ኢንጅነር ግዛቸው የአመቱ ምርጥ ሰው ተብለው ተመረጡ

መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው ኢትዮጵያን ሪቪው የተባለው ድረገፅ ኢንጅነር ግዛቸውን የአመቱ ምርጥ ሰው ብሎ መረጣቸው፡፡

10408033_841669459225138_5718907674055212071_nድረገፁ በየአመቱ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ተፅእኖ ያሳረፉ ፖለቲከኞችን የሚመርጥ ሲሆን በተጠናቀቀው የፈረንጆች አመት ላይ ኢንጅነር ግዛቸውን የአመቱ ምርጥ ሰው ብሎ መርጧቸዋል፡፡ ምርጫው የራሱ መስፈርቶች ያሉት ሲሆን በዋናነት ኢትዮጵያን ለማሻሻል ለተጉ እና ለነፃነት በሚደረገው ትግል አስተዋፅኦ ላበረከቱ ሰዎች ከግምት ያስገባ መሆኑን ድረገፁ አትቷል፡፡

በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ የ2014 ዓ.ም ላይ ለኢትዮጵያ ብዙ ዋጋ የከፈሉና እና የተጉ ሰዎች ቢኖሩም ኢንጅነር ግዛቸው ሊመረጡ የቻሉበት ምክንያት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ያልተለመዱ ሁለት ነገሮችን በመተግበራቸው መሆኑን አስፍሯል፡፡ እነዚህም መሃል “ባልተለመደ መልኩ ስልጣናቸውን አስረክበው መልቀቃቸውና፤ በፓርቲው ውስጥ ወጣት ፖለቲከኞችን ወደመንበሩ ለማምጣት የገቡትን ቃል መተግበራቸው” መሆኑን ገልጿል፡፡ ይህን በማድረጋቸውም ድምፅ አልባ ለሆኑ ኢትዮጵያውያን ድምፅ የሆነውን ጠንካራ የተቃውሞ ፓርቲ ጉልበት እንደጨመረለት ድረገፁ አትቷል፡፡