፉት ዓመታት ከኢትዮጵያ የሚሰደደዉ ጋዜጠኛ ቁጥር በእጥፍ መጨመሩን የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት «CPJ» ገለፀ። እንደ ድርጅቱ ዘገባ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት የጀመረዉን የእስራት ዘመቻ በመፍራት ባለፉት 12 ወራቶች ብቻ ከኢትዮጵያ ከሰላሳ በላይ ጋዜጠኞች ተሰደዋል።
ጋሊፖሊ-900 ስደተኞቹ ከሞት ለጥቂት ዳኑ
የኢጣሊያ የባሕር ጠረፍ ጠባቂ ጦር ቃል አቀባይ ፊሊፖ ማሪኒ እንደሚሉት ባልደረቦቻቸዉ ባይደርሱ ኖሮ ዓለም በሌላ የባሕር ላይ ጥፋት ባዘነ ነበር።አብዛኞቹ ስደተኞች የሶሪያ ዜጎች ናቸዉ።
የኢትዮጵያ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሳዑዲ አረቢያ ጉብኝት
የመልዕክተኞቹ ቡድን ሳዑዲ አረቢያ ከሚኖሩ ከተመረጡና የተወሰኑ ኢትዮጵያዉን ጋር መነጋገሩም ተሰምቷል።
የሳዑዲ አረቢያ ቀጣሪዎች ወይም አሰሪዎች ችግር ያደርሱብናል የሚሉ አብዛኛዎቹን ኢትዮጵያዉያንን ግን አላነጋገረም።
የግሪክ አፋጣኝ የምርጫ ዝግጅት
የአዉሮጳ የቀዉስ እንብርት በምትባለዉ ግሪክ ከመደበኛዉ የምርጫ ጊዜ ቀደም ብሎ በሚቀጥለዉ የጥር ወር አጋማሽ ላይ ጠቅላላ ምርጫ እንደሚደረግ ተነግሯል።
ምርጫ ቦርድ የገንዘብ ክፍፍል ቅምርን እንደገና እንደሚመለከተው አሳወቀ
ምርጫ ቦርድ ዛሬ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ባደረገው ስብሰባ ለምርጫው የገንዘብ ክፍፍል ቀመር መሰረት ዉይይት አድርጓል። ምርጫ ቦርድ ባቀረበው የገንዘብ ክፍፍል ቀመር መሰረት 10 በመቶ ለሴቶች፣ 10 በመቶ ለሁሉም ፓርቲዎች እኩል፣ 25 በመቶ ፓርቲዎች በሚያቀርቡት እጩ፣ 55 በፓርላማና በክልል ምክር ቤት ባላቸው መቀመጫ እንደሚያከፋፍል በማሳወቅ ነበር ስብሰባው የተጀመረው። ምጫ ቦርድ ባቀረበው ቀምር ላይ ሐሳብ እንዲሰጡ የፖለቲካ […]
በሐውዜን ድብደባ፤ የእሥራኤል እጅ አለበት – አቦይ ስብሐት ነጋ
(ፋኑኤል ክንፉ) ከ26 ዓመታት በፊት የደርግ መንግሥት በትግራይ ክልል በሐውዜን ሕዝብ ላይ ያካሄደው የአውሮፕላን ድብደባ በስተጀርባ የእሥራኤል መንግሥት እጅ እንዳለበት የቀድሞ የህወሓት ሊቀመንበር አቶ ስብሃት ነጋ ይፋ አደረጉ። አቶ ስብሃት ይህን የገለፁት በሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ የደርግ 604 ኮር የተደመሰሰበትን የወታደራዊ ሳይንስ ጥበብ አስመልክቶ ሰሞኑን በሽረ ከተማ በተሰናዳ የውይይት መድረክ ላይ ነው። አቦይ ስብሃት ሲያስረዱ፣ “የቀዝቃዛው ጦርነት ማክተምን ተከትሎ ታላቋ ሶቪየት ሕብረት መፈራረስ ጀመረች። ይህን ክስተት ተከትሎ ሶቪየት ሕብረት ከኢትዮጵያ እየወጣች መጣች። በእሷ እግር የተተካውም የሩሲያ ፌዴሬሽን ለደርግ አገዛዝ ከዚህ በፊት ይደረግ የነበረውን ወታደራዊ እርዳታ አቋረጠ። ይህን ዓለም ዓቀፍ የፖለቲካ ዳይናሚዝም ተከትሎ አሜሪካ መራሹ የምዕራብ ዓለም እና የእሥራኤል መንግስት ከደርግ ጋር ወዳጅ ሆኑ። የደርግ አገዛዝን መውደቅን ተከትሎ ሊፈጠር የሚችለውን የጂኦ-ፖለቲካል ኃይል አሰላለፍ በመፍራት የምዕራቡ ዓለምና እሥራኤል ደርግን ወዳጅ አድርገው በእኛ የትግል እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ እርምጃዎች መውሰድ ጀመሩ” ብለዋል። አያይዘውም፣ “በወቅቱ ሕወሓት ወታደራዊና ፖለቲካዊ አቅሙ እየጠነከረ እየመጣ በመሆኑ አሜሪካና እሥራኤል ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ገብተዋል። የአዲስ አበባው መንግስት ወዳጅ ስለሆኑ እንዴት ከተጀመረው የትጥቅ ትግል ሊያድኑት እንደሚችሉ ብዙ መንገዶችን ሞክረዋል። በጊዜው ደርግን ለማትረፍ ያልሞከረ የምዕራብ ሀገር አልነበረም። ሁሉም የሚችለውን አድርጓል። አሜሪካ ለማደራደር ስትሞክር እሥራኤል ግን የተለየ ሚና ወሰደች” ሲሉ ወንጅለዋል። “አሜሪካ አንዴ ወደ ሮማ ሌላ ጊዜ ወደ ለንደን እንድንመጣ ጠራችን። ሮማ ላይ ጂሚ ካርተር አስጠርቶን የነበረ ቢሆንም፣ የደርግ ልዑካን ቡድን እናንተ ስለኢትዮጵያ ምን […]
ፖሊስ የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠናን የተቃወሙ ተማሪዎችን እያፈሰ እያሰረ ነው
ኢህአዴግ አይገዛንም!›› ተማሪዎቹ ፖሊስ የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠናን የተቃወሙ የደብረማርቆስ የመለስተኛ ሁለተኛ እና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ (መሰናዶ) ተማሪዎችን እያፈሰ እያሰረ እንደሚገኝ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡ ተማሪዎቹ በትናንትናው ዕለት ኢህአዴግን የሚተቹ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን በማንሳታቸው ይሰለጥኑበት ከነበረው ሰፊ አዳራሽ ወጥተው 20፣ 20 ሆነው በጠባብ ክፍል እንዲሰለጥኑ ከመደረጉም ባሻገር ጥያቄ የሚያነሱት ላይ ማስፈራሪያ እንደደረሰባቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ዛሬ ጠዋት […]
(Audio) ስብሐት፣ አባይ፣ ስዩም፣ ካህሳይና በረከት በአርቲስቶች የደደቢት ጉብኝት ላይ የሰጡት ገለጻ
በመጪው የካቲት ከሚከበረውን የህወሓት 40ኛ አመት የልደት በዓል ይከበራል፡፡ ከበዐሉ አከባበር ዝግጅት አንዱ የሆነው፤ ከትጥቅ ትግሉን ዋነኛ ሥፍራዎች የተወሰኑት ከታህሳስ 13 -16 ቀን 2007 በታዋቂ አርቲስቶች እና ጋዜጠኞች እንዲጎበኙ ተደርጓል፡፡ ጉብኝቱ የተጀመረው በደደቢት ሲሆን፣ በዚያው ቦታ ላይ በተዘጋጀ ግዜያዊ የሣር ዳስ ውስጥ ገለጻ ተሰጥቶ ነበር፡፡ በዕለቱ ተናጋሪ የነበሩት የህወሓት መሥራቾች አባይ ፀሐዬ፣ ስብሐት ነጋ፣ ስዩም መስፍን እና አቦይ ካህሳይ እንዲሁም የብአዴን መሥራች በረከት ስምዖን ነበሩ፡፡ የገለጻቸውን ቅጂ ከታች ካለው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ፡፡ —— *********** More from Horn Affairs AmharicAudio | በኦሮሞ ተማሪዎች ስለተካሄዱት ተቃውሞዎች የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዘገባAudio| የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ አመራር በአዲሱ ማስተር ፕላን ላይ የሰጡት መግለጫAudio| ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ በመቐለ ያደረጉት ንግግርበደቡብ ሱዳን ያሉ ኢትዮጵያዊያን መንግስታቸው እንዲታደጋቸው ይሻሉሚኒስትር ሽፈራው:- በቅርቡ ለሚመረቀው ተንዳሆ ስኳር መዘግየት ህንዶችን ወቀሱዓባይ ወልዱ፡- ህወሓትን ለድል ያበቃው የውጭና የሌሎች ድጋፍ ሳይሆን የጠራ ሕዝባዊ መስመር ነው
ስለ ገና በዓል እና ጾም አንዳንድ ጥያቄዎች
ከጀርመን ለውህደቱ የተወከሉት የአርበኞች ግንባር አመራር አቶ ካሳዬ መርሻ አስመራ እንዳይገቡ በሻእቢያታገዱ:
የኢሳያስ አፍወሪቂ ጋዜጣዊ መግለጫ እና ወያኔ ከውጪ የሚኖሩ ተቃዋሚዎች ጋር የድርድር ጥያቄ እንዲያዣንብብ እየሰራ መሆኑ ታውቋል:: ተወካዩን አስመራ ለማስገባት ዲፕሎማሲያዊ ጥረቱ ቀጥሏል:: ከአውሮፓ ወደ ኤርትራ ለውህደቱ ስብሰባ እንዲሄድ የተወከለው በጀርመን የሚኖረው አቶ ካሳዬ መርሻ ወደ አስመራ እንዳይገባ በሻእቢያ መከልከሉ ሲታወቅ ከፊል ኤርትራዊ እንደሆነ የሚታወቀው እና ከአውስትራሊያ የተወከለው የወልቃይት ተወላጅ አቶ አለልኝ ከሻእቢያ ፈቃድ ማግኘቱ ታውቋል:: […]
ምክር እስከመቃብር (ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ)
ክፍል ሁለት (በእውቀቱ ሥዩም) እንደምነሽ ሸገር የከሰመው ወንዝሽ የከሰመው ወዝሽ የሚታየው ነጥፎ እንደምነው ጣፎ እንዴት ነው ቀበና እስቲ ድንጋይ ላጥምድ መረብ ልጣልና፡፡ በነገራችን ላይ በኣዲስ ኣበባ የሚገኙ ካፌዎችና ምግብ ቤቶች“ ኒውዮርክ”“ ዴምቨር” “ወዘተረፈ ተብለው የሚጠሩትን ያክል ባውሮፓና በኣሜሪካ ያሉ ሬስቶራንቶች ደግሞ ”ዱከም“ ፤ ኣራትኪሎ ፤ ፒያሳ በሚል ተሰይመዋል፡፡ የዚህ ምክንያቱ ምንድር ነው ፡፡ ኣዲስ ኣበባ […]
ፖሊስ የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠናን የተቃወሙ ተማሪዎችን እያፈሰ እያሰረ እንደሚገኝ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡
ፖሊስ የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠናን የተቃወሙ ተማሪዎችን እያፈሰ እያሰረ ነው
• ‹‹ኢህአዴግ አይገዛንም!›› ተማሪዎቹ
ፖሊስ የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠናን የተቃወሙ የደብረማርቆስ የመለስተኛ ሁለተኛ እና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ (መሰናዶ) ተማሪዎችን እያፈሰ እያሰረ እንደሚገኝ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡
ተማሪዎቹ በትናንትናው ዕለት ኢህአዴግን የሚተቹ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን በማንሳታቸው ይሰለጥኑበት ከነበረው ሰፊ አዳራሽ ወጥተው 20፣ 20 ሆነው በጠባብ ክፍል እንዲሰለጥኑ ከመደረጉም ባሻገር ጥያቄ የሚያነሱት ላይ ማስፈራሪያ እንደደረሰባቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
ዛሬ ጠዋት ጥያቄ ያነሳሉ የተባሉት ተማሪዎች ስልጠና ወደሚሰጡባቸው ትምህርት ቤቶች ግቢ እንዳይገቡ ከመደረጉም ባሻገር የድብዛ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ስልጠናውን መቃወማቸውን ተከትሎ ፖሊስ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የሰሙ የተክለሀይማኖት መልስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እርምጃውን በመቃወም ለድብዛ ተማሪዎች ድጋፍ መስጠታቸው ተገልጾአል፡፡
የሁለቱም ትምህርት ቤት ተማሪዎች በጋር በመሆን ከተማው አደባባይ ላይ በመውጣት ‹‹አህአዴግ አይገዛንም፣ ኢህአዴግ ሌባ፣…›› የመሳሰሉ መፈክሮችን በማሰማት ተቃውሟቸውን መግለጻቸውን ተከትሎም ፖሊስ ተማሪዎቹን እያፈሰ ወዳልታወቀ ቦታ መውሰዱ ተሰምቷል፡፡ ከዚህም ባሻገር ጥያቄ የሚጠይቁና ፖሊስ ተቃውሞውን አደራጅተዋል ብሎ የሚጠረጥራቸውን ተማሪዎች እየፈለገ እያሰረ መሆኑን ተማሪዎቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
በምስራቅ ጎጃም ዞን በ17ቱም ወረዳዎች የሚገኙ ተማሪዎች ስልጠናውን ካልወሰዱ ከትምህርት ቤት እንደሚባረሩና ፈተና ላይ እንደማይቀመጡ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም ስልጠናውን መቃወማቸውን ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡
እንደ ሰው ወይስ እንደ እንስሳ
ኢድሪስ ገላውዴዎስ- አንጋፋው “ጀብሃ”
ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
—–
“ሻዕቢያ” የሚለው ስም ሲነሳ የዑስማን ሳልህ ሳቤ ስምም አብሮ ይነሳል፡፡ በእርግጥም “ሻዕቢያ” የሚለውን ስያሜ በስራ ላይ ከማዋል ጀምሮ ድርጅቱን በሁለት እግሩ እንዲቆም ያደረገው ሳልህ ሳቤ በመሆኑ እርሱን እንደ ሻዕቢያ መስራች መመልከቱ አግባብ ነው፡፡ የ“ጀብሃ” ስም ሲጠቀስ ደግሞ ብዙዎች የሚያስታውሱት ሓሚድ ኢድሪስ አዋቴን ነው፡፡ ሆኖም ስህተት ነው፡፡ ሃሚድ ኢድሪስ አዋቴ በታሪክ የሚታወሰው ጀብሃ የትጥቅ ትግል በጀመረበት ጊዜ የመጀመሪያውን ጥይት የተኮሰ ሰው በመሆኑ ነው፡፡ “ጀብሃት ታሕሪረል ኤርትሪያ” (በአጭሩ “ጀብሃ”) ወይንም በትግርኛ ስሙ “ተጋድሎ ሓርነት ኤርትራ” (ተ.ሓ.ኤ) የሚባለው የኤርትራ አንጋፋ የፖለቲካ ድርጅት የተመሰረተው ግን ሃሚድ አዋቴ ትግሉን በባርካ በረሃ ከመጀመሩ ከአንድ ዓመት አስቀድሞ ነው፡፡ የድርጅቱ መስራቾች በአብዛኛው በካይሮ የሚማሩ ተማሪዎች ሲሆኑ የቀድሞው የኤርትራ ፓርላማ አባላት የሆኑ ጥቂት ሰዎችና ነጋዴዎችም ተቀላቅለቸዋል፡፡ ከመስራቾቹ መካከል ሙሐመድ ሳሊህ ሁመድ፣ ሙሐመድ አደም ኢድሪስ፤ ሰዒድ ሁሴን፣ ጣሓ ሙሐመድ ኑር፣ ወዘተ…ይጠቀሳሉ፡፡ ይሁንና እነዚህን ሰዎች አሰባስቦ የድርጅቱን መሰረት በመጣል ከፍተኛ ሚና የተጫወተው ሰው ኢድሪስ ገላውዴዎስ ይባላል፡፡
ኢድሪስ ዑሥማን ገላውዴዎስ በ1934 በከረን ከተማ አቅራቢያ በነበረችው “በይት ጀክ” በተባለች አነስተኛ ከተማ ነው የተወለደው፡፡ ኢድሪስ የቤኒአምር (ትግረ) ብሄረሰብ ነው፡፡ አባቱ ሀብታም ነጋዴ የነበሩ ከመሆኑም በላይ በተጨማሪም በምዕራባዊው ኤርትራ ሰፊ እርሻ ነበራቸው፡፡ በመሆኑም ኢድሪስ መደበኛ ትምህርቱን የጀመረው በ1942 የአባቱ እርሻ በሚገኝባትና በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር ላይ ባለችው የአሊጊደር ከተማ ነው፡፡ በ1947 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ወደ ከሰላ (ሱዳን) ተላከ፡፡ የፖለቲካ ተሳትፎውንም የጀመረው በከሰላ ከተማ በነበረበት ወቅት ነው፡፡
እንደሚታወቀው በዚያ ዘመን ኤርትራ በእንግሊዞች አስተዳደር ስር ነበረች፡፡ በዘመኑ ኤርትራ ነጻ መውጣት አለባት የሚሉና ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ትቀላቀል የሚሉ ሁለት ጎራዎች ነበሩ፡፡ የመጀመሪያውን ጎራ የሚያንቀሳቅሰው “ራቢጣ አል-ኢስላሚያ” የሚባል ፓርቲ ሲሆን ሁለተኛውን ጎራ የሚመራው ደግሞ “ማሕበር ሀገር ፍቕሪ” የሚባለው ቡድን ነው፡፡ የኢድሪስ አባት የራቢጣ አባል የነበሩ እንደመሆናቸው “ኤርትራ ነጻ ትሁን” በማለት ከሼኽ ሱልጣን ኢብራሂም ጋር ብዙ ተንቀሳቅሰዋል፡፡ ኢድሪስም በአባቱ ላይ ባየው የትግል መንፈስ በጣም ተማረከ፡፡ መሆኑም “የራቢጣ” የወጣቶች ክንፍ አባል ሆነ፡፡
ኢድሪስ በ1951 ትምህርቱን በከፍተኛ በማዕረግ በማጠናቀቁ ከካይሮ ዩኒቨርሲቲ የስኮላርሺፕ እድል አገኘ፡፡ ወደ ዩኒቨርሲቲው ገብቶም የህግ ትምህርት ማጥናት ጀመረ፡፡ ከዓመት በኋላም የኤርትራ ተማሪዎች ማህበር ሲመሰረት የማህበሩ ሊቀመንበር ሆኖ ተመረጠ፡፡ ኢድሪስ በዚህ ማህበር ኤርትራዊያ ስደተኞችን ለማሰባሰብ በሰፊው ተጠቅሞበታል፡፡
ኢድሪስና ጓዶቹ በስደት ላይ ሆነው የሀገር ቤቱን ሁኔታ በቅርበት ይከታተሉት ነበር፡፡ በተለይም የተባበሩት መንግሥታት ለኤርትራ የሰጠው የፌዴሬሽን መብት እየተሸረሸረ ነው በማለት ተቃውሞአቸውን ያሰሙ ነበር፡፡ በ1957 የኤርትራ ሰንደቅ ዓላማ ታገደ፡፡ ከዓመት በኋላም ትግርኛና ዐረብኛ የስራ ቋንቋ መሆናቸው አብቅቶ በአማርኛ ሲተኩ ደግሞ “ሐረካ” (Eritrean Liberation Movement) የተባለው ድርጅት በሚስጢር ተመሰረተ፡፡ ”
የሐረካ ዓላማ ፌዴሬሽኑ በተቀመጠለት ደንብ መሰረት እንዲሰራ መጠየቅና ለዚህም እስከ መጨረሻው መታገል ነበረ፡፡ በተጨማሪም የትጥቅ ትግልን እንደ አማራጭ አልወሰደም፡፡ ይህ ድርጅት በካይሮ የነበሩትን ተማሪዎች በአባልነት ለማሳተፍ ሲሞክር ግን ተቃውሞ ገጠመው፡፡ እነ ኢድሪስ ገላውዴዎስ የሐረካ ዓላማና የትግል ስልት አዋጪ መስሎ ስላልታያቸው ድርጅቱን እንደ ከንቱ ማህበር ነበር ያዩት፡፡
በ1960 ነው፡፡ ኤርትራዊያን በፌዴሬሽኑ አሰራር ሙሉ በሙሉ ተስፋ ቆርጠዋል፡፡ በርካቶቹም በአጼ ኃይለ ሥላሤ መንግሥት የተሾሙት ቢትወደድ አስፋሓ ወልደሚካኤል ለባርነት ሊዳርገን ነው እያሉ መነጋገር ጀምረዋል፡፡ ከዓመት በፊት የኤርትራ ሰራተኞችና ተማሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ ባደረጉበት ወቅት የጸጥታ ሃይሎች በወሰዱት እርምጃ ሳቢያ በሀገር ቤት ተቃውሞ ማድረጉም ብዙ እንደማያራምድ አምነዋል፡፡ በዚህም የተነሳ በርካቶች የመንግሥትና የፓርላማ ስልጣናቸውን በመተው ወደ ውጪ መሰደድ ጀመሩ፡፡ እነዚህ ስደተኞች ካይሮ ከሚገኙት ተማሪዎች ጋር ከተቀላቀሉ በኋላ ስለ ድርጅት ምሥረታ መነጋገር ጀመሩ፡፡ ውይይቱም ፍሬያማ ሆኖ በመውጣቱ በጁላይ ወር 1960 ከነጻነት በስተቀር የፌዴሬሽንን ፎርሙላ የማይቀበል አዲስ ድርጅት ተመሰረተ፡፡ ይህም ድርጅት “ጀብሃት ታሕሪረል ኤሪቲሪያ” ወይንም “ተጋድሎ ሓርነት ኤርትራ” (ተ.ሓ.ኤ) ተብሎ ተሰየመ፡፡
“ጀብሃ” ሲመሰረት የድርጅቱ ሊቀመንበር ሆኖ የተመረጠው የቀድሞ የፓርላማ አባል የነበረው ኢድሪስ ሙሐመድ አደም ነው፡፡ የድርጅቱ ዋና ጸሐፊ ደግሞ ኢድሪስ ገላውዴዎስ ነው፡፡ የድርጅቱ ላዕላይ ምክር ቤት (Supreme Council) አባላት ኢድሪስ ሙሐመድ አደም፤ ኢድሪስ ገላውዴዎስ፣ ሙሐመድ ሳሊሕ አሕመድ፣ ዑሥማን ኢድሪስ ኪያር፣ ሙሐመድ ሰዒድ ኪያር፣ ሲሆኑ ከአንድ ዓመት በኋላም ዑሥማን ሳልህ ሳቤ ተቀላቅሎአቸዋል፡፡
“ጀብሃ” ከተቋቋመ በኋላ በምዕራብ ኤርትራ በረሃ በተበታተነ ሁኔታ ከሚታገሉት እነ ሃሚድ ኢድሪስ አዋቴን መከሳሰሉ ፋኖዎች ጋር ተገናኘ፡፡ ለአዋቴም የግንባሩን ወታደራዊ ክፍል እንዲመሩ ውክልና ሰጣቸው፡፡ በመስከረም 1/1961 በሃሚድ አዋቴ አዝማችነት በጀብሃ ስም የትጥቅ ትግሉ ተጀመረ፡፡ ሃሚድ ኢድሪስ አዋቴ ከአንድ ዓመት በኋላ ሲገደሉ ደግሞ የወታደራዊውን ክንፍ የመምራቱ ስልጣን ለኢድሪስ ገላውዴዎስ ተሰጠ፡፡ በዚህም የኢድሪስ ገላውዴዎስ መቀመጫ ከካይሮ ከተማ ወደ ሱዳኗ ከሰላ ከተማ ተቀየረ፡፡
ኢድሪስ ገላውዴዎስ ከሰላ ከደረሰ በኋላ በሱዳን ውስጥ የሚገኙ ኤርትራዊያን ስደተኞችን እያሰባሰበ ወታደራዊ ስልጠና እንዲያገኙ አድርጓል፡፡ በኋላ ላይ ደግሞ ለድርጅቱ ድጋፍ ለማግኘት ወደ ልዩ ልዩ ሀገራት ተጉዟል፡፡ በዚህም ውጤት አግኝቶበታል፡፡ ለምሳሌ በ1967 ወደ ቻይና ተጉዞ እነ ማኦ ዜዱንግን በማሳመን ለጀብሃ የመሳሪያና የስልጠና ድጋፍ አስገኝቷል (በዚያን ጊዜ ወደ ቻይና ሄደው ስልጠና ካገኙት መካከል አንዱ የአሁኑ የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ናቸው)፡፡ ወደ ኩባ በመሄድም የጀብሃ ተዋጊዎች የፓራ-ኮማንዶ ስልጠና እና የመሳሪያ ድጋፍ እንዲያገኙ አድርጓል፡፡ ከሶሪያና ከኢራቅም ብዙ እርዳታ አስገኝቷል፡፡ የእስያ-አፍሪቃ የወዳጅነት ኮንፈረንስ በተካሄደበት ጊዜም ድርጅቱን በመወከል ተሳትፏል፡፡
ከዚህ ቀደም በጻፍኳቸው ጽሑፎች እንደገለጽኩት “ጀብሃ” የሚባለው ድርጅት በኤርትራዊያን ክርስቲያኖች ላይ ውገና ያካሄድ ነበር፡፡ የዚህም መነሻ “ለኃይለ ሥላሤ መንግሥት አሳልፈው የሸጡን ክርስቲያኖቹ ናቸው” የሚለው የተሳሳተ ፍረጃው ነው፡፡ እርግጥ የኃይለ ሥላሤ መንግሥት ኤርትራዊያን ሙስሊሞች ወደ ስልጣነ-መንግሥቱ እንዳይቀርቡ አድርጓል፡፡ በመንግሥት ስልጣንም ሆነ በፓርላማው ውስጥ የተሰገሰጉት በአብዛኛው ደገኛ ክርስቲያኖች ነበሩ፡፡ ይሁንና የእነዚህ ጥቂት ሰዎች ምግባር ሁሉንም የኤርትራ ህዝበ ክርስቲያን አይወክልም፡፡ ስለዚህ ጀብሃ ኤርትራዊያን ክርስቲያኖችን በጥርጣሬ ማየቱና በድርጅቱ ውስጥ የነበሩትንም እያሳደደ መምታቱ ትክክል አልነበረም፡፡ ድርጅቱንም ለውድቀት ያበቃውም ይህ የውገና አቋሙ ነው፡፡
ይህ ወገንተኛ አቋም የሁሉም የጀብሃ አባላት አቋም አልነበረም፡፡ በመሆኑም በ1969 በወታደራዊ ግንባር የተሰለፉት አባላት ፓርቲው ራሱን እንዲፈትሽና እንዲያሻሽል የሚቀሰቅሰውን የአዶብሃ ኮንፈረንስ ጠሩ፡፡ በኮንፈረንሱ ማጠቃለያም ድርጅቱ ራሱን እስካላሻሻለ ድረስ ካይሮ የሚገኘው ላዕላይ ምክር ቤት የሚያወጣቸውን መመሪያዎች እንደማይቀበሉ አስታወቁ፡፡ የካይሮው ምክር ቤት ኮንፈረንሱን በህገ-ወጥነት ፈረጀው፡፡ ሆኖም በከሰላ የሚገኘው ኢድሪስ ገላውዴዎስ የተነሱትን ጥያቄዎች እንደሚቀበል አስታወቀ፡፡ በዚህም የተነሳ ኢድሪስ ገላውዴዎስ ከአመራሩ ጋር ተጋጨ፡፡ በድርጅቱ ውስጥ የነበረውንም ከፍተኛ ስልጣን አጣ፡፡ ይሁንና የወታደራዊ ኮሚቴ ሊቀመንበርነቱን አልተወውም፡፡
ኢድሪስ ገላውዴዎስ የጀብሃን ወታደራዊ ክንፍ በሚመራበት ወቅት ነበር በዑሥማን ሳልህ ሳቤ እና በኢሳያስ አፍወርቂ የሚመሩት ቡድኖች ከድርጅቱ ተንገጥለው የወጡት፡፡ የጀብሃ አመራር እነዚህን ቡድኖች በወታደራዊ ጥቃት የማጥፋት ውሳኔ አሳለፈ፡፡ ኢድሪስ ገላውዴዎስ ግን ውሳኔው ኤርትራዊያንን የበለጠ ይከፋፍላል በማለት ተቃወመው፡፡ ወታደራዊ ዘመቻዎችንም እንደማያስፈጽም ለድርጅቱ መሪዎች ቁርጡን ነገራቸው፡፡ በዚህም የተነሳ የድርጅቱ መሪዎች ኢድሪስን ከወታደራዊ መሪነቱ አስነሱትና በውጪ ጉዳይ ላይ ሾሙት፡፡
ኢድሪስ ገላውዴዎስ ድርጅቱን በውጪ ጉዳይ ሃላፊነት በሚመራበት ወቅት ድርጅቱ በጣም እየተዳከመ ነበር፡፡ ቢሆንም ኢድሪስ በውጪው ዓለም የድርጅቱን ስም የሚያስጠሩ ስራዎችን ሰርቷል፡፡ ለምሳሌ እ.ኤ.አ. በ1978 ታላቋ ሶቭየት ህብረት ጀብሃ ከደርግ መንግሥት ጋር እንዲወያይ በፈጠረችው መድረክ ላይ ድርጅቱን ወክሎ ተገኝቷል፡፡
ከጥቂት ዓመታት በኋላ ጀብሃ ፍርስርሱ ወጣ፡፡ በኤርትራ ምድር የቀረው ትርፍራፊ ጦሩ በሻዕቢያ ተደመሰሰ፡፡ ድርጅቱም በስም ያለ በተግባር ግን የሌለ ሆኖ ቀረ፡፡ ይህንን የተመለከተው ኢድሪስ ገላውዴዎስ በድርጅቱ መሪዎች ላይ ከፍተኛ ሂስ ጽፎ አቀረበ፡፡ ድርጅቱ ሁሉንም ኤርትራዊያን በእኩል ሁኔታ አለማየቱና ዲሞክራሲያዊ አሰራር የሌለው መሆኑ ለሞት እንዳበቃው አሰመረበት፡፡ በመሆኑም ከጀብሃ አመራር ራሱን አገለለ፡፡
በ1991 ሻዕቢያ ኤርትራን ሙሉ በሙሉ ሲቆጣጠር ኢድሪስ ገላውዴዎስ ለአዲሱ መንግሥት እውቅና እንደሚሰጥ አስታወቀ፡፡ እነ ኢሳያስ አፈወርቂም ወደ ሀገር መጥቶ በስራ እንዲረዳቸው ጥሪ አቀረቡለት፡፡ ኢድሪስም ግብዣውን ተቀብሎ ወደ ሀገር ውስጥ ገባ፡፡ ከ1991-1993 በነበሩት ዓመታትም ከዶ/ር በረከት ሃብተ ሥላሴ ጋር የሪፈረንደም ኮሚሽን ሃላፊ ሆኖ ሰራ፡፡ በተከታዮቹ ዓመታት ደግሞ የህገ-መንግሥት አርቃቂ ኮሚሽን አባል ሆኖ በመስራት ላይ እያለ እ.ኤ.አ በ1998 አረፈ፡፡ የቀብር ስርዓቱም በብሄራዊ ደረጃ ተፈጸመለት፡፡
የጀብሃ አባላት ለኢድሪስ ገላውዴዎስ ሁለት ዓይነት እይታዎች ነው ያላቸው፡፡ ኢድሪስ ድርጅቱን ለመመስረትና የወታደራዊ ክንፉን መሰረት ለመጣል ያደረገውን አስተዋጽኦ በበጎ ዐይኑ ይመለከቱታል፡፡ ከዚያ በኋላ ግን አድርባይ ሆኖ ድርጅቱን ከድቷል በማለት ይኮንኑታል፡፡ የሻዕቢያ አባላትና ደጋፊዎች ግን ኢድሪስ ገላውዴዎስን በበረሃ ውስጥ የተገኘ ተክል አድርገው ነው የሚያዩት፡፡ “ጀብሃ ከውጥኑ ጀምሮ በርሱ ቢመራ ኖሮ ኤርትራዊያን እርስ በራሳቸው አይጋደሉም ነበር” በማለትም ያምናሉ፡፡ ሐቁ የትኛው እንደሆነ ታሪክ ነው የሚፈርደው፡፡ ከብዙ በጥቂቱ ግን ኢድሪስ ገላውዴዎስ ማለት ከላይ የተገለጸው ሰው ነው፡፡
—–
ምንጮች



