በደብረማርቆስ ከተማ ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል! – ፍኖተ-ነፃነት
በርካታ ወጣቶች በፌደራል ፖሊስና በደህነት ሀይሎች በመታሰር ላይ ይገኛሉ!
በደብረማርቆስ ስልጠና ላይ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃና የመሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በመንግስት ላይ ጥያቄ ማንሳታቸውን ተከትሎ እየታሰሩ እንደሚገኙ የፍኖተ-ነፃነት ምንጮች አስታወቁ፡፡
ተማሪዎቹ በመንግስት በኩል የሚሰጠውን ስልጠና ማውገዛቸውን እና በመንግስት በኩልም ቤተሰቦቻቸው ኢህአዴግን እንዲመርጡ እንዲያግባቡ መደረጋቸውን የገለፁት ምንጮች ተማሪዎቹ ይህን በመቃወም የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት ላይ የነበሩ ቢሆንም በፖሊስ ሀይል ስልጠናው ይሰጥበት ከነበረው ትምህርት ቤቶች ተገፍተው መውጣታቸውን የፍኖተ-ነፃነት የደብረብርሃን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
በደብዛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና በተክለሀይማኖት ሁለተኛ ደረጃ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት ስልጠናውን በመከታተል ላይ የነበሩት ተማሪዎች የመንግስትን ጥያቄ ባለመቀበላቸው የተነሳ ከሚገኙበት የተለያዩ ቦታዎች እየታፈሱ እየታሰሩ እንደሚገኝ ምንጮች አያይዘው ገልፀዋል፡፡
በከተማዋ በአሁኑ ሰአት ከፍተኛ ውጥረት መንገሱን ፖሊስም ህፃን ፣ አዋቂ ሳይል በመንገድ ላይ የሚገኙትን ሰዎች በሙላ በማፈስ እያሰረ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡