እኛ የኢህአዴግን ጠመንጃ እንፈራለን፤ ኢህአዴግ ደግሞ 97 ላይ የመጣበትን የህዝብ ጎርፍ ይፈራል ‹‹ኢህአዴግን በሁለት ሳምንት ስራ በዝረራ በአንዳንድ አካባቢዎች ማሸነፍ ይቻላል፤ በአዲስ አበባ ግን ሁለት ቀን በቂ ነው››
ያለማመንታት ፕ/ር መረራ ‹‹ፖለቲከኛ ናቸው›› ማለት ይቻላል፡፡ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዞአቸውም እንደ ፖለቲካ ሳይንስ ምሁርነታቸውና እንደፖለቲከኛነታቸው በሚያደርጉት ተሳትፎአቸው ይታወቃሉ፡፡ በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ ደግሞ በፓርላማ በነበራቸው ቆይታ በግልፅነታቸውና በቀልድ እያዋዙ ተናጋሪነታቸው ነው የሚታወቁት፡፡ በፖለቲካ የተሳትፎ ህይወታቸው የሚጀምረው አምቦ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ እያሉ ነበር፡፡ የንጉሱን አገዛዝ ለመጣል ከተንቀሳቀሱት አፍላ ወጣቶችም አንዱ ናቸው፡ ፡ በወቅቱ የ66ቱ አብዮት እውን […]